ጠብታ....
አሉ አንድ አንድ ሰዎች፤ በተስፋ መቁረጥ ከትቢያ ወድቀን ለመነሳት መፍጨርጨር ሲከብደን በቃላቸው የሚያድሱን። አሉ አንድ አንድ ሰዎች፤ ተካድን፣ የሚረዳ'ን አጣን፣ ዝምድና ግንኙነት ጓደኝነት ምንም አይሰራልንም ብለን እራሳችንን መሸከፍ ስንጀምር ከሩቅ ሆነው ምንም በማለት ውስጥ አለሁ የሚሉን። አሉ ደግሞ፤ በዚህ የሰቀቀን ባህር ውስጥ ስንዋዥቅ ሰልጥቆ የበላን የብቸኝነት፣ ሰውነት ላይ ተስፋ የመቁረጥ አሳ ነባሪ ባህርዳርቻው ላይ እስኪተፋን ዮናስነታችንን አስጠብቀው የሚያቆዩልን ሰዎች አሉ።
ተፈጥሮ ከውልደት እስከ ሞት በስቃይ ማዕበል ስታንገላታን ቆይታ የህይወታችንን መልህቅ ወደ ባህሩ እንዳንለቀው የምታባብልበት ሰዎች አሏት፤ ለጭካኔዋ ማስታገሻ ይመስል ከአንድ ጥግ አኑራ ከዘላለም ዝምታ እኛን የምታቅብበት አንድ አንድ ጠብታ ሰዎች አሉ።
@ourrthought

ቺርስ ለነዛ ሰዎች!
@ourrthought
💊5👌3❤2🫡2
አለም መቶ ጊዜ ቢታጠቡባት አንድ ጊዜ የማይነፁባት ሥፍራ ናት። ምን ጻድቅ ቢኾኑ ተፈጥሮ ነውና መፍራት ፣ መሰሰት ፣ አሳልፎ መስጠት ፣ መጥላት ፣ መስጋት ፣ ክህደት... መከላከል በማንችላቸው መንገዶች መጥተው ሕይወታችን ውስጥ ይከናወናሉ።
የሰው ልጅ ሕይወት ዝንቁ ብዙ ነው። ዕውን ዕውነትን ይወክላል ፤ ህልም ደግሞ ሀሰትን ፤ ዐልፎ አልፎ ሕልምና ቅዠት የዕውነት መፍቻ እንደሚኾነው ኹሉ እንዲሁ ሐሰት የዕውነት ማተራጎሚያ ይኾናል።
ፈሪሳ
አለማየሁ ገላጋይ
@ourrthought
የሰው ልጅ ሕይወት ዝንቁ ብዙ ነው። ዕውን ዕውነትን ይወክላል ፤ ህልም ደግሞ ሀሰትን ፤ ዐልፎ አልፎ ሕልምና ቅዠት የዕውነት መፍቻ እንደሚኾነው ኹሉ እንዲሁ ሐሰት የዕውነት ማተራጎሚያ ይኾናል።
ፈሪሳ
አለማየሁ ገላጋይ
@ourrthought
👍8🔥4❤1
"ስለ ህይወት ሃያልነት ማውራት ከፈለግን ቀድመን ስለሞት እናውራ"
የሞት መኖር ነው ህይወታችንን አጣፍጠን እንድንኖር የሚያደርገን። እንደው ማን ይሙትና 'እሳት' አቅርበው ባያስፈራሩን ኖሮ ህይወት ለመኖር መች አጭር ሆነችና?! ሞት ለህይወት ባለውለታዋ ነው፤ ለመኖር ስስትን ከየት አገኘንና?! እንጂማ እኮ ህይወት የተፈጠረችው እኛን በስቃይ ለመቅጫነት ነበር፤ ለነገ በማሰብ ስቃይ ውስጥ፣ ሰው ምን ይለኛል በሚል ፍርሃት ውስጥ እንድንማቅቅ ለማድረግ። ይመስገን! ‘ህይወት ወደ መቀመቀ ስታወርደን ሞት ነፃ አወጣን።'
የሞት መመጫውን ባለማወቃችን ለነገ ቆጥበን ለቁርስ ያስቀመጥነውን፤ ዛሬ ከመሸ፣ ከዋክብት ጨረቃን አጅበው በሚደንሱበት በዚህች ምሽት፤ ወይ ወይዘሮ አልታዬ ቤት፣ ወይንም ደግሞ ከደንዳሳዋ ከበቡሽ አረቄ ቤት አረቄያችንን እየተጎነጨን፤ ህይወት ቀኑን ሙሉ ያሳየችንን ፍዳ አረቄውን በጥሩ ሲጋራ አጅበን “አሹት!” ይብላኝ እንጂ ላንቺ” እንላታለን።ደግሞም ሞት ህይወትን በስስት እንድንኖራት አድርጎናል አላልንም? ህይወት ብትከፋም ነገ ሞት አባታችን መጥቶ ሊወስደን ስለሚችል፤ ዛሬን!... ዛሬን በጨረቃ ታጅበን፣ ቆንጆ አረቄ ጠጥተን፣ አለፍ ካለም ሞትን ማምለጥ ባንችል በእርካታ ለመቀበል ከአረጋሽ ጭን መሃል እንፋሎት ስንስብ እናድራለን።

ሞት ቀርቶ ነገም ዳግም ህይወት ብትመጣስ ከሆነ ነገሩ፤ ሞት ህይወትን በስስት መኖር አስተምሮን አይደል? እንግዲያውስ...
❤5👍1
የት ነኝ?
ህይወቴ ልክ እንደ ዘጠኙ ሃዋርያት ይመስለኛል...ይሁዳና ጴጥሮስ በክህደት ሲታወሱ ፣ ወንጌላዊ ዩሐንስ በታማኝነቱ እስከ መስቀሉ ሲከተለው!
የተቀሩት ሐዋርያት መኖር አለመኖራቸው የተረሱ ነበሩ! በክፉም ይሁን በመልካም ያለመታወስ ኖረው እዳልኖሩ ከመዘንጋት እንደይሁዳ በክፉ መነሳት አይሻልምን?
ሞቴን እስክመኝ የተረሳው ነበርኩ ፣ መኖሬና አለመኖሬ በቁም የተዘነጋ!
@ourrthought
❤9
ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን
ምጥ አታስተምርም ልጅ እናቷን! "
" ወይድ አታስቆጥረኝ ዘር አጥንቴን
እኔ አውቀው የለም ወይ ማንነቴን! "
ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራየን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማየን!
@ourrthought
ምጥ አታስተምርም ልጅ እናቷን! "
" ወይድ አታስቆጥረኝ ዘር አጥንቴን
እኔ አውቀው የለም ወይ ማንነቴን! "
ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራየን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማየን!
@ourrthought
❤11
ሐሳቦቻችን
ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን ምጥ አታስተምርም ልጅ እናቷን! " " ወይድ አታስቆጥረኝ ዘር አጥንቴን እኔ አውቀው የለም ወይ ማንነቴን! " ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራየን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማየን! @ourrthought
ሁላችንም አንድ የምንጠብቀው ነገር ያለ ይመስለኛል። ከዚህ ዘመን ነፃ የሚያወጣን ወደ ከነዓናዊቷ በልባችን ወደሳልናት ኢትዮጲያ የሚወስደን መሲህ ፍለጋ በልባችን የምንንከራተት የሆንን ይመስላል።
ቴዲ አንደበታችን እስኪመስል ድረስ በልባችን የምናስባትን ኢትዮጲያን የሚያዜምልን የነብሳችን ሰው ነው። የጋራ ደመነብሳችንን ከተበታተነበት እየሰበሰበ የሚሞዝቅልን ስለ ኢትዮጲያችን በዜማዎቹ በግጥሞቹ የሚሰብከንም ጭምር ነው። ሁላችንም አሁን ላይ ደፍረን ማውጣት የከበደችን ስለ ሀገራችን የሚሰማን ባዶ ተስፋ አውጥቶ የሚነግረን የምንጠብቅ ይመስል ስለ ሀገራችን መርዶ የመጠበቅ ያክል በልባችን የምናስበው ትካዜን የሚነግረን የምንጠብቅ ነን እሱንም ቴዲ በዘፈኖቹ የነገረን ይመስለኛል። እኛም መርዶዋችንን የተቀበልን ይመስላል።
ባንድ ወቅት አውጉቸው እና አንድ የመፅሐፍ ሻጭ በደርግ ዘመን ብቻቸውን መስቀል አደባባይ ሰልፍ ወጥተው ነበር። ሀገራቸው ያለችበት የህዝቧ ኑሮ አሳስቧቸው ለውጥ ባያመጡም ለ አገዛዙ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለፅ ነበር የወጡት።
ቴዴ አፍሮ አሁን ላይ እንደነሱ ብቻውን ሰልፍ የወጣ ለዚህች ኢትዮጲያ የሚተክዝና የሚብሰለሰል ነው። እኛ በልባችን የምናዜመውን ሀዘን እሱ ብቻውን አደባባይ ይዞ የሚወጣ አጋዥ ያጣ ብቸኛ ሰው ይመስለኛል። ለውጥ ባያመጣም ያለውን ተቃውሞ ማሳየትን የማይፈራ ለኢትዮጵያዊነት የሚታገል የነብሳችን ሰው ነው።
@ourrthought
❤13
ሐሳቦቻችን
Photo
ዛሬ አለማቀፍ የመፅሐፍ ቀን
ወደ መሞቻቸው አከባቢ ከአንድ ወዳጃቸው ጋር እያወሩ
"ህዝቡ ስለኛ ምን ይላል" አሉት
"ህዝብ ስለርሶ ምንም አይልም ከነ መፈጠሮ እረስቶዎታል" አላቸው
የዛነኔ በጣም ተብከንክነው
"ምናለ የኢትዮጲያ ህዝቡ ቂጡ በገጠመና አንድ ሆኖልኝ በበዳውት" አሉ ይባላል።
@ourrthought
መፅሐፍ ማንበብ ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ቅንጦት ከሆነ ነገሮች ነው የሚመደበው። በብዙ መቶ ሺዎች የሚያወጡ ውድ መጠጦች ከቀረጥ ነፃ በሚገቡባት ሀገር ላይ ወረቀት ላይ የሚጣለው ግብር ቅንጡ ከሚባሉት ግብአቶች ጋር የሚመደብ ነው።
አንድ መፅሐፍ ከጅምሩ እስከ ህትመቱ ጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ የሚጣለው ግብር የሆነ የሚያሳየው ነገር እንዳለ ግልፅ ነው። ደርግ ስልጣኑን እስኪለቅ ድረስ የነበሩን መፅሐፍት ቤቶች ላይብረሪዎች ኢህአዴግ ዘመነ መንግስት ከ 80% በላይ የሚሆኑት ፈርሰው ስጋ ቤት ጫት ቤትና ግሮሰሪ ቤት ነበር የሆኑት። ያነበበ ትውልድ ይጠይቃል የሚጠይቅ ትውልድ ደግሞ ግልፅ ነው።
አሁንም ድረስ የ አፍርካ መሪዎች አንባቢ ትውልድን አይፈልጉም። ከንባብ የተፋታ መንጋ ህዝብን እንጂ። መፅሐፍ ሻጮች ከደርግ ዘመን ጀመሮ እስከ ኢህአዴግ ዘመን ድረስ መፅሐፍ ለመሸጥ የሚያዩት ፈተና አይጣል ነው። በዚህ መንግስት ደሞ ከሁሉ የከፋውን መሳደድ እያዩ ያሉበት ነው። አንድ የ200 ገፅ መፅሐፍ በ 500 ብር የሚሸጥበት ዘመን ነው። እንዳጌታ አስረኞቹ በሚለው መፅሐፍ ላይ ስለ መፅሐፍ ሻጮችና መፅሐፍ በሀገራችን ከ አፄ ኃ/ሥላሴ እስከ ኢህአዴግ ያለውን ተግዳሮት ያስቃኘናል።
በመፅሐፉ ላይም ዳኛቸው ወርቁ ወይ ከበደ ሚካኤል ይመስሉኛል ለ ወያላዎች እቃ ተሸካሚዎችን እቃ አሸክሞ በቤቱ ከወሰዳቸው በኋላ በገንዘብ ፋንታ መፅሐፍ ይሰጧቸው ነበር። እነ ከበደ ሚካኤል የመፅሐፍ ደንበኞቻቸው በፖሊስ ሲያዙ አማላጅ ሆነው ያስፈቱ ነበር። ፅሑፉን በከበደ ሚካኤል ንግግር ዘጋዋለሁ።
ወደ መሞቻቸው አከባቢ ከአንድ ወዳጃቸው ጋር እያወሩ
"ህዝቡ ስለኛ ምን ይላል" አሉት
"ህዝብ ስለርሶ ምንም አይልም ከነ መፈጠሮ እረስቶዎታል" አላቸው
የዛነኔ በጣም ተብከንክነው
"ምናለ የኢትዮጲያ ህዝቡ ቂጡ በገጠመና አንድ ሆኖልኝ በበዳውት" አሉ ይባላል።
ሀገራችን ብዙ መፅሐፍ የፃፉ ሰዎች ተርበው የሚሞቱባት ጠያቂ የሚያጡባት ከእውቀት የተፋታች አሳዛኝ ብኩን መፃጉዕ ትመስላለች።
@ourrthought
😁8😢3❤2
የተጣለ ፈረስ
(በእውቀቱ ስዩም)
ዘመኑ ያለፈ ጋማው የረገፈ ፤
የጎድን አጥንቱ ፤ ማበጠርያ መሳይ
ጠዋት ህያው ፍጡር፥ ሌሊት የጅብ ሲሳይ
ከተማው መግቢያ ላይ አቧራ የሚቅም
የተጣለ ፈረስ አጋጥሞሽ ፤ አያውቅም?
“ካሁን አሁን መጥቶ፤ ይወስደኛል ነድቶ
ከጋጣው አግብቶ ፤ ያበላኛል እብቅ “
እያለ ጌታውን ፥ተግቶ የሚጠብቅ
የዛሬ ተጎታች ፤ የትናንቱ ሰጋር
ተባብሮ የከዳው፤ ጊዜ ከጌታው ጋር
የቸገረው አቅም፥
የተጣለ ፈረስ ፤ አጋጥሞህ አያውቅም?
ደሞስ መች ይጠፋል?
ካንቺም ከኔም መንደር የቀድሞ ወታደር፥
በጨነቀን ጊዜ ፥“በናት ሀገር ጥሪ “
የምናጣድፈው፥
በድል ቀን ከድግስ፥ የማናሳትፈው
ከነጣቂ መዳፍ ፥ አገር የሚያስመልስ
በገዛ አገሩ ላይ፥
መብቱ ከወፍ አንሶ፤ ጎጆ የማይቀልስ፤
ደሞ መች ይጠፋል፤ ከኔም ካንተም ቀየ
መንገድ ላይ ምናልፈው፥ አይተን እንዳለየ
የቀድሞ አስተማሪ
ላብ እያጣቀሰ ፊደል አስቆጣሪ
ቀሪ ሀብት ባይኖረው፤
የቀረውን ዘመን፤ እያሰላ ኗሪ፤
ቪላችንን ሞልተን፥ በሱ ጎጆ ጉድለት
ማሰብ አስተምሮን ፥ የማናስበለት
ቀኖቹን በትኖ፤ ሌሊቶቹን ዘርቶ
ናላውን፥ ጉልበቱን ፥ ውበቱን ሰውቶ
የሚጎተት አገር፥ ከግቡ ለማድረስ
ሺህ መንገድ አቅንቶ፥ ሺህ ገደሎች መውረስ
ሰው ቢሉት ሰው ነው ወይ?
የተጣለ ፈረስ ::
@ourrthought
(በእውቀቱ ስዩም)
ዘመኑ ያለፈ ጋማው የረገፈ ፤
የጎድን አጥንቱ ፤ ማበጠርያ መሳይ
ጠዋት ህያው ፍጡር፥ ሌሊት የጅብ ሲሳይ
ከተማው መግቢያ ላይ አቧራ የሚቅም
የተጣለ ፈረስ አጋጥሞሽ ፤ አያውቅም?
“ካሁን አሁን መጥቶ፤ ይወስደኛል ነድቶ
ከጋጣው አግብቶ ፤ ያበላኛል እብቅ “
እያለ ጌታውን ፥ተግቶ የሚጠብቅ
የዛሬ ተጎታች ፤ የትናንቱ ሰጋር
ተባብሮ የከዳው፤ ጊዜ ከጌታው ጋር
የቸገረው አቅም፥
የተጣለ ፈረስ ፤ አጋጥሞህ አያውቅም?
ደሞስ መች ይጠፋል?
ካንቺም ከኔም መንደር የቀድሞ ወታደር፥
በጨነቀን ጊዜ ፥“በናት ሀገር ጥሪ “
የምናጣድፈው፥
በድል ቀን ከድግስ፥ የማናሳትፈው
ከነጣቂ መዳፍ ፥ አገር የሚያስመልስ
በገዛ አገሩ ላይ፥
መብቱ ከወፍ አንሶ፤ ጎጆ የማይቀልስ፤
ደሞ መች ይጠፋል፤ ከኔም ካንተም ቀየ
መንገድ ላይ ምናልፈው፥ አይተን እንዳለየ
የቀድሞ አስተማሪ
ላብ እያጣቀሰ ፊደል አስቆጣሪ
ቀሪ ሀብት ባይኖረው፤
የቀረውን ዘመን፤ እያሰላ ኗሪ፤
ቪላችንን ሞልተን፥ በሱ ጎጆ ጉድለት
ማሰብ አስተምሮን ፥ የማናስበለት
ቀኖቹን በትኖ፤ ሌሊቶቹን ዘርቶ
ናላውን፥ ጉልበቱን ፥ ውበቱን ሰውቶ
የሚጎተት አገር፥ ከግቡ ለማድረስ
ሺህ መንገድ አቅንቶ፥ ሺህ ገደሎች መውረስ
ሰው ቢሉት ሰው ነው ወይ?
የተጣለ ፈረስ ::
@ourrthought
❤5🔥4
Maybe I'd be a bank robber. Some god damned thing. Something with flare, fire. You only had one shot. Why be a window washer?
Charles Bukowski
@ourrthought
😢13❤2
ዛሬ የ አርበኞች ቀን ነው። ቀኑን ለየት የሚያደርገው የ ጋሽ ስብሐት ልደት መሆኑም ጭምር ነው።
አርበኝነትን ካየን አቦይ ስብሐት በኢትዮጲያ ስነ ፅሑፍ ውስጥ አርበኛ ናቸው።
ከ ስብሐት በፊት የነበረው የሀገራችን ስነ ፅሑፍ ዲስኩር ማስተላለፊያ (Art for purpose) የሚከተል ነው። ንጉሱን ለማወደስ ወይ ለመኮነን የሚጠቀሙበት እንጂ እራሱን የቻለ (Art for art sake) የሚከተል አልነበረም።
ጋሽ ስብሐት ይህን የ አማርኛ ፅነ ፅሑፍ መልክት ለማስተላለፍነት አውጥቶ ስነ ጥበብን ለ ስነ ጥበብ የተጠቀመ ለ ድህረ ዘመናዊ አፃፃፍ ዘዴ በር የከፈተ የማይደፈር የሚመስለውን የስነ ምግባር አጥር ያፈረሰ አርበኛ ነው። ከሱ በፊት ስነ ፅሑፍን ለ ስነ ፅሑፍነት የተጠቀመ ደራሲ ሀገራችን ውስጥ ያለ አይመስለኝም። ድህረ ዘመናዊ አፃፃፍን ከ ስብሐት በፊት የሞከረው ሰው አልነበረም።
ከዛ ባለፈም ብናይ ህልማዊነት (Fantasy) በ ስምንተኛው ጋጋታ በኩል አፃፃፍን ያስኮመኮመን ነው። አቦይ በፅሑፎቹ ውስጥ ለሰዎች ያለውን ርህራሄና የሞት የ እርጅና ፍርሀቶች ታዩበታላቹህ።
አቦይ ያልዳሰሰው የስነ ፅሑፍ አይነት የለም ማለት ይቀላል። ለኔ በላጮቹ አምስት ስድስት ሰባት ፣ ሌቱም አይነጋልኝና ቦርጨቅ ቀዳሚ ምርጫዎቼ ናቸው። ዛሬ አርበኝነትን ሳስብ ለ ሀገራችን የስነ ፅሑፍ እድገት ፈር ቀዳጅ የሆኑትን ስነ ፅሑፍን በራሷ ቆማ እንድትታይ ያደረጉትን አቦይን በአርበኝነት እያሰብኩ ነው። ባለበት ምችት ይበለው።

❤8
😁14🤷♂1
ሐሳቦቻችን
Photo
እውን ግን ስልጡን ህዝቦች ነበርን?
ይህን ጥያቄ ያዕቆብ ብርሀኑ በውቄ እንዲሁም ሌሎች አንስተውት ጥሩ ምላሽ ሰጥተውበታል።
ባንድ ወቅት መለስ ዜናዊ "የ አክሱም ስልጣኔ ለ ሐመሩ ምኑ ነው?" የሚል ሀሳብ ሰጥተው አስታውሳለሁ። ከላይ ሲታይ ንግግሩ ዋዛ የሚመስል ውስጥ ውጡን መዝማዥ ሀሳብ ነው።
የሀገራችን ስልጣኔን ስልጣኔ ለማለትስ የሚያስደፍርስ ነው? ያስብላል። ሥልጣኔያችን መራመድ ያቃተው እነ አክሱም ሀውልቱ ንቅንቅ የማይል የማይወራረስ ነው። ሥልጣኔያችን አማልክቱን ከማወደሻነት ያልዘለሉ እና ኑሮዋችንን ያልቀየሩ ነበሩ ብሎ ይሞግታል ያዕቅብ ብርሀኑ በፍም እሳት ማቃመስ የሚለው መፅሐፉ ላይ። አክሱም ሥልጣኔ ዘመነ መንግስት ኪነ ህንፃዎቻችን ለ አማልክቱ ማወደሻነት የማይዘሉ ከዛ ከመሰለ አክሱም የኪነ ጥበብ ህንፃ ጎን በሳር ጎጆ የምንኖር ነበርን። አስቡት ሸክላ ሰሪ በገል ይበላል ማለት አሁን ነው። ያን የመሰለ ኪነ ህንፃ ህዝቡ የማይወራረሰው አማልክቱን ማወደሻነት የማይዘሉ ኪነ ህንፃዎች ነበሩ። ይሄ ሁሉም ላይ ይሰራል። ዛግዌ ፋሲለደስ ሶፍ ሁመር ሀረር ግንብ የቱም ስልጣኔ ለህዝቡ ግልጋሎት አልዋለም። ህዝቡም ጥበቡን አልተዋረሰም። ግን ለምን ይሆን? ከነዛ ከመሰሉ ጥበቦች ህዝቡ የራሱን ቤተ ህንፃ ሊገነባበት ያልቻለው በጎጆ የዳኸው? አሁንም ግራ አጋቢ ነው።
የራሳችን ቋንቋ ፅሑፍ አለን እያልን ከመሸለል ውጪ እነዚህ ፅሑፍ ቋንቋን ህዝቡ ራሱ ባዳ ነበር። በርግጥ በጥንቱ ዘመን እውቀት የትንሾች ብቻ መገልገያ ነበር (monopolies) የተደረገ ነበር። ለመፃፍ ለማንበብ ከኑሮ ትግል የዘለለ የተደላደለ ባላባት መሆን ይጠበቅበታል። በዚህ ስናየው ፊደላችን ጥበባችን ከጥቂት የቤተ እምነት ሰዎች ውጪ ቀሪው ምንነቱን የማያውቀው ነበር። እሱም ጥቅሙ ለ አማልክቱ መወደሻ እና ረቂቅነት ማወደሻ ነበር የምንጠቀመው እንጂ ኪ ጥበባችን ላይ ምንም የጅምላ አስተዋፆኦ አልነበረውም።
አሁንም ድረስ ከ 10ሺህ አመት በፊት በነበረ የእርሻ ዘዴ የሚጠቀም ከበሬው ጋር የሚለፋ ተስፋውን የሰማይ ላይቃ ተከፍቶ ዝናብ እስኪጣል የሚያደርግ የኑሮው ዘይቤ ከጥንቱ ሰው ያልተሻለ አሁንም ተራ ህመሞች እንደቅጠል የሚያረግፈው የቱ ነበር የሠለጠነው?
ዛሬም ጥያቄ ነው ለኔ እውን ሥልጡን ህዝቦች ነበርን? ወይስ ጥቂት የሠለጠኑ ሰዎች የነበሩበት ሀገር ላይ ነበርን? ሥልጣኔስ ካልተዋረሰ ህዝቡን ኑሮ ካልቀየረ ኑሮውን ባህሉን ወጉ ላይ አስተዋፆኦ ካሌለው ሥልጡን ነበርን ለማለትስ ያስደፍረን ይሆን?
@ourrthought
👍8
😁19👏4👎3❤2
🤔2😁1
ሐሳቦቻችን
እውን ግን ስልጡን ህዝቦች ነበርን? ይህን ጥያቄ ያዕቆብ ብርሀኑ በውቄ እንዲሁም ሌሎች አንስተውት ጥሩ ምላሽ ሰጥተውበታል። ባንድ ወቅት መለስ ዜናዊ "የ አክሱም ስልጣኔ ለ ሐመሩ ምኑ ነው?" የሚል ሀሳብ ሰጥተው አስታውሳለሁ። ከላይ ሲታይ ንግግሩ ዋዛ የሚመስል ውስጥ ውጡን መዝማዥ ሀሳብ ነው። የሀገራችን ስልጣኔን ስልጣኔ ለማለትስ የሚያስደፍርስ ነው? ያስብላል። ሥልጣኔያችን መራመድ ያቃተው እነ…
# የቅንጦት ሥልጣኔ
ሥልጣኔ ማለት ዓለትን መውቀር፣ ወርቅን ማቅለጥ ወይም ረቂቅ የሕግና የፍልስፍና መጻሕፍትን መደርደር ብቻ አይደለም። እውነተኛ ሥልጣኔ የሚለካው በቤተመንግሥቱ አጥር ስፋት ሳይሆን ያ ጥበብ ወርዶ የሰፊውን ሕዝብ ማዕድ ጤናና የዕለት ተዕለት ሕይወት መለወጥ ሲችል ብቻ ነው። የጥቂቶች ዕውቀት የብዙኃኑን ጨለማ ካላበራ ያ ነገር ሥልጣኔ ሳይሆን የአንድ ዘመን “ባህልና ቅንጦት” ተደርጎ ነው የሚወሰደው።
ጥበብ ዓለት ላይ ብቻ ተቀርቅሮ ሲቀርና ወደ ሕዝቡ ደም መዋሃድ ሲያቅተው ማኅበረሰቡ ካለፈው ዘመን ሳይቀዳ ለቀጣዩም ሳይተርፍ በነበረበት የኑሮ አዙሪት ውስጥ ተቀረቅሮ ይኖራል። ትልቁ ስብራት የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው። በጥበብ ማማ ላይ የተቀመጡት ሊቃውንትና የታችኛው ሰፊ ሕዝብ በመካከላቸው የሃሳብና የኑሮ ድልድይ ሳይኖራቸው ሲቀር ሀገር ታሪክ እንጂ ሕይወት አይኖራትም። ትናንት የነበረው ትልቅ የፈጠራ አቅም ዛሬ ላይ ተራ የትዝታ ቅርስ ሆኖ የሚቀረውም ጥበቡ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ስላልተተከለ ነው።
ስለዚህ አንድን ማኅበረሰብ “ሥልጡን” ለማለት የጥቂት ሰዎችን የላቀ አእምሮ ማየት ብቻ በቂ አይደለም። ሥልጣኔ ማለት ሰብዕናን መገንባትና ያንን ጥበብ ለትውልድ ማውረስ መቻል ነው። ጥበቡ የሕዝቡን የሕይወት ትግል ካላቀለለ ከበሽታና ከችጋር ካላዳነው እኛ ያለን የታሪክ ውበት እንጂ የሥልጣኔ እውነት ሊሆን አይችልም። የትናንቱ ትልቅነት ዛሬን መመገብ ካልቻለ ጥያቄው ዛሬም ድረስ ጥያቄ ሆኖ ይቀጥላል።
ሐኑ-ን
6/08/2018 ዓ.ም

🔥6
ይህ የመጀመሪያው ክፍል የመጀመሪያው አንቀፅ ላይ ስለ ሰው ልጅ ህልውና፣ እውነት እና ሥነ ምግባራዊ ውስብስብነት በዘይቤያዊ አነጋገር በ “ግራጫ" ተወክሎ በዶ/ር ምህረት በፍልስፍና የተሰላሰለበት ነው፡፡
ሁለትዮሽ ነገሮች እንዴት በአንድ ነገር ውስጥ ተዋህደው ትርጉም እንደሚሰጡ እና አሻሚነትን እንደ ጉድለት ሳይሆን ትርጉም ያለው ነገር አድርጎ ለማሳየት የተሞከረበት ነው፡፡ ይህንንም በተለያየ መንገድ እንየው
✔ግራጫ ሁለትዮሽ አስተሳሰብን ውድቅ እንደማድረግ
"ግራጫ ነጭ ሚጠቁርበት እና ጥቁር የሚነጣበት ሰፊ ግዛት ነው፡፡''እነዚህ ነጭ እና ጥቁር የተባሉ ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን በምሳሌ እንያቸው
ደግነት/ ክፋት
እውነት / ውሸት
ትክክል / ስህተት
የአንድ ሰው ሁለት ጎኖች ናቸው ። እነኚህ ነገሮች በሰፊ
ግራጫ ድብልቅ ውስጥ ያሉ የሞራል ማዕቀፎች ሲሆኑ እውነትነታቸው በፍፁምነት በወጥነት ሳይሆን በሽግግር ውስጥ የተዋቀረ ነው፡፡
አንዳንድ ድርጊቶች በራሳቸው በግልጽ አጥፊ (ጥቁር) ወይም በግልጽ አልሚ (ነጭ) ናቸው ነገር ግን አብዛኛዎቹ የሰው ልጆች ድርጊቶች ግራጫ ናቸው በተደባለቀ ዓላማ የሚነዱ በሁኔታዎች የተገደቡ ናቸው፡፡
ይህም ሰዎች ከንፁህ በጎነት ወይም ከንፁህ ክፋት እምብዛም እንዳልተሰሩ ያሳየናል።
✔ግራጫ ብርሃን እና ጨለማን እርስ በርስ አንደማዋሀድ
ግራጫ እንደ የብርሃን ኩርፊያ ወይም የጨለማ ፈገግታ ሆኖ ሊታይ ይችላል ወደ አንድ ጎን ዘንበል ብሎ... ግን ሁለቱንም የሚያጣምር ቀለም ነው።
የብርሃን ኩርፊያ ፦ በብርሀን ውስጥ ስጋትን እንደመመልከት ነው
የጨለማ ፈገግታ ፦ በጨለማ ውስጥ ተስፋን እንደመመልከት ነው ግራጫ ተለዋዋጭ ነው የማይንቀሳቀስ አይደለም። ዘንበል ይላል። ይቀየራል።ይህም በጎነት ሊበላሽ ፣ ክፉነት ደሞ ወደ ጥሩነት ሊሻሻል ይችላል ከሚለው ሀሳብ ጋር ይጣጣማል ። ይህም የሞራል ውስብስብነትን ያሳየናል።
✔ግራጫ በአውድ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ከፍልስፍና አንፃር ከነኚህ ሀሳቦች ጋር ይሄዳል
Phenomenology: meaning arises from relations not essences
Buddhist thought: identity lacks fixed self-nature
Postmodernism: truth is contextual, not absolute
✔ ግራጫን እንደ ሰው ልጅ ሌላነት እና የተጋራ ሰብአዊነት
"የሰው ልጅ የሆነ ልዩነት እና እውነት በራሱ ሰፊ ግራጫነት ተደብቆ ተገልጧል።"
"ሌላነት" ስንል እያንዳንዱ ሰው ፈጽሞ የማይለወጥ ልዩነት ያለው መሆኑን
"እውነት" ስንል የጋራ ሰብአዊነታችን አንድ ያደርገናል ተቃርኖ የለውም አብሮ ሚኖር መሆኑን ያስገነዝበናል።
ግራጫ ፦ልዩነት ተመሳሳይነትን የማይሽርበት ቦታ ነው፡፡
እያንዳንዱ ሰው ሌላ ሰው መሆኑን መረዳት እና እያንዳንዱ ሌላ ሰው እንደኛ መሆኑን መረዳት በህይወት ላይ አንድ ግራጫ አመለካከት ነው::
እያንዳንዱ ሰው ሊካድ የማይችል ሌላ ነው። እያንዳንዱ ሰው በመሠረቱ ተመሳሳይ ነው
በአጠቃላይ ግራጫ ድክመት፤ ወጥነትን መፍራት አደለም ወይም በብዥታ ውስጥ ግራ መጋባት አይደለም፣ ነገር ግን በጥልቀት በጥበብ መኖር ማለትም በልዩነት ውስጥ ተመሳሳይነትን ተቀብሎ አምኖ በግራጫ አለም ውስጥ መኖር እንደማለት ነው፡፡ እውነታን በፍፁምነት በተሻለ ሁኔታ አንረዳውም በግራጫነት እንጂ፡፡
ግራጫ የእውነት ቀለም ነው!!
በከነዓናዊት የተከተበ
በውስጥ መስመር የመጣ ፅሑፍ። ትውልዱ ትንታግ ሆኗል።

❤4🔥3