#tiktok
የአሜሪካ #ሴኔት በመላው አሜሪካ " ቲክቶክ" ን ሊያግድ የሚችል አዋጅ ትላንት ለሊት አጽድቋል።
ከቀናት በፊት የተወካዮች ምክር ቤት " ቲክቶክ " እንዲታገድ ረቂቅ ሕግ ማጽደቁ ይታወሳል።
ትላንት ለሊት የአሜሪካ ሴኔት ተሰብስቦ " ቲክቶክ " ከቻይና ካልተፋትና ድርሻው በ9 ወር ውስጥ ለአሜሪካ ኩባንያ የማይሸጥ ከሆነ አሜሪካ ውስጥ አገልግሎት እንዳይሰጥ የሚያግድ አዋጅ አጽድቋል።
ቀጣዩ ሂደት ፕሬዜዳንቱን ይመለከታል።
ይህ አዋጅ ወደ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተመራ ሲሆን እሳቸው ቀደም ሲል " ይህ አዋጅ እኔ ጋር ይድረስ እንጂ ፊርማዬን አኑሬበት ሕግ ሆኖ ይተገበራል " ብለው ነበር።
አሁን አሜሪካ ውስጥ 170 ሚሊዮ ተጠቃሚዎች ያሉት " ቲክቶክ " የመታገዱ ነገር እውን እየሆነ የመጣ ሲሆን ሂደቱ ረጅም ወራትን ሊወስድ ይችላል።
በሌላ በኩል ፥ ሴኔቱ ለዩክሬን ፣ ለእስራኤል እና ለሌሎች የባህር ማዶ የአሜሪካ አጋሮች የ95 ቢሊዮን ዶላር (5,419,427,000,000 ብር) የእርዳታ ጥቅል አፅድቆታል።
@remoteict