Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
417 subscribers
590 photos
6 videos
51 files
34 links
Banking & FInance, Stock market, forex, Fintec and e-commerce
Download Telegram
Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
Photo
ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛው በተጨማሪ የውጪ ምንዛሪ ጨረታ 500 ሚሊዮን ዶላር አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ግቦቹን ለማሳካትና በገበያው ውስጥ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ለማርካት የሚውል የ500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከመደበኛው የየሁለት ሳምንት ጨረታ በተጨማሪ ልዩ የጨረታ ሽያጭ ነገ ቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

ይህ ከፍተኛ የሆነው የውጭ ምንዛሬ ሽያጭ፣ ባንኩ ተግባራዊ እያደረገ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ሥርዓትን ለመደገፍና የጥሬ ገንዘብ የገበያ ውስጥ ዝውውርን ለመቆጣጠር ከሚጠቀምባቸው ስልቶች አንዱ ነው።

በቅርቡ በተደረጉ የውጭ ምንዛሬ ጨረታዎች ላይ ከፍተኛ የባንኮች ፍላጎት የታየ ሲሆን፣ ገበያውም ተወዳዳሪ እየሆነ መምጣቱ ይነገራል።

ይህ የ500 ሚሊዮን ዶላር የገበያ ጣልቃ ገብነት፣ በግል ዘርፉ ለሚታየው የውጭ ምንዛሬ ከፍተኛ ፍላጎት ትልቅ እፎይታን እንደሚሰጥና የብርን የመግዛት አቅም ለማረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።

ባንኩ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም የ500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከመደበኛው በተጨማሪ ልዩ የጨረታ ሽያጭ ማካሄዱ እና የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ 154.81 ብር መድረሱ ይታወቃል።
ባንኩ ባሳለፍነው ማክሰኞ 31 ባንኮች በተሳተፉበት የመደበኛ ልዩ ጨረታ 70 ሚሊየን ዶላር ለ21 ባንኮች መሸጡ የሚታወስ ነው፡፡
2
Best images about life...!
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ብሔራዊ ባንክ የRTGS የሥራ ሰዓት እንዲራዘም ወሰነ።

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሀገሪቱ ባንኮች መካከል የሚደረገውን ፈጣን የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት (RTGS) የሥራ ሰዓት እንዲራዘም መወሰኑን ለሁሉም የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል።

በዚህም አሁን ላይ በሳምንት 6 ቀን በቀን 9 ሰዓት ይሰራ የነበረው ሥርዓት በቀን ለሁለት ተጨማሪ ሰዓታት እንዲራዘም በማድረግ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንዲሰጥ ተወስኗል።

ከፊታችን መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ የብሔራዊ ባንክ ውሳኔ የዘርፉ ተዋናዮች በተራዘመው ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ወደ ባንኮች የሚገቡና የሚወጡ የገንዘብ ዝውውሮችን ያለምንም መስተጓጎል እንዲያከናወኑ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ/ም

Via @tikvahethmagazine