ሐሳቦቻችን
981 subscribers
103 photos
4 videos
5 files
2 links
በዚ ቻናል ላይ የተለያዩ ሀሳቦቻችንን ፣ ምልከታዎቻችንን ፣ ትዝብታችንን ፣ ከተለያዩ መልኮች እያነሳን እንወያያለን!

ሀሳብና አስተያየት ካላቹ @haileabb
Download Telegram
ሐሳቦቻችን
Photo
Existential crisis + Nihilistic = suicide

‎በየ ዘመናቱ ብንመለከት ዘመኑን የሚመራ መንፈስ (sprit of the time) አለው። ይህ ጊዜውን የሚመራ መንፈስ ማለት ጊዜው ላይ ያለው የህዝቡ ስነ ልቦና ባብዛኛው የሚያጋድልበት ጉዳይ ማለት ነው። ከጥንት ጀምሮ ብንመለከት በየ ዘመናቱ የሰውን ልጅ በጋራ የሚመሩት የጋራ ደመነብሱን (collective unconscious) የሚዘውሩት እንደነበሩ ታስተውላላቹህ። የ ኢንዱስትሪ አብዮት ፣ የ ሶሻሊስም ፣ ካፒታሊዝም ፣ የጥቁሮች ነፃነት ንቅናቄ ፣ የሴት ልጅ ነፃነት ንቅናቄ..... አሁን ላይ የጊዜው መንፈስ ያለው የሰው የጋራ ደመነብስ የሚዘወርለት የጊዜውን መንፈስ ብትመለከቱ ባብዛኛው የህይወት ትርጉም ማጣት ላይ ያተኩራል።

‎ዘመኑ በዚህ ደረጃ የህይወት ትርጉም ማጣት ጋር ተፋጠጠ? የሚለውን ጥያቄ እንዴት ከሌላው ዘመን በተለየ መልኩ በዚህ ድህረ ካፒታሊስት አለም ላይ በረታ? የሚለውን በትንሹ ተንትነን እንመልከተው።

‎ወደ ጥንት የሰው ልጅ ዘር መለስ ብለን የተመለከትን እንደሆነ ሰዎች በጋራ ህይወታቸውን እያቆዩ ለመኖር ከተፈጥሮና ከ አራዊቱ ጋር ሲታገሉ የሚኖሩበትን መንገድ እናስተውላለን። ይህ ትግላቸው እንግዲህ የማያቋርጥ በመሆኑ ህይወታቸው በሙሉ በውጥረት የተሞላና ለምንድነው የተፈጠርኩት ከሚለው ጥያቄ በላይ እንዴት ነው ነብሴን የማቆየው ብለው የሚታገሉበት ዘመን ነበር።

‎ከጥንቱ የሰው ልጅ መለስ ብለን ቀረብ ለሚሉት ዘመን ላይ ስንመለከት አሁንም ቢሆን ሰዎች ትልቁ የህይወታቸው ትግል ህይወታቸውን የማሰቀጠል (survival mode) ላይ ሆነው በዚህ ሁኔታ ውስጥ ግን የህይወትን ምንነት በሀይማኖቶች ውስጥ ትርጉም እየሰጡ በዛም ጥያቄ እረክተው እናገኛቸዋለን።

‎ከላይ ባየናቸው ሁለቱ ምሳሌዎች ሰዎች ከህይወት ትርጉም በላይ ህይወታቸውን የሚያቆዩበት ነገር ይበልጥ እንደሚያስጨንቃቸው እናያለን። ታዲያ የዛኔ እምብዛም የሌለው የህይወት ትርጉም ማጣት አሁን ለምን ትልቁ ፈተና ሆነ?  ብለን እንተንትነው። የሰው ልጅ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በማህበረሰብ እሴትና ደንብ ፣ በሀይማኖት ፣ በስነ ምግባር ፣ በህግጋቶች በመሳሰሉት ነገሮች ታጥሮ የህይወቱን ትርጉም በነዚህ ውስጥ እየመለሰ የሚኖር ሆኖ የቆየ ነበር። አሁን ላይ ግን በነፃነት ስም እንዲሁም የግለሰባዊነት መስፋፋት የሰው ልጅ ከ ሀይማኖት ፣ ከቤተሰብ ፣ ከማህበረሰቡ ፣ ከ ሞራል ፣ ከህግጋት ገደቦች ተነጥሎ ተነጥሎ ብቻውን በመቅረቱ የህይወት ትርጉምን ምላሽ የሚሰጥበት መንገድን አጥቷል። በራሱ መንገድም የሚሰጠው ትርጉም የሚያረካው አልሆነም። መነሻው እራሱ ነውና ከባዶ ነገር ላይ ተነስቶ የሚሰጠው ትርጉም በየጊዜው እየተቀያየረ በነገሮች ግራ የተጋባ ሆኗል።

‎ ይህ ጥያቄ (የህይወት ትርጉም) ከ አፍሪካ ይልቅ በምዕራቡ አለም ላይ ይበልጥ የሚሰተዋል ጉዳይ ነው። የምዕራቡ አለም ያለበት የጊዜ መንፈስ (sprite of the time) ግለሰባዊ ነፃነት (individual liberty) ሰዎች ለጥያቄው መልስ ለመስጠት የሚነሱበት መነሻ ቦታን አሳጥቷቸዋል። ሌላው የሚታገሉለት ነገር በመቀነሱ ለዚህ ቀውስ ዳርጓቸዋል። ወደ አፍሪካ ስንመጣ አፍሪካ ላይ ዛሬም ድረስ የ ሀይማኖቶች ፣ ማህበራዊ መስተጋብሩ ፣ ባህል ፣ እሴት አለመፈረሳቸው ይሄን ጥያቄ ለመመለስ ሲረዳቸው ማስተዋል ይቻላል። አፍሪካ ውስጥ አሁንም ድረስ ለኑሮ የመታገሉ (survival mode) ላይ መሆናችን የህይወታችንን ትርጉም ለምንድነው የምኖረው? ከሚለው ጥያቄ በላይ እንዴት ነው የምኖረው? የሚለውን ለመመለስ በሚደረገው ትግል ውስጥ የህይወት ጥያቄያቸውን የሚኖሩበትን ምክንያት በ ህይወት መቆየት ጋር በማያያዛችን እራስን ከማጥፋት ከ አውሮፓውያን ይልቅ በኛ የማይስተዋለው ለዛ ነው።

‎ እንደ መጠቅለያ አንድ ማህበረሰብ ለህይወት ለመቆየት በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ ለህይወቱ የሚታገለው ነገሮች እየተቀነሱና አልጋ ባልጋ እየሆኑ በመጡ ቀጥር ይህ ጥያቄ በ እጅጉ ይበረታል። ሁሉን በማግኘት ውስጥ ሁሉን እንደማጣት ያለ የተራነት ስሜት ማለት ነው።
‎ ከ አንድ ወዳጄ ጋር በሀሳብ ዙሪያ ስንጨዋወት የ አፍሪካን ኑሮ እንዲህ መሆኑን እያማረረና የ አውሮፓ ኑሮ አልጋ ባልጋ መሆኑን እያወደሰ አብራራልኝ። በርግጥ ሀሳቡ ልክ ቢሆንም የኔ ምላሽ የነበረው ቢያንስ እኛ ይሄን ኑሮ ለማሸነፍ በምናደርገው ትግል ውስጥ የህይወት ትርጉማችንን መስራት ችለናል። ለብዙ ሰው ይሄን ህይወት ማሸነፍ የህይወት ዘመን ግቡ ነው። ይሄ ደሞ መልካም ጎን አለው ህይወቱን ከከንቱነት ታድጎለታልና። አፍሪካ ውስጥ ያለ ህይወት በራሱ የህይወት ግብ መሆን ይችላል። ህይወትን ማቆየት (survival mode) ከህይወት ከንቱነት(Nihilistic thought) የተሻለ ነው።

‎ ይህ ዘመን ከመሞት በላይ ለመኖር ከባድ ፈተና ያለበት ጊዜ ነው። ህይወትን ማቆየት በራሱ የህይወት ትርጉም ነው።

@ourrthought

#ሐሳቦቻችን
#ourrthought
9👏4🔥1
Western

“You are responsible for your own success or failure.”

Africa

"We raise together, we fall together"


These quotes show our psychological makeup.

@ourrthought
👍5🤔3😁1
የማህበራዊ ሚዲያ መልካችን

‎አንዳንዴ ረብ የለሽ የ YouTube , tiktok , Facebook...... አጫጭር ምስሎችን (video) ለረጅም ጊዜ የማያት አባዜ አጋጥሟቹህ አያውቅም?

‎ከተወሰኑ ጊዜናቶች በፊት ጊዜዬን የማጠፋባቸው የ ዩቱዩብና የ ፌስቡክ አጫጭር ምስሎች ምንም ጥቅም የሌላቸውና እርባና ቢስ ነበሩ። ለምሳሌ ለረጅም ሰዐት ፈረንጆች የ ሀገራችንን ምግብ እያዳነቁ ሲበሉ ፣ ከቤቱ ከወጣ የቆየ የ አሜሪካ ወታደር ቤት ሲገባ ያለውን የቤተሰብ ደስታ ፣ ፅድት ያሉ ውሾች ቤት ውስጥ እንክብካቤ ሲደረግላቸው.....የመሳሰሉ ምስሎችን ጥቅም እንደሌላቸው እያወኩኝ ግን ለረጅም ጊዜ አፍጥጬባቸው የምውልባቸው ነበሩ። አይቼ ስጨርስ ከራሴ ጋር ቅራኔ እገባለሁ ጊዜዬን በከንቱ ለምን አባክናለሁ ብዬ።

‎ ይሄን ድርጊቴን ለምን እንደማደርገው ምክንያቱን ባሰላስለው ለራሴ ላገኘው አልቻልኩም። ታዲያ ጉዳዩን ሰሞኑን ለ chat GPT ሳማክረው የሰጠኝን ምላሽ ጥሩ ሆኖ ስላገኘሁትና ስለጠቀመኝ ለናንተም ላካፍላቹህ።

‎የማይረቡ ጥቅም የሌላቸውን ምስሎች የማዘውተር ጉዳይ በ psychology ሲብራራ በ 4 ዋና ዋና ጉዳዮች  የሚብራራ የ አዕምሮ የልማድ ስርአት ነው። አብዛኛውን ጊዜ በጣም ስንጨነቅ ፣ የመዛል ስሜት ሲሰማን (በአካልም በ አዕምሮም) እና በትክክለኛ መንገድ አዕምሮዋችን የሚደሰትበትን ነገር ሲያጣ የሚከሰት ነው። አራቱን ዘርዝረን እንያቸው

‎1. Neurological explanation

‎አዕምሮዋችን ከሰውነታችን ክፍል 20% ሀይል (energy) ይወስድብናል። በዛ ምክንያት ብዙ ሀይል ላለመጠቀም በትናንሽ የደስታ ቅንጣቶች (Dopamine) መደሰትን ይመርጣል። ማሰብ የሚጠይቁ ወይም አስተማሪ ምስሎችን ጉልበት ስለሚወስዱበት ከዛ ይልቅ ምንም ማሰብ በማይጠይቁ በፈጣን ምስሎች ፣ ቀለም በበዛባቸው ፣ የውድድር ፣ የቦክስ ግጥሚያ ፣ ቶሎ ቶሎ በሚያልቁ ምስሎች በትንሽ ሀይል ትናንሽ ዶፓሚን እያገኘ የፍታታል። አዕምሮ ይሄን የሚያደርገው ድካም ሲሰማው ፣ ሲዝልና ትላልቅ ማሰላሰል ጉዳዮችን ላለማሰብ በትንሹ መደሰትን ይመርጣል።

‎2. Psychological anticipation

‎" ይህ እንግዲ ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ" የሚሉትን ብሂል የሚከተል መሆኑ ነው። የትኛውንም ቪዲዮ ስናይ ቀጣይ የተሻለ እንደሆነ የመጠበቅ አባዜ እንደማለት ነው። አዕምሮ ካሁን ይልቅ ቀጣይ የሚመጣው የተሻለ ነው ብሎ ያስባል ታዲያ አስቦ ብቻ አያበቃም ቀጣዩን የማሰብ ጉጉት ይፈጥርበታል በዚ ጊዜ የደስታ ሆርሞን ይለቃል ማለት ነው። ይሄ ጉዳዩ ከ ምታዩት የ ምስል ይዘት እፃር ሳይሆን እንደ ቁማር በሉት የመጠባበቅ ሱስ ውስጥ ትገባላቹህ። tiktok ላይ የቀጣዩ የተሻለ ይሆናል እያላቹህ የምታጠፉትን ጊዜ ልብ ካላችሁት ይገለፅላቹሀል።

‎3. Escaping from unwanted thinking

‎አንዳንዴ ህይወትህ ላይ ከባባድ ነገር ሲያጋጥምህ ፣ ወደፊትህን ስታይ ሲጨልምብህ ፣ የምታስበው ነገር ውጥረት ውስጥ ሲከትህ ከዚህ ስሜት ለመውጣት እንደነዚህ አይነት ፈጣንና ማሰላሰል የማይፈልግ ምስል ታያለህ።

‎4. Algorithm Manipulation

‎የምታየውን አንተ ነህ የምትመርጠው? ወይስ የምታየውን ነገር platform ይመርጥልሀል?
‎ ይሄን ሀሳብ ለብቻው ብፅፍበት ደስ የሚለኝ ሰፊ ትንታኔ የሚፈልግ ነው።
‎YouTube ፣ tiktok ፣ Facebook ፣ Instagram.....እነዚህ platform አንተን ካንተ በላይ የሚያው ናቸው። መረጃህን እርስ በርስ ይሻሻጡታል ምን ቪዲዮ ላይ ምን ያክል እንደቆየህ ፣ ምን እንደምትወድ ፣ ምን እንደሚደብርህ....እያንዳንዱ ነገርህን እያጠኑ መረጃህን ይይዙታል ሲደብርህ ፈጠን ያለ ምስል ይለቁልሀል ፣ ብቸነት የተሰማህ ለት ስሜታዊ የሆነ ምስሎችን ያመጣልሀል ለምሳሌ ቤቱን ጥሎ የወጣ ወታደር ቤቱ ሲመለስ ሰዎችን ሰዎች ሲረዱ የመሳሰሉ ፣ የደከመህ ቀን ቀለል ያሉ ምስሎችን እያደረጉ ከዛ platform እንዳትወጣ ጊዜህን እንድታጠፋ ያደርጉሀል። ከላይ የገለፅነውን psychological anticipation የ tiktok platform የሚጠቀመው ነው። ቀጣይ ምን ይመጣ በሚለው እዛው እንድትውል ያደርግሀል።
‎ ሌላው ቅልቅል ያለ ምስል ነው የሚለቁልህ አሁን ያስቁህና አሁን ያስለቅሱሀል አሁን ያስተክዙህና አሁን የ ማሰላሰል ያለው ነገር ይለቁልሀል ይሄ ይበልጥ የቆይታ ጊዜህን ያራዝመዋል dopamine high and low ሲሆን ሙድህን ይቆጣጠሩታል።

‎ እንዳይረዝም የመፍትሄ ሀሳቦችን በሌላ ቀን እንመለስበታለን!

@ourrthought
18👏3👍2
መፅሐፍ በማንበብ አንድ የምናጣው ነገር አለ ምንድነው ብትሉኝ ድንቁርና ጨለምተኝነታችን ይገፈፋል።

እንዳለጌታ ስለማንበብ ሲያወራ የሚያነሳት ምሳሌ አለችው

አንድ የ 80 አመት ዕድሜ ያለፋቸው አባት መፅሐፍ ሲያነቡ አይተው አሁን እርሶ እድሜዎት አልፏል በዚህ እድሜዎ ማንበብዎ ምን ሊበጅዎ ነው? ብለው ቢጠይቋቸው

"አዎ በርግጥ ማንበቤ አይጠቅመኝም ግን መልአከ ሞት መጥቶ ከየት ነው ያገኘኸው? ተብሎ ሲጠየቅ እያነበበ ነው ያገኘሁት እንዲል ነው የምፈልገው።"

ማንበብ ሙሉ ሰው ባያደርግህም ብዙ ጉድለትህን ግን ትሸፍንበታለህ!

@ourrthought
👍20🔥6💋1
‎ ‎ያንቺ ፍቅር....

‎     በ ውድቅት ሌሊት ከሩቅ በሽውታ እንደሚሰማ የቅዳሴ ዜማ በመዓልት እንደሚጣራ የ አዛን ዜማ ....
በውድቅት ሌሊት ናፍቆትሽ ፣ ትዝታሽ ፣ ሳቅሽ ፣ ጠረንሽ ፣ ሁሉ ነገርሽ እንደ ሽውታ በህሊናዬ ይመላለስብኛል...

‎             የአፀደ
        29.03.18 ዓ.ም


@ourrthought
👍2
የጥበቡ ልጅ #አል-አዛር

በውኑ ነብስ ነው የዘራኽባት ተባረክ አቦ

@ourrthought
🔥41
ነገረ ሀይማኖት ወ ጨዋታ

ዘነበ ወላ እንዳወጋት

ከለታት ባንዱ ቀን አንድ ሀበሻ በ ህንድ ሀገር ለጉብኝት ይከትማል። በጉብኝት ጊዜ ሲዘዋወር ታዲያ አንድ ህንዳዊ የ ቡዲሂዝም ተከታይ የ polytheism ተከታይ የሆነ የተለያዩ ምስል ያለባቸውን ምስሎችና ባል ስድስትም ባለ አራትም እግር እግር ጣዖቶችን ደርድሮ ሲፀልይ ይመለከታል።

ታዲያ ይሄ ሀበሻው ባየው ነገር ልቡ ይነካል። እንዴት ጣዖቶች ያመልካል? የ ጌታን ፍቅር ሰብኬው ከዚህ የጣዖት የዳቢሎስ ስራ ልታደገው ይገባል ብሎ እመር ብሎ ወደ ሰውየው ጠጋ ብሎ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትም መንገድም መሆን ስለሱ መሰቀሉን መፅሐፍ ቅዱስ እያጣቀሰ አይኑን ጨፍኖ (አልቅሶም ሊሆን ይችላል) ይሰብከዋል።

ህንዳዊውም ሰውዬ በጥሞና ከሰማው በኋላ "ይሄ ኢየሱስ ያልከው አምላክህ ክፉ ነው? ወይስ ደግ?" አለው ሽቅብ እያየው።

ሀበሻውም "የደጎች ደግ የመልካሞች መልካም ነው" አለ ስብከቱ ፍሬ እንዳገኘ ተሰምቶት እየፈነጠዘ።

ህንዱም " በጣም ጥሩ እንደነገርከኝ ከሆነ ድንቅ አምላክ ነው በውነቱ። እንደው የ አምላክህ ፎቶ ይኖርሀል" ሲል ይጠይቀዋል።

ሀበሻውም ፈጠን ብሎ" እንዴታ እንደውም የስቅለቱን ነው የምሰጥህ" ብሎ ትኩስ እንባውን እያዘራ ስቅለት ያለበትን ፎቶ ይሰጠዋል።

ህንዳዊው ባክብሮት ተቀብሎ በክብር ሳም ሳም ካደረገው በኋላ ከተደረደሩት ጣዖታት መካከል ፎቶውን እያስቀመጠው "በቃ ከዛሬ ጀምሮ 301 ኛው አምላኬ አድርጌ አመልከዋለሁ" ብሎ ወደ ፀሎቱ ተመለሰ።
***
moral of the story

ያመንከውንና የተቀበልከውን ነገር ሁሉ ሰዎች እንዲቀበሉት ማስገደድ ነውር ነው። አንተ የያዝከው እውነት በሌላ ጎን ላለ ሰው ከተረት ላይለይ ይችል ይሆናል።
በርግጥ ይሄ ሰውዬ ሲዖል ይገባል? ብባል በየት በኩል ልል እችላለሁ ቢያንስ ከ 301 አምላኮቹ አንዳቸው ያድኑታል።

@ourrthought
😁23👎1🤔1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሰብለ ወርቅ  መጽሐፍ የቆዩ መጸሐፍት

#ስልክ 0946523397 ይደውሉልን ፡


@sebleoldbook inbox 📑
1
ከራስ በላይ...

ዛሬ ከእንቅልፋችን በጊዜ ለምን ተነሳን? ካሉን ልብሶች ንፁህ የሆነውንና ያምርብናል ብለን ያሰብነውን ለምን መርጠን ለበስን? እግራችን እያጣየፈ ከቤት ይዞን ወጥቶ ወደ ትምህርት ቤት ወይንም መስሪያ ቤት ለምን ይወስደናል? እስከ አሁን አውቀን ተመራምረን የደረስንባቸው ነገሮች ለመኖራችን ዋስትናን ሰጥተውናል? ( ዓለም ላልተማረ ሰው ትልቅ ቦታ ብትሰጥ ግን ምን ያህላችን እንማር ነበር?)፤ ሰርተን ያካበትነው፣ ሰስተን የቆጠብነው ነገን ከስጋት ተላቀን መመልከት እንድንችል አድርጎናል?

ማህበረሰባዊነታችንስ? ምን ያህል የማይቀውን ብቸኝነት አስቀርቶልናል? የፈጠርናቸው ግንኙነቶች ራሳችንን ከመደበቂያነት ባለፈ እኛነታችንን ገልጦ በማሳየት ረገድ ምን ያህል ሚና አላቸው? በፍቅር ስም የመሰረትናቸው ግንኙነቶች ጥንካሬያቸው ምን ድረስ ነው? መፋታት ወይንም መለያየት አንዳችንን ለአንዳችን እንግዳ የሚያደርግን የሚደርገን ከሆነ ቀድሞውኑ የዝምድናው ህልውና ምን ያህል አስተማማኝ ነበረ?

አንዳችን ለአንዳችን መኖራችንን እየማልን ቃል እንገባለን። በህመም በጤናሽ፣ በሀዘን በሳቅህ፣ ላልከዳህ ላልከዳሽ እንላለን፤ ነገር ግን ጊዜው ደርሶ አብሮነት የሚፈተንበት ሰዓቱ ሲመጣ አብሮን የቆየውን " ከራስ በላይ ንፋስ " የሚለውን ብሂላችንን መዘን እንደ ጋሻ መዘዙን እንከልልበታለን።

በቁርጡ ቀን 'እኛነቱን' ያልጠበቀ አብሮነት እንዴት ያለ ይሁን???


#የዝናሽ-ልጅ

@ourrthought
18
ልፈወስ ተብሎ ከመም ከተሻረ
ይጠጣ የለም ወይ ኮሶ እየመረረ
አንዳንድ ጊዜ ዘራፍ ልበል እንጂ እንደወንድ
ወተት ብቻኮ ነው መገፋት የሚወድ

#ይሁኔ በላይ
#ምስጋናው_ደግ_ነው ከሚለው ሙዚቃ የተቀነጨበች

@ourrthought
👍9🔥2
Forwarded from ቀለም መጽሔት
ቀለም መጽሔት ቅጽ 1 እትም 6.pdf
5.7 MB
ቀለም መጽሔት🗞️

ቅፅ 1 እትም 6


እያነበባቹህ ለወዳጅዎ ያጋሩ
ለሀሳብ አስተያየት

@KelemMagazine

Telegram 👇❤️
@kelemofficial
👍41
ሳይታገሉ ያገኙት ነፃነት ከባርነት ይከፋል!

@ourrthought
👍95🔥3🤔2
ሰው አይመከርም!

ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለምዶም በሀዘኔታም ሰዎችን እንመክራለን። ግን ሰውን እንዲህ አድርግ እያሉ ሰዎችን መምከር በራሱ ሰዎቹ ላይ የሚያመጣው ጫና አለ። ማንኛውም ሰው ችግር ውስጥ ፈልጎ እንደማይገባው ሁሉ በሰው ምክርም ከዛ ችግር አይወጣም። ለጊዜው ሊወጣ ይችላል ግን ዘላቂ መፍትሄ የማግኘት እድሉ ጠባብ ነው። ባልተሰቀሉበት መስቀል መፍረድ ቀላል ነው እና ቀለል አድርገን ሰዎችን መምከር ለሰዎቹ ጫናውን ያብሰዋል።

ሁለት አይነት የ ምክክር ሂደት አለ Directive and Non directive ተብለው ይከፈላሉ።

Directive የሚባለው ሂደት ግለሰቡ ና አማካሪው ቁጭ ብለው ሰውየው እንዴት እዚህ ችግር ውስጥ እንደገባና እንዴት ከዚህ ውስጥ ሊወጣ እንደሚችል ከሰውየው ጋር የሚያቅዱበትና አማካሪው(counsellor) ግለሰቡ በቶሎ ችግሩን እንዲያገኘው የሚያግዝበት መንገድ ነው።

Non directive የሚባለው ደግሞ አማካሪው ምንም ጣልቃ ሳይገባበት ግለሰቡ እየመጣ ችግሩን ብቻ እያወራ የሚመለስበት ሲሆን ግለሰቡ ችግሩን በሚያወራበት ጊዜ እራሱ ለራሱ ንቁ እየሆነ የሚመጣበት ሂደት ነው።

ብዙ ሰዎች የስነ ልቦና የምክክር ሂደትን (counseling psychology) አንድ ችግር ያለበትን ሰው ቁጭ አድርጎ እየመከረ ማስተካከል ይመስላቸዋል። ግን የስነ-ልቦና አማካሪ (counselor) እንደዛ ያደርጋል? ወይ ካልን በፍፁም።

የ ምክክር ሂደት (counseling process) ችግር ያለበትን ሰው ቁጭ አድርጎ እየመከሩ የማስተካከል ሂደት ሳይሆን ግለሰቡ ያለበትን ችግር በራሱ እንዴት እንደሚያገኘውና እንደሚፈታው የሚያሳይ ሂደት ነው። እንጂ የመምከር አገልግሎት ሂደት አይደለም።

እና ምን ልላቹህ ነው ዝም ብሎ መስማት በራሱ ትልቅ እርዳታ ነው ግዴታ መምከር አይጠበቅባችሁም ለማለት ያክል ነው።

@ourrthought
👍125
ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት ወንድ አለ የሚያመነዝርና የማመንዘር እድሉን ያላገኘ!

በዕውቀቱ ስዩም


@ourrthought
🤣17🤔1
አንድ ወዳጄ ምን አለኝ "አለም ላይ ሀያል ለመሆን ሁለት ነገር ወሳኝ ናቸው ተስፋን እና ፍርሀትን ለሰዎች መሸጥ"።

ልከኛ ሀሳብ ናት የትም የ አለም ጥግ ብትሄድ መሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ ወይ የሀይማኖት ሰባኪዎች እንዚህን ነገሮች ነው የሚጠቀሙት። ፍርሀት ሰዎችን የሚያስገዛ ሀያሉ መሳሪያ ነው። political hypnotize የሚባል ነገር አለ። የፖለቲካ መሪዎች ትልቅ ጭራቅን ወይም ትልቅ አውሬ በህዝቡ አዕምሮ ምስል ይቀርፁለታል ከዛ ሀያል ጠላት ወይ ጭራቅ እነሱ እንደሚያድኑህ ይሰብኩሀል የዛኔ ቢከፉብህም ዘላለምህን እየተገዛህላቸው ትኖራለህ። ያለነሱ የሚታደግህ ያለ አይመስልህም ወይ እነሱ ከዛ ስልጣን ቢነሱ ሀገሪቷ የምትፈራርስ ይመስልሀል ይሄ እንግዲህ ፍርሀትን በደንብ አዕምሮህ ውስጥ አስገብተዋል ማለት ነው። ከፍርሀት ጋር አያይዘው ደግሞ ተስፋ ይሸጡልሀል ያኔ አዕምሮህ ታሰረ ማለት ነው። በርግጥ ዛሬም ድረስ ይሄ ዲስኩር አለ። የትም የ አለም ጫፍ ብትጓዝ ጠላት የማይሰበክበት ሀገር አታገኝም።

ሀይማኖትም ላይ ሴጣንና ሲዖል ታላቅ ማስፈራሪያና ሰዎችን እንዲገዙ ማድረጊያ መሳሪያቸው ነው። ተስፋ ሲሰጡህ ደግሞ ገነትንና የነሱን ሀይማኖት ብቸኛ ማምለጫ አድርገህ እንድትስል ያደርጉሀል ያም ለዘላለም የሚቀጥል ሰንሰለት ነው።

በግለሰብ ደረጃ ስትሄድ ደግሞ የምትሰራበት ድርጅት የመባረር ፍርሀትንና የደሞዝ ጭማሪ ባዶ ተስፋን ይግትሀል። ትንሽ ካስተዋልን አዕምሮዋችንን የሚቆጣጠሩት ነገሮች ተስፋንና ፍርሀትን ያጣመሩ ነገሮች ናቸው።

@ourrthought
👏11👍4
በለው ተሰማ የነፃነት ቀንዲል!

አለም ላይ አንዳንድ ነገሮች እንዲከሰቱ አንዳንድ ግለሰቦች ምክንያት ነበሩ። እኚህ ግለሰቦች ባይኖሩ አለም መልኳ ምን ይመስል እንደነበር ማሰብ ከባድ ነው። ሮዛ ፓርክን ዛሬም ድረስ አለም የሚያስታውሳት የጥቁር ታጋይ እና የነፃነት ተምሳሌት አድርጎ ነው። ሮዛ ፓርክስ በ Montgomery በ 1955 እ.ኤ.አ ጥቁሮች ከነጮች እኩል አንድ ባስ ላይ ተቀምጠው መሄድ በማይችሉበት ዘመን ላይ ለነጭ ወንበሬን አለቅም ብላት ነፃነትን የሰበከች ጀግና እና ፈር ቀዳጅ ብለን የምናስታውሳት የነፃነት ምሳሌ ናት። ከ ሮዛ በኋላ የጥቁር ነፃነት ጥያቄ ተፋፍሞ እስከ ነፃነት መቀዳጀት ደርሷል።

የ ፓኪስታኗን ማላላን የኛ ዘመን ሰው ስሟን ከፍ አድርጎ ይጠራል። በፓኪስታን ሴት ልጅ ከወንዶች እኩል መማር አለባቸው ብላ ስለነፃነት የሰበከች ህይወቷ አደጋ ላይ እስኪወድቅ ድረስ ዛሬም ድረስ የምትሟገት ነፃነትን እኩልነትን የምታሳድድ ምሳሌ ናት።

  ማንዴላ ፣ ማህተማ ፣ ማርቲን ዛሬም ድረስ አለም ስለነፃነትና መብት ሲሰብክ ስማቸው ይታወሳል። ሀገራችንስ ስንቶቹን ታስባቸው ይሆን? ስለ እኩልነት ስለ ነፃነት የሰበኩላትን ነብሳቸውን የሰጡላትን ብለን ብንጠይቅ ቄሱም ዝም መፅሐፉም ዝም እንዲሉ በቅጡ የማንይታወሱ ግን ዋጋ የከፈሉላት በርካቶች ናቸው። ዛሬ አንድ የሀገራችንን የመብት ታጋች እናንሳ እስኪ።

በለው ተሰማን ስንቶቻችን ይሆን የምናውቀው? ስንቶቻችንስ ጠጃችንን ስንልፍ ስሙ ትዝ ብሎን ይሆን? እንጃ ብቻ። ዘመኑ በንጉስ ተ/ሀይማኖት ዘመነ መንግስት ጊዜ ነው። ከዛ በፊት ጠጅ የንጉስ መጠጥ ነበር። ተራው ህዝብ የጠጅን ቀለም እንጂ የጠጅን ጣዕም አጣጥሞ አያውቅም ነበር። ለዛ ነው ጠጅ የንጉስ መጠጥ የሚባለው። በለው ተሰማ ተከስቶ ለህዝብ እስኪሆን ድረስ።

ከለታት አንድ ቀን በለው ተሰማ ይቺ ጠጅ ትከነክነው ጀመር። ለምንድነው እኛስ የማንቀምሰው የምትል የድፍረት ሀሳብ። ሺህ አመት ይኖራል? የት አባቱ ብድግ አድርጎ ጭልጥ ነዋ አይ በለው ጀግናው ጠጅን አጣጣመው ከዛስ በኋላ ቢሞት ምን ሊገደው ደስታን በጉሮሮ በኩል አጣጥሞታል። ተይዞ ንጉስ ፊት ቀረበ። ያው ይዘው ያቀረቡት ጠጅን ያልቀመሱ ግነ እንደሱ መቅመስ የሚመኙ ድፍረቱን ያጡ አሸከሮች መሆናቸውን ልብ በሉ።

ጠጁን ጠጥተሀል አሉት ንጉሱ። አዎ አለ እሱም በድፍረት። እኮ ለምን አሉት። አማረኝ ጠጣሁት እኛስ ከማን እናንሳለን ዙፋኑ ራቀን እንጂ 😊 ንጉ ለዚህ ድፍረቱ እጅና እግሩን ቆርጠው ግምጃ ቤት ገቢ አደረጉት ከዛን በኋላ ግን ጠጅን ተራው ህዝብ ስለቀመሰው የህዝብ ይሁን ረክሷል ተብሎ ታወጀ። የኛ በለው በሱ ምክንያት እኛም የንጉስን መጠጥ ዛሬም ድረስ እናጣጥመዋለን።

በለው የከፈለው መስዋትነትና ጀግንነት ከሌሎቹ ታጋዮች ቢብስ እንጂ የሚያንስ አይደለም እጅና እግሩን የገበረለት የነፃነት ጉዞ ነው። ታሪክ ግን ስሙንም ግብሩንም እረስቶታል። ጠጅ ቤት እንኳ ስሙ አይዘከርም። ቢሆንም ታጋያችን ነው። በሱ ምክንያት ጠጅ ጣዕሟን አውቀናታል። ስሙ ዛሬም ይታወሳል።

ችርስ ለጠጅ ቀሚቃሚዎች! ለበለው ተሰማ የነፃነት አባት!

@ourrthought
🔥17😁4
‎"...የሰው ልጅ ሁልጊዜ እንባ ውስጥ እንደዋኘ ነው። ነገር ግን በየጊዜው ከዋናው ወጣ እያለ ተጋድሞ የሳቅን ፀሐይ እንደሚሞቅ ደግሞ አትርሳ"

‎ዝም ብዬ አየሁት እውነቱን ነው።

‎"ሌላስ?" አልኩት

‎"እውነትን አታብዛ"

‎"ምን?"

‎" ህይወት ውስጥ እውነት ብቻውን አይገኝም። ህይወት እንደ ቡና በወተት ነው። ወተቱ እውነት ቡናው ውሸት ይሁን። ግን ይሄ ልዩነት ባንጎላችን ውስጥ ይኑር እንጂ ሲኒው ውስጥ በአንድ በኩል ቡናው በሌላው ወተት የለም። ሲኒው ውስጥ ያለው ቡና በወተት ነው። ህይወት ውስጥ በቀኝ በኩል እውነት በግራ በኩል ውሸት አይገኝም። ህይወት ውስጥ የምታገኘው የእውነትና የውሸት ቅልቅል ነው።"

ሌቱም አይነጋል
‎ስብሀት ገ/እግዚአብሔር


@ourrthought
13👍4👏1
ሐሳቦቻችን
Photo
ይሄን የመሰለ ፊልም እስከዛሬ አለማየቴ አስገርሞኛል። ፊልሙ እ.ኤ.አ በ 2002 የተሰራ ፊልም ነው። የፊልሙ አርዕስት Equilibrium የተሰኘ ነው። ፊልሙ በ totalitarian ላይ የተመሰረተ ነው። totalitarian ማለት አገዛዙ የፈቀደልህንና የወሰነልህን ገደብ መኖር እንደማለት ነው።

ፊልሙ ጭብጡን ያደረገው በ totalitarian ሀሳብ ላይ ሆኖ ስሜታችን feeling, sense and emotion የሚባሉት ነገሮች የማይፈቀዱበት እንደወንጀል የሚቆጠርበት ሀገረ መንግስት ነው። ለነገሮች ያለን ስሜት ነው ጦርነቶችና መገዳደሎችን ያስከተሉብን የሚል ሀሳብን በመያዝ የሀገሬው መንግስት ህዝቡ ሁሉ ምንም አይነት ስሜትን እንዳይሰማው በየቀኑ የሚወስዱት መድሀኒት ይሰጣቸዋል። በርግጥ ህዝቡ ግን ያን መድሀኒት ስሜታቸውን እንደሚገለው የሚያውቁት ነገር የለም መድሀኒቱን በየቀኑ በስረመንጅ መልክ መወጋት ግዴታቸው ነው እሱን ያላደረገ በሽብር ወንጀል ይከሰሳል የሞት ፍርድ ይፈረድበታል።

እዚህ ከተማ ውስጥ ምንም አይነት ስሜትን የሚቀሰቅስ ነገር ማድረግ አይቻልም እንስሳትን ማሳደግ አይፈቀድም የጥበብ ስራዎችን መመልከትም ሆነ በመፅሐፍ መልክ ማየትም መስማትም የተከለከለ ነው። ስዕል ፣ ሙዚቃ ፣ ጌጣጌጥ ፣ መስታወት ፣ ቤትን ማስዋብ....ምንም ከስሜት ጋር የተገናኘ ነገር ካደረጉ  የስሜት ተጠርጣሪዎች (sense offenders) ተብለህ ትገደላለህ። ማልቀስ መሳቅ ማፍቀር ውጉዝ ናቸው።

ፊልሙ ሲጀምር የስሜት ተጠርጣሪዎችን በማሳደድ ሲጀምር ይታያል። ከዛም ሁሉንም ተጠርጣሪዎች ከገዱ በኋላ ቤት ውስጥ ያሉትን የጥበብ ስራዎች በሙሉ እንዲቃጠሉ ያዛል እዛ ቤት ውስጥ የሞናሊዛ ስዕልም አብሮ ሲቃጠል ይጀምራል። የዛ ከተማ ኗሪዎች ሚለብሱት ፣ የሚኖሩበት ፣ የሚመገቡት የሁሉም ተመሳሳይ ኑሮን የሚከተል ነው።

እና ባንድ ወቅት ዋና ገፅ በሀሪው የ ከተማዋ ኤጀንት clierk ጠዋት እንክብሏ ወድቃ ትሰበርበታለች ከዛን በኋላ ነገሮች ይሰሙት ይጀምራሉ። ለእንስሳ ፣ ለሚገላቸው ሰዎች ፣ ለነገሮች ስሜት ይሰማው ይጀምራል እያለ የሚቀጥል ፊልም ነው።

በርግጥ ይሄን ፊልም ሳይ የሰው ልጅ ለነገሮች ምንም የማይሰማው ከሆነ ከ አውሮ እንደሚብስና ሮቦት እንደሚሆን ያሳያል። ለልጅህ ለቤተሰብህ ለሰው ለ እንስሳ የማታዝን ከሆነ ለ ስነ ጥበብ ግጥም ሙዚቃ ቦታ ከሌለው ሰው ምንድነው? እንድትሉ የሚያደርግ ነው። ይሄን ፊልም አሁን ካለንበት ዘመን ጋር ብናመጣው ለነገሮች ስሜት ያጣበት ዘመን ላይ ነው። ይሄ ማለት በፊልሙ ላይ ያለውን አይነት ከተማ ለመምሰል ብዙ አንርቅም በመንግስት ጫና ሳይሆን አሁን የተጠናወተን አግበስባሽነት (consumerism) ጋር ይገናኛል። ፊልሙ ላይ ያለችው በየቀኑ የሚወስዷት ስሜት አልባዋ እንክብል እዚህ ዘመን ላይ አግበስባሽነት በሏት።

አሁን ላይ ሰው ደስታን ፍለጋ የማያግበሰብሰው ነገር የለም ግን ደስታ እንደ ሰማይ የራቀው ይመስላል። ከ 19 ነኛው ክፍለ ዘመን በኋላ materialism የገነነበት አለም ነገሮች በመሰብሰብ የሚያምን ከነገሮች ጋር ግንኙነቱ የተቋረጠ ብዙ ስዕል በቤቱ ቢደረደርም ስሜት ማግኘት የቸገረው ለስሜቱ ብዙ ርቀትም ቢሄድ ስሜት አልባ የሆነው postmodernism ዘመን ይሄ ፊልም ብዙ ጭብጥ ይሰጠናል። ስሜት ማጣት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ፊልሙን ኮምኩሙት። ፊልሙን ሀሳብ መስጫ ላይ አስቀምጥላቹሀለሁ

@ourrthought
👍105
የዛ ማዶ ሰዎች ዘፈን አያምራቸው
አጅሬ ትዝታ አልገባም ቤታቸው


አስቴር አወቀ
ትዝታ


@ourrthought
8