AA City Procurement Directorate Adminstration
1.22K subscribers
266 photos
108 files
17 links
Download Telegram
👏2🙏1
Kassahun
Photo
ይህንን መልዕክት ያያችሁ የሚመለከታችሁ አካላት በመልዕክት መላኪያ "ደርሶናል" በሉን። ላልደረሳቸውም ተቋማት share አድርጉላቸው።
👍1
መመሪያ ቁጥር 197/2019 የተቋማትን የግዥ አፈጻጸም ብቃት በማሳደግ በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገለጸ።
########################
ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ፋይናንስ ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥን ግልጽ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊ እና ከሙስና የጸዳ ለማድረግ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የግዥ ሥርዓት እንዲኖር እና የኤሌክትሮኒክ አሠራር ዘዴን ተግባራዊ በማድረግ በዘርፉ የሚታየውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ፣ የአካባቢ ጥበቃንና የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ያገናዘበ እንዲሁም ተቀባይነት ካላቸው ዓለም አቀፍ የግዥ ሥርዓቶች ጋር የተናበበ ለማድረግ እንዲቻል ያዘጋጀውን የመንግሥት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 197/2019 ለሚመለከታቸው ተቋማት ኃላፊዎችና ዳይሬክተሮች ስልጠና ሰጠ።

በመድረኩ ላይ የስልጠና ሰነዱን ያቀረቡት በመንግሥት ግዥ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የሥልጠና ባለሙያ አቶ ደሴ አዳም፤ የመመሪያውን አስፈላጊነት፣ የግዥ ሂደቶችን፣ የሕግ ማዕቀፎችን፣ ስልቶችን እና የፍላጎት መግለጫ አዘገጃጀትን በዝርዝር አቅርበዋል። የግዥ መርሆዎችን እና የሕግ ማዕቀፎችን የተከተለ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ውጤታማ የግዥ አፈጻጸም ሥርዓት በከተማ ደረጃ እውን እንዲሆን ለማስቻል በመንግሥት ግዥ አፈጻጸም መመሪያው ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በአፈጻጸም ወቅት እያጋጠሟቸው ያሉ ችግሮችን በማንሳት ጥያቄዎችን አቅርበዋል፤ ግልጽነት ለጎደላቸው ነጥቦችም ተገቢው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት መመሪያውን የበለጠ ግልጽ እና ተግባራዊ ለማድረግ ተከታታይ ሥልጠናዎች የሚሰጡ መሆኑን የገለጹት በፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ብዙዓየሁ ናቸው።

የመድረኩን ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የፋይናንስ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ጣሌ፤ አዲሱ መመሪያ ረጅም ጊዜ አገልግሎት ላይ የነበረውን የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 3/2002 በማሻሻል የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል።

መመሪያው የከተማዋን ዕድገትና ልማት ፍላጎት በሚመጥን መልኩ የተቋማትን የግዥ አፈጻጸም ብቃት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው ገልጸው፣ መመሪያው ከህዳር 01/2019 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሆነ በመረዳት ለተግባራዊነቱ ትኩረት እንዲሰጠው አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩን አጠናቀዋል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን !!
ዌብሳይት:- aacbof.gov.et
ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/aabof.gov.et?mibextid=ZbWKwL
ቴሌግራም:- https://t.me/AACABOFP
ዩቲዩብ:- youtube.com/channel/UCTPN7Re7T7tp_ekAhVuw2uA
ዋትሳፕ:-https://chat.whatsapp.com/FLSn12vRmsR9JsKUVDWxgtuuuu
ቲክቶክ፡- Addis Ababa finance bureau
የመንግስት ግዢ መመሪያ ቁጥር 197/2019
ለሁሉም ተቋማት!
ለውድ ፋይናንስ ቢሮ ማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቻችን  እና ቤተሰቦች
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥን ግልጽ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊ እና ከሙስና የጸዳ ለማድረግ፣ ግዥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን እና የኤሌክትሮኒክ አሠራር ሥርአት ተግባራዊ በማድረግ በዘርፉ የሚታየውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ፣ የአካባቢ ጥበቃንና የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ያገናዘበ እንዲሁም ተቀባይነት ካላቸው ዓለም አቀፍ የግዥ ሥርዓቶች ጋር የተናበበ ለማድረግ እንዲቻል  አዲስ ያዘጋጀውን ያዘጋጀውን የመንግሥት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 197/2019  ከህዳር 1/2019 ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

ይህ መመሪያ አዲሱ መመሪያ ረጅም ጊዜ አገልግሎት ላይ የነበረውን የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 3/2002 በማሻሻል የተዘጋጀ ሲሆን የመንግስት ገንዘብ ከፍተኛውን ጥቅም (Value for Money) እንዲያስገኝ፣ ጠንካራ መሠረት የሚጥል ነው።
በቀጣይም፦
¡       ግዥዎች ሊመሩባቸው የሚገቡ 8 መሠረታዊ መርሆዎችን፣
. የግዥ ዘዴዎችና የአፈጻጸም ስልቶች
¡        በግዥ ወቅት ለሀገር ውስጥ አምራቾች እና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደረጉ ልዩ ድጋፎችንና ማበረታቻዎችን እና ስለመመሪያው ዝርዝር በተከታታይ ክፍሎች ይዘንላችሁ የምንቀርብ ሲሆን መመሪያውን በቢሮው ዌብሳይት ያገኙታል።
የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን በመቀላቀል መረጃውን ለሌሎችም ያካፍሉ!
¡       ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን !!
ዌብሳይት:- aacbof.gov.et
ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/aabof.gov.et?mibextid=ZbWKwL
ቴሌግራም:- https://t.me/AACABOFP
ዩቲዩብ:- youtube.com/channel/UCTPN7Re7T7tp_ekAhVuw2uA
ዋትሳፕ:-https://chat.whatsapp.com/FLSn12vRmsR9JsKUVDWxgtuuuu
ቲክቶክ፡- Addis Ababa finance bureau
📢  áŠ á‹˛áˆą የመንግስት ግዥ አዋጅና መመሪያ ለሀገር ውስጥ አምራቾችና ማህበራት ይዞት የመጣው እድል
በአዲስ አበባ የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አግባብነት ባለው የግዥ ዘዴ በማወዳደር፣ ለስራ ዕድል ፈጠራ ተቋማት (ማህበራት) የሚከተሉትን ግዥዎች እንዲፈጽሙ ተፈቅዶላቸዋል፦
🔹 የግንባታ ስራዎች፡ ለአንድ ግዥ እስከ 50 ሚሊዮን ብር
🔹 የግንባታ ግብዓት አቅርቦት፡ ለአንድ ጊዜ ግዥ እስከ 5 ሚሊዮን ብር
🔹 የካፌ አገልግሎት፡ ማህበራትን እርስ በርስ በማወዳደር ግዥ መፈጸም
በጨረታ ወቅት የሚደረጉ ልዩ አስተያየቶች (Preference)፦
✅ 3% — በማምረት ስራ ላይ ለተሰማሩ ማህበራት
✅ 3% — በማምረት ስራ ላይ ለተሰማሩ ሴቶች
✅ 3% — በማምረት ስራ ላይ ለተሰማሩ አካል ጉዳተኞች
✅ 7.5% — ለሀገር ውስጥ ተቋራጮች እና አማካሪዎች
✅ እስከ 15% — ለሀገር ውስጥ እቃ አምራቾች (እሴት በጨመሩበት ልክ)
✅ እስከ 25% — ለሀገር ውስጥ የህክምና እቃና መድሀኒት አምራቾች (እሴት በጨመሩበት ልክ)
✅ እስከ 5% — የቴክኖሎጂ ፈጠራስራዎች  áŠĽáŠ“ ለሌሎችም ….
💡 ማጠቃለያ፡ ይህ መመሪያ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራትን፣ ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን በማበረታታት በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ትልቅ እድል የከፈተ ነው።
👏2
የኮሚቴ አሰያየምና ተግባራት