ሐሳቦቻችን
981 subscribers
103 photos
4 videos
5 files
2 links
በዚ ቻናል ላይ የተለያዩ ሀሳቦቻችንን ፣ ምልከታዎቻችንን ፣ ትዝብታችንን ፣ ከተለያዩ መልኮች እያነሳን እንወያያለን!

ሀሳብና አስተያየት ካላቹ @haileabb
Download Telegram
"ሰነፍ ሴትን ማን ሊያገኛት ይቻለዋል? ከ ዕንቁ የከበረች ናትና"

መፅሐፈ ፌሚኒስት

ም.1 ከቁ.3

@ourrthought
😁19👏4👎32
"አላህ ሲጣላ ብትር አይቆርጥም ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም" ይላሉ ወሎዬዎች።

እና አሁን ይሄ ዘበን አላህ የተጣ
.....

@ourrthought
🤔2😁1
ሐሳቦቻችን
እውን ግን ስልጡን ህዝቦች ነበርን? ይህን ጥያቄ ያዕቆብ ብርሀኑ በውቄ እንዲሁም ሌሎች አንስተውት ጥሩ ምላሽ ሰጥተውበታል። ባንድ ወቅት መለስ ዜናዊ "የ አክሱም ስልጣኔ ለ ሐመሩ ምኑ ነው?" የሚል ሀሳብ ሰጥተው አስታውሳለሁ። ከላይ ሲታይ ንግግሩ ዋዛ የሚመስል ውስጥ ውጡን መዝማዥ ሀሳብ ነው። የሀገራችን ስልጣኔን ስልጣኔ ለማለትስ የሚያስደፍርስ ነው? ያስብላል። ሥልጣኔያችን መራመድ ያቃተው እነ…
# የቅንጦት ሥልጣኔ

ሥልጣኔ ማለት ዓለትን መውቀር፣ ወርቅን ማቅለጥ ወይም ረቂቅ የሕግና የፍልስፍና መጻሕፍትን መደርደር ብቻ አይደለም። እውነተኛ ሥልጣኔ የሚለካው በቤተመንግሥቱ አጥር ስፋት ሳይሆን ያ ጥበብ ወርዶ የሰፊውን ሕዝብ ማዕድ ጤናና የዕለት ተዕለት ሕይወት መለወጥ ሲችል ብቻ ነው። የጥቂቶች ዕውቀት የብዙኃኑን ጨለማ ካላበራ ያ ነገር ሥልጣኔ ሳይሆን የአንድ ዘመን “ባህልና ቅንጦት” ተደርጎ ነው የሚወሰደው።

ጥበብ ዓለት ላይ ብቻ ተቀርቅሮ ሲቀርና ወደ ሕዝቡ ደም መዋሃድ ሲያቅተው ማኅበረሰቡ ካለፈው ዘመን ሳይቀዳ ለቀጣዩም ሳይተርፍ በነበረበት የኑሮ አዙሪት ውስጥ ተቀረቅሮ ይኖራል። ትልቁ ስብራት የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው። በጥበብ ማማ ላይ የተቀመጡት ሊቃውንትና የታችኛው ሰፊ ሕዝብ በመካከላቸው የሃሳብና የኑሮ ድልድይ ሳይኖራቸው ሲቀር ሀገር ታሪክ እንጂ ሕይወት አይኖራትም። ትናንት የነበረው ትልቅ የፈጠራ አቅም ዛሬ ላይ ተራ የትዝታ ቅርስ ሆኖ የሚቀረውም ጥበቡ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ስላልተተከለ ነው።

ስለዚህ አንድን ማኅበረሰብ “ሥልጡን” ለማለት የጥቂት ሰዎችን የላቀ አእምሮ ማየት ብቻ በቂ አይደለም። ሥልጣኔ ማለት ሰብዕናን መገንባትና ያንን ጥበብ ለትውልድ ማውረስ መቻል ነው። ጥበቡ የሕዝቡን የሕይወት ትግል ካላቀለለ ከበሽታና ከችጋር ካላዳነው እኛ ያለን የታሪክ ውበት እንጂ የሥልጣኔ እውነት ሊሆን አይችልም። የትናንቱ ትልቅነት ዛሬን መመገብ ካልቻለ ጥያቄው ዛሬም ድረስ ጥያቄ ሆኖ ይቀጥላል።

ሐኑ-ን
6/08/2018 ዓ.ም

@ourrthought
🔥6
ይህ የመጀመሪያው ክፍል የመጀመሪያው አንቀፅ ላይ ስለ ሰው ልጅ ህልውና፣ እውነት እና ሥነ ምግባራዊ ውስብስብነት በዘይቤያዊ አነጋገር በ “ግራጫ" ተወክሎ በዶ/ር ምህረት በፍልስፍና የተሰላሰለበት ነው፡፡

ሁለትዮሽ ነገሮች እንዴት በአንድ ነገር ውስጥ ተዋህደው ትርጉም እንደሚሰጡ እና አሻሚነትን እንደ ጉድለት ሳይሆን ትርጉም ያለው ነገር አድርጎ ለማሳየት የተሞከረበት ነው፡፡ ይህንንም በተለያየ መንገድ እንየው
ግራጫ ሁለትዮሽ አስተሳሰብን ውድቅ እንደማድረግ
"ግራጫ ነጭ ሚጠቁርበት እና ጥቁር የሚነጣበት ሰፊ ግዛት ነው፡፡''እነዚህ ነጭ እና ጥቁር የተባሉ ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን በምሳሌ እንያቸው
ደግነት/ ክፋት
እውነት / ውሸት
ትክክል / ስህተት
የአንድ ሰው ሁለት ጎኖች ናቸው ። እነኚህ ነገሮች በሰፊ
ግራጫ  ድብልቅ ውስጥ ያሉ የሞራል ማዕቀፎች ሲሆኑ እውነትነታቸው በፍፁምነት በወጥነት ሳይሆን በሽግግር ውስጥ የተዋቀረ ነው፡፡
አንዳንድ ድርጊቶች በራሳቸው በግልጽ አጥፊ (ጥቁር) ወይም በግልጽ አልሚ (ነጭ) ናቸው ነገር ግን አብዛኛዎቹ የሰው ልጆች ድርጊቶች ግራጫ ናቸው በተደባለቀ ዓላማ የሚነዱ በሁኔታዎች የተገደቡ ናቸው፡፡
ይህም ሰዎች ከንፁህ በጎነት ወይም ከንፁህ ክፋት እምብዛም እንዳልተሰሩ ያሳየናል።

ግራጫ ብርሃን እና ጨለማን እርስ በርስ አንደማዋሀድ
ግራጫ እንደ የብርሃን ኩርፊያ ወይም የጨለማ ፈገግታ ሆኖ ሊታይ ይችላል ወደ አንድ ጎን ዘንበል ብሎ... ግን ሁለቱንም የሚያጣምር ቀለም ነው።
የብርሃን ኩርፊያ ፦ በብርሀን ውስጥ ስጋትን እንደመመልከት ነው
የጨለማ ፈገግታ ፦ በጨለማ ውስጥ ተስፋን እንደመመልከት ነው ግራጫ ተለዋዋጭ ነው የማይንቀሳቀስ አይደለም። ዘንበል ይላል። ይቀየራል።ይህም በጎነት ሊበላሽ ፣ ክፉነት ደሞ ወደ ጥሩነት ሊሻሻል ይችላል ከሚለው ሀሳብ ጋር ይጣጣማል ። ይህም የሞራል ውስብስብነትን ያሳየናል።

ግራጫ በአውድ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ከፍልስፍና አንፃር ከነኚህ ሀሳቦች ጋር ይሄዳል
Phenomenology: meaning arises from relations not essences
Buddhist thought: identity lacks fixed self-nature
Postmodernism: truth is contextual, not absolute

ግራጫን እንደ ሰው ልጅ ሌላነት እና የተጋራ ሰብአዊነት
"የሰው ልጅ የሆነ ልዩነት እና እውነት በራሱ ሰፊ ግራጫነት ተደብቆ ተገልጧል።"

"ሌላነት" ስንል እያንዳንዱ ሰው ፈጽሞ የማይለወጥ ልዩነት ያለው መሆኑን
"እውነት" ስንል የጋራ ሰብአዊነታችን አንድ ያደርገናል ተቃርኖ የለውም አብሮ ሚኖር መሆኑን ያስገነዝበናል።
ግራጫ ፦ልዩነት ተመሳሳይነትን የማይሽርበት ቦታ ነው፡፡

እያንዳንዱ ሰው ሌላ ሰው መሆኑን መረዳት እና እያንዳንዱ ሌላ ሰው እንደኛ መሆኑን መረዳት በህይወት ላይ አንድ ግራጫ አመለካከት ነው::
እያንዳንዱ ሰው ሊካድ የማይችል ሌላ ነው። እያንዳንዱ ሰው በመሠረቱ ተመሳሳይ ነው

በአጠቃላይ ግራጫ ድክመት፤ ወጥነትን መፍራት አደለም ወይም በብዥታ ውስጥ ግራ መጋባት አይደለም፣ ነገር ግን በጥልቀት በጥበብ መኖር ማለትም በልዩነት ውስጥ ተመሳሳይነትን ተቀብሎ አምኖ በግራጫ አለም ውስጥ መኖር እንደማለት ነው፡፡ እውነታን በፍፁምነት በተሻለ ሁኔታ አንረዳውም በግራጫነት እንጂ፡፡

ግራጫ የእውነት ቀለም ነው!!


በከነዓናዊት የተከተበ

በውስጥ መስመር የመጣ ፅሑፍ። ትውልዱ ትንታግ ሆኗል።

@ourrthought
4🔥3
አለም ውርደት ለመሰላት ነገር ቸልተኛ አይደለችም።

ኩርቢት
መፅሐፍ

@ourrthought
🔥9
Attention Market

አሁን ላይ አለማችን ላይ ትልቁ አቅም ያለው ማነው? ብትሉ Data ያለው እና የሰዎችን ቀልብ ማግኘት የቻለው ነው።
አሁን ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሰዎች የትኩረት መቀነስ እና በ አንድ ነገር ላይ የመቆየት የትኩረት አቅም እየተሟጠጠ ያለበት ጊዜ ላይ ነን። ይህ ያለንበት የ ድህረ ዘመናዊነት age of post modernism era ሰዎችን ከለት ወደ ለት በ tik tok በ Facebook reel Instagram reel እያለ ሰዎች የትኩረት መጠናቸው ዝቅ እያለ አንድ ነገር ላይ ጠንካራ እውቀት እንዳይኖራቸው እያደረገ ያለበት ጊዜ ነው።

በ psychology ADHD የሚባል ህመም አለ። ወደ አማርኛ ስታመጡት የመቅበጥበጥ ችግር ልትሉት ትችላላቹህ። Attention Deficit Hyperactive Disorder የሚባል የ አዕምሮ ችግር አለ። አንድ ነገር ላይ ለ አንድ ደቂቃ ትኩረት የማድረግ አቅም የላቸውም። እዚህ ጋር ስትፈልጓቸው እዛ ጋር እዛ ስትሄዱ እዚህ የምታገኟቸው ናቸው። አሁን ላይ የ አጫጭር ምስሎች መብዛት ሰዎችን መጠኑ ዝቅ ወዳለ ADHD ችግር የሚገፋ ነው።

የነዚህ platform አሰራር cheap dopamine ማለትም በትንሽ ጊዜ ውስጥ የሚገኝ የ ደስታ ሆርሞን አዕምሮ እንዲለቅ የሚያደርጉ ናቸው። ያ ማለት ሰዎች ባጭር ጊዜ ቶሎ ደስታ የመፈለግ ነገር ውስጥ ይከታቸዋል። ለረጅም ደቂቃ አንድ ነገር ላይ ጊዜ አጥፍቶ ጥልቅ እውቀት ከማግኘት ይልቅ ከላይ ከላይ የሆነ ነገር በማየት ቶሎ ቶሎ የደስታ ስሜት ማግኘት እንደማለት ነው። ያ ደሞ አንድን ነገር ለረጅም ጊዜ ከማየት ይልቅ ቶሎ ቶሎ ባጫጭር ቪዲዮ መደሰት ማለት ነው።

Operant conditioning የሚባል የ Behavioral theory ላይ B.F Skinner የተባለ psychologist ስለ ሰዎች ባህሪ ምን shape ያደርጋቸዋል የሚለውን ሲያጠና አንድ ሰው አንድን ነገር ለማስተማር ወይም ለመቅጣት Reinforcement and punishment አስፈላጊ መሆናቸውን በሱ theory ላይ የታየ ነው። ይሄ ማለት ጥሩ ስነ ምግርባር ስታሳዩ በድርጊታቹህ እንድትቀጥሉ Reinforce ትደረጋላቹህ። ለምሳሌ ጥሩ ስራ ስትሰራ ሽልማት አለህ እንደማለት ነው። መጥፎ ስትሰራ ትቀጣለህ punishment አለው። በዚህ ሂደት አንተን ባህሪህን ቅርፅ ያሲዙታል ማለት ነው።

እነ tik tok, Facebook, Instagram የመሳሰሉት platform ሲሰሩ እንደዚህ አይነት theory ይጠናሉ። tik tok ላይ ለረጅም ጊዜ የሚያቆይህ ነገር በ psychologist እንዲሁም በብዙ ጥናት በተጠና ጥናት ነው። አንተን ባህሪህን ያለህበትን ስሜት ከምታየው ቪዲዮ በሰበሰቡት data የሚያውቁህ በመሆኑ ረጅም ጊዜ እንድትቆይ reinforcement ይሰጡሀል። ልክ ሲሰለችህ አከባቢ በጣም የምትወደው አይነት ቪዲዮ ይለቁልሀል ያ ርዝማኔህን ያቆየዋል ማለት ነው።

ታዲያ ካስተዋልክ የምትወደውን ነገር ብቻ አይለቁልህም ለምን ብትል satiation የሚባል ነገር አለ። Satiation ማለት የምትወደውን ነገር ብቻ ቢያደርጉልህ ከመጠን በላይ ሆኖብህ ማር ሲበዛ ይመራል እንዲሉ Over reinforce አይሰጡህም። የማትወደውን ነገር ቀልቀል ያደርጉልሀል። በዛ ቆይታህ ይራዘማል ማለት ነው።

ትልቁ የዘመኑ ችግር ሰዎችን እንዴት manipulate እናድርጋቸው ሳይሆን አሁን ትልቁ ችግር ከ 1 ደቂቃ በታች በማይሆን ጊዜ ውስጥ በዚህ የሰዎች ስልቹነት በገነነበት ዘመን እንዴት ትኩረታቸውን ማግኘት እንችላለን የሚለው ነው። ያንተን ትኩረት Attention ያገኘ ሰዎ አሸናፊ ነው። social media ያለው ጦርነት እንዴት ትኩረት ላግኝ የሚለው ነው። ትኩረት ያገኘ ሰው በ አንድ ቀን ይከብራል። እራስህን ለማሳወቅ ከ 30 ሰከንድ በታች ነው ያለህ በዛች ጠባብ ጊዜ ውስጥ ምን ባደርግ ነው ትኩረት የማገኘው? የሚለውን ካላሰብክ ካለዛ 1000 ሺህ ቪዲዮም ደርድረህ ማንም ሳያውቅህ ዘመንህን ስትለፋ ትኖራለህ።

ይቀጥላል...

@ourrthought
👍111
ሐሳቦቻችን
Photo
Dissociative Identity Disorder

አለም ላይ ምንም ነገር ቢረቅ እንደ አዕምሮ ግን የሚያስገርም ረቂቅ ነገር የለም። ሰዎች አሁን የደረስንበት የተራቀቀ ደረጃ ድንቅ ቢሆንም ስለ አዕምሮ ግን ያወቅነው ጥቂት ነው። የሁሉም ሰዎ አዕምሮ የየራሱ ባህሪና ነገሮችን የሚመዝንበት የራሱ ባህሪው አስገራሚ ነው። ይበልጥ አግራሞቴን የሚያበዛው አንዳንድ የ አዕምሮ ህመም ችግሮች ሳስተውል ነው። ስለ አዕምሮ ከሚያስገርሙኝ አንዱ DID (Dissociative Identity Disorder) ነው።

የአዕምሮ ህመም ወሰብሰብ የሚያደርገው ነገር የ አንዱ ህመም የዳነበት ለሌላ ሰው የማይጠቅም መሆኑ ነው። ለምሳሌ የ ጉንፋን ህመም ቢያመን በጉንፋን መድሀኒት ሁሉም መዳን ይችላል። ግን አንድ ድባቴ ህመም ያለበትን ሰው ከሌላው ድባቴ ከያዘው ጋር በተመሳሳይ መንገድ የማናድነው መሆኑ ነው። እያንዳንዱ ሰው በራሱ መንገድ ክትትልና ህክምና የሚፈልግ መሆኑ የ አዕምሮ ህመም ትንሽ ወሰብሰብ ያደርገዋል።

DID የበፊት ስሙ Multiple Identity Disorder ይባል ነበር። ከብዙ ምርም በኋላ ግን ወደ DID ተቀይሯል። Multiple Identity የተባለበት ምክንያት በፊት በዚህ ህመም የተጠቁ ሰዎች ብዙ የተለያየ ማንነት አላቸው ተብሎ ስለሚታሰብ ነበር። ያ ማንነታቸው ግን ከ Trauma እንደሚነሳ አያውቁትም ነበር። DID እስካሁን በምርምር በሂደት ላይ ያለ የ አዕምሮ ህመም አይነት ነው።

ህመሙ የሚከሰተው ብዙ ጊዜ በልጅነት በሚከሰት Trauma ችግር ነው። ከትራውማም ከባድ post traumatic disorder የሚያመዝን ነው። ግለሰቡ በጊዜው እራሱን ከዛ ነገር መከላከል የማይችልበት ሁኔታ ሲሆን አዕምሮ ከ አዕቅሙ በላይ በመሆኑ እራሱን ለመከላከል የጊዜውን ክስተት የራሱን የቻለ ሁኔታውን የሚያስቀምጥበት የትዝታ ማህደር ያበጃል ማለት ነው። ያ የትዝታ ማህደር ህፃኑን ከጥቃቱ ለማዳንና (ለመበቀል) የራሱን የሆኑ ሂደት እያበጀ ከሰውየው እውቅና ውጪ ድርጊቱ ይከናወናል ማለት ነው።
ያ ማለት አንድ ህፃን ልጅ በልጅነቷ ብትደፈር አዕምሮዋ መቋቋም የሚከብደው በመሆኑ ጉዳዩን ህፃኗን ከ ጥቃት ለመጠበቅ የተደፈረችበትን አጋጣሚ ወደ ድብቁ የ አዕምሮ ክፍል (unconscious mind) ይደብቀዋል ማለት ነው። አስቀምጦት ብቻም አያበቃም የራሱን የሆነ እድሜ ስም እና የቀለም ስያሜ ለብቻው ይሰጠዋል። አዕምሮ ይሄን በሚያደርግበት ሂደት ዋና ግለሰቧ እውቅና የላትም። ያኔ ለብቻው በ ኢንቁ (unconscious mind) የተቀመጠው ያ ስብዕና አብሮ እያደገ የራሱን ስብዕና እያጎለበተ ይሄዳል። በዚህም አያበቃም ልክ ይህች ህፃን ትልቅ ሰው ሆና እሷ በ እንቅልፍ ልብ በምትሆንበት ጊዜ ይህ ክፍል ይነቃና በቀሉን ይፈፅማል ማለት ነው።

ታዲያ አንድ በዚህ ዲስኦርደር የተጠቃ ሰው ከ 10 እስከ 15 ድብቅ ማንነቶች አንድ ሰው ላይ የመከሰት እድላቸው ሰፊ ነው። አልፎ አልፎ ከ 100 በላይ ድብቅ ማንነቶች በአዕምሮ ውስጥ ሊኖር ይችላል ከሰውየው ግንዛቤ ውጪ ማለት ነው። እያንዳንዱ ማንነቶች እራሳቸውን የቻሉ ማንነች ያላቸውና የተለያየ ፍላጎትና እድሜ ያላቸው ናቸው። ግን ዝም ብሎ ይሄ ድብቅ ስብዕና አይገለጥም። እያንዳንዱ ለመገለጥ ከነሱ ጋር የተገናኘ ትስስር ያለው ክስተት መፈጠር አለበት። ለምሳሌ ቅድም ባልኩት መሠረት ህፃን ሆና የደፈራት ሰውየ ቀይ ጃኬት ያደረገና ፊቱ ጥቁር ከሆነ ያቺ ልጅ ትልቅ ሆና እሱን የሚመስል ቀይ ጃኬት ያደረገ ጥቁር ሰው ባየች ቅፅበት አዕምሮዋ ውስጥ የተደበቀው የራሷ ማንነት እራሱን ለመከላከል ይገለጣል ማለት ነው። አንዱ ስብዕና ሲገለጥ ሰውየው ምንም አያስታውስም።

DID የሚከሰተው አዕምሮን ከማይችለው በላይ አደጋ ሲደርስበት ሰውየውን ከጉዳት ለመጠበቅ በ ኢ ንቁ የትውስታ ክፍሉ ይከተዋል። ለዛም ነው በዚህ ህመም የሚጠቁ ሰዎችን ህክምና ለመስጠት አስቸጋሪ የሚያደርገው አንደኛው ስብዕና ስለሌላኛው የማያውቅ በመሆኑ ግለሰቡም የማያውቅ በመሆኑ በጣም ትልቅ ፈተና ያደርገዋል። ይህን ህመም በሚገባ የሚያሳይ ፊልም በሀገራችን ማንያዘዋል የሚለው ፊልም ሲሆን ከ ውጪ ደሞ split የተሰኘው ፊልም ነው። split የሚለው ፊልም ገፀ ባህሪው 6 ደባል ስብዕናዎች ያሉት ሲሆን እያንዳንዳቸው የራሳቸው ባህሪ ማንነትና ዕድሜ ያላቸው ናቸው።

ከመፅሐፍ ደሞ የ ሲድኒ ሼልደን Tell me your dreams የሚለውና የ አዘርግ በኢያሪኮ ከተማ or በኢያሪኮ ጩኸት በዛ የሚለው የማውቃቸው ናቸው።

Tell me your dreams የሚለው መፅሐፉ የሚያጠነጥነው በ DID (ዲሶሴቴቪ አይደንቲቲ ዲስኦርደር) ስላጠቃት ገፀ ባህሪ ነው።
ዋና ገፀ ባህሪዋ በላዩዋ ላይ ደባል ስብዕናዎች ያሏት ስትሆን ሶስት ደባል ስብዕናዎች በውስጧ አሏት። ታዲያ እነዚህ ስብዕናዎች በየተራ ነው የሚገለጡባት ለምሳሌ አንደኛዋ ስብዕና አርት ትወዳለች አንደኛዋ የቢሮ ሰራተኛ ናት አንደኛዋ ጨካኝና ቀበጥ ናት። ታዲያ እነዚህ ስብዕናዎች በ አንድ ጊዜ አይገለጡም በየተራ ነው የሚገለጡባት። ለምሳሌ አርት የምቶደው ስብዕና ከተገለጠች ቢያን ለ ሳምንት በዛ ስብዕና ትቆያለች ግን እሷ ይሄ መከሰቱን አታውቅም።

በዚህ መፅሐፍም ይሄን ነው የገለፀልን ከሦስቱ ስብዕና አንደኛዋ ስብዕናዋ ስትገለጥ ጨካኝ በመሆኗ ሰዎችን እያደነች የምትገድልበትን ሂደት በመጨረሻም በፍርድ ቤት ውሳኔ ነፃ እስክትለቀቅ ድረስ ያለውን ሂደት ያሳያል። ሲድኒ ይሄን መፅሐፍ ሲፅፈው ብዙ የፍርድ ቤት ሂደትን በአካል ተገኝቷል።

አንዳንድ ነገር ለመግለፅ ትንሽ አስቸጋሪ በመሆናቸው ያልተገለጠላቹህ ሀሳብ ካለ በ ሀሳብ መስጫ ልትጠይቁ ትችላላቹህ።

@ourrthought
👏10🔥21👍1
ነገረ ቦለጢቃ

የዘንድሮ ምርጫ የከሸፈ ይመስላቹሀል?

በርግጥ መልሳቹህ የምን ምርጫ ነው? ማን ተፎካካሪ ኖሮ ነው የምንመርጠው? የመሳሰሉ ጥያቄዎች ሊመጣባቹህ እንደሚችል ግልፅ ነው። የዘንድሮ ምርጫ ግን እንደኔ አልከሸፍም። እንዴት? ብትሉ ምርጫ አላማው የዲሞክራሲን መኖር ህዝቡ የሚተገብርበት ይግዛኝ የሚለውን እሳቤ (Ideology) የሚመርጥበት ነው።

የዘንድሮ ምርጫ ብቻ ሳይሆን የ አፍሪካ አጠቃላይ የምርጫ ሂደት ትክክለኛ ዲሞክራሲ እንደሌለ የሚታይበት ትክክለኛ የህዝቡንና የመሪውን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። በዘንድሮ የኛ ምርጫም ህዝቡ በምርጫ ተስፋ የቆረጠ መሆኑን እና ትክክለኛ የምርጫ ስርአትና ተፎካካሪ አካላት እንደሌሉ የታየበት ነው። ብንመርጠም ይሄው መንግስት ባንመርጥም ራሱ መሆኑን ያሳየን ነው። በዚህ ትንታኔ ካየነው ዲሞክራሲና ፍትሀዊ የሆነ የመንግስት ስርአት አለመኖሩን አሳይቶናል እንዲሁም የህዝቡን በምርጫ ተስፋ መቁረጥ እና ምርጫው አልከሸፈም ማለት ይቻላል። እውነታውን ማየት ከቻልንበት ዲሞክራሲ አለመኖሩን ካሳየን ትልቅ ቁም ነገር ነው።

ፅሑፉን በአንድ ቀልድ ልዝጋው።
የ አሜሪካ የ ቻይናና የ ኢትዮጵያ መሪዎች ተገናኝተው ስለ ምርጫ ስርአት እየተነጋገሩ ነው። የ ቻይናው መሪ እኛ ሀገር ከተመረጠ ከ ሳምንት በኋላ ማን እንደተመረጠ ወዲያው ቆጥረን በሀቀኝነት እናሳውቃለን። አለ ቀጥሎ የ አሜሪካው መሪ እኛ ሀገር ከናንተ ይፈጥናል። በተመረጠ በንጋታው ቆጥረን እናሳውቃለን አለ። ሰዎቹ ተደመሙ በቅልጥፍናቸው። ይሄኔ የሀገራችን መሪ ብድግ አለና ይሄ ምኑ ያስገርማል ታዲያ? እኛ ሀገር ከመመረጡ ከ አንድ ሳምንት ቀድመን ነው የምናውቀው አለ። ይባላል። ይህቻትና ዲሞክራሲ። በቅልጥፍናችን መደመም ነው።

@ourrthought
😁225
ከባርነት በላይ ነፃነት ለሰው ልጅ ትልቅ የሀላፊነት ሸክም አለው።

አንድ ባሪያ በባርነት ዘመኑ ውሎው ምግቡ የሚሰራው የሚለብሰው በሙሉ የተወሰነለት በመሆኑ የተለየ የሚያስጨንቀው ነገር የለበትም። ይሄን ባሪያ ከባርነት አውጥታቹ ነፃ ብታደርጉት ግን ወዴት መሄድ እንዳለበት ፣ ምን መስራት እንዳለበት ፣ በትርፍ ጊዜው ምን እንደሚያደርግ ፣ ስለሚለብሰው ፣ ስለሚጠጣው ስለ እያንዳንዱ ነገሩ የማሰብና የመጨነቅ ሀላፊነትም አብሮ ይመጣበታል።

ከመፅሐፍ ቅዱስ ዘፍጥረትን ብትመለከቱ ስለዚህ ሐሳብ በጥሩ ሁኔታ ዬብራራል። ልክ አዳምን ፈጣሪ እንደፈጠረው ሙሉ ለሙሉ ለነፃነቱ ተላልፎ እንዲሰጥና ዝም ብሎ የ አልባሌ ውሎ እንዲውል አላደረገውም። ይልቅስ አዳምን የ ገነትን ዛፎች እንዲንከባከብና ፣ ለእንስሳቱ ስም እንዲሰጥ በመሳሰሉ ነገሮች እንዲጠመድ ነበር ያደረገው።

ሰው ያለምንም ሀላፊነት ሙሉ ለሙሉ ዝም ብሎ ነፃ ሆኖ ቢኖር ግራ መጋባትና ጭንቀት ውስጥ ይገባል። ሰውን በድብርት ለመግደል psychological killing ከፈለክ ዝም ብለህ እየቀለብከው ያለምንም ሀላፊነት እና ስራ ልቀቀው ያኔ መን እንደሚያደርግና መስራት እነዳለበት ምን ሀላፊነት መውሰድ እንዳለበት ባለማወቁ በራሱ ፍላጎቶች ተጠልፎ ይወድቃል።

"ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል"
"ስራ ከምፈታ ልጄን ላፋታ"

@ourrthought
12👍1
Asa - Jailer
naïve
Im in chain you're in chains too
I wear uniform and you wear uniform too
Im a prisoner,
You're a prisoner too Mr Jailer

I have fears you have fears too
I will die, you sef go die too
Life is beautiful
Don't you think so too Mr Jailer

ሸጋ ሙዚንቃ

@ourrthought
👏21🔥1
³⁴ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።

ማቴ ፦ 6
@ourrthought
11😢4
"
He who has a why to live can bear almost any how."
"Wer ein Warum zu leben hat, erträgt fast jedes Wie."

Friedrich Nietzsche


"Why" is the only real source of power.
without it, you are powerless!

Our only hope, our only peace, is to understand it, to understand the why.

Matrix movie

@ourrthought
18🔥4
Astral Projection ስለሚባለው ነገር እንቸክችክ ይሆን?

ምናልባት ሞክራችሁት ልምዱ ያላቹህ ሰዎች በ comment ላይ አስቀምጡና ምናልባት ሰፋ አድርጌ እፅፍላቹሀለሁ።
ወይ ደሞ ቀን መድበን በ voice discuss ልናደርግበትም እንችላለን።
7
ሐሳቦቻችን
Photo
‎Astral Projection

‎በፊት ላይ ትርጉሙ ሳይገባኝ በፊት አልፎ አልፎ እንግዳ ስሜት ይሰማኝ ነበር። በጣም ለረጅም ጊዜ ቁጭ ብዬ በሆነ ነገር ስብሰለሰል የሆነ ነገሬ ንጥል ብሎ ካላቴን ከላይ እስከታች የሚታዘብ ነገር ያጋጥመኝ ነበር። በዛ ሰዐት ለተወሰኑ ደቂቃዎች አካላቴን እንደ ሌላ ሰው እየደነገጥኩ አየው ነበር። እጄን ሰውነቴን ሁሉ ነገሬን እየዳበስኩ ግራ እጋባ ነበር። ምናልባት ለሰዎች ብናገረው ተቃወሰ እንዳልባል ዝምታን እመርጥ ነበር። የሆነ ጊዜ የተቀራረበ ነገር አየሁ Astral projection የሚል እሳቤ።
‎Astral Projection ማለት የነብስ ከ አካላዊ ሰውነት ተነጥላ ከዚህኛው 3D አለም ወደሌላኛው አለም የምትገባበትና ፡ ሌላ ቦታ ላይ መገኘት ማለት ነው። ነብስህ በህይወት እያለህ ከስጋህ ተነጥላ አንተን የምታይህና ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ ምን እየተሰራ እንዳለ መታዘብ የምትችልበት ጥበብ ነው። ይህ ተግባር ከ ኦርቶዶክስ እምነት ጋር ከ 10ሩ የብቃት ደረጃዎች ውስጥ ሁሰት ከሚለው እሳቤ ጋር ይጣጣማል። ሁሰት ማለት አንድ ቦታ ሆነን አካላችን እዚህ ሁኖ ነብሳችን ወይ ንቃተ ህሊናችን (consciousness) ለብቻው ተነጥሎ ወደ ሌላ ቦታ መሄድና ማየት የሚችልበት ጥበብ ነው። ስሙን የማላስታውሰው መፅሐፍ ቅዱስ ላይ እስራኤል ቁጭ ብሎ በሀሳቡ የ አይሁድን ጠላት የሚሰሩትን የጦርነት ዕቅድ እያየ የሚናገር አንድ ቦታ አለ።

‎ ይህ ነገር ከየት መጣ ያላችሁኝ እንደሆን ከ ጥንት ጀምሮ የሚደረግ ጥንታዊ ሀይማኖቶች ልምምድ ላይ ያለ ድርጊት ነው። ግን ወደፊት ሊወጣ የቻለው በ Theosophy እንቅስቃሴ ነው። በነ Helena በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1875 አከባቢ ነው። 1800 ዎቹ ላይ አብርሀሚክ ሀይማኖት ላይ በተለይም ክርስትናው ላይ በአውሮፓ ከፍተኛ የሆነ ጥያቄ የሚነሳበት ወቅት ነበር። በ አመክንዮ ብቻ የሚለው ነውጥ አውሮፓውያኑ ክርስትና ላይ እንዲያምፁ ያደረገበትና ብዙ ጥያቄዎች የሚነሱበት የነበረበት ወቅት የነበረ ነው። በዚህን ጊዜ ነው የ Theosophical movement የተጀመረው። አብዛኛው የ ቡድሂዝም ፣ ሂንዱዝም ፣ ጥንታዊ እምነቶች ላይ ያሉ መፅሐፍ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉመው የምስራቁ አለም ሀይማኖቶች የተጠኑበት ጊዜ ነበር።

‎የዛኔ ነው Helena Petrovna Blavatsky እና ሁለት ጓዶቿ (በሷ ምክንያት) የዚህን የሀይማኖት ንቅናቄ የጀመሩት። የዚህ ሀይማኖት መሰል እንቅስቃሴ ከ ሂንዱ ፣ ቡድሂዝም ፣ ክርስትና ፣ ጥንቁልና ልምምድ ፣ ምዕራባዊ የሀይማኖት ልምምድ ተውጣቶ የተጀመረ ነው። የሀይማኖታቸው እንቅስቃሴን መንፈሳዊውን ጥበብ መመርመር Devine Wisdom (Theosophy) ብለው የጀመሩት። ሁሉም ጥንታዊ ሀይማኖቶች የሚያመሳስላቸው ነገር አለ መንፈሳዊ ጥበብ ያመሳስላቸዋል ብለው ያምናሉ። "There is no religion higher than truth" ይላሉ እንደ መፈክር። Karma ፣ Reincarnation ፣ Astral plane ፣ Nature of human being ፣ psychic energy የሚተኮርባቸው ናቸው። ሁሉም ሰው መንፈሳዊነት ጥበብ አለው ይሄን መንፈሳዊነቱን ጥበቡን እንዲቀዳጅ ነው የምንሻው ይላሉ።

‎ ታዲያ የ Theosophy ሁለት አይነት የሀይማኖት አምልኮ ስርአት አለ ይላሉ። Exoteric የ አደባባይ እውቀት። ይሄ በ የቸርች መስኪድ የምንሰበከው ግልፅ የሀይማኖት ትምህርት ነው። ሌላው Esoteric ነው። ይሄ ዋናው የ ቴዎሶፊ ትኩረት የሆነው ነው። በሂንዱ Mahayan የሚሉት ድብቁ ለብዙሀኑ የማይነገረውና ጥቂቶች ብቻ የሚያውቁት መንፈሳዊ ጥበብ ነው። እንግዲህ ከነዚህ ጥበቦች ውስጥ Astral Projection አንዱ ነው ማለት ነው።

‎The key to theosophy የሚለው የ Helena በጥያቄና መልስ በተዘጋጀ መፅሐፍ ላይ Astral Projection ሰዎች መንፈሳዊ ልምምድ የሚጀምሩበት ብዙ ጥበብ የሚያገኙበት አንዱ ደረጃ ነው ትላለች። ነብሳችን ከ ማይታየው አለም ጋር ከ ስጋ እስር ወጥታ የምትማርበት ከ መንፈሳዊ አለም ጋር የሚገናኝበት ነው ብላ ነው የምትገልፅው። ግን እነዚህን ልምምዶች ሌሎቹንም እንዲሁ እንዲተገበሩ አትመክርም ከዛ ይልቅ ሌሎች መንፈሳዊ ልምምዶችን እንዲያደርጉ ትመክራለች። ወደ Astral realm ለመግባት ዮጋ ፣ እንቅልፍ ፣ ተመስጦ የሚረዱ መንገዶች ናቸው። አንዳንዴ ሳናስበውም ይከሰታል። ጉዳዩ ልክ ነብሳቹ ከሰውነታቹህ ተነጥላ ወይ ኮንሸስነሳቹህ ለብቻው ወደ ፈለገበት ቦታ የሚሄድበት ጥበብ ነው። ለምሳሌ ቤት ተኝታቹህ ሌላ ሀገር ተንሸራሽራቹህ መምጣት የምታዩት ደሞ እውነተኛ ምስልና ትውስታ የሚኖረው ምስል ነው። ብዙዎቹ ከ አስትራል በፊት ሉሲ ድሪም ቢኖራቹ የተመረጠ ነው ይላሉ። ቀጥታ እዛኛው አለም ከመግባት በፊት ከመተኛታቹ በፊት የምታስቡት የራሳቹህ የሆነ ጥሩ የሆነ ያማረና ወደዛኛው አለም ስትገቡ ልታገኙት የምትሹትን ብታስቡ ወደዛኛው አለም ከገባቹህ በኋላ አላማችሁን አትረሱም ይላሉ።

‎ በ እንቅልፍ ልባችን ወደዚህ አለም የምንገባ ቢሆንም ግን ትውስታችን አይኖርም ትላለች። ጉዳዩን ከተለማመዱት እና መቆጣጠር ከቻሉ ከሌላኛው መንፈሳዊ አለም ጋር የምንገናኝ በመሆኑ ብዙ የመንፈሳዊ ጥበብ እውቀት እናገኛለን። ያለ ጥሩ ልምምድ ከሆነ ግን የ ክፉ መንፈስ መጫወቻ እንሆናለን። ግን ብዙ ግዜ እንዲሁ እንዲደረግ የሚመከር አይደለም። ልምምዱን ከመጀመራቹህ በፊት የሆነ የምትወዱትን ዘፈን ወይም ደሞ የሰአት መቁጠሪያ የሚመስል ነገር ቋ ቋ እያለ የሚቆጥር ድምፅ ያለው ነገር ቢኖር ይመረጣል።

‎እንዲህ አይነት ልምምድ ነገሩን ከማወቅ ጉጉት አንፃር የሚገቡ ሰዎች ብዙ ጊዜ ከዚህኛው አለም ወጥተው በ Astral Projection ሌላኛው አለም (realm) ላይ ሲገቡ ምንም አላማ ስለሌላቸው በ ነብስ ነጣቂዎች (parasite) ወጥመድ ይገባሉ። አስፈሪ ምስሎችን ከሌላኛው አለም ማየት ይጀምራሉ። ከባባድ የሆኑ እኛ የማናያቸውን ብዙ ነገር የሚያዩ በመሆናቸው መቋቋም ይከብዳቸዋል። አንዴ እዚህ ልምምድ ከገቡ በኋላ ጉዳዩን ባይፈልጉትም በተኙ ቁጥር ህልም እየመሰላቸው ወደዛኛው አለም እየገቡ መተኛት ይቸገራሉ።
‎ አንዳንዶቹ ገና ወደ መኝታ ሲሄዱ መተኛት ሁሉ በጣም አስፈሪ ምስልና ድምፅ ያስጨንቃቸዋል። ገና ሸለብ እንዳደረጋቸው ብዙ አስፈሪ ነገሮችን ማየት ይጀምራሉ። ሰውነታቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ (sleep paralyzed) ይሆናሉ። አንዳንዶቹ አስፈሪ ድምፆችን በከባድ ሁኔታ ይሰማሉ። መደበኛ ሁኔታቸው ላይ እስኪመጣ ድረስ ይረበሻሉ። ብዙዎቹ መተኛት ይፈራሉ። ቅዠትና እውነታው ይደበላለቅባቸዋል።

‎ዩኒቨርሰቲ እያለን counseling አስተማሪያችን counseling ስንማር የነገረችንን እስካሁንም ቃል በቃል የማስታውሰው ነው።
‎አንድ የሷ ደንበኛ (client) እራሷን ለማረጋጋት ዮጋ ልምምድ ትጀምራለች። ከተወሰኑ ጊዜያቶች በኋላ ሴትየዋ በ ዮጋ ምክንያት ወደ ሌላኛው አለም አሁን ላይ ጉዳዩን ሳጤነው Astral projection ትገባና አዕምሮዋ ቀውስ ውስጥ ይገባል። እኔ ሴትየዋ ማታ በተኛች ቁጥር መንፈሶች ሴጣን ልጆቿንና ባለቤቷን ወደ ሲኦል እያንደፋደፈ ሲመ።ሳቸውና ሊገላቸው እየመጣ ታያለች። ስትነቃ እውነታውና ሌላኛው አለም (ቅዠቱ) ተደባልቆባት ነው ለ counseling የመጣችው።


@ourrthought
3
‎ ሴትየዋ ልጆቿን ከነዚህ ክፉ መናፍስት ለማዳን ታዲያ ልጆቿንና ባሏን እሷንም ክፉ መንፈስ ሳይቀድማት ለመቅደም ገላቸው ቀድማ ገነት ለመግባት ነው የምታስበው።

‎ ሳይኮሎጂው እንዲህ አይነት ነገሮች ሳይንሳዊ ባለመሆናቸው ለመቀበል ይቸገራል። ይንን ነገርም ሳይኮቲክ እያለ ሰዎቹን ከ እውነታው አለም የተለያዩ (Delusional) የቀን ቅዥት ያሌለን ነገር ማየት (Hallucination) እያለ የዳቦ ስም ይሰጣቸዋል። በርግጥ አሁን አሁን ይህን መንፈሳዊ አለም ማግለሉ እንደማያዋጣው ስላወቀው ሳይኮሎጂው መንፈሳዊነት (spirituality) እያለ ማካተት እየጀመረ ነው።ግን ገና ብዙ ይቀረዋል።

‎አጠቃላይ ልምምዱ ጥንት የነበረ ልምምድ ሲሆን ማንኛውም ሰው እንዲያደርገው የማይመከር ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊ ጥንካሬ ካዳበርን በኋላ መደረግ የሚገባው ነው። በዚህ ዙሪያ የተሰሩ Behind her eys እና Insidious የሚሉትን ፊልም review እሰራላቹህና የተሻለ ለመረዳት ይረዳናል።


@ourrthought
👏6🙏2
ሐሳቦቻችን
Photo
Astral Projection በ Insidious እና Behind her eys በሚሉት ፊልሞች ውስጥ እንዴት ተገለፀ የሚለውን እንመልከት።

Behind Her Eyes 6 ክፍሎች ያሉት ሲሆን Astral Projection የተገለፀበት መንገድ ትንሽ የሳሳና ብዙውን እውነት የማያሳይ ነው። በፊልሙ ውስጥ Astral Projection ነብስ ከ አካል ውስጥ በመውጣት ከዚህ በፊት በምታውቃቸው ቦታ ብቻ እየተዘዋወረች የሚከናወነውን የምትታዘብበትን የሚተርክ ነው።

ፊልሙ ላይ በህልማቸው በ ቅዥት አለም የሚቸገሩና በእንቅልፍ ልባቸው ስለሚነሱ ሰዎች (sleep walker) ያትታል። እና የ አዕምሮ ህክምና ማገገሚያ የገቡ ሁለት ካራክተሮች እናያለን። እንቅልፍ መተኛት የሚቸገሩና በህልማቸው ሁል አስፈሪ ተመሳሳይ ህልሞችን የሚያዩ ናቸው። በሂደት አንዷ ካራክተር በ Astral projection በልምምድ ህልሟን መቆጣጠርና ማዘዝ ስትችል ያሳያል። ቤቷ ተኝታ ነብሷ (ንቃተ ህሊናዋ) ከዚህ በፊት የምታውቃቸው ቦታዎች እየተዟዟረች ባሏ ቢሮ ምን እንደሚሰራ ትከታተለዋለች። አብራው ያለውን በቅዥት የሚቸገር ጓደኛዋን ስለ Astral projection ታሳየውና አብረው ልምምዱን ማድረግ ይጀምራሉ።

በፊልሙ ላይ ከ አስትራል በፊት መደረግ ስለሚገባቸው ዝግጅቶች ያሳያል። ጣትን መቁጠር ተመስጦ ማድረግና ከመተኛታችን በፊት ያለች በሰመመን የምናያት የራሳችን የህልም አለም (Lucy dreaming) አስፈላጊ መሆናቸውን ያትታል። ሌላው ስለ አስትራል የተነሳው ጉዳይ በ Astral projection ነብሳችን መሄድ የምትችለው ከዚህ በፊት በምናውቀው ቦታ ብቼ መሆኑን ያትታል። ከዚህ በፊት ያልሄድንበት ቦታ ላይ መሄድ እንደማንችል አፅንዖት ይሰጣል። በተወሰነ መልኩ የነብስ ነጠቃም እንዳለ ያትታል። ሁለት የ አዕምሮ ማገገሚያ ማዕከል ያሉ ጓደኛሞች Astral projection ካሳየችው በኋላ እየተገበሩት ነብሳቸው ከሰውነታቸው ተነጥሎ በሚገዟዟሩበት ጊዜ አካል ተቀያይረው ለመሞከር ይፈልጋሉ። በመሀል የሷ ነብስ የሱ ውስጥ የሱ ነብስ የሷ ውስጥ እንዳሉ ጓደኛዋ የሷን አካል ሲነጥቃትና እሷ የሱ አካል ውስጥ እንዳለች ሲገላት ያሳየናል። ከዛም የሱ ነብስ በሷ ነብስ ውስጥ ገብቶ ሲንቀሳቀስ ያሳያል። ፊልሙ በተወሰነ መልኩ ስለ Astral projection የሚያሳይ ሲሆን የተሳሳቱ ነገሮችንም ይናገራል። ለምሳሌ በ Astral real መጓዝ የምንችለው የምናውቀው ቦታ ብቻ ነው የሚለው ድምዳሜ ከእውነታው የራቀ ነው። አንዳንድ ቦታዎች ለማየት እንደሞከርኩት ነብስ አይታ የማታውቀው ቦታ እንደምትጓዝ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ።

Insidious በሚለው ፊልም ውስጥ

ይሄ ፊልም ስለጉዳዩ የተሻለ የሚገልፅ ሆኖ አጊኝቼዋለሁ

ፊልሙ chapter 2 chapter 3 እያለ 4 ክፍሎች ያሉት ነው።
የመጀመሪያው ክፍል ላይ ፊልሙ ሲጀምር በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አንድ ህፃን ልጃቸው ኮማ ውስጥ ሳይሆንም ሳይነቃ በእንቅልፍ አለም ውስጥ በኦክስጅን ብቻ የሚቆይበትን ሂደት ያስቃኛል። በዚህ ግራ መጋባት ወስጥ እንዳሉ ሀኪሞችም ሳይኮሎጂስቶችም መላ ሊሰጧቸው አልቻሉም።

በዚህን ጊዜ አያቱ አንድ ሴት ታናግራለች። ሴትየዋ ለሰው የማይታይ የምታይ መንፈሳዊ ጥበብ ያላት ናት። ልጁንም ካየችው በኋላ ለቤተሰቡ አንድ ነገር ነገረቻቸው ህፃኑ Astral projection መሆኑን ሳይረዳ በህልም አለም ያለ መስሎት ሳያስበው ሌላቸፈኛው አለም ውስጥ Astral plane ሄዷል። እናም ሳያውቀው ነብሱ ከሰውነቱ በጣም እየራቀ በመሄዱ ለመመለስ እንዳይችል ሆኗል። ነብስ ነጣቂ የሚባሉ (parasite) ዴሞን ክፉ ለሰው የማይታዩ መናፍስት ከዚህ በፊት ኖረው የሞቱ ሰዎች ነብሱን ከአካሉ አርቀዋት በህፃኑ ሰውነት የነሱን ነብስ ለመክተት የሚያደርጉትን ትግል ያሳያል። ህፃኑንም ለመመለስ አባቱ በ Astral ሄዶ ሲመልሰው ያትታል።

ይህች መንፈስ የምታየው የ psychic power ያላት ስለ ጉዳዩ chapter 3 በሚለው ክፍል ላይ አንድ ነገር ትናገራለች። Astral projection ሁለት አለም አለው ትላለች። አንደኛው white ጥሩ ቦታ የምንሄድበትና መንፈሳዊ ጥቅምና እውቀት የምናገኝበት መልካሙ አለም እና መልካም መናፍስት ያሉበት ሲሆን የ Black የሚባለው ክፍል ግን ነብሳችንን ከአካላችን አርቀዋት የነሱን ነብስ በሰውነታችን ለማስገባት የሚጥሩበት ሰዎችን ለማሰቃየት የሚፈልጉ ክፉ መናፍስት ያሉበት ነው።

ፊልሙ አንድ ሰው አስትራል ከማድረጉ በፊት አንድ ትልቅ አላማ ሊኖረው ይገባል የሚል መልእክት ይናገራል። አላማ ካለን ነብስ ነጣቂዎቹ የሙት መንፈሶቹን የመታገል አቅም ይኖረናል የሚል ይናገራል። እነዛን ነብስ ነጣቂዎች አለመፍራትም ዋነኛው ነገር ነው። እነሱ የሞቱ በመሆናቸው ከኛ ጋር በሀይል አይጣጣሙምና። በጥቅሉ የ አስትራልን ትክክለኛ መልክ የሚያሳይ ነው።

ሳጠቃልለው ያለምንም መንፈሳዊ ልምምድ እና ሙከራዎች እንዲህ አይነት ልምምድ የሚሞክር ሰው ትልቅ ቀውስ ውስጥ እንደሚገባ ነው። ከ YouTube ብዙ ቪዲዮ ማግኘት ትችላላቹህ በዚህ ልምምድ ውስጥ ያለፉ ሰዎች የሚያደርጉትን ትግልና ስቃይ።

አንድ ጊዜ Astral projection የሞከረ ሰው ሰውነቱ የመንፈሳዊውን አለም የሚከፍት በመሆኑ የጭለማው አለም ነብስ ነጣቂዎች እስከለተ ሞታችን ድረስ ያሳድዱናል። ብዙ ያየኋቸው ይሄን ልምምድ ያደረጉ ሰዎች ወደ ጭለማው አለም ነው የሚገቡት። ከዛም እንቅልፍ መተኛት እስካይችሉ ድረስ መንፈሳዊው አለም ከ እውነተኛው አለም ጋር ይቀላቀልባቸዋል። ለኛ ባይን የማናያቸው መናፍስት ሙታኖች ለነሱ ይታያቸዋል። የብሳችን ያኛውን አለም ከገባችበት መውጫዋ ሀይማኖታዊ መንገድ ያልታገዘ ከሆነ ውጤታማ የመሆን እድሉ ዝቅ ያለ ነው።

ፊልሙን እንድታዩት እጋብዛለሁ።

@ourrthought
🔥5👍3