ሐሳቦቻችን
981 subscribers
103 photos
4 videos
5 files
2 links
በዚ ቻናል ላይ የተለያዩ ሀሳቦቻችንን ፣ ምልከታዎቻችንን ፣ ትዝብታችንን ፣ ከተለያዩ መልኮች እያነሳን እንወያያለን!

ሀሳብና አስተያየት ካላቹ @haileabb
Download Telegram
Forwarded from ቀለም መጽሔት
ቀለም መጽሔት ቅጽ 1 እትም 6.pdf
5.7 MB
ቀለም መጽሔት🗞️

ቅፅ 1 እትም 6


እያነበባቹህ ለወዳጅዎ ያጋሩ
ለሀሳብ አስተያየት

@KelemMagazine

Telegram 👇❤️
@kelemofficial
👍41
ሳይታገሉ ያገኙት ነፃነት ከባርነት ይከፋል!

@ourrthought
👍95🔥3🤔2
ሰው አይመከርም!

ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለምዶም በሀዘኔታም ሰዎችን እንመክራለን። ግን ሰውን እንዲህ አድርግ እያሉ ሰዎችን መምከር በራሱ ሰዎቹ ላይ የሚያመጣው ጫና አለ። ማንኛውም ሰው ችግር ውስጥ ፈልጎ እንደማይገባው ሁሉ በሰው ምክርም ከዛ ችግር አይወጣም። ለጊዜው ሊወጣ ይችላል ግን ዘላቂ መፍትሄ የማግኘት እድሉ ጠባብ ነው። ባልተሰቀሉበት መስቀል መፍረድ ቀላል ነው እና ቀለል አድርገን ሰዎችን መምከር ለሰዎቹ ጫናውን ያብሰዋል።

ሁለት አይነት የ ምክክር ሂደት አለ Directive and Non directive ተብለው ይከፈላሉ።

Directive የሚባለው ሂደት ግለሰቡ ና አማካሪው ቁጭ ብለው ሰውየው እንዴት እዚህ ችግር ውስጥ እንደገባና እንዴት ከዚህ ውስጥ ሊወጣ እንደሚችል ከሰውየው ጋር የሚያቅዱበትና አማካሪው(counsellor) ግለሰቡ በቶሎ ችግሩን እንዲያገኘው የሚያግዝበት መንገድ ነው።

Non directive የሚባለው ደግሞ አማካሪው ምንም ጣልቃ ሳይገባበት ግለሰቡ እየመጣ ችግሩን ብቻ እያወራ የሚመለስበት ሲሆን ግለሰቡ ችግሩን በሚያወራበት ጊዜ እራሱ ለራሱ ንቁ እየሆነ የሚመጣበት ሂደት ነው።

ብዙ ሰዎች የስነ ልቦና የምክክር ሂደትን (counseling psychology) አንድ ችግር ያለበትን ሰው ቁጭ አድርጎ እየመከረ ማስተካከል ይመስላቸዋል። ግን የስነ-ልቦና አማካሪ (counselor) እንደዛ ያደርጋል? ወይ ካልን በፍፁም።

የ ምክክር ሂደት (counseling process) ችግር ያለበትን ሰው ቁጭ አድርጎ እየመከሩ የማስተካከል ሂደት ሳይሆን ግለሰቡ ያለበትን ችግር በራሱ እንዴት እንደሚያገኘውና እንደሚፈታው የሚያሳይ ሂደት ነው። እንጂ የመምከር አገልግሎት ሂደት አይደለም።

እና ምን ልላቹህ ነው ዝም ብሎ መስማት በራሱ ትልቅ እርዳታ ነው ግዴታ መምከር አይጠበቅባችሁም ለማለት ያክል ነው።

@ourrthought
👍125
ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት ወንድ አለ የሚያመነዝርና የማመንዘር እድሉን ያላገኘ!

በዕውቀቱ ስዩም


@ourrthought
🤣17🤔1
አንድ ወዳጄ ምን አለኝ "አለም ላይ ሀያል ለመሆን ሁለት ነገር ወሳኝ ናቸው ተስፋን እና ፍርሀትን ለሰዎች መሸጥ"።

ልከኛ ሀሳብ ናት የትም የ አለም ጥግ ብትሄድ መሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ ወይ የሀይማኖት ሰባኪዎች እንዚህን ነገሮች ነው የሚጠቀሙት። ፍርሀት ሰዎችን የሚያስገዛ ሀያሉ መሳሪያ ነው። political hypnotize የሚባል ነገር አለ። የፖለቲካ መሪዎች ትልቅ ጭራቅን ወይም ትልቅ አውሬ በህዝቡ አዕምሮ ምስል ይቀርፁለታል ከዛ ሀያል ጠላት ወይ ጭራቅ እነሱ እንደሚያድኑህ ይሰብኩሀል የዛኔ ቢከፉብህም ዘላለምህን እየተገዛህላቸው ትኖራለህ። ያለነሱ የሚታደግህ ያለ አይመስልህም ወይ እነሱ ከዛ ስልጣን ቢነሱ ሀገሪቷ የምትፈራርስ ይመስልሀል ይሄ እንግዲህ ፍርሀትን በደንብ አዕምሮህ ውስጥ አስገብተዋል ማለት ነው። ከፍርሀት ጋር አያይዘው ደግሞ ተስፋ ይሸጡልሀል ያኔ አዕምሮህ ታሰረ ማለት ነው። በርግጥ ዛሬም ድረስ ይሄ ዲስኩር አለ። የትም የ አለም ጫፍ ብትጓዝ ጠላት የማይሰበክበት ሀገር አታገኝም።

ሀይማኖትም ላይ ሴጣንና ሲዖል ታላቅ ማስፈራሪያና ሰዎችን እንዲገዙ ማድረጊያ መሳሪያቸው ነው። ተስፋ ሲሰጡህ ደግሞ ገነትንና የነሱን ሀይማኖት ብቸኛ ማምለጫ አድርገህ እንድትስል ያደርጉሀል ያም ለዘላለም የሚቀጥል ሰንሰለት ነው።

በግለሰብ ደረጃ ስትሄድ ደግሞ የምትሰራበት ድርጅት የመባረር ፍርሀትንና የደሞዝ ጭማሪ ባዶ ተስፋን ይግትሀል። ትንሽ ካስተዋልን አዕምሮዋችንን የሚቆጣጠሩት ነገሮች ተስፋንና ፍርሀትን ያጣመሩ ነገሮች ናቸው።

@ourrthought
👏11👍4
በለው ተሰማ የነፃነት ቀንዲል!

አለም ላይ አንዳንድ ነገሮች እንዲከሰቱ አንዳንድ ግለሰቦች ምክንያት ነበሩ። እኚህ ግለሰቦች ባይኖሩ አለም መልኳ ምን ይመስል እንደነበር ማሰብ ከባድ ነው። ሮዛ ፓርክን ዛሬም ድረስ አለም የሚያስታውሳት የጥቁር ታጋይ እና የነፃነት ተምሳሌት አድርጎ ነው። ሮዛ ፓርክስ በ Montgomery በ 1955 እ.ኤ.አ ጥቁሮች ከነጮች እኩል አንድ ባስ ላይ ተቀምጠው መሄድ በማይችሉበት ዘመን ላይ ለነጭ ወንበሬን አለቅም ብላት ነፃነትን የሰበከች ጀግና እና ፈር ቀዳጅ ብለን የምናስታውሳት የነፃነት ምሳሌ ናት። ከ ሮዛ በኋላ የጥቁር ነፃነት ጥያቄ ተፋፍሞ እስከ ነፃነት መቀዳጀት ደርሷል።

የ ፓኪስታኗን ማላላን የኛ ዘመን ሰው ስሟን ከፍ አድርጎ ይጠራል። በፓኪስታን ሴት ልጅ ከወንዶች እኩል መማር አለባቸው ብላ ስለነፃነት የሰበከች ህይወቷ አደጋ ላይ እስኪወድቅ ድረስ ዛሬም ድረስ የምትሟገት ነፃነትን እኩልነትን የምታሳድድ ምሳሌ ናት።

  ማንዴላ ፣ ማህተማ ፣ ማርቲን ዛሬም ድረስ አለም ስለነፃነትና መብት ሲሰብክ ስማቸው ይታወሳል። ሀገራችንስ ስንቶቹን ታስባቸው ይሆን? ስለ እኩልነት ስለ ነፃነት የሰበኩላትን ነብሳቸውን የሰጡላትን ብለን ብንጠይቅ ቄሱም ዝም መፅሐፉም ዝም እንዲሉ በቅጡ የማንይታወሱ ግን ዋጋ የከፈሉላት በርካቶች ናቸው። ዛሬ አንድ የሀገራችንን የመብት ታጋች እናንሳ እስኪ።

በለው ተሰማን ስንቶቻችን ይሆን የምናውቀው? ስንቶቻችንስ ጠጃችንን ስንልፍ ስሙ ትዝ ብሎን ይሆን? እንጃ ብቻ። ዘመኑ በንጉስ ተ/ሀይማኖት ዘመነ መንግስት ጊዜ ነው። ከዛ በፊት ጠጅ የንጉስ መጠጥ ነበር። ተራው ህዝብ የጠጅን ቀለም እንጂ የጠጅን ጣዕም አጣጥሞ አያውቅም ነበር። ለዛ ነው ጠጅ የንጉስ መጠጥ የሚባለው። በለው ተሰማ ተከስቶ ለህዝብ እስኪሆን ድረስ።

ከለታት አንድ ቀን በለው ተሰማ ይቺ ጠጅ ትከነክነው ጀመር። ለምንድነው እኛስ የማንቀምሰው የምትል የድፍረት ሀሳብ። ሺህ አመት ይኖራል? የት አባቱ ብድግ አድርጎ ጭልጥ ነዋ አይ በለው ጀግናው ጠጅን አጣጣመው ከዛስ በኋላ ቢሞት ምን ሊገደው ደስታን በጉሮሮ በኩል አጣጥሞታል። ተይዞ ንጉስ ፊት ቀረበ። ያው ይዘው ያቀረቡት ጠጅን ያልቀመሱ ግነ እንደሱ መቅመስ የሚመኙ ድፍረቱን ያጡ አሸከሮች መሆናቸውን ልብ በሉ።

ጠጁን ጠጥተሀል አሉት ንጉሱ። አዎ አለ እሱም በድፍረት። እኮ ለምን አሉት። አማረኝ ጠጣሁት እኛስ ከማን እናንሳለን ዙፋኑ ራቀን እንጂ 😊 ንጉ ለዚህ ድፍረቱ እጅና እግሩን ቆርጠው ግምጃ ቤት ገቢ አደረጉት ከዛን በኋላ ግን ጠጅን ተራው ህዝብ ስለቀመሰው የህዝብ ይሁን ረክሷል ተብሎ ታወጀ። የኛ በለው በሱ ምክንያት እኛም የንጉስን መጠጥ ዛሬም ድረስ እናጣጥመዋለን።

በለው የከፈለው መስዋትነትና ጀግንነት ከሌሎቹ ታጋዮች ቢብስ እንጂ የሚያንስ አይደለም እጅና እግሩን የገበረለት የነፃነት ጉዞ ነው። ታሪክ ግን ስሙንም ግብሩንም እረስቶታል። ጠጅ ቤት እንኳ ስሙ አይዘከርም። ቢሆንም ታጋያችን ነው። በሱ ምክንያት ጠጅ ጣዕሟን አውቀናታል። ስሙ ዛሬም ይታወሳል።

ችርስ ለጠጅ ቀሚቃሚዎች! ለበለው ተሰማ የነፃነት አባት!

@ourrthought
🔥17😁4
‎"...የሰው ልጅ ሁልጊዜ እንባ ውስጥ እንደዋኘ ነው። ነገር ግን በየጊዜው ከዋናው ወጣ እያለ ተጋድሞ የሳቅን ፀሐይ እንደሚሞቅ ደግሞ አትርሳ"

‎ዝም ብዬ አየሁት እውነቱን ነው።

‎"ሌላስ?" አልኩት

‎"እውነትን አታብዛ"

‎"ምን?"

‎" ህይወት ውስጥ እውነት ብቻውን አይገኝም። ህይወት እንደ ቡና በወተት ነው። ወተቱ እውነት ቡናው ውሸት ይሁን። ግን ይሄ ልዩነት ባንጎላችን ውስጥ ይኑር እንጂ ሲኒው ውስጥ በአንድ በኩል ቡናው በሌላው ወተት የለም። ሲኒው ውስጥ ያለው ቡና በወተት ነው። ህይወት ውስጥ በቀኝ በኩል እውነት በግራ በኩል ውሸት አይገኝም። ህይወት ውስጥ የምታገኘው የእውነትና የውሸት ቅልቅል ነው።"

ሌቱም አይነጋል
‎ስብሀት ገ/እግዚአብሔር


@ourrthought
13👍4👏1
ሐሳቦቻችን
Photo
ይሄን የመሰለ ፊልም እስከዛሬ አለማየቴ አስገርሞኛል። ፊልሙ እ.ኤ.አ በ 2002 የተሰራ ፊልም ነው። የፊልሙ አርዕስት Equilibrium የተሰኘ ነው። ፊልሙ በ totalitarian ላይ የተመሰረተ ነው። totalitarian ማለት አገዛዙ የፈቀደልህንና የወሰነልህን ገደብ መኖር እንደማለት ነው።

ፊልሙ ጭብጡን ያደረገው በ totalitarian ሀሳብ ላይ ሆኖ ስሜታችን feeling, sense and emotion የሚባሉት ነገሮች የማይፈቀዱበት እንደወንጀል የሚቆጠርበት ሀገረ መንግስት ነው። ለነገሮች ያለን ስሜት ነው ጦርነቶችና መገዳደሎችን ያስከተሉብን የሚል ሀሳብን በመያዝ የሀገሬው መንግስት ህዝቡ ሁሉ ምንም አይነት ስሜትን እንዳይሰማው በየቀኑ የሚወስዱት መድሀኒት ይሰጣቸዋል። በርግጥ ህዝቡ ግን ያን መድሀኒት ስሜታቸውን እንደሚገለው የሚያውቁት ነገር የለም መድሀኒቱን በየቀኑ በስረመንጅ መልክ መወጋት ግዴታቸው ነው እሱን ያላደረገ በሽብር ወንጀል ይከሰሳል የሞት ፍርድ ይፈረድበታል።

እዚህ ከተማ ውስጥ ምንም አይነት ስሜትን የሚቀሰቅስ ነገር ማድረግ አይቻልም እንስሳትን ማሳደግ አይፈቀድም የጥበብ ስራዎችን መመልከትም ሆነ በመፅሐፍ መልክ ማየትም መስማትም የተከለከለ ነው። ስዕል ፣ ሙዚቃ ፣ ጌጣጌጥ ፣ መስታወት ፣ ቤትን ማስዋብ....ምንም ከስሜት ጋር የተገናኘ ነገር ካደረጉ  የስሜት ተጠርጣሪዎች (sense offenders) ተብለህ ትገደላለህ። ማልቀስ መሳቅ ማፍቀር ውጉዝ ናቸው።

ፊልሙ ሲጀምር የስሜት ተጠርጣሪዎችን በማሳደድ ሲጀምር ይታያል። ከዛም ሁሉንም ተጠርጣሪዎች ከገዱ በኋላ ቤት ውስጥ ያሉትን የጥበብ ስራዎች በሙሉ እንዲቃጠሉ ያዛል እዛ ቤት ውስጥ የሞናሊዛ ስዕልም አብሮ ሲቃጠል ይጀምራል። የዛ ከተማ ኗሪዎች ሚለብሱት ፣ የሚኖሩበት ፣ የሚመገቡት የሁሉም ተመሳሳይ ኑሮን የሚከተል ነው።

እና ባንድ ወቅት ዋና ገፅ በሀሪው የ ከተማዋ ኤጀንት clierk ጠዋት እንክብሏ ወድቃ ትሰበርበታለች ከዛን በኋላ ነገሮች ይሰሙት ይጀምራሉ። ለእንስሳ ፣ ለሚገላቸው ሰዎች ፣ ለነገሮች ስሜት ይሰማው ይጀምራል እያለ የሚቀጥል ፊልም ነው።

በርግጥ ይሄን ፊልም ሳይ የሰው ልጅ ለነገሮች ምንም የማይሰማው ከሆነ ከ አውሮ እንደሚብስና ሮቦት እንደሚሆን ያሳያል። ለልጅህ ለቤተሰብህ ለሰው ለ እንስሳ የማታዝን ከሆነ ለ ስነ ጥበብ ግጥም ሙዚቃ ቦታ ከሌለው ሰው ምንድነው? እንድትሉ የሚያደርግ ነው። ይሄን ፊልም አሁን ካለንበት ዘመን ጋር ብናመጣው ለነገሮች ስሜት ያጣበት ዘመን ላይ ነው። ይሄ ማለት በፊልሙ ላይ ያለውን አይነት ከተማ ለመምሰል ብዙ አንርቅም በመንግስት ጫና ሳይሆን አሁን የተጠናወተን አግበስባሽነት (consumerism) ጋር ይገናኛል። ፊልሙ ላይ ያለችው በየቀኑ የሚወስዷት ስሜት አልባዋ እንክብል እዚህ ዘመን ላይ አግበስባሽነት በሏት።

አሁን ላይ ሰው ደስታን ፍለጋ የማያግበሰብሰው ነገር የለም ግን ደስታ እንደ ሰማይ የራቀው ይመስላል። ከ 19 ነኛው ክፍለ ዘመን በኋላ materialism የገነነበት አለም ነገሮች በመሰብሰብ የሚያምን ከነገሮች ጋር ግንኙነቱ የተቋረጠ ብዙ ስዕል በቤቱ ቢደረደርም ስሜት ማግኘት የቸገረው ለስሜቱ ብዙ ርቀትም ቢሄድ ስሜት አልባ የሆነው postmodernism ዘመን ይሄ ፊልም ብዙ ጭብጥ ይሰጠናል። ስሜት ማጣት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ፊልሙን ኮምኩሙት። ፊልሙን ሀሳብ መስጫ ላይ አስቀምጥላቹሀለሁ

@ourrthought
👍105
የዛ ማዶ ሰዎች ዘፈን አያምራቸው
አጅሬ ትዝታ አልገባም ቤታቸው


አስቴር አወቀ
ትዝታ


@ourrthought
8
ሐሳቦቻችን
የዛ ማዶ ሰዎች ዘፈን አያምራቸው አጅሬ ትዝታ አልገባም ቤታቸው አስቴር አወቀ ትዝታ @ourrthought
Aster-Aweke-Tizita-Official-Single
<unknown>
ፍቅር ገደለ አሉ የወደደውን
እሱም እንደሰው ሊቀብረው ይሆን

እስኪ ትንሽ ተብሰልሰሉ ደሞ


@ourrthought
👍21
ከብዙ መጥፋት በኋላ ቴሌግራም ላይ ዛሬ ለመፅሐፍ ተነሳሳሁ። ለተወሰኑ ጊዜያት ፅሑፍ መፃፍ አቋርጬ ነበር። አንዳንዴ ነገሮችን በማድረግና ባለማድረግ መሀል ልዩነቱ ይጠፋብናል። ህይወት ላይ የምናደርገው ነገር ሁሉ ውሉ ይጠፋንና በማድረግና ባለማድረግ መሀል በመኖርና ባለመኖር መሀል ድንበሩ ይጠፋንና የህይወትን ነገር እንዳመጣጡ ለመቀበል በአብዘርድ እና ኒሂሊዝም በሚሉት እሳቤዎች መሀል እንቸነከራለን። ታዲያ ያኔ እንደ እንስሳ በደመነብስ ብቻ እንኖራለን።

ታዲያ ከብዙ ጊዜ በኋላ አንድ የግጥም መፅሐፍ ሳነብ ከዚህ በፊት በትንሹ ከላይ ካጋራኋቹህ ሀሳብ ጋር የምትሰናሰን አንዲት ሀሳብ ከ ሀብታሙ ሀደራ እንዲህም ያለም የለ ከሚለው የግጥም መድብል አግኝቼ ልንጨዋወትባት አመጣኋት። በመጀመሪያ ግጥሟን ላስነብባቹህ

አለመምረጥን መምረጥ፣ ቢቻል

ከጠዋት ጣይና ፥ ከጨረቃ ብርሀን?
ከፊያሜታና ፥ ከሸገሯ ሮማን?
እንዲህ ያለው ምርጫ
ድንቅ ነው እርግማን?

በረሀብ አይደለም
በሲዖል አይደለም
ፈጣሪ ሚቀጣህ
ምርጫ እየሰጠ ነው ፥ ደስታ የሚያሳጣህ።

ይህቺን ግጥም ሳነባት ታዲያ ደስ አለኝ ሀሳባቹሁን በግጥምና በዘፈኖች ተከሽኖ እንደማግኘት ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ? ብፅፈው ብፅፈው ላወጣው የማይቻለኝን ሀሳብ እንዲህ ቅልብጭ ብላ ማግኘት በረከት ነው።

ሀሳቧን ስንጨዋወትባት የዚህ አለም ሁሉ የሰው ልጅ መቃተት ይሄ የምርጫ መቸንከር አይደለም ወይ ያስብላል። በ ሳይኮሎጂ የሆነች ሀሳብ አለች Approach approach የምትሰኝ ይሄ ማለት በጣም ከምትወዱት ከሁለት ነገሮች አንዱን እንደመምረጥ ማለት ነው። ሁለት መንታ ወንድም ቢኖራቹህ አንዱን ምረጡ ብትባሉ የቱን ትመርጣላቹህ?

ከዚህ በፊት አንዲት መስመር ሀሳብ ፅፌ ነበር እንዲህ የምትሰኝ "የሰው ልጅ ለገዛ ነፃ ፈቃዱ ተላልፎ ተሰጥቷል" የምትል። እኛ ሰዎች ሁል ጊዜ ምን መምረጥ እንዳለብን ግራ እንደተጋባን ነው። ትላንት በመረጥነው ነገር ዛሬ እንበሳጫለን የምርጫዎችን እድል መብዛቱ ግራ እንዳጋባን አለ። ዛሬ ላይ አንዳንድ አውሮፓ ሀገራት የልጆቻቸውን ፆታ መምረጥ ባለመቻላቸው ህፃናቱ የራሳቸውን ፆታ እንዲመርጡ ምርጫ ይደረደርላቸዋል ይሄም ቀውስን ይፈጥርባቸዋል በየጊዜው እየቀያየሩፈ ግራ እስኪጋቡ ድረስ። ፈጣሪ ሲጣላ ብትር አይቆርጥም ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም ያሉት ከዚህ ተነስተው ይመስለኛል። ፈጣሪ በምትመርጠው ነገር ሁሉ ደስታህን ከነጠቀህ ቀውስ ውስጥ ትገባለህ።

የሰው ልጅ የውድቀቱ ምክንያት የምርጫው ውጤት ነበረች ግን ምርጫ ባይሰጠውስ ኖሮ? የሰው ልጅ ምርጫ ባይኖረውና በቃ ዝም ብሎ ለተፈጠረለት ነገር ኖሮ ቢሞትስ ምርጫ ባይሰጠው ኖሮ ያስብላል። ግን ደግሞ ምርጫው የደስታውም ምክንያት ናት ዛሬ ያልተመቸውን ነገር ነገ ደግሞ ይቀይራል ምርጫው በመብዛቱ ምርጫዎቹን በማሰስ ጉዞ ውስጥ ህይወት እንዳይሰለቸው ሆኗል። ይሄው ምኞቱ ደግሞ ምን መምረጥ እንዳለበት ግራ እያጋባው ደስታውን ይነጥቀዋል።

ልብስ ቤት ሄደህ ወይ ጫማ ልትገዛ ፈልገህ ቡቲክ ስትሄድ ግራ ትጋባለህ ምናልባት ሳትገዛ ልትመጣ ትችላለህ የምርጫ መብዛት ፍላጎትህን ያሳጣሀል። ግን ደግም የሆነ ሰው ጫማ ገዝቶልህ ዝም ብሎ ቢሰጥህ ከምትገዛው በላይ ደስ ይልሀል። አዕምሮህ ከምትመርጣቸው ነገሮች መሀል ያልመረጥከውን ያመለጠህን ነገር የተሻለ አድርጎ ያቀርብልሀል። ለዛም ነው ቡድሂስቶች ፍላጎትን በማጥፋት ምኞትን በመግታት ምርጫዎቻቸውንም አብረው በመቀነስ በትንሽ ነገር ደሰታ የሚያገኙት። አዕምሮአችን ለምርጫ ግራ ይጋባል። ከመምረጥ ይልቅ የተመረጠለት ነገር ላይ ይበልጥ ደስታ የሚሰማው።

ደሀ ምኞቱን በመቀነስ ሀብታም ይሆናል ይላል የማላስታውሰው ሰው ያ ማለት ምርጫው ይቀነስለታል ለዛ ነው ደሀ 1 ምርጫ ስለሌለው ያገኛትን አንድ ምግብ አጣጥሞ የሚመገበው ሌላ አማራጭ እንደሌለው ያውቃል በሷም ከመደሰት ውጪ አማራጭ የለውም። ገንዘብ ሲኖርህ ከምግቡ በላይ የምትበላበት ቤት ያሳስብሀል ከዛ ምን መብላት እንዳለብህ ያሳስብሀል። ከሳጥንህ ውስጥ የቱን መርጠህ መልበስ እንዳለብህ ግራ ትጋባለህ። ሁለት ልብስ ሲኖርህ አንዱ እስኪደርቅ ያቺኛዋን ለብሰህ ፈታ ነው። ይብላኝ ለኛ ምርጫዎቻችን በዝተውብን ምን መምረጥ እንዳለብን ለማናውቀው።

@ourrthought
👏18👍1
ጣሊያኖች ሲተርቱ ምን ይላሉ መሰላቹህ

"La barba non fa il filosofo" ወደኛ ስናመጣው

" የጢምህ መንጀርገግ ፈላስፋ አያደርግህም"
እንደማለት ነው።

ጥቅሱ ከምስሉ ጋር ዝምድና የለውም👐

@ourrthought
😁17
አቡሽ_ዘለቀ_Fullaanneey_NEW_Ethiopian_Music_Video_2016
<unknown>
አይ ሙዚቃ

አስተርጉማቹህ ስሙት

@ourrthought
7
"ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት ወንድ አለ የሚያመነዝርና የማመንዘር እድሉን ያላገኘ!"

ይህች የ በእውቀቱ ንግግር በቀልድ መልክ የቀረበች የስነ ምግባርን ፍልስፍና የምትዳስስ ሀሳብ ናት። በቀደም አጋርቻት ብዙዎች የ ፈገግታ ኢሞጂ ሲጠቀሙ አይቼ ልፅፍበት ተነሳሳሁ። በርግጥ ስታየው ያስቃል ስታስበው ግን ያብሰለስላል። የቀልድ የምትመስል ነገር ግን ከበድ ያለ ሀሳብ የያዘ ጥቅስ ነው።

‎ለምንድነው በምግባር የታጠርከው? ለምን ለሰዎች ጥሩ ትሆናለህ? ታማኝነትህስ ከየት የመጣ ነው? የሚለውን ጥያቄ የያዘ ነው።
‎ አጋጣሚውን ያጣ የስነምግባር ሰውና አጋጣሚው ኖሮት በስነ ምግባር መታነፅ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ለምንድነው የበደሉህን የማትገድላቸው? ወይ መልሰህ የማትበድላቸው? እውን ምግባር ስላለህ ነው? ሀይማኖትህ ስለከለከለህ? ወይስ አቅሙን አጥተህ? የሆነ የሆነ ቦታዎች ላይ አቅሙን አጥተህ የተውከው ነገር በሰዎች ዘንድ ግን ባ ጥሩ ስነ ምግባር ያስብልሀል።

‎ እዚህ ጋር የ አሪስቶትልን የ እረኛውን ወንድሙን ታሪክ ጋይጂን አንስቶ ስለ ስነ ምግባር ያወራናል። ጋይጂ እረኛ ነው ከ እረኛም የተዘነጋ እረኛ አይነት በሉት በሰዎች ዘንድ ሞኝ ጥሩ ስነ ምግባር ያለው እረኛ። ታዲያ ባንድ ወቅት ከዝናብ ለመጠለል በ አንድ ዋሻ ውስጥ ይገባል። ታዲያ እዚያ ዋሻ ውስጥ አንድ የጥንት ቀለበት ከ ጥንተ ቅሪተ አካል ላይ ያገኛል። ይሄኔ ጋይጂ ቀለበቱን ሲያጠልቅ ከሰው ዘንድ የሚሰውረው መሆኑንን አወቀ። ባለ ጥሩ ስነ ምግባሩ ጋይጂ ምን አደረገ አትሉኝም? ወዲያውኑ ወደ ቤተመንግስቶ ተሰውሮ ገባ ንጉሱን ገድሎ የንጉሱን ሚስት አገባት ወዲያውም ንጉስ ሆነ። ከዚህም ታሪክ አስከትሎ ምን ይላል መሰላቹህ አንተስ የጋይጂ አስማተኛ ከሰዎች የሚሰውር ቀለበት ብታገኝ ምን ታደርጋለህ ይልሀል። ትዘርፋለህ? ወይስ እንደድሮህ ትኖራለህ? ባንክ ቤት መዝረፍ? ስልጣን መገርሰስ? ወይስ እየተደበቅህ የሴት ገላ ልብሷን ስትቀይር ታያለህ? ምን ታደርጋለህ?

‎ከዚህ ታሪክ የምንረዳው በስነ ምግባር የታነፅን የመሰልነው አማራጭና አቅም የማጣት እንጂ በስነ ምግባር መኖሩ ፅድቅ እንዲሆንልን አይደለም እንደማለት ነው። የ በውቄም ጨዋታ እዚህ ትመጣለች እስከዛሬ ያለመነዘሩ ታማኝ የስነ ምግባር ሰው የተባሉት ዕድሉን አጥተው እንጂ እንደዛ ጋይጂ የመሰውሯን ቀለበት ቢያገኙ ምናልባት ዘወትር የሚመኟትን ሴት ከመግለጥ ስነ ምግባራቸው አይይዛቸውም ለማለት ነው። የኛ የምግባር መለኪያ የተዛባ ይመስላል። ዕድሉን አጥቶ ጨዋ የሆነና ጨዋነት ዋጋ እንዳለው አውቆ የታቀበን የምንለይበት መንገድ የለንም። ስለ ምግባርን ለስነ ምግባርነቱ ስትል የምታደርገው ነገር ይመስልሀል። የማትሰርቀው የሰውየው ላብ አሳዝኖህ ያልደከምክበትን ላለመንካት ነው ወይስ ብትያዝ እስሩና የሰው መጠቋቆሚያ ስለምትሆን? አንተ ታውቃለህ።

‎Carl Gustav Jung ሁላችንም የየግል ወይ የማህበረሰብ ጭንብል (persona or mask) አለን ይላል። በሰዎች ፊት የማናሳየው ጋጥ ወጥ ክፍል። እርስ በእርስ ስንገናኝ ወይ ከቤት ስንወጣ የምናጠልቀው ምግባረ ብልሹነታችንን ሸፈነን የምንወጣበት የጋይጂን ቀለበት የመሰለች ጭንብል አለችን። እሷን ገልጦ ላየን ግን አፈንጋጭነታችን አድፍጧል። እሷን ግን የሚገልጣት ብዙ ነገር ሊሆን ይችላል። ወይ ስልጣን ወይ ገንዘብ ለዛ ነው አንዳንድ ሰው ድንገት ገንዘብ ሲያገኝ ወይ ስልጣን ሲያገኝ የሚቀየረው ያደፈጠው ማንነቱ ብቅ ይላል ልክ እንደ ጋይጂ ቀለበት።

‎በውቄ ይሄን ፍልስፍና በቀልድ መልኩ ጣል አድርጎ ያለፈው ይሁን አንጂ ስትተነትነው ሰፊ ነገር ነው የያዘው። ብዙ ጊዜ በቀልድ መልኩ የሚያስተላልፈው መልእክት የሚደንቀኝ ሰው ነው። እና አንተን የስነ ምግባር ሰው ያደረገህ ምን ይሆን? ማህበረሰቡን ፈርተህ? ወይስ አቅሙን አጥተህ? ወይስ የምርም የስነ ምግባር መንገድ ጥሩ እንደሆነ አምነህ? መልሱን ለናንተ ትቼዋለሁ።

@ourrthought
👏118👍2👎1
ነገረ ፖለቲካ ወ አፍሪቃ

እውነተኛ ክስተት ነው የምነግራቹህ
ስሟ በጠፋብኝ አንድ የ አፍሪካ ሀገር ባንድ ወቅት ምርጫ ሊደረግ ሽር ጉዱ ተጀመረ እና የመጨረሻው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ እጩ ተወዳዳሪ እስከዛሬ ያለውን ብልሹ አሰራርና ስርአት አልበኝነት እያነሳ እሱ ከተመረጠ ይሄን ችግር እንደሚፈታ ደሰኮረ ህዝቡም አዳነቀ ተደሰተ።

ከዛም ጠቅላዩ መሪ በመጨረሻ ቅስቀሳው ህዝቡን በ እስታዲዮም ሰብስቦ አንድ ንግግር አደረገ።
"ውድ ህዝቤ ሆይ አርፍሪካ ውስጥ አንድ መሪ የመጀመሪያው ምርጫ ላይ ለ ቤተሰቡና ለራሱ ይሰራል ህይወቱንም ይቀይራል። ቀጣዩ ምርጫ ላይ ደግሞ ለዘመዶቹና ለቅርብ ጓደኞቹ ህይወትና ለወጥ ይሰራል። በ ሦስተኛው ምርጫ ደግሞ አማራጭ ስለሌለው የቀረው ቤተሰብም ዘመድም ጓደኛም ስለማይኖር ለህዝቡ ለውጥ ይተጋል። በዛ መሠረት እኔ ቤተሰቤንም ፣ ዘመዶቼንም ፣ ጓደኞቼንም ለውጫለሁ አሁን ሦስተኛው ምርጫ ላይ ነኝ ለናንተ ከመስራት ውጪ አማራጭ የለኝም። ትኩረቴ ለናንተ ይሆናል። አይ ካላቹህ አዲሱን መሪ ምረጡና ቤተሰቦቹን ፣ ዘመዶቹን እና ጓደኞቹን ቀይሮ እናንተን እስኪይር መጠበቅ ትችላላቹህ።" ህዝቡም ለ ሦስተኛ ጊዜ መረጠው አማራጭ አልነበረውምና።

ሰሞኑን ለ አፍሪካ ጉባኤው ለመሪዎቹ ያለውን ወከባ ሳስተውል የ አፍሪካን ችግር የሚፈቱ ትላልቅ ልሂቃን እንጂ የ አፍሪካን ችግር የሚያባብሱ አልመስልኝ ብለውኝ ግራ ስጋባ ነበር።

ይሄ የ አፍሪካ መሪዎች ስብስብ በራሱ እንኳ መቆም ያልቻለ በ አውሮፓ ሀገሮች የሚደገፍ የመሪዎች ስብሰባ የ አፍሪካን ችግር ሳይሆን የሚፈቱት የ ሀበሻ ሴቶችን የቀሚስ ቋጠሮ እና ቀበቷቸውን ለመፍታት ነው ቋምጠው የሚመጡት። እናት አለም አፍሪቃ መምጫሽ ይናፍቀኛል ቻይው!

@ourrthought
🔥5😁1😢1
እውነታውን አለማወቅ መልካም ነው። አለማወቅን የመሰለ ፍቱን መድሀኒት የለም። ሁሌም ባይሆን!

@ourrthought
👍14
Audio
አንቺን ይመስላል...

@ourrthought
7
ዳግም የተለጠፈች

ብቻ ግን ይመስለናል

ይመስልሀል እንጂ : ሀዘንህ : ስሜት ማጣትህ : ተስፋ መቁረጥህ....ማንም ግድ ሰጥቶት አይብሰለሰልልህም!

ሞትህም ቢሆን ልክ ከአንድ ግዙፍ ግንድ ላይ አንድ ዘለላ ቅጠል ተበጥሳ እንደወደቀች ያህል : እንዲያው እንደነገሩ መሬት ማስ ማስ አድረገው ተጉድጓድ ይጨምሩል እንጂ ጠሀይም ብትሆን አምላኳን እንዳጣችበት ጊዜ አትጠልቅልህም : ጨረቃም ደም አትለብስም : ለሞትህ ከዋክብትም አይረግፉልህም : ስለ ሞትህም የሚቀደድ መጋረጃ አይኖርም : አፈር እስክትገባ የሚከተልህም ታማኝ የ መስቀሉ ዩሐንስን መሳይም ወዳጅም አይኖርህም : አለምም ሰዎችም ምህዋራቸውን አይለውጡም : ምናልባት ትኩስ ዘለላ እምባ ይፈስልህ ይሆናል!

ሞትህ ልክ እንደ ኑረትህ አያስገርምም : አያስቆጭም : እንዳልተፈጠርህ ሁሉ ነበር ትባላለህ!


@ourrthought
10🔥4😭1
Armenian Duduk on Yanni ...
George Kapoyan
ይህች የ ያኒ የመድረክ የ አርመኒያ Duduk በጣም የምታሳሳና ወደ ጥንት የምትመልስ ናት

ለመብሰልሰል ከራስ ጋር ወደ ውስጣቹህ ለመጥፋት ስታስቡ የምትደመጥ አይነት ናት

@ourrthought
👍42🤔1
2