Remote IT ሪሞት አይቲ
2.03K subscribers
973 photos
18 videos
26 files
557 links
✔️በቻናላችን✔️

💫ሰለ ክርፕቶ ካረንሲ
📲 የAndroid መተግበሪያ
💻 የPC SoftWare
📌 ስለ ኮምፒዩተር እና ፕርንተር


👉ለአስተያየትና ሌሎች ፕሮግራሞችን ለማግኘት ይቀላቀላሉ

@remoteict
Download Telegram
📿 #ማርክ ዙከርበርግ የናጠጠ ቢሊየነር ነው። ሚስቱን ለማስደሰት ማንኛውንም በአለም ላይ ውድ የሆነ ቁስ ሊገዛላት ይችላ.....ል—ጌጣጌጦች፣ ቤት፣ መኪና፣ አውሮፕላን፣ የመዝናኛ መርከብ yacht ወዘተ። አንድ ደሴት ወይም ትንሽ ሀገር የሚገዛ ገንዘብ ያለው ሰው ነው። ገንዘብ ሊገዛው የሚችለውን ነገር ሁሉ በስጦታ ሊሰጣት ይችላል።

📿ማርክ ግን ገንዘብ የሚገዛውን ትቶ ገንዘብ የማይገዛውን ሰጣት። ምን ይሆን ገንዘብ የማይገዛው?! የማርክ ሚስት ፕሪሲላ ቻን ትባላለች። በትውልዷ ቻይናዊ ናት። በላቧ ሰርታ የምታድር ሜዲካል ዶክተር ነች። ደግሞ በባህሪዋም ገንዘብ የሚያስደንቃት፣ ግድ የሚሰጣት ሴት አይደለችም።

📿ታዲያ ለዚህች ሴት ማርክ ምን ይስጣት? ማርክ ለሚስቱ ሳይነግራት የቋንቋ ትምህርት ቤት ተመዘገበ። ለአመታት ማንዳሪን አጠና። በነገራችን ላይ ማንዳሪን ለመማር በጣም ከባድ ቋንቋ ነው። አይደለም በሁለተኛ እና ሶስተኛ ቋንቋነት አፈ ለፈቱበትም ዳገት ነው። በተለይ ጽሁፉ።

📿አንዴ ስለ ማንዳሪን ሳነብ ከ48 ሺ በላይ ካራክተርስ አሉት ይላል። መሰረታዊ ጽሁፍ ለማወቅ ቢያንስ 3ሺ ካራክተር ማወቅ ይገባል። ምእራባውያን የለመዱት 26 የላቲን ፊደል ነው።

📿 #ማንዳሪንን ተዉትና የኛ ቋንቋ 231 ፊደላት እንዳለው ሲያውቁ ልባቸው በድንጋጤ ቀጥ ነው የምትለው። አማርኛ ራሱ ለመማር ቀላል ቋንቋ አይደለም። ማንዳሪን የበለጠ ከባድ ነው። ብዙ ትጋት ይጠይቃል።

📿 #ማርክ ራሱ ቋንቋውን በደንብ ለመካን ብዙ አመት ወስዶበታል። ያውም እሱ ከፍተኛ የአእምሮ ብቃት ስላለው ነው እንጂ ቋንቋው የሊማሊሞ ዳገት ነው። ታዲያ ማርክ በማንዳሪን ሲካን ለሚስቱ በመጀመሪያ እንዲህ ነበር ያላት፦

"我爱汝"

ትርጉሙ "አፈቅርሻለሁ" ነው።

📿ከዚህ የሚበልጥ ምን ስጦታ አለ?! በገንዘብ የማይተመን ዋጋ የማይወጣለት ውድ ስጦታ።

📿ፍቅርና ቋንቋ። ቋንቋና ፍቅር። ፍቅር በቋንቋ ይገለጻል። እስኪ አንዳችን የሌሎቻችንን ቋንቋ በፍቅር እንማር። ፍቅራችንን እንገላለጽ። ቋንቋዎቻችን የፍቅር ድልድይ እንጂ የልዩነት ግድግዳ አይሁኑብን።

@remoteict
@remoteict