ሐሳቦቻችን
981 subscribers
103 photos
4 videos
5 files
2 links
በዚ ቻናል ላይ የተለያዩ ሀሳቦቻችንን ፣ ምልከታዎቻችንን ፣ ትዝብታችንን ፣ ከተለያዩ መልኮች እያነሳን እንወያያለን!

ሀሳብና አስተያየት ካላቹ @haileabb
Download Telegram
ከባርነት በላይ ነፃነት ለሰው ልጅ ትልቅ የሀላፊነት ሸክም አለው።

አንድ ባሪያ በባርነት ዘመኑ ውሎው ምግቡ የሚሰራው የሚለብሰው በሙሉ የተወሰነለት በመሆኑ የተለየ የሚያስጨንቀው ነገር የለበትም። ይሄን ባሪያ ከባርነት አውጥታቹ ነፃ ብታደርጉት ግን ወዴት መሄድ እንዳለበት ፣ ምን መስራት እንዳለበት ፣ በትርፍ ጊዜው ምን እንደሚያደርግ ፣ ስለሚለብሰው ፣ ስለሚጠጣው ስለ እያንዳንዱ ነገሩ የማሰብና የመጨነቅ ሀላፊነትም አብሮ ይመጣበታል።

ከመፅሐፍ ቅዱስ ዘፍጥረትን ብትመለከቱ ስለዚህ ሐሳብ በጥሩ ሁኔታ ዬብራራል። ልክ አዳምን ፈጣሪ እንደፈጠረው ሙሉ ለሙሉ ለነፃነቱ ተላልፎ እንዲሰጥና ዝም ብሎ የ አልባሌ ውሎ እንዲውል አላደረገውም። ይልቅስ አዳምን የ ገነትን ዛፎች እንዲንከባከብና ፣ ለእንስሳቱ ስም እንዲሰጥ በመሳሰሉ ነገሮች እንዲጠመድ ነበር ያደረገው።

ሰው ያለምንም ሀላፊነት ሙሉ ለሙሉ ዝም ብሎ ነፃ ሆኖ ቢኖር ግራ መጋባትና ጭንቀት ውስጥ ይገባል። ሰውን በድብርት ለመግደል psychological killing ከፈለክ ዝም ብለህ እየቀለብከው ያለምንም ሀላፊነት እና ስራ ልቀቀው ያኔ መን እንደሚያደርግና መስራት እነዳለበት ምን ሀላፊነት መውሰድ እንዳለበት ባለማወቁ በራሱ ፍላጎቶች ተጠልፎ ይወድቃል።

"ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል"
"ስራ ከምፈታ ልጄን ላፋታ"

@ourrthought
12👍1
Asa - Jailer
naïve
Im in chain you're in chains too
I wear uniform and you wear uniform too
Im a prisoner,
You're a prisoner too Mr Jailer

I have fears you have fears too
I will die, you sef go die too
Life is beautiful
Don't you think so too Mr Jailer

ሸጋ ሙዚንቃ

@ourrthought
👏21🔥1
³⁴ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።

ማቴ ፦ 6
@ourrthought
11😢4
"
He who has a why to live can bear almost any how."
"Wer ein Warum zu leben hat, erträgt fast jedes Wie."

Friedrich Nietzsche


"Why" is the only real source of power.
without it, you are powerless!

Our only hope, our only peace, is to understand it, to understand the why.

Matrix movie

@ourrthought
18🔥4
Astral Projection ስለሚባለው ነገር እንቸክችክ ይሆን?

ምናልባት ሞክራችሁት ልምዱ ያላቹህ ሰዎች በ comment ላይ አስቀምጡና ምናልባት ሰፋ አድርጌ እፅፍላቹሀለሁ።
ወይ ደሞ ቀን መድበን በ voice discuss ልናደርግበትም እንችላለን።
7
ሐሳቦቻችን
Photo
‎Astral Projection

‎በፊት ላይ ትርጉሙ ሳይገባኝ በፊት አልፎ አልፎ እንግዳ ስሜት ይሰማኝ ነበር። በጣም ለረጅም ጊዜ ቁጭ ብዬ በሆነ ነገር ስብሰለሰል የሆነ ነገሬ ንጥል ብሎ ካላቴን ከላይ እስከታች የሚታዘብ ነገር ያጋጥመኝ ነበር። በዛ ሰዐት ለተወሰኑ ደቂቃዎች አካላቴን እንደ ሌላ ሰው እየደነገጥኩ አየው ነበር። እጄን ሰውነቴን ሁሉ ነገሬን እየዳበስኩ ግራ እጋባ ነበር። ምናልባት ለሰዎች ብናገረው ተቃወሰ እንዳልባል ዝምታን እመርጥ ነበር። የሆነ ጊዜ የተቀራረበ ነገር አየሁ Astral projection የሚል እሳቤ።
‎Astral Projection ማለት የነብስ ከ አካላዊ ሰውነት ተነጥላ ከዚህኛው 3D አለም ወደሌላኛው አለም የምትገባበትና ፡ ሌላ ቦታ ላይ መገኘት ማለት ነው። ነብስህ በህይወት እያለህ ከስጋህ ተነጥላ አንተን የምታይህና ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ ምን እየተሰራ እንዳለ መታዘብ የምትችልበት ጥበብ ነው። ይህ ተግባር ከ ኦርቶዶክስ እምነት ጋር ከ 10ሩ የብቃት ደረጃዎች ውስጥ ሁሰት ከሚለው እሳቤ ጋር ይጣጣማል። ሁሰት ማለት አንድ ቦታ ሆነን አካላችን እዚህ ሁኖ ነብሳችን ወይ ንቃተ ህሊናችን (consciousness) ለብቻው ተነጥሎ ወደ ሌላ ቦታ መሄድና ማየት የሚችልበት ጥበብ ነው። ስሙን የማላስታውሰው መፅሐፍ ቅዱስ ላይ እስራኤል ቁጭ ብሎ በሀሳቡ የ አይሁድን ጠላት የሚሰሩትን የጦርነት ዕቅድ እያየ የሚናገር አንድ ቦታ አለ።

‎ ይህ ነገር ከየት መጣ ያላችሁኝ እንደሆን ከ ጥንት ጀምሮ የሚደረግ ጥንታዊ ሀይማኖቶች ልምምድ ላይ ያለ ድርጊት ነው። ግን ወደፊት ሊወጣ የቻለው በ Theosophy እንቅስቃሴ ነው። በነ Helena በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1875 አከባቢ ነው። 1800 ዎቹ ላይ አብርሀሚክ ሀይማኖት ላይ በተለይም ክርስትናው ላይ በአውሮፓ ከፍተኛ የሆነ ጥያቄ የሚነሳበት ወቅት ነበር። በ አመክንዮ ብቻ የሚለው ነውጥ አውሮፓውያኑ ክርስትና ላይ እንዲያምፁ ያደረገበትና ብዙ ጥያቄዎች የሚነሱበት የነበረበት ወቅት የነበረ ነው። በዚህን ጊዜ ነው የ Theosophical movement የተጀመረው። አብዛኛው የ ቡድሂዝም ፣ ሂንዱዝም ፣ ጥንታዊ እምነቶች ላይ ያሉ መፅሐፍ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉመው የምስራቁ አለም ሀይማኖቶች የተጠኑበት ጊዜ ነበር።

‎የዛኔ ነው Helena Petrovna Blavatsky እና ሁለት ጓዶቿ (በሷ ምክንያት) የዚህን የሀይማኖት ንቅናቄ የጀመሩት። የዚህ ሀይማኖት መሰል እንቅስቃሴ ከ ሂንዱ ፣ ቡድሂዝም ፣ ክርስትና ፣ ጥንቁልና ልምምድ ፣ ምዕራባዊ የሀይማኖት ልምምድ ተውጣቶ የተጀመረ ነው። የሀይማኖታቸው እንቅስቃሴን መንፈሳዊውን ጥበብ መመርመር Devine Wisdom (Theosophy) ብለው የጀመሩት። ሁሉም ጥንታዊ ሀይማኖቶች የሚያመሳስላቸው ነገር አለ መንፈሳዊ ጥበብ ያመሳስላቸዋል ብለው ያምናሉ። "There is no religion higher than truth" ይላሉ እንደ መፈክር። Karma ፣ Reincarnation ፣ Astral plane ፣ Nature of human being ፣ psychic energy የሚተኮርባቸው ናቸው። ሁሉም ሰው መንፈሳዊነት ጥበብ አለው ይሄን መንፈሳዊነቱን ጥበቡን እንዲቀዳጅ ነው የምንሻው ይላሉ።

‎ ታዲያ የ Theosophy ሁለት አይነት የሀይማኖት አምልኮ ስርአት አለ ይላሉ። Exoteric የ አደባባይ እውቀት። ይሄ በ የቸርች መስኪድ የምንሰበከው ግልፅ የሀይማኖት ትምህርት ነው። ሌላው Esoteric ነው። ይሄ ዋናው የ ቴዎሶፊ ትኩረት የሆነው ነው። በሂንዱ Mahayan የሚሉት ድብቁ ለብዙሀኑ የማይነገረውና ጥቂቶች ብቻ የሚያውቁት መንፈሳዊ ጥበብ ነው። እንግዲህ ከነዚህ ጥበቦች ውስጥ Astral Projection አንዱ ነው ማለት ነው።

‎The key to theosophy የሚለው የ Helena በጥያቄና መልስ በተዘጋጀ መፅሐፍ ላይ Astral Projection ሰዎች መንፈሳዊ ልምምድ የሚጀምሩበት ብዙ ጥበብ የሚያገኙበት አንዱ ደረጃ ነው ትላለች። ነብሳችን ከ ማይታየው አለም ጋር ከ ስጋ እስር ወጥታ የምትማርበት ከ መንፈሳዊ አለም ጋር የሚገናኝበት ነው ብላ ነው የምትገልፅው። ግን እነዚህን ልምምዶች ሌሎቹንም እንዲሁ እንዲተገበሩ አትመክርም ከዛ ይልቅ ሌሎች መንፈሳዊ ልምምዶችን እንዲያደርጉ ትመክራለች። ወደ Astral realm ለመግባት ዮጋ ፣ እንቅልፍ ፣ ተመስጦ የሚረዱ መንገዶች ናቸው። አንዳንዴ ሳናስበውም ይከሰታል። ጉዳዩ ልክ ነብሳቹ ከሰውነታቹህ ተነጥላ ወይ ኮንሸስነሳቹህ ለብቻው ወደ ፈለገበት ቦታ የሚሄድበት ጥበብ ነው። ለምሳሌ ቤት ተኝታቹህ ሌላ ሀገር ተንሸራሽራቹህ መምጣት የምታዩት ደሞ እውነተኛ ምስልና ትውስታ የሚኖረው ምስል ነው። ብዙዎቹ ከ አስትራል በፊት ሉሲ ድሪም ቢኖራቹ የተመረጠ ነው ይላሉ። ቀጥታ እዛኛው አለም ከመግባት በፊት ከመተኛታቹ በፊት የምታስቡት የራሳቹህ የሆነ ጥሩ የሆነ ያማረና ወደዛኛው አለም ስትገቡ ልታገኙት የምትሹትን ብታስቡ ወደዛኛው አለም ከገባቹህ በኋላ አላማችሁን አትረሱም ይላሉ።

‎ በ እንቅልፍ ልባችን ወደዚህ አለም የምንገባ ቢሆንም ግን ትውስታችን አይኖርም ትላለች። ጉዳዩን ከተለማመዱት እና መቆጣጠር ከቻሉ ከሌላኛው መንፈሳዊ አለም ጋር የምንገናኝ በመሆኑ ብዙ የመንፈሳዊ ጥበብ እውቀት እናገኛለን። ያለ ጥሩ ልምምድ ከሆነ ግን የ ክፉ መንፈስ መጫወቻ እንሆናለን። ግን ብዙ ግዜ እንዲሁ እንዲደረግ የሚመከር አይደለም። ልምምዱን ከመጀመራቹህ በፊት የሆነ የምትወዱትን ዘፈን ወይም ደሞ የሰአት መቁጠሪያ የሚመስል ነገር ቋ ቋ እያለ የሚቆጥር ድምፅ ያለው ነገር ቢኖር ይመረጣል።

‎እንዲህ አይነት ልምምድ ነገሩን ከማወቅ ጉጉት አንፃር የሚገቡ ሰዎች ብዙ ጊዜ ከዚህኛው አለም ወጥተው በ Astral Projection ሌላኛው አለም (realm) ላይ ሲገቡ ምንም አላማ ስለሌላቸው በ ነብስ ነጣቂዎች (parasite) ወጥመድ ይገባሉ። አስፈሪ ምስሎችን ከሌላኛው አለም ማየት ይጀምራሉ። ከባባድ የሆኑ እኛ የማናያቸውን ብዙ ነገር የሚያዩ በመሆናቸው መቋቋም ይከብዳቸዋል። አንዴ እዚህ ልምምድ ከገቡ በኋላ ጉዳዩን ባይፈልጉትም በተኙ ቁጥር ህልም እየመሰላቸው ወደዛኛው አለም እየገቡ መተኛት ይቸገራሉ።
‎ አንዳንዶቹ ገና ወደ መኝታ ሲሄዱ መተኛት ሁሉ በጣም አስፈሪ ምስልና ድምፅ ያስጨንቃቸዋል። ገና ሸለብ እንዳደረጋቸው ብዙ አስፈሪ ነገሮችን ማየት ይጀምራሉ። ሰውነታቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ (sleep paralyzed) ይሆናሉ። አንዳንዶቹ አስፈሪ ድምፆችን በከባድ ሁኔታ ይሰማሉ። መደበኛ ሁኔታቸው ላይ እስኪመጣ ድረስ ይረበሻሉ። ብዙዎቹ መተኛት ይፈራሉ። ቅዠትና እውነታው ይደበላለቅባቸዋል።

‎ዩኒቨርሰቲ እያለን counseling አስተማሪያችን counseling ስንማር የነገረችንን እስካሁንም ቃል በቃል የማስታውሰው ነው።
‎አንድ የሷ ደንበኛ (client) እራሷን ለማረጋጋት ዮጋ ልምምድ ትጀምራለች። ከተወሰኑ ጊዜያቶች በኋላ ሴትየዋ በ ዮጋ ምክንያት ወደ ሌላኛው አለም አሁን ላይ ጉዳዩን ሳጤነው Astral projection ትገባና አዕምሮዋ ቀውስ ውስጥ ይገባል። እኔ ሴትየዋ ማታ በተኛች ቁጥር መንፈሶች ሴጣን ልጆቿንና ባለቤቷን ወደ ሲኦል እያንደፋደፈ ሲመ።ሳቸውና ሊገላቸው እየመጣ ታያለች። ስትነቃ እውነታውና ሌላኛው አለም (ቅዠቱ) ተደባልቆባት ነው ለ counseling የመጣችው።


@ourrthought
3
‎ ሴትየዋ ልጆቿን ከነዚህ ክፉ መናፍስት ለማዳን ታዲያ ልጆቿንና ባሏን እሷንም ክፉ መንፈስ ሳይቀድማት ለመቅደም ገላቸው ቀድማ ገነት ለመግባት ነው የምታስበው።

‎ ሳይኮሎጂው እንዲህ አይነት ነገሮች ሳይንሳዊ ባለመሆናቸው ለመቀበል ይቸገራል። ይንን ነገርም ሳይኮቲክ እያለ ሰዎቹን ከ እውነታው አለም የተለያዩ (Delusional) የቀን ቅዥት ያሌለን ነገር ማየት (Hallucination) እያለ የዳቦ ስም ይሰጣቸዋል። በርግጥ አሁን አሁን ይህን መንፈሳዊ አለም ማግለሉ እንደማያዋጣው ስላወቀው ሳይኮሎጂው መንፈሳዊነት (spirituality) እያለ ማካተት እየጀመረ ነው።ግን ገና ብዙ ይቀረዋል።

‎አጠቃላይ ልምምዱ ጥንት የነበረ ልምምድ ሲሆን ማንኛውም ሰው እንዲያደርገው የማይመከር ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊ ጥንካሬ ካዳበርን በኋላ መደረግ የሚገባው ነው። በዚህ ዙሪያ የተሰሩ Behind her eys እና Insidious የሚሉትን ፊልም review እሰራላቹህና የተሻለ ለመረዳት ይረዳናል።


@ourrthought
👏6🙏2
ሐሳቦቻችን
Photo
Astral Projection በ Insidious እና Behind her eys በሚሉት ፊልሞች ውስጥ እንዴት ተገለፀ የሚለውን እንመልከት።

Behind Her Eyes 6 ክፍሎች ያሉት ሲሆን Astral Projection የተገለፀበት መንገድ ትንሽ የሳሳና ብዙውን እውነት የማያሳይ ነው። በፊልሙ ውስጥ Astral Projection ነብስ ከ አካል ውስጥ በመውጣት ከዚህ በፊት በምታውቃቸው ቦታ ብቻ እየተዘዋወረች የሚከናወነውን የምትታዘብበትን የሚተርክ ነው።

ፊልሙ ላይ በህልማቸው በ ቅዥት አለም የሚቸገሩና በእንቅልፍ ልባቸው ስለሚነሱ ሰዎች (sleep walker) ያትታል። እና የ አዕምሮ ህክምና ማገገሚያ የገቡ ሁለት ካራክተሮች እናያለን። እንቅልፍ መተኛት የሚቸገሩና በህልማቸው ሁል አስፈሪ ተመሳሳይ ህልሞችን የሚያዩ ናቸው። በሂደት አንዷ ካራክተር በ Astral projection በልምምድ ህልሟን መቆጣጠርና ማዘዝ ስትችል ያሳያል። ቤቷ ተኝታ ነብሷ (ንቃተ ህሊናዋ) ከዚህ በፊት የምታውቃቸው ቦታዎች እየተዟዟረች ባሏ ቢሮ ምን እንደሚሰራ ትከታተለዋለች። አብራው ያለውን በቅዥት የሚቸገር ጓደኛዋን ስለ Astral projection ታሳየውና አብረው ልምምዱን ማድረግ ይጀምራሉ።

በፊልሙ ላይ ከ አስትራል በፊት መደረግ ስለሚገባቸው ዝግጅቶች ያሳያል። ጣትን መቁጠር ተመስጦ ማድረግና ከመተኛታችን በፊት ያለች በሰመመን የምናያት የራሳችን የህልም አለም (Lucy dreaming) አስፈላጊ መሆናቸውን ያትታል። ሌላው ስለ አስትራል የተነሳው ጉዳይ በ Astral projection ነብሳችን መሄድ የምትችለው ከዚህ በፊት በምናውቀው ቦታ ብቼ መሆኑን ያትታል። ከዚህ በፊት ያልሄድንበት ቦታ ላይ መሄድ እንደማንችል አፅንዖት ይሰጣል። በተወሰነ መልኩ የነብስ ነጠቃም እንዳለ ያትታል። ሁለት የ አዕምሮ ማገገሚያ ማዕከል ያሉ ጓደኛሞች Astral projection ካሳየችው በኋላ እየተገበሩት ነብሳቸው ከሰውነታቸው ተነጥሎ በሚገዟዟሩበት ጊዜ አካል ተቀያይረው ለመሞከር ይፈልጋሉ። በመሀል የሷ ነብስ የሱ ውስጥ የሱ ነብስ የሷ ውስጥ እንዳሉ ጓደኛዋ የሷን አካል ሲነጥቃትና እሷ የሱ አካል ውስጥ እንዳለች ሲገላት ያሳየናል። ከዛም የሱ ነብስ በሷ ነብስ ውስጥ ገብቶ ሲንቀሳቀስ ያሳያል። ፊልሙ በተወሰነ መልኩ ስለ Astral projection የሚያሳይ ሲሆን የተሳሳቱ ነገሮችንም ይናገራል። ለምሳሌ በ Astral real መጓዝ የምንችለው የምናውቀው ቦታ ብቻ ነው የሚለው ድምዳሜ ከእውነታው የራቀ ነው። አንዳንድ ቦታዎች ለማየት እንደሞከርኩት ነብስ አይታ የማታውቀው ቦታ እንደምትጓዝ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ።

Insidious በሚለው ፊልም ውስጥ

ይሄ ፊልም ስለጉዳዩ የተሻለ የሚገልፅ ሆኖ አጊኝቼዋለሁ

ፊልሙ chapter 2 chapter 3 እያለ 4 ክፍሎች ያሉት ነው።
የመጀመሪያው ክፍል ላይ ፊልሙ ሲጀምር በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አንድ ህፃን ልጃቸው ኮማ ውስጥ ሳይሆንም ሳይነቃ በእንቅልፍ አለም ውስጥ በኦክስጅን ብቻ የሚቆይበትን ሂደት ያስቃኛል። በዚህ ግራ መጋባት ወስጥ እንዳሉ ሀኪሞችም ሳይኮሎጂስቶችም መላ ሊሰጧቸው አልቻሉም።

በዚህን ጊዜ አያቱ አንድ ሴት ታናግራለች። ሴትየዋ ለሰው የማይታይ የምታይ መንፈሳዊ ጥበብ ያላት ናት። ልጁንም ካየችው በኋላ ለቤተሰቡ አንድ ነገር ነገረቻቸው ህፃኑ Astral projection መሆኑን ሳይረዳ በህልም አለም ያለ መስሎት ሳያስበው ሌላቸፈኛው አለም ውስጥ Astral plane ሄዷል። እናም ሳያውቀው ነብሱ ከሰውነቱ በጣም እየራቀ በመሄዱ ለመመለስ እንዳይችል ሆኗል። ነብስ ነጣቂ የሚባሉ (parasite) ዴሞን ክፉ ለሰው የማይታዩ መናፍስት ከዚህ በፊት ኖረው የሞቱ ሰዎች ነብሱን ከአካሉ አርቀዋት በህፃኑ ሰውነት የነሱን ነብስ ለመክተት የሚያደርጉትን ትግል ያሳያል። ህፃኑንም ለመመለስ አባቱ በ Astral ሄዶ ሲመልሰው ያትታል።

ይህች መንፈስ የምታየው የ psychic power ያላት ስለ ጉዳዩ chapter 3 በሚለው ክፍል ላይ አንድ ነገር ትናገራለች። Astral projection ሁለት አለም አለው ትላለች። አንደኛው white ጥሩ ቦታ የምንሄድበትና መንፈሳዊ ጥቅምና እውቀት የምናገኝበት መልካሙ አለም እና መልካም መናፍስት ያሉበት ሲሆን የ Black የሚባለው ክፍል ግን ነብሳችንን ከአካላችን አርቀዋት የነሱን ነብስ በሰውነታችን ለማስገባት የሚጥሩበት ሰዎችን ለማሰቃየት የሚፈልጉ ክፉ መናፍስት ያሉበት ነው።

ፊልሙ አንድ ሰው አስትራል ከማድረጉ በፊት አንድ ትልቅ አላማ ሊኖረው ይገባል የሚል መልእክት ይናገራል። አላማ ካለን ነብስ ነጣቂዎቹ የሙት መንፈሶቹን የመታገል አቅም ይኖረናል የሚል ይናገራል። እነዛን ነብስ ነጣቂዎች አለመፍራትም ዋነኛው ነገር ነው። እነሱ የሞቱ በመሆናቸው ከኛ ጋር በሀይል አይጣጣሙምና። በጥቅሉ የ አስትራልን ትክክለኛ መልክ የሚያሳይ ነው።

ሳጠቃልለው ያለምንም መንፈሳዊ ልምምድ እና ሙከራዎች እንዲህ አይነት ልምምድ የሚሞክር ሰው ትልቅ ቀውስ ውስጥ እንደሚገባ ነው። ከ YouTube ብዙ ቪዲዮ ማግኘት ትችላላቹህ በዚህ ልምምድ ውስጥ ያለፉ ሰዎች የሚያደርጉትን ትግልና ስቃይ።

አንድ ጊዜ Astral projection የሞከረ ሰው ሰውነቱ የመንፈሳዊውን አለም የሚከፍት በመሆኑ የጭለማው አለም ነብስ ነጣቂዎች እስከለተ ሞታችን ድረስ ያሳድዱናል። ብዙ ያየኋቸው ይሄን ልምምድ ያደረጉ ሰዎች ወደ ጭለማው አለም ነው የሚገቡት። ከዛም እንቅልፍ መተኛት እስካይችሉ ድረስ መንፈሳዊው አለም ከ እውነተኛው አለም ጋር ይቀላቀልባቸዋል። ለኛ ባይን የማናያቸው መናፍስት ሙታኖች ለነሱ ይታያቸዋል። የብሳችን ያኛውን አለም ከገባችበት መውጫዋ ሀይማኖታዊ መንገድ ያልታገዘ ከሆነ ውጤታማ የመሆን እድሉ ዝቅ ያለ ነው።

ፊልሙን እንድታዩት እጋብዛለሁ።

@ourrthought
🔥5👍3
የAustriaው psychologist Alfred Adler የምትጣፍጥ "Social Interest" የምትል ሃሳብ አለችው። እሱም እንዲህ ሲል ያብራራታል Social Interest(social feeling) is our attitude of relatedness or oneness to social community of all people። ቀጥሎም social community of all people ሲል literally "Humanity" ማለቱ እንደሆነ ይነግረናል።
እኔም ማውራት የፈለኩት ስለዚህች humanity ወይንም ደግሞ ሰዋዊነት ስለምትለዋ ሃሳብ ነው። ታዲያ ይህ የሰዋዊነት ሃሳብ በጣም ብዙ በሆኑ ሃሳቦች እና ድርጊቶች ምክንያት ከሞላ ጎደል እንደ ዓለም እየጠፋ ያለ ነገር ነው። የሰው ልጅ እራሱን የሰዋዊነት(ሰብዓዊነት) አንድ ክፍል አድርጎ ማየት ካቆመ ትንሽ ሰንበትበት ብሏል። ለዚህም የፈጠርናቸው ideologyዎች፣ ስርዓቶች፣ ተጠያቂዎች ናቸው። እስቲ በትንሹ እንያቸው።...

1. በመጀምሪያ በተለያዩ ጊዜያት መልኳን እየቀየረች የተከሰተችው የ"CLASS" ሃሳብ የሰውን ልጅ ሰዋዊነቱን ትቶ፣ ከሰዋዊነቱ ውጪ ራሱን የሚያይበት መከፋፈልን ሰጥታለች፣ እንደ ምሳሌ ያህል የBourgeoisie class (የባላባት መደብ) እና የProletariat class (የሰራተኛ መደብ) ብለን እራሳችንን ከፍለን በሰውነት ከመታወስ በሆነ መደብ ስር ራሳችንን ከትተን በዚያ መታወስን መርጠናል።
 
2.ከዚያ አለፍ ሲልም "MATTER OF COLOR" ወይን ደግሞ ራስን በቆዳ ቀለም ለይቶ የአንዱ ጎራ ሆኖ መመደብ እንዲሁ ከሰዋዊነት ያወጣን ሃሳብ ነው። ጥቁር መሆን የምድር እርግማን መሆን እስኪመስል ድረስ ጥቁር መሆን ባሪያ(slave)፣ ጥቁር መሆን ገረድ፣ ጥቁር መሆን አመፀኛ፣ ጥቁር መሆን ሌባ መሆን እንደሆነ ተደርጎ ተወስዶ ጥቁሮች ላይ በታሪክ ስንዳስሰው የማይረሳ ጠባሳ ጥሎ አልፏል። በሌላ ጎኑ ደግሞ ነጭ ማለት ጥበበኛ፣ ሁሉን አዋቂ፣ የፈጣሪ የብቻ የእጁ ስራ ምናምን ተደርጎ ሲወሰድ ሰንብቷል ለብዙህ ጊዜ። የቀለም ልዩነቱን ገፋ አድርገን አለፍ ብለን ስናየው፣ በውስጡ ጥቁር ለጥቁር ይደግፍ፣ ነጭ ለነጭ ይደግፍ የሚል ሰውን በቀለም የመለየት ሃሳብን በውስጡ ይይዛል።
 
3. አለፍ ስንል ሰዋዊነታችንን ትተን በ አህጉር መከፋፈልም አለ። ማለትም አፍሪካዊ፣ አውሮፓዊ፣ ኤዢያዊ ምናምን እያልን ወደመከፋፈልም አልፈናል ማለት ነው። ስፋቱ ጠቦ መከፋፈሉ የሚሰፋው ደግሞ አለፍ ብለን በሃገር ደረጃ ወደመከፋፈላችን ስንሄድ ይሆናል። ከዚህም ደግሞ ሲለጥቅ እንደኛ እንደ እማማ ኢትዮጲያ ባሉ ሃገራቶች ውስጥ ደግሞ በዘር መከፋፈል፣ በሃይማኖት መከፋፈል፣ ይቀጥል ይቀጥል እና ደግሞ በሰፈር ወደመከፋፈል ድረስ ይደርሳል።

ሃሳቡ እንዴት መሰላቹ፣ ፈጣሪ ሲፈጥረን የፈጠረው፣ ተዋደዱ ሲል ተዋደዱ ያለው ሙስሊሙን ከሙስሊሙ፣ ጉራጌውን ከጉራጌው፣ እትዮጲያውን ከኢትዮጲያዊ፣ አፍሪካውን ከአፍሪካዊ፣ ነጩን ከነጩ አይደለም። ከዚያ ይልቅ ሰውን ከሰው ነው፣ ይህንን ነው Adler oneness to the social community of all people የሚለው። humanity ማለትም ይሄ ነው። ጓደኛዬ ብለህ የጠራኸውን ሰው ጉዳዩ የሃይማኖት ወይንም ደግሞ የዘር ሲሆን ጀርባህን ከሰጠኸው ከዚህ social community of all people (humanity) ጋር የ oneness ስሜት የለህም ማለት ነው።ይሄም ይመስለኛል ትልቁ ችግር በሁሉም ግንኙነታችን ውስጥ የhumanity sense ከሌለ ግንኙነታችን ለመፍረስ ጊዜ ተጠባባቂ ነው ማለት ነው፣ ማለትም የሚዘልቅ አይሆንም ምክንያቱም ግኑኝነታችን የተመሰረተው ሰውነታችን ላይ ሳይሆን ቡድናዊነታችን ላይ ነዋ፣ ቡድናዊነት ደግሞ የሚዘልቅ አይደለም መቼም ቢሆን የሆነ ሰዓት ላይ ሊቀየር ይችላል።  እንደውም ለዚህ የሚሆን አሪፍ ማሳያ የሚሆነው በዕድሜያችን ያን ያህል ባልራቀው የኢትዮጲያ እና የኤርትራ ግንኙት ነው፣ አንድ ነበርን ፣ ተቀላቅለን፣ ተቀላልደን፣ ተፈቃቅደን ኖረናል፣ ተዋልደናል፣ አልፈናል። ከዚያ ግን ምንድነው የሆነው በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት? ባል ከሚስቱ በሚስቱ ትውልደ ኤርትራዊ በመሆን ብቻ ላይገናኙ ተለያይተዋል፣ ከዚህም ባለፈ ሌላም አይነት የተለያዩ ላይገናኙ የመለያየት ታሪኮችን ሰምተናል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ  አንድነታችን የተገነባው መለያየታችን ላይ ስለሆነ ነው። ባልና ሚስቱን ያለያያቸው የትውልድ ቦታ ልዩነታቸው ነው እንጂ የፍቅር ጉድለት ምናምን አልነበረም የሌላውን እንደዛው።

ይሄ ሃሳብ ከምንም በላይ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጲያ ላይ ይንፀባረቃል።ሁሉም ሰው ከጎረቤቱ ጋር እንደ ድሮው በፍቅር ሳይሆን በአይነ ቁራኛ መተያየት ጀምሯል። መዋደድ፣ መከባበር፣ መቻቻል ምናምን የሚሉ ሃሳቦች በሃገራችን ውስጥ ተዘቅዝቀው ከተሰቀሉ ሰንብተዋል። ማንም ሰው አጠገቡ ያለውን ሰው የሚለካው ባለበት የሃይማኖት ቡድን ወይንም ደግሞ የዘር ጎሳ ምናምን እንጂ  በሰውነቱ አይደለም። even እንደውም ይለይላቹ ሲለን ኢትዮጲያ ውስጥ አይደለም በሰውነት መለካት ይቅርና የኢትዮጲያዊነት ስሜቱ ራሱ እየጠፋ ሁላችንም የሆነ ቡድን አካል ተደርገን ተወስደን ነው ልኬት የሚሰጠን። ከምንም በላይ ግን  idea of humanity መቅደም ነበረበት። ማንም ሰው መዳኘት ያለበት በቆዳ ቀለሙ መሆን የለበትም፣ በሚኖርበት ሃገር ወይንም አህጉር መሆን የለበትም፣ በሚከተለው ሃይማኖት ወይንም ደግሞ በተወለደበት ጎሳ አይደለም መዳኘትም፣ መወደድም፣ መነቀፍም ያለበት ከዚያ ይልቅ በሰውነቱ እንጂ። የሃገሬ ሰው ከማለታችን በፊት ሰውነቱ መቅደም ነው ያለበት፣ ካልሆነማ የሃገር ልጅነትም በፖለቲካ ይነጠቅና ወደ ጠላትነት ይቀየራል። እና ሃሳቤን ሳሳጥረው...
                    
ከጥቁርነት፣ ከአፍሪካዊነት፣ከኢትዮጲያዊነት፣ከጌዴዮንነት፣ከክርስቲያንነት፣ ሰዋዊነት (humanity) ይቀድማልና ትስስራችን ከቡድናዊነት ጋር ሳይሆን ከሰዋዊነት ጋር ይሁን።!



@ourrthought
🔥42👍1
“As soon as man comes to life, he is at once old enough to die.”

"የሠው ልጅ ወደ ህይወት በመጣበት ቅፅበት ለሞት የተዘጋጀ ይሆናል"

Martin Heidegger

@ourrthought
🔥91
የትምህርት ቤት ምገባ (School feeding program)

እንደ ሀገር ትኩረቶቻችን ምን ላይ የተኮረ ነው? ብባል በድፍረት መናገር የምችለው ነገር ቢኖር ለችግር ምላሽ በመስጠት ላይ እላለሁ። ብዙ ጊዜ ችግር ሳይከሰት (prevention) ከመከላከል ይልቅ ችግሩ ከተከሰተ በኋላ (response) መፍትሄ መስጠት ይቀለናል። ለምሳሌ አንድ የመብራት ገመድ ለመውደቅ እየተንጋደደ 2 አመት ቢቆይ ዘወር ብሎ የሚመለከት አይኖርም። ይልቅ ፖሉ ወድቆ ሰው ከጎዳ ወይ ኤሌክትሪክ ተበጥሶ ጉዳቱን ለመከላከል እንፋጠናለን። ለምን? የሚለውን ዋቃ ነው የሚያውቀው።

ልክ እንደዛ ሁሉ የትምህርት ቤት ምገባ ከዛ የተለየ አላየውም። በ 2011 ዓ.ም በ ታከለ ኡማ ከንቲባነት ጊዜ በይፋ የተጀመረ በ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረ ፕሮግራም ነው። አሁን ላይ በ አዲስ አበባ ብቻ በቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች ላይ 779 ሺ ህፃናት በትምህርት ቤቶች ላይ ቁርስና ምሳ ይመገባሉ። ቢያንስ ለ አንዱ ህፃን 54 ብር ይወጣል ብለን ብናስብ በቀን ብቻ 42 ሚሊዮን ብር ለህፃናቱ ምገባ ይወጣል። ይሄ እንግዲህ የሰራተኞችን ወጪ አይጨምርም።

ይሄን ነገር በብዙ መልኩ ጠቃሚ ቢሆንም ግን ለኔ ጉዳቱ ያመዝናል። አላማው የተማሪዎችን የትምህርት መገኘት (attendance) ፣ ማቋረጥ ፣ በክፍል ውስጥ ርሀብ ለመቀነስና ከወላጆች ጫንቃ ለማላቀቅ የታሰበ ነው። ከላይ ከላዩ ጥሩ ጎኖች ያሉት ይመስላል። ግን አሁን ላይ የመንግስት ት/ቤት ምገባ በመኖሩ ብቻ ልጆችን በድፍረት ይወልዳሉ (ጥናት ቢሻም) ከብዙ ቦታ ተሰደው ወደ ምገባ ወዳለበት ቦታ ይጣሉ ፣ የተፈጠረውን ዕድል ተጠቅመው ህይወታቸውን ከመቀየር ይልቅ ሌላ ለመውለድ ይነሳሳሉ። አሁን ላይ ትምህርት ቤቶች ከትምህርት ቤትነት ይልቅ የሆድ መሙያ ገበታነታቸው በዝቷል። ልጆች ከትምህርቱ ይልቅ ስለ ምግቡ ነው የሚሄዱት ቤተሰቦቻቸውም (ሁሉንም አይወክልም) ከትምህርት ይልቅ እንዲመገቡ ብቻ የሚልኩ ናቸው። ትምህርት ቤቶች በግዴለሽ ለሚወለዱ ልጆች የሆድ መሙያነት ብቻ የተቀየረ ይመስላል። የመማር ማስተማር ስራው ሁለተኛ የሆነ ይመስላል።

አሁን ላይ ትምህርት ቤቶች ለ 2 ወር በመዘጋታቸው ልጆችን የሚመግባቸውና የሚውሉበት የጠፋ ይመስላል። ብዙዎቹ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ማብላት አቅቷቸው ለልመና እጃቸውን የሚዘረጉበት የ ጭንቅ 2 ወራቶች ናቸው። ልጅ እንደ ልጅ ሳይሆን ምግብ የሚበላና ቤት ውስጥ የሚውል መሆኑ ትዝ የሚላቸው አሁን ነው። በርግጥ ጉዳዩ ጥናት የሚፈልግ ቢሆንም ግን ለምን ሆነ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ቀላል ነው። ለችግሩ ጊዜያዊ መፍትሄ መስጠት እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ላይ አናተኩርም።

በወር ብቻ እስከ 935 ሚሊዮን ብር በጀት የሚወጣበት ማዕከል ልጆቹን አብልቶ ከመላክ እናቶቹን የስራ ዕድል መፍጠር ላይ አያተኩርም። ምናልባት ይሄ ገንዘብ ብቻ በየወሩ ለምገባ የሚወጣው ገንዘብ በየወሩ አነስተኛ ፋብሪካ እየተከፈተ እንደየ ችሎታቸው እናቶቻቸውን የስራ እድል ቢፈጠር የተሻለ የጥገኝነት እና የድህነት መጠኑን መቀነስ የሚቻልበት መንገድ ጥሩ ነው ባይ ነኝ። በዚህ መንገድ ከቀጠልን ቤተሰብ መሸከም የሚገባውን ሀላፊነት ወደሌሎች ተቋሞች ባዞርነው ቁጥር የ ተረጂነት ሱስና ልጆቻቸውን የበለጠ ከመዘንጋት ያለፈ ጥቅም አይኖረውም። ብዙዎቹ በግዴለሽነት የሚወልዱ አሉ። መንግስት ለሚያበላቸው ለምን እጨነቃለሁ? የሚሉ ገጥመውኛል።

ችግሩ እንዳይፈጠር መፍትሄ ማበጀት እንጂ ለችግሩ መፍትሄ መመለስ አስተማማኝ አይደለም። ብዙ የመንግስት ትምርህት ቤቶች ባለ 3 ፎቅ ሆነው ምንም የሚከላከል ብረት ሳይኖረው ልቅ ናቸው። ልጆች ከወደቁ በኋላ ለህክምና እና ለሌላ ወጪ የሚወጣው ብዙ ነው ግን ማንም ያንን ፎቆች በብረት ወይ በ ሽቦ ፍርግርግ ለማጠር የሚሞክር የለም። ልጆች ሲወድቁ ግን ልጆች ማሳከሚያ መለመን ይቀለናል።

ከመጎዳታችን በፊት መፍትሄ ሰጪ ያድርገን።

@ourrthought
👍95👏2
ሐሳቦቻችን
Photo
ማንነትን መቀበል

ማንነትህን ትቀበለዋለህ? ወይስ ዘወትር ትሸማቀቅበታለህ? የምታፍርበትስ ነገሮች አሉህ? ካሁን ካሁን ሰዎች ስለዛ ነገር አንስተው ተረቡኝ አበሸቁኝ የምትልበት ስስ ጎንህ? የምትሸሸው ርዕሰ ጉዳይ አለህ? የሚያባትትህ? ላብ የሚያጠምቅህ?

“Never forget what you are. The rest of the world will not. Wear it like armor, and it can never be used to hurt you.”

"ማንነትህን በፍፁም አትርሳው። የተቀረው አለም አይረሳውምና። እንደ ጦር ልብስ ታጠቀው። ማንም በዛ በኩል ሊጎዳህ አይቻለውም።"
ይህች ከላይ ያለችው ንግግር Game of thrones ላይ ከማደንቃት የ Tyrion Lannister ለ Jon snow ከነገረው ንግግር ውስጥ ቅመም ናት።

Jon snow ቤት ውስጥ የ አባት ልጅ ብቻ በመሆኑ ዲቃላ እየተባለ የሚጠራ ሙሉ ክብር ያላገኘ በዛ የሚበሳጭ ልጅ ነው። እድሉን የሚያማርርና መቀበል ያቃተው በመሆኑ ሰዎች በዛ ክፍተቱ እሱን ለማጥቃት ይቀላቸዋል። እና Tyrion ይሄን ነገር አስተውሎ Jon ብቻውን አዝኖ ይህችን ከላይ ያለችውን ንግግር ለ Jon snow ሲናገረው እናያለን።

በ psychology ውስጥ አንድ ሰው ጤናማ መሆኑ ከሚታይባቸው  መንገዶች አንዱ የሚመጣበትን የህይወት ፈተና ወይ ችግር  የሚቋቋምበት መንገድ ነው። በ psychology አንድ ሰው ለችግሩ የሚሰጠው ምላሽ ሁለት አይነት መንገድ አለ። የመጣብህን የህይወት ፈተና መቀየር ከቻልክ ትቀይረዋለህ። ከ አቅምህ በላይ ከሆነ ግን ትቀበለዋለህ። መቀየር የማትችለውን ነገር መቀበል ካልቻልክ ግን አዕምሮህን እየመረዘው የ አዕምሮህን ጤና ያዛባዋል። ይህ ችግርን ለመቆጣጠርና በችግርህ ላለመውደቅ ይረዳሀል።

Tyrion Lannister ድንክ (Dwarf) በመሆኑ በቤት ውስጥ ሲንቁትና እንደ አውሬ ሲያዩት ያደገ ሰው ነው። እንደ ታላቅ ወንድሙ የጦርነት ጀብድ የሌለው የሻሞላ ችሎታ የሌለው ነው። ድክመቱን በማመኑና በመቀበሉ የማይችለውን ሻሞላ አንስቶ አያቅተኝም የሚል ባለመሆኑ ትኩረቱን ወደ ንባብ በማዞር ወንድሙ በጦርነት ያገኘውን ጀብድ እሱ በንባብ አዕምሮውን በመጠቀም ብኩርናውን ለማግኘትና ከሰዎች ያጣውን ክብር ሲያገኝ እናያለን።

Jon snow አንድ ቀን Tyrion lannisrter ሲያነብ ለምን አብዝቶ እንደሚያነብ ይጠይቀዋል። የ Tyrion መልስ ድንቅ ነው።

"My brother has a sword and I have my mind. The sword needs a whetstone, and the mind needs to read.


"ወንድሜ ጎራዴ አለው እኔ ደሞ አዕምሮ አለኝ። ጎራዴ እንዲሳል ሞረድ እንደሚሻው ሁሉ አዕምሮም የሰላ እንዲሆን ንባብ ይፈልጋል።"

የ Tyrion ትልቁ ጥንካሬው ማንነቱን በመቀበሉ ውስጥ ያለ ከራስ ጋር የመስማማት ሂደት ነው። ከማንም በፊት አንተ ለራስህ ቦታ ሊኖርህና ሁሉን ነገርህን የመቀበል አቅም ሊኖርህ ይገባል።

ችግርህን ለማለፍና ጥንካሬ እንዲኖርህ ያለብህን ጉድለት ተቀብለህ መቀየር የምትችለውን እየቀየርክ የማትችለውን በመቀበል ነው። ከ ስብሀት ይሄን የሚገልፅ ጥሩ አባባል አለው። ቃል በቃል ባላስታውሰውም

"አምፖል ተቃጠለ ተብሎ ቤት አይቀየርም አምፖል ይቀየራል እንጂ። የማትችለውን ነገር መታገል መሸነፍ ሳይሆን አቅምን ለማይጠቅም ነገር ማባከን ነው።" የሚል።

አብዝተህ የምትሸሸው ነገር ያልተቀበልከው ማንነትህ የድክመትህ ምንጭ በመሆኑ አንተን በዛ በኩል ለመጣል መታገልም አይጠበቅባቸውም። ማንነትህን መቀበል የጥንካሬህ ምንጭ ነው። በጣም የምታፍርበትን ነገርህን የተቀበልከው ቀን ሰዎች እና እራስህ በዛ ነገር አንተን ማጥቃት ያቆማሉ። ወይ ትቀበለዋለህ አልያ በዛ ነገር እያሳደዱ ይወግሩሀል።

@ourrthought
11🔥2
Narcissistic Personality Disorder NPD

‎ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሙ እንደ ዳዊት ከሚደጋገሙ የ አዕምሮ ችግሮች ውስጥ Narcissistic Personality Disorder ዋነኛው ነው። ይህ ስም ከየት ነው የመጣው? ከሚለው ጀምሮ እንመልከት።

‎Narcissistic የሚለው ቃል የመጣው ከ ግሪክ አፈታሪክ (Greek myth) ነው። Narcissus የተባለ አንድ መልከመልካም ቆንጆ ወጣት የሆነ ያዩት ሴቶች በፍቅሩ የሚከንፉ እሱ ግን ለነሱ ፍቅር ቁብ የማይሰጠው ነበር። ከብዙ በፍቅር ከወደቁለት ሴቶች መሀል የገደል ማሚቶ (Echo) አንዷ ነበረች። ልቧ በፍቅር ተጎድቶ በሱ ፍቅር  ስሙን እየደጋገመች ድምጿ ብቻ እኪቀር በና ትጠፋለች።
‎ይሄን ያዩ የግሪክ አማልክት Narcissus ለ Echo ያሳየውን ሀዘኔታ የማጣትና ርህራሄ ቢስነት ለመቀጣጫ እንዲሆነው ዘንድ ዉሀ ሊጠጣ ሲሄድ የራሱን ፊት በውሀ ነፀብራቅ አይቶ በፍቅር እንዲወድቅና ፊቱን ብቻ እያየ ከራሱ ፍቅር ወድቆ ምግብና ውሀ ተጠምቶ ይሞታል። በሞተበት ቦታ Narcissus የተባለ አበባ በቀለበት።

‎ይህችን አፈ ታሪክ በመውሰድ Paul Nacke 1889 G.C Narcissism ለማብራራት የተጠቀመው። Narcissus የራሱን ምስል ውሀው ውስጥ አይቶ የራሱ ፊት መሆኑን ሳያውቅ ሌላ ሰው መስሎት በፍቅር የወደቀ መሆኑ ታሪኩ የሚያስረዳን ከራሱ ትክክለኛ ማንነት ጋር ሳይሆን በፍቅር የወደቀው በውጪ ከሚታየው ምስሉ ጋር በመሆኑ Narcissistic Personality Disorder ያለባቸውም ሰዎች ከሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት በሰዎች ውስጥ የራሳቸውን ስሜትና ፍላጎት ብቻ የሚመለከቱ መሆኑንና ከሰዎች ጋር ባላቸው በግንኙነት ውስጥ የራሳቸውን ነገር ብቻ ማዕከል ያደረጉ መሆኑን ለመግለፅ ነው።

‎Narcissistic Personality Disorder (NPD) ከ Personality Disorder ውስጥ የሚመደብ ዲስኦርደር ነው። NPD ማለት ከእውነታው የማይገናኝ ከፍተኛ ግምት ለራስ መስጠት የማይቋረጥ ከመጠን ያለፈ ትኩረትና እንክብካቤና አድናቆት ከሌላ የሚሹ ለሰዎች ስሜትና ጉዳት ግድ የማይላቸው ነገሮችን ከራሳቸው አንፃር የሚመለከቱ ከማንም በላይ እንደሆኑ የሚሰማቸው ርህራሄ የሌላቸው ናቸው። Narcissistic የሆኑ ሰዎች አለማቸውን የሚገነቡት ከውጪ ባለው አስተያየት ሙገሳ እንክብካቤ እንጂ ከራሳቸው ጋር ባላቸው እውነተኛ ማንነት አይደለም። የፍቅርና የጓደኝነት ግንኙነት መመስረት የሚቸገሩ ናቸው። cold lover ይባላሉ። ሰጥቶ ከመቀበል ይልቅ በመቀበል የሚኖሩ ናቸው። የትኛውም ግንኙነት ሲመሰርቱ ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ ናቸው።

‎በዚህ ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች እራሳቸውን የሚያዩት ለ አለም በጣም አስፈላጊ እንደሆኑ ከሁሉ በላይ ያልተገደበ ችሎታ ፣ጂኒየስ ፣ ቆንጆ ፣ አስተዋይ እና ፍቅር ያላቸው እንደሆኑ አድርገው ነው። ለሚያደርጉት ድርጊት ሙገሳን የሚሹ ካልተሞገሱ ግራ የሚገባቸው እነሱ መደነቅ የሚፈልጉበትን ድርጊት ሌላ ሰው ሲያደርገው የሚያጣጥሉ የሌሎችን ስኬት የሚያፌዙ እና የሚንቁ ናቸው። እራሳቸውን አያይዘው ማንሳትና ማወዳደር የሚፈልጉት ከታላላቅ ሰዎች ጋር ነው። እውቀት ባይኖራቸውም ችሎታቸው ውስን ቢሆንም እነሱ ግን ከ ስመ ጥር ዶ/ር ፣ ጠበቃ ፣ ሳይንቲስት ፣ ፈላስፋ ጋር የራሳቸውን ስራና ስም አያይዘው ማንሳትና መፎካከር የሚሹ ናቸው። መሬት ላይ ግን ምንም እውቀቱም ችሎታውም የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ።
‎ ስለራሳቸው የሚሰማቸው ምን አይነት ምጡት እንደሆኑ ፣ ማንም የሌለው ተሰጦ ያላቸው ፣ የተለዩ አድርገው ነው።

‎በ Narcissistic personality disorder የተጠቁ ሰዎች ትችትን አጥብቀው የሚፈሩ ሰዎች ሲነቅፏቸው እነዛ ሰዎች ከነሱ ጋር ችግር ስላለበትና ስለሚመቀኝ እንጂ ስህተት ሰርተው እንዳልሆነ የሚያስቡ ናቸው። አድናቆትን አብዝተው የመሻትና ሲደነቁ ጥሩ የሆነ ስሜት የሚሰማቸው (Hypo mood) ላይ የሚገቡ በተቃራኒ ትችትን የመፍራት ሁኔታቸው አቅማቸውን እንዳይጠቀሙ ያግዳቸዋል። ከሰዎች እራሳቸውን ማግለል እና ብቸኝነት የመሆን ስሜት ያሳድርባቸዋል።

‎በዚህ ችግር የተጠቁ ሰዎች ትልቁ ችግር ያላቸውን ባህሪ ማስተዋል አይችሉም። ሰዎች ችግራቸውን ሊነግሯቸው ሲሞክሩ ምን አለብኝና ነው? በማለት ወደ ሰውየው የሚያዞሩ ናቸው። የራሳቸውን ችግር የሰውየው እንደሆነ እንዲሰማው (Gaslight) የሚያደርጉ ሰዎችን ለራሳቸው ጥቅም (Manipulate) በማድረግ የሚታወቁ ናቸው። ግን ችግር እንዳለባቸው ማመን አይፈልጉም። ይልቅ ሰዎች ስለማይረዷቸው እንደሆነ ይሰማቸዋል።

Narcissistic Personality Disorder በዋናነት በ 4 ይከፈላል

Grandiosity Narcissistic : ስለራሳቸው ያላቸው ምልከታ ከመጠን ያለፈ ነው። አለም ያለሱ የሚጨለምባት የሚመስላቸው የሚመስላቸው። ነቀፌታን የማይቀበሉ ከፍተኛ የሆነ ሙገሳን የሚሹ ናቸው። እኔ እንዲህ አድርጌ እንዲህ ሰርቼ ማንም ያላሳያችሁን አሳይቼ የሚሉ ናቸው። ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመን ያላቸው የሚመስሉ ሰዎችን የሚንቁ ናቸው።

Malignant Narcissistic : እኚህ ውስጥ ያሉ ሰዎችን manipulate, gaslight, exploit የሚያደርጉ ለ ፍቅር አጋሮቻቸው ሀዘኔታ የሌላቸው በሰዎች የሚጠቀሙ ናቸው።

Covert Narcissistic : በዚህኛው የ Narcissism ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች እነሱ በጣም እምቅ አቅም ኖሮዋቸው አለም ግን እነሱን ሊረዳቸው እንዳልቻለና እነሱ ያላቸውን የንቃት ደረጃ አለም ያልደረሰ በመሆኑና የነሱ አቅም ከሁሉ በላይ እንደሆነና አለምንና ሰዎቿን ለውድቀታቸው የሚወቅሱ ናቸው። ብዙ ግዜ በዚህ ውስጥ ያሉ ሰዎች Low self esteem ያላቸው ሊመስሉ ይችላሉ። ግን ነገሩን ጠልቀው ሲያስተውሏቸው ከሁሉ በላይ የሆነ እውቀት እንዳላቸው በውጣቸው የሚያስቡ ናቸው። የነሱ ችሎታና እውቀት መውጣት ያልቻለው አለም የነሱ የማወቅና የማሰላሰል አቅም ላይ ስላልደረሰ ነው ብለው እራሳቸውን እንደ ተጠቂ የሚቆጥሩት ናቸው። ብዙ ጊዜ የሚረዳቸው ሰው እንደሌለ ስለሚያስቡ በ ድባቴ (Depression) የመጠቃትና በሱስ የመውደቅ እድላቸው ሰፊ ነው። አልፎ አልፎ አንዳንድ ደራሲዎች ሽው ትልባቸዋለች።

Communal Narcissistic : ይሄኛው አሁን ላይ ባለው የ social media ዘመን በስፋት የሚታይ ነው። ልክ የሆነች ችግር በተከሰተች ቁጥር ችግሩ በተከሰተበት ቦታ የሆነች ድጋፍ ይዘው በመሄድ የሚሰጡትን ድጋፍ በየ social media ያጥለቀልቁታል። ላደረጓት እያንዳንዷ ዕርዳታ ምስጋና የሚሹ አቤት ቸርነትህ አቤት መልካምነትህ አንተኮ ባትደግፋቸው ማለቃቸው ነበር እንዲባሉ የሚሹ ከ ካሜራ ጀርባ ምንም ድጋፍ ማድረግ የማይፈልጉ ናቸው። ልክ የሆነች ድርቅ ስትከሰት ወይ ጎርፍ ለነሱ ፌሽታ ነው። አንድ ኪሎ ዱቄትና አንድ ዘይት ሰጥተው በዛ ነገር መወደስና መመስገን የሚሹ ናቸው። ድጋፍ የሚያደርጉት ለሰዎቹ አዝነው ሳይሆን ለ መወደስና ለመመስገን በዛም Like እና የበጎ ሰው አዋርድ ለማግኘት አቅደው ነው። ከላይ ከላይ ስፊታዩ ምስኪንና ደግ ነው የሚመስሉት ከጀርባቸው ግን ያለው ምክንያት ውዳሴ እና Like ነው። የ Tik tok አለም ይሄን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። የሆነች ኮሽ ያለች ነገር ስትኖር ካሜራቸውን አንጠልጥለው ሲሯሯጡ ማየት የተለመደ ነው።

@ourrthought
🔥43

‎በአምስተኛነት የሚያዝ አለ (Bening) በቅርቡ የመጣ። ያላቸውን ቁስና ማንኛውንም ነገር የሚያስቆጥሩ የሌሎቹን የሚያናንቁ። እነሱ የሚቀቡት ሽቶ ማንም የሌለው እንደሆነ የሚነዱት መኪና ሱፍ ማንም የሌውወ መሆኑን የሌሎቹ ቁስ ተራና ርካሽ መሆኑን የሚያሳዩ ስለሚበሉት ምግብ ውድነት በየቀኑ በየደቂቃው የሚያዳንቁ የሚያወሩ።

የ Narcissism Personality Disorder ዋና ዋና ምልክቶች ከሚባሉት በዋናነት 9 ምልክቶች ይጠቀሳሉ።

1. Lack of empathy ( ርህራሄ ያለማሳየት) : በዚህ በ Narcisstic የተጠቁ ሰዎች ለሌሎች ሰዎት ሀዘኔታና ርህራሄ የላቸውም። በድለዋችሁም ወይ በነሱ ምክንያት እናንተ ችግር ገብታቹሁም ህይወታቹህ ተመሰቃቅሎ ምንም ርህራሄ አይሰማቸውም። ትዳር ውስጥ ወይ ለልጆቻቸውም ስሜት አልባ የመሆን ችግር ይታይባቸዋል። ብዙ ጊዜን ችግር ከ Psychopath ጋር የሚያገናኙበት መንገድ አለ ልዩነቱ psychopath ከነጭራሹን ርህራሄና ሀዘን የማይሰማቸው ሲሆን ናርሲስቲክ ችግር ያለባቸው ግን ስለድርጊታቸው አልፎ አልፎ ሀዘን ውል ሊልባቸው ይችላል።

2. Entitlement : ከሌሎች የተለዩ እንደሆኑ ማሰብ። እኔ የተሻለ ትኩረትና እንክብካቤ ማግኘት አለብኝ። ልዩ በመሆኔ እኔን ብቻ እንክብካቤ ይገባኛል የሚል አጀባና እንክብካቤ የሚሹ ናቸው።

3.Grandiosity behavior : ስለራሳው ያላቸው ግምት ከነባራዊው ሁኔታ ጋር የማይገጥምና ስለራሳቸው ያላቸው ግምት መሬት ላይ ካለው የማይገናኝ ከልክ በላይ የተጋነነ ነው። ህልማቸው ከሁሉ የበላይ የሆነ ያክል ይሰማቸዋል። ግን በውኑ አለም ያለው የራሳቸው አቅምና እውቀት ከዛ ያነሰ ነው።

4. Superficiality : ሁሉ ነገራቸውን ከሚኖሩበት መኖሪያ ግዝፈት ፣ ከሚበሉት ምግብ ውድነት ፣ ከሚለብሱት ልብስ ፣ ጫማ ፣ መኪና ወዘተረፈ የሚለኩ ከዛ በስተጀርባ ያለውን ማንነታቸውን የማያሳዩ በውጪው ነገር ብቻ ለራሳቸውና ለሰዎች ግምት የሚሰጡ ናቸው።

5. Chronic seeking of admiration : ይሄኛው የማይቋረጥ ውደሳ ሙገሳ መቀበል የሚሹ ናቸው። አንተኮ ትለያየህ ፣ ካንተ ውጪ ሰው ለምኔ ፣ ዛሬ ደሞ ያደረከው ድንቅ ነው እያላቹህ በሚሰሩት እያንዳንዱ ነገር እየተከተላቹሁ ማቆለጳጳስ አለባቹህ። ይሄ በዚህ ባለንበት like, comment and share እየቆጠሩ የሚደሰቱና like በቀነሰ ቁጥር አለማቸው የሚጨልምባቸው አይነተኞች ናቸው።

6. Tendency to rage : ይሄኛው ባህሪ ከነሱ ሀሳብ ጋር ካልተስማማቹህ እና እነሱን እሺ ካላላቹህ ስሜታቸውን ቁጣቸውን መቆጣጠርና መግራት የሚቸግራቸው ናቸው። በትንሹ ነገር እያንባረቁ ሊያሸብሯቹህ ይችላል። ትዕግስት እና መረጋጋት የተሳናቸው ናቸው። እንዲህ አድርጉ ብለው ከዘገያቹህ በቁጣ በጩኸት መድረሻ ያሳጧቹሀል። ብዙ ጊዜ አለቆች የሚታይባቸው ችግር ነው።

7. Arrogance : ይሄኛው ደሞ በቃ ከኔ በላይ አንተ ታውቃለህ? ማነው ከኔ በላይ አዋቂ? የሚሉ ሁሉም ነገር ላይ ከነሱ በላይ አዋቂ ያለ የማይመስላቸው ሰዎች ናቸው። ምንም በማያውቁት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ፕሮፌሰሩን እከሌኮ መሀይም ነው ሊሏቹህ ይችላል። በግልፅ እኔ ካንተም ከማንም በላይ ነኝ ይላሉ በድፍረት እውነታው የተገላቢጦሽም ሆኖ።

8. High or low self esteem : ይሄኛው ከልክ ያለፈ በራስ መተማመን ወይ ዝቅ ያለ ይኖራቸዋል።

9. Envy and satisfaction by others suffering : ከፍተኛ የሆነ ቅናት ይሰማቸዋል። ሰው ሲሳካለት ይደብራቸዋል ፍቅረኛቸውም ሊሆን ይችላል። በሌሎች ሰዎች ስቃይና ሀዘን ከነሱ ጋር ጠላት ባትሆኑም በስቃያቹ ሊደሰቱ ይችላሉ ማግኘታቹህ ያንገበግባቸዋል።

ሌሎችም ብዙ አሉ ግን አብዛኛዎቹን ናርሲስቲክ ሰዎች የሚያመሳስላቸው እነዚህ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ቢያንስ አምስቱ ምልክቶችን በራሳቹህ ላይ የምታዩ ከሆነ ይህ ችግር እንዳለባቹህ አምናቹህ counseling መጀመር ነው ያለባቹህ።

ይሄ የ Narcissism Personality Disorder ችግር መነሻው ከየት ነው? ወይ አባባሹ ምንድነው? ካላቹህ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል። Nature (በተፈጥሮ) vs Nurture (በመማር) ቤተሰብ የሚቀርፅበት ወይ የሚያሳድግበት መንገድ ማለት ነው። አብዛኛውን ድርሻ የሚወስደው ከተወለድን በኋላ ያለው የ አስተዳደግ ውጤትና ልምምድ ነው።

Nature (በተፈጥሮ) አንዳንድ ልጆች በተፈጥሮ በ Biological dysfunction ከሌሎች ጋር ያላቸው መስተጋብር የላላ ሊሆን ይችላል ያም ባህሪያቸው በቤተሰብ እንክብካቤና ፍቅር ካልተያዘ ችግሩን ሊያባብሰው ይችላል።
የቤተሰብ አስተዳደግ ዘዴ (Attachment styles) ወሳኝ ነው። ከ 4ቱ የ attachment style ልጆች Avoidant attachment እና Neglect Attachment ያለበት ቤት ውስጥ የሚያድጉ ልጆች በልጅነታቸው Sensitive ሲሆኑና emotinal ሲሆኑ ለዛ ስሜታቸው ሲያድጉምላሽ የማያገኙ ከሆነ የ NPD የመጠቃት እድላቸውን የሰፋ ያደርገዋል።

በ Modeling (አርዕያ) : የ ናርሲስቲክ ቤት ውስጥ የሚያድጉ ልጆች ወላጆቻቸውን በመኮረጅ ባህሪያቸውን ይወስዳሉ።
Conditional love : ልጆች የሆነ ስራ ስለሰሩ ብቻ ቤተሰብ ደስ የሚለውን ስላደረጉ የምናመሰግናቸውና የምንወዳቸው ከሆነ ለመወደድ ብለው ወይ ይሁንታ ለማግኘች ያልተገባ ነገር ለማድረግ ይነሳሳሉ። Communal narcissism ብዙ ጊዜ ከዚህ ጋር ትስስር አለው።
Extrinsic focus : ልጆችን በውጫዊው አለም ብቻ ለነሱ ቦታ መስጠት ለምሳሌ ትምህርት አንደኛ ስለወጡ የሆነን ነገር ስላሸነፉ በዛ ነገር ብቻ እነሱን ገድበን የምናወድስና በውጪው አለም ባሳኩት ነገር የምናወድስና የምንወስናቸው ከሆነ ትልቅም ከሆኑ በኋላ በ tik tok like IG Fb like and comment እራሳቸውን የማያያዝ ችግር ላይ ይወድቃሉ።

NPD አብዛኛውን ጊዜ ከ Boarder line disorder, sociopath, Depression, paranoid disorder ጋር የመያያዝ እድሉ ሰፊ ነው።

ይህን ችግር እንደማንኛውም የ ማንነት ችግሮች በ Counseling እንዲሻሻል ለማድረግ ይቻላል። በ Dr. Ramania ገለፃ መሠረት በ አሜሪካ ውስጥ 6 ሰዎች 1 ሰው የ ናርሲስቲክ ህመም ተጠቂ እንደሆነ ይታሰባል። በ DSM መሠረት በ community sample 6.2% እንደሆነ ይታሰባል።

@ourrthought
🔥75
የኢትዮጵያ ህዝብ የእውቀትን ጥቅም በደንብ ለመገንዘብ ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩት ፤ ትልቁና ቁልፉ የ እውቀት መንገድ ጽሕፈት ነው ፤ ፊደል ነው ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የራሳችን ፊደል ነበረን ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የራሳችን በበሬዎች የማረስ ዘዴ ነበረን ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት በአጋሜ ፤ በየጁ ፤ በኮንሶ የእርከንና የመስኖ ዘዴዎች ነበሩን ፤ ለምዕተ-ዓመታት ታላላቅ ሐውልቶችንና ሕንፃዎችን የመሥራት ጥበብ ነበረን ፤ ከብዙ ምዕተ-ዓመታት በፊት በሰረገላ እንጠቀም ነበር ፤ ለብዙ ዘመናት መፍተልና መሸመን የታወቀ ነበር ፤ ይህ ሁሉ ዘዴ እንደ እውቀት በጽሑፍ አልተላለፈም ፤ ስለዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ አህያ ከመንዳትና በጎጆ ውስጥ ከመኖር ያልወጣበት ምክንያት ምንድን ነው?

በኢትዮጵያ ውስጥ እውቀት ፈላጊ አልነበረውም ፤ አሁንም የለውም።


አዳፍኔ ፍርሀትና መክሸፍ
‎ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም


@ourrthought
9🔥2
ሐሳቦቻችን
የኢትዮጵያ ህዝብ የእውቀትን ጥቅም በደንብ ለመገንዘብ ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩት ፤ ትልቁና ቁልፉ የ እውቀት መንገድ ጽሕፈት ነው ፤ ፊደል ነው ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የራሳችን ፊደል ነበረን ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የራሳችን በበሬዎች የማረስ ዘዴ ነበረን ፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት በአጋሜ ፤ በየጁ ፤ በኮንሶ የእርከንና የመስኖ ዘዴዎች ነበሩን ፤ ለምዕተ-ዓመታት ታላላቅ ሐውልቶችንና ሕንፃዎችን የመሥራት ጥበብ…
ስለ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ካነሳን አይቀር አንድ የምወደው ጨዋታ አለች።

«ኬንያ ናይሮቢ አንዲት መዝናኛ ቤት ተገኝቼ እየተዝናናሁ ነው። ቤቱ እንደ ፓርቲ ቤት ያለ ነው። ባንዱ ጥግ መጠጤን ይዤ፣ የዳንሱ ወለል ላይ ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚደንሱ ወጣቶችን አያለሁ። በዚህ መሃል የባሕር ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ እንግሊዛዊያን ነጮች ገቡ። አንዱ እንግሊዛዊ ቀጥታ ወደ ዳንስ ወለሉ ሄደና ከወዳጁ ጋር እየደነሰ ያለውን ኬንያዊ በካልቾ መታው። ኬንያዊው ተርበድብዶ የሴት ወዳጁን ጥሎ ገሸሽ አለ። እንግሊዛዊውም ከዛች ኬንያዊት ጋር መደነስ ጀመረ። በእንግሊዛዊው ድርጊት በጣም ተናደድኩ። ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁና ወደ ዳንስ ወለሉ አመራሁ። እኔም እንግሊዛዊውን በካልቾ ጠልዤ ኬንያዊቷን ተቀበልኩ። ጥቂት ካስደነስኳትም በኋላ ለተቀማው ኬንያዊ አስረከብኩ። ይህን ፈፅሜ ወደ መቀመጫዬ ሳመራ እንግሊዛዊው የጠየቀኝ አንድ ጥያቄ ነበር ፦ "ኢትዮጵያዊ ነህ?" የሚል።»

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ነብሳቸው በሰላም ትረፍ ባሉበት ይመቻቸው።

@ourrthought
9🔥2😁2🙏2