አንቶኒ ጆሹዋ ጦማሪውን ጄክ ፖልን በማንኳኳት መንጋጋውን በሁለት ቦታ ሰበረ።
ኢያሱ ጳውሎስን ደጋግሞ ደበደበው እና በ6ኛው ዙር ጨዋታውን በመምታት አጠናቋል።

❤1👍1
በታይዋን ውስጥ የሽብር ጥቃት: አንድ የሥነ ልቦና ሦስት ሰዎችን በስለት ወግቷል, ሌሎች አምስት ቆስለዋል
ከዚህ ቀደም ጥፋተኛ ተብሎ የተፈረደበት የ27 ዓመት ወጣት በታይፔ ዋና ጣቢያ የጭስ ቦምቦችን ተጠቅሞ ወደ አንድ የምድር ውስጥ ባቡር ጣቢያ በመሄድ በዘፈቀደ መንገድ አላፊዎችን በቢላ ማጥቃት ጀመረ። አጥቂውን ለመቋቋም ሲሞክር የ57 አመት ሰው ህይወቱ አልፏል።
ከዚህ በኋላ ወንጀለኛው አምልጦ እራሱን ከህንጻው ላይ በመጣል እራሱን አጠፋ።

🇪🇹🇷🇺 የሞስኮ “የአቶም ሙዝየም” ድንቅ ቦታ – የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ኮሚሽነር
🏛 ሳንዶካን ደበበ በራሲያ ፌደሬሽን እያደረጉ ባሉት ቆይታ በዋና ከተማዋ ሞስኮ የሚገኘውን ግዙፉን “የአቶም ሙዝየም” መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።
🤝 ታህሳስ 9፣ በሳንዶካን ደበበ በተመራ ልዑክ ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኒውክሌር ኃይል ማመንጪያ ጣቢያ በኢትዮጵያ መገንባት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ከሮሳቶም ኃላፊዎች ጋር በሞስኮ ውይይት አድርጓል፡፡

ኮሚሽነሩ ጉብኝታቸውን ተከትሎ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት የአድናቆት ጽሑፍ “ከኒውክሌር ተክኖሎጂ ታሪካዊ ጅማሮ እስከ ዘመኑ የደረሰበትን የአቶሚክ ኃይልና ተያያዥ ወጤቶች በአንድ ጣሪያ ውስጥ መመልከት የሚያስችል ድንቅ ቦታ ነው።” ብለዋል፡፡
🤝 ታህሳስ 9፣ በሳንዶካን ደበበ በተመራ ልዑክ ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኒውክሌር ኃይል ማመንጪያ ጣቢያ በኢትዮጵያ መገንባት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ከሮሳቶም ኃላፊዎች ጋር በሞስኮ ውይይት አድርጓል፡፡
❤2👍1
ሞት ተፈርዶበታል !
በዓዲግራት የዩኒቨርሲቲ ሰራተኛዋን የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ።
በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት ከተማ ዙሪያ አንዲትን የ25 ዓመት ወጣት አስገድዶ በመድፈር እና በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተከሰሰው ግለሰብ ከስምንት ወራት እልህ አስጨራሽ የምርመራ ሂደት በኋላ በሞት ቅጣት እንዲቀጣ ተወሰነበት።
እንደ ትግራይ ክልል ፖሊስ መረጃ፣ የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ተከሳሹ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሰራተኛ በሆነችው ወጣት መኖሪያ ቤት ሰላማዊ ሰው መስሎ ዘልቆ ይገባል። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ በሩን ከውስጥ በመቆለፍ ወጣቷን አስገድዶ ይደፍራታል።
ወንጀለኛው ፀያፍ ተግባሩን ፈጽሞ ከቤት ሊወጣ ሲል ተበዳይዋ " ለፈጸምከው በደል ህግ ዋጋህን ይከፍልሃል " ትለዋለች።
ይህ ጠንካራ ምላሽ ያስቆጣው ገዳይ ወጣቷን 12 ቦታ በስለት ከወጋት በኋላ በገመድ አንቆ ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል።
ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላም የሟችን ስልክ ይዞ ይሰወራል።
ግድያው የተፈጸመው በጨለማ ተገን በማድረግ እና ምስክር በሌለበት ሁኔታ በመሆኑ የፖሊስን የምርመራ ሂደት እጅግ አዳጋች አድርጎት ቆይቷል።
ሆኖም ለአካሄዱ ትልቅ ፍንጭ የሆነው አንዲት ወጣት የሰጠችው ጥቆማ ነበር።
ይህች ወጣት፥ ግለሰቡ ስልኳን በሃይል ነጥቆ መውሰዱን፤ ወደ እህቱ ደውሎ "ሰው ገድያለሁ፣ ተስፋ ቆርጫለሁና ከአገር ለመውጣት ገንዘብ ላኪልኝ " ሲል መስማቷን ለፖሊስ አሳውቃለች።
ፖሊስ ያገኘውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ገዳዩ በቤተሰቦቹ ቤት ተደብቆ ከቆየ በኋላ በአፋር በኩል ከአገር ለማምለጥ ሲሰናዳ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ጥቆማ የሰጠችው ወጣትም ግለሰቡን ለይታ በማመልከት በምርመራው ሂደት ትልቅ እገዛ አድርጋለች።
ተከሳሹ በተደረገበት ምርመራ ወንጀሉን መፈጸሙን በአንደበቱ አምኗል። በዚህም መሠረት ፍርድ ቤቱ ግለሰቡን በሦስት ዋና ዋና ወንጀሎች ማለትም፦
• በአስገድዶ መድፈር
• ግፍ በተሞላበት ግድያ
• በቅሚያ ጥፋተኛ ሆኖ በማግኘቱ #በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
ፖሊስ ሟች ከመሞቷ በፊት የተናገረችውን ቃል በማስታወስ " ህግ ዋጋህን ይሰጥሃል ብላው ነበር ፤ ቃሏ ተግባር ሆነና ህግ ፍትህን ሰጠ፤ ገዳይንም በሞት ተቀጣ " ብሏል።
መረጃውን ከትግራይ ፖሊስ ነው ያገኘነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia

❤3👍1
አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አምባሳደር ቆንጂት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በ1950ዎቹ በለጋ እድሜያቸው ተቀላቅለው ከዴስክ ኦፊሰርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት አገልግለዋል።
አምባሳደር ቆንጂት ከዮዲት እምሩ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደርም ናቸው።
አምባሳደሯ ፦
- በኦቶዋ፣
- በካይሮ፣
- በቴል አቪቭና ቬይና በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።
በአፍሪካ ሕብረትና በተባባሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ መልዕክተኛ በመሆንም ሰርተዋል።
ከሰኔ 2009 እስከ መስከረም 2011 ዓ.ም ደግሞ ኢጋድ በመራው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ላይ ልዩ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል።
ከአንጋፋ ዲፕሎማት ህልፈት ጋር በተያያዘ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
" ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ " ብለዋል።
" አምባሳደር ቆንጂት ከልጅነት እስከ ዕውቀት ኢትዮጵያን በዲፕሎማትነት በማገልገል፣ ከአምባሳደር ዮዲት እምሩ ቀጥለው ሁለተኛዋ ሴት የኢትዮጵያ አምባሳደር ናቸው " ብለዋል።
" ለሕግ፣ ለአሠራር፣ ለፕሮቶኮል እና ለኢትዮጵያ ጥቅሞች በነበራቸው የጸና አቋም እናስታውሳቸዋለን። ከእርሳቸው በኋላ አያሌ ሴት ዲፕሎማቶች በመስኩ እንዲሠማሩ መንገዱን አስፍተዋል " ሲሉ አወድሰዋቸዋል።
" ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያውያን መጽናናት እመኛለሁ " ብለዋል።

#Fintech
በ "ፊንቴክ" የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ ፖሊስ የጠየቀው የተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ላይ ለመወሰን ፍርድ ቤት ለነገ ቀጥሯል።
ከ "ፊንቴክ ኢንቨስትመንት " ጋር በተያያዘ በከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ዛሬ መጋቢት 30/2018 ዓ.ም በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።
መርማሪ ፖሊስ በቀሪ የምርመራ ስራዎች ምክንያት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል።
ባለፉት 12 የምርመራ ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት ለፍርድ ቤቱ ያስረዳው ፖሊስ 12 የመንግስት እና የግል ሚዲያዎች እንዲሁም ሁሉም የሀገሪቱ ባንኮች በጉዳዩ ዙሪያ ያላቸውን መረጃ በጽሁፍ እንዲልኩ መጠየቁን አስረድቷል።
እስካሁን የ150 ምስክሮችን ቃል የተቀበለ ሲሆን ገና ያልተሰሙ ሌሎች ተጨማሪ ምስክሮች መኖራቸውን ጠቁሟል።
እያንዳንዱ ተጠርጣሪ በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ የነበረውን የግል ተሳትፎና የጥቅም ትስስር የሚገልጽ ማብራሪያ ለችሎቱ አቅርቧል።
የተጀመሩ የሰነድና የሰው ማስረጃ ማሰባሰብ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል።
በተቃራኒው የተጠርጣሪ ጠበቆች ደንበኞቻቸው በዋስ እንዲፈቱ ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርበዋል።
ጠበቆቹ ባቀረቡት መከራከሪያ ፖሊስ የጠቀሳቸው ቀሪ የምርመራ ስራዎች ተጠርጣሪዎቹ ውጭ ወጥተው ሊከናወኑ የሚችሉ እንጂ የእነሱን መታሰር የግድ የማይሉ መሆናቸውን ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን እና የተወሰኑት ደግሞ የጤና እክል ያለባቸው መሆኑን በመጥቀስ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ፣ የፖሊስን የምርመራ መዝገብ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ሚያዝያ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ/ም

❤1
ህወሓት ከስድስት ዓመት በፊት በተደረገው ምርጫ የተቋቋመው "የትግራይ መንግሥት ምክር ቤት" እንዲመለስ ወሰነ ህወሓት ከስድስት ዓመት በፊት (በ2012 ዓ.ም) የተካሄደውና በፌደራል መንግሥቱ ውድቅ የተደረገው የትግራይ ምርጫ ውጤት እንዲመለስና በወቅቱ ተመርጦ የነበረው ምክር ቤት ወደ ሥራው እንዲገባ ወስኗል። ድርጅቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው የፌደራል መንግሥት የጊዜያዊ አስተዳደሩን የቆይታ ጊዜ ያለ ህወሓት ተሳትፎ አራዝሟል በሚል ተቃውሞውን በገለጸበት መግለጫው ላይ ነው። ህወሓት የፌደራል መንግሥቱ በክልሉ ላይ ዳግም ጦርነት ለመክፈትና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለመጣስ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲል የወነጀለ ሲሆን፣ ለዚህም እንደ ምላሽ የቀድሞው ምክር ቤት እንዲመለስና አስፈጻሚው አካል ደግሞ ሁሉንም የትግራይ ኃይሎች ያካተተ ሆኖ እንዲቋቋም መግባባት ላይ መደረሱን አስታውቋል።
በሌላ በኩል፣ ይህ ውሳኔ በክልሉ አመራሮችና በፌደራል መንግሥቱ መካከል አዲስ ውጥረት ሊፈጥር እንደሚችል ስጋቶች እየተደመጡ ነው። በተለይ በፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካላት እና የቀድሞ የድርጅቱ አመራሮች ውሳኔውን ተቃውመውታል። ለምሳሌ አቶ ጌታቸው ረዳ ይህ እርምጃ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ የሚጥልና አዲስ ግጭት ሊቀሰቅስ የሚችል "የተናጠል ውሳኔ" ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ህወሓት ግን በበኩሉ ከጎረቤት ሕዝቦችና ከፌደራል መንግሥት ጋር ያለውን ልዩነት በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን እየገለጸ፣ የትግራይ ሕዝብ ግን ለህልውናው ሲል ከድርጅቱ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል።

#Update
" የታሰሩት ሰዎች 7 ድርሰዋል። ... እስካሁን ፍርድ ቤት የቀረቡት 2 ናቸው " - የቴዲ አፍሮ የስራ ባልደረባ (ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ)
➡ " ለጊዜው በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ መረጃ ለመስጠት አልችልም " - ፖሊስ
ከዚህ ቀደም የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አልበም "ኢቶሪካ" መውጣቱን ተከትሎ በዙሪያው ባሉ ሰዎች ላይ ጫና ስለመድረሱ፣ ምክትል ማነጀሩ ሃና ሰለሞን እና የረጅም ጊዜ ጓደኛው ዩሱፍ ያሲን መታሰራቸው መነገሩ ይታወሳል።
አሁን ላይ ከአርቲስቱ ጋር ቅርበት ያላቸውና በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ሰባት ስለመድረሳቸው የጀርመን ድምጽ ሬድዮ ጣቢያ (ዶቼ ቨለ) ዘግቧል።
ለሬድዮ ጣቢያው ቃላቸውን የሰጡ ስማቸው ይፋ እንዲደረግ ያልፈቀዱ ከቴዲ አፍሮ ጋር የቅርብ የሥራ ግንኙነት ያላቸው ግለሰብ " ተጨማሪ ሰዎች መታሰራቸን " ገልጸዋል።
" ከቅርብ ጓደኛው አቶ ዩሱፍ ያሲን እና አዲስ የሙዚቃ ሥራዎቹ በዩትዩብ መድረክ ማስታወቂያ እንዲታጀቡ አስፈላጊ ሂደቶችን ለማመቻቸት ጀምራ ከነበረው ወይዘሮ ማኅሌት ሰለሞን (በትክክለኛ ስሟ ሃና ሰለሞን) ሌላ ሁለት የቴዲ አፍሮ ስቱዲዮ ጠባቂዎችም ታስረዋል " ብለዋል።
በተጨማሪም " ከአርቲስቱ ድረገጽ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን የሚሠራ አንድ ሰው፤ እንዲሁም ሞምባሳ በተደረገው የሙዚቃ ድግስ (ኮንሰርት) ላይ ተሳትፎ የነበራቸው ሌሎች ሁለት ሰዎችም በዚሁ ሰሞን ተይዘዋል " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
" የታሰሩት አዲስ አበባ ሲኤሚሲ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው የቴዲ አፍሮ ስቱዲዮ ጠባቂዎች ድርጊቱ በተፈጸመ ዕለት ሚያዝያ 15 ምሽት ሦስት ሰዓት ገደማ ስቱዲዮውን በዘረፉት አካላት ድብደባ ደርሶባቸዋል " ብለዋል።
" በዚህ ስፍራ ኤ እና ቢ ያሏቸው ሁለት ስቱዲዮዎች ነበሩ ፤ የተጠቀሱት አካላት በገመድ አምስተኛ ፎቅ ወደሚገኘው የአርቲስቱ ስቱዲዮ ለመግባት ሞክረው ሳይሳካላቸው ሲቀር በበር ለመግባት ሲሉ በመከላከላቸው ደብድበዋቸው ሰብረው በመግባት ከሁለቱም ስቱዲዮዎች ፦
- ሁለት ላፕ ቶፖች፤
- አራት ስፒከሮች፤
- የተለያዩ መሣሪያዎችን ወስደዋል " ብለዋል።
" የተሰባበሩ ነገሮችም አሉ በአጠቃላይ ስቱዲዮውን ከጥቅም ውጪ አድርገውት ወጥተዋል " ሲሉ አክለዋል።
ሆኖም ግን " በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን የሚዘዋወሩ ፎቶዎች እውነተኛ አይደሉም " ብለዋል።
" ከታሠሩት ውስጥ እስካሁን ፍርድ ቤት ሁለቱ ማለትም አቶ ያሲን እና ወ/ሮ ማኅሌት (ወ/ሮ ሃና) ብቻ ቀርበዋል። በእነሱ ላይም ፖሊስ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል " ሲሉ እኚሁ የአርቲስቱ የስራ ባልደረባ ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።
ፖሊስ ምን አለ ?
የጀርመን ድምጽ ሬድዮ ከፌደራል ፖሊስ መረጃ ለማጣራት ጥረት ማድረጉን ገልጿል።
ስለታሠሩት እንዲሁም ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀን ጊዜ ተጠየቀባቸው ስለተባሉት ሰዎች በተመለከተ የተጠየቁት የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጀላን አብዲ ፤ " ለጊዜው በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ መረጃ ለመስጠት አልችልም " ሲሉ መልሰዋል።
ከዚህ ቀደም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለ ስቱዲዮ ዝርፊያውና እየተደረገ ነው ስለተባለው ጫና ያነጋገራቸው በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምርያ የወንጀል ምርመራ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ አብዲሳን ፤ " የፌደራል ፖሊስ እንደዚህ አይነት ውንብድና አይሰራም። ስብእናውም አይደለም። የሚሰራው በህግና በህግ ብቻ ነው " ሲሉ መልሰዋል።
" ብዙ ኦፕሬሽኖችን እንሰራለን በነዚህ ኦፕሬሽኖች ውስጥ ከእሱ (ከቴዲ አፍሮ) ጋር የሚገናኙ እኛ ያደረግነው ነገር የለም " ሲሉም ገልጸዋል።
" ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪ እንዳልሆነ ፣ በእሱ ላይ ምንም አይነት ምርመራ እንዳልተደረገ / የምርመራ ስራ እንዳልተሰራ ፣ እንዲሁም ከእሱ ጋር የሚገናኝ ጥቆማ ለፖሊስ እንዳልደረሰውና ፌዴራል ፖሊስ እሱ ላይ አንድም ነገር እንዳላደረገ ፤ ህዝቡም ይሄን እንዲያውቅ " ነበር የገለጹት።
ኮሚሽነር ሙሊሳ አብዲሳ " እሱ አርቲስት ነው ሙዚቃውን አውጥቷል ፤ ቤቱ ነው ያለው በስርዓት እየኖረ ነው ያለው ፤ በእሱ ላይ የተደረገ ምንም አይነት ነገር የለም። ... የሙዚቃ መሳሪያው ተወሰደ ተብሎ የተወራውም ውሸት ነው ፎቶውም AI ነው " ሲሉ ገልጸው " ሌላ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች እሱን መጠቀሚያ ለማድረግ እየሰሩ ነው " ብለው ነበር።
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከአልበሙ መውጣት ጋር ተያያዞ እስካሁን እየተነሱ ስላሉት ጉዳዮች በይፋ በማኔጅመንት ክፍሉ በኩል የሰጠው ማብራሪያ የሌለ ሲሆን የሚሰጥ ከሆነ ተከታትለን እናቀርባለን።
ሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ/ም
#TikvahEthiopia

ዲላን ፔጅ በዓድዋ ሙዚየም
በሚሊዮኖች ዘንድ “የዜና አባት” በሚል የሚታወቀውና ከ19.3 ሚሊዮን በላይ የቲክቶክ ተከታዮች ያሉት የእንግሊዝ ዲጂታል ጋዜጠኛና የይዘት ፈጣሪ ዲላን ፔጅ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎብኝቷል።
ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ “በቅኝ አገዛዝ ስር ወድቃ የማታውቅ ሀገር” በማለት ስለ ኢትዮጵያ ያለውን ጥልቅ አድናቆት የገለጸው ዲላን፣ በመታሰቢያው በአካል ተገኝቶ ባየውና በሰማው የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ታሪክ መደመሙን ተናግሯል። በጉብኝቱ ወቅት ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን፣ የታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሎጎ ያለባቸው ልዩ ስጦታዎች የተበረከቱለት ሲሆን፤ የኢትዮጵያን ባህላዊ ቡናም አጣጥሟል።
ከዚህ ቀደም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ “በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የሚቀይረው የአፍሪካ የብርሃን ተስፋ” በሚል ርዕስ በሠራው ቪዲዮ የኢትዮጵያውያንን የአንድነት መንፈስ ለዓለም ያስተዋወቀው ዲላን፣ አሁን ላይ የዓድዋን ታሪክ በአካል መጎብኘቱ ለሀገሪቱ ዲጂታል ዲፕሎማሲና ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ አቅም ይፈጥራል። ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነው ወጣት፣ በመታሰቢያውና በሌሎች የቱሪስት መዳረሻዎች ያደረገውን አስደናቂ ጉብኝት እንዲሁም የኢትዮጵያን እውነተኛ ገጽታ በቀጣይ ቀናት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ ተከታዮቹ በሶሻል ሚዲያ ገጾቹ እንደሚያጋራ ይጠበቃል።