እንግሊዝ ሩሲያን አስጠነቀቀች
እንግሊዝ በአትላንቲክ የሩሲያ የባህር ላይ እንቅስቃሴ መጨመሩን ማረጋገጧን አስታወቀች።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ጆን ሂሊ ሶስት የባህር ሰርጓጅ መርከቦች በቀጣናው በውል ያልታወቀ ተልዕኮን ማከናወናቸውን ገልጸዋል።
በምላሹም ዩናይትድ ኪንግደም የጦር መርከቦችንና አውሮፕላኖችን በቀጣናው በማሰማራት አንድ ወር ለቆየ ግዜ የሩሲያ መርከቦች እንቅስቃሴ ላይ ክትትል ማድረጓን ተናግረዋል።
እንግሊዝ በቀጣናው የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዕቅድ የሆነውን ስውር እንቅስቃሴን በማጋለጥ አክሽፋለች ብለዋል።
መከላከያ ሚኒስትሩ ለፑቲን ቀጥታ ባስተላለፉት መልዕክት ‘’በገመድና ትቦ መሰረተልማቶቻችን ላይ የምታደርጉትን እንቅስቃሴ አይተናል፤ እንድታውቁት የምንፈልገው በመሰረተ ልማቶቹ ላይ የጥቃት ሙከራ ብታደርጉ ምላሽ እንደሚጠብቃችሁ ነው’’ ብለዋል።
በአትላንቲክ በእንግሊዝ መሰረተ ልማቶች ላይ የደረሰ ውድመት ስለመኖሩ ግን የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩን ጠቁመዋል።
@primezena
#primenews

ደቡብ ኮሪያ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የነዳጅ ጫኝ መርከቦች በሰላም እንዲያልፉ ለማድረግ ወደ ኢራን ልዩ መልዕክተኛ ልትልክ ነው።
@primezena
#primenews
@primezena
#primenews
ኢትዮጽያዊው ዕጩ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የባለሙያዎች ኮሚቴ አባል ሆነው ተመረጡ
ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ዓብዲ ጅብሪል ዓሊ በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ፣ ለኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ኮሚቴ አባልነት በከፍተኛ ድምፅ ተመርጠዋል።
በአሁኑ ወቅት በኢሰመኮ ኮሚሽነር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት ዶ/ር ዓብዲ፣ ከአፍሪካ የቀረቡ ስድስት ዕጩዎችን በመብለጥ 49 ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸው የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ስኬትና የባለሙያውን ብቃት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

“እሳቱን አሁኑኑ አጥፉ” — ኢራን ለአሜሪካና እስራኤል ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጠች
የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤና የሀገሪቱ ከፍተኛ ተደራዳሪ ሞሃመድ ባገር ጋሊባፍ፣ ሊባኖስና መላው የ“መቋቋም ዘንግ” ከኢራን ጋር የማይነጣጠሉና የተኩስ አቁም ስምምነቱ ቀጥተኛ አካል መሆናቸውን በፅኑ አሳስበዋል። ጋሊባፍ በሰጡት መግለጫ፣ የሊባኖስ ጉዳይ በስምምነቱ ውስጥ እንዲካተት የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ በግልጽ ማረጋገጫ የሰጡበት በመሆኑ፣ አሁን ላይ ሰበብ በመፈለግ ወደ ኋላ ለማፈግፈግ የሚደረግ ሙከራ በፍጹም ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀዋል።
አፈ ጉባኤው አክለውም፣ የተኩስ አቁም ስምምነቱን መጣስ ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍልና ከኢራን በኩል እጅግ የላቀና ጠንካራ ምላሽ እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል። “እሳቱን አሁኑኑ አጥፉ” ሲሉ ጥሪያቸውን ያስተላለፉት ጋሊባፍ፣ እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርገውን ጥቃት ካላቆመች በፓኪስታን አደራዳሪነት የተጀመረው የሰላም ጥረት አደጋ ላይ እንደሚወድቅና የኢራን ጦር አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑን አመልክተዋል።

PRIME NEWS ፕራይም ዜና
Photo
update
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ ሀገራቸው ታጣቂውን የሄዝቦላህ ቡድን ትጥቅ ለማስፈታት እና ሰላማዊ ግንኙነት ለመመስረት ያለመ ቀጥተኛ የሰላም ድርድር ከሊባኖስ ጋር "በተቻለ ፍጥነት" እንደምትጀምር ይፋ አደረጉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ላይ እንዳብራሩት፣ "ሊባኖስ ከእስራኤል ጋር ቀጥተኛ ድርድር ለመክፈት ደጋግማ እያቀረበች ያለውን ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤቴ (ካቢኔው) በተቻለ ፍጥነት ከሊባኖስ ጋር ቀጥተኛ ድርድር እንዲጀምር ትናንትና ትዕዛዝ አስተላልፌያለሁ" ብለዋል።
ይህ በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ውይይት፣ በዋናነት የሄዝቦላህን ወታደራዊ አቅም እና የጦር መሳሪያ በማስፈታት እንዲሁም በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል ዘላቂ ሰላማዊ ግንኙነትን በመገንባት ላይ እንደሚያተኩር ኔታንያሁ አስታውቀዋል።
በተያያዘም የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዋና ከተማዋን ቤሩትን ከጦር መሳሪያ እና ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ (ማድረግ ያቀረቡትን ጥሪ፣ እስራኤል በበጎ እንደምትመለከተው እና እንደምታደንቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። ይህ እርምጃ በቀጠናው የተፈጠረውን አስከፊ የጦርነት ውጥረት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ትልቅ የሰላም ጭላንጭል የፈነጠቀ ሆኗል።

#Tigray
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲቀጥል በፌዴራል መንግስት የተላለፈውን ውሳኔ "የፕሪቶሪያውን ስምምነት የጣሰና እውቅና የሌለው ነው" ሲል ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ተቃውሟል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋም ያለበት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት በሁለቱ ፈራሚ አካላት (በህወሓት እና በኢትዮጵያ መንግስት) መካከል በሚደረግ የሁለትዮሽ ፖለቲካዊ ውይይት መሆን ሲገባው አሁን የተደረገው ግን ይህንን አካሄድ የሳተ ነው ብሏል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ የስራ ዘመን በመጋቢት 30/2018 ዓ.ም ለአንድ ተጨማሪ ዓመት እንዲራዘም የተወሰነው የኢትዮጵያ መንግስት ከስምምነቱ በፊት በነበረ ህግ በመጠቀም የወሰነው "የተናጠል ውሳኔ" መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።
ይህ የጊዜ ማራዘሚያ ውሳኔ ከህወሓት እውቅና እና ተሳትፎ ውጪ የተከናወነ በመሆኑ ድርጅቱ እንደማይቀበለው አስታውቋል።
ላለፉት ሦስት ዓመታት የቆየው ጊዜያዊ አስተዳደር በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ አልፎ በሁለቱ አካላት ስምምነት የተመሰረተ እንደነበር ያስታወሰው መግለጫው፤ አሁን ያለው አካሄድ ግን ስምምነቱን ወደ ጎን ያገለለ ነው ሲል ወቅሷል።
ከትላንት በስቲያ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ለተጨማሪ አንድ አመት ትግራይ ክልልን በፕሬዜዳንትነት እንዲመሩ ስልጣናቸውን እንዳራዘሙላቸው ይታወቃል።
ሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ/ም

❤1
ይህ ምን ያስከትል ይሆን ?
የኢራን ፓርላማ የአሜሪካ እና የእስራኤል መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል በዘላቂነት እንዳያልፉ ሊያግድ ነው።
በባሕረ ሰላጤው አገራት የሚመረተው የነዳጅ ምርት የሚተላለፍበት ወሳኙ የሆርሙዝ ሰርጥን ለመቆጣጠር የሚያስችል ወሳኝ ዕቅድ የኢራን ፓርላማ አዘጋጅቶ በሚቀጥለው ሳምንት ድምጽ እንደሚሰጥበት ተነገረ።
የፋርስ ዜና ወኪል፤ በዚህ ዕቅድ ውስጥ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያላቸው መርከቦች በመተላለፊያው በኩል እንዳይጠቀሙ በዘላቂነት ዕገዳ የሚጥል ሃሳብ ተካቶበታል ብሏል።
የሆርሙዝ ሰርጥ እና በፋርስ ባሕረ ሰላጤው አካባቢ ያለውን ደኅንነት እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በሚል በተዘጋጀው በአዲሱ ዕቅድ መሠረት በመርከቦች እንቅስቃሴ እና የሚገኝ ገቢን በተመለከተ ጉልህ ለውጥ እንደሚኖር የፓርላማው የሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮሚሽን ኃላፊ ተናግረዋል።
ኃላፊው እንደተናገሩት የሆርሙዝ ሰርጥ የሚተዳደርበት አዲሱ አሠራርን የተመለከተው ዕቅድ በኢራን ፓርላማ " ሙሉ ድጋፍ አግኝቶ ተግባራዊ " ይሆናል።
ባለሥልጣኑ የኢራን መንግሥት በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የሚኖረውን ቁጥጥር እና የበላይነት ለማረጋገጥ በተዘጋጀው አዲስ ዕቅድ ውስጥ 5 ዋና ዋና ነጥቦች መካተታቸውን ኃላፊው ዘርዝረዋል።
1. የ ' ጠላት ' መርከቦች እንዳይተላለፉ መከልከል
ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያላቸው ነዳጅ ጫን መርከቦች በዘላቂነት በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል እንዳያልፉ ይታገዳሉ።
2. ከመርከቦች ክፍያ መሰብሰብ
በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦች ለደኅንነታቸው እና ለሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ለሚያገኙት አገልግሎት ክፍያ ይጠበቅባቸዋል።
3. የኢራን ገንዘብን ማጠናከር
የኢራን ገንዘብ የሆነውን ሪያል ለማጠናከር በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ከሚያልፉ መርከቦች የሚሰበሰቡት ሁሉም ክፍያዎች በኢራን ገንዘብ ብቻ ይሆናል።
4. ፋርስ ባሕረ ሰላጤ የሚለው ስም ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ
ሁሉም በሰርጡ የሚተላለፉ መርከቦች በሚኖራቸው የደብዳቤ ልውውጥ፣ በሚያዘጋጇቸው ሰነዶች እና የሬዲዮ መልዕክቶቻቸው ይፋዊውን እና ታሪካዊውን ፋርስ ባሕረ ሰላጤ የሚለውን ስያሜ እንዲጠቀሙ ማድረግ።
5. የሚሰበሰበው ገንዘብ አጠቃቀም
ከሆርሙዝ ሰርጥ ከሚገኘው ገቢ ውስጥ 30 በመቶው የኢራን ወታደራዊ አቅምን ለማጠናከር ሲውል፣ 70 በመቶው ደግሞ የአገሪቱን ዜጎች ሕይወት ለማሻሻል ይውላል።
6 ሳምንታት ከአሜሪካና እስራኤል ጋር በተካሄደው ጦርነት ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን በመዝጋት ከ20 በመቶ በላይ የሚሆነው የዓለም የነዳጅ ፍጆታ እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ ችላለች።
ኢራን ከአሜሪካ ጋር የደረሰችውን የተኩስ አቁም ተከትሎ ፓኪስታን ውስጥ በሚደረገው ድርድር የሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ እንደሚሆን ይጠበቃል።
መረጃው የቢቢሲ ነው።
ሚያዚያ 2 ቀን 2018 ዓ/ም

Forwarded from ዜና ማዕዘን - Breaking
የሴኔጋል ጠ/ሚኒስትር ትራምፕን
"የመረጋጋት ጠንቅ" ሲሉ ከሰሱ
ሐሙስ ሚያዝያ 9 ቀን 2026 በዳካር የጥቁር ህዝቦች ስልጣኔ ሙዚየም በተካሄደው ጉባኤ ላይ የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስት ኡስማን ሶንኮ የዶናልድ ትራምፕን አስተዳደርና የምዕራባውያንን የሀይል የበላይነት ፖሊሲ በጽኑ ተችተዋል።
ሶንኮ ትራምፕን "የመረጋጋት ጠንቅ" ሲሉ የገለጹ ሲሆን፣ የዋይት ሀውስ መሪው አለምን በሰላም ከመጠበቅ ይልቅ ትርምስን እየዘሩ ነው ብለዋል። ትራምፕ "የኖቤል የሰላም ሽልማት ይገባኛል" ብለው መጠየቃቸውም አሳፋሪ መሆኑን ጠቁመው፣ በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ተፅዕኖ ለአለም ደህንነት ስጋት እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት አስርት ዓመታት ምዕራባውያን በቬትናም፣ በኢራቅ፣ በአፍጋኒስታን፣ በሊቢያና በሶማሊያ ያደረጓቸው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቶች ሙሉ በሙሉ መክሸፋቸውን አብራርተዋል።
እነዚህ ጦርነቶች ከተቀመጠላቸው ግብ አንዱንም አለማሳካታቸውን የገለጹት ሶንኮ፣ ውጤታቸውም በየሀገራቱ ውድመትንና ምስቅልቅልን መፍጠር ብቻ እንደነበር ገልጸዋል።
በተለይም "ዲሞክራሲን ወደ ውጭ መላክ" የሚለው አስተሳሰብ የተሳሳተ መሆኑንና የሌላ ሀገር መሪዎችን አውጥቶ በባዕድ ፍርድ ቤት የመክሰስ አካሄድ የህዝቦችን ክብርና ዓለም አቀፍ ህግን የሚጥስ መሆኑን አውግዘዋል።
@Zena_maezen

የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማኅበር በሀገሪቱ የወጪ ንግድ ዘርፍ ላይ የታየውን ከፍተኛ የፍላጎት ጭማሪ ታሳቢ በማድረግ፣ ባዶ ኮንቴይነሮችን ከጅቡቲ ወደብ ወደ እንዶዴ ሁለገብ የደረቅ ወደብ የማጓጓዝ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።
ተቋሙ ይህንን ስትራቴጂካዊ እርምጃ የወሰደው በዚህኛው የሩብ ዓመት የሚጠበቀውን ከፍተኛ የወጪ ንግድ ፍላጎት በብቃት ለማስተናገድና የኮንቴይነር አቅርቦት ፍጥነትን ለማሳደግ መሆኑን ገልጿል።
በዚህ የኮንቴይነር ማጓጓዝ ሂደት ውስጥም ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለሚያበረክቱ ስትራቴጂካዊ ምርቶች ማለትም ለቡና፣ ለጥራጥሬ እና ለቅባት እህሎች ላኪዎች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ተቋሙ ላኪዎችና የመርከብ ወኪሎች ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው ምርቶቻቸውን በወቅቱ እንዲልኩ ጥሪ አቅርቧል።

ሶማሊያ በእስራኤል ውሳኔ ላይ ያላትን ተቃውሞ ገለጸች።
የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ እስራኤል ለሶማሊላንድ ዲፕሎማሲያዊ ተወካይ ለመሾም ያሳለፈችውን ውሳኔ በጽኑ እንደምትቃወም አስታወቀች።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ " ይህ የእስራኤል እርምጃ የሶማሊያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት የሚጥስ ነው " ብሏል።
ሶማሊላንድ የሶማሊያ አንድ አካል መሆኗን የጠቀሰው መግለጫው ማንኛውም ከፌዴራል መንግሥቱ እውቅና ውጭ የሚደረግ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዓለም አቀፍ ሕግንና የተባበሩት መንግሥታትን ቻርተር የሚጥስ መሆኑን ገልጿል።
የተባበሩት መንግሥታት ፣ የአፍሪካ ሕብረት ፣ የአረብ ሊግ እና የኢስላማዊ ትብብር ድርጅት (OIC) እስራኤል ውሳኔዋን እንድትቀለብስ ግፊት እንዲያደርጉና የሶማሊያን አንድነት እንዲያስከብሩ ጥሪ አቅርቧል።
የሶማሊያ መንግስት የሀገሪቱን አንድነትና ሉዓላዊ መብቶች ለማስከበር ማንኛውም ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ሕጋዊ መንገዶችን እንደሚጠቀም አረጋግጧል።
#primenews
ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ/ም

#ኢትዮጵያ🇪🇹
100 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚገኝበት የአሰላ ንፋስ ኃይል ማመንጫ እውን መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳወቁ።
" ኢትዮጵያ ነፋስን እንዴት መጠቀም እና ወደ ኃይል መቀየር እንደምትችል ታውቅበታለች " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) " ቀድሞ የመድረስ ምንዳ፣ የአዳማ፣ አሸጎዳ እና የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ለዚህ ህያው ምስክር ናቸው " ብለዋል።
" ሀገር በኃይል አማራጭ የሚገባትን እስክታገኝ ስራችን ስለማይቆም ፤ ዛሬ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን እውን አድርገን ሌላኛውን ለማስቀጠል በልዩ ዝግጅት ተነስተናል " ሲሉ ገልጸዋል።
ስለአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ምን ይታወቃል ?
- ለአምስት አመታት ሲገነባ ቆይቷል።
- ኃይል ማመንጫው አንድ መቶ ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ይገኝበታል።
- የንፋስ ኃይል ማመምጫው የኢትዮጵያ እና የዴንማርክ መንግሥታት አጋር ሆነው የሰሩበት ፕሮጀክት ነው።
- የትርባኖቹ ማማ ቁመት ከከዚህ ቀደምቶቹ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች የላቀ ነው፤ 84 ሜትር ይረዝማል። የእያንዳንዱ ተርባይን የማመንጨት አቅምም ይለያል ፤ 29 ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 3.46 ሜጋዋት ኃይል ያመነጫሉ።
- ማመንጫው የንፋስ ኃይል ቴክኖሎጂ የደረሰበት የመጨረሻው ቴክኖሎጂ ታጥቋል።
- አሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ተቋራጭ የተገነባና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቆጣጣሪነት የተሰራ ነው።

በአሜሪካ ኢራን አዲስ ዙር ድርድር ዙሪያ ለመምከር በፓኪስታን ከፍተኛ የጦር አዛዦች የተመራ ቡድን ወደ ኢራን አቀና
በኢራንና አሜሪካ መካከል ይደረጋል የተባለው አዲስ ዙር ውይይት ተስፉ ሰጪ ስለመሆኑ የነጩ ቤተመንግስት ቃል አቀባይ ገልፀዋል።
ኢራን በበኩሏ መጪው ድርድር በፓኪስታን መዲና ኢስላማባድ ሊደረግ ይችላል ብላለች።
የኢራን ጦር አሜሪካ በኢራን ወደቦች ላይ እገዳዋን ከቀጠለች የቀይ ባህርን፣ የገልፍ እንቅስቃሴን እንደሚያግድ አስጠንቅቋል።