PROGRAMMERS TECH
66 subscribers
93 photos
123 videos
33 files
214 links
If you learn here you are going to hack any account and you are gonna be programmer
Contact us @Programhack_bot
Download Telegram
Ethical Hacking የሚሆኑ ምርጥ አሪፍ ቱሎች!
..............................................

ወደ Ethical Hacking በጥልቀት ከመሄዳችን በፊት ስለ አንዳንድ ቱሎቹ ቴክኖሎጂ ምንነት እንጀምር።
የሳይበር ደህንነት ተጠቃሚዎችን ከሳይበር ጥቃት የሚከላከል ከሆነ፣ ሀከር ደሞ የተጠቀሚዎችን ግላዊ ዳታ ወይም ሚስጥር ለመውሰድ ሰብሮ የሚገባ ነው። ግን አዚህ ጋር እንዳትሳሳት #hacking ሁሌም መጥፎ ነገር ብቻ የሚሰራበት አይደለም። ጥሩ ጎኑን ለማሳየት "ethical" የሚለው ቃል ከፊቱ የተጨመረበት ለዛ ነው።
#ethical_hacker የአንድን መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት በኮምፒዩተር ሲስተማቸው ብሎም ኔትወርካቸው ውስጥ ያለውን ክፍተት (vulnerabilities) በማጣራት የሳይበር ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚሰራ ግለሰብ ነው። በአጭር አገላለጽ፣ አንድ ሰው ቤሄራዊ ደህንነት ለማስጠበቅ የግድ መከላኪያ መግባት አይጠበቅበትም፣ #ethical_hacker ም ሆኖ የሀገሩን የሳይበር ደህንነት ከሌሎች ሀገር የተቃጣ የሳይበር ጥቃት መከላከል ይችላል።

ልምድ ያላቸው ሰዎች በስፋት የሚጠቀሙትን ቱሎች እንያ እስቲ..

💠1. Nmap
Nmap (ወይም Network Mapped)፣ ፈጣንና አስተማማኝ የኔትወረክና ፖርት ስካኒንግ ቱል ነው፣ የተፈጠረው በ #GordonLyon ሲሆን፣ የመጀመሪያው የተለቀቀው በ1997 አመተ ምህረት ነበር።
Nmap ለደህንነት ብሎም የተለያዩ ክፍተቶችን ስካን ማድረግ የሚችል ሀይለኛ ቱል ነው!