Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
416 subscribers
590 photos
6 videos
51 files
34 links
Banking & FInance, Stock market, forex, Fintec and e-commerce
Download Telegram
#NBE

📌የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ መመሪያ አውጥቷል።

በመመሪያው መሠረት...

📌ከገቢ ንግድ ጋር በተያያዘ በቅድመ ክፍያ /Advance payment/ ያለ ባንክ ጋራንቲ ወደ ውጭ ሀገር የሚላከውን የገንዘብ መጠን ከ5,000 ዶላር ወደ 50,000 ዶላር ከፍ አድርጓል።

📌 ለግል ተጓዦች የሚፈቀደውን ጥሬ ዶላር ከ5,000 ወደ 10,000፣ እንዲሁም ለንግድ ተጓዦች የሚፈቀደውን ዶላር ከ10,000 ወደ 15,000 ከፍ አድርጓል።

📌ባንኮች ከገቢ ንግድ /Import trade/ጋር፣ ከአገልግሎት ክፍያ /invisible payments/ ወይም ከጥሬ ገንዘብ /Cash fcy sales/ ጋር የተያያዘ የሚያስከፍሏችውን ማናቸውም አስተዳደራዊ ወጪዎችና ክፍያዎች ከግንቦት 18፣ 2017 ጀምሮ ከ4% እንዳይበልጡ ተወስኗል።
________
የመመሪያው እንድምታ (የግል አስተያየት)፣

📌 መመሪያው ለረጅም ዘመን በ5,000 ዶላር ተወስኖ የቆየውን የቅድመ ክፍያ ዘዴ /Advance payment mode of payment/ ወደ 50,000 ዶላር ማሳደጉ የገቢ ንግድ በፍጥነት እንዲሳለጥ በማድረግ በሌሎች ውስብስብ የክፍያ ስርዐቶች /ለምሳሌ መተማመኛ ሰነድ/LC/ ምክንያት የሚፈጠረውን የንግድ መዘግየት እና ገበያ ላይ የሚፈጠረውን የሸቀጥ እጥረት ያስወግዳል።

📌 ባንኮች የገቢ ንግድ ላይ የሚያስከፍሉትን የተጋነነ የአገልግሎት ክፍያ 4% ላይ መገደቡ ከገቢ ንግድ ጋር የተያያዙ የዋጋ ንረቶች /imported inflation/ ለመቀነስ እና ግልጽነትን ለመፍጠር ይረዳል።

📌 ለግል ጉዳይም ሆነ ለሥራ ጉዳይ የሚጓዙ ግለሰቦች የገንዘብ እጥረት እንዳይገጥማቸው ይረዳል።

(Tilahun Girma)

@PatternFin
#NBE

💵 The National Bank of Ethiopia (NBE) has Increased the upfront foreign exchange payment limit for importers to $50,000 per transaction, up from $5,000.

💵 NBE also permits cash FX purchases up to $10,000 for personal travelers and $15,000 for business travelers.

💵 Individuals with foreign exchange accounts can now use 20% of their FX balance via debit cards, an increase from the previous 10%.

💵 Effective May 26, banks are advised to charge a maximum fee of 4% for purchasing foreign exchange for imports, service payments, or cash note purchases.

💵 starting June 2025, Banks will regularly disclose FX-related fees on the central bank’s website.

@PatternFin
👍1
🌟 Thank You! 🌟

If you enjoy our content, please share our channel with friends who might find it helpful! Your support helps us grow.

👉 @PatternFin

Thank you!
Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ pinned «🌟 Thank You! 🌟 If you enjoy our content, please share our channel with friends who might find it helpful! Your support helps us grow. 👉 @PatternFin Thank you!»
Mastering Trade Finance: How a Letter of Credit (L/C) Works in International Trade
@PatternFin
👍1
Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
Mastering Trade Finance: How a Letter of Credit (L/C) Works in International Trade @PatternFin
Mastering Trade Finance: How a Letter of Credit (L/C) Works in International Trade

In the world of global trade, managing risk between buyers and sellers is crucial.

One of the most reliable tools to secure international transactions is the Letter of Credit (#L/C).

What is a Letter of Credit

A Letter of Credit is a financial guarantee issued by a bank ensuring that a seller will receive payment once the agreed documents are properly submitted and verified.

🦺 It protects both sides: the #seller is sure of payment, and the #buyer ensures goods are shipped under contract terms.

🛄Here’s a simple breakdown of how it works:

1️⃣. Buyer and Seller sign a Sales Agreement with L/C terms.

2️⃣. Buyer applies to their Issuing Bank for a Letter of Credit.

3️⃣. Issuing Bank issues the L/C and sends it to the Advising Bank.

4️⃣. Advising Bank notifies the Seller.

5️⃣. Seller ships the goods.

6️⃣. Seller presents all required shipping documents.

7️⃣. Banks verify documents match the contract.

8️⃣. Seller is paid by the bank.

9️⃣. Buyer uses the documents to claim the goods.

📊Why Letters of Credit matter:

📌Risk Mitigation: Payment is assured upon document compliance.

📌Secure Financing: Sellers can access working capital faster.

📌 International Trust: Makes it easier to trade across borders with unknown counterparties.

@PatternFin
👍1
Foreign Exchange (Amendment) Directive No. FXD/03/2025

@PatternFin
May 21, 2025 FX New Measures Breakdown.pdf
1.6 MB
Brief breakdown of the new NBE measures released yesterday.

#NBE #Forex #FCY

@PatternFin
👍1
𝗡𝗕𝗘 𝘁𝗼 𝗖𝗼𝗻𝗱𝘂𝗰𝘁 𝗨𝗦𝗗𝟱𝟬 𝗠𝗶𝗹𝗹𝗶𝗼𝗻 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗔𝘂𝗰𝘁𝗶𝗼𝗻 𝗮𝘀 𝗣𝗮𝗿𝘁 𝗼𝗳 𝗕𝗶-𝗪𝗲𝗲𝗸𝗹𝘆 𝗠𝗮𝗿𝗸𝗲𝘁 𝗦𝘁𝗮𝗯𝗶𝗹𝗶𝘇𝗮𝘁𝗶𝗼𝗻

The National Bank of Ethiopia (NBE) has announced it will conduct its sixth bi-weekly foreign exchange auction on Thursday, May 22, 2025, as part of its broader effort to stabilize the forex market and uphold price and external stability.

The central bank is offering USD 50 million to commercial banks, reinforcing its ongoing shift toward a market-based exchange rate system.

@PatternFin
Macroeconomic Performance Numbers in the Past 9 Months.pdf
9.3 MB
Ethiopian Key Macroeconomic Performance Numbers in the Past 9 Months

ባለፉት 9 ወራቶች ውስጥ የኢትዮጵያ ቁልፍ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ቁጥሮች

#PragmaInsights

@PatternFin
FOREIGN EXCHANGE AUCTION NO. 6 ANNOUNCEMENT OF RESULTS

#NBE
ወደ ኢትዮጵያ ይዞ መግባት የሚቻለው የውጭ ምንዛሪ መጠን ምን ያህል ነው ?
Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
ወደ ኢትዮጵያ ይዞ መግባት የሚቻለው የውጭ ምንዛሪ መጠን ምን ያህል ነው ?
ወደ ኢትዮጵያ ይዞ መግባት የሚቻለው የውጭ ምንዛሪ መጠን ምን ያህል ነው ?

ወደ ኢትዮጵያ ይዞ መግባትና ከኢትዮጵያ ይዞ መውጣት ስለሚቻለው የገንዘብ መጠን በተመለከተ የብሔራዊ ባንክ ባለፈው አመት መመሪያ አውጥቷል፡፡

ይኸው መመሪያ ነዋሪነቱ በኢትዮጵያ የሆነ አንድ ሰው ከውጭ ሀገራት መልስ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የውጭ ምንዛሪ ይዞ ከገባ በ30 ቀናት ውስጥ በንግድ ባንኮች ወይም በተፈቀደላቸው የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ወደ ብር መቀየር አለበት ወይም ወደ ውጭ ምንዛሪ ባንክ ሒሳቡ ማስገባት ይኖርበታል ይላል፡፡ ከውጭ ያስገባው የገንዘብ መጠን ከ4ሺህ ዶላር በላይ ከሆነ ግን ወደ ባንክ ሒሳቡ ሲያስገባው ለጉምሩክ ማሳወቅ እንዳለበት መመሪያው ይደነግጋል፡፡

ሁለተኛ የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከ90 ቀናት በላይ በኢትዮጵያ ለመቆየት ከፈለገ ከውጭ ይዞት የገባውን የውጭ ምንዛሪ በ 90 ቀናት ውስጥ ወደ ውጭ ምንዛሪ የባንክ ሒሳቡ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡ ይዞት የገባው የገንዘብ መጠን ከ 10 ሺህ ዶላር በላይ ከሆነ ግን፣ ወደ ብር ሲቀይረው አለያም ወደ ባንክ ሒሳቡ ሲያስገባው ለጉምሩክ ማሳወቅ/ማስመዝገብ አለበት ይላል መመሪያው፡፡

የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ የውጭ ዜጋ የውጭ ምንዛሪውን የቪዛ ጊዜው እስኪያልቅ ድረስ መያዝ ይችላል፡፡

ስለ ጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየት የሰጡ የባንክ ባለሙያ ፥ አንድ ሰው ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ለጉምሩክ ማሳወቅ/ማስመዝገብ  ከሚጠበቅበት መጠን በታች የሆነ የውጭ ምንዛሪ ከያዘ በጉምሩክ እንዲያስመዘግብ አይገደድም ብለዋል፡፡

ለምሳሌ ከ10 ሺህ ዶላር በታች ይዞ የሚገባ ሰው ሳያስመዘግብ ወይም ማሳወቅ ሳያስፈልገው በቀጥታ ይዞት መግባት ይችላል ማለት ነው፡፡ ከ10 ሺህ ዶላር በላይ ከሆነ አሳውቅ የሚባለው አንደኛ ወደ ጥቁር ገበያው ወስደህ እንዳትሸጠው ነው ፤ ሁለተኛ ለምን አላማ ከ10 ሺህ ዶላር በላይ ይዘህ እንደገባህ መግለፅ አለብህ ይላሉ ባለሙያው፡፡ ለንግድ ከሆነም በአግባቡ ማሳወቅ ይጠበቅብሀል፡፡

ሆኖም መመሪያው ከ10 ሺህ ዶላር በላይ ከሆነ አስመዝግብ ቢልም ከዛም በታች ከሆነ ማስመዝገቡ እንደሚመረጥ ገልጸዋል። ሳታሳውቅ ያስገባኸውን ዶላር፣ ስትመለስ ይዘህ መውጣት አትችልም፡፡

ቀደም ሲል ከአንድ ዶላር ጀምሮ ተመዝግቦ ይግባ የሚል አሰራር ነበር አሁን እንደዛ ባይባልም በተለይም የተረፈህን ይዘህ ስትወጣ ችግር ላይ ላለመውደቅ ከጅምሩ አስመዝግበህ መግባቱ ይመረጣል ባይ ናቸው፡፡

ለምን ቢባል ከውጭ ይዞት ከመጣው የዶላር መጠን ያልተጠቀመበት ካለና እሱን ይዤ ልውጣ ቢል ችግር ይገጥመዋል፡፡ የራሴን ዶላር የተረፈኝን ነው ይዤ የምወጣው ቢል ማስረጃ አቅርብ ስትገባ አሳውቀሀል ወይ ? ይባላል፡፡ ከኢትዮጵያ በጥቁር ገበያ ገዝቶ የያዘውስ ቢሆን ምን ማረጋገጫ አለ ሊባል ይችላል፡፡ ስለዚህ የቀረውን ገንዘብ በዶላር ይዞ ለመውጣት ይቸገራል ብለዋል ባለሙያው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ እንደዛ ቢልም የመነሻው ሀገር ራሱ ይህን ያህል ገንዘብ በካሽ ይዞ እንዲወጣ ላይፈቅድለት ይችላል ሲሉም ገልፀዋል፡፡ ለምን በባንክ አታስተላልፍም ይባላል፡፡ በባንክ የምታዘዋውርም ከሆነ ለምን ምክንያት እንደሆነ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት ወይም ለሌላ አላማ ስለመሆኑ መገለፅ አለበት እንደሚባል አስገንዝበዋል፡፡ በተለይም በአውሮፓና በአሜሪካ ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚደረግበት ይናገራሉ ባለሙያው፡፡ ህጋዊ ስለመሆኑ ግብር የተከፈለበት ስለመሆኑና ለህጋዊ አገልግሎት እንደሚወጣ አሳውቆ ነው መውጣት ያለበት ባይ ናቸው፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ


@PatternFin
👍21
ማዕከላዊ ባንክ ባንኮች የማገገሚያ እቅድ እንዲያዘጋጁ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ አወጣ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ከባድ የገንዘብ ችግር ሲያጋጥማቸው ራሳቸውን እንዲያገግሙ የሚያስችል ዝርዝር እቅድ እንዲያዘጋጁ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ ቁጥር SBB/93/2025 አውጥቷል። ይህ መመሪያ የባንኮችን የገንዘብ መረጋጋት ለማረጋገጥ እና ቀውስ ከመከሰቱ በፊት ዝግጁ እንዲሆኑ ለመርዳት ያለመ ነው።

በአዲሱ መመሪያ መሰረት፣ ሁሉም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ባንኮች አጠቃላይ እና አስተማማኝ የማገገሚያ እቅድ ማዘጋጀት አለባቸው። ይህ እቅድ አስፈጻሚ ማጠቃለያ፣ ስትራቴጂካዊና የአመራር ትንተና፣ የማገገሚያ አማራጮችን፣ የአሰራር የአደጋ ጊዜ እቅድ እንዲሁም የግንኙነትና ይፋ የማድረግ እቅድን ማካተት ይኖርበታል።

የብሔራዊ ባንክ ዋና ዓላማ ባንኮች የገንዘብ ቀውስ ሲገጥማቸው ከብሔራዊ ባንክ ወይም ከመንግስት ልዩ ድጋፍ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው የማገገም አቅም እንዲኖራቸው ማስቻል መሆኑን ገልጿል።

ካፒታል ከመመሪያው እንደተመለከተው ፣ ባንኮች በቂ እና የተለያዩ የማገገሚያ አማራጮችን ማካተት አለባቸው። እነዚህ አማራጮች የካፒታል እና  ስጋትን መቀነስ፣ በቂና የተለያየ የገንዘብ ምንጮችን ማግኘት፣ እንዲሁም እዳዎችን እንደገና ማዋቀርን የመሳሰሉ እርምጃዎችን ያካትታሉ። #Capital

@PatternFin
Recovery-Plan-of-Banks-Directive-SBB932025.pdf
5.8 MB
ብሔራዊ ባንክ ያወጣውን የማገገሚያ እቅድ መመሪያ ቁጥር SBB/93/2025

@PatternFin
👍1
📌CBE exchange rate

May 23... $1 = 124 ETB

May 24 ... $1 = 128 ETB

⬆️4 Birr in 24 hours!

@PatternFin