Qelem Meda Technologies | QMT
13.9K subscribers
202 photos
5 videos
10 files
92 links
This is the offical channel of Qelem Meda Technologies.

you can ask any questions at

t.me/qelemmedatechnologiesgroupchat

🌐 www.qelemmeda.com
☎️ 0933210000
📨 qelemmeda@gmail.com
Youtube: youtube.com/@qelemmedatechnologies
twitter: @qelemmedatech
Download Telegram
ቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂስ የብቃት ማረጋገጫ ሲስተም በማበልጸግ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በማስተግበር ላይ ይገኛል። ይህ ሲስተም ከተፈታኞች ምዝገባ ጀምሮ እስከ ሰርቲፊኬት ህትመት ድረስ ማከናወን የሚያስችል ሲስተም ሲሆን በሲስተሙ ከሚከናወኑት ሂደቶች ውስጥ የተፈታኞች ምዝግባ ፣መለያ ቁጥር መስጠት፣ የተፈታኞች መለያ ካርድ ዝግጅት፣ ቅድመ ፈተና የተፈታኞች ሪፖርት ፣ እርማት ፣ የድህረ እርማት የተፈታኞች ሪፖርት እና ትንታኔዎች እና የሰርቲፊኬት ዝግጅት ዋና ዋና ተግባራት ናቸው። እስካሁን የነበረው የፈተና እርማት ሂደት ተፈታኞች በወረቀት ተፈትነው በሲስተም የሚታረምበት ሂደት ነበር።

ኩባንያው ይህን ሲስተም ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የኮምፒውተር እና የኢንተርኔት መሰረተ ልማት በተሟላባቸው አካባቢዎች የፈተና ሂደቱን ሙሉ በሙሉ በበይነመረብ መፈተን የሚያስችል ዲጂታል ፕላትፎርም ማበልጸጉን አሳውቋል። ኩባንያው አዲስ ያስተዋወቀው ዲጂታል ፕላትፎርም ሁለቱንም የእርማት ዘዴ ማለተም ወረቀት ተኮር (paper based ) እና የበይነ መረብ ፈተና (online exam) አማራጭ ያካተተ ሲስተም ሲሆን ይህም ሲስተም ወደ ትግበራ የሚገባበትን ሁኔታ እና የአጠቃቀም ሂደቱን በተመለከተ የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ አባገዳ አዳራሽ ስልጠና ሰጥቷል። በስልጠናው ላይ የተገኙት የቀለም ሜዳ ስራ አስኪያጅ እና ሌሎች የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮው ኃላፊዎች የሲስተሙን ፋይዳ ለሰልጣኞች አብራርተዋል። ሰልጣኞችም ባገኙት ስልጠና መሰረት የተፈታኞችን መረጃ በማደረጀት የበይነ መረብ ምዝገባ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

ቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂስን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጫኑ።
ድረ ገጽ |ቴሌግራም | ዩቱዩብ
Qelem Meda Technologies | QMT
school registration template.xlsx
Please use this template to register new school
ቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂስ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል የሮስተር ማስተዳደሪያን እና እርማት ሲስተምን አስመልከቶ ለኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ   የትምህርት ባለሙያዎች እና ኃላፊዎች ስልጠና ሰጠ

በቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂስ ተበልጽጎ በ2014 ዓ.ም  ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ተግባር ላይ የዋለው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ የሮስተር ማስተዳደሪያ እና እርማት ሲስተም ለአጠቃቀም ምቹ ፣ ቀላል እና  ወጪ ቆጣቢ መሆኑ ይታወቃል።  በ2015 ዓ.ም ከ2014 ዓ.ም ከነበረው  በተሻለ መልኩ ሂደቶችን ቀላል እና ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ መልኩ ተሻሽሎ  ለመተግበር  የተቻለ ሲሆን  በዚሁ አመትም ከ8 በላይ የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተገበሩት ሲሆን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ማጠቃለያ እርማት በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተግባራዊ ለማድረግ ተችሏል።
በተያዘው  የ2016 ዓ.ም  የትምህርት ዘመንም  የኦሮሚያ ክልል ለሚያስፈትናቸው የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ማጠቃለያ ተፈታኝ ተማሪዎች የሲስተሙን አጠቃቀም አሰመልክቶ ቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂስ በአዳማ ከተማ በክልሉ ከተለያዩ ዞኖች ፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ወረዳዎች ለተወጣጡ የፈተና ክፍል ኃላፊዎች እና የአይሲቲ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል። ሰልጣኞችም ባገኙት ስልጠና መሰረት የተፈታኞችን መረጃ በማደረጀት የበይነ መረብ ምዝገባ ማካሄድ  ላይ ይገኛሉ:: በተያያዘ ዜና እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት በዚህ ዓመት ከ11 ክልሎች በላይ በዚህ ሲስተም ከምዝገባ እስከ ሰርቲፊኬት ህትመት ያለውን ስራቸውን ለማከናወን ውል ወስደው ወደ ሾል መግባታቸውን የድርጅቱ ዋና ስራአስኪያጅ ገልፀዋል ።
ቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂስ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቦንጋ ከተማ የሚኒስትሪ ሮስተር ማስተዳደሪያ ሲስተምን በተመለከተ ስልጠና ሰጠ

የሚኒስትሪ ሮስተር ማስተዳደሪያ ሲስተም በቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂስ ተበልፅጎ በ2015 የትምህርት ዘመን  ተግባር ላይ ከዋለባቸው ክልሎች ውስጥ አንዱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ነው ። በ2016 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ ክልሉ ከተማሪዎች ምዝገባ እስከ ድህረ እርማት ያሉ የሪፖርት እና ሰርተፊኬትን ለህትመት ዝግጁ ማድረግ የሚያስችለው ሀገር በቀል ባለብዙ የመፈትሄ አማራጭ ሲስተም ለመጠቀም ዝግጅት ላይ ናቸው ። ስልጠናው በክልሉ መዲና ቦንጋ ከተማ ከተለያዩ ዞን ፣ ከተሞች እና  ወረዳዎች ለተወጣጡ ባለሙያዎች እና የስራ ኃላፊዎች በቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂሰ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በስልጠናውም  ላይ የተገኙት የክልሉ የፈተና ምዘና ዳይሬክተር ኃላፊ አቶ ሲሳይ ኃይለ ሚካኤል  የመክፈቻ áŠ•áŒáŒáˆ­ ያደረጉ ሲሆን በተጨማሪም የስልጠናው አላማ እና ሂደቱ አስመልክቶ ለስልጣኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል። በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የ ክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ   ለስልጠናው ተሳታፊዎች የተማሪዎችን መረጃ  በጥንቃቄ  ማደራጀት እና መመዝገብ እንዳለባቸው አሳስበዋል። ሰልጣኞችም በተሰጣቸው ስልጠና መሰረት የተማሪዎችን ምዝገባ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።