ረከብኪ ቲዩብ | Rekebki Tube
310 subscribers
50 photos
29 links
"ተዘከሩ መኳንንቲክሙ ዘነገሩክሙ ቃለ እግዚአብሔር። " የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ።ዕብ ፲፫፡፯


https://youtube.com/@rekebkitube
ረከብኪ ቲዩብ
https://t.me/+VJhnnXdC4rsxYjU0
Download Telegram
#መልዕክት 📨

ዝም እንበል

አባ በምዋ ዓለምን ትቶ ወደ በረሃ በሄደ ጊዜ፣ ለዚህ አዲስ ሕይወቱ የሚጠቅመውን ምክር ይሰጡት ዘንድ ወደ አንድ ቅዱስ አረጋዊ ቀርቦ "ምን ላድርግ" ሲል ጠየቃቸው። እኒህም አረጋዊ ንግግራቸውን የጀመሩት "በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ" በሚለው በቅዱስ ዳዊት የመዝሙር ቃል ነበር። (መዝ ፴፱፥፩) አባ በምዋም ይህንን የመጽሐፍ ቃል በሰማ ጊዜ "ይበቃል አባቴ፣ ይህን ተምሬ እስክፈጽም ድረስ ሌላ ምንም አዲስ ትምህርት አይንገሩኝ" በማለት ወደ በዓቱ ሄደ።

ከዚያም ቀን ጀምሮ ለብዙ ጊዜያት ወደ አረጋዊው አልተመለሰም ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን አረጋዊው ጻድቅ አባ በምዋን አግኝተው ለምን ለሌላ ተጨማሪ ትምህርት መልሶ ወደ እርሳቸው እንዳልመጣ ጠየቁት። እርሱም "እመኑኝ አባቴ፣ ገና የመጀመሪያውን ትምህርት በሚገባ አልተማርኹትም" ሲል መለሰላቸው። ከረጅም ዓመታትም በኋላ ወዳጁ የሆነ አንድ መነኩሴ የሰማውን የነቢዩ የዳዊትን ቃል እስከ አሁን አጥንቶ ጨርሶ እንደሆነ አባ በምዋን ጠየቀው። ቅዱሱም "በዚህ የነቢዩ ቃል ላይ ለማሰላሰል እና በሚገባ ወደ ተግባር ለመቀየር አርባ አምስት ዓመታት ወስዶብኛል" ሲል በትሕትና መለሰለት። የአባ በምዋን ታሪክ የጻፈልን ቅዱስ ጰላድዮስ እንደሚናገረው አባ በምዋ በሕይወቱ ሁሉ ፍጽምት የሆነች የዝምታን ሕይወት የመራ ሲሆን፣ በሞቱም ጊዜ "ምነው ይህን ባልተናገርኩ" የሚል አንድም የሕሊና ወቀሳ ሳያገኘው በሰላም አርፏል።

ቅዱስ እንጦንስም በአንድ ወቅት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ሲል መክሯቸው ነበር ፦ "ዝም በሉ፤ ዝምተኛን ሰው እግዚአብሔር በፊቱ ካሉት ሠራዊተ መላእክት እንደ አንዱ ይቆጠረዋልና"

ዲያቆን አቤል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የዐቢይ ጾም ስድስተኛው ሰንበት (ሳምንት) ገብር ኄር በመባል ይታወቃል፡፡ ገብር ኄር ማለትም ‹‹ቸር፣ ታማኝ፣ ቅን አገልጋይ›› ማለት ነው፡፡ ይህንን ስያሜ ያገኘበት ምክንያት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‹‹ገብር ኄር ወገብር ምእመን ገብር ዘአሥመሮ ለእግዚኡ፤ ጌታውን ደስ ያሰኘ ታማኝና ቸር አገልጋይ ማነው?›› በማለት በቅዱስ ያሬድ ዜማ ሊቃውንቱ ስለሚያመሰግኑ ነው፡፡ (ጾመ ድጓ ዘገብር ኄር)
ረከብኪ ቲዩብ | Rekebki Tube
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የዐቢይ ጾም ስድስተኛው ሰንበት (ሳምንት) ገብር ኄር በመባል ይታወቃል፡፡ ገብር ኄር ማለትም ‹‹ቸር፣ ታማኝ፣ ቅን አገልጋይ›› ማለት ነው፡፡ ይህንን ስያሜ ያገኘበት ምክንያት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‹‹ገብር ኄር ወገብር ምእመን ገብር ዘአሥመሮ ለእግዚኡ፤ ጌታውን ደስ ያሰኘ ታማኝና ቸር አገልጋይ ማነው?›› በማለት በቅዱስ ያሬድ…
በዚህ ዕለትም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የነገራቸውና በማቴዎስ ወንጌል ላይ የተመዘገበው የአንድ ባለ ሀብትና የሦስት አገልጋዮቹ ታሪክ ይነበባል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀንም ያ ባለጠጋ አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዱ እንደአቅሙ ለአንዱ አምስት መክሊት፣ ለአንዱ ሁለት መክሊት፣ ለአንዱም አንድ መክሊት ሰጠና ወደሌላ ሀገር ሄደ፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ ተመልሶ መጣ፤ አገልጋዮቹንም ትእዛዙን መፈጸም አለመፈጸማቸውን፣ መታዘዝ አለመታዘዛቸውን ለማወቅ ጠየቃቸው፡፡ በዚህን ጊዜ አምስት መክሊት የተሰጠው ወጥቶ ወርዶ ነግዶና አምስት አትርፎ ደርቦ ዐሥር ስላመጣ ለጌታው እንዲህ አለው፤ ‹‹አቤቱ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት አተረፍሁ›› ብሎ አምስት መክሊት አስረከበ፡፡ ጌታውም፡- ‹‹መልካም፥ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በብዙ እሾምሀለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡›› ሁለት መክሊት የተቀበለውም መጥቶ፡- ‹‹አቤቱ፥ ሁለት መክሊትን ሰጥተኸኝ አልነበረምን? እነሆ ሌላ ሁለት መክሊትን አተረፍሁ›› አለ፤ ጌታውም ‹‹ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡›› አንድ መክሊት የተቀበለው መጣና እንዲህ አለ፡- ‹‹አቤቱ፥ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፥ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ስለ ፈራሁም ሄድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፤ እንግዲህ እነሆ፥ መክሊትህ፡፡›› ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፡- ‹‹አንተ ክፉና ሰነፍ አገልጋይ፥ እኔ ካልዘራሁበት የማጭድ፥ ካልበተንሁበትም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? ገንዘቤን ለለዋጮች መስጠት በተገባህ ነበር፤ እኔም ራሴ መጥቼ ገንዘቤን ከትርፉ ጋር በወሰድሁ ነበር፡፡›› ከዚያም ጌታቸው ‹‹ይህን መክሊት ከእርሱ ተቀብላችሁ ዐሥር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ሁሉ ይሰጡታልና፤ ይጨምሩለታልም፤ ለሌለው ግን ያንኑ ያለውን ይወስዱበታል፡፡ ክፉውን አገልጋይ ግን፥ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወደ አለ ጨለማ አውጡት›› ብሎ አገልጋዮቹን አዘዘ፡፡ (ማቴ.፳፭፥፲፬-፴)
ረከብኪ ቲዩብ | Rekebki Tube
በዚህ ዕለትም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የነገራቸውና በማቴዎስ ወንጌል ላይ የተመዘገበው የአንድ ባለ ሀብትና የሦስት አገልጋዮቹ ታሪክ ይነበባል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀንም ያ ባለጠጋ አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዱ እንደአቅሙ ለአንዱ አምስት መክሊት፣ ለአንዱ ሁለት መክሊት፣ ለአንዱም አንድ መክሊት ሰጠና ወደሌላ ሀገር ሄደ፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ ተመልሶ መጣ፤ አገልጋዮቹንም ትእዛዙን…
ባለ አምስት መክሊት የነበረው አገልጋይ ፍጹም ትምህርትን ተምሮ መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ ደቀ መዝሙር ባፈራ መምህር ይመሰላል፡፡ ባለ ሁለት መክሊት የተባለ ፍጹም ትምህርትን ተምሮ መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ ባወጣ መምህር ይመሰላል፤ ቅዱስ ጴጥሮስ ቀሌሜንጦስን፣ ቅዱስ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን እንዳፈሩ ማለት ነው፡፡ ባለ አንድ መክሊት የተባለ ተምሮ ሳያስተምር የቀረ ነዉ፡፡ ዕውቀት፣ ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት እያለው በግዴለሽነት ኃላፊነቱን ያልተወጣ ነው፡፡ ፍጹም ትምህርት የተማረው ወጥቶ ወርዶ መክሮና አስተምሮ ራሱን አስመስሎ አወጣ፡፡ ባለአንዱ መክሊት ዐላውያን ‹‹እሳት ስለት አሳይተው ቢያስክዱኝ፣ መናፍቃን ተከራክረው ምላሽ ቢያሳጡኝ›› ብሎ ፈርቶ ሃይማኖቱን በልቡ በመያዝ ደብቆ በሚኖር ዓይነት ሰው ይመሰላል፡፡ ባለአምስት የተባለ ነቢዩ ሙሴ ነው፤ አምስቱን ብሔረ ኦሪት ጽፏልና፡፡ ሁለት የተባሉ ብሉይና ሐዲስ ናቸው፤ ባለአንድ የተባለ ይሁዳ ነው፡፡ አምላኩን ሽጦ፣ አባቱን ሰልቦ፣ እናቱን አግብቶ ንስሓ ሳይገባ ሞቷልና፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ባላአምስት የተባሉ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው፤ ቆሞሳትን፣ ቀሳውስትን፣ ዲያቆናትን በአንብሮተ እድ ይሾማሉ፤ ያጠምቃሉ፤ ያቈርባሉና፡፡ ባለሁለት የተባሉ ቀሳውስት ናቸው፤ እነርሱም ያጠምቃሉ ያቆርባሉና፡፡ ባለአንድ መክሊት የተባሉ ዲያቆናት ናቸዉ፤ ለተልእኮ ይፋጠናሉና፡፡ በዚህ ዘመን ባለ አምስትም፣ ባለ ሁለትም፣ ባለ አንድም ቢሆኑ የተሰጣቸውን መክሊት ተጠቅመው ወጥተው ወርደው ካተረፉ ‹‹ወደ ጌታህ ደስታ ግባ›› የሚለውን ቃል ሰምተው በተድላ ይኖራሉ፡፡
ረከብኪ ቲዩብ | Rekebki Tube
ባለ አምስት መክሊት የነበረው አገልጋይ ፍጹም ትምህርትን ተምሮ መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ ደቀ መዝሙር ባፈራ መምህር ይመሰላል፡፡ ባለ ሁለት መክሊት የተባለ ፍጹም ትምህርትን ተምሮ መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ ባወጣ መምህር ይመሰላል፤ ቅዱስ ጴጥሮስ ቀሌሜንጦስን፣ ቅዱስ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን እንዳፈሩ ማለት ነው፡፡ ባለ አንድ መክሊት የተባለ ተምሮ ሳያስተምር የቀረ ነዉ፡፡ ዕውቀት፣ ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት…
ከዚህ ታሪክ እንደምንገነዘበው ዛሬም እያንዳንዳችን እንደአቅማችን ከአምላካችን ዘንድ የተሰጠን መክሊት እንዳለን ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ወደ ዓለም ያመጣነው የለንምና›› እንዳለ ወደዚህ ዓለም ከመጣን በኋላ መንፈሳዊ ስጦታም ይሁን ቁሳዊ ነገሮች ሁሉንም ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀብለናል፡፡ በእርግጥ አላስተዋልንም እንጂ ከእግዚአብሔር ያልተቀበልነውና የእኛ የምንለው ነገር ቢኖር ኃጢአት ብቻ ነው፡፡ የምንሰጠው የእርሱን ለእርሱ ነው እንጂ የራሳችን የሆነ ምንም ሀብት የለንም፡፡ (፩ኛ ጢሞ. ፮፥፯)
ብሂለ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

https://t.me/abew_z_orthodox
https://t.me/abew_z_orthodox
ምንተ እንከ ንብል እንበይነዝ ለእመ እግዚአብሔር ምስሌነ መኑ ይክለነ?
ሮሜ ፰፥፴፩
እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
ሮሜ ፰፥፴፩
#ሥነ_ግጥም

🌕✤የትንሳኤ ፍሬ✤🌕

ደረሰ ሊፈታ፣ሕማምህን ልረሳ
ዳግም የተውኳትን፣ሐጥያትን ላነሳ
ሞቴ ሊጀምር ነው፣ከሞት ሰትነሳ
ጌታ ሆይ! ዳግም አትሙት በልቤ
ትንሳኤህ ያድርገኝ እንጂ፣አንተን እንዳቅህ ቀርቤ

የልቤ መቃን ይከፈት፣መቃብሩ ሰውነቴን በትንሳኤ ብርሃን ይፍረስ
ሞቴ በአንተ እንደሞተ፣ሕማምህ በልቤ ይንገስ
እባክህ! የጋረደኝን ጨለማ፣ከዓይኔ ክበብ ላይ አውልቀው
ከትንሳኤህ ማዶ ያለውን አንተነትህን ልወቀው
እንደ ማርያም መግደላዊት፣ማንን ትሻለህ በለኝ
እንዳይገባይኝ ባውቀውም፣በቸርነትህ ጠይቀኝ

ትችላለህ አውቀዋለው በኤማሁስ ስታበራ
ላልተረዳሁ ላልገባኝ ምስጢርህን ስታብራራ
አይቻለው ከዚህ ቀደም፣በተዘጋ በር ስትገባ
እሻለሁኝ! ምን በዘጋውየልቤን በር፣ በጥበብህ እንድትገባ
አቤቱ ውስጤን አድሰው፣የፍቅር ማረሻ አንስተህ፣የልቤን ዙፍን እረሰው
ዳግም ሞቶ እንዳይቀር፣ ከትንሳኤህ ፍሬ አጉርሰው።


  ​ እንቋዕ አብጽሐክሙ አብጽሐክን ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወሐምስቱ ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤ በሰላም በፍቅር ወበጥዒና።

ሠናይ በዓል
ምስለ ጻድቅ ትጸድቅ፤ ወምስለ ብእሲ ንጹሕ ንጹሐ ትከውን። ፤ ወምስለ ኅሩይ ኅሩየ ትከውን፤ ወምስለ ጠዋይ ትጠዊ።