ነገረ ፖለቲካ ወ አፍሪቃ
እውነተኛ ክስተት ነው የምነግራቹህ
ስሟ በጠፋብኝ አንድ የ አፍሪካ ሀገር ባንድ ወቅት ምርጫ ሊደረግ ሽር ጉዱ ተጀመረ እና የመጨረሻው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ እጩ ተወዳዳሪ እስከዛሬ ያለውን ብልሹ አሰራርና ስርአት አልበኝነት እያነሳ እሱ ከተመረጠ ይሄን ችግር እንደሚፈታ ደሰኮረ ህዝቡም አዳነቀ ተደሰተ።
ከዛም ጠቅላዩ መሪ በመጨረሻ ቅስቀሳው ህዝቡን በ እስታዲዮም ሰብስቦ አንድ ንግግር አደረገ።
"ውድ ህዝቤ ሆይ አርፍሪካ ውስጥ አንድ መሪ የመጀመሪያው ምርጫ ላይ ለ ቤተሰቡና ለራሱ ይሰራል ህይወቱንም ይቀይራል። ቀጣዩ ምርጫ ላይ ደግሞ ለዘመዶቹና ለቅርብ ጓደኞቹ ህይወትና ለወጥ ይሰራል። በ ሦስተኛው ምርጫ ደግሞ አማራጭ ስለሌለው የቀረው ቤተሰብም ዘመድም ጓደኛም ስለማይኖር ለህዝቡ ለውጥ ይተጋል። በዛ መሠረት እኔ ቤተሰቤንም ፣ ዘመዶቼንም ፣ ጓደኞቼንም ለውጫለሁ አሁን ሦስተኛው ምርጫ ላይ ነኝ ለናንተ ከመስራት ውጪ አማራጭ የለኝም። ትኩረቴ ለናንተ ይሆናል። አይ ካላቹህ አዲሱን መሪ ምረጡና ቤተሰቦቹን ፣ ዘመዶቹን እና ጓደኞቹን ቀይሮ እናንተን እስኪይር መጠበቅ ትችላላቹህ።" ህዝቡም ለ ሦስተኛ ጊዜ መረጠው አማራጭ አልነበረውምና።
ሰሞኑን ለ አፍሪካ ጉባኤው ለመሪዎቹ ያለውን ወከባ ሳስተውል የ አፍሪካን ችግር የሚፈቱ ትላልቅ ልሂቃን እንጂ የ አፍሪካን ችግር የሚያባብሱ አልመስልኝ ብለውኝ ግራ ስጋባ ነበር።
ይሄ የ አፍሪካ መሪዎች ስብስብ በራሱ እንኳ መቆም ያልቻለ በ አውሮፓ ሀገሮች የሚደገፍ የመሪዎች ስብሰባ የ አፍሪካን ችግር ሳይሆን የሚፈቱት የ ሀበሻ ሴቶችን የቀሚስ ቋጠሮ እና ቀበቷቸውን ለመፍታት ነው ቋምጠው የሚመጡት። እናት አለም አፍሪቃ መምጫሽ ይናፍቀኛል ቻይው!
@ourrthought

🔥5😁1😢1
ዳግም የተለጠፈች
@ourrthought
ብቻ ግን ይመስለናል
ይመስልሀል እንጂ : ሀዘንህ : ስሜት ማጣትህ : ተስፋ መቁረጥህ....ማንም ግድ ሰጥቶት አይብሰለሰልልህም!
ሞትህም ቢሆን ልክ ከአንድ ግዙፍ ግንድ ላይ አንድ ዘለላ ቅጠል ተበጥሳ እንደወደቀች ያህል : እንዲያው እንደነገሩ መሬት ማስ ማስ አድረገው ተጉድጓድ ይጨምሩል እንጂ ጠሀይም ብትሆን አምላኳን እንዳጣችበት ጊዜ አትጠልቅልህም : ጨረቃም ደም አትለብስም : ለሞትህ ከዋክብትም አይረግፉልህም : ስለ ሞትህም የሚቀደድ መጋረጃ አይኖርም : አፈር እስክትገባ የሚከተልህም ታማኝ የ መስቀሉ ዩሐንስን መሳይም ወዳጅም አይኖርህም : አለምም ሰዎችም ምህዋራቸውን አይለውጡም : ምናልባት ትኩስ ዘለላ እምባ ይፈስልህ ይሆናል!
ሞትህ ልክ እንደ ኑረትህ አያስገርምም : አያስቆጭም : እንዳልተፈጠርህ ሁሉ ነበር ትባላለህ!@ourrthought
❤10🔥4😭1
Armenian Duduk on Yanni ...
George Kapoyan
ይህች የ ያኒ የመድረክ የ አርመኒያ Duduk በጣም የምታሳሳና ወደ ጥንት የምትመልስ ናት
ለመብሰልሰል ከራስ ጋር ወደ ውስጣቹህ ለመጥፋት ስታስቡ የምትደመጥ አይነት ናት
@ourrthought
ለመብሰልሰል ከራስ ጋር ወደ ውስጣቹህ ለመጥፋት ስታስቡ የምትደመጥ አይነት ናት
@ourrthought
👍4❤2🤔1
ሐሳቦቻችን
Photo
ሀገርና ትርክት
@ourrthought
ስለ አድዋ ታሪክ ማውራቱ ምን ይበጃል የራስህን ዘመን ታሪክ ካልሰራህ? የሚል ብሂል በቅርቡ እንደ ፋሽን የሚስተዋል የዘመኑ ብሂል ሆኗል። ምናልባት የታሪክንና የትርክትን ጥቅም ያለማወቅ እንደሆነ ግልፅ ነዎ።
ትርክት (myth) በሁለት መንገድ ሊከፈል ይችላል። የመጀመሪያው በታሪክ ያልተደረገ ክስተት ላይ (utopianism idea) ላይ መሠረት ያደረገ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ አፄ ኃ/ሥላሴ እንደቆሙበት አይነት ትርክት ሥዩመ እግዚአብሔር ብለው እራሳቸውን እንደሚሰይሙት። ወይ እንደነ ጀርመን ያሉ ሀገራት የ Aryan ዘር እያሉ ልዩ ህዝብ ነን የሚል ትርክት ሊሆን ይችላል። ሁለተኛው አንድ የታሪክ ክስተት ላይ ተመስርቶ የሚነገር ታሪክ ላይ መሠረት ያደረገ ሊሆን ይችላል።
በርግጥ ወደ ኋላ ወደ ብዙ ዘመን ብትመለስ ሀገር የቆመው በ ትርክትና በ ታሪክ መሆኑን ትገነዘባለህ። የሰው ልጅ ስልጣኔን ሳይቀዳጅ በፊት ቴክኖሎጂን ሳይፈበርክ በፊት ህላዌነትን (existence) ፣ ባህልን ፣ ስነ-ምግባርን ፣ ተፈጥሮን ፣ ፈጣሪን ሁሉንም ነገር የሚመረምርበትና የሚያነፅርበት መስኮቱ በ ተረት ወይ ትርክት (myth) እና ታሪክ ነበሩ።
ወደ ጥንቷ እንኳ ብትመለከት ሀገራቸውን እንደ ሀገር ለማቆም የተጠቀሙበት የ አማልክቶቻቸውን የነ ራሙለስ ዙውስ ትርክት ነበር የተጠቀሙት።
እዚህቺው አፍሪካ እንኳ ናይጄሪያ በቺኑዋ አቼቤ Things fall apart በሚለው ልቦለድ ለሀገራዊ አንድነትና ቅኝ ግዛትን እንድትታገል እረድቷታል። የትኛውም ሀገር ብትሄድ ትርክት አላቸው።
Carl Jung Archetype and unconscious vol ላይ በሰፊው የሚያትትበት መፅሐፉ ላይ ትርክት (myth) የሰውን ልጅ የጋራ ድብቁን የ አዕምሮ ክፍል (collective unconscious) የሚዘውርና የሚቀርፅ ነው። ይህን የሰውን ልጆች የጋራ ስነ ልቦና በብዙ መልኩ ይቀርፁታል ይላል። ለምሳሌ የጀግና ምስል (Hero archetype) የትም ሀገር ብትሄዱ የሚያመሳስለው ነገር አለ። እራሱን ለሌሎች የሚያስቀድም ፣ ለእውነት የሚሰዋ ፣ ለሀቅ የሚዋደቅ የሚል መልክ አለ። በፊልም በልቦለድ የምናያቸው ዋና ገፀ ባህሪያት (protagonist) ሁላችንንም የሚያስማሙን ለዛ ነው። ድብቁ የ አዕምሮዋችን ክፍል ውስጥ የጀግና ምስል አለን።
የትርክትን ጉልበት ለማየት የትም እሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ እዚሁ ሩዋንዳን ማየት በቂ ነው። በትንሽዬ ትርክት ብዙ ሰው የረገፈበት። እነ ጀርመን እራሳቸው በፈጠሩት ትርክት ነው 5 ሚሊዮን ጂዊሾችን የጨፈጨፉት። እኛም ሀገር የምናየው ትርክት አለ። ምንሊክ ጡት እና እጅ ቆረጠ እየተባለ አንድ ልቦለድ ላይ ባለ ታሪክ በእውቀቱ እንዳለው አንዲት መንገድ ላይ ካገኛት አሮጊት ሰምቶ የፃፈውን ቅዥቢ መፅሐፍ የትርክት ሀውልት ቆሞለት ምን ያክል እንደምንጫረስበት ግልፅ ነው። ትርክትን ማቅለልና ማየት የለብንም።
እኛ ትርክት ለመፍጠር ልቦለድ አያሻንም ከበቂ በላይ የሆነ ጥሩ ትርክት መሆን የሚችሉ ታሪኮች አሉን። አድዋ አንዱ ነው። አድዋ የኢትዮጵያና የ ጣሊያን የጦርነት ታሪክ ብቻ አይደለም። የ እኩልነት ምሳሌያችን ነው። ከ አድዋ በፊት የነጭ የበላይነትና የጥቁር የበታችነት ትርክት (myth) ነበር የነበረው። አድዋ ይሄን የነጭ የበላይነት (white supremacy) የሰበረበትና የሰው ልጆችን እኩል ያደረገ ታሪክ ነው። አድዋ የጥቁር ድል ነው ከሁሉ በላይ ሀበሻ ስነ ልቦና ውስጥ ያለ መገዛት ፣ ለባርነት እምቢ ባይነትን በስነ ልቦናችን ያተመ ደማቅ ታሪክ ነው። በ Jung እሳቤ ካየነው የ ጀግና ምስል (Hero archetype) የሰራልን ነው። ሰው ለሰው የተሰዋበት ፣ የአባቶቻችንን ፍቅርን የምናይበት የታሪክ መስታወታችን ነው ፣ ሰው ለሰው ሲል ሞትን የተጋፈጠበት ነው ከዛም ከፍ ሲል የሀበሻና የ እምነቱን ቁርኝንት የምናይበት የጊዮርጊስን እረዳትነት የምንዘክርበት ከሀይማኖት በላይ ፈጣሪና ኢትዮጵያ ያላቸውን ትስስር የምናይበት ነው። አድዋ ትልቅ የጋራ ደመ ነብሳችን ላይ የታተመ እምቢ ባይነት ስነ ልቦና ነው።
በርግጥ አለማየሁ ዋሴ እንዳለው "እኛ ታሪካችን የከበደን ህዝቦች ነን" ታሪክ መስራት ይቅርና በታሪካችን እንኳ አንድ መሆን ያልቻልን ህዝቦች ነን። አድዋ ከኛ አልፎ ለአለም ህዝብ እኩልነትን የሰውን ክብር ያሳየ ደማቅ ታሪክ ቢሆንም ለኛ ግን የፀባችን ምንጭ ሆኗል። ይህ የሚያሳየው የሀሰት ትርክት ምን ያክል ቦታውን እንደያዘው ነው። በታሪክ የሚስቅና የሚያላግጥ ትውልድ ፈጥረናል የታሪክንና የትርክት ጥቅም የተገለጠልን አይመስልም። ዛሬ አድዋን ማሰብ አሳፋሪ ነገር መስሏል ፣ የምኒልክን ስም መጥራት የሚያሸማቅቅና ፣ የሚያስከስስ ድርጊት ሆኗል ትርክቱ በተቃራኒው ሀገር ከመስራት ይልቅ ሀገራችንን ማፍረሻ ሆኗል። ሮፍናን እንዳለው የነሱን አድዋ ብናሸንፍም የኛን አድዋ ተሸንፈናል።
እኛ ግን ባንድነት ለመቆም ልቦለድ ፣ ፊልም ፣ ተረት ፣ የሀሰት ትርክት አያሻንም ነበር። የተቆለለ የታሪክ ትርክት ሞልቶልን ነበር። አልታደልንምና ታሪካችንን ለአንድነት ከመጠቀም ይልቅ መበሻሸቂያችን አድርገነዋል። ከመ አርዮስ ዉጉዝ!
@ourrthought
❤11
ላለፉት ሦስትና አራት አመታት ለማውቃቸውና የስልኬ መዝገብ ላይ ላሉ ሰዎች ሁሉ ከላይ እንዳሉት መልእክቶች መልካም አድዋ የሚል መልእክት እልክ ነበር።
ዘንድሮ እስኪ ከነሱይምጣ ብዬ ብጠብቅም ምንም መልክት እንኳን አደረሰህ የሚል ሰው የለም። ከዚህ የተማርኩት ነገር አድዋ ከመከበሩ ይልቅ አድዋ ሰኞ መከበሩ ከስራና ከትምህርት ስለመቅረቱ በማሰብ የሚደሰተው ነው የሚበልጠው።
@ourrthought
ዘንድሮ እስኪ ከነሱይምጣ ብዬ ብጠብቅም ምንም መልክት እንኳን አደረሰህ የሚል ሰው የለም። ከዚህ የተማርኩት ነገር አድዋ ከመከበሩ ይልቅ አድዋ ሰኞ መከበሩ ከስራና ከትምህርት ስለመቅረቱ በማሰብ የሚደሰተው ነው የሚበልጠው።
ምድረ ሶላቶና ባንዳ
@ourrthought
😁13
Esubalew_Yetayew(የሺ)_-_Heyaw_Sem(ህያው_ስም)_-_New_Ethiopian_Music_…
<unknown>
ህያው ስም
እስሱባለው ይታየው ቆንጆ የ አርበኛ ዘፈን ነው ከ ጂጂ ቀጥሎ።
የናንተንም ቆንጆ ዘፈን ካላቹህ ሀሳብ መስጫ ላይ ብታስቀምጡት እንሰማዋለን።
@ourrthought
እስሱባለው ይታየው ቆንጆ የ አርበኛ ዘፈን ነው ከ ጂጂ ቀጥሎ።
የናንተንም ቆንጆ ዘፈን ካላቹህ ሀሳብ መስጫ ላይ ብታስቀምጡት እንሰማዋለን።
@ourrthought
👍3❤1
መዝረክረክ
ፀሀይ የለበለበው ቀይ መልክ ፣ የተመሰቃቀለ ያልተበጠረ የተበታተነ ፀጉር ፡ ቀለም ያልዳበሰው ገርበብ ያለ ከንፈር ፡ እንደነገሩ የተመሳቀለ ሻርፕ ፡ የተሸበሸበ ረጅም ቀሚስ የደፈረሱ አይኖች ከንፋሱ ጋር አብሮ የሚደንስ እግር አጣጣል ያለው አረማመድ ድንገት ባጠገቤ ስታልፍ አየኋት ምኗ ነው ልቤን የገዛው? ቀልቤን የሳበው የትኛው ያጌጠው መልኳ ነው?
በውበታቸው አምልኮን የሚሹ ውዳሴ ከንቱ አጋያጮች እንኳ እድሜ ዘመናቸውን ቢለፉ እሷን የሚደርሱ አይመስለኝም። ተዝረክርኮ ተጎሳቅሎ ማማር እንዴት ተቻላት። ተመሰቃቅሎ ያልጎደለበት ያማረ መልክ። እንጃ ብቻ ተዝረክርካም ሙሉ ናት።

🔥7✍3❤1👍1
ሐሳቦቻችን
Photo
የሁለት ሊቆች ወግ
@ourrthought
እ.ኤ.አ 24/06/1907 ዓ.ም Sigmund Freud እና Carl Gustav Jung ለመጀመሪያ ጊዜ በ Freud ቤት በ Vienna የተገናኙበት ወቅት ነው። እነዚህ ሁለት ሰዎች ሲገናኙ የመጀመሪያቸው ቢሆንም ያለምንም እረብሻና ማቋረጥ ለ 13 ሰዓታት ቁጭ ብለው ነበር ያወሩት። ይህ ንግግር ስለ ሰው ልጅ አዕምሮ ውስብስብነት ስለ ስነ ልቦና (psychology) የሚያትት ወሬ ነበር። Freud የዛኔ ጎልማሳና psychoanalysis theory ያሳወቀበት ወቅት ነበር። Jung በ Zurich ከተማ የ ሳይካትሪ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ወጣት ነበር።
Jung በ አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ስለ ሁኔታው ሲያወሳ
"I just paid a visit to him in Vienna then we talked for 13 hours without interruption. We didn’t realize that we were almost dead at the end of it, but it was tremendously interesting. He was the old man and had great experience and he was of course way ahead of me, and so I settled down to learn something."
ታዲያ Freud ዩንግን እንደተመለከተው ቀላል ሰው እንዳልሆነ ካወሩም በኋላ ያለውን ምልከታ በማየት ተደሟል። ወዲያውም የ ራሱን ሀሳቦች እንዲያስቀጥልለት እና የ psychoanalysis theoryን ከሱ ተቀብሎ ወደፊት እንደሚያራምድለትም የተማመነበት ሰው ነበር። Jung ከ Freud በ 20 አከባቢ በ ዕድሜ ማነሱና የ psychiatry ባክግራውንድ ያለው በመሆኑ ለሱ theory ተቀባይነት ጥሩ መሆኑንም ያውቀው ነበር። በዛ ላይ Jung ትጉህ ፣ ታታሪ ፣ የማይሰለቸው ፣ አዋቂ ነው። ከዛ ከ Vienna ግንኙነት በኋላ በ አጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ ብዙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደብዳቤዎችን ተላልከዋል። እነዛ ደብዳቤዎች በ ሳይኮሎጂው ዘርፍ የ psychoanalysis ጥናትን ለማከናወን ዛሬም ድረስ ያገለግላሉ።
ታዲያ እንዲህ እንዲህ እያለ ግንኙነታቸው ቢያድግም የ psychoanalysis theory ን ለማስፋፋት የጋራ ሀሳብ የነበራቸው ቢሆንም በ አንድ አንድ የሀሳብ ልዩነቶች ግን Jung ቅሬታዎች ነበሩት ከ ፍሩይድ ጋር የማይስማማባቸው። ይህን ቅሬታውን ለረጅም ጊዜ ግን በውስጡ ይዞት ነበር።
Jung በ Freud ሀሳብ ከማይስማማበት አንዱ በ Freud የ Sexual theory ነው። ሰዎችን ከ ጀርባ ሆኖ የሚመራው Libido የሚባለው የ ወሲብ ሀይል ነው ብሎ ነበር የሚያምነው። ሰዎች በዚህ ሀይል ግፊት ነው የሚመሩት ይሄም ከወሲብ ጋር የተያያዘ ነው እሱም ሀይል ደስታን ወደ ማግኘት (will to pleasure) ነው የሚመራው ይህ ሀይል ደሞ ሊቢዶ (Libido) ነው ብሎ ያምን ነበር። Jung የውስጣዊ ሀይልን Libido ከ ወሲብ ስሜት እና ከ ደስታ ስሜት በላይ እንደሚያየውና ይህ ሀይል ለፈጠራ ፣ እራስን ለመመርመር ፣ የመንፈሳዊ ህይወትን ለመፈተሽ እና የህይወትን አላማ የሚወክል ነው የሚል እሳቤ ነበር የነበረው። ታዲያ Jung ይሄን ሀሳብ በውጡ ያብሰልስለው እንጂ አውጥቶ አይሞግተውም ነበር። ያው ጋሼ ፍሩድ ይቆጣሉና።
ሌላው የሚያጋጫቸው ጉዳይ James በፃፈው article ላይ lay analyst ነው ይለናል። Lay analyst ማለት አንድ ሰው ምንም የ psychiatry background የህክምና ምሩቅ ሳይኖራቸው የ psychoanalytic ስራን የሚሰሩ ሰዎችን የሚመለከት ነበር። Jung ያለ medical degree እንዲሰራ የማይፈልግ ሲሆን Freud ግን አጫጭር ትምህርቶችን በመከታተልና ከህይወት ልምድ እንዲሁም ከብዙ የ psychoanalysis ንባቦች ተምሮ ቢሰራ የማይቃወም ነበር።
እንዲህ እንዲያ እያለ ግንኙነታቸው ባንዳንድ ጉዳዮች እየተለያዩ ቢመጡም Jung "The psychology of the Unconscious" ብሎ ባሳተመው መፅሐፍ አባት Freud ተቆጥተው ግንኙነታቸው ከወዳጅነት ይልቅ የስራ ብቻ እንዲሆንና የቀደመ ግንኙነታቸው እንደተቋረጠ ለ Jung የፃፉለት ደብዳቤ ያሳያል። በርግጥ አባት Freud ይሄን መፅሐፍ Jung ሲያሳትም ሊሰሩ ባሰቡት የ psychoanalysis theory በአለም ማሳወቅና ማስፋትን የሚጣረስ theory በመሆኑ አባት Freud ተካድኩኝ ያሉበት ሁኔታ ነበር።
በ " Psychology of the Unconscious" ላይ Jung አፅንዖት ሰጥቶ የፃፈው ነገር የሰውን ልጅ ድብቅ አዕምሮ ነው። Freud Unconscious mind ማለትም ድብቁ የሰውል ልጅ አዕምሮ የሰው ልጅ ከተወለደ በኋላ የሚያጎለብተውና የማህበረሰብ የተከለከሉ ህግጋት ፣ ብዙ ጊዜ የማይጠቀምባቸው ፣ የማህበረሰቡ ፀረ ህግጋቶች ፣ የታፈኑ ስሜቶች ባጭሩ የተረሱ ነገሮችና መጥፎ ነገሮችና የተከለከሉ ነገሮች የሚታጨቁበት መጋዘን ነው የሚል ማብራሪያ ነው ያለው።
Jung ግን Unconscious mindን የሚያየው ከዚህ ለየት ባለ መንገድ ነው። መጋዘን ሳይሆን ከዛ የጠለቀ የሰውን ልጅ የጋራ ደመ ነብስ የሚያንቀሳቅስ ነገሮችን ከማጠራቀም በዘለለ የ ሰው ልጅ ልክ በዝግመት በ evolution እንደመጣውና አሁን ያለበትን አቋም እንደያዘ ሁሉ ይህ ድብቁም የአዕምሮአችን ክፍል ከ ጥንት የሰው ልጅ መነሻ ጀምሮ በ evolution ከ ጥንት የሰው ዘር የወረስነው የሰው ልጅ ሁሉ የጋራ የንቃት ህሊና ነው እንጂ ከተወለደ በኋላ የሚመጣና ትውስታና የተከለከሉ ነገሮችን ብቻ የሚያጭቅ አይደለም ብሎ ያምናል። ይህን ለማወቅ ደግሞ የሚነገሩ ትርክቶች እና ተረቶች አስረጅ ናቸው ብሎ ይሞግታል። ሁሉም ሀገር ብትሄዱ የሰውን ልጅ ድብቁ የ አዕምሮ ክፍል ውስጥ የተቀመጠ ከ አያቶቻችን የወረስነው ስንወለድ ጀምሮ ደመነብሳዊ ዕውቀት አለን ይላል። ተረቶችን ፣ ንግርቶችን ብትመለከቱ ስለ ጀግና የሚተረቱ ስለ ሴጣን ወይም ስለ ህላዌ ተመሳሳይ ተረቶችን ነው ይህም የሚያሳየው ስንወለድ ጀምሮ ከጥንት አያቶቻችን በ evolution ሂደት የወረስነው ስንወለድም ያለ እውቀት አለን በደመነብስ የሚያግባባን የሚል ነጥብ የያዘ ነው።
ሌላው የሚለያቸው ነጥብ ህልም ላይ ያላቸው እሳቤ ነው። ህልምን የሚያዩበት መንገድም ለየቅል ነበር። Freud ህልምን wishful thinking ነው ብሎ ይገልፀዋል የተደበቁ የ ድብቁ አዕምሮ እራሱን የሚገልጥ ሰው በውን ያጣውን ፍላጎት የሚያሟላበት ሂደት ነው ቁም ነገር የለውም ብሎ ያስባል። Jung ደግሞ ህልምንም የሚያየው ከዛ በላይ ከተፈጥሮ የሚመጣ ወይም ደግሞ ህይወታችን ላይ የሚከሰቱትን ነገሮች ማወቂያና የነብስ ጥሪ የሚመረበት ከተራ ምኞትና እንቶፈንቶ በላይ ቁም ነገር ያዘለ ነገር ነው ብሎ ነው።
ለመጨረሻ ጊዜ ሲለያዩ ያጋጠማቸውን ነገር አውስቼ ልጨርስላቹ
ወደ መለያያቸው አከባቢ እ.ኤ.አ 1909 በ America New York City የእግር መንገድ እናደረጉ የሆድ የሆዳቸውን ስለ ስነልቦና እየጠረቁ ባሉበት ወቅት ጋሼ Freud ፌንት ይገጩና ልብሳቸው ላይ ሽንታቸው ያመልጣቸዋል። ከዛ ከነቁ በኋላ ስለ ጉዳዩ አንስተው ማታ ባዩት ህልም ተረብሸው እንደነበረ ለ Jung ያወሩታል ይህም የተከሰተው ከዛ ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ሲነግሩት Jung ህልሙን ይጠይቃቸዋል። Freud ግን ሊነግረው አልፈለገም። ጉዳዩን ሊነግረው እንደማይፈልግና አለቅነቱንም የሚንድ ስለመሰለው።@ourrthought
👍4❤2👏2
Jung የዛኔ ስለ ህልም የነበረው ምልከታ ለየት ስለሚል ከህልሙ ባሻገር ያለውን የ ስነ ልቦና ችግር ለማወቅና ለመርዳት የፈለገ ቢሆንም ጋሼ ግን ህልማቸውን መናገራቸውንና ያላቸውን የበላይነት እንዳይናድ ፈርተው ነበር።
እንደ መውጫ ሳጠቃልለው ሁለቱም በየ ፊናቸው ታላላቅ የስነ ልቦና ግኝት ያላቸውና አለም አሁን ለደረሰበት የ ስነ ልቦና ምርምር ቁልፍ ሰዎች ናቸው። ቢሆንም አለም ለ Freud የሰጠችውን ቦታ ለ Jung ሰጠችው ብዬ አላምንም። ቢሆንም የነዚህ ሰዎች ግን መለያየት አዳዲስ ሀሳቦችን Jung በነፃነት እንዲፅፍ አግዞታል። አሁን ላይ የ Jung ሀሳቦች ከበፊቱ የበለጠ እየተፈተሸ የመጣበት ጊዜ ነው ከ Freud ይልቅ። ብቻ ለሁለቱም ባሉበት ይመቻቸው። ለሰው ልጅ ትልቅ ውለታ ውለዋልና።
@ourrthought
👍8
The Homeless Wanderer
Tsegue-Maryam Guebrou
Title : The homeless wonderer
Artist : Emahoy Tsegemariyam Gebru
የሴቶችን ቀን በማስመልከት የ እማሆይ ፅጌ ማርያም ገብሩ ዘፈን ልጋብዛቹህ ወደድኩ። ለምን የሳቸውን ካላቹህ ህይወታቸው አስደናቂ ስለሆነ ነው። መነኩሴ ናቸው ግን ደግሞ ከ ሙዚቃ ፍቅር ያገዳቸው አልነበረም። በሀገራችን የመጀመሪያዋ ሴት ፔያኒስት ይመስሉኛል።
አለም ያጨበጨበላቸው ነበሩ ነገር ግን የሳቸውን የሚጫወቱበትን የሙዚቃ መሳሪያ ለ ያሬድ ሙዚቃ ት/ት ቤት በአደራ መልክ ቢናዘዙም እሳቸው 2015 አከባቢ ሲያርፉ በ ታክስ ምክንያት ቤተሰቦቻቸው ፒያኖውን ለማስገባት ተወዶባቸው እንዳልገባ ሰምቼ ነበር። የሴቶች ቀን ሲከበር ምናልባት የኚህን ድንቅ የጥበብ ሰው ኑዛዜ ተፈፃሚ ሆኖ ቢሆን ማክበሩም ግቡን ይመታ ነበር። አስገብተውትም ከሆነ መልካም ነው።

🔥9👍2
ከረጅም ጊዜ በኋላ ከመፅሐፎቼ ውስጥ "የጨለማው ዓለም ህዝቦች
ሰላቢና እና ቡዳ" የምትል መፅሐፍ በተመስገን አጭቆ የተፃፈ መፅሐፍ ትላንትና ዛሬ ሳገላብጥ ትንሽ ያስገረመኝን ስለ ሰላቢና ቡዳ አነበብኩኝ።
የዚህች መፅሐፍ አዘጋጅ በ ሰላቢና ቡዳ ዙሪያ ለረጅም ጊዜ ምርምር (research) የሰራና እሱ እንደሚለው እራሩም ተጠቂ የነበረ በመሆኑ ለመረጃው እንደረዳው ነው። የተለያዩ ሀገሮችን የቁዳና የሰላቢ አይነትና ባህሪያት በደንብ ሰብስቦ ነው የፃፈው። መፅሐፉ ከተራ አሉባልታ ያለፈ በብዙ ምርምር የተፃፈ ነው።
በርግጥ እኔን ያስገረመኝ ፀሀፊው ሰላቢና ቡዳን ከ (Chakra) ጋር አያይዞ ያብራራበት መንገድ ነው። Chakra የህንዶች መንፈሳዊ ልምምድ ሲሆን በ አካላችን ላይ የሚገኙ ዋና ዋና የሚገኙ በዋናነት በ 7 ቦታዎች የሚመደቡ የመንፈሳዊ ፣ አዕምሮአዊ ፣ አካላዊ ንቃትን የሚጨምሩ ልምምዶች ናቸው። እኚህ ዋና ዋና 7 Chakra የሚገኙት በጀርባ አካላችን ከ ቂጣችን ብልታችን አከባቢ ተነስቶ (base chakra) እስከ መሀል አናታችን ዋናው (crown chakra) ድረስ የሚገኙ ናቸው። እኚህን chakra ለማብራት እና ለመክፈት እንደ ሜድቴሽን ኩንድሊኒ አዌክኒንግ በመጠቀም ሰዎች ከፍተኛ የሆነ መገለጥ ደረጃ ላይ ለመድረስ የሚያስችላቸው የ አብርሆትን መንገድ የሚያቀዳጅ መንገድ ነው።
እና ፀሐፊው እንደሚለው ከሆነ ቡዳ እና ሰላቢ ከሰዎች እኚህን chakra የመንፈስ መውጫ መውጫና መግቢያ በር በመምጠጥ በመጠቀም ነው ከሰዎች መንፈሳዊ ሀይላቸውን የሚወስዱት ይለናል። እኚህ ቻክራዎች የሰው ልጅ መንፈሳዊ ሀይላቸው የሚገኙባቸው ቦታዎች እንደመሆናቸው ቡዳ እና ሰላቢ ከሰዎች ላይ ይሄን ሀይል ይወስዱታል ይለናል። ቡዳና ሰላቢ ከሰዎች ላይ (Halo) የማየት አቅም አላቸው ይለናል። ይሄ ማለት ከፍተኛ ወይም ጥሩ የመንፈስ ሀይል ያላቸውን ሰዎች ልክ በ ቤ/ክርስቲያን ላይ እንደሚታዩት የቅዱሳን ስዕለ አድኖ ላይ በአናታቸው ዙሪያ የ ቢጫ አክሊል ያለ ምልክት ቡዳና ሰላቢ ከሰዎች ላይ መንፈሳዊ ሀይልን የሚለዩበት ቢጫ ክብ የመሰለ በግለሰቡ ላይ እንደዛ ሆኖ ይታያቸዋል ያም በቀላሉ የሚበሉትን እና የማይበሉትን ሰው መለየት ያስችላቸዋል ይለናል። ዘይገርም ነው። በቡዳና ሰላቢ የሚበላው ሰው በየቀኑ አሸን ነው የአንዳንዱ አንድ ቀን ይቆያል አንዳንዱ ይከርምበታል አንዳንዱ ይሞታል። ግን እነሱ ሰውን የመግደል ፍላጎት የላቸውም መንፈሳዊ ሀይሉን ግን ይፈልጉታል።
መፅሐፉ እኛ ከምናስበው መደበኛ የትርጉም የራቀና የረቀቀ ነው የቡዳና ሰላቢ ስራና ተንኮል ይለናል። ቡዳ ሰውን በአይኑ ጨረር ነው የሚበላው ሰላቢ የሰውን ገንዘብ ይሰልባል የሚለውን ወሬ የሚያሶሩት እራሳቸው ናቸው ባይ ነው። ለምን ብትሉ ትክክለኛ ስራቻው እንዳይታወቅ ማወናበጃ ዘዴያቸው ነው ባይ ነው። እንጂ ሰላቢም ቡዳም ከፈጣሪ ሀይል ማግኘት የማይችሉ የሴጣን ግብረ አበሮች በመሆናቸው ሀይል የሚያገኙት ከሰው ብቻ ሳይሆን ከመላው ፍጥረት ነው። ከሰው ፣ ከእንስሳው ፣ ከመሬት ፣ ውሀው ፣ መብረቅ ፣ ዛፍ ፣ ምግብ አረ ምኑ ቅጡ የማይበሉት የለም።
በዛ ላይ ቡዳ በአይኑ ብቻ ነው የሚባለው ውሸት ነው ይለናል። እንደሱ ጥናት ከሆነ ቡዳ አይን ለአይን ካየ ብቻ ነው ሊበላን የሚችለው። ግን ደግሞ ከዛም ሌላ መንገድ አለው ይለናል ለምሳሌ እናንተን በማውራት ፣ መልእክት በመላክ ፣ ደዘድምፃቹን በመስማት ፣ ፎቶ በማየት ፣ በመዳበስ በመሳሰሉት ይበሉናል። እና እንደ ፀሐፊው ገለፃ ከሆገ ቡዳ እና ሰላቡ ከ ፈጣሪ ፀጋ የተለዩ መንፈሳዊ ሀይላቸውን ከፈጣሪ ማግኘት የተሳናቸው እና በጎውን የፈጣሪ መንፈሳዊ ሀይል ከሰዎች የሚወስዱ ናቸው።
ከመፅሐፉ ቡዙ ያልዳሰስኩት አለ በዛ ላይ ግማሽ ንባብ ነው ያነበብኩት ስላላስቻለኝ ነው። ያጋራኋቹህ ምናልባት ከሸነጠኝ ሰፋ አድርጌ ልመለስበት ችላለሁ ከ 9 ክፍሎች እኔ 2 ክፍሎችን ነው ያጋራኋቹህ። ፈጣሪ ከቡዳ እና ሰላቢ ይሰውራቹህ።
@ourrthought
👍7❤2👏1
እኛና አምላክ
ለራሳችሁ አልቅሱ አይደለ ያልከን? ይሄው ለራሳችን እያለቀስን ነው። ፈቃዳችንን ሳትጠይቀን በራስህ ፈቃድ ስላመጣህን እያለቀስን ነው። በግጥሙ ድንገት ዱብ እንዳለው ኦማር ካያም ካመጣህን በኋላ ስለ አሁን፣ ስለ ዛሬ፣ ስለ ነገ ባለማወቃችን እያለቀስን ነው። መኖር ቅጣት ሆኖብን እያለቀስን ነው። ለራሳችን ባዕድ በመሆናችን እያለቀስን ነው። ባጭሩ ከልደት እስከ ሞት የኛ ፈቃድ ስለሌለበት እያለቀስን ነው። የማናውቀውን ሕይወት እየኖርን የማናውቀውን ሞት እንሞታለን።
እግዚአብሔርም በቃሉ በኩል እንዲህ ሲል መለሰልኝ። ያለ እውቀት በሚነገር ቃል ምክርን የሚያጨልም ይህ ማነው? እንገዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ እጠይቅሀለሁ አንተም ተናገረኝ ምድርን በመሰረትኩ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርክ? ታስተውል እንደሆነ ተናገር። በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋራ ይከራከራልን? እጠይቅሃለሁ አንተም ተናገረኝ በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን? አንተስ ፃድቅ ትሆን ዘንድ በኔ ትፈርዳለህን? እንግዲህ በፊቴ መቆም የሚችል ማነው? እመልስለት ዘንድ መጀመሪያ የሰጠኝ ማነው?
እኔም ተናገርኩ እነሆ ስለ ፍትህ ጠየቅኩህ; አንተ ግን ስለ ታላቅነትህ፣ ስለ ሁሉን ቻይነትህ፣ ስለ ሉአላዊነትህ ነገርከኝ። ያልጠየቅኩትን መለስክልኝ። አንተ ታላቅ ሰው ግን ታናሽ፣ ትቢያ፣ እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን ትነግረኛለህ። ሰውን አንተው ፈጥረኸው አንተው ትንቀዋለህ። ደካማ በመፍጠር ብርቱነት አለን? ሟች የሆነን ፍጡር በመፍጠር እኔ ግን ሕያው ነኝ ማለት ይቻላልን? ትንሽ ነገር በመፍጠር ታላቅነት አለን? እፍ ብለህ ልታጠፋው የምትችለውን ሰው በመፍጠር ሁሉን ቻይነት ይገኛልን? ወሰን የሌለው አምላክ ወሰን ባለው ሰው ላይ ኃይሉን ማሳዬቱ አስደናቂ ያሰኘዋልን? በደካማ ላይ መበርታት እንዴት ኃያል የሚል ማዕረግ ያሰጣል? እባክህ ተለመነን፣ ለዘለአለም እራራልን፣ እጅህን አታክብድብን፣ እኛን ከማጥፋት ተመለስ፣ በፈጠርከው የሰው ልጅ ላይ ግፍ አትዋልበት።
እግዚአብሔርም በቃሉ እንዲህ ሲል መለሰ። እንደ እግዚአብሔር ያለ ክንድ አለህን? ወይስ እንደሱ ባለ ድምፅ ታንጎዳጉዳለህን? በውኑ ከተወለድክ ጀምሮ ማለዳን አዘሀልን? ከሰማይ ሁሉ በታች ያለው ገንዘቤ ነው አለኝ።
ይሄው እንደምታዩት የእግዚአብሔር መልስ ጥያቄ ነው። ስጠይቀው መልሶ እኔኑ ይጠይቀኛል። ሰውንና እግዚአብሔርን አንድ የሚያደርጋቸው ይሄው ነው። ጥያቄ ጥያቄ ጥያቄ።
ከ ዮናስ ጎርፌ ስነ አመክንዮ podcast የተቀነጨበ
©ዳዊት ጸጋዬ

❤14
ከመንጋው እንደተበተነ ግልገል ከባህሩ እንደወጣ አሳ ባዕድነት ይሰማኛል። እግዚሀር ያለ ዘመኔ ከሰው ጫካ የጣለኝ ያኽል ይመስለኛል። እኔን በሚመስሉ ግን እንደኔ ባልሆኑ የሰው መንጋ መሀል ለብቻ የተወኝ ይመስል ፈጣሪ ላይ አቂሜበታለሁ። ዘመኔ አይጥመኝም ምርጫ ቢሰጠኝ ከዘመኔ ወደ ኋላ እልፍ አመታትን ብመለስ እሻለሁ አልያ ወደፊት ከብዙ ዘመን በኋላ ብፈጠርና ከዚህ ዘመን ባመልጥ እያልኩ አስባለሁ።
ህይወቴን ለመቀየር ተፍጨርጭሬ አላውቅም ልክ የውሀው ማዕበል እንደሚወስዳት ዳክዬ ዘመን ወደሚወስደኝ የህይወት አፅናፍ በዝምታ አዘግማለሁ። ለህይወቴ ግድ ማጣቴ ያስፈራኛል ኑሮዬን ለመቀየር አለመታገሌ የዘበትነት ስሜቴ ሁሉ እየሱስ ክርስቶስ ለጲላጦስ ያሳየውን የዘላለም ዝምታ ይመስለኛል። ህልም ማጣቴ ማለም አለመቻሌ በሸላቾቹ ፊት እንደቆመው የፋሲካ በግ በሩጫ ዘመን በዝግታ አዘግማለሁ።
ዘመኔ አጭር ይመስለኛል። እረጅም እድሜ እንደኖረ ሰው በወጣትነቴ አለም ያታክተኛል። 80 አመት ያለምንም ለውጥ እንዳሳለፈ አዛውንት ወደ ኋላዬ ስመለከት ይጨፈግግኛል። ዘመናትን ያሳለፍኩ ያህል ምድር አሰልችቶኛል። መብላት ፣ መተኛት ፣ መነሳት ፣ መኖር ፣ ለህልም መታገል ጠቢቡ እንዳለው የከንቱ ከንቱ አይደሉምን? ሰው ከኑረቱ ምን አትርፏል? ምናልባት ትዝታን። ከዚህ ሁሉ በኋላ ያለ ህልም መኖር ዘበትን መላመድ ባለሁበት መንቧቸቼን እንደ ምቾት መቁጠሬ ሁሉ እያስፈራኝ መጥቷል። ሰው ህይወቱን ለመቀየር ሲለፋ ሱሪ ለመቀየር አለመታገሌ ያስደነግጠኝ ጀምሯል። ምኑ ጋር ነው ከህይወት ጋር የተላለፍኩት? ለምንድነው በወጣትነቴ ያዛውንት ከንቱነት የተጫነኝ? መኖር የማያጓጓኝ? ያልሞከርኩት የማይማርከኝ?
ለመሞት ሦስት ቀን ይቀርሀል እንደተባለ ሞቱን ነጭ ጋውን ካደረገ መነጥር አጥላቂ ሾካካ ሰው እንደሰማ ጎልማሳ ሞቴን የምጠብቅ ይመስለኛል። ብር ብዬ ሰዎች ወደሌሉበት ወደ ጫካ ወደ በረሀ መጓዝ ያምረኛል ቅሉ ያለ ሰው መኖር የማይችል ደካማ አድርጎኛል። እንጃራ ብቻውን የማይቆርስ ፈሪ እንዴትስ ብቻውን ከሰው ተገሎ እንደ ባህታዊ ሊመንን ይቻለዋል?
ከእውነተኛ የግል ማስታወሻ

❤6😢6
እዛው ነኝ
አልጨመርኩም ክብደት ቁመት
አለወጥኩም ቀለም ውበት
አላወራሁ ከማንም ጋር
አልተሸሸኩ እምንም ጋር
እንደያኔው
ቀጠሮ እንዳስያሺኝ
መጣለሁ እንዳልሺኝ
እንደዛ ነኝ
ዘመናት ቢነጉድም
አለም ቢለወጥም
አኔ አልተለወጥኩም
አንቺን እንዳይከፋሽ
ላንቺ እንዳልጠፋሽ
Iinspired by Baheta G/hiwot music
እዛው ነኝ
12/07/2018 ዓ.ም
@ourrthought
አልጨመርኩም ክብደት ቁመት
አለወጥኩም ቀለም ውበት
አላወራሁ ከማንም ጋር
አልተሸሸኩ እምንም ጋር
እንደያኔው
ቀጠሮ እንዳስያሺኝ
መጣለሁ እንዳልሺኝ
እንደዛ ነኝ
ዘመናት ቢነጉድም
አለም ቢለወጥም
አኔ አልተለወጥኩም
አንቺን እንዳይከፋሽ
ላንቺ እንዳልጠፋሽ
Iinspired by Baheta G/hiwot music
እዛው ነኝ
12/07/2018 ዓ.ም
@ourrthought
❤5🔥1😢1
ጠብታ....
አሉ አንድ አንድ ሰዎች፤ በተስፋ መቁረጥ ከትቢያ ወድቀን ለመነሳት መፍጨርጨር ሲከብደን በቃላቸው የሚያድሱን። አሉ አንድ አንድ ሰዎች፤ ተካድን፣ የሚረዳ'ን አጣን፣ ዝምድና ግንኙነት ጓደኝነት ምንም አይሰራልንም ብለን እራሳችንን መሸከፍ ስንጀምር ከሩቅ ሆነው ምንም በማለት ውስጥ አለሁ የሚሉን። አሉ ደግሞ፤ በዚህ የሰቀቀን ባህር ውስጥ ስንዋዥቅ ሰልጥቆ የበላን የብቸኝነት፣ ሰውነት ላይ ተስፋ የመቁረጥ አሳ ነባሪ ባህርዳርቻው ላይ እስኪተፋን ዮናስነታችንን አስጠብቀው የሚያቆዩልን ሰዎች አሉ።
ተፈጥሮ ከውልደት እስከ ሞት በስቃይ ማዕበል ስታንገላታን ቆይታ የህይወታችንን መልህቅ ወደ ባህሩ እንዳንለቀው የምታባብልበት ሰዎች አሏት፤ ለጭካኔዋ ማስታገሻ ይመስል ከአንድ ጥግ አኑራ ከዘላለም ዝምታ እኛን የምታቅብበት አንድ አንድ ጠብታ ሰዎች አሉ።

ቺርስ ለነዛ ሰዎች!
@ourrthought
💊5👌3❤2🫡2