ሐሳቦቻችን
Photo
አንድ አንዴ ውስጤ ያለሁ ሀሳብ ልክ እንደ ማዕበል ይንጠኛል። ሲብስበት ደግሞ ልክ እንደ ወተት ገንፍዬ ካሎጣው ይለኛል። ዝም ካልኩት በዛው ይጠፋል እና ከመጥፋቱ በፊት ብዕሬን አንስቼ እሞነጫጭረዋለሁ ካልሆነ ሰላም አይሰጠኝም። የሆነ ጊዜ አለማየሁ ገላጋይ የማከብረው ደራሲ የሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ እንዲህ ሲል ሰምቼዋለሁ፤
"እኔ ብዙ ጊዜ መፅሀፍ ከመፃፌ በፊት በ አእምሮዬ ታሪኩን ጀምሬ እጨርሰዋለሁ ከዛን በኋላ ነው በወረቀት የማሰፍር ፣ እስከዛሬ አንድ ሶስት የሚሆኑ ሙሉ ያለቁ ልብወለድ መፅሀፍ አእምሮዬ ውስጥ ጠፍቶብኛል" ያለውን አልረሳውም፣ እኔም ሀሳቤ እንደንጋት ጤዛ ከመጥፋቱ በፊት ልፅፈው ብዕሬን አንስቼ መሞነጫጨር ጀመርኩ።
"ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እነሆ ለሀገራችን ክብር ብለው ህይወታቸውን አሳልፈው ከሰጡ 86 ዓመታትን አስቆጠሩ።" እያለ ሬድዮኑ ይለፈልፋል። እኔም በዛው በሀሳብ ባህር ጭልጥ ብዬ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም የሽምጥ የኋሊት ጋለብኩና በምናቤ አቡነ ጴጥሮስ ጋር ተሰየምኩ።
ወቅቱ ዳግም ጣሊያን ወረራ ላይ ነበር። ቂጡን በሳንጃ ተወግቶ ከተባረረ በኋላ አርባ አመታትን ቆይቶ ዳግም ለበቀል የመጣበት ወቅት ነበር። ታዲያ የዛን ጊዜ ህዝቡ ሁሉ በአንድነት የሚሰማቸው፣ የሚያከብራቸው እና የሚወዳቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ነበር። ታዲያ ይሄን የተገነዘበው ግራዚያኒ አቡነ ጴጥሮስ ዘንድ ሄዶ ህዝቡን ከጣሊያን ጎን ሆኖ እንዲያስገዙት ህዝቡ እንዲታዘዝ እሳቸውም የተሻለ ነገር እንደሚያገኙ ነገራቸው።
እሳቸውም " ጣሊያንን ተቀበሉ ብዬ አልሰብክም፣ እንኳን ህዝቡ መሬቱ እንዳይታዘዝ ብዬ አውግዤዋለሁ" አሉ። ግራዚያኒም ህዝብ በተሰበሰበበት አስረሽኖ ገደላቸው።
እንኳንም ዛሬ ላይ አልሆነ ብዬ ፈጣሪን አመሰገንኩት። ለምን አትሉም!? አሁን ዘመን ላይ ቢሆን ደግሞ ግራዚያኒ ሳይሆን ህዝቡ ነበር 'ሚረሽናቸው። የስልጣኔ ፀር፣ እኛ እንዳናድግ እንቅፋት ሊሆኑብን ነው፣ የድሮ ናፊቂ! ብሎ ሲያበሻቅጣቸው ሳልኩትና ዘገነነኝ፣ እንኳንም የዛኔ ሆነ ሆሆሆ።
ግራዚያኒ ህዝቡን "ጠላታችን ስለሞተ አጨብጭቡ።" አላቸው። ህዝቡም በጭብጨባ አቀለጠው አሉ ይሄ አጨብጫቢ ህዝብ! ለገዳዩም ላስገዳዩም እንዳጨበጨበ ይሄው እስከአሁን አለ። የእነሱ ልጆች ዛሬም ድረስ በየስብሰባው በየፓርላማው እንዳጨበጨቡ ነው አሉ። አይ አንቺ ሀገር ስንት ጠባቂ ልጆችሽን በጭብጨባ ሸኘሽ!፣ መች ይሁን ማጨብጨቡ የሚበቃሽ!? መዳፍሽ ለጠላቶችሽ ማጨብጨቡን ትቶ ሰይፍ የሚጨብጠው! መች ይሆን ልጆችሽን መገበር የሚበቃሽ? እንጃልሽ!።
በአንድ ወቅት የሆነ ፍልስፍና ፀጣፍ ላይ የቃረምኩት ትዝ አለኝ። " በአንድ ወቅት ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ እስራኤል ከተማ ሲመጣ በመንገድ ያገኙት ሰዎች እየሱስን እየሰደቡ እየተፉበት እርሱ ግን በመካከላቸው ምንም ሳይናገር በዝምታ ያልፋል። ታዲያ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ነገሩን ሲከታተሉ ቆይተው ኖሮ ለምን ዝም እንዳለ ጠየቁት። በዚህ ጊዜ እየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው " ሰው ከቅርጫቱ ውስጥ የሚያወጣው ቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ነው። እነዚህም ሰዎች ከስድብና ጥላቻ ውጪ ሌላ ነገር አያውቁም አትፍረዱባቸው" ብሎ ነገራቸው።
አቤት! የዚህ ዘመን ቅርጫት ሲከፈት ውስጡን አሰብኩት። ዘረኝነት፣ እርኩሰት፣ ሴሰኝነት፣ ጥላቻ፣ ተንኮል ወዘተ ተጭቀውበት ታየኝ። ስንት ዘመን ከዚህ ቅርጫት እንደምንኖር እንጃ! ስንት ዘመን አዳኞቻችን ታዳጊዎቻችንን ከዚህ ቅርጫ እንደምንወረውርባቸው እንጃ! ማን ያውቃል!? ብቻ ተስፋ አልቆርጥም።
22/11/2014 ዓ.ም የተከተበ
@ourrthought

🔥5❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንዳንዴ ዘመንን የሚቀድሙ ሰዎች አሉ። ጂጂ ከነዛ ሰዎች ውስጥ አንዷ ናት። ስራዎቿ ትንቢት የሆኑላት "እኔን የራበኝ ፍቅር ነው ብላ የዘር ቡካታችንን የተነበየች ፣ አባይን በሌላ መልኩ የገለጠች አረ ስንቱ። ብቻ ትቆጨኛለች።
@ourrthought
@ourrthought
🥰8❤3
Ethiopia by GIGI
fabfishsos
ሙዚቃ በዚህ ልክ እንደ ነብስ ምግብ ኩልል ብሎ ሲዎርድ ሀሴት ነው። ይህ ሙዚቃ የነብስ እነጂ የስጋ አይደለም።
@ourrthought
አይርብ አይጠማውም አይከፋውም ደሜ
ቢርበኝ በላለሁ ዶቅማውን እንኮይም ለቅሜ
ክፉም ንጉስ መጣ ደግም ንጉስ መጣኢትዮጵያ
ሁሉም ይሄዳሉ እንዳመጣጣቸው
ሳቅና ለቅሶሽን አይገዙትምና
አትፍሪ እናታለም ኑሪልኝ በጤና
@ourrthought
❤11🥰2
ማርጀትህን የምታውቀው የሆነ ቀን ታኪሲ ላይ ከረዳቱ ጋር ተናንቀህ አሮጌ ብር ነው የሰጠኸኝ ፣ ያረጀ ብር ነው ብለህ ስትጨቃጨቅ እራስህን ስታስተውል ነው። እድሜ ይጋልባል።
@ourrthought
@ourrthought
😁8🤣5👎2❤1🤨1
እንደውም ሲሲፈስ እድለኛ ነበር። የሚገፋው አንድ ቋጥኝ ብቻ ነበር። በዛ ላይ የመግፊያው አቅምም ነበረው። እዚህ ዘመን ላይ ቢሆን ኖሮ አማልክቱ ቅጣቱን አዘምነው የሚቀጡት ለዘላለም Tik tok ፣ Facebook ፣ IG ፣ TG ፣ X scroll እንዲያደርግ ነበር የሚቀጡት።
@ourrthought
@ourrthought
😁12❤3🤣3
ከጠዋት እስከማታ social media እየተጠቀማቹህ ጤነኛ የሆናቹህ ሰዎች እንኳን Disorder ቀርቶ Cancer ራሱ አይገላቹሁም። ሰማያዊ እገዛ አላቹህ በውነቱ።
በጌታ ስም አለ ያሬድ ነጉ ቀኑን ሙሉ social media ተጠቅሞ መሆን አለበት። ስካር በስንት ጣዕሙ። 🙌
@ourrthought
በጌታ ስም አለ ያሬድ ነጉ ቀኑን ሙሉ social media ተጠቅሞ መሆን አለበት። ስካር በስንት ጣዕሙ። 🙌
@ourrthought
😢7❤4👍1
አሁን አሁን እንደ ፋሽን እየመጣ ያለ ነገር ቢኖር የሚወለዱ ልጆችን ስም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እያወጡ በ 1250 የነበሩ አይሁዶች የቀበሌ ስም (Torah ላይ ራሱ የጠፉ) እያወጡ አይሁዶች ራሱ የማይጠሩበትን ስም ያወጣሉ። ትርጉሙ ምንድነው ሲባሉ ላባና ያዕቆብ የታረቁበት ቦታ ትኖር የነበረች ድንቢጥ ናት ምናምን ይላሉ።
ፅድቅ በስም ቢሆን ይሁዳ (የስሙ ትርጉም ታማኝ ነው) ነበር ቅዱስ። በዚህ ልክ ከማንነታችን መራቅም ያስተዛዝባል።
@ourrthought
ፅድቅ በስም ቢሆን ይሁዳ (የስሙ ትርጉም ታማኝ ነው) ነበር ቅዱስ። በዚህ ልክ ከማንነታችን መራቅም ያስተዛዝባል።
@ourrthought
😁8🤨5❤3
ሐሳቦቻችን
አሁን አሁን እንደ ፋሽን እየመጣ ያለ ነገር ቢኖር የሚወለዱ ልጆችን ስም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እያወጡ በ 1250 የነበሩ አይሁዶች የቀበሌ ስም (Torah ላይ ራሱ የጠፉ) እያወጡ አይሁዶች ራሱ የማይጠሩበትን ስም ያወጣሉ። ትርጉሙ ምንድነው ሲባሉ ላባና ያዕቆብ የታረቁበት ቦታ ትኖር የነበረች ድንቢጥ ናት ምናምን ይላሉ። ፅድቅ በስም ቢሆን ይሁዳ (የስሙ ትርጉም ታማኝ ነው) ነበር ቅዱስ። በዚህ ልክ…
"ነጮቹ መጀመሪያ ወደ አፍሪካ ሲመጡ እነሱ መፅሐፍ ቅዱስ እኛ መሬት ነበረን። መፅሐፍ ቅዱስ ሰጡንና አይናችንን ጨፍነን መፀለይ አስተማሩን። አይናችንን ስንገልጥ ግን እነሱ መሬት እኛ መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ነበረን።"
ቄስ ዴዝሞን ቱቱ
@ourrthought
ቄስ ዴዝሞን ቱቱ
@ourrthought
🔥5👍4❤1👎1
ሐሳቦቻችን
Photo
ዛሬ በባስ ታጭቄ እየሄድኩ በባስ የተከፈተ ሬዲዮ ላይ ጆሮዬን ጣል አድርጊያለሁ። ወንድና ሴት ጋዜጠኛዋ ስለ ቡሄ ወሬ ይጠርቃሉ። በመሀል ወንዱ ጋዜጠኛ ሆያ ሆዬ ማለት ጀመረ።
"እዚህ ማዶ አንድ ጄሪካን
እዛ ማዶ አንድ ጄሪካን
የኔማ እከሌ (ስሟን ረስቸዋለሁ) ልሸኝሽ አሜሪካ።" ብሎ ግጥሙን ሲጨርስ በደስታ እየተፍነከነከች ግሩም አለች። ወዲያው ግርምታ ይሉት ቁጭት ውልብ አለብኝ። በየቤታችን ልናወራ እንችላለን ግን በሚዲያ የሚተላለፍ ጉዳይ ላይ እንዲህ በግልፅ ስደትን የሚያበረታቱ ጉዳዮች መወሳታቸው ቁጭት ቢጤ ዳሰሰኝ።
ከሁለት ቀን በፊት አባይ ቲቪ ላይ የጨርቆስ ልጆችን ሰብስበው ስለጨርቆስ የ አብሮነት ኑሮ መተሳሰብ ፍቅር እያወሩ ፊልሞች ላይ የተወነ አቼኖ ይመስለኛል ስሙ "የጨርቅስ ልጅ ፈር ቀዳጅ ነው። ሊቢያ በመሰደድ የመጀመሪያው የጨርቆስ ልጅ ነው። ከማንም በፊት ስደትን ሀ ብሎ የጀመረ ጨርቅስ ነው። የትም ሀገር ብትሄጂ የጨርቆስ ልጅ አይጠፋም።" ብሎ በኩራት ቲቪ ላይ የሚታይ ፕሮግራም ላይ ሲተላለፍ ታዝቢያለሁ ዩቲዩብ ላይ አሁይም አለ።
ሰሞኑን አላፊ መንገደኛ ቁጥር 2 በሚል ርዕስ በደቡብ አፍሪቃ ዙሪያ የሚያጠነጥን በስደት ዙሪያ የተፃፈ የ ዮርዳኖስ አልማዝ የምርምር መፅሐፍ እያነበብኩ በመሆኑና በስደት ዙሪያ የተደረጉ ቃለ መጠይቆች እያየሁ በመሆኑ የስደት ርዕሶች ሲወራ ጆሮዬ ይቆማል።
በሀገራችን ስደት መቼ ተጀመረ የሚለውን አንድ አርቲክል ሳገላብጥ ከ አፄ ምኒልክ ጊዜ ጀምሮ ስልጣኔን ተምረው እንዲመጡና ለትምህርት ጉዳይ ከሚላኩት የሚነሳ ነው። ከዛም በመቀጠል አፄ ኃ/ሥላሴ የ አፄ ምኒልክን ፈለግ ተከትለው ተማሪዎችን ወደ ተለያዩ ሀገራት መላክ መቀጠላቸውንና በፋሽስት ጊዜ እራሳቸው ንጉሱ መሰደዳቸውን ማንሳት ይቻላል። ከዛን በኋላ በደርግ ጊዜ የስደት ሥርዐትና ቅርፁን በመቀየር የ ፖለቲካ ነክ ይዘት ይዞ ከዘመቻ ለመሸሽ ወደ ተለያዩ ሀገራት በ አራት መስመሮች ወደ ስደት ያቀኑት። በ ኢህአዴግ ዘመነ መንግስት ተባብሶ የመጣው የፖለቲካ ስደት ኢኮኖሚንም አካቶ እስከ አሁን እንደ ቀጠለ ነው።
ወደ ደቡብ አፍሪቃ የሚደረጉ የስደት ጉዞዎችና ደቡብ አፍሪቃ ያሉ የሀገራችን ልጆችን ጉዳይ የሚያጠናው ዮርዳኖስ አልማዝ በደቡብ አፍሪቃ ስለሚደረጉ ጉዞ እና እዛ ያለ የስደተኞች ሁኔታ የሀገሩን ነባራዊ ሁኔታ በ 2 መፅሐፍት ጀባ ብሏል። ከዛም ውስጥ አንዱ እጄ ላይ ያለው እላፊ መንገደኛ ቁጥር 2 መፅሐፍ ነው። በዚህ መፅሐፍ ላይ ደቡብ አፍሪቃ ያሉ የሀገራችን ስደተኞች አፓርታይድ ካበቃ በኋላ ደቡብ አፍሪካ በሯን ለስደተኞች የከፈተች በመሆኑ ብዙ የተለያዩ የ አፍሪካ ሀገራት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለስራ አቅንተዋል። በዛም የመጀመሪያ ስራቸው ቀበቶ ሰዐት የተለያዩ በእጅ የሚያዙ እቃዎችን ይዘው መንገድ ለመንገድ ይሸጡ ነበር። ደቡብ አፍሪካውን አፓርታይድ አብቅቶ ከእስር ሲፈቱ ቀበቶ የሌላቸው በመሆኑ ቀበቶ መሸጥ አዋጭ ቢዝነስ ነበር።
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከ ኢትዮጵያም ከተለያዩ ቦታዎች የሚሄዱ ስደተኞች ህጋዊ ስለማይሆኑ የ ስደተኛ የመሆኛ ጥያቄ መጠየቂያው እንኳ ሂደቱ ብዙ ስለሆነ ያለምንም ወረቀት የሚሰሩ በመሆኑ የባንክ አገልግሎት ስለማይጠቀሙ ገንዘባቸውን በኪሳቸው ወይም በሌላ ቦታ በካሽ ይዘው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑ የደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ቀማኞች Mobile ATM ሁላ ይሏቸዋል። በቀንም ሆነ በለሊት የሰሩበትን ሁሉ በአንድ ቀን ይቀማሉ። ነብሳቸውንም ይቀማሉ። ደቡብ አፍሪካ 40% የስራ አጥ ቁጥር ያለባት ሀገር ስትሆን መንግስት በሚሰጣቸው የወር ድጎማ የሚተዳደሩ ገንዘብ የመቆጠብ ልማድ የሌላቸው ናቸው። በዛ በዛ ስደተኞችን እያጠቁ ገንዘባቸውን ይቀማሉ ይሰርቃሉ። ደቡብ አፍሪካ በቀን ራሱ መንቀሳቀስ ጭንቅ ጥብ የሆነበት ሀገሮ ነው። በማንኛውም ሰዐት ልትዘረፉ ሊገድሏቹህ ይችላሉ። ግን ደግሞ የሀገሬው ነዋሪ የመግዛት አቅሙ ከሀገራችን ጋር ሲነፃፀር 40% ይበልጣል። ይህ ማለት ፍላጎቱም አቅሙም አለ ማለት ነው።
በደቡብ አፍሪካ የስጋት ህይወት የሚኖሩ በፖሊስም ጭምር የሚዘረፉ ሞልተዋል። ግን ህጋዊ ባለመሆናቸው ብዙ ስቃይና እንግልት ይደርስባቸዋል። አሁን አሁን መጤ ጠልነት Xenophobia እየተበራከተ በመምጣቱ "ምንድነው ጫጫታው ሀገሩ የኛ ነው" የሚል መፈክር በመያዝ በገጠራማው በሚገኘው ደቡብ አፍሪቃ ላይ በተጋጋሚ ሱቃቸውና ብራቸው ይዘረፋል። የሀገራችን ውሾች ከናንተ ይሻላሉ የሚሉም ተበራክተዋል። የሰው ነብስ እንደ ቀላል የሚጠፋበት ሀገር ነው። ብዙዎች ደሞ ተቀይረው ኑሯቸውን ሊደጉሙ ችለዋል። ጥሩ ኑሮም የሚኖሩም አሉ። ህጋዊ ቢሆኑም ብዙ የመብት ጥሰቶችን ያስተናግዳሉ። ገንዘብ ከፍለው እንኳ ልጆቻቸውን ማስተማር የሚከለከሉበት ጊዜም አለ።
በሆሳዕናና በሌሎች አንዳንድ የደቡብ አከባቢዎች ሁሉም ደቡብ አርፍሪካ የቃል ኪዳኗ ምድር ለመግባት የሚጓጓ ብዙ ነው። በሻሼጎ ቦኖሻ የሚገኝ የመሰናዶ ትምህርት ቤት ሰባ በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ፓስፖርት አውጥተው ለመሰደድ የተዘጋጁ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። ብዙዎቹ እዛ ከሄዱ በኋላ በአመት አንድ ጊዜ የሚዝናኑበትን ቦታ በፎቶ በመልቀቅ ሀገር ቤት ያሉ ሰዎችን ያጓጓሉ። የቤተቦቻቸውን ቤት እቃ ይሞላሉ። በሆሳእና አከባቢ ሀገር ቤት ያሉ ያልተሰደዱ ቤተሰቦችና የተሰደደ ልጅ ያላቸው እኩል አይከበሩም የተሰደደ ልጅ ያላቸው የተሻለ ክብርና ቦታ ይሰጣቸዋል። ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄደው ሞተው የሚመለሱ ስደተኞች የሀገር ቤት መቃብራቸው የአይሮፕላን ምስል ይሳልበታል። ቢያንስ ሬሳው በአይሮፕላን ነው የመጣው ብለው ቦታ ይሰጡታል። በተቃራኒው በሀገር ቤት ያለ ወዳጅ ዘመድ ቦታ አይሰጣቸውም። ዬሄ ለስደት ይገፋቸዋል የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ይገፋፋቸዋል። የሚሄዱት በህገወጥ መንገድ በመሆኑ መሬት ሸጠው ተበድረው ሄደው በመንገድ ላይ የሚሞቱም አሉ። በስደት ጊዜ ከ 6 ወር በላይ የሚፈጅባቸውም አይጠፉም። በ ድንበር ጠባቂዎችና ደላሎች የሚደፈሩ ሴቶች በመብዛታቸው ሴቶቹ ቀድመው የወሊድ መከላከያ ይጠቀማሉ።
ወደ አረብ ሀገርም የሚሰደዱ ሴቶች እውቀትና የዘመናዊ ኑሮ ልምድ የሌላቸው በመሆኑና የሀገራችንም የቆንፅላ ፅ/ቤት የደከመ በመሆኑ ቦታና ክብር አይሰጣቸውም። በአንድ ወቅት ባህሬን ያሉ ሰራተኛ አገናኞች አንድ ፊሊፕናዊት ሰራተኛ ሲቀጥሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ሴት በነፃ ትመረቅላቹሀለች የሚል ክብር የሚነካ ማስታወቂያ አውጥተው ደራሲ ፕሮሞተር እስከዳር ግርማ ተከራክረው ደላላውን ከሰዋል። ይህ የሆነው ያለ እውቀትና ልምድ ስለሚጋዙና የሀገራችንም ግንኙነትና ለህዝቡ ደንታ ቢስ የሆነ በመሆኑ ነው።
በዚህ በ ዮርዳኖስ መፅሐፍ ላይ ሰዎት ከመሰደዳቸው በፊት ስለሚሰደዱበት ሀገር ቋንቋ ባህል ቢያውቁና መኪና ሳይክል ዋና ምግብ ማብሰል ሁነኛ ጉዳዮች እንደሆኑ አፅኖት ይሰጣል። የኛ ሀገር ዜጎች በደቡብ አፍሪካ ብዙ የሚሄዱት ከ ገጠር የሀገሪቷ ክፍሎች በመሆኑ ቋንቋ እጥረት ያለባቸው በመሆኑ ብዙ ነገር ይስተጓጎልባቸዋል።

👍3👏1
ሐሳቦቻችን
ዛሬ በባስ ታጭቄ እየሄድኩ በባስ የተከፈተ ሬዲዮ ላይ ጆሮዬን ጣል አድርጊያለሁ። ወንድና ሴት ጋዜጠኛዋ ስለ ቡሄ ወሬ ይጠርቃሉ። በመሀል ወንዱ ጋዜጠኛ ሆያ ሆዬ ማለት ጀመረ። "እዚህ ማዶ አንድ ጄሪካን እዛ ማዶ አንድ ጄሪካን የኔማ እከሌ (ስሟን ረስቸዋለሁ) ልሸኝሽ አሜሪካ።" ብሎ ግጥሙን ሲጨርስ በደስታ እየተፍነከነከች ግሩም አለች። ወዲያው ግርምታ ይሉት ቁጭት ውልብ አለብኝ። በየቤታችን ልናወራ…
ሀሳቡን ከመፅሐፉ ቦታ ካስገረመኝ ቦታ ጠቅሼ ላብቃ። አንድ የሀገራችን ሰው በደቡብ አፍሪካ የገጠር አከባቢ አነስተኛ ሸቀጣሸቀጥ ከፍቶ ይሰራል። በዛ አከባቢ ስትራይካ (መጤ ጠል አመፅ) አሁን አሁን በተደጋጋሚ የሚከሰትበት ነው። እና የሰፈሩ ደንበኞች በጣም የሚግባባቸው ሁለት የደቡብ አፍሪካ ዜጎች በማታ ወደ ሱቁ መጥተው ልጁ እያለ አንገታቸውን አስገብተው በራሳቸው ቋንቋ በዙሉኛ ነገ አመፅ ሲነሳ የትኛውን እቃ ማን እንደሚወስድ ይከራከራሉ። እሱን ከመጤፍም አልቆጠሩት። እኔ ነኝ ያን እቃ የምወስደው ሲል አንደኛው ታያለህ ቀድሜ ስለምመጣ እኔ ነኝ የምወስደው ተባብለው የሚፈልጉትን እቃ መርጠው ይሄዳሉ። በነጋታው አመፁ ተነስቶ ሌሎች አመፅኞች ቀደሟቸውና በሱቁ ደና እቃውን ወሰዱት። እነሱ ሲመጡ ሌላ እቃ ይዘው እየወጡ ደንበኛ የሀገራችንን ልጅ "በርታ እንግዲህ እኛም እናግዝሀለን "try again" ብለውት ወጡ። እንግዲ ከዜሮ መጀመር ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሀገራችን ላይ የሆነ እቃ ላይ በነጋታው ስትሄዱ ዋጋ እንደመጨመር በሉት። ደቡብ አፍሪካዊ የስደተኛ ሱቅ ገብቶ ነገ ያቺን ዕቃ አዘጋጅልኝ መጥቼ ወስዳለው ብሎ በነጋታው መጥቶ ይወስደውና በርታ አግዝሀለሁ ብሎ ይሄዳል።
ስደት በሌሎችም አውሮፓ ሀገሮች ከአፍሪካ የሚሄዱ ስደተኞች ከሰውነት በታች በደልንም የሚቀምሱበት ቦታም ነው። ከዩኒቨርስቲ ዶክተር የነበረ አስተማሪ አሁን ላይ አሜሪካ ሽንት ቤት እንደሚያፀዳ ሰምቼ ምን እንደምል ግራ እስኪገባኝ በዚህ ልክ ስደት የሚንቆለጳጰስ መሆኑ ያስገርመኛል።

👍4🔥2👏2❤1
እንደ ዶሮ ወጥ 12 ዙር እናያለን ብለን ብንጓጓም እንደ ኢንዶሚን ከ 3 ደቂቃ የማያልፍ መሆኑ ያንገበግባል።
ከ ሀገራችን EFC ኢንዶሚን ይቆያል።
@ourrthought
ከ ሀገራችን EFC ኢንዶሚን ይቆያል።
@ourrthought
😁7❤1
ሐሳቦቻችን
Photo
የ ህይወት ትርጉም (meaning of life)
የህይወት ትርጉም ምንድነው? ህይወትስ በራሷ ትርጉም አላት ወይስ እኛ ነን በራሳችን ትርጉም የምንሰጣት? የሚሉትን ጥያቄዎች ለዘመናት አከራካሪ ጉዳይ ቢሆንም አሁንም የተጨበጠ ሁሉንም የሚያስማማ መልስ ማግኘት ይቸግራል።
ሀይማኖት ህይወት በራሷ ትርጉም አላት ሲል እንደነ ካሙ ያሉ ፈላስፎች ሀይማኖት በሚሰጠው ትርጉም ማመን ትርጉም በሌለው አለም ውስጥ ለትርጉም ነው የተፈጠርኩት ማለት በራሱ እራስን በማታለል እራስ ላይ ያለ እራስን ማጥፋት (Philosophical suicide) ይላል።
ለምንድነው እዚህ ምድር የመጣሁት? ምን እየሰራሁ ነው? ለምንድነው የምኖረው? አላማዬስ ምንድነው? የሚሉ ጥያቄዎች ከየትኛውም ጊዜ በላይ ከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የ 21 ኛው ክፍለ ዘመን ትልቁ ጥያቄ ሆኗል። ለምን ይሄ ጥያቄ ከሌላው ጊዜ በላይ አሁን ይበልጥ ሰውን ማስጨነቅ ጀመረ? የህይወት ትርጉም ማጣትስ? እራስን ማጥፋት ቁጥሩ ለምን ጨመረ? የሚሉት ብዙ ምክንያቶች አሉ።
እንደ ካምዩ ሀሳብ ሲጀመርም ህይወት በራሷ ትርጉም የላትም ስለዚህ ትርጉም አላት እያሉ ከመሞኘት ይልቅ እና ህይወት ትርጉም ባይኖራትም የራስህን ትርጉም ፈጥረህ የራስህ ጀግና (Absurd hero) ሆነህ መኖር ትችላለህ ይለናል። እንደ ሲሲፈስ ድንጋዩን ማንከባለሉን ማቆም ባይችልም ግን ለመግፋቱ ለራሱ ምክንያት እንደሰጠው ሁሉ አንተም ለራስህ የሆነ ግብ ይዘህ ለሱ መኖርና ትርጉም መስጠት ትችላለህ ይለናል። ግን ሰው እራሱ ለራሱ የሚሰጠው ምክንያት በቂው ነው? የራሴ ነው የሚለውስ ጥያቄ እውን የራሱ ነው ማለት ይቻላል? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው።
ለምሳሌ አስቡትና ብቻችሁን ምድር ላይ ቀራችሁ እንበል። ሌላ ማንም ሰው ምድር ላይ የለም። እና ትልቁ የህይወት ግባቹህ ምን የሚሆን ይመስላቹሀል? የራሳችሁን ትርጉምስ ምን ሊሆን ይችላል? አሁን የህይወታቹህ ትርጉም አድርጋችሁ የምትኖሩለትን ነገር አለም ላይ ብቻችሁን ብትሆኑ ታስቀጥሉታላቹህ? ጥያቄውን ለናንተ ልተው።
ወደ ጥንታዊው ሰው ስንመለከት የማህበረሰቡ ኑሮ በጋራ የሆነና እኔነት የሌለው ነው። ኑሮው ሁሉ በጋራ እንደመሆኑ መጠን በጋራ እራስን የማቆየት (survival) የሆነ በመሆኑ አንድ ህፃን ሲወለድ ጀምሮ እስከ መሞቻው ኑሮው የታወቀ እና የተገመተ ማህበረሰቡ በቀደደው የጋራ መስመር የሚፈስ የነበረ ነው። በጋራ ማደን በጋራ መጨፈር መብላት መዋለድ ውስን ተግባሮች የነበሩበትና የጋራ የሆነ በመሆኑ ሰው ግራ መጋባት በህይወቱ እምብዛም የለውም ነበር።
ሀይማኖት ተደራጅቶ ከመጣ በኋላም የህይወትን ትርጉም ከፈጣሪ ጋር በማያያዝ በቂ የሆነ ምላሽ ለማህበረሰቡ የሰጠ የነበረ በመሆኑ የተፈጠረለት አላማ በፈጣሪና ስለፈጣሪ መሆኑን አማኙ ተቀብሎ በደስታ ይኖር ነበር። ከ ዘመነ አብርሆት በኋላ (Age of enlightenment) ሀይማኖቶች ጥያቄ ውስጥ መግባታቸው ሀይማኖት ይሰጥ የነበረው ትርጉምም አብሮ ተጠየቅ ውስጥ ገብቷል።
አሁን ላይ ይበልጥ የህይወት ትርጉም ለምን ጥያቄ ውስጥ ገባ? የሚለው ዘመኑ የ ግለሰባዊነት (Individualism) በመሆኑ እንደ ቀደምት ዘመን የጋራ ትርጉምና ኑሮ የሌለው የተወሰነለት ትርጉም የሌለው በመሆኑ ፡ ጥያቄው ከጋራ ምላሽ ይልቅ በግለሰብ ደረጃ በመሆኑ የየራሳችንን ትርጉም መፈለግ ለብዙ ሰው አዳጋች ሆኗል። ምን ላድርግ? ምን ልስራ? ወዴት ልሂድ? የሚሉ ጥያቄዎች ከራሳችን ተነስተው እራሳችን ላይ የሚያቆሙ በመሆናቸው የራስን ትርጉም ከምን አንፃር መመለስ እንዳለብን ግራ ይገባናል። ይህ ግራ መጋባት ብዙ ሰዎችን የሚያስጨንቅ በመሆኑ ህይወቱን ትርጉም ለመስጠት ፡ አብዛኛው ሰው አሁን ላይ ዋጋ የሚሰጠውን ነገር በመምረጥ ለዛ ነገር ለመኖር ይወስናል። ለምሳሌ ሀብታም መሆን ፣ ቤትና መኪና መግዛት ፣ ታዋቂ መሆን ትርጉም አድርጎ ለመኖር ይወስናል። አሁን ላይ አብዛኛው የህይወት ትርጉም ከ ቁሳዊ ነገሮች (materialisem) ጋር የተሳሰረ እየሆነ መጥቷል። ይህ ለምን ሆነ ስንል ዘመኑ ለ ቁሳዊ የሚሰጠው ወጋ ከፍ ያለ በመሆኑ ላይ የተመሠረተ ነው። የህይወት ትርጉም ምንድነው? ብንል አሁንም ያልተመለሰ ጥያቄ ነው።

❤7👍1🔥1
ሐሳቦቻችን
Photo
የዛሬ አመት ለ ቀለም ዲጅታል መፅሔት መግቢያ የምትሆን ፅሑፍ ስለ አዲስ አመት የከተብኳትን ዛሬ ደግሜ ላካፍላቹህ።
“ጊዜ በረርክ፤ በረርክ፤
ጊዜ በረርክ፤ በረርክ፤
ግና ምን አተረፍክ፤
ግና ምን አጎደልክ፤
ሞትን አላሸነፍክ፤
ሕይወትን አልገደልክ፡፡”
ገጣሚ ደበበ ሠይፉ “ ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ” በሚለው የግጥም መድብል ውስጥ ይህቺን ግጥም ታስደንቃለች። በስድስት አጫጭር መስመር ብዙ ሀቅን ይነግረናል። ጊዜ እንደዚህ ሮጦ ሞት የሚባልን የሰው ልጅ ዕዳ ካላሸነፈ መወለድ የሚሉትን የህይወት ትግል ካልገደለልን ታዲያ እውነትም ጊዜ ይሄ ሁሉ ዘመን ያለማቋረጥ መገስገሱ ምን ይሉት ብሂል ነው? ግዜ ራሱ የት እየሔደ ይሆን? እንጃ እኛ የምናውቀው ከጊዜ ጋር አብረን መፍሰሳችንን እንጂ ምስጢሩ ገና በውል የገባን አይመስልም።
ብዙ ጊዜ እኛ ሰዎች ጊዜ መሸምጠጡን የምናስተውለው ዓመት ሲቀየር ነው። ታዲያ ዛሬም አዲስ ዓመት የተቀየረ በመሆኑ ስለ ጊዜ ቆም ብሎ ለማሰብ ፋታ ያገኘንበት ሰሞን ይመስለኛል። የሰው ልጅ ከ አቻው ጀምሮ ተፈጥሮን ፣ አራዊቱን ፣ ሥነ-ፈለክን ፣ አፅናፉን ወዘተ ያለምረመረውና ያልታገለው ነገር የለም። ኧረ እንደውም በመፅሐፍ ቅዱስ ሰው ከፈጣሪው ሁሉ ታግሏል ካልባረከኝ አለቅህም ብሎ አምላኩን ሙጥኝ ብሎ እምብኝ ማለቱን አንብበናል። ግን ይሄን ጊዜ ይሉት ነገር የት አግኝቶ ይታገለው? እዳ ነው ጃል።
ገጣሚው በዕውቀቱ ስዩም በስብስብ ግጥሞቹ ውስጥ እንዲህ ይለናል:-
“እኛኮ ለዘመን
ክንፎቹ አይደለንም ሰንኮፍ ነን ለገላው
በታደሰ ቁጥር የምንቀር ከኋላው።” ይለናል።
እንደልቤ የተባለለት ልብ አምላክ ዳዊት በመዝሙሩ ውስጥ “የጣቶችህን ስራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፤ ጨረቃንና ክዋክብትን አንተ የሰራካቸውን ፤ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው? ትጎበኘውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?” እንዳለው የሰው ልጅስ ለጊዜ ምኑ ነው? ሀያል ሆንህ ደቃቃ ፣ አዋቂ ሆንህ መሀይም ፣ ሶሬሳ (ሀብታም) ሆንህ ቤሳ የሌለህ ደሀ ፣ ታማኝ ሆንህ ከሀዲ ምንስ ብትሆን ለግዜ ምን ገዶት? እንዳልነበርክ ሁሉ እርስት ያደርግሀል። ትቶህ ሂድት ጥሎህ ፍርጥጥ። ለ አፈር ሰጥቶህ እብስ። በቃ ይሄን እውነት ነው ገጣሚው የሚነግረን።
ከ ቀለም መፅሔት መግቢያ ከ መስከረም 15/2018 ዓ.ም ቅፅ 1 ዕትም 3 ላይ የተቀነጨበች።

🔥3👌2❤1