Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
417 subscribers
590 photos
6 videos
51 files
34 links
Banking & FInance, Stock market, forex, Fintec and e-commerce
Download Telegram
The National Bank of Ethiopia has issued Directive No. SBB/95/2025 – Risk-Based Capital Adequacy Requirements for Banks, introducing updated regulatory provisions in line with ongoing financial sector reforms.

The Directive aims to strengthen regulatory clarity, enhance sound banking practices, and support a stable, efficient, and inclusive financial system.

Explore the key highlights in the explainer graphics and read the full Directive at nbe.gov.et/directive.

@PatternFin
CBE Launches Direct Agricultural Loans for Smallholder Farmers

CBE has launched a new loan product specifically designed for smallholder farmers and pastoralists. The service, announced at an event attended by State Minister of Agriculture, Meles Mekonnen (PhD) and other officials, marks a direct effort to increase formal credit access for individual farmers and herding groups.

Unlike the bank's existing agricultural loans, this new product targets the needs of small-scale producers. CBE's Corporate Services Executive Vice President, Ephrem Mekuria, stated the loans will support a range of activities including crop and vegetable production, animal husbandry, fertilizers, dairy farming, and the purchase of machinery.

Farmers who own agricultural land, are organized in groups, have been with the bank for 6 months or more, and are engaged in crop cultivation, vegetables and fruits, milk and milk products, and livestock development will benefit from the service. #EBR

@PatternFin
1
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአየር መንገድ ሠራተኞች ቤት ግንባታ የሚውል የ27.8 ቢሊዮን ብር የብድር ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል የ27.8 ቢሊዮን ብር የብድር ስምምነት ማድረጉ ተገልጿል።

ይህ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል የተደረገው ስምምነት፤ የአየር መንገዱን ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና አስፈላጊውን የፋይናንስ አቅርቦት ለማመቻቸት ያለመ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ተወካይ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እንደገለጹት፤
ባለፈው ዓመት ባንኩ ካቀረበው 458 ቢሊዮን ብር ብድር ውስጥ 88 በመቶው ለግል ዘርፉ ተሰጥቷል፤ ይህም ባንኩ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች የሚሰጠውን ትኩረት እንደሚያሳይ ተገልጸዋል። አሁን የተደረገው ስምምነትም የሀገሪቱን ግዙፍ ልማቶች ለማሳለጥ የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው አክለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ አየር መንገዱ የሠራተኞቹን የቤት ችግር ለመፍታት ቀደም ሲል 1 ሺህ 200 ቤቶችን አስገንብቶ ማስተላለፉን አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅትም ለተጨማሪ 5 ሺህ ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ይህ ሰፊ የግንባታ ሂደት ከፍተኛ ፋይናንስ የሚጠይቅ በመሆኑ፤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የተደረገው የብድር ስምምነት ለግንባታው መሳካትና መጠናቀቅ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት አቶ መስፍን ገልጸዋል።
#Capital
3👍1
CBE Deposits Surpass Two Trillion Birr as Half-Year Mobilization Tops Birr 325 Billion

The Commercial Bank of Ethiopia (CBE) said its total deposits have surpassed two trillion birr, after mobilizing more than 325 billion birr in the first half of the 2025/26 fiscal year.

In a statement, CBE said the performance was presented during an internal half-year performance review attended by senior management.
Imagine building a $30 billion empire that touches 1 billion lives with just ~30 elite engineers, no offices, no HR drama, and pure relentless focus.

Pavel Durov proves it: Less isn't limitation, it's superpower. Automation over armies. Vision over bureaucracy. Freedom over fences.

In 2026, build lean. Think bold. Execute fearless.

The future belongs to the efficient.
3
#Carrefour

Carrefour announces a franchise and supply Partnership with Queens Supermarket PLC, a subsidiary of Midroc Investment Group, for the roll-out of Carrefour banners, expertise and products in Ethiopia.

Under this agreement, will support Midroc teams in the transformation of the entire stores network under Carrefour banners, and in the implementation of an ambitious expansion plan. The first stores will be rebranded by first half of 2026.

This new agreement illustrates the strength and dynamism of the franchise model championed by the Carrefour Group, and marks the achievement of our objective to expand in 10 new countries under franchise as part of our Carrefour 2026 strategic plan.

“We are delighted to initiate this collaboration with a leading retail player in Ethiopia. Beyond the rapid transformation of the 13 existing stores, the Midroc and Carrefour International Partnership teams are already working hand-in-hand on the future growth of our activities in the country: by 2028, we project the opening of 17 additional stores. This launch in Ethiopia is another milestone in the execution of our international franchise expansion strategy, which already saw us pass the 3,000 franchised store mark in October 2025.”, declares Patrick Lasfargues, CEO of Carrefour International Partnership.

"I am very proud to announce, along with the entire Midroc team, our integration into Carrefour's international franchise network. By leveraging our deep knowledge of the local Ethiopian market, the dedication of the Midroc teams, and Carrefour's excellence, we will be able to offer Ethiopian consumers high-quality, affordable products and an experience that perfectly meets their expectations.”, declares Jemal Ahmed, CEO of Midroc Investment Group.
2
#ኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ በግማሽ ዓመቱ ከዘጠኝ ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት በዲጂታል አማራጮች ማከናወኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በዲጂታል የባንክ አገልግሎቶቹ በኩል ከዘጠኝ ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን አስታወቀ።

ይህም በባንኩ በኩል ከተከናወኑ ጠቅላላ ዝውውሮች እና ክፍያዎች 88 በመቶ ገደማ ድርሻ ይይዛል ተብሏል።

ይህ ውጤት ይፋ የተደረገው ባንኩ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት ሲሆን፣ የስትራቴጂክ ዕቅድ እና ትራንስፎርሜሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ወጋየሁ ገብረማርያም የባንኩን የስድስት ወራት ሪፖርት አቅርበዋል።

እንደ አቶ ወጋየሁ ገለጻ፣ በተያዘው ወቅት በዲጂታል መሠረተ-ልማቶች ከዘጠኝ ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት የተከናወነ ሲሆን፣ ይህም ከጠቅላላ የባንክ ግብይቱ 87.9 በመቶ ድርሻ አለው ብለዋል።

በባለፈው በጀት ዓመት ባንኩ በሀገሪቱ የዲጂታል ግብይት እና ክፍያ ውስጥ 73 በመቶ ድርሻ እንደነበረው የጠቀሱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ በዚህ ዓመትም ባንኩ በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ዘርፍ ያለውን የበላይነት እንደሚያስቀጥል አመልክተዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ ይህ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ እና ይህም የደንበኞችን ተደራሽነትና የባንኩን የሥራ ቅልጥፍና በማሻሻሉ እንደሆነ ተናግረዋል።

በተያያዘም፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግማሽ ዓመቱ 36.19 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።

#AddisStandard
Forwarded from Anbesa Bank
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንደ አንበሳ ባንክ አንበሳ በበላይነቱ፣ በግርማ ሞገሱ፣ በግሳቱ ብቻ ተወስኖ ይገለጻል የሚል ዕምነት የለንም በድፍረቱ፣ በጥንካሬው፣ በክብሩ ጭምር እንጂ፡፡ በሕይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት የጭረት ያክል ብልጭታ ለመፍጠር ድፍረቱ ያለው ሁሉ ለእኛ አንባሳ ነው፡፡

ይህ ዕምነት በአርማችን ውስጥ ይኖራል፡፡

እንደ አንበሳ ባንክ ከምቾት ይልቅ ትጋትን፣ ከፍርሃት ይልቅ መራመድን፣ ከማመንታት ይልቅ መጀመርን ከመረጡት ጎን እንቆማለን፡፡

ምክንያቱም ለውጥ ከፍጹምነት አይጀመርም ከውሳኔ እንጂ፡፡

እንጀምረው!

At Anbessa Bank, we believe a lion is not defined by noise or dominance. A lion is anyone who finds the courage to spark something new in their life.

This belief lives inside our logo.

At Anbessa Bank, we stand with those who choose courage over comfort, movement over fear, and beginnings over hesitation.

Because progress doesn’t start with perfection. It starts with a decision.

LET’S GO FOR IT.

ቪዲዮውን እንዲመለከቱ በአክብሮት እንጋብዛለን

#anbesabank #brandmainfesto #newlogo
👏1🙏1
በተመረጡ የገቢ ዕቃዎች ላይ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አመላካች ዋጋዎችን አጠቃቀም በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ
የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ ስለመደረጉ የተሰጠ መግለጫ
👍2
የዳታ ጥበቃና የግለኝነት መብት ነገር...

ትላንት ከወዳጆቼ ጋር መጪውን የጾም ወር ለመቀበል ምሳ ለመብላት ቀጠሮ ያዝን። የተቀጣጠርንበት ቤት የፍየል ስጋ የሚሸጥበት ሬስቶራንት ነው።

የሆድ የሆዳችንን እያወራን ምሳችንን ከበላን በኋላ ቢል ቀረበልን። ምሳ ጋባዥ ተረኛው እኔ በመሆኔ ከTelebirr ሒሳቤ ወደ XXX ባንክ ቢል ከፈዬ ተያይዘን ከሬስቶራንቱ ተያይዘን ወጣን።

ይሁንና ከደቂቃዎች በኋላ ከጓደኞቼ ጋር ቡና እየጠጣን ከአንድ አንጋፋ ባንክ ስልክ ተደወለልኝ።

"አቶ ጥላሁን?!"

"አዎ ነኝ"

"ከXXX ባንክ፣ yyy ቅርንጫፍ ነው የምንደውልልህ። የቅርንጫፋችን ደንበኛ ከሆነው ZZZ ሬስቶራንት ምሳ በልተው ሒሳብ ሲከፍሉ በስህተት ሳይከፍሉት የቀረ ሒሳብ እንዳለ ነግረውን እንዲከፍሏቸው ለመጠየቅ ነው የደወልነው"

"What?! እኔ ሒሳብ የከፈልኩት በቴሌብር ነው በምን መንገድ ነው ስልኬን ያገኛችሁት?! በደንበኞች ግብይት ውስጥ ባንኩ ጣልቃ የመግባት መብት አለው? እንዴት የግለኝነት መብቴን ጥሳችሁ ከፈቃዴ ውጪ ሒሳቤን በርብራችሁ ልትደውሉልኝ ቻላችሁ? ዛሬ ላይ ሒሳብ አልከፈለም ብላችሁ መረጃዬን አውጥታችሁ ከደወላችሁ ነገ ለሽፍታ ሰጥታችሁ እንደማታስፍኑኝና እንደማታስዘርፉኝ ምን ማረጋገጫ አለኝ?" (በነገራችን እኔም የእዚሁ ቅርንጫፍ ደንበኛ ነኝ)

ከደወለልኝ የባንክ ሰራተኛ በቂ ምላሽ አላገኘሁም። ጭራሽ ደንበኛቸው በሌላ ጊዜ ተመሳሳይ ሲገጥማቸው በእዚህ መንገድ እንደሚረዷቸው ነገረኝ፣ የሰማሁትን ለማመን አልቻልኩም።

"የሬስቶራንቱ ሥራ አስኪያጅ አጠገባችን ናቸው። ፈቃደኛ ከሆኑ ያናግሯቸው"

የሬስቶራንቱን ሥራ አስኪያጅ በስልክ አወራኋቸው ችግሩ የእኔ እንዳልሆነና የአስተናጋጇ እንደነበረ፣ ሳይከፈል የቀረ ቢል እንዳለ አስረዱኝ። ከእሳቸው ጋር ጉንጭ መላፋት ስላልፈለግኩ ቀረ የተባለውን ሒሳብ ከፈልኩ። ተመሳሳይ ችግር ሲፈጠር እንዴት ሊፈታ እንደሚችል ሂደቱን ባላውቅም በጭራሽ ከፈቃዴ ውጪ ከባንክ ሊደወልልኝ እንደማይገባ ግን ጠንቅቄ አውቃለሁ።

በመቀጠል ያደረግሁት ነገር ባንኩ ለደንበኞች አስተያየት ወደ ከፈተው ነጻ የስልክ መስመር መደወል ነበር። ስልኩን ያነሳው ኦፊሰር ጉዳዬን በጥሞና ከሰማ በኋላ "ከቴሌ ብር የከፈሉትን ሒሳብ በምን መንገድ ስልክዎን ሊያገኝ ቻለ?!" ሲል ጠየቀኝ። "ያ የእኔም ጥያቄ ነው" ስል መለስኩ።

"ይህ ጉዳይ በጣም serious ስለሆነ ወደ በላይ አለቃ ላስተላልፍዎ" ሲል ከአለቃው ጋር አገናኘኝ። እኔም ከላይ የጻፍኩትን ኩነት በሙሉ አብራራሁ። አለቃው ክሴን በሙሉ መስማታቸውንና ማቀረጹን በቅርቡም አስፈላጊውን ምርመራ አድርገው እንደሚደውሉልኝ ቃል ገብተውልኝ ተለያየን። (በነገራችን ላይ ባንኩ በሚወስደው እርምጃ ካልረካሁ ሁነኛ ጠበቃ ፈልጌ በግለኝነት መብቴ ላይ ባደረሰብኝ ጥቃት ክስ የምመሰርት ይሆናል)

ደንበኛ ለባንክ ምስጢሩን የሚሰጠው ከገንዘብ እኩል እንደውም በላይ የግለኝነት ምስጢሬን ይጠብቅልኛል ብሎ በማመን ነው። ባንኮች ለፍርድ ቤት እና ሌሎች ስልጣን ከተሰጣቸው አካላት ውጪ የደንበኛ ምስጢር ለሥጋ ቤት አሳልፈው ይሰጣሉ ተብሎ አይታሰብም። ይሄንን ለማወቅ የባንክ ሰራተኛ ሳይሆን ሰው መሆን በቂ ነው።

ባንኮች ለሰራተኞቻችሁ ተገቢውን ስልጠና ብትሰጡ ከተመሳሳይ ችግርና የደንበኛ ትምምን እጦት እራሳችሁን ትጠብቃላችሁ ብዬ ጽሁፌን እደመድማለሁ።

መልካም ቀን
(Tilahun Girma)
👍4
Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
Photo
ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛው በተጨማሪ የውጪ ምንዛሪ ጨረታ 500 ሚሊዮን ዶላር አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ግቦቹን ለማሳካትና በገበያው ውስጥ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ለማርካት የሚውል የ500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከመደበኛው የየሁለት ሳምንት ጨረታ በተጨማሪ ልዩ የጨረታ ሽያጭ ነገ ቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

ይህ ከፍተኛ የሆነው የውጭ ምንዛሬ ሽያጭ፣ ባንኩ ተግባራዊ እያደረገ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ሥርዓትን ለመደገፍና የጥሬ ገንዘብ የገበያ ውስጥ ዝውውርን ለመቆጣጠር ከሚጠቀምባቸው ስልቶች አንዱ ነው።

በቅርቡ በተደረጉ የውጭ ምንዛሬ ጨረታዎች ላይ ከፍተኛ የባንኮች ፍላጎት የታየ ሲሆን፣ ገበያውም ተወዳዳሪ እየሆነ መምጣቱ ይነገራል።

ይህ የ500 ሚሊዮን ዶላር የገበያ ጣልቃ ገብነት፣ በግል ዘርፉ ለሚታየው የውጭ ምንዛሬ ከፍተኛ ፍላጎት ትልቅ እፎይታን እንደሚሰጥና የብርን የመግዛት አቅም ለማረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።

ባንኩ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም የ500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከመደበኛው በተጨማሪ ልዩ የጨረታ ሽያጭ ማካሄዱ እና የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ 154.81 ብር መድረሱ ይታወቃል።
ባንኩ ባሳለፍነው ማክሰኞ 31 ባንኮች በተሳተፉበት የመደበኛ ልዩ ጨረታ 70 ሚሊየን ዶላር ለ21 ባንኮች መሸጡ የሚታወስ ነው፡፡
2