"...የሰው ልጅ ሁልጊዜ እንባ ውስጥ እንደዋኘ ነው። ነገር ግን በየጊዜው ከዋናው ወጣ እያለ ተጋድሞ የሳቅን ፀሐይ እንደሚሞቅ ደግሞ አትርሳ"
ዝም ብዬ አየሁት እውነቱን ነው።
"ሌላስ?" አልኩት
"እውነትን አታብዛ"
"ምን?"
" ህይወት ውስጥ እውነት ብቻውን አይገኝም። ህይወት እንደ ቡና በወተት ነው። ወተቱ እውነት ቡናው ውሸት ይሁን። ግን ይሄ ልዩነት ባንጎላችን ውስጥ ይኑር እንጂ ሲኒው ውስጥ በአንድ በኩል ቡናው በሌላው ወተት የለም። ሲኒው ውስጥ ያለው ቡና በወተት ነው። ህይወት ውስጥ በቀኝ በኩል እውነት በግራ በኩል ውሸት አይገኝም። ህይወት ውስጥ የምታገኘው የእውነትና የውሸት ቅልቅል ነው።"
ሌቱም አይነጋል
ስብሀት ገ/እግዚአብሔር
@ourrthought

❤13👍4👏1
ሐሳቦቻችን
Photo
ይሄን የመሰለ ፊልም እስከዛሬ አለማየቴ አስገርሞኛል። ፊልሙ እ.ኤ.አ በ 2002 የተሰራ ፊልም ነው። የፊልሙ አርዕስት Equilibrium የተሰኘ ነው። ፊልሙ በ totalitarian ላይ የተመሰረተ ነው። totalitarian ማለት አገዛዙ የፈቀደልህንና የወሰነልህን ገደብ መኖር እንደማለት ነው።
ፊልሙ ጭብጡን ያደረገው በ totalitarian ሀሳብ ላይ ሆኖ ስሜታችን feeling, sense and emotion የሚባሉት ነገሮች የማይፈቀዱበት እንደወንጀል የሚቆጠርበት ሀገረ መንግስት ነው። ለነገሮች ያለን ስሜት ነው ጦርነቶችና መገዳደሎችን ያስከተሉብን የሚል ሀሳብን በመያዝ የሀገሬው መንግስት ህዝቡ ሁሉ ምንም አይነት ስሜትን እንዳይሰማው በየቀኑ የሚወስዱት መድሀኒት ይሰጣቸዋል። በርግጥ ህዝቡ ግን ያን መድሀኒት ስሜታቸውን እንደሚገለው የሚያውቁት ነገር የለም መድሀኒቱን በየቀኑ በስረመንጅ መልክ መወጋት ግዴታቸው ነው እሱን ያላደረገ በሽብር ወንጀል ይከሰሳል የሞት ፍርድ ይፈረድበታል።
እዚህ ከተማ ውስጥ ምንም አይነት ስሜትን የሚቀሰቅስ ነገር ማድረግ አይቻልም እንስሳትን ማሳደግ አይፈቀድም የጥበብ ስራዎችን መመልከትም ሆነ በመፅሐፍ መልክ ማየትም መስማትም የተከለከለ ነው። ስዕል ፣ ሙዚቃ ፣ ጌጣጌጥ ፣ መስታወት ፣ ቤትን ማስዋብ....ምንም ከስሜት ጋር የተገናኘ ነገር ካደረጉ የስሜት ተጠርጣሪዎች (sense offenders) ተብለህ ትገደላለህ። ማልቀስ መሳቅ ማፍቀር ውጉዝ ናቸው።
ፊልሙ ሲጀምር የስሜት ተጠርጣሪዎችን በማሳደድ ሲጀምር ይታያል። ከዛም ሁሉንም ተጠርጣሪዎች ከገዱ በኋላ ቤት ውስጥ ያሉትን የጥበብ ስራዎች በሙሉ እንዲቃጠሉ ያዛል እዛ ቤት ውስጥ የሞናሊዛ ስዕልም አብሮ ሲቃጠል ይጀምራል። የዛ ከተማ ኗሪዎች ሚለብሱት ፣ የሚኖሩበት ፣ የሚመገቡት የሁሉም ተመሳሳይ ኑሮን የሚከተል ነው።
እና ባንድ ወቅት ዋና ገፅ በሀሪው የ ከተማዋ ኤጀንት clierk ጠዋት እንክብሏ ወድቃ ትሰበርበታለች ከዛን በኋላ ነገሮች ይሰሙት ይጀምራሉ። ለእንስሳ ፣ ለሚገላቸው ሰዎች ፣ ለነገሮች ስሜት ይሰማው ይጀምራል እያለ የሚቀጥል ፊልም ነው።
በርግጥ ይሄን ፊልም ሳይ የሰው ልጅ ለነገሮች ምንም የማይሰማው ከሆነ ከ አውሮ እንደሚብስና ሮቦት እንደሚሆን ያሳያል። ለልጅህ ለቤተሰብህ ለሰው ለ እንስሳ የማታዝን ከሆነ ለ ስነ ጥበብ ግጥም ሙዚቃ ቦታ ከሌለው ሰው ምንድነው? እንድትሉ የሚያደርግ ነው። ይሄን ፊልም አሁን ካለንበት ዘመን ጋር ብናመጣው ለነገሮች ስሜት ያጣበት ዘመን ላይ ነው። ይሄ ማለት በፊልሙ ላይ ያለውን አይነት ከተማ ለመምሰል ብዙ አንርቅም በመንግስት ጫና ሳይሆን አሁን የተጠናወተን አግበስባሽነት (consumerism) ጋር ይገናኛል። ፊልሙ ላይ ያለችው በየቀኑ የሚወስዷት ስሜት አልባዋ እንክብል እዚህ ዘመን ላይ አግበስባሽነት በሏት።
አሁን ላይ ሰው ደስታን ፍለጋ የማያግበሰብሰው ነገር የለም ግን ደስታ እንደ ሰማይ የራቀው ይመስላል። ከ 19 ነኛው ክፍለ ዘመን በኋላ materialism የገነነበት አለም ነገሮች በመሰብሰብ የሚያምን ከነገሮች ጋር ግንኙነቱ የተቋረጠ ብዙ ስዕል በቤቱ ቢደረደርም ስሜት ማግኘት የቸገረው ለስሜቱ ብዙ ርቀትም ቢሄድ ስሜት አልባ የሆነው postmodernism ዘመን ይሄ ፊልም ብዙ ጭብጥ ይሰጠናል። ስሜት ማጣት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ፊልሙን ኮምኩሙት። ፊልሙን ሀሳብ መስጫ ላይ አስቀምጥላቹሀለሁ
@ourrthought
👍10❤5
ከብዙ መጥፋት በኋላ ቴሌግራም ላይ ዛሬ ለመፅሐፍ ተነሳሳሁ። ለተወሰኑ ጊዜያት ፅሑፍ መፃፍ አቋርጬ ነበር። አንዳንዴ ነገሮችን በማድረግና ባለማድረግ መሀል ልዩነቱ ይጠፋብናል። ህይወት ላይ የምናደርገው ነገር ሁሉ ውሉ ይጠፋንና በማድረግና ባለማድረግ መሀል በመኖርና ባለመኖር መሀል ድንበሩ ይጠፋንና የህይወትን ነገር እንዳመጣጡ ለመቀበል በአብዘርድ እና ኒሂሊዝም በሚሉት እሳቤዎች መሀል እንቸነከራለን። ታዲያ ያኔ እንደ እንስሳ በደመነብስ ብቻ እንኖራለን።
ታዲያ ከብዙ ጊዜ በኋላ አንድ የግጥም መፅሐፍ ሳነብ ከዚህ በፊት በትንሹ ከላይ ካጋራኋቹህ ሀሳብ ጋር የምትሰናሰን አንዲት ሀሳብ ከ ሀብታሙ ሀደራ እንዲህም ያለም የለ ከሚለው የግጥም መድብል አግኝቼ ልንጨዋወትባት አመጣኋት። በመጀመሪያ ግጥሟን ላስነብባቹህ
አለመምረጥን መምረጥ፣ ቢቻል
ከጠዋት ጣይና ፥ ከጨረቃ ብርሀን?
ከፊያሜታና ፥ ከሸገሯ ሮማን?
እንዲህ ያለው ምርጫ
ድንቅ ነው እርግማን?
በረሀብ አይደለም
በሲዖል አይደለም
ፈጣሪ ሚቀጣህ
ምርጫ እየሰጠ ነው ፥ ደስታ የሚያሳጣህ።
ይህቺን ግጥም ሳነባት ታዲያ ደስ አለኝ ሀሳባቹሁን በግጥምና በዘፈኖች ተከሽኖ እንደማግኘት ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ? ብፅፈው ብፅፈው ላወጣው የማይቻለኝን ሀሳብ እንዲህ ቅልብጭ ብላ ማግኘት በረከት ነው።
ሀሳቧን ስንጨዋወትባት የዚህ አለም ሁሉ የሰው ልጅ መቃተት ይሄ የምርጫ መቸንከር አይደለም ወይ ያስብላል። በ ሳይኮሎጂ የሆነች ሀሳብ አለች Approach approach የምትሰኝ ይሄ ማለት በጣም ከምትወዱት ከሁለት ነገሮች አንዱን እንደመምረጥ ማለት ነው። ሁለት መንታ ወንድም ቢኖራቹህ አንዱን ምረጡ ብትባሉ የቱን ትመርጣላቹህ?
ከዚህ በፊት አንዲት መስመር ሀሳብ ፅፌ ነበር እንዲህ የምትሰኝ "የሰው ልጅ ለገዛ ነፃ ፈቃዱ ተላልፎ ተሰጥቷል" የምትል። እኛ ሰዎች ሁል ጊዜ ምን መምረጥ እንዳለብን ግራ እንደተጋባን ነው። ትላንት በመረጥነው ነገር ዛሬ እንበሳጫለን የምርጫዎችን እድል መብዛቱ ግራ እንዳጋባን አለ። ዛሬ ላይ አንዳንድ አውሮፓ ሀገራት የልጆቻቸውን ፆታ መምረጥ ባለመቻላቸው ህፃናቱ የራሳቸውን ፆታ እንዲመርጡ ምርጫ ይደረደርላቸዋል ይሄም ቀውስን ይፈጥርባቸዋል በየጊዜው እየቀያየሩፈ ግራ እስኪጋቡ ድረስ። ፈጣሪ ሲጣላ ብትር አይቆርጥም ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም ያሉት ከዚህ ተነስተው ይመስለኛል። ፈጣሪ በምትመርጠው ነገር ሁሉ ደስታህን ከነጠቀህ ቀውስ ውስጥ ትገባለህ።
የሰው ልጅ የውድቀቱ ምክንያት የምርጫው ውጤት ነበረች ግን ምርጫ ባይሰጠውስ ኖሮ? የሰው ልጅ ምርጫ ባይኖረውና በቃ ዝም ብሎ ለተፈጠረለት ነገር ኖሮ ቢሞትስ ምርጫ ባይሰጠው ኖሮ ያስብላል። ግን ደግሞ ምርጫው የደስታውም ምክንያት ናት ዛሬ ያልተመቸውን ነገር ነገ ደግሞ ይቀይራል ምርጫው በመብዛቱ ምርጫዎቹን በማሰስ ጉዞ ውስጥ ህይወት እንዳይሰለቸው ሆኗል። ይሄው ምኞቱ ደግሞ ምን መምረጥ እንዳለበት ግራ እያጋባው ደስታውን ይነጥቀዋል።
ልብስ ቤት ሄደህ ወይ ጫማ ልትገዛ ፈልገህ ቡቲክ ስትሄድ ግራ ትጋባለህ ምናልባት ሳትገዛ ልትመጣ ትችላለህ የምርጫ መብዛት ፍላጎትህን ያሳጣሀል። ግን ደግም የሆነ ሰው ጫማ ገዝቶልህ ዝም ብሎ ቢሰጥህ ከምትገዛው በላይ ደስ ይልሀል። አዕምሮህ ከምትመርጣቸው ነገሮች መሀል ያልመረጥከውን ያመለጠህን ነገር የተሻለ አድርጎ ያቀርብልሀል። ለዛም ነው ቡድሂስቶች ፍላጎትን በማጥፋት ምኞትን በመግታት ምርጫዎቻቸውንም አብረው በመቀነስ በትንሽ ነገር ደሰታ የሚያገኙት። አዕምሮአችን ለምርጫ ግራ ይጋባል። ከመምረጥ ይልቅ የተመረጠለት ነገር ላይ ይበልጥ ደስታ የሚሰማው።
ደሀ ምኞቱን በመቀነስ ሀብታም ይሆናል ይላል የማላስታውሰው ሰው ያ ማለት ምርጫው ይቀነስለታል ለዛ ነው ደሀ 1 ምርጫ ስለሌለው ያገኛትን አንድ ምግብ አጣጥሞ የሚመገበው ሌላ አማራጭ እንደሌለው ያውቃል በሷም ከመደሰት ውጪ አማራጭ የለውም። ገንዘብ ሲኖርህ ከምግቡ በላይ የምትበላበት ቤት ያሳስብሀል ከዛ ምን መብላት እንዳለብህ ያሳስብሀል። ከሳጥንህ ውስጥ የቱን መርጠህ መልበስ እንዳለብህ ግራ ትጋባለህ። ሁለት ልብስ ሲኖርህ አንዱ እስኪደርቅ ያቺኛዋን ለብሰህ ፈታ ነው። ይብላኝ ለኛ ምርጫዎቻችን በዝተውብን ምን መምረጥ እንዳለብን ለማናውቀው።

👏18👍1
ጣሊያኖች ሲተርቱ ምን ይላሉ መሰላቹህ
"La barba non fa il filosofo" ወደኛ ስናመጣው
" የጢምህ መንጀርገግ ፈላስፋ አያደርግህም" እንደማለት ነው።
ጥቅሱ ከምስሉ ጋር ዝምድና የለውም👐
@ourrthought
"La barba non fa il filosofo" ወደኛ ስናመጣው
" የጢምህ መንጀርገግ ፈላስፋ አያደርግህም" እንደማለት ነው።
ጥቅሱ ከምስሉ ጋር ዝምድና የለውም👐
@ourrthought
😁17
"ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት ወንድ አለ የሚያመነዝርና የማመንዘር እድሉን ያላገኘ!"
@ourrthought
ይህች የ በእውቀቱ ንግግር በቀልድ መልክ የቀረበች የስነ ምግባርን ፍልስፍና የምትዳስስ ሀሳብ ናት። በቀደም አጋርቻት ብዙዎች የ ፈገግታ ኢሞጂ ሲጠቀሙ አይቼ ልፅፍበት ተነሳሳሁ። በርግጥ ስታየው ያስቃል ስታስበው ግን ያብሰለስላል። የቀልድ የምትመስል ነገር ግን ከበድ ያለ ሀሳብ የያዘ ጥቅስ ነው።
ለምንድነው በምግባር የታጠርከው? ለምን ለሰዎች ጥሩ ትሆናለህ? ታማኝነትህስ ከየት የመጣ ነው? የሚለውን ጥያቄ የያዘ ነው።
አጋጣሚውን ያጣ የስነምግባር ሰውና አጋጣሚው ኖሮት በስነ ምግባር መታነፅ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ለምንድነው የበደሉህን የማትገድላቸው? ወይ መልሰህ የማትበድላቸው? እውን ምግባር ስላለህ ነው? ሀይማኖትህ ስለከለከለህ? ወይስ አቅሙን አጥተህ? የሆነ የሆነ ቦታዎች ላይ አቅሙን አጥተህ የተውከው ነገር በሰዎች ዘንድ ግን ባ ጥሩ ስነ ምግባር ያስብልሀል።
እዚህ ጋር የ አሪስቶትልን የ እረኛውን ወንድሙን ታሪክ ጋይጂን አንስቶ ስለ ስነ ምግባር ያወራናል። ጋይጂ እረኛ ነው ከ እረኛም የተዘነጋ እረኛ አይነት በሉት በሰዎች ዘንድ ሞኝ ጥሩ ስነ ምግባር ያለው እረኛ። ታዲያ ባንድ ወቅት ከዝናብ ለመጠለል በ አንድ ዋሻ ውስጥ ይገባል። ታዲያ እዚያ ዋሻ ውስጥ አንድ የጥንት ቀለበት ከ ጥንተ ቅሪተ አካል ላይ ያገኛል። ይሄኔ ጋይጂ ቀለበቱን ሲያጠልቅ ከሰው ዘንድ የሚሰውረው መሆኑንን አወቀ። ባለ ጥሩ ስነ ምግባሩ ጋይጂ ምን አደረገ አትሉኝም? ወዲያውኑ ወደ ቤተመንግስቶ ተሰውሮ ገባ ንጉሱን ገድሎ የንጉሱን ሚስት አገባት ወዲያውም ንጉስ ሆነ። ከዚህም ታሪክ አስከትሎ ምን ይላል መሰላቹህ አንተስ የጋይጂ አስማተኛ ከሰዎች የሚሰውር ቀለበት ብታገኝ ምን ታደርጋለህ ይልሀል። ትዘርፋለህ? ወይስ እንደድሮህ ትኖራለህ? ባንክ ቤት መዝረፍ? ስልጣን መገርሰስ? ወይስ እየተደበቅህ የሴት ገላ ልብሷን ስትቀይር ታያለህ? ምን ታደርጋለህ?
ከዚህ ታሪክ የምንረዳው በስነ ምግባር የታነፅን የመሰልነው አማራጭና አቅም የማጣት እንጂ በስነ ምግባር መኖሩ ፅድቅ እንዲሆንልን አይደለም እንደማለት ነው። የ በውቄም ጨዋታ እዚህ ትመጣለች እስከዛሬ ያለመነዘሩ ታማኝ የስነ ምግባር ሰው የተባሉት ዕድሉን አጥተው እንጂ እንደዛ ጋይጂ የመሰውሯን ቀለበት ቢያገኙ ምናልባት ዘወትር የሚመኟትን ሴት ከመግለጥ ስነ ምግባራቸው አይይዛቸውም ለማለት ነው። የኛ የምግባር መለኪያ የተዛባ ይመስላል። ዕድሉን አጥቶ ጨዋ የሆነና ጨዋነት ዋጋ እንዳለው አውቆ የታቀበን የምንለይበት መንገድ የለንም። ስለ ምግባርን ለስነ ምግባርነቱ ስትል የምታደርገው ነገር ይመስልሀል። የማትሰርቀው የሰውየው ላብ አሳዝኖህ ያልደከምክበትን ላለመንካት ነው ወይስ ብትያዝ እስሩና የሰው መጠቋቆሚያ ስለምትሆን? አንተ ታውቃለህ።
Carl Gustav Jung ሁላችንም የየግል ወይ የማህበረሰብ ጭንብል (persona or mask) አለን ይላል። በሰዎች ፊት የማናሳየው ጋጥ ወጥ ክፍል። እርስ በእርስ ስንገናኝ ወይ ከቤት ስንወጣ የምናጠልቀው ምግባረ ብልሹነታችንን ሸፈነን የምንወጣበት የጋይጂን ቀለበት የመሰለች ጭንብል አለችን። እሷን ገልጦ ላየን ግን አፈንጋጭነታችን አድፍጧል። እሷን ግን የሚገልጣት ብዙ ነገር ሊሆን ይችላል። ወይ ስልጣን ወይ ገንዘብ ለዛ ነው አንዳንድ ሰው ድንገት ገንዘብ ሲያገኝ ወይ ስልጣን ሲያገኝ የሚቀየረው ያደፈጠው ማንነቱ ብቅ ይላል ልክ እንደ ጋይጂ ቀለበት።
በውቄ ይሄን ፍልስፍና በቀልድ መልኩ ጣል አድርጎ ያለፈው ይሁን አንጂ ስትተነትነው ሰፊ ነገር ነው የያዘው። ብዙ ጊዜ በቀልድ መልኩ የሚያስተላልፈው መልእክት የሚደንቀኝ ሰው ነው። እና አንተን የስነ ምግባር ሰው ያደረገህ ምን ይሆን? ማህበረሰቡን ፈርተህ? ወይስ አቅሙን አጥተህ? ወይስ የምርም የስነ ምግባር መንገድ ጥሩ እንደሆነ አምነህ? መልሱን ለናንተ ትቼዋለሁ።
@ourrthought
👏11❤8👍2👎1
ነገረ ፖለቲካ ወ አፍሪቃ
እውነተኛ ክስተት ነው የምነግራቹህ
ስሟ በጠፋብኝ አንድ የ አፍሪካ ሀገር ባንድ ወቅት ምርጫ ሊደረግ ሽር ጉዱ ተጀመረ እና የመጨረሻው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ እጩ ተወዳዳሪ እስከዛሬ ያለውን ብልሹ አሰራርና ስርአት አልበኝነት እያነሳ እሱ ከተመረጠ ይሄን ችግር እንደሚፈታ ደሰኮረ ህዝቡም አዳነቀ ተደሰተ።
ከዛም ጠቅላዩ መሪ በመጨረሻ ቅስቀሳው ህዝቡን በ እስታዲዮም ሰብስቦ አንድ ንግግር አደረገ።
"ውድ ህዝቤ ሆይ አርፍሪካ ውስጥ አንድ መሪ የመጀመሪያው ምርጫ ላይ ለ ቤተሰቡና ለራሱ ይሰራል ህይወቱንም ይቀይራል። ቀጣዩ ምርጫ ላይ ደግሞ ለዘመዶቹና ለቅርብ ጓደኞቹ ህይወትና ለወጥ ይሰራል። በ ሦስተኛው ምርጫ ደግሞ አማራጭ ስለሌለው የቀረው ቤተሰብም ዘመድም ጓደኛም ስለማይኖር ለህዝቡ ለውጥ ይተጋል። በዛ መሠረት እኔ ቤተሰቤንም ፣ ዘመዶቼንም ፣ ጓደኞቼንም ለውጫለሁ አሁን ሦስተኛው ምርጫ ላይ ነኝ ለናንተ ከመስራት ውጪ አማራጭ የለኝም። ትኩረቴ ለናንተ ይሆናል። አይ ካላቹህ አዲሱን መሪ ምረጡና ቤተሰቦቹን ፣ ዘመዶቹን እና ጓደኞቹን ቀይሮ እናንተን እስኪይር መጠበቅ ትችላላቹህ።" ህዝቡም ለ ሦስተኛ ጊዜ መረጠው አማራጭ አልነበረውምና።
ሰሞኑን ለ አፍሪካ ጉባኤው ለመሪዎቹ ያለውን ወከባ ሳስተውል የ አፍሪካን ችግር የሚፈቱ ትላልቅ ልሂቃን እንጂ የ አፍሪካን ችግር የሚያባብሱ አልመስልኝ ብለውኝ ግራ ስጋባ ነበር።
ይሄ የ አፍሪካ መሪዎች ስብስብ በራሱ እንኳ መቆም ያልቻለ በ አውሮፓ ሀገሮች የሚደገፍ የመሪዎች ስብሰባ የ አፍሪካን ችግር ሳይሆን የሚፈቱት የ ሀበሻ ሴቶችን የቀሚስ ቋጠሮ እና ቀበቷቸውን ለመፍታት ነው ቋምጠው የሚመጡት። እናት አለም አፍሪቃ መምጫሽ ይናፍቀኛል ቻይው!

🔥5😁1😢1
ዳግም የተለጠፈች
@ourrthought
ብቻ ግን ይመስለናል
ይመስልሀል እንጂ : ሀዘንህ : ስሜት ማጣትህ : ተስፋ መቁረጥህ....ማንም ግድ ሰጥቶት አይብሰለሰልልህም!
ሞትህም ቢሆን ልክ ከአንድ ግዙፍ ግንድ ላይ አንድ ዘለላ ቅጠል ተበጥሳ እንደወደቀች ያህል : እንዲያው እንደነገሩ መሬት ማስ ማስ አድረገው ተጉድጓድ ይጨምሩል እንጂ ጠሀይም ብትሆን አምላኳን እንዳጣችበት ጊዜ አትጠልቅልህም : ጨረቃም ደም አትለብስም : ለሞትህ ከዋክብትም አይረግፉልህም : ስለ ሞትህም የሚቀደድ መጋረጃ አይኖርም : አፈር እስክትገባ የሚከተልህም ታማኝ የ መስቀሉ ዩሐንስን መሳይም ወዳጅም አይኖርህም : አለምም ሰዎችም ምህዋራቸውን አይለውጡም : ምናልባት ትኩስ ዘለላ እምባ ይፈስልህ ይሆናል!
ሞትህ ልክ እንደ ኑረትህ አያስገርምም : አያስቆጭም : እንዳልተፈጠርህ ሁሉ ነበር ትባላለህ!@ourrthought
❤10🔥4😭1
Armenian Duduk on Yanni ...
George Kapoyan
ይህች የ ያኒ የመድረክ የ አርመኒያ Duduk በጣም የምታሳሳና ወደ ጥንት የምትመልስ ናት
ለመብሰልሰል ከራስ ጋር ወደ ውስጣቹህ ለመጥፋት ስታስቡ የምትደመጥ አይነት ናት
@ourrthought
ለመብሰልሰል ከራስ ጋር ወደ ውስጣቹህ ለመጥፋት ስታስቡ የምትደመጥ አይነት ናት
@ourrthought
👍4❤2🤔1
ሐሳቦቻችን
Photo
ሀገርና ትርክት
@ourrthought
ስለ አድዋ ታሪክ ማውራቱ ምን ይበጃል የራስህን ዘመን ታሪክ ካልሰራህ? የሚል ብሂል በቅርቡ እንደ ፋሽን የሚስተዋል የዘመኑ ብሂል ሆኗል። ምናልባት የታሪክንና የትርክትን ጥቅም ያለማወቅ እንደሆነ ግልፅ ነዎ።
ትርክት (myth) በሁለት መንገድ ሊከፈል ይችላል። የመጀመሪያው በታሪክ ያልተደረገ ክስተት ላይ (utopianism idea) ላይ መሠረት ያደረገ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ አፄ ኃ/ሥላሴ እንደቆሙበት አይነት ትርክት ሥዩመ እግዚአብሔር ብለው እራሳቸውን እንደሚሰይሙት። ወይ እንደነ ጀርመን ያሉ ሀገራት የ Aryan ዘር እያሉ ልዩ ህዝብ ነን የሚል ትርክት ሊሆን ይችላል። ሁለተኛው አንድ የታሪክ ክስተት ላይ ተመስርቶ የሚነገር ታሪክ ላይ መሠረት ያደረገ ሊሆን ይችላል።
በርግጥ ወደ ኋላ ወደ ብዙ ዘመን ብትመለስ ሀገር የቆመው በ ትርክትና በ ታሪክ መሆኑን ትገነዘባለህ። የሰው ልጅ ስልጣኔን ሳይቀዳጅ በፊት ቴክኖሎጂን ሳይፈበርክ በፊት ህላዌነትን (existence) ፣ ባህልን ፣ ስነ-ምግባርን ፣ ተፈጥሮን ፣ ፈጣሪን ሁሉንም ነገር የሚመረምርበትና የሚያነፅርበት መስኮቱ በ ተረት ወይ ትርክት (myth) እና ታሪክ ነበሩ።
ወደ ጥንቷ እንኳ ብትመለከት ሀገራቸውን እንደ ሀገር ለማቆም የተጠቀሙበት የ አማልክቶቻቸውን የነ ራሙለስ ዙውስ ትርክት ነበር የተጠቀሙት።
እዚህቺው አፍሪካ እንኳ ናይጄሪያ በቺኑዋ አቼቤ Things fall apart በሚለው ልቦለድ ለሀገራዊ አንድነትና ቅኝ ግዛትን እንድትታገል እረድቷታል። የትኛውም ሀገር ብትሄድ ትርክት አላቸው።
Carl Jung Archetype and unconscious vol ላይ በሰፊው የሚያትትበት መፅሐፉ ላይ ትርክት (myth) የሰውን ልጅ የጋራ ድብቁን የ አዕምሮ ክፍል (collective unconscious) የሚዘውርና የሚቀርፅ ነው። ይህን የሰውን ልጆች የጋራ ስነ ልቦና በብዙ መልኩ ይቀርፁታል ይላል። ለምሳሌ የጀግና ምስል (Hero archetype) የትም ሀገር ብትሄዱ የሚያመሳስለው ነገር አለ። እራሱን ለሌሎች የሚያስቀድም ፣ ለእውነት የሚሰዋ ፣ ለሀቅ የሚዋደቅ የሚል መልክ አለ። በፊልም በልቦለድ የምናያቸው ዋና ገፀ ባህሪያት (protagonist) ሁላችንንም የሚያስማሙን ለዛ ነው። ድብቁ የ አዕምሮዋችን ክፍል ውስጥ የጀግና ምስል አለን።
የትርክትን ጉልበት ለማየት የትም እሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ እዚሁ ሩዋንዳን ማየት በቂ ነው። በትንሽዬ ትርክት ብዙ ሰው የረገፈበት። እነ ጀርመን እራሳቸው በፈጠሩት ትርክት ነው 5 ሚሊዮን ጂዊሾችን የጨፈጨፉት። እኛም ሀገር የምናየው ትርክት አለ። ምንሊክ ጡት እና እጅ ቆረጠ እየተባለ አንድ ልቦለድ ላይ ባለ ታሪክ በእውቀቱ እንዳለው አንዲት መንገድ ላይ ካገኛት አሮጊት ሰምቶ የፃፈውን ቅዥቢ መፅሐፍ የትርክት ሀውልት ቆሞለት ምን ያክል እንደምንጫረስበት ግልፅ ነው። ትርክትን ማቅለልና ማየት የለብንም።
እኛ ትርክት ለመፍጠር ልቦለድ አያሻንም ከበቂ በላይ የሆነ ጥሩ ትርክት መሆን የሚችሉ ታሪኮች አሉን። አድዋ አንዱ ነው። አድዋ የኢትዮጵያና የ ጣሊያን የጦርነት ታሪክ ብቻ አይደለም። የ እኩልነት ምሳሌያችን ነው። ከ አድዋ በፊት የነጭ የበላይነትና የጥቁር የበታችነት ትርክት (myth) ነበር የነበረው። አድዋ ይሄን የነጭ የበላይነት (white supremacy) የሰበረበትና የሰው ልጆችን እኩል ያደረገ ታሪክ ነው። አድዋ የጥቁር ድል ነው ከሁሉ በላይ ሀበሻ ስነ ልቦና ውስጥ ያለ መገዛት ፣ ለባርነት እምቢ ባይነትን በስነ ልቦናችን ያተመ ደማቅ ታሪክ ነው። በ Jung እሳቤ ካየነው የ ጀግና ምስል (Hero archetype) የሰራልን ነው። ሰው ለሰው የተሰዋበት ፣ የአባቶቻችንን ፍቅርን የምናይበት የታሪክ መስታወታችን ነው ፣ ሰው ለሰው ሲል ሞትን የተጋፈጠበት ነው ከዛም ከፍ ሲል የሀበሻና የ እምነቱን ቁርኝንት የምናይበት የጊዮርጊስን እረዳትነት የምንዘክርበት ከሀይማኖት በላይ ፈጣሪና ኢትዮጵያ ያላቸውን ትስስር የምናይበት ነው። አድዋ ትልቅ የጋራ ደመ ነብሳችን ላይ የታተመ እምቢ ባይነት ስነ ልቦና ነው።
በርግጥ አለማየሁ ዋሴ እንዳለው "እኛ ታሪካችን የከበደን ህዝቦች ነን" ታሪክ መስራት ይቅርና በታሪካችን እንኳ አንድ መሆን ያልቻልን ህዝቦች ነን። አድዋ ከኛ አልፎ ለአለም ህዝብ እኩልነትን የሰውን ክብር ያሳየ ደማቅ ታሪክ ቢሆንም ለኛ ግን የፀባችን ምንጭ ሆኗል። ይህ የሚያሳየው የሀሰት ትርክት ምን ያክል ቦታውን እንደያዘው ነው። በታሪክ የሚስቅና የሚያላግጥ ትውልድ ፈጥረናል የታሪክንና የትርክት ጥቅም የተገለጠልን አይመስልም። ዛሬ አድዋን ማሰብ አሳፋሪ ነገር መስሏል ፣ የምኒልክን ስም መጥራት የሚያሸማቅቅና ፣ የሚያስከስስ ድርጊት ሆኗል ትርክቱ በተቃራኒው ሀገር ከመስራት ይልቅ ሀገራችንን ማፍረሻ ሆኗል። ሮፍናን እንዳለው የነሱን አድዋ ብናሸንፍም የኛን አድዋ ተሸንፈናል።
እኛ ግን ባንድነት ለመቆም ልቦለድ ፣ ፊልም ፣ ተረት ፣ የሀሰት ትርክት አያሻንም ነበር። የተቆለለ የታሪክ ትርክት ሞልቶልን ነበር። አልታደልንምና ታሪካችንን ለአንድነት ከመጠቀም ይልቅ መበሻሸቂያችን አድርገነዋል። ከመ አርዮስ ዉጉዝ!
@ourrthought
❤11
ላለፉት ሦስትና አራት አመታት ለማውቃቸውና የስልኬ መዝገብ ላይ ላሉ ሰዎች ሁሉ ከላይ እንዳሉት መልእክቶች መልካም አድዋ የሚል መልእክት እልክ ነበር።
ዘንድሮ እስኪ ከነሱይምጣ ብዬ ብጠብቅም ምንም መልክት እንኳን አደረሰህ የሚል ሰው የለም። ከዚህ የተማርኩት ነገር አድዋ ከመከበሩ ይልቅ አድዋ ሰኞ መከበሩ ከስራና ከትምህርት ስለመቅረቱ በማሰብ የሚደሰተው ነው የሚበልጠው።
@ourrthought
ዘንድሮ እስኪ ከነሱይምጣ ብዬ ብጠብቅም ምንም መልክት እንኳን አደረሰህ የሚል ሰው የለም። ከዚህ የተማርኩት ነገር አድዋ ከመከበሩ ይልቅ አድዋ ሰኞ መከበሩ ከስራና ከትምህርት ስለመቅረቱ በማሰብ የሚደሰተው ነው የሚበልጠው።
ምድረ ሶላቶና ባንዳ
@ourrthought
😁13
Esubalew_Yetayew(የሺ)_-_Heyaw_Sem(ህያው_ስም)_-_New_Ethiopian_Music_…
<unknown>
ህያው ስም
እስሱባለው ይታየው ቆንጆ የ አርበኛ ዘፈን ነው ከ ጂጂ ቀጥሎ።
የናንተንም ቆንጆ ዘፈን ካላቹህ ሀሳብ መስጫ ላይ ብታስቀምጡት እንሰማዋለን።
@ourrthought
እስሱባለው ይታየው ቆንጆ የ አርበኛ ዘፈን ነው ከ ጂጂ ቀጥሎ።
የናንተንም ቆንጆ ዘፈን ካላቹህ ሀሳብ መስጫ ላይ ብታስቀምጡት እንሰማዋለን።
@ourrthought
👍3❤1
መዝረክረክ
ፀሀይ የለበለበው ቀይ መልክ ፣ የተመሰቃቀለ ያልተበጠረ የተበታተነ ፀጉር ፡ ቀለም ያልዳበሰው ገርበብ ያለ ከንፈር ፡ እንደነገሩ የተመሳቀለ ሻርፕ ፡ የተሸበሸበ ረጅም ቀሚስ የደፈረሱ አይኖች ከንፋሱ ጋር አብሮ የሚደንስ እግር አጣጣል ያለው አረማመድ ድንገት ባጠገቤ ስታልፍ አየኋት ምኗ ነው ልቤን የገዛው? ቀልቤን የሳበው የትኛው ያጌጠው መልኳ ነው?
በውበታቸው አምልኮን የሚሹ ውዳሴ ከንቱ አጋያጮች እንኳ እድሜ ዘመናቸውን ቢለፉ እሷን የሚደርሱ አይመስለኝም። ተዝረክርኮ ተጎሳቅሎ ማማር እንዴት ተቻላት። ተመሰቃቅሎ ያልጎደለበት ያማረ መልክ። እንጃ ብቻ ተዝረክርካም ሙሉ ናት።

🔥7✍3❤1👍1
ሐሳቦቻችን
Photo
የሁለት ሊቆች ወግ
@ourrthought
እ.ኤ.አ 24/06/1907 ዓ.ም Sigmund Freud እና Carl Gustav Jung ለመጀመሪያ ጊዜ በ Freud ቤት በ Vienna የተገናኙበት ወቅት ነው። እነዚህ ሁለት ሰዎች ሲገናኙ የመጀመሪያቸው ቢሆንም ያለምንም እረብሻና ማቋረጥ ለ 13 ሰዓታት ቁጭ ብለው ነበር ያወሩት። ይህ ንግግር ስለ ሰው ልጅ አዕምሮ ውስብስብነት ስለ ስነ ልቦና (psychology) የሚያትት ወሬ ነበር። Freud የዛኔ ጎልማሳና psychoanalysis theory ያሳወቀበት ወቅት ነበር። Jung በ Zurich ከተማ የ ሳይካትሪ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ወጣት ነበር።
Jung በ አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ስለ ሁኔታው ሲያወሳ
"I just paid a visit to him in Vienna then we talked for 13 hours without interruption. We didn’t realize that we were almost dead at the end of it, but it was tremendously interesting. He was the old man and had great experience and he was of course way ahead of me, and so I settled down to learn something."
ታዲያ Freud ዩንግን እንደተመለከተው ቀላል ሰው እንዳልሆነ ካወሩም በኋላ ያለውን ምልከታ በማየት ተደሟል። ወዲያውም የ ራሱን ሀሳቦች እንዲያስቀጥልለት እና የ psychoanalysis theoryን ከሱ ተቀብሎ ወደፊት እንደሚያራምድለትም የተማመነበት ሰው ነበር። Jung ከ Freud በ 20 አከባቢ በ ዕድሜ ማነሱና የ psychiatry ባክግራውንድ ያለው በመሆኑ ለሱ theory ተቀባይነት ጥሩ መሆኑንም ያውቀው ነበር። በዛ ላይ Jung ትጉህ ፣ ታታሪ ፣ የማይሰለቸው ፣ አዋቂ ነው። ከዛ ከ Vienna ግንኙነት በኋላ በ አጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ ብዙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደብዳቤዎችን ተላልከዋል። እነዛ ደብዳቤዎች በ ሳይኮሎጂው ዘርፍ የ psychoanalysis ጥናትን ለማከናወን ዛሬም ድረስ ያገለግላሉ።
ታዲያ እንዲህ እንዲህ እያለ ግንኙነታቸው ቢያድግም የ psychoanalysis theory ን ለማስፋፋት የጋራ ሀሳብ የነበራቸው ቢሆንም በ አንድ አንድ የሀሳብ ልዩነቶች ግን Jung ቅሬታዎች ነበሩት ከ ፍሩይድ ጋር የማይስማማባቸው። ይህን ቅሬታውን ለረጅም ጊዜ ግን በውስጡ ይዞት ነበር።
Jung በ Freud ሀሳብ ከማይስማማበት አንዱ በ Freud የ Sexual theory ነው። ሰዎችን ከ ጀርባ ሆኖ የሚመራው Libido የሚባለው የ ወሲብ ሀይል ነው ብሎ ነበር የሚያምነው። ሰዎች በዚህ ሀይል ግፊት ነው የሚመሩት ይሄም ከወሲብ ጋር የተያያዘ ነው እሱም ሀይል ደስታን ወደ ማግኘት (will to pleasure) ነው የሚመራው ይህ ሀይል ደሞ ሊቢዶ (Libido) ነው ብሎ ያምን ነበር። Jung የውስጣዊ ሀይልን Libido ከ ወሲብ ስሜት እና ከ ደስታ ስሜት በላይ እንደሚያየውና ይህ ሀይል ለፈጠራ ፣ እራስን ለመመርመር ፣ የመንፈሳዊ ህይወትን ለመፈተሽ እና የህይወትን አላማ የሚወክል ነው የሚል እሳቤ ነበር የነበረው። ታዲያ Jung ይሄን ሀሳብ በውጡ ያብሰልስለው እንጂ አውጥቶ አይሞግተውም ነበር። ያው ጋሼ ፍሩድ ይቆጣሉና።
ሌላው የሚያጋጫቸው ጉዳይ James በፃፈው article ላይ lay analyst ነው ይለናል። Lay analyst ማለት አንድ ሰው ምንም የ psychiatry background የህክምና ምሩቅ ሳይኖራቸው የ psychoanalytic ስራን የሚሰሩ ሰዎችን የሚመለከት ነበር። Jung ያለ medical degree እንዲሰራ የማይፈልግ ሲሆን Freud ግን አጫጭር ትምህርቶችን በመከታተልና ከህይወት ልምድ እንዲሁም ከብዙ የ psychoanalysis ንባቦች ተምሮ ቢሰራ የማይቃወም ነበር።
እንዲህ እንዲያ እያለ ግንኙነታቸው ባንዳንድ ጉዳዮች እየተለያዩ ቢመጡም Jung "The psychology of the Unconscious" ብሎ ባሳተመው መፅሐፍ አባት Freud ተቆጥተው ግንኙነታቸው ከወዳጅነት ይልቅ የስራ ብቻ እንዲሆንና የቀደመ ግንኙነታቸው እንደተቋረጠ ለ Jung የፃፉለት ደብዳቤ ያሳያል። በርግጥ አባት Freud ይሄን መፅሐፍ Jung ሲያሳትም ሊሰሩ ባሰቡት የ psychoanalysis theory በአለም ማሳወቅና ማስፋትን የሚጣረስ theory በመሆኑ አባት Freud ተካድኩኝ ያሉበት ሁኔታ ነበር።
በ " Psychology of the Unconscious" ላይ Jung አፅንዖት ሰጥቶ የፃፈው ነገር የሰውን ልጅ ድብቅ አዕምሮ ነው። Freud Unconscious mind ማለትም ድብቁ የሰውል ልጅ አዕምሮ የሰው ልጅ ከተወለደ በኋላ የሚያጎለብተውና የማህበረሰብ የተከለከሉ ህግጋት ፣ ብዙ ጊዜ የማይጠቀምባቸው ፣ የማህበረሰቡ ፀረ ህግጋቶች ፣ የታፈኑ ስሜቶች ባጭሩ የተረሱ ነገሮችና መጥፎ ነገሮችና የተከለከሉ ነገሮች የሚታጨቁበት መጋዘን ነው የሚል ማብራሪያ ነው ያለው።
Jung ግን Unconscious mindን የሚያየው ከዚህ ለየት ባለ መንገድ ነው። መጋዘን ሳይሆን ከዛ የጠለቀ የሰውን ልጅ የጋራ ደመ ነብስ የሚያንቀሳቅስ ነገሮችን ከማጠራቀም በዘለለ የ ሰው ልጅ ልክ በዝግመት በ evolution እንደመጣውና አሁን ያለበትን አቋም እንደያዘ ሁሉ ይህ ድብቁም የአዕምሮአችን ክፍል ከ ጥንት የሰው ልጅ መነሻ ጀምሮ በ evolution ከ ጥንት የሰው ዘር የወረስነው የሰው ልጅ ሁሉ የጋራ የንቃት ህሊና ነው እንጂ ከተወለደ በኋላ የሚመጣና ትውስታና የተከለከሉ ነገሮችን ብቻ የሚያጭቅ አይደለም ብሎ ያምናል። ይህን ለማወቅ ደግሞ የሚነገሩ ትርክቶች እና ተረቶች አስረጅ ናቸው ብሎ ይሞግታል። ሁሉም ሀገር ብትሄዱ የሰውን ልጅ ድብቁ የ አዕምሮ ክፍል ውስጥ የተቀመጠ ከ አያቶቻችን የወረስነው ስንወለድ ጀምሮ ደመነብሳዊ ዕውቀት አለን ይላል። ተረቶችን ፣ ንግርቶችን ብትመለከቱ ስለ ጀግና የሚተረቱ ስለ ሴጣን ወይም ስለ ህላዌ ተመሳሳይ ተረቶችን ነው ይህም የሚያሳየው ስንወለድ ጀምሮ ከጥንት አያቶቻችን በ evolution ሂደት የወረስነው ስንወለድም ያለ እውቀት አለን በደመነብስ የሚያግባባን የሚል ነጥብ የያዘ ነው።
ሌላው የሚለያቸው ነጥብ ህልም ላይ ያላቸው እሳቤ ነው። ህልምን የሚያዩበት መንገድም ለየቅል ነበር። Freud ህልምን wishful thinking ነው ብሎ ይገልፀዋል የተደበቁ የ ድብቁ አዕምሮ እራሱን የሚገልጥ ሰው በውን ያጣውን ፍላጎት የሚያሟላበት ሂደት ነው ቁም ነገር የለውም ብሎ ያስባል። Jung ደግሞ ህልምንም የሚያየው ከዛ በላይ ከተፈጥሮ የሚመጣ ወይም ደግሞ ህይወታችን ላይ የሚከሰቱትን ነገሮች ማወቂያና የነብስ ጥሪ የሚመረበት ከተራ ምኞትና እንቶፈንቶ በላይ ቁም ነገር ያዘለ ነገር ነው ብሎ ነው።
ለመጨረሻ ጊዜ ሲለያዩ ያጋጠማቸውን ነገር አውስቼ ልጨርስላቹ
ወደ መለያያቸው አከባቢ እ.ኤ.አ 1909 በ America New York City የእግር መንገድ እናደረጉ የሆድ የሆዳቸውን ስለ ስነልቦና እየጠረቁ ባሉበት ወቅት ጋሼ Freud ፌንት ይገጩና ልብሳቸው ላይ ሽንታቸው ያመልጣቸዋል። ከዛ ከነቁ በኋላ ስለ ጉዳዩ አንስተው ማታ ባዩት ህልም ተረብሸው እንደነበረ ለ Jung ያወሩታል ይህም የተከሰተው ከዛ ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ሲነግሩት Jung ህልሙን ይጠይቃቸዋል። Freud ግን ሊነግረው አልፈለገም። ጉዳዩን ሊነግረው እንደማይፈልግና አለቅነቱንም የሚንድ ስለመሰለው።@ourrthought
👍4❤2👏2