ሐሳቦቻችን
981 subscribers
103 photos
4 videos
5 files
2 links
በዚ ቻናል ላይ የተለያዩ ሀሳቦቻችንን ፣ ምልከታዎቻችንን ፣ ትዝብታችንን ፣ ከተለያዩ መልኮች እያነሳን እንወያያለን!

ሀሳብና አስተያየት ካላቹ @haileabb
Download Telegram
ሐሳቦቻችን
Photo
ዛሬ አለማቀፍ የመፅሐፍ ቀን

መፅሐፍ ማንበብ ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ቅንጦት ከሆነ ነገሮች ነው የሚመደበው። በብዙ መቶ ሺዎች የሚያወጡ ውድ መጠጦች ከቀረጥ ነፃ በሚገቡባት ሀገር ላይ ወረቀት ላይ የሚጣለው ግብር ቅንጡ ከሚባሉት ግብአቶች ጋር የሚመደብ ነው።

አንድ መፅሐፍ ከጅምሩ እስከ ህትመቱ ጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ የሚጣለው ግብር የሆነ የሚያሳየው ነገር እንዳለ ግልፅ ነው። ደርግ ስልጣኑን እስኪለቅ ድረስ የነበሩን መፅሐፍት ቤቶች ላይብረሪዎች ኢህአዴግ ዘመነ መንግስት ከ 80% በላይ የሚሆኑት ፈርሰው ስጋ ቤት ጫት ቤትና ግሮሰሪ ቤት ነበር የሆኑት። ያነበበ ትውልድ ይጠይቃል የሚጠይቅ ትውልድ ደግሞ ግልፅ ነው።

አሁንም ድረስ የ አፍርካ መሪዎች አንባቢ ትውልድን አይፈልጉም። ከንባብ የተፋታ መንጋ ህዝብን እንጂ። መፅሐፍ ሻጮች ከደርግ ዘመን ጀመሮ እስከ ኢህአዴግ ዘመን ድረስ መፅሐፍ ለመሸጥ የሚያዩት ፈተና አይጣል ነው። በዚህ መንግስት ደሞ ከሁሉ የከፋውን መሳደድ እያዩ ያሉበት ነው። አንድ የ200 ገፅ መፅሐፍ በ 500 ብር የሚሸጥበት ዘመን ነው። እንዳጌታ አስረኞቹ በሚለው መፅሐፍ ላይ ስለ መፅሐፍ ሻጮችና መፅሐፍ በሀገራችን ከ አፄ ኃ/ሥላሴ እስከ ኢህአዴግ ያለውን ተግዳሮት ያስቃኘናል።

በመፅሐፉ ላይም ዳኛቸው ወርቁ ወይ ከበደ ሚካኤል ይመስሉኛል ለ ወያላዎች እቃ ተሸካሚዎችን እቃ አሸክሞ በቤቱ ከወሰዳቸው በኋላ በገንዘብ ፋንታ መፅሐፍ ይሰጧቸው ነበር። እነ ከበደ ሚካኤል የመፅሐፍ ደንበኞቻቸው በፖሊስ ሲያዙ አማላጅ ሆነው ያስፈቱ ነበር። ፅሑፉን በከበደ ሚካኤል ንግግር ዘጋዋለሁ።

ወደ መሞቻቸው አከባቢ ከአንድ ወዳጃቸው ጋር እያወሩ

"ህዝቡ ስለኛ ምን ይላል" አሉት

"ህዝብ ስለርሶ ምንም አይልም ከነ መፈጠሮ እረስቶዎታል" አላቸው

የዛነኔ በጣም ተብከንክነው
"ምናለ የኢትዮጲያ ህዝቡ ቂጡ በገጠመና አንድ ሆኖልኝ በበዳውት" አሉ ይባላል።

ሀገራችን ብዙ መፅሐፍ የፃፉ ሰዎች ተርበው የሚሞቱባት ጠያቂ የሚያጡባት ከእውቀት የተፋታች አሳዛኝ ብኩን መፃጉዕ ትመስላለች።

@ourrthought
😁8😢32
የተጣለ ፈረስ
(በእውቀቱ ስዩም)


ዘመኑ ያለፈ ጋማው የረገፈ ፤
የጎድን አጥንቱ ፤ ማበጠርያ መሳይ
ጠዋት  ህያው ፍጡር፥  ሌሊት የጅብ ሲሳይ
ከተማው መግቢያ ላይ አቧራ የሚቅም
የተጣለ ፈረስ አጋጥሞሽ ፤ አያውቅም?

“ካሁን አሁን መጥቶ፤ ይወስደኛል ነድቶ 
ከጋጣው  አግብቶ ፤ ያበላኛል እብቅ “
እያለ ጌታውን ፥ተግቶ  የሚጠብቅ
የዛሬ ተጎታች ፤ የትናንቱ ሰጋር
ተባብሮ የከዳው፤ ጊዜ ከጌታው ጋር
የቸገረው አቅም፥
የተጣለ ፈረስ ፤ አጋጥሞህ አያውቅም?

ደሞስ መች ይጠፋል?
ካንቺም ከኔም መንደር የቀድሞ ወታደር፥
በጨነቀን ጊዜ ፥“በናት ሀገር ጥሪ “
የምናጣድፈው፥
በድል ቀን ከድግስ፥ የማናሳትፈው
ከነጣቂ መዳፍ ፥ አገር  የሚያስመልስ
በገዛ አገሩ ላይ፥
መብቱ ከወፍ አንሶ፤ ጎጆ የማይቀልስ፤
  
ደሞ መች ይጠፋል፤ ከኔም ካንተም ቀየ
መንገድ ላይ ምናልፈው፥  አይተን እንዳለየ
የቀድሞ አስተማሪ
ላብ እያጣቀሰ ፊደል አስቆጣሪ
ቀሪ ሀብት ባይኖረው፤
የቀረውን ዘመን፤ እያሰላ ኗሪ፤

ቪላችንን ሞልተን፥ በሱ ጎጆ ጉድለት
ማሰብ አስተምሮን ፥ የማናስበለት
ቀኖቹን በትኖ፤ ሌሊቶቹን ዘርቶ
ናላውን፥ ጉልበቱን ፥ ውበቱን  ሰውቶ 
የሚጎተት አገር፥ ከግቡ ለማድረስ
ሺህ መንገድ አቅንቶ፥ ሺህ ገደሎች  መውረስ
ሰው ቢሉት ሰው ነው ወይ?
የተጣለ ፈረስ ::

@ourrthought
5🔥4
Maybe I'd be a bank robber. Some god damned thing. Something with flare, fire. You only had one shot. Why be a window washer?

Charles Bukowski


@ourrthought
😢132
ዛሬ የ አርበኞች ቀን ነው። ቀኑን ለየት የሚያደርገው የ ጋሽ ስብሐት ልደት መሆኑም ጭምር ነው።

አርበኝነትን ካየን አቦይ ስብሐት በኢትዮጲያ ስነ ፅሑፍ ውስጥ አርበኛ ናቸው።

ከ ስብሐት በፊት የነበረው የሀገራችን ስነ ፅሑፍ ዲስኩር ማስተላለፊያ (Art for purpose) የሚከተል ነው። ንጉሱን ለማወደስ ወይ ለመኮነን የሚጠቀሙበት እንጂ እራሱን የቻለ (Art for art sake) የሚከተል አልነበረም።

ጋሽ ስብሐት ይህን የ አማርኛ ፅነ ፅሑፍ መልክት ለማስተላለፍነት አውጥቶ ስነ ጥበብን ለ ስነ ጥበብ የተጠቀመ ለ ድህረ ዘመናዊ አፃፃፍ ዘዴ በር የከፈተ የማይደፈር የሚመስለውን የስነ ምግባር አጥር ያፈረሰ አርበኛ ነው። ከሱ በፊት ስነ ፅሑፍን ለ ስነ ፅሑፍነት የተጠቀመ ደራሲ ሀገራችን ውስጥ ያለ አይመስለኝም። ድህረ ዘመናዊ አፃፃፍን ከ ስብሐት በፊት የሞከረው ሰው አልነበረም።

ከዛ ባለፈም ብናይ ህልማዊነት (Fantasy) በ ስምንተኛው ጋጋታ በኩል አፃፃፍን ያስኮመኮመን ነው። አቦይ በፅሑፎቹ ውስጥ ለሰዎች ያለውን ርህራሄና የሞት የ እርጅና ፍርሀቶች ታዩበታላቹህ።

አቦይ ያልዳሰሰው የስነ ፅሑፍ አይነት የለም ማለት ይቀላል። ለኔ በላጮቹ አምስት ስድስት ሰባት ፣ ሌቱም አይነጋልኝና ቦርጨቅ ቀዳሚ ምርጫዎቼ ናቸው። ዛሬ አርበኝነትን ሳስብ ለ ሀገራችን የስነ ፅሑፍ እድገት ፈር ቀዳጅ የሆኑትን ስነ ፅሑፍን በራሷ ቆማ እንድትታይ ያደረጉትን አቦይን በአርበኝነት እያሰብኩ ነው። ባለበት ምችት ይበለው።

@ourrthought
8
በ 2018 ዓ.ም አሳካዋለሁ ብላቹህ 10 ወረቀት ፅሑፍ አቅዳቹህ የነበራቹህ ዘጠነኛ ወር ላይ ነን ላስታውሳቹህ ብዬ ነው።

@ourrthought
😁14🤷‍♂1
ሐሳቦቻችን
Photo
እውን ግን ስልጡን ህዝቦች ነበርን?

ይህን ጥያቄ ያዕቆብ ብርሀኑ በውቄ እንዲሁም ሌሎች አንስተውት ጥሩ ምላሽ ሰጥተውበታል።

ባንድ ወቅት መለስ ዜናዊ "የ አክሱም ስልጣኔ ለ ሐመሩ ምኑ ነው?" የሚል ሀሳብ ሰጥተው አስታውሳለሁ። ከላይ ሲታይ ንግግሩ ዋዛ የሚመስል ውስጥ ውጡን መዝማዥ ሀሳብ ነው።

የሀገራችን ስልጣኔን ስልጣኔ ለማለትስ የሚያስደፍርስ ነው? ያስብላል። ሥልጣኔያችን መራመድ ያቃተው እነ አክሱም ሀውልቱ ንቅንቅ የማይል የማይወራረስ ነው። ሥልጣኔያችን አማልክቱን ከማወደሻነት ያልዘለሉ እና ኑሮዋችንን ያልቀየሩ ነበሩ ብሎ ይሞግታል ያዕቅብ ብርሀኑ በፍም እሳት ማቃመስ የሚለው መፅሐፉ ላይ።  አክሱም ሥልጣኔ ዘመነ መንግስት ኪነ ህንፃዎቻችን ለ አማልክቱ ማወደሻነት የማይዘሉ ከዛ ከመሰለ አክሱም የኪነ ጥበብ ህንፃ ጎን በሳር ጎጆ የምንኖር ነበርን። አስቡት ሸክላ ሰሪ በገል ይበላል ማለት አሁን ነው። ያን የመሰለ ኪነ ህንፃ ህዝቡ የማይወራረሰው አማልክቱን ማወደሻነት የማይዘሉ ኪነ ህንፃዎች ነበሩ። ይሄ ሁሉም ላይ ይሰራል። ዛግዌ ፋሲለደስ ሶፍ ሁመር ሀረር ግንብ የቱም ስልጣኔ ለህዝቡ ግልጋሎት አልዋለም። ህዝቡም ጥበቡን አልተዋረሰም። ግን ለምን ይሆን? ከነዛ ከመሰሉ ጥበቦች ህዝቡ የራሱን ቤተ ህንፃ ሊገነባበት ያልቻለው በጎጆ የዳኸው? አሁንም ግራ አጋቢ ነው።

የራሳችን ቋንቋ ፅሑፍ አለን እያልን ከመሸለል ውጪ እነዚህ ፅሑፍ ቋንቋን ህዝቡ ራሱ ባዳ ነበር። በርግጥ በጥንቱ ዘመን እውቀት የትንሾች ብቻ መገልገያ ነበር (monopolies) የተደረገ ነበር። ለመፃፍ ለማንበብ ከኑሮ ትግል የዘለለ የተደላደለ ባላባት መሆን ይጠበቅበታል። በዚህ ስናየው ፊደላችን ጥበባችን ከጥቂት የቤተ እምነት ሰዎች ውጪ ቀሪው ምንነቱን የማያውቀው ነበር። እሱም ጥቅሙ ለ አማልክቱ መወደሻ እና ረቂቅነት ማወደሻ ነበር የምንጠቀመው እንጂ ኪ ጥበባችን ላይ ምንም የጅምላ አስተዋፆኦ አልነበረውም።

አሁንም ድረስ ከ 10ሺህ አመት በፊት በነበረ የእርሻ ዘዴ የሚጠቀም ከበሬው ጋር የሚለፋ ተስፋውን የሰማይ ላይቃ ተከፍቶ ዝናብ እስኪጣል የሚያደርግ የኑሮው ዘይቤ ከጥንቱ ሰው ያልተሻለ አሁንም ተራ ህመሞች እንደቅጠል የሚያረግፈው የቱ ነበር የሠለጠነው?

ዛሬም ጥያቄ ነው ለኔ እውን ሥልጡን ህዝቦች ነበርን? ወይስ ጥቂት የሠለጠኑ ሰዎች የነበሩበት ሀገር ላይ ነበርን? ሥልጣኔስ ካልተዋረሰ ህዝቡን ኑሮ ካልቀየረ ኑሮውን ባህሉን ወጉ ላይ አስተዋፆኦ ካሌለው ሥልጡን ነበርን ለማለትስ ያስደፍረን ይሆን?

@ourrthought
👍8
"ሰነፍ ሴትን ማን ሊያገኛት ይቻለዋል? ከ ዕንቁ የከበረች ናትና"

መፅሐፈ ፌሚኒስት

ም.1 ከቁ.3

@ourrthought
😁19👏4👎32
"አላህ ሲጣላ ብትር አይቆርጥም ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም" ይላሉ ወሎዬዎች።

እና አሁን ይሄ ዘበን አላህ የተጣ
.....

@ourrthought
🤔2😁1
ሐሳቦቻችን
እውን ግን ስልጡን ህዝቦች ነበርን? ይህን ጥያቄ ያዕቆብ ብርሀኑ በውቄ እንዲሁም ሌሎች አንስተውት ጥሩ ምላሽ ሰጥተውበታል። ባንድ ወቅት መለስ ዜናዊ "የ አክሱም ስልጣኔ ለ ሐመሩ ምኑ ነው?" የሚል ሀሳብ ሰጥተው አስታውሳለሁ። ከላይ ሲታይ ንግግሩ ዋዛ የሚመስል ውስጥ ውጡን መዝማዥ ሀሳብ ነው። የሀገራችን ስልጣኔን ስልጣኔ ለማለትስ የሚያስደፍርስ ነው? ያስብላል። ሥልጣኔያችን መራመድ ያቃተው እነ…
# የቅንጦት ሥልጣኔ

ሥልጣኔ ማለት ዓለትን መውቀር፣ ወርቅን ማቅለጥ ወይም ረቂቅ የሕግና የፍልስፍና መጻሕፍትን መደርደር ብቻ አይደለም። እውነተኛ ሥልጣኔ የሚለካው በቤተመንግሥቱ አጥር ስፋት ሳይሆን ያ ጥበብ ወርዶ የሰፊውን ሕዝብ ማዕድ ጤናና የዕለት ተዕለት ሕይወት መለወጥ ሲችል ብቻ ነው። የጥቂቶች ዕውቀት የብዙኃኑን ጨለማ ካላበራ ያ ነገር ሥልጣኔ ሳይሆን የአንድ ዘመን “ባህልና ቅንጦት” ተደርጎ ነው የሚወሰደው።

ጥበብ ዓለት ላይ ብቻ ተቀርቅሮ ሲቀርና ወደ ሕዝቡ ደም መዋሃድ ሲያቅተው ማኅበረሰቡ ካለፈው ዘመን ሳይቀዳ ለቀጣዩም ሳይተርፍ በነበረበት የኑሮ አዙሪት ውስጥ ተቀረቅሮ ይኖራል። ትልቁ ስብራት የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው። በጥበብ ማማ ላይ የተቀመጡት ሊቃውንትና የታችኛው ሰፊ ሕዝብ በመካከላቸው የሃሳብና የኑሮ ድልድይ ሳይኖራቸው ሲቀር ሀገር ታሪክ እንጂ ሕይወት አይኖራትም። ትናንት የነበረው ትልቅ የፈጠራ አቅም ዛሬ ላይ ተራ የትዝታ ቅርስ ሆኖ የሚቀረውም ጥበቡ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ስላልተተከለ ነው።

ስለዚህ አንድን ማኅበረሰብ “ሥልጡን” ለማለት የጥቂት ሰዎችን የላቀ አእምሮ ማየት ብቻ በቂ አይደለም። ሥልጣኔ ማለት ሰብዕናን መገንባትና ያንን ጥበብ ለትውልድ ማውረስ መቻል ነው። ጥበቡ የሕዝቡን የሕይወት ትግል ካላቀለለ ከበሽታና ከችጋር ካላዳነው እኛ ያለን የታሪክ ውበት እንጂ የሥልጣኔ እውነት ሊሆን አይችልም። የትናንቱ ትልቅነት ዛሬን መመገብ ካልቻለ ጥያቄው ዛሬም ድረስ ጥያቄ ሆኖ ይቀጥላል።

ሐኑ-ን
6/08/2018 ዓ.ም

@ourrthought
🔥6
ይህ የመጀመሪያው ክፍል የመጀመሪያው አንቀፅ ላይ ስለ ሰው ልጅ ህልውና፣ እውነት እና ሥነ ምግባራዊ ውስብስብነት በዘይቤያዊ አነጋገር በ “ግራጫ" ተወክሎ በዶ/ር ምህረት በፍልስፍና የተሰላሰለበት ነው፡፡

ሁለትዮሽ ነገሮች እንዴት በአንድ ነገር ውስጥ ተዋህደው ትርጉም እንደሚሰጡ እና አሻሚነትን እንደ ጉድለት ሳይሆን ትርጉም ያለው ነገር አድርጎ ለማሳየት የተሞከረበት ነው፡፡ ይህንንም በተለያየ መንገድ እንየው
ግራጫ ሁለትዮሽ አስተሳሰብን ውድቅ እንደማድረግ
"ግራጫ ነጭ ሚጠቁርበት እና ጥቁር የሚነጣበት ሰፊ ግዛት ነው፡፡''እነዚህ ነጭ እና ጥቁር የተባሉ ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን በምሳሌ እንያቸው
ደግነት/ ክፋት
እውነት / ውሸት
ትክክል / ስህተት
የአንድ ሰው ሁለት ጎኖች ናቸው ። እነኚህ ነገሮች በሰፊ
ግራጫ  ድብልቅ ውስጥ ያሉ የሞራል ማዕቀፎች ሲሆኑ እውነትነታቸው በፍፁምነት በወጥነት ሳይሆን በሽግግር ውስጥ የተዋቀረ ነው፡፡
አንዳንድ ድርጊቶች በራሳቸው በግልጽ አጥፊ (ጥቁር) ወይም በግልጽ አልሚ (ነጭ) ናቸው ነገር ግን አብዛኛዎቹ የሰው ልጆች ድርጊቶች ግራጫ ናቸው በተደባለቀ ዓላማ የሚነዱ በሁኔታዎች የተገደቡ ናቸው፡፡
ይህም ሰዎች ከንፁህ በጎነት ወይም ከንፁህ ክፋት እምብዛም እንዳልተሰሩ ያሳየናል።

ግራጫ ብርሃን እና ጨለማን እርስ በርስ አንደማዋሀድ
ግራጫ እንደ የብርሃን ኩርፊያ ወይም የጨለማ ፈገግታ ሆኖ ሊታይ ይችላል ወደ አንድ ጎን ዘንበል ብሎ... ግን ሁለቱንም የሚያጣምር ቀለም ነው።
የብርሃን ኩርፊያ ፦ በብርሀን ውስጥ ስጋትን እንደመመልከት ነው
የጨለማ ፈገግታ ፦ በጨለማ ውስጥ ተስፋን እንደመመልከት ነው ግራጫ ተለዋዋጭ ነው የማይንቀሳቀስ አይደለም። ዘንበል ይላል። ይቀየራል።ይህም በጎነት ሊበላሽ ፣ ክፉነት ደሞ ወደ ጥሩነት ሊሻሻል ይችላል ከሚለው ሀሳብ ጋር ይጣጣማል ። ይህም የሞራል ውስብስብነትን ያሳየናል።

ግራጫ በአውድ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ከፍልስፍና አንፃር ከነኚህ ሀሳቦች ጋር ይሄዳል
Phenomenology: meaning arises from relations not essences
Buddhist thought: identity lacks fixed self-nature
Postmodernism: truth is contextual, not absolute

ግራጫን እንደ ሰው ልጅ ሌላነት እና የተጋራ ሰብአዊነት
"የሰው ልጅ የሆነ ልዩነት እና እውነት በራሱ ሰፊ ግራጫነት ተደብቆ ተገልጧል።"

"ሌላነት" ስንል እያንዳንዱ ሰው ፈጽሞ የማይለወጥ ልዩነት ያለው መሆኑን
"እውነት" ስንል የጋራ ሰብአዊነታችን አንድ ያደርገናል ተቃርኖ የለውም አብሮ ሚኖር መሆኑን ያስገነዝበናል።
ግራጫ ፦ልዩነት ተመሳሳይነትን የማይሽርበት ቦታ ነው፡፡

እያንዳንዱ ሰው ሌላ ሰው መሆኑን መረዳት እና እያንዳንዱ ሌላ ሰው እንደኛ መሆኑን መረዳት በህይወት ላይ አንድ ግራጫ አመለካከት ነው::
እያንዳንዱ ሰው ሊካድ የማይችል ሌላ ነው። እያንዳንዱ ሰው በመሠረቱ ተመሳሳይ ነው

በአጠቃላይ ግራጫ ድክመት፤ ወጥነትን መፍራት አደለም ወይም በብዥታ ውስጥ ግራ መጋባት አይደለም፣ ነገር ግን በጥልቀት በጥበብ መኖር ማለትም በልዩነት ውስጥ ተመሳሳይነትን ተቀብሎ አምኖ በግራጫ አለም ውስጥ መኖር እንደማለት ነው፡፡ እውነታን በፍፁምነት በተሻለ ሁኔታ አንረዳውም በግራጫነት እንጂ፡፡

ግራጫ የእውነት ቀለም ነው!!


በከነዓናዊት የተከተበ

በውስጥ መስመር የመጣ ፅሑፍ። ትውልዱ ትንታግ ሆኗል።

@ourrthought
4🔥3
አለም ውርደት ለመሰላት ነገር ቸልተኛ አይደለችም።

ኩርቢት
መፅሐፍ

@ourrthought
🔥9
Attention Market

አሁን ላይ አለማችን ላይ ትልቁ አቅም ያለው ማነው? ብትሉ Data ያለው እና የሰዎችን ቀልብ ማግኘት የቻለው ነው።
አሁን ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሰዎች የትኩረት መቀነስ እና በ አንድ ነገር ላይ የመቆየት የትኩረት አቅም እየተሟጠጠ ያለበት ጊዜ ላይ ነን። ይህ ያለንበት የ ድህረ ዘመናዊነት age of post modernism era ሰዎችን ከለት ወደ ለት በ tik tok በ Facebook reel Instagram reel እያለ ሰዎች የትኩረት መጠናቸው ዝቅ እያለ አንድ ነገር ላይ ጠንካራ እውቀት እንዳይኖራቸው እያደረገ ያለበት ጊዜ ነው።

በ psychology ADHD የሚባል ህመም አለ። ወደ አማርኛ ስታመጡት የመቅበጥበጥ ችግር ልትሉት ትችላላቹህ። Attention Deficit Hyperactive Disorder የሚባል የ አዕምሮ ችግር አለ። አንድ ነገር ላይ ለ አንድ ደቂቃ ትኩረት የማድረግ አቅም የላቸውም። እዚህ ጋር ስትፈልጓቸው እዛ ጋር እዛ ስትሄዱ እዚህ የምታገኟቸው ናቸው። አሁን ላይ የ አጫጭር ምስሎች መብዛት ሰዎችን መጠኑ ዝቅ ወዳለ ADHD ችግር የሚገፋ ነው።

የነዚህ platform አሰራር cheap dopamine ማለትም በትንሽ ጊዜ ውስጥ የሚገኝ የ ደስታ ሆርሞን አዕምሮ እንዲለቅ የሚያደርጉ ናቸው። ያ ማለት ሰዎች ባጭር ጊዜ ቶሎ ደስታ የመፈለግ ነገር ውስጥ ይከታቸዋል። ለረጅም ደቂቃ አንድ ነገር ላይ ጊዜ አጥፍቶ ጥልቅ እውቀት ከማግኘት ይልቅ ከላይ ከላይ የሆነ ነገር በማየት ቶሎ ቶሎ የደስታ ስሜት ማግኘት እንደማለት ነው። ያ ደሞ አንድን ነገር ለረጅም ጊዜ ከማየት ይልቅ ቶሎ ቶሎ ባጫጭር ቪዲዮ መደሰት ማለት ነው።

Operant conditioning የሚባል የ Behavioral theory ላይ B.F Skinner የተባለ psychologist ስለ ሰዎች ባህሪ ምን shape ያደርጋቸዋል የሚለውን ሲያጠና አንድ ሰው አንድን ነገር ለማስተማር ወይም ለመቅጣት Reinforcement and punishment አስፈላጊ መሆናቸውን በሱ theory ላይ የታየ ነው። ይሄ ማለት ጥሩ ስነ ምግርባር ስታሳዩ በድርጊታቹህ እንድትቀጥሉ Reinforce ትደረጋላቹህ። ለምሳሌ ጥሩ ስራ ስትሰራ ሽልማት አለህ እንደማለት ነው። መጥፎ ስትሰራ ትቀጣለህ punishment አለው። በዚህ ሂደት አንተን ባህሪህን ቅርፅ ያሲዙታል ማለት ነው።

እነ tik tok, Facebook, Instagram የመሳሰሉት platform ሲሰሩ እንደዚህ አይነት theory ይጠናሉ። tik tok ላይ ለረጅም ጊዜ የሚያቆይህ ነገር በ psychologist እንዲሁም በብዙ ጥናት በተጠና ጥናት ነው። አንተን ባህሪህን ያለህበትን ስሜት ከምታየው ቪዲዮ በሰበሰቡት data የሚያውቁህ በመሆኑ ረጅም ጊዜ እንድትቆይ reinforcement ይሰጡሀል። ልክ ሲሰለችህ አከባቢ በጣም የምትወደው አይነት ቪዲዮ ይለቁልሀል ያ ርዝማኔህን ያቆየዋል ማለት ነው።

ታዲያ ካስተዋልክ የምትወደውን ነገር ብቻ አይለቁልህም ለምን ብትል satiation የሚባል ነገር አለ። Satiation ማለት የምትወደውን ነገር ብቻ ቢያደርጉልህ ከመጠን በላይ ሆኖብህ ማር ሲበዛ ይመራል እንዲሉ Over reinforce አይሰጡህም። የማትወደውን ነገር ቀልቀል ያደርጉልሀል። በዛ ቆይታህ ይራዘማል ማለት ነው።

ትልቁ የዘመኑ ችግር ሰዎችን እንዴት manipulate እናድርጋቸው ሳይሆን አሁን ትልቁ ችግር ከ 1 ደቂቃ በታች በማይሆን ጊዜ ውስጥ በዚህ የሰዎች ስልቹነት በገነነበት ዘመን እንዴት ትኩረታቸውን ማግኘት እንችላለን የሚለው ነው። ያንተን ትኩረት Attention ያገኘ ሰዎ አሸናፊ ነው። social media ያለው ጦርነት እንዴት ትኩረት ላግኝ የሚለው ነው። ትኩረት ያገኘ ሰው በ አንድ ቀን ይከብራል። እራስህን ለማሳወቅ ከ 30 ሰከንድ በታች ነው ያለህ በዛች ጠባብ ጊዜ ውስጥ ምን ባደርግ ነው ትኩረት የማገኘው? የሚለውን ካላሰብክ ካለዛ 1000 ሺህ ቪዲዮም ደርድረህ ማንም ሳያውቅህ ዘመንህን ስትለፋ ትኖራለህ።

ይቀጥላል...

@ourrthought
👍111
ሐሳቦቻችን
Photo
Dissociative Identity Disorder

አለም ላይ ምንም ነገር ቢረቅ እንደ አዕምሮ ግን የሚያስገርም ረቂቅ ነገር የለም። ሰዎች አሁን የደረስንበት የተራቀቀ ደረጃ ድንቅ ቢሆንም ስለ አዕምሮ ግን ያወቅነው ጥቂት ነው። የሁሉም ሰዎ አዕምሮ የየራሱ ባህሪና ነገሮችን የሚመዝንበት የራሱ ባህሪው አስገራሚ ነው። ይበልጥ አግራሞቴን የሚያበዛው አንዳንድ የ አዕምሮ ህመም ችግሮች ሳስተውል ነው። ስለ አዕምሮ ከሚያስገርሙኝ አንዱ DID (Dissociative Identity Disorder) ነው።

የአዕምሮ ህመም ወሰብሰብ የሚያደርገው ነገር የ አንዱ ህመም የዳነበት ለሌላ ሰው የማይጠቅም መሆኑ ነው። ለምሳሌ የ ጉንፋን ህመም ቢያመን በጉንፋን መድሀኒት ሁሉም መዳን ይችላል። ግን አንድ ድባቴ ህመም ያለበትን ሰው ከሌላው ድባቴ ከያዘው ጋር በተመሳሳይ መንገድ የማናድነው መሆኑ ነው። እያንዳንዱ ሰው በራሱ መንገድ ክትትልና ህክምና የሚፈልግ መሆኑ የ አዕምሮ ህመም ትንሽ ወሰብሰብ ያደርገዋል።

DID የበፊት ስሙ Multiple Identity Disorder ይባል ነበር። ከብዙ ምርም በኋላ ግን ወደ DID ተቀይሯል። Multiple Identity የተባለበት ምክንያት በፊት በዚህ ህመም የተጠቁ ሰዎች ብዙ የተለያየ ማንነት አላቸው ተብሎ ስለሚታሰብ ነበር። ያ ማንነታቸው ግን ከ Trauma እንደሚነሳ አያውቁትም ነበር። DID እስካሁን በምርምር በሂደት ላይ ያለ የ አዕምሮ ህመም አይነት ነው።

ህመሙ የሚከሰተው ብዙ ጊዜ በልጅነት በሚከሰት Trauma ችግር ነው። ከትራውማም ከባድ post traumatic disorder የሚያመዝን ነው። ግለሰቡ በጊዜው እራሱን ከዛ ነገር መከላከል የማይችልበት ሁኔታ ሲሆን አዕምሮ ከ አዕቅሙ በላይ በመሆኑ እራሱን ለመከላከል የጊዜውን ክስተት የራሱን የቻለ ሁኔታውን የሚያስቀምጥበት የትዝታ ማህደር ያበጃል ማለት ነው። ያ የትዝታ ማህደር ህፃኑን ከጥቃቱ ለማዳንና (ለመበቀል) የራሱን የሆኑ ሂደት እያበጀ ከሰውየው እውቅና ውጪ ድርጊቱ ይከናወናል ማለት ነው።
ያ ማለት አንድ ህፃን ልጅ በልጅነቷ ብትደፈር አዕምሮዋ መቋቋም የሚከብደው በመሆኑ ጉዳዩን ህፃኗን ከ ጥቃት ለመጠበቅ የተደፈረችበትን አጋጣሚ ወደ ድብቁ የ አዕምሮ ክፍል (unconscious mind) ይደብቀዋል ማለት ነው። አስቀምጦት ብቻም አያበቃም የራሱን የሆነ እድሜ ስም እና የቀለም ስያሜ ለብቻው ይሰጠዋል። አዕምሮ ይሄን በሚያደርግበት ሂደት ዋና ግለሰቧ እውቅና የላትም። ያኔ ለብቻው በ ኢንቁ (unconscious mind) የተቀመጠው ያ ስብዕና አብሮ እያደገ የራሱን ስብዕና እያጎለበተ ይሄዳል። በዚህም አያበቃም ልክ ይህች ህፃን ትልቅ ሰው ሆና እሷ በ እንቅልፍ ልብ በምትሆንበት ጊዜ ይህ ክፍል ይነቃና በቀሉን ይፈፅማል ማለት ነው።

ታዲያ አንድ በዚህ ዲስኦርደር የተጠቃ ሰው ከ 10 እስከ 15 ድብቅ ማንነቶች አንድ ሰው ላይ የመከሰት እድላቸው ሰፊ ነው። አልፎ አልፎ ከ 100 በላይ ድብቅ ማንነቶች በአዕምሮ ውስጥ ሊኖር ይችላል ከሰውየው ግንዛቤ ውጪ ማለት ነው። እያንዳንዱ ማንነቶች እራሳቸውን የቻሉ ማንነች ያላቸውና የተለያየ ፍላጎትና እድሜ ያላቸው ናቸው። ግን ዝም ብሎ ይሄ ድብቅ ስብዕና አይገለጥም። እያንዳንዱ ለመገለጥ ከነሱ ጋር የተገናኘ ትስስር ያለው ክስተት መፈጠር አለበት። ለምሳሌ ቅድም ባልኩት መሠረት ህፃን ሆና የደፈራት ሰውየ ቀይ ጃኬት ያደረገና ፊቱ ጥቁር ከሆነ ያቺ ልጅ ትልቅ ሆና እሱን የሚመስል ቀይ ጃኬት ያደረገ ጥቁር ሰው ባየች ቅፅበት አዕምሮዋ ውስጥ የተደበቀው የራሷ ማንነት እራሱን ለመከላከል ይገለጣል ማለት ነው። አንዱ ስብዕና ሲገለጥ ሰውየው ምንም አያስታውስም።

DID የሚከሰተው አዕምሮን ከማይችለው በላይ አደጋ ሲደርስበት ሰውየውን ከጉዳት ለመጠበቅ በ ኢ ንቁ የትውስታ ክፍሉ ይከተዋል። ለዛም ነው በዚህ ህመም የሚጠቁ ሰዎችን ህክምና ለመስጠት አስቸጋሪ የሚያደርገው አንደኛው ስብዕና ስለሌላኛው የማያውቅ በመሆኑ ግለሰቡም የማያውቅ በመሆኑ በጣም ትልቅ ፈተና ያደርገዋል። ይህን ህመም በሚገባ የሚያሳይ ፊልም በሀገራችን ማንያዘዋል የሚለው ፊልም ሲሆን ከ ውጪ ደሞ split የተሰኘው ፊልም ነው። split የሚለው ፊልም ገፀ ባህሪው 6 ደባል ስብዕናዎች ያሉት ሲሆን እያንዳንዳቸው የራሳቸው ባህሪ ማንነትና ዕድሜ ያላቸው ናቸው።

ከመፅሐፍ ደሞ የ ሲድኒ ሼልደን Tell me your dreams የሚለውና የ አዘርግ በኢያሪኮ ከተማ or በኢያሪኮ ጩኸት በዛ የሚለው የማውቃቸው ናቸው።

Tell me your dreams የሚለው መፅሐፉ የሚያጠነጥነው በ DID (ዲሶሴቴቪ አይደንቲቲ ዲስኦርደር) ስላጠቃት ገፀ ባህሪ ነው።
ዋና ገፀ ባህሪዋ በላዩዋ ላይ ደባል ስብዕናዎች ያሏት ስትሆን ሶስት ደባል ስብዕናዎች በውስጧ አሏት። ታዲያ እነዚህ ስብዕናዎች በየተራ ነው የሚገለጡባት ለምሳሌ አንደኛዋ ስብዕና አርት ትወዳለች አንደኛዋ የቢሮ ሰራተኛ ናት አንደኛዋ ጨካኝና ቀበጥ ናት። ታዲያ እነዚህ ስብዕናዎች በ አንድ ጊዜ አይገለጡም በየተራ ነው የሚገለጡባት። ለምሳሌ አርት የምቶደው ስብዕና ከተገለጠች ቢያን ለ ሳምንት በዛ ስብዕና ትቆያለች ግን እሷ ይሄ መከሰቱን አታውቅም።

በዚህ መፅሐፍም ይሄን ነው የገለፀልን ከሦስቱ ስብዕና አንደኛዋ ስብዕናዋ ስትገለጥ ጨካኝ በመሆኗ ሰዎችን እያደነች የምትገድልበትን ሂደት በመጨረሻም በፍርድ ቤት ውሳኔ ነፃ እስክትለቀቅ ድረስ ያለውን ሂደት ያሳያል። ሲድኒ ይሄን መፅሐፍ ሲፅፈው ብዙ የፍርድ ቤት ሂደትን በአካል ተገኝቷል።

አንዳንድ ነገር ለመግለፅ ትንሽ አስቸጋሪ በመሆናቸው ያልተገለጠላቹህ ሀሳብ ካለ በ ሀሳብ መስጫ ልትጠይቁ ትችላላቹህ።

@ourrthought
👏10🔥21👍1
ነገረ ቦለጢቃ

የዘንድሮ ምርጫ የከሸፈ ይመስላቹሀል?

በርግጥ መልሳቹህ የምን ምርጫ ነው? ማን ተፎካካሪ ኖሮ ነው የምንመርጠው? የመሳሰሉ ጥያቄዎች ሊመጣባቹህ እንደሚችል ግልፅ ነው። የዘንድሮ ምርጫ ግን እንደኔ አልከሸፍም። እንዴት? ብትሉ ምርጫ አላማው የዲሞክራሲን መኖር ህዝቡ የሚተገብርበት ይግዛኝ የሚለውን እሳቤ (Ideology) የሚመርጥበት ነው።

የዘንድሮ ምርጫ ብቻ ሳይሆን የ አፍሪካ አጠቃላይ የምርጫ ሂደት ትክክለኛ ዲሞክራሲ እንደሌለ የሚታይበት ትክክለኛ የህዝቡንና የመሪውን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። በዘንድሮ የኛ ምርጫም ህዝቡ በምርጫ ተስፋ የቆረጠ መሆኑን እና ትክክለኛ የምርጫ ስርአትና ተፎካካሪ አካላት እንደሌሉ የታየበት ነው። ብንመርጠም ይሄው መንግስት ባንመርጥም ራሱ መሆኑን ያሳየን ነው። በዚህ ትንታኔ ካየነው ዲሞክራሲና ፍትሀዊ የሆነ የመንግስት ስርአት አለመኖሩን አሳይቶናል እንዲሁም የህዝቡን በምርጫ ተስፋ መቁረጥ እና ምርጫው አልከሸፈም ማለት ይቻላል። እውነታውን ማየት ከቻልንበት ዲሞክራሲ አለመኖሩን ካሳየን ትልቅ ቁም ነገር ነው።

ፅሑፉን በአንድ ቀልድ ልዝጋው።
የ አሜሪካ የ ቻይናና የ ኢትዮጵያ መሪዎች ተገናኝተው ስለ ምርጫ ስርአት እየተነጋገሩ ነው። የ ቻይናው መሪ እኛ ሀገር ከተመረጠ ከ ሳምንት በኋላ ማን እንደተመረጠ ወዲያው ቆጥረን በሀቀኝነት እናሳውቃለን። አለ ቀጥሎ የ አሜሪካው መሪ እኛ ሀገር ከናንተ ይፈጥናል። በተመረጠ በንጋታው ቆጥረን እናሳውቃለን አለ። ሰዎቹ ተደመሙ በቅልጥፍናቸው። ይሄኔ የሀገራችን መሪ ብድግ አለና ይሄ ምኑ ያስገርማል ታዲያ? እኛ ሀገር ከመመረጡ ከ አንድ ሳምንት ቀድመን ነው የምናውቀው አለ። ይባላል። ይህቻትና ዲሞክራሲ። በቅልጥፍናችን መደመም ነው።

@ourrthought
😁225
ከባርነት በላይ ነፃነት ለሰው ልጅ ትልቅ የሀላፊነት ሸክም አለው።

አንድ ባሪያ በባርነት ዘመኑ ውሎው ምግቡ የሚሰራው የሚለብሰው በሙሉ የተወሰነለት በመሆኑ የተለየ የሚያስጨንቀው ነገር የለበትም። ይሄን ባሪያ ከባርነት አውጥታቹ ነፃ ብታደርጉት ግን ወዴት መሄድ እንዳለበት ፣ ምን መስራት እንዳለበት ፣ በትርፍ ጊዜው ምን እንደሚያደርግ ፣ ስለሚለብሰው ፣ ስለሚጠጣው ስለ እያንዳንዱ ነገሩ የማሰብና የመጨነቅ ሀላፊነትም አብሮ ይመጣበታል።

ከመፅሐፍ ቅዱስ ዘፍጥረትን ብትመለከቱ ስለዚህ ሐሳብ በጥሩ ሁኔታ ዬብራራል። ልክ አዳምን ፈጣሪ እንደፈጠረው ሙሉ ለሙሉ ለነፃነቱ ተላልፎ እንዲሰጥና ዝም ብሎ የ አልባሌ ውሎ እንዲውል አላደረገውም። ይልቅስ አዳምን የ ገነትን ዛፎች እንዲንከባከብና ፣ ለእንስሳቱ ስም እንዲሰጥ በመሳሰሉ ነገሮች እንዲጠመድ ነበር ያደረገው።

ሰው ያለምንም ሀላፊነት ሙሉ ለሙሉ ዝም ብሎ ነፃ ሆኖ ቢኖር ግራ መጋባትና ጭንቀት ውስጥ ይገባል። ሰውን በድብርት ለመግደል psychological killing ከፈለክ ዝም ብለህ እየቀለብከው ያለምንም ሀላፊነት እና ስራ ልቀቀው ያኔ መን እንደሚያደርግና መስራት እነዳለበት ምን ሀላፊነት መውሰድ እንዳለበት ባለማወቁ በራሱ ፍላጎቶች ተጠልፎ ይወድቃል።

"ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል"
"ስራ ከምፈታ ልጄን ላፋታ"

@ourrthought
12👍1
Asa - Jailer
naïve
Im in chain you're in chains too
I wear uniform and you wear uniform too
Im a prisoner,
You're a prisoner too Mr Jailer

I have fears you have fears too
I will die, you sef go die too
Life is beautiful
Don't you think so too Mr Jailer

ሸጋ ሙዚንቃ

@ourrthought
👏21🔥1
³⁴ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።

ማቴ ፦ 6
@ourrthought
11😢4
"
He who has a why to live can bear almost any how."
"Wer ein Warum zu leben hat, erträgt fast jedes Wie."

Friedrich Nietzsche


"Why" is the only real source of power.
without it, you are powerless!

Our only hope, our only peace, is to understand it, to understand the why.

Matrix movie

@ourrthought
18🔥4