Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
416 subscribers
590 photos
6 videos
51 files
34 links
Banking & FInance, Stock market, forex, Fintec and e-commerce
Download Telegram
ወጋገን ባንክ ከቪዛ ጋር የአጋርነት እና ለደንበኞቹ
የኢ-ኮሜርስ የክፍያ ስርዓት (CyberSource) መተግበር የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡


ወጋገን ባንክ ከቪዛ ጋር ለደንበኞቹ የኢ-ኮሜርስ (የበይነ መረብ ግብይት) አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ስምምነት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተፈራረመ፡፡

በወጋገን ባንክ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት አቶ ሰለሞን ተስፋዬ የባንኩ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሲሆኑ በቪዛ በኩል ደግሞ ሚስተር ሚካኤል በርነር የቪዛ የደቡብ እና ምስራቅ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝ ዳንት ናቸው።

ባንኩ ከቪዛ ጋር የተፈራረመው ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የባንኩ ደንበኛ የሆኑ የንግድና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ከቪዛ የኢ-ኮሜርስ የክፍያ ስርዓት (CyberSource) ጋር በማስተሳሰር ከየትኛውም የዓለም ክፍል የኢ-ኮሜርስ (በይነ መረብ) ግብይት መፈፀም እንደሚያስችላቸው ታውቋል፡፡

በተጨማሪም በውጪ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች በዚሁ ዓለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ተጠቅመው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ከየትኛውም የዓለም ክፍል ደህንነነቱ በተጠበቀ መንገድ ገንዘብ በሀዋላ መላክ እንደሚችሉ ተገልጿል።

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ወጋገን ባንክ ዓለም አቀፍ የክፍያ ስርዓትን ከማሳለጥ በተጨማሪ ከቪዛ ጋር ያለውን አጋርነት የበለጠ በማጠናከር ለደንበኞቹ ደህንነቱ የተጠበቀ የኢ-ኮሜርስ (በይነ መረብ) ግብይት እና የሀዋላ አገልግሎት ማስፋፋት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

#WegagenBank #WegagenCapital

@PatternFin
የአፍሪካ ልማት ባንክ 40 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ዋስትና ለዳሽን ባንክ ሰጠ

የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያን ንግድ ለማሳደግ ዳሸን ባንክን የሚያግዝ የ40 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ዋስትና ስምምነት ተፈራርሟል።

ይህ የዋስትና መስጫ ዳሸን ባንክ የማስመጣት እና የመላክ ንግድ ፋይናንስ ፍላጎቶችን እንዲያመቻች በማስቻል የባንኩን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ወሳኝ ዘርፎች የመደገፍ አቅም ያሳድጋል።

እንዲሁም የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) አጀንዳን በመደገፍ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ንግድ ያበረታታል ተብሏል።

የአፍዴብ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሊአንድሬ ባሶል ይህ ታሪካዊ ግብይት ዳሸን ባንክ የንግድ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን እና የአገር ውስጥ ኩባንያዎችን በፋይናንስ በመደገፍ ረገድ ያለውን መልካም ስም የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ ላለ የግል ባንክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ መሆኑ ለመረዳት ተችሏል።

ይህ የዋስትና መስጫ በተለይም እንደ ማዳበሪያ፣ መድኃኒት እና የእርሻ መሣሪያዎች ያሉ አስፈላጊ ዕቃዎችን ለማስገባት ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። #Capital
👍4
Comparison between 🇰🇪 & 🇪🇹 banks.

@PatternFin
E𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮 𝗧𝗼 𝗢𝗽𝗲𝗻 𝗥𝗲𝗮𝗹 𝗘𝘀𝘁𝗮𝘁𝗲 𝗠𝗮𝗿𝗸𝗲𝘁 𝘁𝗼 𝗙𝗼𝗿𝗲𝗶𝗴𝗻𝗲𝗿𝘀 𝗜𝗻 𝗡𝗲𝘄 𝗗𝗿𝗮𝗳𝘁 𝗟𝗮𝘄

The Council of Ministers has approved a draft law that would allow foreigners to own immovable property—part of a broader effort to attract foreign capital, expand housing access, and spur job creation. The Council also ratified major international agreements, including interest-free development loans from Italy and the World Bank, Ethiopia’s accession to the African Finance Corporation, and implementation of the African Continental Free Trade Area tariff reduction. A new air transport deal with Austria and updated service fee regulations were also approved.
Via #EBR

@PatternFin
ኢትዮጵያ አባል በሆነችው ብሪክስ የንግድ ልውውጥ ከዶላር እየራቀ 65 በመቶ በብሔራዊ ገንዘቦች ተከናወነ

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያን ጨምሮ አባል የሆኑት የብሪክስ አገራት (ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ኢራን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች) በንግድ ልውውጣቸው ከአሜሪካ ዶላር እየራቁ ሲሆን ከ65 በመቶ በላይ የሚሆነው ንግድ አሁን በአባል አገራቱ ብሔራዊ ገንዘቦች እየተከናወነ ነው።

ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በብራዚል በተካሄደው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ በሰጡት መግለጫ ሲሆን፣ ይህ አዝማሚያ ቡድኑ በፋይናንስ ረገድ ያለውን ነፃነት ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

ላቭሮቭ አክለውም "BRICS Pay" የተባለ ገለልተኛ የክፍያ ስርዓት ለመመስረት የሚደረጉ ውይይቶች እየተሻሻሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በተጨማሪም የBRICS የገንዘብ ሚኒስትሮች እና የማዕከላዊ ባንክ ገዥዎች በካዛን ጉባኤ በተሰጠው መመሪያ መሠረት በጋራ ንግድ ውስጥ ብሔራዊ ገንዘቦችን በንቃት ለመጠቀም ተስማምተዋል።

ይህ እርምጃ ብሪክስ በምዕራባውያን የገንዘብ ስርዓቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ የፋይናንስ መሠረተ ልማት ለመገንባት የሚያደርገውን የጋራ ጥረት ያሳያል።

በቅርቡ ኢትዮጵያ ለአዲሱ የልማት ባንክ (ቀደም ሲል የብሪክስ ልማት ባንክ በመባል ይታወቅ የነበረው) በይፋ አባልነት ለመቀላቀል ማመልከቻ ማስገባቷና የዚህ ሂደት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ገልፃ እንደነበር ይታወሳል። #Capital
👍1
𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮'𝘀 𝗖𝗲𝗻𝘁𝗿𝗮𝗹 𝗕𝗮𝗻𝗸 𝗧𝗼 𝗦𝗲𝗹𝗹 𝗨𝗦𝗗 𝟲𝟬 𝗠𝗶𝗹𝗹𝗶𝗼𝗻 𝗶𝗻 𝗟𝗮𝘁𝗲𝘀𝘁 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗔𝘂𝗰𝘁𝗶𝗼𝗻

The NBE has announced its fifth foreign exchange auction under the country’s ongoing market-based currency reform, with USD60 million set to be offered to commercial banks on Tomorrow, May 7, 2025.

The bi-weekly auction—part of NBE’s broader strategy to enhance foreign exchange transparency, reduce black market dependency, and stabilize the Birr—continues the central bank’s shift toward more predictable and competitive currency allocation mechanisms.

According to the notice, banks are invited to submit their bids electronically between 10:00 AM and 12:00 noon, with results expected to be announced by 5:00 PM the same day. The settlement will be finalized by close of business on May 7.

This auction follows last month's USD70 million round, which met 96% of banks' demand and marked a strong stride toward stabilizing forex flows through formal channels. #EBR

@PatternFin
Microsoft Shuts Down Skype After 23 Years

Microsoft officially retired Skype on May 5, 2025, ending the pioneering video-calling service's 23-year run as the company shifts its focus to Microsoft Teams. Skype first launched in Tallinn, Estonia, on August 29, 2003, when a six-person team from Estonia, Sweden and Denmark introduced what would become a communications revolution.

In May 2011, Microsoft paid $8.5 billion for Skype—its largest acquisition at the time—building on an active-user base of 170 million. The service's monthly active users swelled to roughly 300 million at its 2013–2016 peak, marking the high point of a journey that began with just 10,000 downloads on day one. Yet by 2021, Zoom had captured nearly half the market while Skype’s share had slipped to about 6 percent.

@PatternFin
ኢትዮ ቴሌኮም በዲጂታል መንገድ ግብይት የሚከናወንበት " ዘመን " የተሰኘ ዲጂታል ገበያን ይፋ የማድረግ ስነ ስርዓት አከናወነ።

ይህ ዲጅታል ገበያ ሃገራዊ የሆነ የተበታተነ የንግድ ስርዓትን በዲጂታል መንገድ የሚያገናኝ ነው ተብሎለታል።

የዲጂታል ኢኮኖሚ ኢትዮጵያ አካል ነው የተባለው " ዘመን ገበያ " ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው መገበያየት እና መሸጥ መለወጥ የሚችሉበት ነው።

ዲጂታል ገበያውን ይፋ ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮምኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት " ዘመን ገበያ " የተሰኘ የዲጂታል ግብይት ፕላትፎርም (Digital Market Place Platform) አገልግሎት ማስጀመሪያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ " የኢትዮጵያ የንግድ ስርዓት እንዲሁም አምራቹን ማሳለጥ በተለያየ ጥግ ያሉ ኢትዮጵያውያን እንዲገበያዩ ማስቻል አላማው ነው " ብለዋል።

እነዚህን ቁጥሮች ስንመለከት የዘመን ገበያን ይፋ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች አሉ ብሎ መውሰድ ይቻላል።

ይህ ዲጂታል ገበያ ቀላል ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሁም ከቴሌ ብር ጋር በቀጥታ የተገናኘ በመሆኑ የተለየ ያደረገዋል።

ወደ ፊት በቨርችዋል ሪያሊቲ የተደገፈ ይሆናል።

ይህንን በመጀመራችን እና ይፋ በማደረጋችን ያልነበሩ የሚፈጠሩ የስራ እድሎች አሉ ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ተጨማሪ የስራ እድል የምትፈጥርበት ሁኔታ ይኖራል " ብለዋል።
#ZemenGebeya #ዘመንገበያ

@PatternFin
The Auto Universe 2025: Who’s Driving the Future?

As of April 2025, the global automotive industry is evolving rapidly — and the market cap landscape shows who’s leading the charge.

Top Highlights:
• Tesla remains the giant with a staggering $776B, dwarfing traditional giants.
• China’s surge is undeniable: BYD ($147B) and Xiaomi ($140B) are redefining the EV game.
• Toyota ($234B) continues to dominate among legacy manufacturers.
• German engineering holds strong with Mercedes-Benz, BMW, Porsche, and Volkswagen together making up a powerful bloc.

This visual clearly outlines the shifting power dynamics — from traditional automakers to tech-driven EV disruptors.

@PatternFin
👍2
𝗘𝗫𝗜𝗠 𝗕𝗮𝗻𝗸 𝗼𝗳 𝗞𝗼𝗿𝗲𝗮 𝗔𝗻𝗰𝗵𝗼𝗿𝘀 𝗨𝗦𝗗𝟴𝟳𝟭𝗠 𝗜𝗻𝘃𝗲𝘀𝘁𝗺𝗲𝗻𝘁 𝗶𝗻 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮’𝘀 𝗚𝗿𝗼𝘄𝘁𝗵 𝗦𝗲𝗰𝘁𝗼𝗿𝘀

Ethiopia and Korea have taken a bold step in deepening their 70-year partnership, as Korea EXIM Bank pledges USD871 million to fund 11 major infrastructure projects in Ethiopia.

The commitment was announced during a high-level Development Cooperation Policy Dialogue hosted by Ethiopia’s Ministry of Finance, signaling stronger collaboration in transport, energy, health, and technology.

The two nations also reaffirmed their shared vision for inclusive growth, private sector engagement, and long-term development.

@PatternFin
👍1
D𝗮𝘀𝗵𝗲𝗻 𝗕𝗮𝗻𝗸 𝗝𝗼𝗶𝗻𝘀 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮’𝘀 𝗘𝘅𝗽𝗮𝗻𝗱𝗶𝗻𝗴 𝗗𝗶𝗴𝗶𝘁𝗮𝗹 𝗙𝘂𝗲𝗹 𝗣𝗮𝘆𝗺𝗲𝗻𝘁 𝗙𝗿𝗼𝗻𝘁𝗶𝗲𝗿 𝗮𝘀 𝗦𝗲𝗰𝘁𝗼𝗿 𝗢𝗽𝗲𝗻𝘀 𝗨𝗽

Dashen Bank has rolled out a new feature on its Super App, allowing customers to pay for fuel digitally—marking a major step toward breaking the long-standing monopoly in Ethiopia’s fuel payment system.

The move follows the government’s fuel sector reform aimed at increasing efficiency and competition. (EBR)

#DashenBank #DashenSuperapp

@PatternFin
𝗖𝗼𝗼𝗽 𝗕𝗮𝗻𝗸 𝗝𝗼𝗶𝗻𝘀 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮’𝘀 𝗘𝘅𝗽𝗮𝗻𝗱𝗶𝗻𝗴 𝗗𝗶𝗴𝗶𝘁𝗮𝗹 𝗨𝘁𝗶𝗹𝗶𝘁𝘆 𝗣𝗮𝘆𝗺𝗲𝗻𝘁 𝗟𝗮𝗻𝗱𝘀𝗰𝗮𝗽𝗲

The Cooperative Bank of Oromia , via its mobile platform Coopay e-Birr, has launched electricity bill payment services in partnership with the Ethiopian Electric Utility.

The move aims to expand digital payment access to rural areas and support Ethiopia’s push toward financial inclusion.
#CoopPay #Ebirr #UtilityPayment #Coop

@PatternFin
E𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮 𝗕𝗲𝘁𝘀 𝗼𝗻 𝗔𝗜 𝗶𝗻 𝗟𝗮𝗻𝗱𝗺𝗮𝗿𝗸 𝗔𝗴𝗿𝗶𝗰𝘂𝗹𝘁𝘂𝗿𝗮𝗹 𝗣𝗮𝗰𝘁 𝘄𝗶𝘁𝗵 𝗖𝗵𝗶𝗻𝗮

Ethiopia has signed a strategic agricultural research agreement with China that puts artificial intelligence (AI) at the heart of farming transformation.

The Ethiopian Institute of Agricultural Research and the Beijing Academy of Agricultural and Forestry Sciences will collaborate on AI-driven crop productivity, soil and water conservation, and smart lab development. (EBR)

#PrecisionFarming #SmartFarming #AI

@PatternFin
👍21
ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ምንዛሪ መገበያየት ይቻላል ? የብሔራዊ ባንክ መመሪያ በትክክል ምን ይላል ?
Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ምንዛሪ መገበያየት ይቻላል ? የብሔራዊ ባንክ መመሪያ በትክክል ምን ይላል ?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ባለፈው አመት 2016 ሐምሌ ወር ላይ የውጭ ምንዛሬ ግብይት በነፃ ገበያ እንዲመራ ከወሰነ በኋላ፣ አብሮ ይፋ በተደረገው መመሪያ በውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ አንዳንድ ማሻሻዎችን ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በመመሪያው ላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት መሰረት በማድረግም፣ ከህብረተሰቡ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ምንዛሪ መገበያየት ይቻላል ወይ ? የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ይህን በሚመለከት የባንክ ባለሙያዎች ማብራሪያ ጠይቋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ዙርያ ማብራሪያቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የብሔራዊ ባንክ ባለሙያ ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈቀደላቸው ሰዎች ውጪ፣ በውጭ ምንዛሪ መገበያየት አይፈቀድም፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በውጭ ምንዛሪ ወይም ዶላር መገበያየት አይችልም፡፡

ግብይትን በዶላር የሚፈፅሙ ሰዎች፣ የተፈቀደላቸው ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህም ዶላር ይዘው ከውጭ የሚመጡ ቱሪስቶች፣ ዲያስፖራዎች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከውጭ ሲመጡ እስከ 10 ሺህ ዶላር ይዘው እንዲገቡ ስለሚፈቀድላቸው፣ በጉምሩክ አስመዝግበው ባስገቡት ዶላር መገበያየት ይችላሉ፡፡  "

አገልግሎት ሰጭዎችስ በዶላር ማስከፈል ይችላሉ ?

" እነዚህ ሰዎች በዶላር መገበያየት የሚችሉት፣ አገልግሎታቸውን በውጭ ምንዛሪ እንዲሸጡ ከተፈቀደላቸው ተቋማት ብቻ ነው፡፡

ለምሳሌ ነጋዴዎችና አገልግሎት ሰጭዎች፣ ማለትም ሆቴሎችና አስጎብኝዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለሰጡት አገልግሎተት በዶላር ክፍያ መቀበል እንዲችሉ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ያላቸው ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊ ሆኖ፣ በዶላር ግብይት መፈፀም አይችልም፣ ከተፈቀደላቸው ተቋማትም ቢሆን፡፡

እኔ ኢትዮጵያዊ ሆኜ በዶላር እንዲያስከፍል ወደ ተፈቀደለት ሆቴል ሄጄ በዶላር መጠቀም አልችልም፡፡ ዲያስፖራ ከሆነንክ ግን፣ የሆነ ሆቴል ሔደህ ለተሰጠህ አገልግሎት በዶላር መክፈል ትችላለህ፡፡ ሆቴል ደግሞ ለሰጠው አገልግሎት በዶላር የማስከፈል ፈቃድ ያለው መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ከፋዩም፣ አስከፋዩም (ተጠቃሚውና አገልግሎት ሰጪው) በዶላር ለመገበያየት የተፈቀደላቸው ወይም እውቅና የተሰጣቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

ከአንድ የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ዶላር ማስተላለፍ ይቻላል ?

" የውጭ ምንዛሪ ማስተላለፍን (ትራንስፈርን) በተመለከተ፣ ከአንድ የዶላር ሒሳብ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለ ሌላ የዶላር ሒሳብ የውጭ ምንዛሪ ማስተላለፍ አይቻልም፡፡ ለምን ዓላማ ነው የሚተላለፈው ? የሚለው ይታያል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ዕቃ ገዝተህ በዶላር ልክፈል ብትል፣ አንተም በዶላር የመክፈል መብት የለህም፣ ሻጩም በዶላር ክፍያ የመቀበል ፈቃድ የለውም፣ ስለዚህ አይቻልም፡፡

ነገር ግን የዶላር አካውንት ኖሮህ፣ ከውጪ ሀገር እቃ ብትገዛ፣ ለእሱ በዶላር የመክፈል መብት አለህ፡፡ በቀጥታ ለእቃ ሻጩ ነው ዶላሩ የሚተለላለፈው፡፡ ውጭ ሀገር እቃ ወደገዛህበት መደብር ትራንስፈር ይደረጋል/ይተላለፋል፡፡ መረጃ አቅርበህ፣ ባንኩ ያንን መረጃ አይቶ አሳማኝ ሆኖ ካገኘው ይህንን ያደርግልሀል፡፡ ከራስህ ዶላር መፅሐፉን ለሸጠልህ ነጋዴ በቀጥታ ማስተላለፍ ይቻላል፡፡ ዋናው ነገር ለምን አላማ ነው የምታስተላልፈው የሚለው ነው፡፡ "

ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ምንዛሪ ግብይት መቼ ሊጀመር ይችላል ?

" በውጭ ምንዛሪ ግብይት መቼም አይጀመርም፡፡ በየትም ሀገር በውጭ ምንዛሪ ግብይት አይደረግም፡፡ እንደዛ ከሆነ፣ የሚነግርህ ትርጉም የሀገርህን ብር አታምነውም ማለት ነው፡፡ ኢኮኖሚዋ ችግር ላይ የወደቀባት ዚምባብዌ እንኳን ያንን አላደረገችም፡፡

የውጭ ምንዛሪ ፍሰትን ለመጨመር፣ ኤክስፖርትን ለማበረታታት፣ የምታደርጋቸው ማስተካከያዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ከዛ ውጪ፣ ዜጎችህን በዶላር ተገበያዩ ልትል አትችልም፡፡

ለምሳሌ፣ ሪልስቴቶች ወይም አለምአቀፍ ት/ቤቶች የዋጋ እና የክፍያ ተመንን በዶላር ሲያወጡ ይታያል፡፡ ይህ ችግር የለውም፡፡ ክፍያው ሲፈፀም ግን በኢትዮጵያ ብር ነው የምትከፍለው፡፡ "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይ ፦
- ለውጭ ጉዞ ዶላር/የውጭ ምንዛሪ እንዴት ነው የሚሰጠው ?
- የባንኮች ቪዛ ካርዶች እንዴት ነው የምንጠቀምባቸው ?
- የባንኮች ቪዛ ካርዶች በሀገር ውስጥ የምንጠቀምበት ዕድል አለ ?
- የዶላር አካውንት/የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት ቅድመ ሁኔታ አለ ? በሚሉ ጥያቄዎች ላይ የባለሙያ ማብራሪያ ያቀርባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@PatternFin
👍1