Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
416 subscribers
590 photos
6 videos
51 files
34 links
Banking & FInance, Stock market, forex, Fintec and e-commerce
Download Telegram
" 4 ኪሎ ቤተመንግስት ዙሪያ ያሉ መንገዶች ከዚህ በኋላ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አገልግሎት ይሰጣሉ " - የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

ከዚህ በኋላ 4 ኪሎ ቤተመንግስት ዙሪያ ያሉ መንገዶች በአንድ አቅጣጫ ብቻ አገልግሎት እንደሚሰጡ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

በመሆኑም ፦
- ከጥይት ቤት  እስከ ፓርላማ ትራፊክ መብራት፣
- ከቤተመንግስት ፖርክንግ እስከ ጥይት ቤት
- ከፓርላማ ትራፊክ መብራት እስከ ሳይንስ ሙዝየም ድረስ ያሉ መንገዶች ቀድሞ ከነበረው ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ወደ አንድ አቅጣጫ መንገድ ተቀይረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳን መስመሮቹ እንደ ቀድሞው ባለ ሁለት አቅጣጫ ሆነው አገልግሎት መስጠታቸውን መቼ ይጀምራሉ ? ሲል ጠይቋል።

በምላሻቸው በአንድ አቅጣጫ እንጂ ወደበፊቱ ተመልሶ በሁለት አቅጣጫ አገልግሎት እንደማይሰጡ ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አስቀድመው " ለሁለት ቀን ወደ አንድ አቅጣጫ (One way) ተደርገው አገልግሎት ይሰጣሉ " በሚል ለቲክቫህ  ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

ሆኖም  " ለሁለት ቀን ያልኩት በአንድ አቅጣጫ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎች እና የጎደሉትን የማሟላት ስራ ለመስራት ነው " ሲሉ መንገዶቹ በቀጣይነትም ባለ አንድ አቅጣጫ መንገድ ሆነው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።

አክለውም " የትራፊክ ስራ ዳይናሚክ ነው፣ እንደ የአስፈላጊነቱ  በየጊዜው የማሻሻል ስራዎች ሊኖሩ ይችላሉ " በማለት ጠቁመዋል።

ከዚህ በኃላ ግን መንገዶቹ ባለ አንድ አቅጣጫ ብቻ እንደሆኑ አስገንዝበዋል።
በቀጣይ ዓመታት ከብሔራዊ ባንክ እንደነዚህ አይነት መግለጫዎች ይጠበቃሉ!

#Merger&Acquisition #M&A
#NBE

@PatternFin
👍2
ብሔራዊ ባንክ የ70 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ነገ እንደሚካሄድ ገለፀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀጣዩን በየሁለት ሳምንቱ የሚካሄደውን የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ነገ ሐሙስ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም.  እንደሚካሄድ ዛሬ አስታውቋል።

በዚህ ጨረታ የሚቀርበው ጠቅላላ የውጭ ምንዛሬ መጠን 70 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መሆኑን ባንኩ አሳውቋል። ፍላጎት ያላቸው ባንኮች በተሰጠው መመሪያ መሰረት በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።
👍3🤔1
Why Meles Opposed.pdf
10.8 MB
Part 2: Why Meles Opposed Financial Sector Liberalization in Africa—Game Theorizing high stake moves. Take your turn—explore the games in these slides and decide your next move.

📌 Which piece would you prioritize to revolutionize Africa’s financial sector?

©️Bayu Samuel
👍1
𝗬𝗮𝗻𝗴𝗼, 𝗡𝗜𝗕 𝗕𝗮𝗻𝗸, 𝗮𝗻𝗱 𝗡𝗜𝗕 𝗜𝗻𝘀𝘂𝗿𝗮𝗻𝗰𝗲 𝗙𝗼𝗿𝗴𝗲 𝗚𝗿𝗼𝘂𝗻𝗱𝗯𝗿𝗲𝗮𝗸𝗶𝗻𝗴 𝗗𝗲𝗮𝗹 𝘁𝗼 𝗣𝗿𝗼𝘁𝗲𝗰𝘁 𝗗𝗿𝗶𝘃𝗲𝗿𝘀 𝗶𝗻 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮

In a bold move to transform the economic resilience of ride-hailing drivers in Ethiopia, G2G IT Solutions (Yango), NIB Bank, and NIB Insurance have signed a landmark tri-party agreement that directly addresses one of the most pressing challenges for drivers: the lack of affordable, comprehensive car insurance.
𝗞𝗲𝗿𝗰𝗵𝗮𝗻𝘀𝗵𝗲 𝗕𝗲𝗰𝗼𝗺𝗲𝘀 𝗘𝘅𝗰𝗹𝘂𝘀𝗶𝘃𝗲 𝗗𝗶𝘀𝘁𝗿𝗶𝗯𝘂𝘁𝗼𝗿 𝗼𝗳 𝗚𝗲𝗲𝗹𝘆 𝗩𝗲𝗵𝗶𝗰𝗹𝗲𝘀 𝗶𝗻 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮

Kerchanshe Group has announced that it has become the official and sole distributor of Geely vehicles in the country.

The landmark agreement brings one of China’s leading automotive brands into the Ethiopian market through a trusted local partner.

As part of a long-term strategy, Kerchanshe is also preparing to launch local assembly operations for Geely vehicles under its automotive division, Kerchanshe Auto. #EBR
👍1
𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮'𝘀 𝗖𝗲𝗻𝘁𝗿𝗮𝗹 𝗕𝗮𝗻𝗸 𝗦𝗮𝘁𝗶𝘀𝗳𝗶𝗲𝘀 𝟵𝟲% 𝗼𝗳 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗗𝗲𝗺𝗮𝗻𝗱 𝗶𝗻 𝗨𝗦𝗗𝟳𝟬 𝗠𝗶𝗹𝗹𝗶𝗼𝗻 𝗔𝘂𝗰𝘁𝗶𝗼𝗻

NBE today reported that it successfully allocated $70 million in its fourth foreign exchange auction, meeting 96% of the total forex demand from participating banks.

A total of #26 #commercial_banks secured allocations during the auction, with the weighted average exchange rate settling at Birr 131.4961 per US Dollar, reflecting the continued transition toward a market-reflective exchange mechanism.

The results underscore the central bank’s recent efforts to enhance foreign currency accessibility, restore market confidence, and stabilize the exchange rate by aligning demand and supply through bi-weekly auctions.

This high satisfaction rate signals growing liquidity and may ease pressure on parallel markets, while offering relief to importers and exporters navigating a rapidly evolving forex environment.
👍2
𝗘𝗖𝗫 𝗜𝗻𝗸𝘀 𝗠𝗮𝗷𝗼𝗿 𝗖𝗼𝗻𝘀𝘁𝗿𝘂𝗰𝘁𝗶𝗼𝗻 𝗔𝗴𝗿𝗲𝗲𝗺𝗲𝗻𝘁 𝗳𝗼𝗿 𝗡𝗲𝘄 𝗛𝗤 𝘁𝗼 𝗕𝗼𝗼𝘀𝘁 𝗠𝗼𝗱𝗲𝗿𝗻 𝗧𝗿𝗮𝗱𝗲

The Ethiopian Commodity Exchange (ECX) has signed a major construction agreement with the Ethiopian Construction Works Corporation  to build a new 36-story headquarters that will support Ethiopia’s growing role in modern commodity trading.
👏1
ሕዝብ እንዲማርበት የተሰራጨ !!

ይቺን ሿሿ አንድ ጓደኛዬ ተበልቶበት ነበር። ሌላ ጊዜ ግን ተበቀላቸው።

ሰው እንዲማርበት የተሰራጨ። -- ነገሩ እንዲህ ነው።

አንድ ጓደኛዬ ከውጭ ሃገር ዶላር ልኮልኝ እሱን በብላክ ልመነዝር ብሔራዊ አካባቢ
ሄድኩ። እዚያ አካባቢ "ምንዛሬ" የሚሉ ሰዎች አሉ። እሽ ብዬ ዶላሬን ላዘረዝር ተስማማሁ። የምንዛሬውን መጠን ተስማማን። መጀመሪያ ዶላሩን ስጠኝ ብሎ መቶ መቶ ብር ያለው ወደ አምስት እስር ብር በእጁ ይዟል። ሲቪል ደህንነቶች እንዳይመጡብን አፍጥነው ብሎ አስቸኮለኝ። አዕምሮን ሰረቀኝ። እኔም ዶላሩን ሰጠሁትና አምስት እስር ብሩን በእጄ አስታቅፎኝ በዩሴን ቦልት ፍጥነት ከአካባቢው ተሰወረ።

እኔም መኪናዬን እየነዳሁ ወደ ቤት ሄድኩና የታሰረውን ብር ለመቁጠር ፈታሁት። በድንጋጤ ክው አልኩልህዠ። የታሰረው ብር መቶ መቶ ብር ከውጭ በኩል ሆኖ ውስጡ ለካ በአምስት ብር ጥቅጥቅ ተብሎ የተደረደረ ነው። አምስቱም እስር ተመሳሳይ ነው። እንዲህ ሆኜ የጉድ ጉድ ተሰራሁ።

እነዚህን ዶላር እንመነዝራለን የሚሉትን ለመበቀል ጊዜ ስጠብቅ ነበር የቆየሁት። ሰሞኑን አንድ ሰው ከውጭ አገር ዶላር ላከልኝ። እኔም ዶላሩን ለመመንዘር ባለፈው ዓመት ያታለሉኝን ሰዎች ለማግኘት ፈለግሁ። የሚገርመው ያንኑ ልጅ አገኘሁት። እኔ አውቄዋለሁ፣ እሱ ግን አላወቀኝም።

እነዚህ በብላክ ዶላር የሚመነዝሩ ሰዎች በቡድን የተደራጁ መሆናቸውን አወቅሁ። ወደኔ የተላከው በጣም ብልጥና አራዳ የተባለው ነው። እንደ አምናው ሊያታልለኝ ሞከረ። አንድ ቦታ ላይ ቁጭ ብለን በምንዛሬው መጠን ስንደራደር ቆየን። አንዴ ከፍ፣ አንዴ ዝቅ እያደረገ እና ምርጫ የሌለኝ ለማስመሰል ሞከረ። በመጨረሻም በምንዛሬው መጠን ተስማማን። የተለመደውን ሲቪል ደህንነቶች እንዳይዙን በማለት ያጣድፈኛል።

እኔ ግን በውስጤ በቀልን አስቤ ስለነበረ "መኪና ውስጥ እንግባና እዚያው ስጠኝ፣ ዶላሩም መኪና ውስጥ ነው" አልኩት። ብዙ አቅማማ፣ ተጠራጠረ። ከዚያም እንደምንም ብሎ ተስማምቶ ወደ መኪና ውስጥ ገባ እና ስጋት ስለነበረው ወዲያው ወጣ። እኔም የዶላሩን ጫፍ ከፓስፖርቴ አውጥቼ አሳየሁት። በጣም እየቸኮለ ዶላሩን ስጠኝ አለኝ። እኔም ይኽው እያየኸው እኮ ነው፣ እሰጥሃለሁ፣ ግን መጀመሪያ አንተ ዝርዝር ብሩን ስጠኝ አልኩት። እሱም ከተጨቃጨቀ በኋላ በእጁ የያዘውን የታሰረ ብር ሰጠኝ።

እኔም ዶላር የምሰጥ መሰልኩና እንዳይታይ ደብቄው የነበረውን ሕጋዊ የ*ጦ*ር መሣሪያዬን ቀስ ብዬ መዘዝኩና ፊቱ ላይ ደግኜ "አንተ ሌባ፣ ባለፈው ዓመት አምስት ብር ጥቅጥቅ አድርገህ አስረህ 500 ዶላሬን የበላኸኝ አንተ ነህ፣ አሁንም ልትበላኝ ነው?" ብዬ አነጣ*ጠርኩበት። እሱም እንደ አምናው በዩሴን ቦልት ፍጥነት የተደገፈውን የመኪናዬን በር ትቶ እየሮጠ አመለጠኝ። እኔም እየተከተልኩ "አለቅህም፣ አታመልጠኝም" እያልኩ አሯሯጥኩት።

አካባቢው የነበሩት የሱን ጓደኞች ሳይቀር እያሯሯጥኩ በጠራራ ፀሐይ ተበቀልኳቸው። መኪናው ውስጥ ገብቶ የሰጠኝ ብር እንደ አምናው ከውጭ መቶ ብር ሆኖ ውስጡ ደግሞ አምስት አምስት ብር ስለሆነ ገና ከአምናው የቀረኝ ትንሽ ገንዘብ አለ።

እንዲህ ብዬ በመጠኑም ቢሆን የተታለልኩትን ገንዘብ አስመልሻለሁ። ስቴዲየም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት ይሄንኑ ሿሿ የሚሰሩ ቁጥሩ በርካታ የሆነ ሰው ይገኛል። ሁሌም በተለያየ የሿሿ ስልት የሚሸወድ ሰው በመኖሩ ምንም ቢደረጉ ተመልሰው በቦታው ይገኛሉ።

ሌሎች እንደ እኔ እንዳይሸወዱ ለማስተማር ይህን አጋራዋችሁ።
👍3
መልካም የትንሳኤ በዓል🙏

ርሑስ በዓል ትንሳኤ🙏
Dashen Bank Launches E-Commerce Service Through Its Super App

Dashen Bank has taken a significant step in enhancing customer convenience by launching an e-commerce service through its innovative Dashen Super App. This new feature is designed to simplify shopping for holiday essentials and everyday items, making it easier for customers to access a wide range of products from the comfort of their homes. #EBR
ኢትዮጵያ በሞያሌ ድንበር የንግድ ልውውጥን በ1 ሺህ ዶላር ጣሪያ ለመጀመር ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለሁለት ዓመታት በዘለቀ ድርድር በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕቀፍ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት  ተፈራርመዋል።

በዚህም መሰረት በሞያሌ ድንበር ላይ ለሚደረጉ የሸቀጦች ንግድ የመጀመሪያ ጣሪያ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዲሆን ተወስኗል።

በሞምባሳ የተጠናቀቀው ይህ ስምምነት የንግድ ሂደቶችን በማቅለል የድንበር ማህበረሰቦችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ያለመ ነው።

በስምምነቱ የኢትዮጵያ የድንበር ንግድ ዞን ከሞያሌ በ50 ኪሎ ሜትር እንዲሁም የኬንያ ደግሞ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚወሰን ሲሆን ነጋዴዎችም በጋራ በተስማሙበት የምርት ዝርዝር መሰረት እስከ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የንግድ ልውውጥ በወር እስከ አራት ጊዜ ድረስ ማካሄድ ይችላሉ ተብሏል።

ይህ ስምምነት የንግድ ዋጋ ጣሪያዎችን፣ የጉዞ ድግግሞሽን እና የድንበር ንግድ ዞኖችን የመሳሰሉ ጉዳዮችን በመዳሰስ ለሁለት ዓመታት በዘለቀ ድርድር የተገኘ ውጤት ነው።

በኬንያ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ጠቀሜታ የሚያሳዩ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እ.ኤ.አ በ 2023 ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ለኬንያ ትልቁ የኤክስፖርት መዳረሻ ነበረች።

ኬንያ ወደ ኢትዮጵያ በላከቻቸው ሸቀጦች 86.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የገቡት ምርቶች በዋናነት ቡና፣ ሻይ፣ ህይወት ያላቸው እንስሳት እና የዘይት እህሎች ሲሆኑ መጠናቸው 36.7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድረሱ ይታወቃል። #Capital
👍4
𝗕𝗼𝗲𝗶𝗻𝗴 𝗢𝗽𝗲𝗻𝘀 𝗙𝗶𝗿𝘀𝘁 𝗔𝗳𝗿𝗶𝗰𝗮 𝗢𝗳𝗳𝗶𝗰𝗲 𝗶𝗻 𝗔𝗱𝗱𝗶𝘀 𝗔𝗯𝗮𝗯𝗮

Boeing has officially opened its Africa office in Addis Ababa, marking a major milestone in Ethiopia’s aviation journey. The move underscores Ethiopia’s vision of becoming a key player in Africa’s aerospace ecosystem. (EBR)

#Boeing #EthiopianAirlines
Deposit Insurance Fund welcomes rising T-Bill yields

The Ethiopian Deposit Insurance Fund (EDIF), aimed at enhancing confidence in the financial sector, has embraced the recent surge in Treasury bill (T-bill) yields, identifying it as a crucial factor for revenue growth.

Since becoming operational in 2023, EDIF has increasingly favored the rising T-bill rates at National Bank of Ethiopia (NBE) auctions for investments.
"ማኪያቶ 3000 ብር ፤ አምቦ ውሃ 1000 ብር"

---

ይኸውልህማ ማኪያቶ 125 ብር ፣ በርገር 3000 ብር ፣ አምቦ ውሃ 400 ብር ከፈልኩ ብለህ አናቱን በዱላ እንደተመታ ውሻ እየተሽከረከርክ ብትጮህ Just because you can not afford something doesn't mean it's overpriced. ይልቅ It just means you're not the target customer. Indeed!

እንደዚህ አይነት አንጀት ጨምቆ አጥንት አድቅቆ ልብ ሰንጥቆ ከነፍስህ ጓዳ ዘልቆ ከህብረሰረሰር እስከ ተረከዝ የሚነዝር የሚያንዘረዝር ሂሳብ የሚያስከፍሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋሞች/ሆቴሎች/ካፌዎች ለእንደ'ኔ እና አንተ አይነቱ ወር ጠብቆ ገንዘብ ቆጣሪ - የመንግስት ተቀጣሪ ፣ ጉልት ቸርቻሪ ቀበቶ አዟሪ ቦንዳ አባራሪ ለሆነው ግለሰቦች ሳይሆን

ፈርጣማ የፋይናንስ ኢምፓየር ለዘረጉ:: ዱባይ ፣ ቻይና ቬጋስ እሽኮለሌ እያሉ ለሚያነጉ ባለሀብቶች ፣ አስመጪና ላኪዎች ፣ ብላክ የሴት አቅራቢዎች ፣ ፖለቲከኞች ፣ ቤት አልሚዎች ፣ ሼር ሆልደሮች ወዘተ ስለቀጣዩ ስራቸው:: ስለፕሮጀክት ማስፋፊያቸው ስለበጀት አጋጋጣቸው ምናምን ከባለድርሻ አካላታቸው ጋር Coffee Time Discuss እያደረጉ እንዲመክሩበት:: አልያም Business Lunch/Diners እንዲያደርጉ በሚል Core Purpose ዲዛይን ተደርገው የተሰሩ ቤቶች ናቸው::

እንጂ እንደ እኔ እና አንተ አይነቱ ኑሮ እንደ ሸማኔ መዳወሪያ ሰርክ ግራ እና ቀኝ ሲያሮጠው ለሚውል ሜዳሊያ አልባ አትሌት ለሆንን ምስኪን ዝርዝራም ሰቀቀናም Low Class ግለሰቦች ከላይ የእግዜር ፀሐይ ከስር ቻይና ጫማ ስላቃጠለን ብቻ ሮጠን ገብተን Free Table አግኝተን ጉብ አልን ማለት የእነሱ Target Customers ነን ማለት አይደለም:: ተረዲእኻ?

"የፈለገ ቢሆንስ ማኪያቶ ማኪያቶ ውሃም ውሃ ነው" ካልከኝ ደግሞ:: አትሳሳት እነዚህ ቤቶች የሚሸጡት ማኪያቶ ፣ ውሃ በርገር የሚባሉ F&B አይደለም:: They are design to sell an exclusive experience, not just accommodation. They cater to guests who seek Status, Personalization, and emotional fulfillment. Thus, ማኪያቶህን ቤትህ ሾላ ወተት እና Pecticide የጨረሰውን ቡናህን በጥብተህ ጠጣ ነው የሚሉህ::

BTW, They're objectively correct, ምክንያቱም ማንም ሰው ሰዓት ለማየት ብሎ Rolex, Patek Philippe, Richard Millie የመሳሰሉ ውድ የእጅ ሰዓቶችን አይገዛም:: ሰዓቱን ለማወቅ ለማወቅማ የእጅ ሞባይልህም ሰዓት አለው:: የተሳፈርክበት ታክሲም ሰዓት አለው:: የቤትህም ግርዳም ሰዓት አለው:: አንተ ባይኖርህ ጎረቤትህ ይኖረዋል:: ቢጠፋ ቢጠፋ መንገደኛ አስቁመህ መጠየቅ ትችላለህ ስለዚህ ሰዎች Rolex, Patek Philippe እና Richard Millie የመሳሰሉ ውድ ሰዓት የሚገዙት ሰዓት ለመመልከት ሳይሆን ለስታተሳቸው ነው:: Success Validate ለማድረግ ነው:: Financial Trust Build ለማድረግ ነው:: ያው ፍሌክሱም እንዳለ::

Likewise, Rolls-Royce መኪና አይደለም የሚሸጠው Social Hierarchy, Power and Identity ነው:: እንደ Burj Al Arab, Aman Resorts, The Ritz ያሉ ሆቴሎች ደግሞ የሚሰጡት የምግብ የመጠጥ እና የማረፊያ አገልግሎት ሳይሆን

ስለዚህ ጎቤ አንተ የገባኸው Status, Royal እና Exclusive የሚሸጡ ቤቶች ስለሆነ ሹልክ ብለህ ውጣ እንጂ ዋጋው ተወደደ ብለህ አታጉረምርም:: አንተ የእነሱ ቀጥተኛ እና ትክክለኛ የገበያ ተጠቃሚ ኢላማ ወይም Target Customer አይደለም በቃ! ለእኔ እና አንተ የእማማ አበሩ ቤት Target Customer ነን። "Price is what you pay. Value is what you get" ብሎሃል Warren Buffett

----
©Yoakin Bekele Pachi
👍4
Ethiopia’s Central Bank Unveils Modernized National Transfer System

In a significant stride toward financial modernization, NBE has launched an upgraded Ethiopian Automated Transfer System (EATS), a move designed to reshape the country’s payment ecosystem.

The upgraded transfer system aligns with the globally recognized ISO 20022 standard. By adopting this global benchmark, the NBE positions Ethiopia’s financial sector for increased interoperability, transparency, and resilience.

The system is being rolled out in collaboration with 35 financial institutions nationwide, indicating broad industry adoption. With its promise of faster transaction times and enhanced security, the upgraded EATS is expected to reduce bottlenecks in interbank transfers, boost user confidence, and improve the overall customer experience.

According to the central bank, is a foundational move to overcome longstanding structural inefficiencies in the financial sector and foster a robust, trustworthy financial system. #EBR
28 ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸው ተነገረ።

28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡

የባንኩ ሪፖርት እስከ ሰኔ 2024 ድረስ ያሉ የገንዘብ እንቅስቀሴዎች ዙሪያ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

ባንኩ በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው 28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በአጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን አጥተዋል ብሏል።

የማጭበርበር ድርጊቶቹ የተፈጸሙት ፦
- በሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች፣
- በተሰረቁ የኤትኤም ማሽኖች፣
- በሐሰተኛ ቼኮች፣
- በሐሰተኛ የስልክ መልዕክት እና ተያያዥ መንገዶች አማካኝነት ነው፡፡

በዚህ ዓመት ባንኮች ያጡት ገንዘብ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ300 ሚሊዮን ብር ጭማሪ እንዳሳየም በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ካሉ 31 ባንኮች ውስጥ 28ቱ ሲጭበረበሩ የቀሪዎቹ ሶስት ባንኮች ማንነት ግን በሪፖርቱ ላይ አልተጠቀሰም፡፡

ባንኮች ከአነስተኛ የብድር እና ቁጠባ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ብድሮችን እየሰጡ ነው የተባለ ሲሆን ይህ አገልግሎት እየጨመረ መሄድ እና የበይነ መረብ ማጭበርበሮች መበራከት ባንኮች የሚያጡት ገንዘብ ሊጨምር እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ በሪፖርቱ ላይ መጥቀሱን ከፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተጭበረበሩ የተባሉት ባንኮች ዝርዝር በይፋ አልተገለጸም።

@PatternFin