Psychology Spotlight
507 subscribers
193 photos
15 videos
72 files
3 links
🌟 Welcome to Psy-COOL-ogy!
A destination for students and psychology enthusiasts. Enhance your understanding of psychology. Get study guides, short videos, and practice questions for an enjoyable learning experience. 🌟
Download Telegram
ይቆፍራል። መቃብሩንም ከቆፈረ ሰንብቷል-  ቆፈረ 2ኛ ምንጭ፣ ቆፈረ 3ኛ ምንጭ ፣ ቆፈረ 4ኛ ምንጭ........... ይቆፍራል...

አባባ:- ስንት ምንጭ አደፈረስክ፣ እስቲ ተመርመር?

አደፍርስ:- ምነው የታመምኩ እመስላለሁ?

አባባ:- አዎ ከአንገተ በላይ (ቅንጭላቱን እየጠቆሙ)

አደፍርስ:- am normal, እንዴ በግድ እበድ ልትለኝ ነው?

አባባ:- Brain እንዴት ነው bro?,  ከታችማ ሁሉም አንድ ነው። አንተ ደሞ 1 እግር ከቀረህ እንጂ ኮ***- ተነስ እንሂድ dude

የአይምሮ ንጽህና መጠበቂያ ማእከል ይላል — ማእከሉ የ brain እጥበቶችን ያስተናግዳል የነ አደፍርስ አይነትን ጨምሮ

ገቡ ምርመራ ተካሄደ......

ውጤት:- አባባ ለጊዜው እኛ ጋር  ቦታ ሞልቷል፣ ቦታ እስኪለቀቅ ሴቶች የማይደርስበት ቦታ ይቀመጥ።

አባባ:- የት where የት ላስቀምጠው እ?  ኡ ኡ ኡ ኡ dear እህቶች ሴቶች ሆይ ግዛታችሁን ጠብቁ pleaseee
❤4🤣3😁1
TCFBONMCBXNV /    2810925249

💥 እነዚህን letters ወይም ቁጥሮች ማስታወስ ከባድ ነው።

ግን CNN  FOX  BBC  MTV ወይም ቁጥሮቹን 281  0925  249 ስናደርገው ለመያዝና ለማስታወስ ይቀላል።

💥ረዥም፣ የተወሳሰቡ እና ብዙ መረጃዎችን ወደ ትናንሽ group ስንመድብ በቀላሉ ለመረዳትና ለማስታወስ ይረዳናል። ይህ process ቸንኪንግ (Chunking) ይባላል።  

💥 Short-term ሚሞሪያችን (STM) ፈጣን ነው ነገር ግን ውስን አቅም ነው ያለው። በአንዴ 7±2 (5-9) info/መረጃ ብቻ ነው የሚይዘው።

💥Chunking የ short-term ሚሞሪያችንን አቅም maximize ለማድረግ የሚጠቅም አንዱ መንገድ ነው።

CNN  FOX  BBC  MTV (በአንዴ 12 letters መያዝ ከSTM አቅም በላይ ነው ወደ 4 group አሳነስናቸው STM ላይ መያዝ ያስችለናል)

💥 ሌላ ቀላል ምሳሌ እንዴት ነው ስልክ ቁጥር memorize የምናደርገው:- ከእያንዳንዱን digit ይልቅ ቸንክ አርገን ነው የምንይዘው

💥 የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅመን information ቸንክ ማድረግ ይቻላል። ለምሳሌ:- የመረጃውን pattern ወይም context በማየት፣ association በመፍጠር፣ Acronyms ጭምር በመጠቀም chunk ማድረግ እንችላለን። 

💥Chunking መረጃውን short-term ሚሞሪ ላይ ቶሎ ለመያዝ ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ ለአመታት በቃላሉ እንድናስታውሰው long-term ሚሞሪ ላይ እንዲሰራ ያስችለናል
❤4👍2🥰1
እናዝናለን

አንዳንድ ሴቶች፣ እህቶች፣ እናቶችስ የነሱ ወንድም፣ ባል፣ ልጅ፣ ጓደኛ... ጥቃት ሲፈጽም ጥቃቱ ጥቃት የማይመስላቸው። ሽንጣቸውን ገትረው unfairly የሚከራከሩለት። የሚደብቁ፣  አብረው የሚያጠቁ። ከገባሽ በዚ አቋማችን ጥቃት መቼም መቼም መቼም..... አይቀንስም። ጥቃት ጥቃት ነው ቀፋፊ ነው። አንዳንዶች ላይ የሚያምር አንዳንዶች ላይ የሚቀፍ መልክ የለውም።
Once again, ይሄን ድንቁርና ለምታራምዱ የኛ ጾታ አባላት እናተ ትኩሳቶች ለእናተም እናዝናለን 😭😭😭

March ስለሆነ እንጻፈው
😢8💯1
Catcallers (ለካፊዎች) ለከፋቸው ጉዳት እንደሌለው ወይም fun እንደሆነ ያስባሉ። ነገር ግን ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለከፋ በመጥፎ እና serious በሆነ መልኩ የተለካፊውን የስነ-ልቦና ደህንነት ይጎዳል።

💥ማንም ሰው መለከፍ አይፈልግም

💥 ሰብአዊ የሆነውን ነገር እንኳን ትተን ለከፋ እና የመሳሰሉት ማለት: የኔ መብት ያንተ መብት ጋር ወይም ያንተ መብት የሷ መብት ጋር እንደሚያቆም አለማስተዋላችን ነው?

የኛ መብት የሌላኛው ሰው መብት ጋር ያቆማል
❤5
Saroonni ni boo'u, garuu karavaan itti fufa
👌4💯2
Inni waan jal'aa hojjetu, jal'aadhuma isaa haa hojjetu; inni xuraa'aan, ittumaa of haa xureessu; inni waan qajeelaa hojjetu, qajeelaadhuma isaa haa hojjetu; inni Waaqayyoof qulqullaa'e, isumaaf haa qulqullaa'u!” jedhee anatti hime.
Inni dhufu sun, “Kunoo, ani dafee nan dhufa, gatii isa ani adduma addaan akka hojii isaatiitti namaaf kennus fidee nan dhufa.
❤7👍4👌3🙏1
ምልመላ

ሱቅ ተልካ እየሄደች ነው

እነ አደፍርስ:-  "ሚጣ ስታድጊ ልምጣ"

ሚጣ:- (ቤት ገብታ አባቷን) አባ እኔ ለእነሱ ነው እንዴ ማድገው?

አባባ:- የኔ እንቡጥ ምን ውስጥ ልደብቅሽ? (እንባ ወደ ልባቸው ቋት ዱብ ዱብ)

ሚጣዬ እያደገች ነው! አሁን መች ስትላክ ብቻ? ምልመላው ቀጥሏል (ት/ቤት፣ ኮሌጅ/ስራ ፍለጋ/ስራ ቦታ/  እግሯ የረገጠበት everywhere.... )

1ኛው አደፍርስ:- ቆይ ምንም ስለሌለኝ ንቀት ነው አደል; ወይኔ አዴው (የሚሰማውን ጎዶሎነት በሷ ያላክካል ይፎክራል)

ሌላኛው አደፍርስ:-  እናደርግልሻለን፣ የሚያስፈልግሽን እንሰጥሻለን ብቻ  አንቺ አ***ይ

አባባ:- ተያቸው እንደፈለጉ ይወረግረጉ። እዚ ምድር ላይ ፍጥረት ሁሉ የራሱ ድርሻ አለው። መቼ ያንቺን ጨርሰሽ የእሱን ትፈልጊያለሽ? ያንቺ መቼ ተነካና, እ? አትዘናጊ, ቢከልሉሽም ተንጠራርተሽ የራስሽን ትኩር ብለሸ እዪ።
ጥንብ አንሳ እራሱ አድኖ ገሎ በልቶ አያውቅም። ትርፍራፊያቸውን ሊያስለምዱሽ ነው

ሚጣ:- አባ የኔ ፍቅርርር ልቤ ጥፍት እስኪል ነው የምወድህ 😘😘😘
👍4😁3
Deflection በሳይኮሎጂ ምንድነው?

💥 የማንስማማበት ነገር እንዳለ እያወቁ አለመስማማቱን independently እንዳይታይ,  የራሳቸውን ስህተት ለማስቀጠል እና interest ለማስጠበቅ ሲሉ እኛ Personalize ሳናደርግ አደረጋቹ እያሉ (ይኼ ላንተ ብቻ/ላንቺ ብቻ አደለም እያሉ ጥያቄያችን ወይም ምላሻችን ላይ እኛ የ perception ችግር እንዳለብን እያስመሰሉ ወዳላሰብነው የሚጠመዝዙ፣ የሚያስወስዱብን፣ በእኛ የሚያላክኩ ጠ***ዝ የሆኑ ሰዎችን ይወክላል
👍7
Diffusion of responsibility

💥 ብዙ ሰዎች ባሉበት ሁኔታ በሚፈጠሩ ክስተቶች እያንዳንዱ በቦታው ያሉ ሰዎች (bystanders) እርምጃ ከመውሰድ ወይም ከመርዳት ይልቅ ሌላኛ ሰው action እንደሚወስድ መጠበቅ እና ለእርዳታ አለመዘርጋት ነው

💥 Diffusion of responsibility ዝም ብለን እንድናልፍ ወይም እንድንመለከት ሊያደርገን ይችላል።

💥 ተመራማሪዎች እንደሚነግሩን 2 ምክንያቶች አሉ። 1ኛ ሌላ ሰው ሊረዳት/ሊረዳው ይችላል ብሎ ማሰብ ሲሆን 2ኛው ብዙ ሰዎች በመኖራቸው የእኔ ሃላፊነት ብቻ አይሆንም ወይም እኔ ብቻ ተጠያቂ ልሆን አልችልም ብሎ እያንዳንዱ ሰው የማሰብ ዝንባሌ ስላለው እንደሆነ አጥንተዋል

💥 ጥናቶቹ እንደሚያሳዩን Diffusion of responsibility ሰዎች የተለያዩ ድንገተኛ ክስተቶችን እና አደጋዎችን (ድንገተኛ ህመም፣ ግድያ፣ ዘረፋ፣ የመኪና አደጋ፣ ጠለፉ፣ የተለያዩ ችግሮችን.....) report ሳያደርጉ ወይም እርዳታ ሳይሰጡ እንዲያልፏ  አድርጓቸዋል

💥 ሁኔታው የሚፈቅድ ከሆነ አንድ ሰው ሊረዳኝ ይችላል ብሎ ከመጠበቅ ይልቅ የሚፈልጉትን እርዳታ ግለሰቦችን እርጂኝ/ዳኝ ብሎ መጠየቅ አደጋውን ለመቀነስ ወይም emergency እርዳታ ለማግኘት ይመከራል
👍6
Deindividuation

💥 ሰዎች በ group ውስጥ ሲሆኑ ግላዊ ማንነታቸውና ሃላፊነታቸው እንደሚቀንስ ስለሚሰማቸው ብቻቸውን ቢሆኑ የማያደርጉት ድርጊት ውስጥ ይሳተፋሉ።

Deindividuation ውስጥ:

💥 Anonymity አለ:- ግለሰቦች በቀላሉ ልለይ ወይም ተጠያቂ ልሆን አልችልም ብለው ሲያስቡ የሚቃወሙት ድርጊት ውስጥ ጭምር ሊሳተፏ ይችላሉ።

💥 ሌላው ሁሉም ሰው እያደረገው ነው የሚለው ሃሳብ ግለሰቡ collective mindset ውስጥ እንዲገባና በዛ መሰረት ድርጊቱን justify እንዲያደርግ ያደርገዋል።

💥 በተጨማሪ self-perception ይቀየራል:- በgroup የሚደረጉ ድርጊቶች ውስጥ ግለሰቦች እራሳቸውን እንደ አንድ የድርጊቱ ፈጻሚ ሳይሆን የgroup አባል አድርገው ይቆጥራሉ። የ group identity ስለሚፈጠር moral responsibility ይቀንሳል

💥 የቁጥጥር አለመኖርና social norm ሳይሰራ ሲቀር ሰዎች በቅጽበታዊነትና selfishly ያለ ፍርሃት ድርጊቶችን እንዲፈጽሙ፣ የግል ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙበት opportunistic behaviors ውስጥ እንዲሳተፏ ሊያደርጋቸው ይችላል
❤6💯4👍2
PERSONALITY PSYCHOLOGY NOTE 1.pdf
79.6 KB
Introductory note on personality psychology and practice questions
👍6
Tetris Effect

💥 ለአንድ activity ወይም ለሚታይ ነገር ጊዜን፣ ትኩረትን ሰጥቶ ለረዥም ጊዜ መጋለጥ እንዴት ሳንፈልግ involuntarily ሃሳባችን፣ ልምምዳችን፣ እንቅልፋችን ላይ ጭምር ተጽኖ እንዳለው ይገልጻል ።

💥 Tetris (ቴትሬስ) የሚለው ቃል የመጣው በጣም ታዋቂና ቀላል ከሆነው Tetris game ነው።

💥 ጥናቱ እንደሚነግረን ለረዥም ጊዜ የተጫወቱ ሰዎች ላይ ጨዋታውን ካቆሙ በኋላም የጌሙ effect ይቀጥላል። በ real-world የሚያዩትን ነገሮች እንዴት እንደሚገጣጠሙ፣ pattern እንደሚሰሩ...

💥ለምሳሌ:-  ሙዚቀኞች እንዴት በተለየ structure ሙዚቃውን compose እንደሚያደርጉ፣ visual አርቲስቶች፣ Architects እንዴት design እንደሚያወጡ፣ ሌሎችም የሚያዩትን የተለያዩ ቅርጾችን ፣ እቃዎችን፣ ሳጥኖችን፣ ቦታዎችን፣ ህንጻዎችን እንዴት arrange፣ rotate እንደሚያደርጉ በልባቸው አይን እንደሚያዩ፣ እንደሚያስቡ፣ ተኝተው እንደሚያልሙ report አድርገዋል።

💥 Tetris effect የፈጠራ ችሎታን ሲጨምር። ለአንዳንዶችም ለጊዜው ዙሪያቸው ካለው አለም ማምለጫ አይነት መንገድ ነው

💥 Rare ቢሆንም አንዳንዶች ላይ ጤናማ ባልሆነ መልኩ obsessed እስኪሆኑ በ hallucinatory ኢሜጆች እንዲታወኩ ሊያደርግ እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ።

💥 ይህ effect አዕምሮአችን እንዴት off-hours ላይ እንኳን የዕለት ድርጊታችንን process እንደሚያደርግና ተደጋጋሚ ድርጊቶች በሃሳባችን ላይ ያላቸውን ተጽኖ አሳይቷል።
❤9💯1