በአምስተኛነት የሚያዝ አለ (Bening) በቅርቡ የመጣ። ያላቸውን ቁስና ማንኛውንም ነገር የሚያስቆጥሩ የሌሎቹን የሚያናንቁ። እነሱ የሚቀቡት ሽቶ ማንም የሌለው እንደሆነ የሚነዱት መኪና ሱፍ ማንም የሌውወ መሆኑን የሌሎቹ ቁስ ተራና ርካሽ መሆኑን የሚያሳዩ ስለሚበሉት ምግብ ውድነት በየቀኑ በየደቂቃው የሚያዳንቁ የሚያወሩ።
የ Narcissism Personality Disorder ዋና ዋና ምልክቶች ከሚባሉት በዋናነት 9 ምልክቶች ይጠቀሳሉ።
1. Lack of empathy ( ርህራሄ ያለማሳየት) : በዚህ በ Narcisstic የተጠቁ ሰዎች ለሌሎች ሰዎት ሀዘኔታና ርህራሄ የላቸውም። በድለዋችሁም ወይ በነሱ ምክንያት እናንተ ችግር ገብታቹሁም ህይወታቹህ ተመሰቃቅሎ ምንም ርህራሄ አይሰማቸውም። ትዳር ውስጥ ወይ ለልጆቻቸውም ስሜት አልባ የመሆን ችግር ይታይባቸዋል። ብዙ ጊዜን ችግር ከ Psychopath ጋር የሚያገናኙበት መንገድ አለ ልዩነቱ psychopath ከነጭራሹን ርህራሄና ሀዘን የማይሰማቸው ሲሆን ናርሲስቲክ ችግር ያለባቸው ግን ስለድርጊታቸው አልፎ አልፎ ሀዘን ውል ሊልባቸው ይችላል።
2. Entitlement : ከሌሎች የተለዩ እንደሆኑ ማሰብ። እኔ የተሻለ ትኩረትና እንክብካቤ ማግኘት አለብኝ። ልዩ በመሆኔ እኔን ብቻ እንክብካቤ ይገባኛል የሚል አጀባና እንክብካቤ የሚሹ ናቸው።
3.Grandiosity behavior : ስለራሳው ያላቸው ግምት ከነባራዊው ሁኔታ ጋር የማይገጥምና ስለራሳቸው ያላቸው ግምት መሬት ላይ ካለው የማይገናኝ ከልክ በላይ የተጋነነ ነው። ህልማቸው ከሁሉ የበላይ የሆነ ያክል ይሰማቸዋል። ግን በውኑ አለም ያለው የራሳቸው አቅምና እውቀት ከዛ ያነሰ ነው።
4. Superficiality : ሁሉ ነገራቸውን ከሚኖሩበት መኖሪያ ግዝፈት ፣ ከሚበሉት ምግብ ውድነት ፣ ከሚለብሱት ልብስ ፣ ጫማ ፣ መኪና ወዘተረፈ የሚለኩ ከዛ በስተጀርባ ያለውን ማንነታቸውን የማያሳዩ በውጪው ነገር ብቻ ለራሳቸውና ለሰዎች ግምት የሚሰጡ ናቸው።
5. Chronic seeking of admiration : ይሄኛው የማይቋረጥ ውደሳ ሙገሳ መቀበል የሚሹ ናቸው። አንተኮ ትለያየህ ፣ ካንተ ውጪ ሰው ለምኔ ፣ ዛሬ ደሞ ያደረከው ድንቅ ነው እያላቹህ በሚሰሩት እያንዳንዱ ነገር እየተከተላቹሁ ማቆለጳጳስ አለባቹህ። ይሄ በዚህ ባለንበት like, comment and share እየቆጠሩ የሚደሰቱና like በቀነሰ ቁጥር አለማቸው የሚጨልምባቸው አይነተኞች ናቸው።
6. Tendency to rage : ይሄኛው ባህሪ ከነሱ ሀሳብ ጋር ካልተስማማቹህ እና እነሱን እሺ ካላላቹህ ስሜታቸውን ቁጣቸውን መቆጣጠርና መግራት የሚቸግራቸው ናቸው። በትንሹ ነገር እያንባረቁ ሊያሸብሯቹህ ይችላል። ትዕግስት እና መረጋጋት የተሳናቸው ናቸው። እንዲህ አድርጉ ብለው ከዘገያቹህ በቁጣ በጩኸት መድረሻ ያሳጧቹሀል። ብዙ ጊዜ አለቆች የሚታይባቸው ችግር ነው።
7. Arrogance : ይሄኛው ደሞ በቃ ከኔ በላይ አንተ ታውቃለህ? ማነው ከኔ በላይ አዋቂ? የሚሉ ሁሉም ነገር ላይ ከነሱ በላይ አዋቂ ያለ የማይመስላቸው ሰዎች ናቸው። ምንም በማያውቁት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ፕሮፌሰሩን እከሌኮ መሀይም ነው ሊሏቹህ ይችላል። በግልፅ እኔ ካንተም ከማንም በላይ ነኝ ይላሉ በድፍረት እውነታው የተገላቢጦሽም ሆኖ።
8. High or low self esteem : ይሄኛው ከልክ ያለፈ በራስ መተማመን ወይ ዝቅ ያለ ይኖራቸዋል።
9. Envy and satisfaction by others suffering : ከፍተኛ የሆነ ቅናት ይሰማቸዋል። ሰው ሲሳካለት ይደብራቸዋል ፍቅረኛቸውም ሊሆን ይችላል። በሌሎች ሰዎች ስቃይና ሀዘን ከነሱ ጋር ጠላት ባትሆኑም በስቃያቹ ሊደሰቱ ይችላሉ ማግኘታቹህ ያንገበግባቸዋል።
ሌሎችም ብዙ አሉ ግን አብዛኛዎቹን ናርሲስቲክ ሰዎች የሚያመሳስላቸው እነዚህ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ቢያንስ አምስቱ ምልክቶችን በራሳቹህ ላይ የምታዩ ከሆነ ይህ ችግር እንዳለባቹህ አምናቹህ counseling መጀመር ነው ያለባቹህ።
ይሄ የ Narcissism Personality Disorder ችግር መነሻው ከየት ነው? ወይ አባባሹ ምንድነው? ካላቹህ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል። Nature (በተፈጥሮ) vs Nurture (በመማር) ቤተሰብ የሚቀርፅበት ወይ የሚያሳድግበት መንገድ ማለት ነው። አብዛኛውን ድርሻ የሚወስደው ከተወለድን በኋላ ያለው የ አስተዳደግ ውጤትና ልምምድ ነው።
Nature (በተፈጥሮ) አንዳንድ ልጆች በተፈጥሮ በ Biological dysfunction ከሌሎች ጋር ያላቸው መስተጋብር የላላ ሊሆን ይችላል ያም ባህሪያቸው በቤተሰብ እንክብካቤና ፍቅር ካልተያዘ ችግሩን ሊያባብሰው ይችላል።
የቤተሰብ አስተዳደግ ዘዴ (Attachment styles) ወሳኝ ነው። ከ 4ቱ የ attachment style ልጆች Avoidant attachment እና Neglect Attachment ያለበት ቤት ውስጥ የሚያድጉ ልጆች በልጅነታቸው Sensitive ሲሆኑና emotinal ሲሆኑ ለዛ ስሜታቸው ሲያድጉምላሽ የማያገኙ ከሆነ የ NPD የመጠቃት እድላቸውን የሰፋ ያደርገዋል።
በ Modeling (አርዕያ) : የ ናርሲስቲክ ቤት ውስጥ የሚያድጉ ልጆች ወላጆቻቸውን በመኮረጅ ባህሪያቸውን ይወስዳሉ።
Conditional love : ልጆች የሆነ ስራ ስለሰሩ ብቻ ቤተሰብ ደስ የሚለውን ስላደረጉ የምናመሰግናቸውና የምንወዳቸው ከሆነ ለመወደድ ብለው ወይ ይሁንታ ለማግኘች ያልተገባ ነገር ለማድረግ ይነሳሳሉ። Communal narcissism ብዙ ጊዜ ከዚህ ጋር ትስስር አለው።
Extrinsic focus : ልጆችን በውጫዊው አለም ብቻ ለነሱ ቦታ መስጠት ለምሳሌ ትምህርት አንደኛ ስለወጡ የሆነን ነገር ስላሸነፉ በዛ ነገር ብቻ እነሱን ገድበን የምናወድስና በውጪው አለም ባሳኩት ነገር የምናወድስና የምንወስናቸው ከሆነ ትልቅም ከሆኑ በኋላ በ tik tok like IG Fb like and comment እራሳቸውን የማያያዝ ችግር ላይ ይወድቃሉ።
NPD አብዛኛውን ጊዜ ከ Boarder line disorder, sociopath, Depression, paranoid disorder ጋር የመያያዝ እድሉ ሰፊ ነው።
ይህን ችግር እንደማንኛውም የ ማንነት ችግሮች በ Counseling እንዲሻሻል ለማድረግ ይቻላል። በ Dr. Ramania ገለፃ መሠረት በ አሜሪካ ውስጥ 6 ሰዎች 1 ሰው የ ናርሲስቲክ ህመም ተጠቂ እንደሆነ ይታሰባል። በ DSM መሠረት በ community sample 6.2% እንደሆነ ይታሰባል።
@ourrthought

🔥7❤5
የኢትዮጵያ ህዝብ የእውቀትን ጥቅም በደንብ ለመገንዘብ ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩት ፤ ትልቁና ቁልፉ የ እውቀት መንገድ ጽሕፈት ነው ፤ ፊደል ነው ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የራሳችን ፊደል ነበረን ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የራሳችን በበሬዎች የማረስ ዘዴ ነበረን ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት በአጋሜ ፤ በየጁ ፤ በኮንሶ የእርከንና የመስኖ ዘዴዎች ነበሩን ፤ ለምዕተ-ዓመታት ታላላቅ ሐውልቶችንና ሕንፃዎችን የመሥራት ጥበብ ነበረን ፤ ከብዙ ምዕተ-ዓመታት በፊት በሰረገላ እንጠቀም ነበር ፤ ለብዙ ዘመናት መፍተልና መሸመን የታወቀ ነበር ፤ ይህ ሁሉ ዘዴ እንደ እውቀት በጽሑፍ አልተላለፈም ፤ ስለዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ አህያ ከመንዳትና በጎጆ ውስጥ ከመኖር ያልወጣበት ምክንያት ምንድን ነው?
አዳፍኔ ፍርሀትና መክሸፍ
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
@ourrthought
በኢትዮጵያ ውስጥ እውቀት ፈላጊ አልነበረውም ፤ አሁንም የለውም።
አዳፍኔ ፍርሀትና መክሸፍ
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
@ourrthought
❤9🔥2
ሐሳቦቻችን
የኢትዮጵያ ህዝብ የእውቀትን ጥቅም በደንብ ለመገንዘብ ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩት ፤ ትልቁና ቁልፉ የ እውቀት መንገድ ጽሕፈት ነው ፤ ፊደል ነው ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የራሳችን ፊደል ነበረን ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የራሳችን በበሬዎች የማረስ ዘዴ ነበረን ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት በአጋሜ ፤ በየጁ ፤ በኮንሶ የእርከንና የመስኖ ዘዴዎች ነበሩን ፤ ለምዕተ-ዓመታት ታላላቅ ሐውልቶችንና ሕንፃዎችን የመሥራት ጥበብ…
ስለ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ካነሳን አይቀር አንድ የምወደው ጨዋታ አለች።
«ኬንያ ናይሮቢ አንዲት መዝናኛ ቤት ተገኝቼ እየተዝናናሁ ነው። ቤቱ እንደ ፓርቲ ቤት ያለ ነው። ባንዱ ጥግ መጠጤን ይዤ፣ የዳንሱ ወለል ላይ ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚደንሱ ወጣቶችን አያለሁ። በዚህ መሃል የባሕር ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ እንግሊዛዊያን ነጮች ገቡ። አንዱ እንግሊዛዊ ቀጥታ ወደ ዳንስ ወለሉ ሄደና ከወዳጁ ጋር እየደነሰ ያለውን ኬንያዊ በካልቾ መታው። ኬንያዊው ተርበድብዶ የሴት ወዳጁን ጥሎ ገሸሽ አለ። እንግሊዛዊውም ከዛች ኬንያዊት ጋር መደነስ ጀመረ። በእንግሊዛዊው ድርጊት በጣም ተናደድኩ። ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁና ወደ ዳንስ ወለሉ አመራሁ። እኔም እንግሊዛዊውን በካልቾ ጠልዤ ኬንያዊቷን ተቀበልኩ። ጥቂት ካስደነስኳትም በኋላ ለተቀማው ኬንያዊ አስረከብኩ። ይህን ፈፅሜ ወደ መቀመጫዬ ሳመራ እንግሊዛዊው የጠየቀኝ አንድ ጥያቄ ነበር ፦ "ኢትዮጵያዊ ነህ?" የሚል።»
ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ነብሳቸው በሰላም ትረፍ ባሉበት ይመቻቸው።

❤9🔥2😁2🙏2
ቅድም ከ አንድ ኢ-አማኝ (Atheist) ጋር እያወራሁ ምን አለኝ
"እንደውም አለም ላይ ላለ ችግር ሁሉ ተጠያቂው ፈጣሪ ነው።" እኔም ቢቸግረኝ
"ፈጣሪ የለም ብለህ ካመንክ አሁን ከየት አገኘኸው?"
ፈጣሪ ከሌለ መውቀስ ይቻላል?

😁9👏2
ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥለሴ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ይህ ፎቶ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ በ እስር ላይ እያሉ የተነሱት ነው። በወርቅ መታጠቢያ የታጠቡ በቅንጦት የኖሩ ንጉሠ ነገስት በመጨረሻዎቹ ሰዐታት ግን በአንዲት ጣውላ ወንበር ላይ ተክዘው ማየት ልብ የሚሰብር ነው።

😢7😭1
ሐሳቦቻችን
Photo
The Logical Problem of Evil (የሎጂክ የመከራ ጥያቄ)
በጄ.ኤል. ማኪ (J.L. Mackie) እና በአልቪን ፕላንቲንጋ (Alvin Plantinga) መካከል የተደረገ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተካሄዱት ታላላቅ የሃይማኖት ፍልስፍና (Philosophy of Religion) ክርክሮች አንዱ ነው::
አውስትራሊያዊው ኤቲስት ፈላስፋ ማኪ 'Evil and Omnipotence' በተሰኘው ታዋቂ ጽሁፉ የሚከተለውን ጥንካሬ ያለው የሎጂክ አጣብቂኝ አቀረበ፦
- እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው (Omnipotent):
- እግዚአብሔር ፍጹም ደግ/ርህሩህ ነው (Wholly Good):
- መከራ/ክፋት በዓለም ላይ አለ (Evil exists)
ማኪ እንደተናገረው እኚህ ሶስት ሀሳቦች በአንድ ላይ ሲቀመጡ በሎጂክ እርስ በእርሳቸው ይጋጫሉ (Logical Contradiction)::
የማኪ ዋና ጥያቄ፦ 'አንድ ፍጹም ደግ የሆነ አካል በተቻለው መጠን ክፋትን ያጠፋል::ሁሉን ቻይ የሆነ አካል ደግሞ ማድረግ የማይችለው ነገር የለም::ስለዚህ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እና ፍጹም ደግ ከሆነ ክፋት በፍጹም ሊኖር አይችልም ነበር::ነገር ግን ክፋት አለ: ስለዚህ ሁሉን ቻይ እና ፍጹም ደግ የሆነ ፈጣሪ በሎጂክ ደረጃ ሊኖር አይችልም::'
ማኪ የነፃ ፈቃድን (Free Will) ሀሳብ ውድቅ ሲያደርግም፦ 'ሁሉን ቻይ ፈጣሪ ሰዎችን በነፃ ፈቃዳቸው ሁልጊዜ መልካም ነገርን ብቻ የሚያደርጉ አድርጎ መፍጠር ይችል ነበር::ያንን አለማድረጉ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ወይም ደግ አለመሆኑን ያሳያል' አለ::
አሜሪካዊው ክርስቲያን ፈላስፋ አልቪን ፕላንቲንጋ 'The Nature of Necessity' በሚለው መጽሐፉ ለተጠየቀው ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ሰጠ::ፕላንቲንጋ የማኪን መከራከሪያ ለማፍረስ የሞከረው 'የሎጂክ ወሰን' እና 'የነፃ ፈቃድ'( Free will defense )ባህሪ ላይ በማተኮር ነው፦
አንደኛ በሎጂክ የማይቻሉ ነገሮች (Logical Impossibilities)ፕላንቲንጋ እንዳለው በፍልስፍና እና በሎጂክ ህግ 'በሎጂክ የማይቻል ነገር' የሚባለው የፈጣሪ የአቅም ማነስ ሳይሆን: የሀሳቡ ወይም የቃላቱ ራሱ እርስ በእርስ መጋጨት እና ትርጉም አልባ መሆን ነው:: ለምሳሌ ኢአማንያን 'ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ከሆነ ራሱ ሊሸከመው የማይችለውን ድንጋይ መፍጠር ይችላል?' የሚል አጣብቂኝ ጥያቄ ያነሳሉ:: ነገር ግን 'ሁሉን ቻይ አካል' እና 'እሱ ሊሸከመው የማይችለው ድንጋይ: የሚሉት ሁለት ሀሳቦች በቃላት ደረጃ እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ተቃራኒ ሀሳቦች ናቸው:: ሁሉን ቻይነት (Omnipotence) ማለት በሎጂክ ሊከናወኑ የሚችሉ ነገሮችን በሙሉ ማድረግ እንጂ: እንደ 'ባለ አራት ማዕዘን ክበብ' ወይም 'ሊሸከሙት የማይችሉት ድንጋይ' ያሉ ትርጉም አልባ እና እርስ በእርስ የሚቃረኑ ሀሳቦችን መፍጠር ማለት አይደለም:: ስለዚህ ነገሩ ያልተደረገው ፈጣሪ የመሸከም ወይም የመፍጠር አቅም አጥቶ ሳይሆን: ሀሳቡ በራሱ በሎጂክ ደረጃ የማይቻል ስለሆነ ነው::
ሁለተኛ ነፃ ፈቃድ እና በግድ ማሰራት(Transworld Depravity)
አንድ ሰው 'እውነተኛ ነፃ ፈቃድ' አለው ከተባለ ያንን ሰው 'በግድ ሁልጊዜ መልካም ብቻ እንዲመርጥ ማድረግ በሎጂክ እርስ በእርሱ የሚጋጭ (Contradiction) ነው!ፈጣሪ ሰዎችን በግድ መልካም ብቻ የሚያደርጉ አድርጎ ቢፈጥራቸው ኖሮ ሰዎች ነፃ ፈቃድ ያላቸው ፍጡራን አይሆኑም ነበር:: እውነተኛ ነፃ ፈቃድ ለመስጠት ደግሞ ሰዎቹ የመሳሳት እና ክፉ የመምረጥ እድል/አማራጭ ሊኖራቸው ይገባል::
በስተመጨረሻም የፕላንቲንጋ ድምዳሜ 'እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ቢሆንም እንኳ ነፃ ፈቃድ ያላቸውን ፍጡራን ፈጥሮ በዚያው ቅጽበት በግድ መልካም ብቻ እንዲሰሩ ሊያደርጋቸው አይችልም::ስለዚህ የክፋት/መከራ መኖር የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት ወይም ፍጹም ደግነት በሎጂክ አይቃረንም::' የሚል ነው::
በፍልስፍናው ዓለም ይህ ክርክር ከተጠናቀቀ በኋላ በሰፊው የታመነበት ውጤት የፕላንቲንጋን አሸናፊነት ሚያስረግጥ ነው:: አብዛኞቹ የአካዳሚክ ፈላስፎች (ኢ-አማንያንን ጨምሮ) ፕላንቲንጋ 'የሎጂክ የመከራ ጥያቄን'(The Logical Problem of Evil) ሙሉ በሙሉ ማፍረሱን ተቀብለዋል::ማኪ ራሱ በበኩሉ የፕላንቲንጋ ምላሽ የነበረበትን የሎጂክ አጣብቂኝ እንደፈታው በኋላ ላይ አምኗል::ግን ይህ ውጤት ክርክሩን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዛውሮት ነበር የተቋጨው ::የፕላንቲንጋ 'Free Will Defense' የሎጂክ አጣብቂኙን ቢፈታውም ኢ-አማንያን ክርክሩን ከሎጂክ ጥያቄ ወደ 'Evidential Problem of Evil' (የመከራው መጠን እና አይነት አሳማኝነት) አዞሩት።
በጠቅላላው ማኪ 'እግዚአብሔር እና ክፋት በሎጂክ አብረው ሊኖሩ አይችሉም' ብሎ ሲሞግት ፕላንቲንጋ ደግሞ 'በነፃ ፈቃድ ምክንያት ሁለቱ በሎጂክ አብረው ሊኖሩ ይችላሉ' በማለት ክርክሩን በበላይነት አጠናቋል።
Evidential Problem of Evil (በማስረጃ ላይ የተመሰረተው የመከራ ጥያቄ)
በፍልስፍና እና በሃይማኖት ጥናት (Theology) ውስጥ 'መከራ እና ፍጹም ፈጣሪ በሎጂክ አብሮ መኖር አይችሉም' ከሚለው ይልቅ 'በዓለም ላይ ያለው የመከራ መጠን: አይነት እና ከንቱነት ፈጣሪ የመኖሩን እድል በጣም ያቀጥነዋል/ያሳንሰዋል' የሚል መከራከሪያ ነው::
አልቪን ፕላንቲንጋ 'ፈጣሪ እና መከራ በሎጂክ ደረጃ አብረው ሊኖሩ ይችላሉ' ብሎ ማስመስከሩን ተከትሎ: ኢ-አማንያን (Atheists) መከራከሪያቸውን ከቀጥታ የሎጂክ ግጭት ወደዚህ በማስረጃ/በእድል (Probability) ላይ የተመሰረተ የአመንክዮ አቀራረብ አዞሩት:-ሁሉን ቻይ: ሁሉን አዋቂ እና ፍጹም ርህሩህ የሆነ ፈጣሪ ካለ :ያለ በቂ/መልካም ምክንያት የሚከሰት ህመም ወይም መከራ እንዲኖር አይፈቅድም! ነገር ግን በዓለም ላይ ምንም አይነት መልካም ነገር የማይወጣቸው: ከንቱ እና እጅግ በጣም አሰቃቂ የሆኑ የመከራ አይነቶች (Gratuitous Evils) አሉ:: ስለዚህ ሁሉን ቻይ እና ፍጹም ርህሩህ የሆነ ፈጣሪ የመኖር እድሉ እጅግ በጣም አነስተኛ ነው (ወይም የለም)::
ይህንን መከራከሪያ በስፋት ወደ ፍልስፍና ዓለም ያመጣው አሜሪካዊው ፈላስፋ ዊልያም ሮው(William Rowe) ሲሆን:ሀሳቡን በሁለት ታዋቂ ምሳሌዎች ያስረዳል፦ የመጀመሪያው የጫካው ሚዳቆ (The Fawn in the Forest)ነው ::ሰው በማይደርስበት የራቀ ደን ውስጥ የመብረቅ አደጋ አጋጥሞ ሰደድ እሳት ይነሳል::በዚያ እሳት ውስጥ አንድ የዱር ሚዳቆ በጽኑ ተቃጥሎ ለቀናት እየተሰቃየ ይሞታል::
ይህ መከራ የሰውን ነፃ ፈቃድ አይመለከትም:: ለማንም ሰው ትምህርት ወይም 'የነፍስ ማነፅያ' አይሆንም: ምክንያቱም ማንም አላየውምና::ጥያቄውም: ሁሉን አዋቂ እና ርህሩህ ፈጣሪ ይሄን አሰቃቂ ህመም ሚዳቆዋ ሳትሰቃይ ቀጥታ እንድትሞት ማድረግ ወይም ማስቀረት አይችልም ነበር? ነው::
ሁለተኛው ምሳሌ ደሞ የህፃናት መበደል/መሰቃየት ነው::በንጹሃን ህፃናት ላይ የሚደርሱ አሰቃቂ ጥቃቶች በሽታዎች እና ሰቆቃዎችን ኃላፊነት ማን ይወስዳል? የሚል::

❤7🔥2
ለዚህ Evidential Problem of Evil እሳቤ አማንያን እና የሃይማኖት ፈላስፎች መከራከሪያ ሚሆኑ ሶስት ዋና ዋና ምላሾችን ይሰጣሉ፦
አንደኛ Skeptical Theism (የሰው ልጅ እውቀት ውስንነት) ሲሆን :ሀሳቡ፦ እኛ የሰው ልጆች የፈጣሪን ሙሉ እቅድ እና ትልቅ ምስል (Big Picture) የማየት አቅም የለንም::ለምሳሌ፦ አንድ ትንሽ ልጅ ሀኪም መርፌ ሲወጋው ሀኪሙ ያለ ምክንያት የሚያሰቃየው ይመስለዋል::ምክንያቱም መርፌው ከከፋ በሽታ እንደሚጠብቀው የመረዳት አቅም ስለሌለው ነው:: እኛም አንድ መከራ 'ከንቱ ነው' ብለን ስንደመድም ከጀርባው ያለውን አጠቃላይ ምክንያት የማወቅ ውስንነት ስላለን ሊሆን ይችላል::
ሁለተኛ Greater Good Defense (ታላቁ መልካም ነገር) ፈጣሪ አንዳንድ አሰቃቂ መከራዎችን የሚፈቅደው: ከእነዚያ መከራዎች በስተጀርባ የበለጠ ታላቅ መልካም ነገር (Greater Good) ስለሚወጣ ወይም ከእዚያ የከፋ ነገር ስለሚከለክል ነው የሚል መከራከሪያ ነው::
ሌላኛውና ሶስተኛው Theistic Evidence (የፈጣሪ ህልውና ሌሎች ማስረጃዎች) ሲሆን: የመከራ ጥያቄ ብቻውን አይቆምም:: የዓለም መፈጠር: የፊዚክስ ህግጋት ውስብስብነት (Fine-tuning): የሞራል ህጎች መኖር እና የህይወት አመጣጥ ፈጣሪ የመኖሩን እድል እጅግ በጣም ከፍተኛ ያደርጉታል:: ስለዚህ ሌሎች ሚዛኖች ፈጣሪ እንዳለ የሚያሳዩ ከሆነ: የመከራን ምክንያት ሙሉ በሙሉ ባናውቀውም ፈጣሪ የለም ወደሚል መደምደሚያ አንደርስም::
16/11/2018 ዓ.ም
By ሀኑ-ን

🔥8❤3😁1
ሐሳቦቻችን
Photo
አንድ አንዴ ውስጤ ያለሁ ሀሳብ ልክ እንደ ማዕበል ይንጠኛል። ሲብስበት ደግሞ ልክ እንደ ወተት ገንፍዬ ካሎጣው ይለኛል። ዝም ካልኩት በዛው ይጠፋል እና ከመጥፋቱ በፊት ብዕሬን አንስቼ እሞነጫጭረዋለሁ ካልሆነ ሰላም አይሰጠኝም። የሆነ ጊዜ አለማየሁ ገላጋይ የማከብረው ደራሲ የሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ እንዲህ ሲል ሰምቼዋለሁ፤
"እኔ ብዙ ጊዜ መፅሀፍ ከመፃፌ በፊት በ አእምሮዬ ታሪኩን ጀምሬ እጨርሰዋለሁ ከዛን በኋላ ነው በወረቀት የማሰፍር ፣ እስከዛሬ አንድ ሶስት የሚሆኑ ሙሉ ያለቁ ልብወለድ መፅሀፍ አእምሮዬ ውስጥ ጠፍቶብኛል" ያለውን አልረሳውም፣ እኔም ሀሳቤ እንደንጋት ጤዛ ከመጥፋቱ በፊት ልፅፈው ብዕሬን አንስቼ መሞነጫጨር ጀመርኩ።
"ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እነሆ ለሀገራችን ክብር ብለው ህይወታቸውን አሳልፈው ከሰጡ 86 ዓመታትን አስቆጠሩ።" እያለ ሬድዮኑ ይለፈልፋል። እኔም በዛው በሀሳብ ባህር ጭልጥ ብዬ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም የሽምጥ የኋሊት ጋለብኩና በምናቤ አቡነ ጴጥሮስ ጋር ተሰየምኩ።
ወቅቱ ዳግም ጣሊያን ወረራ ላይ ነበር። ቂጡን በሳንጃ ተወግቶ ከተባረረ በኋላ አርባ አመታትን ቆይቶ ዳግም ለበቀል የመጣበት ወቅት ነበር። ታዲያ የዛን ጊዜ ህዝቡ ሁሉ በአንድነት የሚሰማቸው፣ የሚያከብራቸው እና የሚወዳቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ነበር። ታዲያ ይሄን የተገነዘበው ግራዚያኒ አቡነ ጴጥሮስ ዘንድ ሄዶ ህዝቡን ከጣሊያን ጎን ሆኖ እንዲያስገዙት ህዝቡ እንዲታዘዝ እሳቸውም የተሻለ ነገር እንደሚያገኙ ነገራቸው።
እሳቸውም " ጣሊያንን ተቀበሉ ብዬ አልሰብክም፣ እንኳን ህዝቡ መሬቱ እንዳይታዘዝ ብዬ አውግዤዋለሁ" አሉ። ግራዚያኒም ህዝብ በተሰበሰበበት አስረሽኖ ገደላቸው።
እንኳንም ዛሬ ላይ አልሆነ ብዬ ፈጣሪን አመሰገንኩት። ለምን አትሉም!? አሁን ዘመን ላይ ቢሆን ደግሞ ግራዚያኒ ሳይሆን ህዝቡ ነበር 'ሚረሽናቸው። የስልጣኔ ፀር፣ እኛ እንዳናድግ እንቅፋት ሊሆኑብን ነው፣ የድሮ ናፊቂ! ብሎ ሲያበሻቅጣቸው ሳልኩትና ዘገነነኝ፣ እንኳንም የዛኔ ሆነ ሆሆሆ።
ግራዚያኒ ህዝቡን "ጠላታችን ስለሞተ አጨብጭቡ።" አላቸው። ህዝቡም በጭብጨባ አቀለጠው አሉ ይሄ አጨብጫቢ ህዝብ! ለገዳዩም ላስገዳዩም እንዳጨበጨበ ይሄው እስከአሁን አለ። የእነሱ ልጆች ዛሬም ድረስ በየስብሰባው በየፓርላማው እንዳጨበጨቡ ነው አሉ። አይ አንቺ ሀገር ስንት ጠባቂ ልጆችሽን በጭብጨባ ሸኘሽ!፣ መች ይሁን ማጨብጨቡ የሚበቃሽ!? መዳፍሽ ለጠላቶችሽ ማጨብጨቡን ትቶ ሰይፍ የሚጨብጠው! መች ይሆን ልጆችሽን መገበር የሚበቃሽ? እንጃልሽ!።
በአንድ ወቅት የሆነ ፍልስፍና ፀጣፍ ላይ የቃረምኩት ትዝ አለኝ። " በአንድ ወቅት ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ እስራኤል ከተማ ሲመጣ በመንገድ ያገኙት ሰዎች እየሱስን እየሰደቡ እየተፉበት እርሱ ግን በመካከላቸው ምንም ሳይናገር በዝምታ ያልፋል። ታዲያ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ነገሩን ሲከታተሉ ቆይተው ኖሮ ለምን ዝም እንዳለ ጠየቁት። በዚህ ጊዜ እየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው " ሰው ከቅርጫቱ ውስጥ የሚያወጣው ቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ነው። እነዚህም ሰዎች ከስድብና ጥላቻ ውጪ ሌላ ነገር አያውቁም አትፍረዱባቸው" ብሎ ነገራቸው።
አቤት! የዚህ ዘመን ቅርጫት ሲከፈት ውስጡን አሰብኩት። ዘረኝነት፣ እርኩሰት፣ ሴሰኝነት፣ ጥላቻ፣ ተንኮል ወዘተ ተጭቀውበት ታየኝ። ስንት ዘመን ከዚህ ቅርጫት እንደምንኖር እንጃ! ስንት ዘመን አዳኞቻችን ታዳጊዎቻችንን ከዚህ ቅርጫ እንደምንወረውርባቸው እንጃ! ማን ያውቃል!? ብቻ ተስፋ አልቆርጥም።
22/11/2014 ዓ.ም የተከተበ

🔥5❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንዳንዴ ዘመንን የሚቀድሙ ሰዎች አሉ። ጂጂ ከነዛ ሰዎች ውስጥ አንዷ ናት። ስራዎቿ ትንቢት የሆኑላት "እኔን የራበኝ ፍቅር ነው ብላ የዘር ቡካታችንን የተነበየች ፣ አባይን በሌላ መልኩ የገለጠች አረ ስንቱ። ብቻ ትቆጨኛለች።
@ourrthought
@ourrthought
🥰8❤3
Ethiopia by GIGI
fabfishsos
ሙዚቃ በዚህ ልክ እንደ ነብስ ምግብ ኩልል ብሎ ሲዎርድ ሀሴት ነው። ይህ ሙዚቃ የነብስ እነጂ የስጋ አይደለም።
@ourrthought
አይርብ አይጠማውም አይከፋውም ደሜ
ቢርበኝ በላለሁ ዶቅማውን እንኮይም ለቅሜ
ክፉም ንጉስ መጣ ደግም ንጉስ መጣኢትዮጵያ
ሁሉም ይሄዳሉ እንዳመጣጣቸው
ሳቅና ለቅሶሽን አይገዙትምና
አትፍሪ እናታለም ኑሪልኝ በጤና
@ourrthought
❤11🥰2
ማርጀትህን የምታውቀው የሆነ ቀን ታኪሲ ላይ ከረዳቱ ጋር ተናንቀህ አሮጌ ብር ነው የሰጠኸኝ ፣ ያረጀ ብር ነው ብለህ ስትጨቃጨቅ እራስህን ስታስተውል ነው። እድሜ ይጋልባል።
@ourrthought
@ourrthought
😁8🤣5👎2❤1🤨1
እንደውም ሲሲፈስ እድለኛ ነበር። የሚገፋው አንድ ቋጥኝ ብቻ ነበር። በዛ ላይ የመግፊያው አቅምም ነበረው። እዚህ ዘመን ላይ ቢሆን ኖሮ አማልክቱ ቅጣቱን አዘምነው የሚቀጡት ለዘላለም Tik tok ፣ Facebook ፣ IG ፣ TG ፣ X scroll እንዲያደርግ ነበር የሚቀጡት።
@ourrthought
@ourrthought
😁12❤3🤣3
ከጠዋት እስከማታ social media እየተጠቀማቹህ ጤነኛ የሆናቹህ ሰዎች እንኳን Disorder ቀርቶ Cancer ራሱ አይገላቹሁም። ሰማያዊ እገዛ አላቹህ በውነቱ።
በጌታ ስም አለ ያሬድ ነጉ ቀኑን ሙሉ social media ተጠቅሞ መሆን አለበት። ስካር በስንት ጣዕሙ። 🙌
@ourrthought
በጌታ ስም አለ ያሬድ ነጉ ቀኑን ሙሉ social media ተጠቅሞ መሆን አለበት። ስካር በስንት ጣዕሙ። 🙌
@ourrthought
😢7❤4👍1
አሁን አሁን እንደ ፋሽን እየመጣ ያለ ነገር ቢኖር የሚወለዱ ልጆችን ስም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እያወጡ በ 1250 የነበሩ አይሁዶች የቀበሌ ስም (Torah ላይ ራሱ የጠፉ) እያወጡ አይሁዶች ራሱ የማይጠሩበትን ስም ያወጣሉ። ትርጉሙ ምንድነው ሲባሉ ላባና ያዕቆብ የታረቁበት ቦታ ትኖር የነበረች ድንቢጥ ናት ምናምን ይላሉ።
ፅድቅ በስም ቢሆን ይሁዳ (የስሙ ትርጉም ታማኝ ነው) ነበር ቅዱስ። በዚህ ልክ ከማንነታችን መራቅም ያስተዛዝባል።
@ourrthought
ፅድቅ በስም ቢሆን ይሁዳ (የስሙ ትርጉም ታማኝ ነው) ነበር ቅዱስ። በዚህ ልክ ከማንነታችን መራቅም ያስተዛዝባል።
@ourrthought
😁8🤨5❤3
ሐሳቦቻችን
አሁን አሁን እንደ ፋሽን እየመጣ ያለ ነገር ቢኖር የሚወለዱ ልጆችን ስም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እያወጡ በ 1250 የነበሩ አይሁዶች የቀበሌ ስም (Torah ላይ ራሱ የጠፉ) እያወጡ አይሁዶች ራሱ የማይጠሩበትን ስም ያወጣሉ። ትርጉሙ ምንድነው ሲባሉ ላባና ያዕቆብ የታረቁበት ቦታ ትኖር የነበረች ድንቢጥ ናት ምናምን ይላሉ። ፅድቅ በስም ቢሆን ይሁዳ (የስሙ ትርጉም ታማኝ ነው) ነበር ቅዱስ። በዚህ ልክ…
"ነጮቹ መጀመሪያ ወደ አፍሪካ ሲመጡ እነሱ መፅሐፍ ቅዱስ እኛ መሬት ነበረን። መፅሐፍ ቅዱስ ሰጡንና አይናችንን ጨፍነን መፀለይ አስተማሩን። አይናችንን ስንገልጥ ግን እነሱ መሬት እኛ መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ነበረን።"
ቄስ ዴዝሞን ቱቱ
@ourrthought
ቄስ ዴዝሞን ቱቱ
@ourrthought
🔥5👍4❤1👎1