ሐሳቦቻችን
981 subscribers
103 photos
4 videos
5 files
2 links
በዚ ቻናል ላይ የተለያዩ ሀሳቦቻችንን ፣ ምልከታዎቻችንን ፣ ትዝብታችንን ፣ ከተለያዩ መልኮች እያነሳን እንወያያለን!

ሀሳብና አስተያየት ካላቹ @haileabb
Download Telegram
‎ ሴትየዋ ልጆቿን ከነዚህ ክፉ መናፍስት ለማዳን ታዲያ ልጆቿንና ባሏን እሷንም ክፉ መንፈስ ሳይቀድማት ለመቅደም ገላቸው ቀድማ ገነት ለመግባት ነው የምታስበው።

‎ ሳይኮሎጂው እንዲህ አይነት ነገሮች ሳይንሳዊ ባለመሆናቸው ለመቀበል ይቸገራል። ይንን ነገርም ሳይኮቲክ እያለ ሰዎቹን ከ እውነታው አለም የተለያዩ (Delusional) የቀን ቅዥት ያሌለን ነገር ማየት (Hallucination) እያለ የዳቦ ስም ይሰጣቸዋል። በርግጥ አሁን አሁን ይህን መንፈሳዊ አለም ማግለሉ እንደማያዋጣው ስላወቀው ሳይኮሎጂው መንፈሳዊነት (spirituality) እያለ ማካተት እየጀመረ ነው።ግን ገና ብዙ ይቀረዋል።

‎አጠቃላይ ልምምዱ ጥንት የነበረ ልምምድ ሲሆን ማንኛውም ሰው እንዲያደርገው የማይመከር ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊ ጥንካሬ ካዳበርን በኋላ መደረግ የሚገባው ነው። በዚህ ዙሪያ የተሰሩ Behind her eys እና Insidious የሚሉትን ፊልም review እሰራላቹህና የተሻለ ለመረዳት ይረዳናል።


@ourrthought
👏6🙏2
ሐሳቦቻችን
Photo
Astral Projection በ Insidious እና Behind her eys በሚሉት ፊልሞች ውስጥ እንዴት ተገለፀ የሚለውን እንመልከት።

Behind Her Eyes 6 ክፍሎች ያሉት ሲሆን Astral Projection የተገለፀበት መንገድ ትንሽ የሳሳና ብዙውን እውነት የማያሳይ ነው። በፊልሙ ውስጥ Astral Projection ነብስ ከ አካል ውስጥ በመውጣት ከዚህ በፊት በምታውቃቸው ቦታ ብቻ እየተዘዋወረች የሚከናወነውን የምትታዘብበትን የሚተርክ ነው።

ፊልሙ ላይ በህልማቸው በ ቅዥት አለም የሚቸገሩና በእንቅልፍ ልባቸው ስለሚነሱ ሰዎች (sleep walker) ያትታል። እና የ አዕምሮ ህክምና ማገገሚያ የገቡ ሁለት ካራክተሮች እናያለን። እንቅልፍ መተኛት የሚቸገሩና በህልማቸው ሁል አስፈሪ ተመሳሳይ ህልሞችን የሚያዩ ናቸው። በሂደት አንዷ ካራክተር በ Astral projection በልምምድ ህልሟን መቆጣጠርና ማዘዝ ስትችል ያሳያል። ቤቷ ተኝታ ነብሷ (ንቃተ ህሊናዋ) ከዚህ በፊት የምታውቃቸው ቦታዎች እየተዟዟረች ባሏ ቢሮ ምን እንደሚሰራ ትከታተለዋለች። አብራው ያለውን በቅዥት የሚቸገር ጓደኛዋን ስለ Astral projection ታሳየውና አብረው ልምምዱን ማድረግ ይጀምራሉ።

በፊልሙ ላይ ከ አስትራል በፊት መደረግ ስለሚገባቸው ዝግጅቶች ያሳያል። ጣትን መቁጠር ተመስጦ ማድረግና ከመተኛታችን በፊት ያለች በሰመመን የምናያት የራሳችን የህልም አለም (Lucy dreaming) አስፈላጊ መሆናቸውን ያትታል። ሌላው ስለ አስትራል የተነሳው ጉዳይ በ Astral projection ነብሳችን መሄድ የምትችለው ከዚህ በፊት በምናውቀው ቦታ ብቼ መሆኑን ያትታል። ከዚህ በፊት ያልሄድንበት ቦታ ላይ መሄድ እንደማንችል አፅንዖት ይሰጣል። በተወሰነ መልኩ የነብስ ነጠቃም እንዳለ ያትታል። ሁለት የ አዕምሮ ማገገሚያ ማዕከል ያሉ ጓደኛሞች Astral projection ካሳየችው በኋላ እየተገበሩት ነብሳቸው ከሰውነታቸው ተነጥሎ በሚገዟዟሩበት ጊዜ አካል ተቀያይረው ለመሞከር ይፈልጋሉ። በመሀል የሷ ነብስ የሱ ውስጥ የሱ ነብስ የሷ ውስጥ እንዳሉ ጓደኛዋ የሷን አካል ሲነጥቃትና እሷ የሱ አካል ውስጥ እንዳለች ሲገላት ያሳየናል። ከዛም የሱ ነብስ በሷ ነብስ ውስጥ ገብቶ ሲንቀሳቀስ ያሳያል። ፊልሙ በተወሰነ መልኩ ስለ Astral projection የሚያሳይ ሲሆን የተሳሳቱ ነገሮችንም ይናገራል። ለምሳሌ በ Astral real መጓዝ የምንችለው የምናውቀው ቦታ ብቻ ነው የሚለው ድምዳሜ ከእውነታው የራቀ ነው። አንዳንድ ቦታዎች ለማየት እንደሞከርኩት ነብስ አይታ የማታውቀው ቦታ እንደምትጓዝ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ።

Insidious በሚለው ፊልም ውስጥ

ይሄ ፊልም ስለጉዳዩ የተሻለ የሚገልፅ ሆኖ አጊኝቼዋለሁ

ፊልሙ chapter 2 chapter 3 እያለ 4 ክፍሎች ያሉት ነው።
የመጀመሪያው ክፍል ላይ ፊልሙ ሲጀምር በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አንድ ህፃን ልጃቸው ኮማ ውስጥ ሳይሆንም ሳይነቃ በእንቅልፍ አለም ውስጥ በኦክስጅን ብቻ የሚቆይበትን ሂደት ያስቃኛል። በዚህ ግራ መጋባት ወስጥ እንዳሉ ሀኪሞችም ሳይኮሎጂስቶችም መላ ሊሰጧቸው አልቻሉም።

በዚህን ጊዜ አያቱ አንድ ሴት ታናግራለች። ሴትየዋ ለሰው የማይታይ የምታይ መንፈሳዊ ጥበብ ያላት ናት። ልጁንም ካየችው በኋላ ለቤተሰቡ አንድ ነገር ነገረቻቸው ህፃኑ Astral projection መሆኑን ሳይረዳ በህልም አለም ያለ መስሎት ሳያስበው ሌላቸፈኛው አለም ውስጥ Astral plane ሄዷል። እናም ሳያውቀው ነብሱ ከሰውነቱ በጣም እየራቀ በመሄዱ ለመመለስ እንዳይችል ሆኗል። ነብስ ነጣቂ የሚባሉ (parasite) ዴሞን ክፉ ለሰው የማይታዩ መናፍስት ከዚህ በፊት ኖረው የሞቱ ሰዎች ነብሱን ከአካሉ አርቀዋት በህፃኑ ሰውነት የነሱን ነብስ ለመክተት የሚያደርጉትን ትግል ያሳያል። ህፃኑንም ለመመለስ አባቱ በ Astral ሄዶ ሲመልሰው ያትታል።

ይህች መንፈስ የምታየው የ psychic power ያላት ስለ ጉዳዩ chapter 3 በሚለው ክፍል ላይ አንድ ነገር ትናገራለች። Astral projection ሁለት አለም አለው ትላለች። አንደኛው white ጥሩ ቦታ የምንሄድበትና መንፈሳዊ ጥቅምና እውቀት የምናገኝበት መልካሙ አለም እና መልካም መናፍስት ያሉበት ሲሆን የ Black የሚባለው ክፍል ግን ነብሳችንን ከአካላችን አርቀዋት የነሱን ነብስ በሰውነታችን ለማስገባት የሚጥሩበት ሰዎችን ለማሰቃየት የሚፈልጉ ክፉ መናፍስት ያሉበት ነው።

ፊልሙ አንድ ሰው አስትራል ከማድረጉ በፊት አንድ ትልቅ አላማ ሊኖረው ይገባል የሚል መልእክት ይናገራል። አላማ ካለን ነብስ ነጣቂዎቹ የሙት መንፈሶቹን የመታገል አቅም ይኖረናል የሚል ይናገራል። እነዛን ነብስ ነጣቂዎች አለመፍራትም ዋነኛው ነገር ነው። እነሱ የሞቱ በመሆናቸው ከኛ ጋር በሀይል አይጣጣሙምና። በጥቅሉ የ አስትራልን ትክክለኛ መልክ የሚያሳይ ነው።

ሳጠቃልለው ያለምንም መንፈሳዊ ልምምድ እና ሙከራዎች እንዲህ አይነት ልምምድ የሚሞክር ሰው ትልቅ ቀውስ ውስጥ እንደሚገባ ነው። ከ YouTube ብዙ ቪዲዮ ማግኘት ትችላላቹህ በዚህ ልምምድ ውስጥ ያለፉ ሰዎች የሚያደርጉትን ትግልና ስቃይ።

አንድ ጊዜ Astral projection የሞከረ ሰው ሰውነቱ የመንፈሳዊውን አለም የሚከፍት በመሆኑ የጭለማው አለም ነብስ ነጣቂዎች እስከለተ ሞታችን ድረስ ያሳድዱናል። ብዙ ያየኋቸው ይሄን ልምምድ ያደረጉ ሰዎች ወደ ጭለማው አለም ነው የሚገቡት። ከዛም እንቅልፍ መተኛት እስካይችሉ ድረስ መንፈሳዊው አለም ከ እውነተኛው አለም ጋር ይቀላቀልባቸዋል። ለኛ ባይን የማናያቸው መናፍስት ሙታኖች ለነሱ ይታያቸዋል። የብሳችን ያኛውን አለም ከገባችበት መውጫዋ ሀይማኖታዊ መንገድ ያልታገዘ ከሆነ ውጤታማ የመሆን እድሉ ዝቅ ያለ ነው።

ፊልሙን እንድታዩት እጋብዛለሁ።

@ourrthought
🔥5👍3
የAustriaው psychologist Alfred Adler የምትጣፍጥ "Social Interest" የምትል ሃሳብ አለችው። እሱም እንዲህ ሲል ያብራራታል Social Interest(social feeling) is our attitude of relatedness or oneness to social community of all people። ቀጥሎም social community of all people ሲል literally "Humanity" ማለቱ እንደሆነ ይነግረናል።
እኔም ማውራት የፈለኩት ስለዚህች humanity ወይንም ደግሞ ሰዋዊነት ስለምትለዋ ሃሳብ ነው። ታዲያ ይህ የሰዋዊነት ሃሳብ በጣም ብዙ በሆኑ ሃሳቦች እና ድርጊቶች ምክንያት ከሞላ ጎደል እንደ ዓለም እየጠፋ ያለ ነገር ነው። የሰው ልጅ እራሱን የሰዋዊነት(ሰብዓዊነት) አንድ ክፍል አድርጎ ማየት ካቆመ ትንሽ ሰንበትበት ብሏል። ለዚህም የፈጠርናቸው ideologyዎች፣ ስርዓቶች፣ ተጠያቂዎች ናቸው። እስቲ በትንሹ እንያቸው።...

1. በመጀምሪያ በተለያዩ ጊዜያት መልኳን እየቀየረች የተከሰተችው የ"CLASS" ሃሳብ የሰውን ልጅ ሰዋዊነቱን ትቶ፣ ከሰዋዊነቱ ውጪ ራሱን የሚያይበት መከፋፈልን ሰጥታለች፣ እንደ ምሳሌ ያህል የBourgeoisie class (የባላባት መደብ) እና የProletariat class (የሰራተኛ መደብ) ብለን እራሳችንን ከፍለን በሰውነት ከመታወስ በሆነ መደብ ስር ራሳችንን ከትተን በዚያ መታወስን መርጠናል።
 
2.ከዚያ አለፍ ሲልም "MATTER OF COLOR" ወይን ደግሞ ራስን በቆዳ ቀለም ለይቶ የአንዱ ጎራ ሆኖ መመደብ እንዲሁ ከሰዋዊነት ያወጣን ሃሳብ ነው። ጥቁር መሆን የምድር እርግማን መሆን እስኪመስል ድረስ ጥቁር መሆን ባሪያ(slave)፣ ጥቁር መሆን ገረድ፣ ጥቁር መሆን አመፀኛ፣ ጥቁር መሆን ሌባ መሆን እንደሆነ ተደርጎ ተወስዶ ጥቁሮች ላይ በታሪክ ስንዳስሰው የማይረሳ ጠባሳ ጥሎ አልፏል። በሌላ ጎኑ ደግሞ ነጭ ማለት ጥበበኛ፣ ሁሉን አዋቂ፣ የፈጣሪ የብቻ የእጁ ስራ ምናምን ተደርጎ ሲወሰድ ሰንብቷል ለብዙህ ጊዜ። የቀለም ልዩነቱን ገፋ አድርገን አለፍ ብለን ስናየው፣ በውስጡ ጥቁር ለጥቁር ይደግፍ፣ ነጭ ለነጭ ይደግፍ የሚል ሰውን በቀለም የመለየት ሃሳብን በውስጡ ይይዛል።
 
3. አለፍ ስንል ሰዋዊነታችንን ትተን በ አህጉር መከፋፈልም አለ። ማለትም አፍሪካዊ፣ አውሮፓዊ፣ ኤዢያዊ ምናምን እያልን ወደመከፋፈልም አልፈናል ማለት ነው። ስፋቱ ጠቦ መከፋፈሉ የሚሰፋው ደግሞ አለፍ ብለን በሃገር ደረጃ ወደመከፋፈላችን ስንሄድ ይሆናል። ከዚህም ደግሞ ሲለጥቅ እንደኛ እንደ እማማ ኢትዮጲያ ባሉ ሃገራቶች ውስጥ ደግሞ በዘር መከፋፈል፣ በሃይማኖት መከፋፈል፣ ይቀጥል ይቀጥል እና ደግሞ በሰፈር ወደመከፋፈል ድረስ ይደርሳል።

ሃሳቡ እንዴት መሰላቹ፣ ፈጣሪ ሲፈጥረን የፈጠረው፣ ተዋደዱ ሲል ተዋደዱ ያለው ሙስሊሙን ከሙስሊሙ፣ ጉራጌውን ከጉራጌው፣ እትዮጲያውን ከኢትዮጲያዊ፣ አፍሪካውን ከአፍሪካዊ፣ ነጩን ከነጩ አይደለም። ከዚያ ይልቅ ሰውን ከሰው ነው፣ ይህንን ነው Adler oneness to the social community of all people የሚለው። humanity ማለትም ይሄ ነው። ጓደኛዬ ብለህ የጠራኸውን ሰው ጉዳዩ የሃይማኖት ወይንም ደግሞ የዘር ሲሆን ጀርባህን ከሰጠኸው ከዚህ social community of all people (humanity) ጋር የ oneness ስሜት የለህም ማለት ነው።ይሄም ይመስለኛል ትልቁ ችግር በሁሉም ግንኙነታችን ውስጥ የhumanity sense ከሌለ ግንኙነታችን ለመፍረስ ጊዜ ተጠባባቂ ነው ማለት ነው፣ ማለትም የሚዘልቅ አይሆንም ምክንያቱም ግኑኝነታችን የተመሰረተው ሰውነታችን ላይ ሳይሆን ቡድናዊነታችን ላይ ነዋ፣ ቡድናዊነት ደግሞ የሚዘልቅ አይደለም መቼም ቢሆን የሆነ ሰዓት ላይ ሊቀየር ይችላል።  እንደውም ለዚህ የሚሆን አሪፍ ማሳያ የሚሆነው በዕድሜያችን ያን ያህል ባልራቀው የኢትዮጲያ እና የኤርትራ ግንኙት ነው፣ አንድ ነበርን ፣ ተቀላቅለን፣ ተቀላልደን፣ ተፈቃቅደን ኖረናል፣ ተዋልደናል፣ አልፈናል። ከዚያ ግን ምንድነው የሆነው በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት? ባል ከሚስቱ በሚስቱ ትውልደ ኤርትራዊ በመሆን ብቻ ላይገናኙ ተለያይተዋል፣ ከዚህም ባለፈ ሌላም አይነት የተለያዩ ላይገናኙ የመለያየት ታሪኮችን ሰምተናል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ  አንድነታችን የተገነባው መለያየታችን ላይ ስለሆነ ነው። ባልና ሚስቱን ያለያያቸው የትውልድ ቦታ ልዩነታቸው ነው እንጂ የፍቅር ጉድለት ምናምን አልነበረም የሌላውን እንደዛው።

ይሄ ሃሳብ ከምንም በላይ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጲያ ላይ ይንፀባረቃል።ሁሉም ሰው ከጎረቤቱ ጋር እንደ ድሮው በፍቅር ሳይሆን በአይነ ቁራኛ መተያየት ጀምሯል። መዋደድ፣ መከባበር፣ መቻቻል ምናምን የሚሉ ሃሳቦች በሃገራችን ውስጥ ተዘቅዝቀው ከተሰቀሉ ሰንብተዋል። ማንም ሰው አጠገቡ ያለውን ሰው የሚለካው ባለበት የሃይማኖት ቡድን ወይንም ደግሞ የዘር ጎሳ ምናምን እንጂ  በሰውነቱ አይደለም። even እንደውም ይለይላቹ ሲለን ኢትዮጲያ ውስጥ አይደለም በሰውነት መለካት ይቅርና የኢትዮጲያዊነት ስሜቱ ራሱ እየጠፋ ሁላችንም የሆነ ቡድን አካል ተደርገን ተወስደን ነው ልኬት የሚሰጠን። ከምንም በላይ ግን  idea of humanity መቅደም ነበረበት። ማንም ሰው መዳኘት ያለበት በቆዳ ቀለሙ መሆን የለበትም፣ በሚኖርበት ሃገር ወይንም አህጉር መሆን የለበትም፣ በሚከተለው ሃይማኖት ወይንም ደግሞ በተወለደበት ጎሳ አይደለም መዳኘትም፣ መወደድም፣ መነቀፍም ያለበት ከዚያ ይልቅ በሰውነቱ እንጂ። የሃገሬ ሰው ከማለታችን በፊት ሰውነቱ መቅደም ነው ያለበት፣ ካልሆነማ የሃገር ልጅነትም በፖለቲካ ይነጠቅና ወደ ጠላትነት ይቀየራል። እና ሃሳቤን ሳሳጥረው...
                    
ከጥቁርነት፣ ከአፍሪካዊነት፣ከኢትዮጲያዊነት፣ከጌዴዮንነት፣ከክርስቲያንነት፣ ሰዋዊነት (humanity) ይቀድማልና ትስስራችን ከቡድናዊነት ጋር ሳይሆን ከሰዋዊነት ጋር ይሁን።!



@ourrthought
🔥42👍1
“As soon as man comes to life, he is at once old enough to die.”

"የሠው ልጅ ወደ ህይወት በመጣበት ቅፅበት ለሞት የተዘጋጀ ይሆናል"

Martin Heidegger

@ourrthought
🔥91
የትምህርት ቤት ምገባ (School feeding program)

እንደ ሀገር ትኩረቶቻችን ምን ላይ የተኮረ ነው? ብባል በድፍረት መናገር የምችለው ነገር ቢኖር ለችግር ምላሽ በመስጠት ላይ እላለሁ። ብዙ ጊዜ ችግር ሳይከሰት (prevention) ከመከላከል ይልቅ ችግሩ ከተከሰተ በኋላ (response) መፍትሄ መስጠት ይቀለናል። ለምሳሌ አንድ የመብራት ገመድ ለመውደቅ እየተንጋደደ 2 አመት ቢቆይ ዘወር ብሎ የሚመለከት አይኖርም። ይልቅ ፖሉ ወድቆ ሰው ከጎዳ ወይ ኤሌክትሪክ ተበጥሶ ጉዳቱን ለመከላከል እንፋጠናለን። ለምን? የሚለውን ዋቃ ነው የሚያውቀው።

ልክ እንደዛ ሁሉ የትምህርት ቤት ምገባ ከዛ የተለየ አላየውም። በ 2011 ዓ.ም በ ታከለ ኡማ ከንቲባነት ጊዜ በይፋ የተጀመረ በ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረ ፕሮግራም ነው። አሁን ላይ በ አዲስ አበባ ብቻ በቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች ላይ 779 ሺ ህፃናት በትምህርት ቤቶች ላይ ቁርስና ምሳ ይመገባሉ። ቢያንስ ለ አንዱ ህፃን 54 ብር ይወጣል ብለን ብናስብ በቀን ብቻ 42 ሚሊዮን ብር ለህፃናቱ ምገባ ይወጣል። ይሄ እንግዲህ የሰራተኞችን ወጪ አይጨምርም።

ይሄን ነገር በብዙ መልኩ ጠቃሚ ቢሆንም ግን ለኔ ጉዳቱ ያመዝናል። አላማው የተማሪዎችን የትምህርት መገኘት (attendance) ፣ ማቋረጥ ፣ በክፍል ውስጥ ርሀብ ለመቀነስና ከወላጆች ጫንቃ ለማላቀቅ የታሰበ ነው። ከላይ ከላዩ ጥሩ ጎኖች ያሉት ይመስላል። ግን አሁን ላይ የመንግስት ት/ቤት ምገባ በመኖሩ ብቻ ልጆችን በድፍረት ይወልዳሉ (ጥናት ቢሻም) ከብዙ ቦታ ተሰደው ወደ ምገባ ወዳለበት ቦታ ይጣሉ ፣ የተፈጠረውን ዕድል ተጠቅመው ህይወታቸውን ከመቀየር ይልቅ ሌላ ለመውለድ ይነሳሳሉ። አሁን ላይ ትምህርት ቤቶች ከትምህርት ቤትነት ይልቅ የሆድ መሙያ ገበታነታቸው በዝቷል። ልጆች ከትምህርቱ ይልቅ ስለ ምግቡ ነው የሚሄዱት ቤተሰቦቻቸውም (ሁሉንም አይወክልም) ከትምህርት ይልቅ እንዲመገቡ ብቻ የሚልኩ ናቸው። ትምህርት ቤቶች በግዴለሽ ለሚወለዱ ልጆች የሆድ መሙያነት ብቻ የተቀየረ ይመስላል። የመማር ማስተማር ስራው ሁለተኛ የሆነ ይመስላል።

አሁን ላይ ትምህርት ቤቶች ለ 2 ወር በመዘጋታቸው ልጆችን የሚመግባቸውና የሚውሉበት የጠፋ ይመስላል። ብዙዎቹ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ማብላት አቅቷቸው ለልመና እጃቸውን የሚዘረጉበት የ ጭንቅ 2 ወራቶች ናቸው። ልጅ እንደ ልጅ ሳይሆን ምግብ የሚበላና ቤት ውስጥ የሚውል መሆኑ ትዝ የሚላቸው አሁን ነው። በርግጥ ጉዳዩ ጥናት የሚፈልግ ቢሆንም ግን ለምን ሆነ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ቀላል ነው። ለችግሩ ጊዜያዊ መፍትሄ መስጠት እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ላይ አናተኩርም።

በወር ብቻ እስከ 935 ሚሊዮን ብር በጀት የሚወጣበት ማዕከል ልጆቹን አብልቶ ከመላክ እናቶቹን የስራ ዕድል መፍጠር ላይ አያተኩርም። ምናልባት ይሄ ገንዘብ ብቻ በየወሩ ለምገባ የሚወጣው ገንዘብ በየወሩ አነስተኛ ፋብሪካ እየተከፈተ እንደየ ችሎታቸው እናቶቻቸውን የስራ እድል ቢፈጠር የተሻለ የጥገኝነት እና የድህነት መጠኑን መቀነስ የሚቻልበት መንገድ ጥሩ ነው ባይ ነኝ። በዚህ መንገድ ከቀጠልን ቤተሰብ መሸከም የሚገባውን ሀላፊነት ወደሌሎች ተቋሞች ባዞርነው ቁጥር የ ተረጂነት ሱስና ልጆቻቸውን የበለጠ ከመዘንጋት ያለፈ ጥቅም አይኖረውም። ብዙዎቹ በግዴለሽነት የሚወልዱ አሉ። መንግስት ለሚያበላቸው ለምን እጨነቃለሁ? የሚሉ ገጥመውኛል።

ችግሩ እንዳይፈጠር መፍትሄ ማበጀት እንጂ ለችግሩ መፍትሄ መመለስ አስተማማኝ አይደለም። ብዙ የመንግስት ትምርህት ቤቶች ባለ 3 ፎቅ ሆነው ምንም የሚከላከል ብረት ሳይኖረው ልቅ ናቸው። ልጆች ከወደቁ በኋላ ለህክምና እና ለሌላ ወጪ የሚወጣው ብዙ ነው ግን ማንም ያንን ፎቆች በብረት ወይ በ ሽቦ ፍርግርግ ለማጠር የሚሞክር የለም። ልጆች ሲወድቁ ግን ልጆች ማሳከሚያ መለመን ይቀለናል።

ከመጎዳታችን በፊት መፍትሄ ሰጪ ያድርገን።

@ourrthought
👍95👏2
ሐሳቦቻችን
Photo
ማንነትን መቀበል

ማንነትህን ትቀበለዋለህ? ወይስ ዘወትር ትሸማቀቅበታለህ? የምታፍርበትስ ነገሮች አሉህ? ካሁን ካሁን ሰዎች ስለዛ ነገር አንስተው ተረቡኝ አበሸቁኝ የምትልበት ስስ ጎንህ? የምትሸሸው ርዕሰ ጉዳይ አለህ? የሚያባትትህ? ላብ የሚያጠምቅህ?

“Never forget what you are. The rest of the world will not. Wear it like armor, and it can never be used to hurt you.”

"ማንነትህን በፍፁም አትርሳው። የተቀረው አለም አይረሳውምና። እንደ ጦር ልብስ ታጠቀው። ማንም በዛ በኩል ሊጎዳህ አይቻለውም።"
ይህች ከላይ ያለችው ንግግር Game of thrones ላይ ከማደንቃት የ Tyrion Lannister ለ Jon snow ከነገረው ንግግር ውስጥ ቅመም ናት።

Jon snow ቤት ውስጥ የ አባት ልጅ ብቻ በመሆኑ ዲቃላ እየተባለ የሚጠራ ሙሉ ክብር ያላገኘ በዛ የሚበሳጭ ልጅ ነው። እድሉን የሚያማርርና መቀበል ያቃተው በመሆኑ ሰዎች በዛ ክፍተቱ እሱን ለማጥቃት ይቀላቸዋል። እና Tyrion ይሄን ነገር አስተውሎ Jon ብቻውን አዝኖ ይህችን ከላይ ያለችውን ንግግር ለ Jon snow ሲናገረው እናያለን።

በ psychology ውስጥ አንድ ሰው ጤናማ መሆኑ ከሚታይባቸው  መንገዶች አንዱ የሚመጣበትን የህይወት ፈተና ወይ ችግር  የሚቋቋምበት መንገድ ነው። በ psychology አንድ ሰው ለችግሩ የሚሰጠው ምላሽ ሁለት አይነት መንገድ አለ። የመጣብህን የህይወት ፈተና መቀየር ከቻልክ ትቀይረዋለህ። ከ አቅምህ በላይ ከሆነ ግን ትቀበለዋለህ። መቀየር የማትችለውን ነገር መቀበል ካልቻልክ ግን አዕምሮህን እየመረዘው የ አዕምሮህን ጤና ያዛባዋል። ይህ ችግርን ለመቆጣጠርና በችግርህ ላለመውደቅ ይረዳሀል።

Tyrion Lannister ድንክ (Dwarf) በመሆኑ በቤት ውስጥ ሲንቁትና እንደ አውሬ ሲያዩት ያደገ ሰው ነው። እንደ ታላቅ ወንድሙ የጦርነት ጀብድ የሌለው የሻሞላ ችሎታ የሌለው ነው። ድክመቱን በማመኑና በመቀበሉ የማይችለውን ሻሞላ አንስቶ አያቅተኝም የሚል ባለመሆኑ ትኩረቱን ወደ ንባብ በማዞር ወንድሙ በጦርነት ያገኘውን ጀብድ እሱ በንባብ አዕምሮውን በመጠቀም ብኩርናውን ለማግኘትና ከሰዎች ያጣውን ክብር ሲያገኝ እናያለን።

Jon snow አንድ ቀን Tyrion lannisrter ሲያነብ ለምን አብዝቶ እንደሚያነብ ይጠይቀዋል። የ Tyrion መልስ ድንቅ ነው።

"My brother has a sword and I have my mind. The sword needs a whetstone, and the mind needs to read.


"ወንድሜ ጎራዴ አለው እኔ ደሞ አዕምሮ አለኝ። ጎራዴ እንዲሳል ሞረድ እንደሚሻው ሁሉ አዕምሮም የሰላ እንዲሆን ንባብ ይፈልጋል።"

የ Tyrion ትልቁ ጥንካሬው ማንነቱን በመቀበሉ ውስጥ ያለ ከራስ ጋር የመስማማት ሂደት ነው። ከማንም በፊት አንተ ለራስህ ቦታ ሊኖርህና ሁሉን ነገርህን የመቀበል አቅም ሊኖርህ ይገባል።

ችግርህን ለማለፍና ጥንካሬ እንዲኖርህ ያለብህን ጉድለት ተቀብለህ መቀየር የምትችለውን እየቀየርክ የማትችለውን በመቀበል ነው። ከ ስብሀት ይሄን የሚገልፅ ጥሩ አባባል አለው። ቃል በቃል ባላስታውሰውም

"አምፖል ተቃጠለ ተብሎ ቤት አይቀየርም አምፖል ይቀየራል እንጂ። የማትችለውን ነገር መታገል መሸነፍ ሳይሆን አቅምን ለማይጠቅም ነገር ማባከን ነው።" የሚል።

አብዝተህ የምትሸሸው ነገር ያልተቀበልከው ማንነትህ የድክመትህ ምንጭ በመሆኑ አንተን በዛ በኩል ለመጣል መታገልም አይጠበቅባቸውም። ማንነትህን መቀበል የጥንካሬህ ምንጭ ነው። በጣም የምታፍርበትን ነገርህን የተቀበልከው ቀን ሰዎች እና እራስህ በዛ ነገር አንተን ማጥቃት ያቆማሉ። ወይ ትቀበለዋለህ አልያ በዛ ነገር እያሳደዱ ይወግሩሀል።

@ourrthought
11🔥2
Narcissistic Personality Disorder NPD

‎ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሙ እንደ ዳዊት ከሚደጋገሙ የ አዕምሮ ችግሮች ውስጥ Narcissistic Personality Disorder ዋነኛው ነው። ይህ ስም ከየት ነው የመጣው? ከሚለው ጀምሮ እንመልከት።

‎Narcissistic የሚለው ቃል የመጣው ከ ግሪክ አፈታሪክ (Greek myth) ነው። Narcissus የተባለ አንድ መልከመልካም ቆንጆ ወጣት የሆነ ያዩት ሴቶች በፍቅሩ የሚከንፉ እሱ ግን ለነሱ ፍቅር ቁብ የማይሰጠው ነበር። ከብዙ በፍቅር ከወደቁለት ሴቶች መሀል የገደል ማሚቶ (Echo) አንዷ ነበረች። ልቧ በፍቅር ተጎድቶ በሱ ፍቅር  ስሙን እየደጋገመች ድምጿ ብቻ እኪቀር በና ትጠፋለች።
‎ይሄን ያዩ የግሪክ አማልክት Narcissus ለ Echo ያሳየውን ሀዘኔታ የማጣትና ርህራሄ ቢስነት ለመቀጣጫ እንዲሆነው ዘንድ ዉሀ ሊጠጣ ሲሄድ የራሱን ፊት በውሀ ነፀብራቅ አይቶ በፍቅር እንዲወድቅና ፊቱን ብቻ እያየ ከራሱ ፍቅር ወድቆ ምግብና ውሀ ተጠምቶ ይሞታል። በሞተበት ቦታ Narcissus የተባለ አበባ በቀለበት።

‎ይህችን አፈ ታሪክ በመውሰድ Paul Nacke 1889 G.C Narcissism ለማብራራት የተጠቀመው። Narcissus የራሱን ምስል ውሀው ውስጥ አይቶ የራሱ ፊት መሆኑን ሳያውቅ ሌላ ሰው መስሎት በፍቅር የወደቀ መሆኑ ታሪኩ የሚያስረዳን ከራሱ ትክክለኛ ማንነት ጋር ሳይሆን በፍቅር የወደቀው በውጪ ከሚታየው ምስሉ ጋር በመሆኑ Narcissistic Personality Disorder ያለባቸውም ሰዎች ከሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት በሰዎች ውስጥ የራሳቸውን ስሜትና ፍላጎት ብቻ የሚመለከቱ መሆኑንና ከሰዎች ጋር ባላቸው በግንኙነት ውስጥ የራሳቸውን ነገር ብቻ ማዕከል ያደረጉ መሆኑን ለመግለፅ ነው።

‎Narcissistic Personality Disorder (NPD) ከ Personality Disorder ውስጥ የሚመደብ ዲስኦርደር ነው። NPD ማለት ከእውነታው የማይገናኝ ከፍተኛ ግምት ለራስ መስጠት የማይቋረጥ ከመጠን ያለፈ ትኩረትና እንክብካቤና አድናቆት ከሌላ የሚሹ ለሰዎች ስሜትና ጉዳት ግድ የማይላቸው ነገሮችን ከራሳቸው አንፃር የሚመለከቱ ከማንም በላይ እንደሆኑ የሚሰማቸው ርህራሄ የሌላቸው ናቸው። Narcissistic የሆኑ ሰዎች አለማቸውን የሚገነቡት ከውጪ ባለው አስተያየት ሙገሳ እንክብካቤ እንጂ ከራሳቸው ጋር ባላቸው እውነተኛ ማንነት አይደለም። የፍቅርና የጓደኝነት ግንኙነት መመስረት የሚቸገሩ ናቸው። cold lover ይባላሉ። ሰጥቶ ከመቀበል ይልቅ በመቀበል የሚኖሩ ናቸው። የትኛውም ግንኙነት ሲመሰርቱ ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ ናቸው።

‎በዚህ ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች እራሳቸውን የሚያዩት ለ አለም በጣም አስፈላጊ እንደሆኑ ከሁሉ በላይ ያልተገደበ ችሎታ ፣ጂኒየስ ፣ ቆንጆ ፣ አስተዋይ እና ፍቅር ያላቸው እንደሆኑ አድርገው ነው። ለሚያደርጉት ድርጊት ሙገሳን የሚሹ ካልተሞገሱ ግራ የሚገባቸው እነሱ መደነቅ የሚፈልጉበትን ድርጊት ሌላ ሰው ሲያደርገው የሚያጣጥሉ የሌሎችን ስኬት የሚያፌዙ እና የሚንቁ ናቸው። እራሳቸውን አያይዘው ማንሳትና ማወዳደር የሚፈልጉት ከታላላቅ ሰዎች ጋር ነው። እውቀት ባይኖራቸውም ችሎታቸው ውስን ቢሆንም እነሱ ግን ከ ስመ ጥር ዶ/ር ፣ ጠበቃ ፣ ሳይንቲስት ፣ ፈላስፋ ጋር የራሳቸውን ስራና ስም አያይዘው ማንሳትና መፎካከር የሚሹ ናቸው። መሬት ላይ ግን ምንም እውቀቱም ችሎታውም የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ።
‎ ስለራሳቸው የሚሰማቸው ምን አይነት ምጡት እንደሆኑ ፣ ማንም የሌለው ተሰጦ ያላቸው ፣ የተለዩ አድርገው ነው።

‎በ Narcissistic personality disorder የተጠቁ ሰዎች ትችትን አጥብቀው የሚፈሩ ሰዎች ሲነቅፏቸው እነዛ ሰዎች ከነሱ ጋር ችግር ስላለበትና ስለሚመቀኝ እንጂ ስህተት ሰርተው እንዳልሆነ የሚያስቡ ናቸው። አድናቆትን አብዝተው የመሻትና ሲደነቁ ጥሩ የሆነ ስሜት የሚሰማቸው (Hypo mood) ላይ የሚገቡ በተቃራኒ ትችትን የመፍራት ሁኔታቸው አቅማቸውን እንዳይጠቀሙ ያግዳቸዋል። ከሰዎች እራሳቸውን ማግለል እና ብቸኝነት የመሆን ስሜት ያሳድርባቸዋል።

‎በዚህ ችግር የተጠቁ ሰዎች ትልቁ ችግር ያላቸውን ባህሪ ማስተዋል አይችሉም። ሰዎች ችግራቸውን ሊነግሯቸው ሲሞክሩ ምን አለብኝና ነው? በማለት ወደ ሰውየው የሚያዞሩ ናቸው። የራሳቸውን ችግር የሰውየው እንደሆነ እንዲሰማው (Gaslight) የሚያደርጉ ሰዎችን ለራሳቸው ጥቅም (Manipulate) በማድረግ የሚታወቁ ናቸው። ግን ችግር እንዳለባቸው ማመን አይፈልጉም። ይልቅ ሰዎች ስለማይረዷቸው እንደሆነ ይሰማቸዋል።

Narcissistic Personality Disorder በዋናነት በ 4 ይከፈላል

Grandiosity Narcissistic : ስለራሳቸው ያላቸው ምልከታ ከመጠን ያለፈ ነው። አለም ያለሱ የሚጨለምባት የሚመስላቸው የሚመስላቸው። ነቀፌታን የማይቀበሉ ከፍተኛ የሆነ ሙገሳን የሚሹ ናቸው። እኔ እንዲህ አድርጌ እንዲህ ሰርቼ ማንም ያላሳያችሁን አሳይቼ የሚሉ ናቸው። ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመን ያላቸው የሚመስሉ ሰዎችን የሚንቁ ናቸው።

Malignant Narcissistic : እኚህ ውስጥ ያሉ ሰዎችን manipulate, gaslight, exploit የሚያደርጉ ለ ፍቅር አጋሮቻቸው ሀዘኔታ የሌላቸው በሰዎች የሚጠቀሙ ናቸው።

Covert Narcissistic : በዚህኛው የ Narcissism ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች እነሱ በጣም እምቅ አቅም ኖሮዋቸው አለም ግን እነሱን ሊረዳቸው እንዳልቻለና እነሱ ያላቸውን የንቃት ደረጃ አለም ያልደረሰ በመሆኑና የነሱ አቅም ከሁሉ በላይ እንደሆነና አለምንና ሰዎቿን ለውድቀታቸው የሚወቅሱ ናቸው። ብዙ ግዜ በዚህ ውስጥ ያሉ ሰዎች Low self esteem ያላቸው ሊመስሉ ይችላሉ። ግን ነገሩን ጠልቀው ሲያስተውሏቸው ከሁሉ በላይ የሆነ እውቀት እንዳላቸው በውጣቸው የሚያስቡ ናቸው። የነሱ ችሎታና እውቀት መውጣት ያልቻለው አለም የነሱ የማወቅና የማሰላሰል አቅም ላይ ስላልደረሰ ነው ብለው እራሳቸውን እንደ ተጠቂ የሚቆጥሩት ናቸው። ብዙ ጊዜ የሚረዳቸው ሰው እንደሌለ ስለሚያስቡ በ ድባቴ (Depression) የመጠቃትና በሱስ የመውደቅ እድላቸው ሰፊ ነው። አልፎ አልፎ አንዳንድ ደራሲዎች ሽው ትልባቸዋለች።

Communal Narcissistic : ይሄኛው አሁን ላይ ባለው የ social media ዘመን በስፋት የሚታይ ነው። ልክ የሆነች ችግር በተከሰተች ቁጥር ችግሩ በተከሰተበት ቦታ የሆነች ድጋፍ ይዘው በመሄድ የሚሰጡትን ድጋፍ በየ social media ያጥለቀልቁታል። ላደረጓት እያንዳንዷ ዕርዳታ ምስጋና የሚሹ አቤት ቸርነትህ አቤት መልካምነትህ አንተኮ ባትደግፋቸው ማለቃቸው ነበር እንዲባሉ የሚሹ ከ ካሜራ ጀርባ ምንም ድጋፍ ማድረግ የማይፈልጉ ናቸው። ልክ የሆነች ድርቅ ስትከሰት ወይ ጎርፍ ለነሱ ፌሽታ ነው። አንድ ኪሎ ዱቄትና አንድ ዘይት ሰጥተው በዛ ነገር መወደስና መመስገን የሚሹ ናቸው። ድጋፍ የሚያደርጉት ለሰዎቹ አዝነው ሳይሆን ለ መወደስና ለመመስገን በዛም Like እና የበጎ ሰው አዋርድ ለማግኘት አቅደው ነው። ከላይ ከላይ ስፊታዩ ምስኪንና ደግ ነው የሚመስሉት ከጀርባቸው ግን ያለው ምክንያት ውዳሴ እና Like ነው። የ Tik tok አለም ይሄን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። የሆነች ኮሽ ያለች ነገር ስትኖር ካሜራቸውን አንጠልጥለው ሲሯሯጡ ማየት የተለመደ ነው።

@ourrthought
🔥43

‎በአምስተኛነት የሚያዝ አለ (Bening) በቅርቡ የመጣ። ያላቸውን ቁስና ማንኛውንም ነገር የሚያስቆጥሩ የሌሎቹን የሚያናንቁ። እነሱ የሚቀቡት ሽቶ ማንም የሌለው እንደሆነ የሚነዱት መኪና ሱፍ ማንም የሌውወ መሆኑን የሌሎቹ ቁስ ተራና ርካሽ መሆኑን የሚያሳዩ ስለሚበሉት ምግብ ውድነት በየቀኑ በየደቂቃው የሚያዳንቁ የሚያወሩ።

የ Narcissism Personality Disorder ዋና ዋና ምልክቶች ከሚባሉት በዋናነት 9 ምልክቶች ይጠቀሳሉ።

1. Lack of empathy ( ርህራሄ ያለማሳየት) : በዚህ በ Narcisstic የተጠቁ ሰዎች ለሌሎች ሰዎት ሀዘኔታና ርህራሄ የላቸውም። በድለዋችሁም ወይ በነሱ ምክንያት እናንተ ችግር ገብታቹሁም ህይወታቹህ ተመሰቃቅሎ ምንም ርህራሄ አይሰማቸውም። ትዳር ውስጥ ወይ ለልጆቻቸውም ስሜት አልባ የመሆን ችግር ይታይባቸዋል። ብዙ ጊዜን ችግር ከ Psychopath ጋር የሚያገናኙበት መንገድ አለ ልዩነቱ psychopath ከነጭራሹን ርህራሄና ሀዘን የማይሰማቸው ሲሆን ናርሲስቲክ ችግር ያለባቸው ግን ስለድርጊታቸው አልፎ አልፎ ሀዘን ውል ሊልባቸው ይችላል።

2. Entitlement : ከሌሎች የተለዩ እንደሆኑ ማሰብ። እኔ የተሻለ ትኩረትና እንክብካቤ ማግኘት አለብኝ። ልዩ በመሆኔ እኔን ብቻ እንክብካቤ ይገባኛል የሚል አጀባና እንክብካቤ የሚሹ ናቸው።

3.Grandiosity behavior : ስለራሳው ያላቸው ግምት ከነባራዊው ሁኔታ ጋር የማይገጥምና ስለራሳቸው ያላቸው ግምት መሬት ላይ ካለው የማይገናኝ ከልክ በላይ የተጋነነ ነው። ህልማቸው ከሁሉ የበላይ የሆነ ያክል ይሰማቸዋል። ግን በውኑ አለም ያለው የራሳቸው አቅምና እውቀት ከዛ ያነሰ ነው።

4. Superficiality : ሁሉ ነገራቸውን ከሚኖሩበት መኖሪያ ግዝፈት ፣ ከሚበሉት ምግብ ውድነት ፣ ከሚለብሱት ልብስ ፣ ጫማ ፣ መኪና ወዘተረፈ የሚለኩ ከዛ በስተጀርባ ያለውን ማንነታቸውን የማያሳዩ በውጪው ነገር ብቻ ለራሳቸውና ለሰዎች ግምት የሚሰጡ ናቸው።

5. Chronic seeking of admiration : ይሄኛው የማይቋረጥ ውደሳ ሙገሳ መቀበል የሚሹ ናቸው። አንተኮ ትለያየህ ፣ ካንተ ውጪ ሰው ለምኔ ፣ ዛሬ ደሞ ያደረከው ድንቅ ነው እያላቹህ በሚሰሩት እያንዳንዱ ነገር እየተከተላቹሁ ማቆለጳጳስ አለባቹህ። ይሄ በዚህ ባለንበት like, comment and share እየቆጠሩ የሚደሰቱና like በቀነሰ ቁጥር አለማቸው የሚጨልምባቸው አይነተኞች ናቸው።

6. Tendency to rage : ይሄኛው ባህሪ ከነሱ ሀሳብ ጋር ካልተስማማቹህ እና እነሱን እሺ ካላላቹህ ስሜታቸውን ቁጣቸውን መቆጣጠርና መግራት የሚቸግራቸው ናቸው። በትንሹ ነገር እያንባረቁ ሊያሸብሯቹህ ይችላል። ትዕግስት እና መረጋጋት የተሳናቸው ናቸው። እንዲህ አድርጉ ብለው ከዘገያቹህ በቁጣ በጩኸት መድረሻ ያሳጧቹሀል። ብዙ ጊዜ አለቆች የሚታይባቸው ችግር ነው።

7. Arrogance : ይሄኛው ደሞ በቃ ከኔ በላይ አንተ ታውቃለህ? ማነው ከኔ በላይ አዋቂ? የሚሉ ሁሉም ነገር ላይ ከነሱ በላይ አዋቂ ያለ የማይመስላቸው ሰዎች ናቸው። ምንም በማያውቁት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ፕሮፌሰሩን እከሌኮ መሀይም ነው ሊሏቹህ ይችላል። በግልፅ እኔ ካንተም ከማንም በላይ ነኝ ይላሉ በድፍረት እውነታው የተገላቢጦሽም ሆኖ።

8. High or low self esteem : ይሄኛው ከልክ ያለፈ በራስ መተማመን ወይ ዝቅ ያለ ይኖራቸዋል።

9. Envy and satisfaction by others suffering : ከፍተኛ የሆነ ቅናት ይሰማቸዋል። ሰው ሲሳካለት ይደብራቸዋል ፍቅረኛቸውም ሊሆን ይችላል። በሌሎች ሰዎች ስቃይና ሀዘን ከነሱ ጋር ጠላት ባትሆኑም በስቃያቹ ሊደሰቱ ይችላሉ ማግኘታቹህ ያንገበግባቸዋል።

ሌሎችም ብዙ አሉ ግን አብዛኛዎቹን ናርሲስቲክ ሰዎች የሚያመሳስላቸው እነዚህ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ቢያንስ አምስቱ ምልክቶችን በራሳቹህ ላይ የምታዩ ከሆነ ይህ ችግር እንዳለባቹህ አምናቹህ counseling መጀመር ነው ያለባቹህ።

ይሄ የ Narcissism Personality Disorder ችግር መነሻው ከየት ነው? ወይ አባባሹ ምንድነው? ካላቹህ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል። Nature (በተፈጥሮ) vs Nurture (በመማር) ቤተሰብ የሚቀርፅበት ወይ የሚያሳድግበት መንገድ ማለት ነው። አብዛኛውን ድርሻ የሚወስደው ከተወለድን በኋላ ያለው የ አስተዳደግ ውጤትና ልምምድ ነው።

Nature (በተፈጥሮ) አንዳንድ ልጆች በተፈጥሮ በ Biological dysfunction ከሌሎች ጋር ያላቸው መስተጋብር የላላ ሊሆን ይችላል ያም ባህሪያቸው በቤተሰብ እንክብካቤና ፍቅር ካልተያዘ ችግሩን ሊያባብሰው ይችላል።
የቤተሰብ አስተዳደግ ዘዴ (Attachment styles) ወሳኝ ነው። ከ 4ቱ የ attachment style ልጆች Avoidant attachment እና Neglect Attachment ያለበት ቤት ውስጥ የሚያድጉ ልጆች በልጅነታቸው Sensitive ሲሆኑና emotinal ሲሆኑ ለዛ ስሜታቸው ሲያድጉምላሽ የማያገኙ ከሆነ የ NPD የመጠቃት እድላቸውን የሰፋ ያደርገዋል።

በ Modeling (አርዕያ) : የ ናርሲስቲክ ቤት ውስጥ የሚያድጉ ልጆች ወላጆቻቸውን በመኮረጅ ባህሪያቸውን ይወስዳሉ።
Conditional love : ልጆች የሆነ ስራ ስለሰሩ ብቻ ቤተሰብ ደስ የሚለውን ስላደረጉ የምናመሰግናቸውና የምንወዳቸው ከሆነ ለመወደድ ብለው ወይ ይሁንታ ለማግኘች ያልተገባ ነገር ለማድረግ ይነሳሳሉ። Communal narcissism ብዙ ጊዜ ከዚህ ጋር ትስስር አለው።
Extrinsic focus : ልጆችን በውጫዊው አለም ብቻ ለነሱ ቦታ መስጠት ለምሳሌ ትምህርት አንደኛ ስለወጡ የሆነን ነገር ስላሸነፉ በዛ ነገር ብቻ እነሱን ገድበን የምናወድስና በውጪው አለም ባሳኩት ነገር የምናወድስና የምንወስናቸው ከሆነ ትልቅም ከሆኑ በኋላ በ tik tok like IG Fb like and comment እራሳቸውን የማያያዝ ችግር ላይ ይወድቃሉ።

NPD አብዛኛውን ጊዜ ከ Boarder line disorder, sociopath, Depression, paranoid disorder ጋር የመያያዝ እድሉ ሰፊ ነው።

ይህን ችግር እንደማንኛውም የ ማንነት ችግሮች በ Counseling እንዲሻሻል ለማድረግ ይቻላል። በ Dr. Ramania ገለፃ መሠረት በ አሜሪካ ውስጥ 6 ሰዎች 1 ሰው የ ናርሲስቲክ ህመም ተጠቂ እንደሆነ ይታሰባል። በ DSM መሠረት በ community sample 6.2% እንደሆነ ይታሰባል።

@ourrthought
🔥75
የኢትዮጵያ ህዝብ የእውቀትን ጥቅም በደንብ ለመገንዘብ ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩት ፤ ትልቁና ቁልፉ የ እውቀት መንገድ ጽሕፈት ነው ፤ ፊደል ነው ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የራሳችን ፊደል ነበረን ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የራሳችን በበሬዎች የማረስ ዘዴ ነበረን ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት በአጋሜ ፤ በየጁ ፤ በኮንሶ የእርከንና የመስኖ ዘዴዎች ነበሩን ፤ ለምዕተ-ዓመታት ታላላቅ ሐውልቶችንና ሕንፃዎችን የመሥራት ጥበብ ነበረን ፤ ከብዙ ምዕተ-ዓመታት በፊት በሰረገላ እንጠቀም ነበር ፤ ለብዙ ዘመናት መፍተልና መሸመን የታወቀ ነበር ፤ ይህ ሁሉ ዘዴ እንደ እውቀት በጽሑፍ አልተላለፈም ፤ ስለዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ አህያ ከመንዳትና በጎጆ ውስጥ ከመኖር ያልወጣበት ምክንያት ምንድን ነው?

በኢትዮጵያ ውስጥ እውቀት ፈላጊ አልነበረውም ፤ አሁንም የለውም።


አዳፍኔ ፍርሀትና መክሸፍ
‎ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም


@ourrthought
9🔥2
ሐሳቦቻችን
የኢትዮጵያ ህዝብ የእውቀትን ጥቅም በደንብ ለመገንዘብ ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩት ፤ ትልቁና ቁልፉ የ እውቀት መንገድ ጽሕፈት ነው ፤ ፊደል ነው ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የራሳችን ፊደል ነበረን ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የራሳችን በበሬዎች የማረስ ዘዴ ነበረን ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት በአጋሜ ፤ በየጁ ፤ በኮንሶ የእርከንና የመስኖ ዘዴዎች ነበሩን ፤ ለምዕተ-ዓመታት ታላላቅ ሐውልቶችንና ሕንፃዎችን የመሥራት ጥበብ…
ስለ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ካነሳን አይቀር አንድ የምወደው ጨዋታ አለች።

«ኬንያ ናይሮቢ አንዲት መዝናኛ ቤት ተገኝቼ እየተዝናናሁ ነው። ቤቱ እንደ ፓርቲ ቤት ያለ ነው። ባንዱ ጥግ መጠጤን ይዤ፣ የዳንሱ ወለል ላይ ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚደንሱ ወጣቶችን አያለሁ። በዚህ መሃል የባሕር ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ እንግሊዛዊያን ነጮች ገቡ። አንዱ እንግሊዛዊ ቀጥታ ወደ ዳንስ ወለሉ ሄደና ከወዳጁ ጋር እየደነሰ ያለውን ኬንያዊ በካልቾ መታው። ኬንያዊው ተርበድብዶ የሴት ወዳጁን ጥሎ ገሸሽ አለ። እንግሊዛዊውም ከዛች ኬንያዊት ጋር መደነስ ጀመረ። በእንግሊዛዊው ድርጊት በጣም ተናደድኩ። ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁና ወደ ዳንስ ወለሉ አመራሁ። እኔም እንግሊዛዊውን በካልቾ ጠልዤ ኬንያዊቷን ተቀበልኩ። ጥቂት ካስደነስኳትም በኋላ ለተቀማው ኬንያዊ አስረከብኩ። ይህን ፈፅሜ ወደ መቀመጫዬ ሳመራ እንግሊዛዊው የጠየቀኝ አንድ ጥያቄ ነበር ፦ "ኢትዮጵያዊ ነህ?" የሚል።»

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ነብሳቸው በሰላም ትረፍ ባሉበት ይመቻቸው።

@ourrthought
9🔥2😁2🙏2
ቅድም ከ አንድ ኢ-አማኝ (Atheist) ጋር እያወራሁ ምን አለኝ

"እንደውም አለም ላይ ላለ ችግር ሁሉ ተጠያቂው ፈጣሪ ነው።" እኔም ቢቸግረኝ
"ፈጣሪ የለም ብለህ ካመንክ አሁን ከየት አገኘኸው
?"

ፈጣሪ ከሌለ መውቀስ ይቻላል?

@ourrthought
😁9👏2
ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥለሴ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ

ይህ ፎቶ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ በ እስር ላይ እያሉ የተነሱት ነው። በወርቅ መታጠቢያ የታጠቡ በቅንጦት የኖሩ ንጉሠ ነገስት በመጨረሻዎቹ ሰዐታት ግን በአንዲት ጣውላ ወንበር ላይ ተክዘው ማየት ልብ የሚሰብር ነው።

@ourrthought
😢7😭1
ሐሳቦቻችን
Photo
The Logical Problem of Evil (የሎጂክ የመከራ ጥያቄ)

በጄ.ኤል. ማኪ (J.L. Mackie) እና በአልቪን ፕላንቲንጋ (Alvin Plantinga) መካከል የተደረገ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተካሄዱት ታላላቅ የሃይማኖት ፍልስፍና (Philosophy of Religion) ክርክሮች አንዱ ነው::

አውስትራሊያዊው ኤቲስት ፈላስፋ ማኪ 'Evil and Omnipotence' በተሰኘው ታዋቂ ጽሁፉ የሚከተለውን ጥንካሬ ያለው የሎጂክ አጣብቂኝ አቀረበ፦
​- እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው (Omnipotent):
​- እግዚአብሔር ፍጹም ደግ/ርህሩህ ነው (Wholly Good):
​- መከራ/ክፋት በዓለም ላይ አለ (Evil exists)
​ማኪ እንደተናገረው እኚህ ሶስት ሀሳቦች በአንድ ላይ ሲቀመጡ በሎጂክ እርስ በእርሳቸው ይጋጫሉ (Logical Contradiction)::
​የማኪ ዋና ጥያቄ፦ 'አንድ ፍጹም ደግ የሆነ አካል በተቻለው መጠን ክፋትን ያጠፋል::ሁሉን ቻይ የሆነ አካል ደግሞ ማድረግ የማይችለው ነገር የለም::ስለዚህ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እና ፍጹም ደግ ከሆነ ክፋት በፍጹም ሊኖር አይችልም ነበር::ነገር ግን ክፋት አለ: ስለዚህ ሁሉን ቻይ እና ፍጹም ደግ የሆነ ፈጣሪ በሎጂክ ደረጃ ሊኖር አይችልም::'
ማኪ የነፃ ፈቃድን (Free Will) ሀሳብ ውድቅ ሲያደርግም፦ 'ሁሉን ቻይ ፈጣሪ ሰዎችን በነፃ ፈቃዳቸው ሁልጊዜ መልካም ነገርን ብቻ የሚያደርጉ አድርጎ መፍጠር ይችል ነበር::ያንን አለማድረጉ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ወይም ደግ አለመሆኑን ያሳያል' አለ::

​አሜሪካዊው ክርስቲያን ፈላስፋ አልቪን ፕላንቲንጋ 'The Nature of Necessity' በሚለው መጽሐፉ ለተጠየቀው ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ሰጠ::ፕላንቲንጋ የማኪን መከራከሪያ ለማፍረስ የሞከረው 'የሎጂክ ወሰን' እና 'የነፃ ፈቃድ'( Free will defense )ባህሪ ላይ በማተኮር ነው፦
​አንደኛ በሎጂክ የማይቻሉ ነገሮች (Logical Impossibilities)​ፕላንቲንጋ እንዳለው ​በፍልስፍና እና በሎጂክ ህግ 'በሎጂክ የማይቻል ነገር' የሚባለው የፈጣሪ የአቅም ማነስ ሳይሆን: የሀሳቡ ወይም የቃላቱ ራሱ እርስ በእርስ መጋጨት እና ትርጉም አልባ መሆን ነው:: ለምሳሌ ኢአማንያን 'ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ከሆነ ራሱ ሊሸከመው የማይችለውን ድንጋይ መፍጠር ይችላል?' የሚል አጣብቂኝ ጥያቄ ያነሳሉ:: ነገር ግን 'ሁሉን ቻይ አካል' እና 'እሱ ሊሸከመው የማይችለው ድንጋይ: የሚሉት ሁለት ሀሳቦች በቃላት ደረጃ እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ተቃራኒ ሀሳቦች ናቸው:: ሁሉን ቻይነት (Omnipotence) ማለት በሎጂክ ሊከናወኑ የሚችሉ ነገሮችን በሙሉ ማድረግ እንጂ: እንደ 'ባለ አራት ማዕዘን ክበብ' ወይም 'ሊሸከሙት የማይችሉት ድንጋይ' ያሉ ትርጉም አልባ እና እርስ በእርስ የሚቃረኑ ሀሳቦችን መፍጠር ማለት አይደለም:: ስለዚህ ነገሩ ያልተደረገው ፈጣሪ የመሸከም ወይም የመፍጠር አቅም አጥቶ ሳይሆን: ሀሳቡ በራሱ በሎጂክ ደረጃ የማይቻል ስለሆነ ነው::
​ሁለተኛ ነፃ ፈቃድ እና በግድ ማሰራት(Transworld Depravity)
​አንድ ሰው 'እውነተኛ ነፃ ፈቃድ' አለው ከተባለ ያንን ሰው 'በግድ ሁልጊዜ መልካም ብቻ እንዲመርጥ ማድረግ በሎጂክ እርስ በእርሱ የሚጋጭ (Contradiction) ነው!​ፈጣሪ ሰዎችን በግድ መልካም ብቻ የሚያደርጉ አድርጎ ቢፈጥራቸው ኖሮ ሰዎች ነፃ ፈቃድ ያላቸው ፍጡራን አይሆኑም ነበር:: እውነተኛ ነፃ ፈቃድ ለመስጠት ደግሞ ሰዎቹ የመሳሳት እና ክፉ የመምረጥ እድል/አማራጭ ሊኖራቸው ይገባል::

​በስተመጨረሻም የፕላንቲንጋ ድምዳሜ 'እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ቢሆንም እንኳ ነፃ ፈቃድ ያላቸውን ፍጡራን ፈጥሮ በዚያው ቅጽበት በግድ መልካም ብቻ እንዲሰሩ ሊያደርጋቸው አይችልም::ስለዚህ የክፋት/መከራ መኖር የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት ወይም ፍጹም ደግነት በሎጂክ አይቃረንም::' የሚል ነው::
​በፍልስፍናው ዓለም ይህ ክርክር ከተጠናቀቀ በኋላ በሰፊው የታመነበት ውጤት የፕላንቲንጋን አሸናፊነት ሚያስረግጥ ነው:: አብዛኞቹ የአካዳሚክ ፈላስፎች (ኢ-አማንያንን ጨምሮ) ፕላንቲንጋ 'የሎጂክ የመከራ ጥያቄን'(The Logical Problem of Evil) ሙሉ በሙሉ ማፍረሱን ተቀብለዋል::ማኪ ራሱ በበኩሉ የፕላንቲንጋ ምላሽ የነበረበትን የሎጂክ አጣብቂኝ እንደፈታው በኋላ ላይ አምኗል::ግን ይህ ውጤት ክርክሩን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዛውሮት ነበር የተቋጨው ::የፕላንቲንጋ 'Free Will Defense' የሎጂክ አጣብቂኙን ቢፈታውም ኢ-አማንያን ክርክሩን ከሎጂክ ጥያቄ ወደ 'Evidential Problem of Evil' (የመከራው መጠን እና አይነት አሳማኝነት) አዞሩት።
​በጠቅላላው ማኪ 'እግዚአብሔር እና ክፋት በሎጂክ አብረው ሊኖሩ አይችሉም' ብሎ ሲሞግት ፕላንቲንጋ ደግሞ 'በነፃ ፈቃድ ምክንያት ሁለቱ በሎጂክ አብረው ሊኖሩ ይችላሉ' በማለት ክርክሩን በበላይነት አጠናቋል።

Evidential Problem of Evil (በማስረጃ ላይ የተመሰረተው የመከራ ጥያቄ)

በፍልስፍና እና በሃይማኖት ጥናት (Theology) ውስጥ 'መከራ እና ፍጹም ፈጣሪ በሎጂክ አብሮ መኖር አይችሉም' ከሚለው ይልቅ 'በዓለም ላይ ያለው የመከራ መጠን: አይነት እና ከንቱነት ፈጣሪ የመኖሩን እድል በጣም ያቀጥነዋል/ያሳንሰዋል' የሚል መከራከሪያ ነው::
​አልቪን ፕላንቲንጋ 'ፈጣሪ እና መከራ በሎጂክ ደረጃ አብረው ሊኖሩ ይችላሉ' ብሎ ማስመስከሩን ተከትሎ: ኢ-አማንያን (Atheists) መከራከሪያቸውን ከቀጥታ የሎጂክ ግጭት ወደዚህ በማስረጃ/በእድል (Probability) ላይ የተመሰረተ የአመንክዮ አቀራረብ አዞሩት:-ሁሉን ቻይ: ሁሉን አዋቂ እና ፍጹም ርህሩህ የሆነ ፈጣሪ ካለ :ያለ በቂ/መልካም ምክንያት የሚከሰት ህመም ወይም መከራ እንዲኖር አይፈቅድም! ነገር ግን በዓለም ላይ ምንም አይነት መልካም ነገር የማይወጣቸው: ከንቱ እና እጅግ በጣም አሰቃቂ የሆኑ የመከራ አይነቶች (Gratuitous Evils) አሉ:: ስለዚህ ሁሉን ቻይ እና ፍጹም ርህሩህ የሆነ ፈጣሪ የመኖር እድሉ እጅግ በጣም አነስተኛ ነው (ወይም የለም)::
​ይህንን መከራከሪያ በስፋት ወደ ፍልስፍና ዓለም ያመጣው አሜሪካዊው ፈላስፋ ዊልያም ሮው(William Rowe) ሲሆን:ሀሳቡን በሁለት ታዋቂ ምሳሌዎች ያስረዳል፦ የመጀመሪያው የጫካው ሚዳቆ (The Fawn in the Forest)ነው ::ሰው በማይደርስበት የራቀ ደን ውስጥ የመብረቅ አደጋ አጋጥሞ ሰደድ እሳት ይነሳል::በዚያ እሳት ውስጥ አንድ የዱር ሚዳቆ በጽኑ ተቃጥሎ ለቀናት እየተሰቃየ ይሞታል::
​ይህ መከራ የሰውን ነፃ ፈቃድ አይመለከትም:: ለማንም ሰው ትምህርት ወይም 'የነፍስ ማነፅያ' አይሆንም: ምክንያቱም ማንም አላየውምና::​ጥያቄውም: ሁሉን አዋቂ እና ርህሩህ ፈጣሪ ይሄን አሰቃቂ ህመም ሚዳቆዋ ሳትሰቃይ ቀጥታ እንድትሞት ማድረግ ወይም ማስቀረት አይችልም ነበር? ነው::
​ሁለተኛው ምሳሌ ደሞ የህፃናት መበደል/መሰቃየት ነው::በንጹሃን ህፃናት ላይ የሚደርሱ አሰቃቂ ጥቃቶች በሽታዎች እና ሰቆቃዎችን ኃላፊነት ማን ይወስዳል? የሚል::

@ourrthought
7🔥2
​ለዚህ Evidential Problem of Evil እሳቤ አማንያን እና የሃይማኖት ፈላስፎች መከራከሪያ ሚሆኑ ሶስት ዋና ዋና ምላሾችን ይሰጣሉ፦
​አንደኛ Skeptical Theism (የሰው ልጅ እውቀት ውስንነት) ሲሆን :ሀሳቡ፦ እኛ የሰው ልጆች የፈጣሪን ሙሉ እቅድ እና ትልቅ ምስል (Big Picture) የማየት አቅም የለንም::ለምሳሌ፦ አንድ ትንሽ ልጅ ሀኪም መርፌ ሲወጋው ሀኪሙ ያለ ምክንያት የሚያሰቃየው ይመስለዋል::ምክንያቱም መርፌው ከከፋ በሽታ እንደሚጠብቀው የመረዳት አቅም ስለሌለው ነው:: እኛም አንድ መከራ 'ከንቱ ነው' ብለን ስንደመድም ከጀርባው ያለውን አጠቃላይ ምክንያት የማወቅ ውስንነት ስላለን ሊሆን ይችላል::
​ሁለተኛ Greater Good Defense (ታላቁ መልካም ነገር) ​ፈጣሪ አንዳንድ አሰቃቂ መከራዎችን የሚፈቅደው: ከእነዚያ መከራዎች በስተጀርባ የበለጠ ታላቅ መልካም ነገር (Greater Good) ስለሚወጣ ወይም ከእዚያ የከፋ ነገር ስለሚከለክል ነው የሚል መከራከሪያ ነው::
ሌላኛውና ሶስተኛው Theistic Evidence (የፈጣሪ ህልውና ሌሎች ማስረጃዎች) ሲሆን: የመከራ ጥያቄ ብቻውን አይቆምም:: የዓለም መፈጠር: የፊዚክስ ህግጋት ውስብስብነት (Fine-tuning): የሞራል ህጎች መኖር እና የህይወት አመጣጥ ፈጣሪ የመኖሩን እድል እጅግ በጣም ከፍተኛ ያደርጉታል:: ​ስለዚህ ሌሎች ሚዛኖች ፈጣሪ እንዳለ የሚያሳዩ ከሆነ: የመከራን ምክንያት ሙሉ በሙሉ ባናውቀውም ፈጣሪ የለም ወደሚል መደምደሚያ አንደርስም::

16/11/2018 ዓ.ም
By ሀኑ-ን

@ourrthought
🔥83😁1
👏2
ሐሳቦቻችን
Photo
አንድ አንዴ ውስጤ ያለሁ ሀሳብ ልክ እንደ ማዕበል ይንጠኛል። ሲብስበት ደግሞ ልክ እንደ ወተት ገንፍዬ ካሎጣው ይለኛል። ዝም ካልኩት በዛው ይጠፋል እና ከመጥፋቱ በፊት ብዕሬን አንስቼ እሞነጫጭረዋለሁ ካልሆነ ሰላም አይሰጠኝም። የሆነ ጊዜ አለማየሁ ገላጋይ የማከብረው ደራሲ የሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ እንዲህ ሲል ሰምቼዋለሁ፤

"እኔ ብዙ ጊዜ መፅሀፍ ከመፃፌ በፊት በ አእምሮዬ ታሪኩን ጀምሬ እጨርሰዋለሁ ከዛን በኋላ ነው በወረቀት የማሰፍር ፣ እስከዛሬ አንድ ሶስት የሚሆኑ ሙሉ ያለቁ ልብወለድ መፅሀፍ አእምሮዬ ውስጥ ጠፍቶብኛል" ያለውን አልረሳውም፣ እኔም ሀሳቤ እንደንጋት ጤዛ ከመጥፋቱ በፊት ልፅፈው ብዕሬን አንስቼ መሞነጫጨር ጀመርኩ።

"ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እነሆ ለሀገራችን ክብር ብለው ህይወታቸውን አሳልፈው ከሰጡ 86 ዓመታትን አስቆጠሩ።" እያለ ሬድዮኑ ይለፈልፋል። እኔም በዛው በሀሳብ ባህር ጭልጥ ብዬ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም የሽምጥ የኋሊት ጋለብኩና በምናቤ አቡነ ጴጥሮስ ጋር ተሰየምኩ።

ወቅቱ ዳግም ጣሊያን ወረራ ላይ ነበር። ቂጡን በሳንጃ ተወግቶ ከተባረረ በኋላ አርባ አመታትን ቆይቶ ዳግም ለበቀል የመጣበት ወቅት ነበር። ታዲያ የዛን ጊዜ ህዝቡ ሁሉ በአንድነት የሚሰማቸው፣ የሚያከብራቸው እና የሚወዳቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ነበር። ታዲያ ይሄን የተገነዘበው ግራዚያኒ አቡነ ጴጥሮስ ዘንድ ሄዶ ህዝቡን ከጣሊያን ጎን ሆኖ እንዲያስገዙት ህዝቡ እንዲታዘዝ እሳቸውም የተሻለ ነገር እንደሚያገኙ ነገራቸው።

እሳቸውም " ጣሊያንን ተቀበሉ ብዬ አልሰብክም፣ እንኳን ህዝቡ መሬቱ እንዳይታዘዝ ብዬ አውግዤዋለሁ" አሉ። ግራዚያኒም ህዝብ በተሰበሰበበት አስረሽኖ ገደላቸው።

እንኳንም ዛሬ ላይ አልሆነ ብዬ ፈጣሪን አመሰገንኩት። ለምን አትሉም!? አሁን ዘመን ላይ ቢሆን ደግሞ ግራዚያኒ ሳይሆን ህዝቡ ነበር 'ሚረሽናቸው። የስልጣኔ ፀር፣ እኛ እንዳናድግ እንቅፋት ሊሆኑብን ነው፣ የድሮ ናፊቂ! ብሎ ሲያበሻቅጣቸው ሳልኩትና ዘገነነኝ፣ እንኳንም የዛኔ ሆነ ሆሆሆ።

ግራዚያኒ ህዝቡን "ጠላታችን ስለሞተ አጨብጭቡ።" አላቸው። ህዝቡም በጭብጨባ አቀለጠው አሉ ይሄ አጨብጫቢ ህዝብ! ለገዳዩም ላስገዳዩም እንዳጨበጨበ ይሄው እስከአሁን አለ። የእነሱ ልጆች ዛሬም ድረስ በየስብሰባው በየፓርላማው እንዳጨበጨቡ ነው አሉ። አይ አንቺ ሀገር ስንት ጠባቂ ልጆችሽን በጭብጨባ ሸኘሽ!፣ መች ይሁን ማጨብጨቡ የሚበቃሽ!? መዳፍሽ ለጠላቶችሽ ማጨብጨቡን ትቶ ሰይፍ የሚጨብጠው! መች ይሆን ልጆችሽን መገበር የሚበቃሽ? እንጃልሽ!።

በአንድ ወቅት የሆነ ፍልስፍና ፀጣፍ ላይ የቃረምኩት ትዝ አለኝ። " በአንድ ወቅት ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ እስራኤል ከተማ ሲመጣ በመንገድ ያገኙት ሰዎች እየሱስን እየሰደቡ እየተፉበት እርሱ ግን በመካከላቸው ምንም ሳይናገር በዝምታ ያልፋል። ታዲያ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ነገሩን ሲከታተሉ ቆይተው ኖሮ ለምን ዝም እንዳለ ጠየቁት። በዚህ ጊዜ እየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው " ሰው ከቅርጫቱ ውስጥ የሚያወጣው ቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ነው። እነዚህም ሰዎች ከስድብና ጥላቻ ውጪ ሌላ ነገር አያውቁም አትፍረዱባቸው" ብሎ ነገራቸው።

አቤት! የዚህ ዘመን ቅርጫት ሲከፈት ውስጡን አሰብኩት። ዘረኝነት፣ እርኩሰት፣ ሴሰኝነት፣ ጥላቻ፣ ተንኮል ወዘተ ተጭቀውበት ታየኝ። ስንት ዘመን ከዚህ ቅርጫት እንደምንኖር እንጃ! ስንት ዘመን አዳኞቻችን ታዳጊዎቻችንን ከዚህ ቅርጫ እንደምንወረውርባቸው እንጃ! ማን ያውቃል!? ብቻ ተስፋ አልቆርጥም።

22/11/2014 ዓ.ም የተከተበ

@ourrthought
🔥51
ማጭድ ይሆን ዘንድ ምንሽር ቀለጠ
ዳሩ ብረት እንጂ ልብ አልተለወጠ
ለሳር ያልነው ስለት እልፍ አንገት ቆረጠ..


በዕውቀቱ ስዩም

@ourrthought
😢13🔥2