The Homeless Wanderer
Tsegue-Maryam Guebrou
Title : The homeless wonderer
Artist : Emahoy Tsegemariyam Gebru
የሴቶችን ቀን በማስመልከት የ እማሆይ ፅጌ ማርያም ገብሩ ዘፈን ልጋብዛቹህ ወደድኩ። ለምን የሳቸውን ካላቹህ ህይወታቸው አስደናቂ ስለሆነ ነው። መነኩሴ ናቸው ግን ደግሞ ከ ሙዚቃ ፍቅር ያገዳቸው አልነበረም። በሀገራችን የመጀመሪያዋ ሴት ፔያኒስት ይመስሉኛል።
አለም ያጨበጨበላቸው ነበሩ ነገር ግን የሳቸውን የሚጫወቱበትን የሙዚቃ መሳሪያ ለ ያሬድ ሙዚቃ ት/ት ቤት በአደራ መልክ ቢናዘዙም እሳቸው 2015 አከባቢ ሲያርፉ በ ታክስ ምክንያት ቤተሰቦቻቸው ፒያኖውን ለማስገባት ተወዶባቸው እንዳልገባ ሰምቼ ነበር። የሴቶች ቀን ሲከበር ምናልባት የኚህን ድንቅ የጥበብ ሰው ኑዛዜ ተፈፃሚ ሆኖ ቢሆን ማክበሩም ግቡን ይመታ ነበር። አስገብተውትም ከሆነ መልካም ነው።
@ourrthought

🔥9👍2
ከረጅም ጊዜ በኋላ ከመፅሐፎቼ ውስጥ "የጨለማው ዓለም ህዝቦች
ሰላቢና እና ቡዳ" የምትል መፅሐፍ በተመስገን አጭቆ የተፃፈ መፅሐፍ ትላንትና ዛሬ ሳገላብጥ ትንሽ ያስገረመኝን ስለ ሰላቢና ቡዳ አነበብኩኝ።
የዚህች መፅሐፍ አዘጋጅ በ ሰላቢና ቡዳ ዙሪያ ለረጅም ጊዜ ምርምር (research) የሰራና እሱ እንደሚለው እራሩም ተጠቂ የነበረ በመሆኑ ለመረጃው እንደረዳው ነው። የተለያዩ ሀገሮችን የቁዳና የሰላቢ አይነትና ባህሪያት በደንብ ሰብስቦ ነው የፃፈው። መፅሐፉ ከተራ አሉባልታ ያለፈ በብዙ ምርምር የተፃፈ ነው።
በርግጥ እኔን ያስገረመኝ ፀሀፊው ሰላቢና ቡዳን ከ (Chakra) ጋር አያይዞ ያብራራበት መንገድ ነው። Chakra የህንዶች መንፈሳዊ ልምምድ ሲሆን በ አካላችን ላይ የሚገኙ ዋና ዋና የሚገኙ በዋናነት በ 7 ቦታዎች የሚመደቡ የመንፈሳዊ ፣ አዕምሮአዊ ፣ አካላዊ ንቃትን የሚጨምሩ ልምምዶች ናቸው። እኚህ ዋና ዋና 7 Chakra የሚገኙት በጀርባ አካላችን ከ ቂጣችን ብልታችን አከባቢ ተነስቶ (base chakra) እስከ መሀል አናታችን ዋናው (crown chakra) ድረስ የሚገኙ ናቸው። እኚህን chakra ለማብራት እና ለመክፈት እንደ ሜድቴሽን ኩንድሊኒ አዌክኒንግ በመጠቀም ሰዎች ከፍተኛ የሆነ መገለጥ ደረጃ ላይ ለመድረስ የሚያስችላቸው የ አብርሆትን መንገድ የሚያቀዳጅ መንገድ ነው።
እና ፀሐፊው እንደሚለው ከሆነ ቡዳ እና ሰላቢ ከሰዎች እኚህን chakra የመንፈስ መውጫ መውጫና መግቢያ በር በመምጠጥ በመጠቀም ነው ከሰዎች መንፈሳዊ ሀይላቸውን የሚወስዱት ይለናል። እኚህ ቻክራዎች የሰው ልጅ መንፈሳዊ ሀይላቸው የሚገኙባቸው ቦታዎች እንደመሆናቸው ቡዳ እና ሰላቢ ከሰዎች ላይ ይሄን ሀይል ይወስዱታል ይለናል። ቡዳና ሰላቢ ከሰዎች ላይ (Halo) የማየት አቅም አላቸው ይለናል። ይሄ ማለት ከፍተኛ ወይም ጥሩ የመንፈስ ሀይል ያላቸውን ሰዎች ልክ በ ቤ/ክርስቲያን ላይ እንደሚታዩት የቅዱሳን ስዕለ አድኖ ላይ በአናታቸው ዙሪያ የ ቢጫ አክሊል ያለ ምልክት ቡዳና ሰላቢ ከሰዎች ላይ መንፈሳዊ ሀይልን የሚለዩበት ቢጫ ክብ የመሰለ በግለሰቡ ላይ እንደዛ ሆኖ ይታያቸዋል ያም በቀላሉ የሚበሉትን እና የማይበሉትን ሰው መለየት ያስችላቸዋል ይለናል። ዘይገርም ነው። በቡዳና ሰላቢ የሚበላው ሰው በየቀኑ አሸን ነው የአንዳንዱ አንድ ቀን ይቆያል አንዳንዱ ይከርምበታል አንዳንዱ ይሞታል። ግን እነሱ ሰውን የመግደል ፍላጎት የላቸውም መንፈሳዊ ሀይሉን ግን ይፈልጉታል።
መፅሐፉ እኛ ከምናስበው መደበኛ የትርጉም የራቀና የረቀቀ ነው የቡዳና ሰላቢ ስራና ተንኮል ይለናል። ቡዳ ሰውን በአይኑ ጨረር ነው የሚበላው ሰላቢ የሰውን ገንዘብ ይሰልባል የሚለውን ወሬ የሚያሶሩት እራሳቸው ናቸው ባይ ነው። ለምን ብትሉ ትክክለኛ ስራቻው እንዳይታወቅ ማወናበጃ ዘዴያቸው ነው ባይ ነው። እንጂ ሰላቢም ቡዳም ከፈጣሪ ሀይል ማግኘት የማይችሉ የሴጣን ግብረ አበሮች በመሆናቸው ሀይል የሚያገኙት ከሰው ብቻ ሳይሆን ከመላው ፍጥረት ነው። ከሰው ፣ ከእንስሳው ፣ ከመሬት ፣ ውሀው ፣ መብረቅ ፣ ዛፍ ፣ ምግብ አረ ምኑ ቅጡ የማይበሉት የለም።
በዛ ላይ ቡዳ በአይኑ ብቻ ነው የሚባለው ውሸት ነው ይለናል። እንደሱ ጥናት ከሆነ ቡዳ አይን ለአይን ካየ ብቻ ነው ሊበላን የሚችለው። ግን ደግሞ ከዛም ሌላ መንገድ አለው ይለናል ለምሳሌ እናንተን በማውራት ፣ መልእክት በመላክ ፣ ደዘድምፃቹን በመስማት ፣ ፎቶ በማየት ፣ በመዳበስ በመሳሰሉት ይበሉናል። እና እንደ ፀሐፊው ገለፃ ከሆገ ቡዳ እና ሰላቡ ከ ፈጣሪ ፀጋ የተለዩ መንፈሳዊ ሀይላቸውን ከፈጣሪ ማግኘት የተሳናቸው እና በጎውን የፈጣሪ መንፈሳዊ ሀይል ከሰዎች የሚወስዱ ናቸው።
ከመፅሐፉ ቡዙ ያልዳሰስኩት አለ በዛ ላይ ግማሽ ንባብ ነው ያነበብኩት ስላላስቻለኝ ነው። ያጋራኋቹህ ምናልባት ከሸነጠኝ ሰፋ አድርጌ ልመለስበት ችላለሁ ከ 9 ክፍሎች እኔ 2 ክፍሎችን ነው ያጋራኋቹህ። ፈጣሪ ከቡዳ እና ሰላቢ ይሰውራቹህ።
@ourrthought
👍7❤2👏1
እኛና አምላክ
ለራሳችሁ አልቅሱ አይደለ ያልከን? ይሄው ለራሳችን እያለቀስን ነው። ፈቃዳችንን ሳትጠይቀን በራስህ ፈቃድ ስላመጣህን እያለቀስን ነው። በግጥሙ ድንገት ዱብ እንዳለው ኦማር ካያም ካመጣህን በኋላ ስለ አሁን፣ ስለ ዛሬ፣ ስለ ነገ ባለማወቃችን እያለቀስን ነው። መኖር ቅጣት ሆኖብን እያለቀስን ነው። ለራሳችን ባዕድ በመሆናችን እያለቀስን ነው። ባጭሩ ከልደት እስከ ሞት የኛ ፈቃድ ስለሌለበት እያለቀስን ነው። የማናውቀውን ሕይወት እየኖርን የማናውቀውን ሞት እንሞታለን።
እግዚአብሔርም በቃሉ በኩል እንዲህ ሲል መለሰልኝ። ያለ እውቀት በሚነገር ቃል ምክርን የሚያጨልም ይህ ማነው? እንገዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ እጠይቅሀለሁ አንተም ተናገረኝ ምድርን በመሰረትኩ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርክ? ታስተውል እንደሆነ ተናገር። በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋራ ይከራከራልን? እጠይቅሃለሁ አንተም ተናገረኝ በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን? አንተስ ፃድቅ ትሆን ዘንድ በኔ ትፈርዳለህን? እንግዲህ በፊቴ መቆም የሚችል ማነው? እመልስለት ዘንድ መጀመሪያ የሰጠኝ ማነው?
እኔም ተናገርኩ እነሆ ስለ ፍትህ ጠየቅኩህ; አንተ ግን ስለ ታላቅነትህ፣ ስለ ሁሉን ቻይነትህ፣ ስለ ሉአላዊነትህ ነገርከኝ። ያልጠየቅኩትን መለስክልኝ። አንተ ታላቅ ሰው ግን ታናሽ፣ ትቢያ፣ እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን ትነግረኛለህ። ሰውን አንተው ፈጥረኸው አንተው ትንቀዋለህ። ደካማ በመፍጠር ብርቱነት አለን? ሟች የሆነን ፍጡር በመፍጠር እኔ ግን ሕያው ነኝ ማለት ይቻላልን? ትንሽ ነገር በመፍጠር ታላቅነት አለን? እፍ ብለህ ልታጠፋው የምትችለውን ሰው በመፍጠር ሁሉን ቻይነት ይገኛልን? ወሰን የሌለው አምላክ ወሰን ባለው ሰው ላይ ኃይሉን ማሳዬቱ አስደናቂ ያሰኘዋልን? በደካማ ላይ መበርታት እንዴት ኃያል የሚል ማዕረግ ያሰጣል? እባክህ ተለመነን፣ ለዘለአለም እራራልን፣ እጅህን አታክብድብን፣ እኛን ከማጥፋት ተመለስ፣ በፈጠርከው የሰው ልጅ ላይ ግፍ አትዋልበት።
እግዚአብሔርም በቃሉ እንዲህ ሲል መለሰ። እንደ እግዚአብሔር ያለ ክንድ አለህን? ወይስ እንደሱ ባለ ድምፅ ታንጎዳጉዳለህን? በውኑ ከተወለድክ ጀምሮ ማለዳን አዘሀልን? ከሰማይ ሁሉ በታች ያለው ገንዘቤ ነው አለኝ።
ይሄው እንደምታዩት የእግዚአብሔር መልስ ጥያቄ ነው። ስጠይቀው መልሶ እኔኑ ይጠይቀኛል። ሰውንና እግዚአብሔርን አንድ የሚያደርጋቸው ይሄው ነው። ጥያቄ ጥያቄ ጥያቄ።
ከ ዮናስ ጎርፌ ስነ አመክንዮ podcast የተቀነጨበ
©ዳዊት ጸጋዬ

❤14
ከመንጋው እንደተበተነ ግልገል ከባህሩ እንደወጣ አሳ ባዕድነት ይሰማኛል። እግዚሀር ያለ ዘመኔ ከሰው ጫካ የጣለኝ ያኽል ይመስለኛል። እኔን በሚመስሉ ግን እንደኔ ባልሆኑ የሰው መንጋ መሀል ለብቻ የተወኝ ይመስል ፈጣሪ ላይ አቂሜበታለሁ። ዘመኔ አይጥመኝም ምርጫ ቢሰጠኝ ከዘመኔ ወደ ኋላ እልፍ አመታትን ብመለስ እሻለሁ አልያ ወደፊት ከብዙ ዘመን በኋላ ብፈጠርና ከዚህ ዘመን ባመልጥ እያልኩ አስባለሁ።
ህይወቴን ለመቀየር ተፍጨርጭሬ አላውቅም ልክ የውሀው ማዕበል እንደሚወስዳት ዳክዬ ዘመን ወደሚወስደኝ የህይወት አፅናፍ በዝምታ አዘግማለሁ። ለህይወቴ ግድ ማጣቴ ያስፈራኛል ኑሮዬን ለመቀየር አለመታገሌ የዘበትነት ስሜቴ ሁሉ እየሱስ ክርስቶስ ለጲላጦስ ያሳየውን የዘላለም ዝምታ ይመስለኛል። ህልም ማጣቴ ማለም አለመቻሌ በሸላቾቹ ፊት እንደቆመው የፋሲካ በግ በሩጫ ዘመን በዝግታ አዘግማለሁ።
ዘመኔ አጭር ይመስለኛል። እረጅም እድሜ እንደኖረ ሰው በወጣትነቴ አለም ያታክተኛል። 80 አመት ያለምንም ለውጥ እንዳሳለፈ አዛውንት ወደ ኋላዬ ስመለከት ይጨፈግግኛል። ዘመናትን ያሳለፍኩ ያህል ምድር አሰልችቶኛል። መብላት ፣ መተኛት ፣ መነሳት ፣ መኖር ፣ ለህልም መታገል ጠቢቡ እንዳለው የከንቱ ከንቱ አይደሉምን? ሰው ከኑረቱ ምን አትርፏል? ምናልባት ትዝታን። ከዚህ ሁሉ በኋላ ያለ ህልም መኖር ዘበትን መላመድ ባለሁበት መንቧቸቼን እንደ ምቾት መቁጠሬ ሁሉ እያስፈራኝ መጥቷል። ሰው ህይወቱን ለመቀየር ሲለፋ ሱሪ ለመቀየር አለመታገሌ ያስደነግጠኝ ጀምሯል። ምኑ ጋር ነው ከህይወት ጋር የተላለፍኩት? ለምንድነው በወጣትነቴ ያዛውንት ከንቱነት የተጫነኝ? መኖር የማያጓጓኝ? ያልሞከርኩት የማይማርከኝ?
ለመሞት ሦስት ቀን ይቀርሀል እንደተባለ ሞቱን ነጭ ጋውን ካደረገ መነጥር አጥላቂ ሾካካ ሰው እንደሰማ ጎልማሳ ሞቴን የምጠብቅ ይመስለኛል። ብር ብዬ ሰዎች ወደሌሉበት ወደ ጫካ ወደ በረሀ መጓዝ ያምረኛል ቅሉ ያለ ሰው መኖር የማይችል ደካማ አድርጎኛል። እንጃራ ብቻውን የማይቆርስ ፈሪ እንዴትስ ብቻውን ከሰው ተገሎ እንደ ባህታዊ ሊመንን ይቻለዋል?
ከእውነተኛ የግል ማስታወሻ

❤6😢6
እዛው ነኝ
አልጨመርኩም ክብደት ቁመት
አለወጥኩም ቀለም ውበት
አላወራሁ ከማንም ጋር
አልተሸሸኩ እምንም ጋር
እንደያኔው
ቀጠሮ እንዳስያሺኝ
መጣለሁ እንዳልሺኝ
እንደዛ ነኝ
ዘመናት ቢነጉድም
አለም ቢለወጥም
አኔ አልተለወጥኩም
አንቺን እንዳይከፋሽ
ላንቺ እንዳልጠፋሽ
Iinspired by Baheta G/hiwot music
እዛው ነኝ
12/07/2018 ዓ.ም
@ourrthought
አልጨመርኩም ክብደት ቁመት
አለወጥኩም ቀለም ውበት
አላወራሁ ከማንም ጋር
አልተሸሸኩ እምንም ጋር
እንደያኔው
ቀጠሮ እንዳስያሺኝ
መጣለሁ እንዳልሺኝ
እንደዛ ነኝ
ዘመናት ቢነጉድም
አለም ቢለወጥም
አኔ አልተለወጥኩም
አንቺን እንዳይከፋሽ
ላንቺ እንዳልጠፋሽ
Iinspired by Baheta G/hiwot music
እዛው ነኝ
12/07/2018 ዓ.ም
@ourrthought
❤5🔥1😢1
ጠብታ....
አሉ አንድ አንድ ሰዎች፤ በተስፋ መቁረጥ ከትቢያ ወድቀን ለመነሳት መፍጨርጨር ሲከብደን በቃላቸው የሚያድሱን። አሉ አንድ አንድ ሰዎች፤ ተካድን፣ የሚረዳ'ን አጣን፣ ዝምድና ግንኙነት ጓደኝነት ምንም አይሰራልንም ብለን እራሳችንን መሸከፍ ስንጀምር ከሩቅ ሆነው ምንም በማለት ውስጥ አለሁ የሚሉን። አሉ ደግሞ፤ በዚህ የሰቀቀን ባህር ውስጥ ስንዋዥቅ ሰልጥቆ የበላን የብቸኝነት፣ ሰውነት ላይ ተስፋ የመቁረጥ አሳ ነባሪ ባህርዳርቻው ላይ እስኪተፋን ዮናስነታችንን አስጠብቀው የሚያቆዩልን ሰዎች አሉ።
ተፈጥሮ ከውልደት እስከ ሞት በስቃይ ማዕበል ስታንገላታን ቆይታ የህይወታችንን መልህቅ ወደ ባህሩ እንዳንለቀው የምታባብልበት ሰዎች አሏት፤ ለጭካኔዋ ማስታገሻ ይመስል ከአንድ ጥግ አኑራ ከዘላለም ዝምታ እኛን የምታቅብበት አንድ አንድ ጠብታ ሰዎች አሉ።

ቺርስ ለነዛ ሰዎች!
@ourrthought
💊5👌3❤2🫡2
አለም መቶ ጊዜ ቢታጠቡባት አንድ ጊዜ የማይነፁባት ሥፍራ ናት። ምን ጻድቅ ቢኾኑ ተፈጥሮ ነውና መፍራት ፣ መሰሰት ፣ አሳልፎ መስጠት ፣ መጥላት ፣ መስጋት ፣ ክህደት... መከላከል በማንችላቸው መንገዶች መጥተው ሕይወታችን ውስጥ ይከናወናሉ።
የሰው ልጅ ሕይወት ዝንቁ ብዙ ነው። ዕውን ዕውነትን ይወክላል ፤ ህልም ደግሞ ሀሰትን ፤ ዐልፎ አልፎ ሕልምና ቅዠት የዕውነት መፍቻ እንደሚኾነው ኹሉ እንዲሁ ሐሰት የዕውነት ማተራጎሚያ ይኾናል።
ፈሪሳ
አለማየሁ ገላጋይ
@ourrthought
የሰው ልጅ ሕይወት ዝንቁ ብዙ ነው። ዕውን ዕውነትን ይወክላል ፤ ህልም ደግሞ ሀሰትን ፤ ዐልፎ አልፎ ሕልምና ቅዠት የዕውነት መፍቻ እንደሚኾነው ኹሉ እንዲሁ ሐሰት የዕውነት ማተራጎሚያ ይኾናል።
ፈሪሳ
አለማየሁ ገላጋይ
@ourrthought
👍8🔥4❤1
"ስለ ህይወት ሃያልነት ማውራት ከፈለግን ቀድመን ስለሞት እናውራ"
የሞት መኖር ነው ህይወታችንን አጣፍጠን እንድንኖር የሚያደርገን። እንደው ማን ይሙትና 'እሳት' አቅርበው ባያስፈራሩን ኖሮ ህይወት ለመኖር መች አጭር ሆነችና?! ሞት ለህይወት ባለውለታዋ ነው፤ ለመኖር ስስትን ከየት አገኘንና?! እንጂማ እኮ ህይወት የተፈጠረችው እኛን በስቃይ ለመቅጫነት ነበር፤ ለነገ በማሰብ ስቃይ ውስጥ፣ ሰው ምን ይለኛል በሚል ፍርሃት ውስጥ እንድንማቅቅ ለማድረግ። ይመስገን! ‘ህይወት ወደ መቀመቀ ስታወርደን ሞት ነፃ አወጣን።'
የሞት መመጫውን ባለማወቃችን ለነገ ቆጥበን ለቁርስ ያስቀመጥነውን፤ ዛሬ ከመሸ፣ ከዋክብት ጨረቃን አጅበው በሚደንሱበት በዚህች ምሽት፤ ወይ ወይዘሮ አልታዬ ቤት፣ ወይንም ደግሞ ከደንዳሳዋ ከበቡሽ አረቄ ቤት አረቄያችንን እየተጎነጨን፤ ህይወት ቀኑን ሙሉ ያሳየችንን ፍዳ አረቄውን በጥሩ ሲጋራ አጅበን “አሹት!” ይብላኝ እንጂ ላንቺ” እንላታለን።ደግሞም ሞት ህይወትን በስስት እንድንኖራት አድርጎናል አላልንም? ህይወት ብትከፋም ነገ ሞት አባታችን መጥቶ ሊወስደን ስለሚችል፤ ዛሬን!... ዛሬን በጨረቃ ታጅበን፣ ቆንጆ አረቄ ጠጥተን፣ አለፍ ካለም ሞትን ማምለጥ ባንችል በእርካታ ለመቀበል ከአረጋሽ ጭን መሃል እንፋሎት ስንስብ እናድራለን።

ሞት ቀርቶ ነገም ዳግም ህይወት ብትመጣስ ከሆነ ነገሩ፤ ሞት ህይወትን በስስት መኖር አስተምሮን አይደል? እንግዲያውስ...
❤5👍1
የት ነኝ?
ህይወቴ ልክ እንደ ዘጠኙ ሃዋርያት ይመስለኛል...ይሁዳና ጴጥሮስ በክህደት ሲታወሱ ፣ ወንጌላዊ ዩሐንስ በታማኝነቱ እስከ መስቀሉ ሲከተለው!
የተቀሩት ሐዋርያት መኖር አለመኖራቸው የተረሱ ነበሩ! በክፉም ይሁን በመልካም ያለመታወስ ኖረው እዳልኖሩ ከመዘንጋት እንደይሁዳ በክፉ መነሳት አይሻልምን?
ሞቴን እስክመኝ የተረሳው ነበርኩ ፣ መኖሬና አለመኖሬ በቁም የተዘነጋ!
@ourrthought
❤9
ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን
ምጥ አታስተምርም ልጅ እናቷን! "
" ወይድ አታስቆጥረኝ ዘር አጥንቴን
እኔ አውቀው የለም ወይ ማንነቴን! "
ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራየን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማየን!
@ourrthought
ምጥ አታስተምርም ልጅ እናቷን! "
" ወይድ አታስቆጥረኝ ዘር አጥንቴን
እኔ አውቀው የለም ወይ ማንነቴን! "
ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራየን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማየን!
@ourrthought
❤11
ሐሳቦቻችን
ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን ምጥ አታስተምርም ልጅ እናቷን! " " ወይድ አታስቆጥረኝ ዘር አጥንቴን እኔ አውቀው የለም ወይ ማንነቴን! " ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራየን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማየን! @ourrthought
ሁላችንም አንድ የምንጠብቀው ነገር ያለ ይመስለኛል። ከዚህ ዘመን ነፃ የሚያወጣን ወደ ከነዓናዊቷ በልባችን ወደሳልናት ኢትዮጲያ የሚወስደን መሲህ ፍለጋ በልባችን የምንንከራተት የሆንን ይመስላል።
ቴዲ አንደበታችን እስኪመስል ድረስ በልባችን የምናስባትን ኢትዮጲያን የሚያዜምልን የነብሳችን ሰው ነው። የጋራ ደመነብሳችንን ከተበታተነበት እየሰበሰበ የሚሞዝቅልን ስለ ኢትዮጲያችን በዜማዎቹ በግጥሞቹ የሚሰብከንም ጭምር ነው። ሁላችንም አሁን ላይ ደፍረን ማውጣት የከበደችን ስለ ሀገራችን የሚሰማን ባዶ ተስፋ አውጥቶ የሚነግረን የምንጠብቅ ይመስል ስለ ሀገራችን መርዶ የመጠበቅ ያክል በልባችን የምናስበው ትካዜን የሚነግረን የምንጠብቅ ነን እሱንም ቴዲ በዘፈኖቹ የነገረን ይመስለኛል። እኛም መርዶዋችንን የተቀበልን ይመስላል።
ባንድ ወቅት አውጉቸው እና አንድ የመፅሐፍ ሻጭ በደርግ ዘመን ብቻቸውን መስቀል አደባባይ ሰልፍ ወጥተው ነበር። ሀገራቸው ያለችበት የህዝቧ ኑሮ አሳስቧቸው ለውጥ ባያመጡም ለ አገዛዙ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለፅ ነበር የወጡት።
ቴዴ አፍሮ አሁን ላይ እንደነሱ ብቻውን ሰልፍ የወጣ ለዚህች ኢትዮጲያ የሚተክዝና የሚብሰለሰል ነው። እኛ በልባችን የምናዜመውን ሀዘን እሱ ብቻውን አደባባይ ይዞ የሚወጣ አጋዥ ያጣ ብቸኛ ሰው ይመስለኛል። ለውጥ ባያመጣም ያለውን ተቃውሞ ማሳየትን የማይፈራ ለኢትዮጵያዊነት የሚታገል የነብሳችን ሰው ነው።
@ourrthought
❤13
ሐሳቦቻችን
Photo
ዛሬ አለማቀፍ የመፅሐፍ ቀን
ወደ መሞቻቸው አከባቢ ከአንድ ወዳጃቸው ጋር እያወሩ
"ህዝቡ ስለኛ ምን ይላል" አሉት
"ህዝብ ስለርሶ ምንም አይልም ከነ መፈጠሮ እረስቶዎታል" አላቸው
የዛነኔ በጣም ተብከንክነው
"ምናለ የኢትዮጲያ ህዝቡ ቂጡ በገጠመና አንድ ሆኖልኝ በበዳውት" አሉ ይባላል።
@ourrthought
መፅሐፍ ማንበብ ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ቅንጦት ከሆነ ነገሮች ነው የሚመደበው። በብዙ መቶ ሺዎች የሚያወጡ ውድ መጠጦች ከቀረጥ ነፃ በሚገቡባት ሀገር ላይ ወረቀት ላይ የሚጣለው ግብር ቅንጡ ከሚባሉት ግብአቶች ጋር የሚመደብ ነው።
አንድ መፅሐፍ ከጅምሩ እስከ ህትመቱ ጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ የሚጣለው ግብር የሆነ የሚያሳየው ነገር እንዳለ ግልፅ ነው። ደርግ ስልጣኑን እስኪለቅ ድረስ የነበሩን መፅሐፍት ቤቶች ላይብረሪዎች ኢህአዴግ ዘመነ መንግስት ከ 80% በላይ የሚሆኑት ፈርሰው ስጋ ቤት ጫት ቤትና ግሮሰሪ ቤት ነበር የሆኑት። ያነበበ ትውልድ ይጠይቃል የሚጠይቅ ትውልድ ደግሞ ግልፅ ነው።
አሁንም ድረስ የ አፍርካ መሪዎች አንባቢ ትውልድን አይፈልጉም። ከንባብ የተፋታ መንጋ ህዝብን እንጂ። መፅሐፍ ሻጮች ከደርግ ዘመን ጀመሮ እስከ ኢህአዴግ ዘመን ድረስ መፅሐፍ ለመሸጥ የሚያዩት ፈተና አይጣል ነው። በዚህ መንግስት ደሞ ከሁሉ የከፋውን መሳደድ እያዩ ያሉበት ነው። አንድ የ200 ገፅ መፅሐፍ በ 500 ብር የሚሸጥበት ዘመን ነው። እንዳጌታ አስረኞቹ በሚለው መፅሐፍ ላይ ስለ መፅሐፍ ሻጮችና መፅሐፍ በሀገራችን ከ አፄ ኃ/ሥላሴ እስከ ኢህአዴግ ያለውን ተግዳሮት ያስቃኘናል።
በመፅሐፉ ላይም ዳኛቸው ወርቁ ወይ ከበደ ሚካኤል ይመስሉኛል ለ ወያላዎች እቃ ተሸካሚዎችን እቃ አሸክሞ በቤቱ ከወሰዳቸው በኋላ በገንዘብ ፋንታ መፅሐፍ ይሰጧቸው ነበር። እነ ከበደ ሚካኤል የመፅሐፍ ደንበኞቻቸው በፖሊስ ሲያዙ አማላጅ ሆነው ያስፈቱ ነበር። ፅሑፉን በከበደ ሚካኤል ንግግር ዘጋዋለሁ።
ወደ መሞቻቸው አከባቢ ከአንድ ወዳጃቸው ጋር እያወሩ
"ህዝቡ ስለኛ ምን ይላል" አሉት
"ህዝብ ስለርሶ ምንም አይልም ከነ መፈጠሮ እረስቶዎታል" አላቸው
የዛነኔ በጣም ተብከንክነው
"ምናለ የኢትዮጲያ ህዝቡ ቂጡ በገጠመና አንድ ሆኖልኝ በበዳውት" አሉ ይባላል።
ሀገራችን ብዙ መፅሐፍ የፃፉ ሰዎች ተርበው የሚሞቱባት ጠያቂ የሚያጡባት ከእውቀት የተፋታች አሳዛኝ ብኩን መፃጉዕ ትመስላለች።
@ourrthought
😁8😢3❤2
የተጣለ ፈረስ
(በእውቀቱ ስዩም)
ዘመኑ ያለፈ ጋማው የረገፈ ፤
የጎድን አጥንቱ ፤ ማበጠርያ መሳይ
ጠዋት ህያው ፍጡር፥ ሌሊት የጅብ ሲሳይ
ከተማው መግቢያ ላይ አቧራ የሚቅም
የተጣለ ፈረስ አጋጥሞሽ ፤ አያውቅም?
“ካሁን አሁን መጥቶ፤ ይወስደኛል ነድቶ
ከጋጣው አግብቶ ፤ ያበላኛል እብቅ “
እያለ ጌታውን ፥ተግቶ የሚጠብቅ
የዛሬ ተጎታች ፤ የትናንቱ ሰጋር
ተባብሮ የከዳው፤ ጊዜ ከጌታው ጋር
የቸገረው አቅም፥
የተጣለ ፈረስ ፤ አጋጥሞህ አያውቅም?
ደሞስ መች ይጠፋል?
ካንቺም ከኔም መንደር የቀድሞ ወታደር፥
በጨነቀን ጊዜ ፥“በናት ሀገር ጥሪ “
የምናጣድፈው፥
በድል ቀን ከድግስ፥ የማናሳትፈው
ከነጣቂ መዳፍ ፥ አገር የሚያስመልስ
በገዛ አገሩ ላይ፥
መብቱ ከወፍ አንሶ፤ ጎጆ የማይቀልስ፤
ደሞ መች ይጠፋል፤ ከኔም ካንተም ቀየ
መንገድ ላይ ምናልፈው፥ አይተን እንዳለየ
የቀድሞ አስተማሪ
ላብ እያጣቀሰ ፊደል አስቆጣሪ
ቀሪ ሀብት ባይኖረው፤
የቀረውን ዘመን፤ እያሰላ ኗሪ፤
ቪላችንን ሞልተን፥ በሱ ጎጆ ጉድለት
ማሰብ አስተምሮን ፥ የማናስበለት
ቀኖቹን በትኖ፤ ሌሊቶቹን ዘርቶ
ናላውን፥ ጉልበቱን ፥ ውበቱን ሰውቶ
የሚጎተት አገር፥ ከግቡ ለማድረስ
ሺህ መንገድ አቅንቶ፥ ሺህ ገደሎች መውረስ
ሰው ቢሉት ሰው ነው ወይ?
የተጣለ ፈረስ ::
@ourrthought
(በእውቀቱ ስዩም)
ዘመኑ ያለፈ ጋማው የረገፈ ፤
የጎድን አጥንቱ ፤ ማበጠርያ መሳይ
ጠዋት ህያው ፍጡር፥ ሌሊት የጅብ ሲሳይ
ከተማው መግቢያ ላይ አቧራ የሚቅም
የተጣለ ፈረስ አጋጥሞሽ ፤ አያውቅም?
“ካሁን አሁን መጥቶ፤ ይወስደኛል ነድቶ
ከጋጣው አግብቶ ፤ ያበላኛል እብቅ “
እያለ ጌታውን ፥ተግቶ የሚጠብቅ
የዛሬ ተጎታች ፤ የትናንቱ ሰጋር
ተባብሮ የከዳው፤ ጊዜ ከጌታው ጋር
የቸገረው አቅም፥
የተጣለ ፈረስ ፤ አጋጥሞህ አያውቅም?
ደሞስ መች ይጠፋል?
ካንቺም ከኔም መንደር የቀድሞ ወታደር፥
በጨነቀን ጊዜ ፥“በናት ሀገር ጥሪ “
የምናጣድፈው፥
በድል ቀን ከድግስ፥ የማናሳትፈው
ከነጣቂ መዳፍ ፥ አገር የሚያስመልስ
በገዛ አገሩ ላይ፥
መብቱ ከወፍ አንሶ፤ ጎጆ የማይቀልስ፤
ደሞ መች ይጠፋል፤ ከኔም ካንተም ቀየ
መንገድ ላይ ምናልፈው፥ አይተን እንዳለየ
የቀድሞ አስተማሪ
ላብ እያጣቀሰ ፊደል አስቆጣሪ
ቀሪ ሀብት ባይኖረው፤
የቀረውን ዘመን፤ እያሰላ ኗሪ፤
ቪላችንን ሞልተን፥ በሱ ጎጆ ጉድለት
ማሰብ አስተምሮን ፥ የማናስበለት
ቀኖቹን በትኖ፤ ሌሊቶቹን ዘርቶ
ናላውን፥ ጉልበቱን ፥ ውበቱን ሰውቶ
የሚጎተት አገር፥ ከግቡ ለማድረስ
ሺህ መንገድ አቅንቶ፥ ሺህ ገደሎች መውረስ
ሰው ቢሉት ሰው ነው ወይ?
የተጣለ ፈረስ ::
@ourrthought
❤5🔥4
Maybe I'd be a bank robber. Some god damned thing. Something with flare, fire. You only had one shot. Why be a window washer?
Charles Bukowski
@ourrthought
😢13❤2
ዛሬ የ አርበኞች ቀን ነው። ቀኑን ለየት የሚያደርገው የ ጋሽ ስብሐት ልደት መሆኑም ጭምር ነው።
አርበኝነትን ካየን አቦይ ስብሐት በኢትዮጲያ ስነ ፅሑፍ ውስጥ አርበኛ ናቸው።
ከ ስብሐት በፊት የነበረው የሀገራችን ስነ ፅሑፍ ዲስኩር ማስተላለፊያ (Art for purpose) የሚከተል ነው። ንጉሱን ለማወደስ ወይ ለመኮነን የሚጠቀሙበት እንጂ እራሱን የቻለ (Art for art sake) የሚከተል አልነበረም።
ጋሽ ስብሐት ይህን የ አማርኛ ፅነ ፅሑፍ መልክት ለማስተላለፍነት አውጥቶ ስነ ጥበብን ለ ስነ ጥበብ የተጠቀመ ለ ድህረ ዘመናዊ አፃፃፍ ዘዴ በር የከፈተ የማይደፈር የሚመስለውን የስነ ምግባር አጥር ያፈረሰ አርበኛ ነው። ከሱ በፊት ስነ ፅሑፍን ለ ስነ ፅሑፍነት የተጠቀመ ደራሲ ሀገራችን ውስጥ ያለ አይመስለኝም። ድህረ ዘመናዊ አፃፃፍን ከ ስብሐት በፊት የሞከረው ሰው አልነበረም።
ከዛ ባለፈም ብናይ ህልማዊነት (Fantasy) በ ስምንተኛው ጋጋታ በኩል አፃፃፍን ያስኮመኮመን ነው። አቦይ በፅሑፎቹ ውስጥ ለሰዎች ያለውን ርህራሄና የሞት የ እርጅና ፍርሀቶች ታዩበታላቹህ።
አቦይ ያልዳሰሰው የስነ ፅሑፍ አይነት የለም ማለት ይቀላል። ለኔ በላጮቹ አምስት ስድስት ሰባት ፣ ሌቱም አይነጋልኝና ቦርጨቅ ቀዳሚ ምርጫዎቼ ናቸው። ዛሬ አርበኝነትን ሳስብ ለ ሀገራችን የስነ ፅሑፍ እድገት ፈር ቀዳጅ የሆኑትን ስነ ፅሑፍን በራሷ ቆማ እንድትታይ ያደረጉትን አቦይን በአርበኝነት እያሰብኩ ነው። ባለበት ምችት ይበለው።

❤8
😁14🤷♂1
ሐሳቦቻችን
Photo
እውን ግን ስልጡን ህዝቦች ነበርን?
ይህን ጥያቄ ያዕቆብ ብርሀኑ በውቄ እንዲሁም ሌሎች አንስተውት ጥሩ ምላሽ ሰጥተውበታል።
ባንድ ወቅት መለስ ዜናዊ "የ አክሱም ስልጣኔ ለ ሐመሩ ምኑ ነው?" የሚል ሀሳብ ሰጥተው አስታውሳለሁ። ከላይ ሲታይ ንግግሩ ዋዛ የሚመስል ውስጥ ውጡን መዝማዥ ሀሳብ ነው።
የሀገራችን ስልጣኔን ስልጣኔ ለማለትስ የሚያስደፍርስ ነው? ያስብላል። ሥልጣኔያችን መራመድ ያቃተው እነ አክሱም ሀውልቱ ንቅንቅ የማይል የማይወራረስ ነው። ሥልጣኔያችን አማልክቱን ከማወደሻነት ያልዘለሉ እና ኑሮዋችንን ያልቀየሩ ነበሩ ብሎ ይሞግታል ያዕቅብ ብርሀኑ በፍም እሳት ማቃመስ የሚለው መፅሐፉ ላይ። አክሱም ሥልጣኔ ዘመነ መንግስት ኪነ ህንፃዎቻችን ለ አማልክቱ ማወደሻነት የማይዘሉ ከዛ ከመሰለ አክሱም የኪነ ጥበብ ህንፃ ጎን በሳር ጎጆ የምንኖር ነበርን። አስቡት ሸክላ ሰሪ በገል ይበላል ማለት አሁን ነው። ያን የመሰለ ኪነ ህንፃ ህዝቡ የማይወራረሰው አማልክቱን ማወደሻነት የማይዘሉ ኪነ ህንፃዎች ነበሩ። ይሄ ሁሉም ላይ ይሰራል። ዛግዌ ፋሲለደስ ሶፍ ሁመር ሀረር ግንብ የቱም ስልጣኔ ለህዝቡ ግልጋሎት አልዋለም። ህዝቡም ጥበቡን አልተዋረሰም። ግን ለምን ይሆን? ከነዛ ከመሰሉ ጥበቦች ህዝቡ የራሱን ቤተ ህንፃ ሊገነባበት ያልቻለው በጎጆ የዳኸው? አሁንም ግራ አጋቢ ነው።
የራሳችን ቋንቋ ፅሑፍ አለን እያልን ከመሸለል ውጪ እነዚህ ፅሑፍ ቋንቋን ህዝቡ ራሱ ባዳ ነበር። በርግጥ በጥንቱ ዘመን እውቀት የትንሾች ብቻ መገልገያ ነበር (monopolies) የተደረገ ነበር። ለመፃፍ ለማንበብ ከኑሮ ትግል የዘለለ የተደላደለ ባላባት መሆን ይጠበቅበታል። በዚህ ስናየው ፊደላችን ጥበባችን ከጥቂት የቤተ እምነት ሰዎች ውጪ ቀሪው ምንነቱን የማያውቀው ነበር። እሱም ጥቅሙ ለ አማልክቱ መወደሻ እና ረቂቅነት ማወደሻ ነበር የምንጠቀመው እንጂ ኪ ጥበባችን ላይ ምንም የጅምላ አስተዋፆኦ አልነበረውም።
አሁንም ድረስ ከ 10ሺህ አመት በፊት በነበረ የእርሻ ዘዴ የሚጠቀም ከበሬው ጋር የሚለፋ ተስፋውን የሰማይ ላይቃ ተከፍቶ ዝናብ እስኪጣል የሚያደርግ የኑሮው ዘይቤ ከጥንቱ ሰው ያልተሻለ አሁንም ተራ ህመሞች እንደቅጠል የሚያረግፈው የቱ ነበር የሠለጠነው?
ዛሬም ጥያቄ ነው ለኔ እውን ሥልጡን ህዝቦች ነበርን? ወይስ ጥቂት የሠለጠኑ ሰዎች የነበሩበት ሀገር ላይ ነበርን? ሥልጣኔስ ካልተዋረሰ ህዝቡን ኑሮ ካልቀየረ ኑሮውን ባህሉን ወጉ ላይ አስተዋፆኦ ካሌለው ሥልጡን ነበርን ለማለትስ ያስደፍረን ይሆን?
@ourrthought
👍8