ሐሳቦቻችን
981 subscribers
103 photos
4 videos
5 files
2 links
በዚ ቻናል ላይ የተለያዩ ሀሳቦቻችንን ፣ ምልከታዎቻችንን ፣ ትዝብታችንን ፣ ከተለያዩ መልኮች እያነሳን እንወያያለን!

ሀሳብና አስተያየት ካላቹ @haileabb
Download Telegram
‎ሰው ሰውነትን ለመገንባት የሄደበት መንገድ የተሳሳተ እንደሆነ አስባለሁ። ምድር የእብዶች ጉባኤ ሆናለች። ዓለምን የ አመጻ ቤተሙከራ አድርገዋታል። ቀደም ባለው ጊዜ በቅዱሳቱና ተረታቱ መጻሐፍት እንደተነገረን በዚህ በ አመጻ ግብሩ አማልክት ሳይቀሩ ተሳታፊ ነበሩ። በጥንቱ ዘመን ሰዎች ጠንካራ ህብረትና መተባበር እንዲመሰርቱ ብሎም ትንንሽ ግዛቶችና ሀገራት እንዲፈጠሩ ጦርነቶች ሚና እንደነበራቸው ይነገራል። ምናልባት ዘመኑ < Age of formation> ስለነበር ይሄን ፈቅዶ ይሆናል። አሁን ግን ዘመኑ የመበስበስ ፣ የመፈራረስ < Age of decadence> በመሆኑ በጦርነት የምትፈራርስ እንጂ የምትገነባ ሀገር አትኖርም።


በፍም እሳት ማቃመስ
‎ ያዕቆብ ብርሀኑ


@ourrthought
👏7
ሚስት : ሴቶች ሁል ጊዜ ቤት ውስጥ ምግብ እየሰሩ ባላቸውን መመገብ ግዴታ ያለባቸው ይመስሀል እንዴ😡

ባል : አዎ ግዴታችሁ ነው!

ሚስት: እንዴት ሲባል😡

ባል: በህጉ መሠረት እስረኛ በቀን ሦስት ጊዜ መመገብ አለበት ይላል።🙄

ሚስት : እስረኛ ነኝ ብለህ ነው የምታስበው 🤬

ባል : ካልሆንኩኝ ሌላ ሴት ጋር እንድሄድ ፍቀጂልኛ☺️

ሚስት : ቁጭ በል : ንቅንቅ እንዳትል! ጥይቷን ደቅናበት

ከዛን በሰላም ተስማሙ! በንግግር የማይፈታ ነገር የለም።

@ourrthought
😁23🔥2
ሀበሻ ልቦና ውስጥ እግዜር አፈግፍጓል

ዓለማየሁ ገላጋይ የተጠላው እንዳልተጠላው በሚለው መፅሐፉ መግቢያ ላይ "ሰዎች ሲበረቱ እግዚአብሔር ያፈገፍጋል።
‎ከህሊናቸው ፣ ከመንፈሳቸው ፣ ከነብሳቸው ይወጣል።" ብሎ ይጀምርና በዚሁ ምዕራፉ ዝቅ ብሎ ደሞ " ኢትዮጵያውያን መች ይበረታሉ?
‎እግዚአብሔራቸው የሚያፈገፍግበት ቀኑ መቼ ነው?
‎ከህሊናቸው ፣ ከመንፈሳቸው ፣ ከነብሳቸው የሚወጣው?
‎ ፍዳቸውን ስራቸውን ፤ ሀብታቸውን እንደምን ይተውላቸዋል?" ይላል። እኔም እላለሁ የ እግዚአብሔር መልኩ በኢትዮጵያውያን ላይ የት አለና? በመንፈሳችን ፣ በህሊናችን ፣ በነብሳችን እግዚአብሔርን ካሸሸን አያሌ ብዙ ጊዜያት ተቆጠሩ።

‎በቅርቡ የአለም መንግስታት በአለም ላይ ያለውን የ ሀይማኖት ስብጥር ባስቀመጠበት ቻርተሩ ላይ ሀገራችን በ አማኞች ብዛት ከ አለም በቁጥር 1 የ አማኝ ብዛት ያለባት ሀገር እንደሆነች ይገልፃል። አስቡት ሀገራችን በቁጥሩ ብትመራም የሀይማኖቶቹን ስነ ምግባር በመጣስ ሰብዐዊነትን በመደፍጠጥ የሚደርሰን የለም። ሀይማኖተኛ ነን በምንልበት ሀገር ላይ በ ሀይማኖት የምንገዳደል ፣ ሰው ዘቅዝቀን የምንገድል ፣ በ ቪዲዮ እየቀረፅን የምናርድ ፣ ህፃናትን የምንጨፈጭፍ ከኛስ ውጪ በጭካኔው የሚበልጠን ይኖር ይሆን?

‎እግዚአብሔር ሲባል ውጪ ያለ አካል የምናስስ ከሆነ ያስቀኛል። እግዚአብሔር የልባችን ቅንነትና መልካምነት አይደለምን? እኛ ግን ከልባችን ይልቅ ግዙፍ ቤተመቅደሶችን በብዙ ብር እንገነባለን። "ሰማይም ለዙፋኔ : ምድርም ለመረገጫዬ አትበቃኝም" ላለው ፈጣሪ በቤተመቅደሶቻችን ልናጥረው ቤተ እምነቶች ይታነፃሉ። ልባችን ግን ከዛ ርቋል : በምንለው ልክ ቅንነትና አምልኮ ውስጣችን የለም : ለይምሰል ልምድ ሆኖብን በየ ቤተክርስቲያኑና መስጂዱ እንመላለሳለን እንጂ።

‎ለ አውሮፓውያን የ እግዜርን መሞት ኒቼ በ Thus spake Zarathustra መፅሐፉ እንዳረዳቸው። ለእኛም የሚያረዳንን በመጠባበቅ አመታት አልፎናል። ዛሬም ድረስ ስለሌለን መልካምነትና ቅንነት ከበሮ እንደልቃለን። እኛኮ ዘመንን የቀደምን ህዝቦች ነን እያልን ስናወራ እንኳ እፍረቱ የለንም። ዛሬም ድረስ ላሊበላ ስለሰራው ቤተመቅደስ እኛኮ ብለን እንታበያለን ግን እንዴት እንኳ እንደተሰራ ማብራራቱ ከብዶናል። የ ሐረር መስጂዶችን ዛሬ የሚያንፃቸው ቀርቶ የሚያብራራቸውም የለም ግን ዘወትር ባለፈው ተተብትበን ማንትቤዎቻችን ስለሰሩት ነገር እኛ እንደሰራን ይወራል። ኢትዮጵያውያን ፈርሀ እግዚያር ናቸው ይባላል። እኛ ግን ፈጣሪን በልባችን ከቀበርነው አመታት አልፈዋል። በስሙ ዛሬም ድረስ ይነገድበት ይሆናል እንጂ የፈጣሪን መልክ በህዝባችን ላይ ካጣነው የትየለሌ ዘመን ሆኗል። ፈጣሪ ከሀበሻ ልብ ውስጥ አፈግፍጓል።

Sigmund Freud "Identification" ego defense mechanism የሚባል እሳቤ አለው። እራሱን ከፀፀትና ከተጠያቂነት እራሱን ego ውን የሚሸፍንበት ከዛ ዘዴዎች ውስጥ እኛ እንደ ሀገር collective conscious የምንጠቀመው Identification የሚባል ዘዴ ነው። ይሄ ego defense mechanism እኛ ያላሳካነውን ግን ሌሎች ሰዎች ያሳኩትን ነገር እራሳችንን አካተን ማሰብና መፅናናት ነው። አሁን ኢትዮጵያ ምን አይነት ሀገር ናት ብትሉ አንድ ሰው አቁማቹሁ ጥንት ስልጣኔ ያነፅን ላሊበላን የገነባን ጣሊያንን ያባረርን ብሎ ነው የሚያብራራው እራሱን ያልነበረበት ቦታ ከቶ ነው ሚያብራራው። ይሄ ዘዴ ደሞ Identification ego defense ይባላል። በሀይማኖቱም ተመሳሳይ ነው። የድሮውን ፅድቃችንን እንጂ አሁን ላይ የምናወራው ፅድቅ የለንም።

‎ሀበሻ የፈጣሪን ስም የሚጠራው ለስንፍናው እና ለንዋይ ከሆነ ሰነባበተ። ቅዱስ መፅሐፉም የሚለውም "ኢትዮጵያዊ ቀለሙን ነብር ዥንጉርጉርነቱን አይተውም" የሚለው። ይሄ ይሄ ስንፍናችንን ይሆን?

@ourrthought
🙏6💔43👏2
‎የ/አ/ጨ/ላ/ማ

‎የተባበሩት የአለም ጨጓራ ላጭ እና አቃጣይ ማህበር ድርጅት ሀገራችን ነው ለካ ያለው። ከላይ እስከ ታች ያለክፍያ በትጋት የምንሰራው ብቸኛው ስራ ነው።

ከመ አርዮስ ውጉዝ

@ourrthought
😢4🤣1
ፈረንጅ ትራንስፖርት ለትንሽ ሲያመልጠው : አርፍጃለሁ ማለት ነው ለሌላ ጊዜ በጊዜ ነው የምነሳው ቀደም ብዬ። ላሁን ቀጣይዋን ልያዝና ልድረስ።

ሀበሻ ትራንስፖርት ሲያመልጠው : ፈጣሪዬ ከ አደጋ ሊያተርፈኝ ነው ያስመለጠኝ። ቆይ እንደውም የ አደጋ ዜና ልከታተል ብሎ ያመለጠውን መኪና ተገለበጠ የሚል ዜና ይጠባበቃል።

ዘይገርም ነው ጃል😤

@ourrthought
😁261
‎ ቴ/ተክለ አረጋይ ፍልስምና በሚለው መፅሐፉ ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝን ቃለመጠይቅ ባደረገበት ላይ ስለ ህይወት የተናገረው ነገር ይገዛኛል። ሐሳቧ እንዲህ ናት " ህይወት ማለት ወይ ማዘን ወይ መደሰት በሚሉት የመንቶ እሳቤ የሚመራ አይደለም። ብዙ ሰው ደስተኛ ካልሆነ ያዘነ ይመስለዋል ፣ ካዘነ ደሞ ደስተኛ ያልሆነ ይመስለዋል። እና ህይወቱ በነዚህ ሁለት ፅንፎች የሚመራ ይመስለዋል። ግን ህይወት ላይ ስንኖር መደበኛ ኑሮ ነው የምንኖረው። ደስታም ሆነ መከራ በየፈረቃ እየተቀያየረ የሚመጣ ነገር እንጂ አብዛኛው ኑሮዋችን ዝም ብለን ነው የምንኖረው። ደስታም የሆነ ጊዜ ላይ ይመጣል : ሀዘንም እንደዛው። ሁለቱም በሆነ ወቅት እየሄዱ የሚመጡ ጉዳዮች ናቸው።" የምትል ሀሳብ ናት።

‎ እና አስተውለን ካየነው ሀሳቡ ገዢ ሀሳብ ነው። አብዛኛው ኑሮዋችን ሀዘንም ደስታም ውጡ የለሌለበት ዝም ያለ ነው። ለሁሉም ነገር ቢሆን መደበኛ ስሜት ነው የሚኖረን መከፋትም መደሰትም የሌለበት ህይወት ነው። ይሄን ካለማስተዋል አንዳንዴ ህይወታችን ሙሉ በስቃይ ያለፍን ይመስለናል። ወይ ደሞ በደስታ ብቻ የተሞላ። ይሄን ዝም ያለውን ኑሮ ልብ ብለነው አናውቅም። ህይወታችን ላይ መቼ ነው የምንደሰተው?  ብለን ወደ ኋላ ስንመለከት የሚታወሰን የተሰቃየንባቸው የመከራ ጊዜያቶቻችን ናቸው።

‎ግን ይሄን ዝም ያለውን መከፋትም መደሰትም የሌለበትን ህይወት ማስታወስ የቻለ ህይወት ደስታ ወይ ደሞ መከራ ብቻ እንዳልሆነ ይረዳል። ይልቅስ ደስታም ሆነ መከራ እየተፈራረቁ የሚመጡ የህይወት ዑደቶች እንደሆኑ ልብ ይሏል።

@ourrthought
👍64
ሐሳቦቻችን
Photo
Existential crisis + Nihilistic = suicide

‎በየ ዘመናቱ ብንመለከት ዘመኑን የሚመራ መንፈስ (sprit of the time) አለው። ይህ ጊዜውን የሚመራ መንፈስ ማለት ጊዜው ላይ ያለው የህዝቡ ስነ ልቦና ባብዛኛው የሚያጋድልበት ጉዳይ ማለት ነው። ከጥንት ጀምሮ ብንመለከት በየ ዘመናቱ የሰውን ልጅ በጋራ የሚመሩት የጋራ ደመነብሱን (collective unconscious) የሚዘውሩት እንደነበሩ ታስተውላላቹህ። የ ኢንዱስትሪ አብዮት ፣ የ ሶሻሊስም ፣ ካፒታሊዝም ፣ የጥቁሮች ነፃነት ንቅናቄ ፣ የሴት ልጅ ነፃነት ንቅናቄ..... አሁን ላይ የጊዜው መንፈስ ያለው የሰው የጋራ ደመነብስ የሚዘወርለት የጊዜውን መንፈስ ብትመለከቱ ባብዛኛው የህይወት ትርጉም ማጣት ላይ ያተኩራል።

‎ዘመኑ በዚህ ደረጃ የህይወት ትርጉም ማጣት ጋር ተፋጠጠ? የሚለውን ጥያቄ እንዴት ከሌላው ዘመን በተለየ መልኩ በዚህ ድህረ ካፒታሊስት አለም ላይ በረታ? የሚለውን በትንሹ ተንትነን እንመልከተው።

‎ወደ ጥንት የሰው ልጅ ዘር መለስ ብለን የተመለከትን እንደሆነ ሰዎች በጋራ ህይወታቸውን እያቆዩ ለመኖር ከተፈጥሮና ከ አራዊቱ ጋር ሲታገሉ የሚኖሩበትን መንገድ እናስተውላለን። ይህ ትግላቸው እንግዲህ የማያቋርጥ በመሆኑ ህይወታቸው በሙሉ በውጥረት የተሞላና ለምንድነው የተፈጠርኩት ከሚለው ጥያቄ በላይ እንዴት ነው ነብሴን የማቆየው ብለው የሚታገሉበት ዘመን ነበር።

‎ከጥንቱ የሰው ልጅ መለስ ብለን ቀረብ ለሚሉት ዘመን ላይ ስንመለከት አሁንም ቢሆን ሰዎች ትልቁ የህይወታቸው ትግል ህይወታቸውን የማሰቀጠል (survival mode) ላይ ሆነው በዚህ ሁኔታ ውስጥ ግን የህይወትን ምንነት በሀይማኖቶች ውስጥ ትርጉም እየሰጡ በዛም ጥያቄ እረክተው እናገኛቸዋለን።

‎ከላይ ባየናቸው ሁለቱ ምሳሌዎች ሰዎች ከህይወት ትርጉም በላይ ህይወታቸውን የሚያቆዩበት ነገር ይበልጥ እንደሚያስጨንቃቸው እናያለን። ታዲያ የዛኔ እምብዛም የሌለው የህይወት ትርጉም ማጣት አሁን ለምን ትልቁ ፈተና ሆነ?  ብለን እንተንትነው። የሰው ልጅ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በማህበረሰብ እሴትና ደንብ ፣ በሀይማኖት ፣ በስነ ምግባር ፣ በህግጋቶች በመሳሰሉት ነገሮች ታጥሮ የህይወቱን ትርጉም በነዚህ ውስጥ እየመለሰ የሚኖር ሆኖ የቆየ ነበር። አሁን ላይ ግን በነፃነት ስም እንዲሁም የግለሰባዊነት መስፋፋት የሰው ልጅ ከ ሀይማኖት ፣ ከቤተሰብ ፣ ከማህበረሰቡ ፣ ከ ሞራል ፣ ከህግጋት ገደቦች ተነጥሎ ተነጥሎ ብቻውን በመቅረቱ የህይወት ትርጉምን ምላሽ የሚሰጥበት መንገድን አጥቷል። በራሱ መንገድም የሚሰጠው ትርጉም የሚያረካው አልሆነም። መነሻው እራሱ ነውና ከባዶ ነገር ላይ ተነስቶ የሚሰጠው ትርጉም በየጊዜው እየተቀያየረ በነገሮች ግራ የተጋባ ሆኗል።

‎ ይህ ጥያቄ (የህይወት ትርጉም) ከ አፍሪካ ይልቅ በምዕራቡ አለም ላይ ይበልጥ የሚሰተዋል ጉዳይ ነው። የምዕራቡ አለም ያለበት የጊዜ መንፈስ (sprite of the time) ግለሰባዊ ነፃነት (individual liberty) ሰዎች ለጥያቄው መልስ ለመስጠት የሚነሱበት መነሻ ቦታን አሳጥቷቸዋል። ሌላው የሚታገሉለት ነገር በመቀነሱ ለዚህ ቀውስ ዳርጓቸዋል። ወደ አፍሪካ ስንመጣ አፍሪካ ላይ ዛሬም ድረስ የ ሀይማኖቶች ፣ ማህበራዊ መስተጋብሩ ፣ ባህል ፣ እሴት አለመፈረሳቸው ይሄን ጥያቄ ለመመለስ ሲረዳቸው ማስተዋል ይቻላል። አፍሪካ ውስጥ አሁንም ድረስ ለኑሮ የመታገሉ (survival mode) ላይ መሆናችን የህይወታችንን ትርጉም ለምንድነው የምኖረው? ከሚለው ጥያቄ በላይ እንዴት ነው የምኖረው? የሚለውን ለመመለስ በሚደረገው ትግል ውስጥ የህይወት ጥያቄያቸውን የሚኖሩበትን ምክንያት በ ህይወት መቆየት ጋር በማያያዛችን እራስን ከማጥፋት ከ አውሮፓውያን ይልቅ በኛ የማይስተዋለው ለዛ ነው።

‎ እንደ መጠቅለያ አንድ ማህበረሰብ ለህይወት ለመቆየት በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ ለህይወቱ የሚታገለው ነገሮች እየተቀነሱና አልጋ ባልጋ እየሆኑ በመጡ ቀጥር ይህ ጥያቄ በ እጅጉ ይበረታል። ሁሉን በማግኘት ውስጥ ሁሉን እንደማጣት ያለ የተራነት ስሜት ማለት ነው።
‎ ከ አንድ ወዳጄ ጋር በሀሳብ ዙሪያ ስንጨዋወት የ አፍሪካን ኑሮ እንዲህ መሆኑን እያማረረና የ አውሮፓ ኑሮ አልጋ ባልጋ መሆኑን እያወደሰ አብራራልኝ። በርግጥ ሀሳቡ ልክ ቢሆንም የኔ ምላሽ የነበረው ቢያንስ እኛ ይሄን ኑሮ ለማሸነፍ በምናደርገው ትግል ውስጥ የህይወት ትርጉማችንን መስራት ችለናል። ለብዙ ሰው ይሄን ህይወት ማሸነፍ የህይወት ዘመን ግቡ ነው። ይሄ ደሞ መልካም ጎን አለው ህይወቱን ከከንቱነት ታድጎለታልና። አፍሪካ ውስጥ ያለ ህይወት በራሱ የህይወት ግብ መሆን ይችላል። ህይወትን ማቆየት (survival mode) ከህይወት ከንቱነት(Nihilistic thought) የተሻለ ነው።

‎ ይህ ዘመን ከመሞት በላይ ለመኖር ከባድ ፈተና ያለበት ጊዜ ነው። ህይወትን ማቆየት በራሱ የህይወት ትርጉም ነው።

@ourrthought

#ሐሳቦቻችን
#ourrthought
9👏4🔥1
Western

“You are responsible for your own success or failure.”

Africa

"We raise together, we fall together"


These quotes show our psychological makeup.

@ourrthought
👍5🤔3😁1
የማህበራዊ ሚዲያ መልካችን

‎አንዳንዴ ረብ የለሽ የ YouTube , tiktok , Facebook...... አጫጭር ምስሎችን (video) ለረጅም ጊዜ የማያት አባዜ አጋጥሟቹህ አያውቅም?

‎ከተወሰኑ ጊዜናቶች በፊት ጊዜዬን የማጠፋባቸው የ ዩቱዩብና የ ፌስቡክ አጫጭር ምስሎች ምንም ጥቅም የሌላቸውና እርባና ቢስ ነበሩ። ለምሳሌ ለረጅም ሰዐት ፈረንጆች የ ሀገራችንን ምግብ እያዳነቁ ሲበሉ ፣ ከቤቱ ከወጣ የቆየ የ አሜሪካ ወታደር ቤት ሲገባ ያለውን የቤተሰብ ደስታ ፣ ፅድት ያሉ ውሾች ቤት ውስጥ እንክብካቤ ሲደረግላቸው.....የመሳሰሉ ምስሎችን ጥቅም እንደሌላቸው እያወኩኝ ግን ለረጅም ጊዜ አፍጥጬባቸው የምውልባቸው ነበሩ። አይቼ ስጨርስ ከራሴ ጋር ቅራኔ እገባለሁ ጊዜዬን በከንቱ ለምን አባክናለሁ ብዬ።

‎ ይሄን ድርጊቴን ለምን እንደማደርገው ምክንያቱን ባሰላስለው ለራሴ ላገኘው አልቻልኩም። ታዲያ ጉዳዩን ሰሞኑን ለ chat GPT ሳማክረው የሰጠኝን ምላሽ ጥሩ ሆኖ ስላገኘሁትና ስለጠቀመኝ ለናንተም ላካፍላቹህ።

‎የማይረቡ ጥቅም የሌላቸውን ምስሎች የማዘውተር ጉዳይ በ psychology ሲብራራ በ 4 ዋና ዋና ጉዳዮች  የሚብራራ የ አዕምሮ የልማድ ስርአት ነው። አብዛኛውን ጊዜ በጣም ስንጨነቅ ፣ የመዛል ስሜት ሲሰማን (በአካልም በ አዕምሮም) እና በትክክለኛ መንገድ አዕምሮዋችን የሚደሰትበትን ነገር ሲያጣ የሚከሰት ነው። አራቱን ዘርዝረን እንያቸው

‎1. Neurological explanation

‎አዕምሮዋችን ከሰውነታችን ክፍል 20% ሀይል (energy) ይወስድብናል። በዛ ምክንያት ብዙ ሀይል ላለመጠቀም በትናንሽ የደስታ ቅንጣቶች (Dopamine) መደሰትን ይመርጣል። ማሰብ የሚጠይቁ ወይም አስተማሪ ምስሎችን ጉልበት ስለሚወስዱበት ከዛ ይልቅ ምንም ማሰብ በማይጠይቁ በፈጣን ምስሎች ፣ ቀለም በበዛባቸው ፣ የውድድር ፣ የቦክስ ግጥሚያ ፣ ቶሎ ቶሎ በሚያልቁ ምስሎች በትንሽ ሀይል ትናንሽ ዶፓሚን እያገኘ የፍታታል። አዕምሮ ይሄን የሚያደርገው ድካም ሲሰማው ፣ ሲዝልና ትላልቅ ማሰላሰል ጉዳዮችን ላለማሰብ በትንሹ መደሰትን ይመርጣል።

‎2. Psychological anticipation

‎" ይህ እንግዲ ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ" የሚሉትን ብሂል የሚከተል መሆኑ ነው። የትኛውንም ቪዲዮ ስናይ ቀጣይ የተሻለ እንደሆነ የመጠበቅ አባዜ እንደማለት ነው። አዕምሮ ካሁን ይልቅ ቀጣይ የሚመጣው የተሻለ ነው ብሎ ያስባል ታዲያ አስቦ ብቻ አያበቃም ቀጣዩን የማሰብ ጉጉት ይፈጥርበታል በዚ ጊዜ የደስታ ሆርሞን ይለቃል ማለት ነው። ይሄ ጉዳዩ ከ ምታዩት የ ምስል ይዘት እፃር ሳይሆን እንደ ቁማር በሉት የመጠባበቅ ሱስ ውስጥ ትገባላቹህ። tiktok ላይ የቀጣዩ የተሻለ ይሆናል እያላቹህ የምታጠፉትን ጊዜ ልብ ካላችሁት ይገለፅላቹሀል።

‎3. Escaping from unwanted thinking

‎አንዳንዴ ህይወትህ ላይ ከባባድ ነገር ሲያጋጥምህ ፣ ወደፊትህን ስታይ ሲጨልምብህ ፣ የምታስበው ነገር ውጥረት ውስጥ ሲከትህ ከዚህ ስሜት ለመውጣት እንደነዚህ አይነት ፈጣንና ማሰላሰል የማይፈልግ ምስል ታያለህ።

‎4. Algorithm Manipulation

‎የምታየውን አንተ ነህ የምትመርጠው? ወይስ የምታየውን ነገር platform ይመርጥልሀል?
‎ ይሄን ሀሳብ ለብቻው ብፅፍበት ደስ የሚለኝ ሰፊ ትንታኔ የሚፈልግ ነው።
‎YouTube ፣ tiktok ፣ Facebook ፣ Instagram.....እነዚህ platform አንተን ካንተ በላይ የሚያው ናቸው። መረጃህን እርስ በርስ ይሻሻጡታል ምን ቪዲዮ ላይ ምን ያክል እንደቆየህ ፣ ምን እንደምትወድ ፣ ምን እንደሚደብርህ....እያንዳንዱ ነገርህን እያጠኑ መረጃህን ይይዙታል ሲደብርህ ፈጠን ያለ ምስል ይለቁልሀል ፣ ብቸነት የተሰማህ ለት ስሜታዊ የሆነ ምስሎችን ያመጣልሀል ለምሳሌ ቤቱን ጥሎ የወጣ ወታደር ቤቱ ሲመለስ ሰዎችን ሰዎች ሲረዱ የመሳሰሉ ፣ የደከመህ ቀን ቀለል ያሉ ምስሎችን እያደረጉ ከዛ platform እንዳትወጣ ጊዜህን እንድታጠፋ ያደርጉሀል። ከላይ የገለፅነውን psychological anticipation የ tiktok platform የሚጠቀመው ነው። ቀጣይ ምን ይመጣ በሚለው እዛው እንድትውል ያደርግሀል።
‎ ሌላው ቅልቅል ያለ ምስል ነው የሚለቁልህ አሁን ያስቁህና አሁን ያስለቅሱሀል አሁን ያስተክዙህና አሁን የ ማሰላሰል ያለው ነገር ይለቁልሀል ይሄ ይበልጥ የቆይታ ጊዜህን ያራዝመዋል dopamine high and low ሲሆን ሙድህን ይቆጣጠሩታል።

‎ እንዳይረዝም የመፍትሄ ሀሳቦችን በሌላ ቀን እንመለስበታለን!

@ourrthought
18👏3👍2
መፅሐፍ በማንበብ አንድ የምናጣው ነገር አለ ምንድነው ብትሉኝ ድንቁርና ጨለምተኝነታችን ይገፈፋል።

እንዳለጌታ ስለማንበብ ሲያወራ የሚያነሳት ምሳሌ አለችው

አንድ የ 80 አመት ዕድሜ ያለፋቸው አባት መፅሐፍ ሲያነቡ አይተው አሁን እርሶ እድሜዎት አልፏል በዚህ እድሜዎ ማንበብዎ ምን ሊበጅዎ ነው? ብለው ቢጠይቋቸው

"አዎ በርግጥ ማንበቤ አይጠቅመኝም ግን መልአከ ሞት መጥቶ ከየት ነው ያገኘኸው? ተብሎ ሲጠየቅ እያነበበ ነው ያገኘሁት እንዲል ነው የምፈልገው።"

ማንበብ ሙሉ ሰው ባያደርግህም ብዙ ጉድለትህን ግን ትሸፍንበታለህ!

@ourrthought
👍20🔥6💋1
‎ ‎ያንቺ ፍቅር....

‎     በ ውድቅት ሌሊት ከሩቅ በሽውታ እንደሚሰማ የቅዳሴ ዜማ በመዓልት እንደሚጣራ የ አዛን ዜማ ....
በውድቅት ሌሊት ናፍቆትሽ ፣ ትዝታሽ ፣ ሳቅሽ ፣ ጠረንሽ ፣ ሁሉ ነገርሽ እንደ ሽውታ በህሊናዬ ይመላለስብኛል...

‎             የአፀደ
        29.03.18 ዓ.ም


@ourrthought
👍2
የጥበቡ ልጅ #አል-አዛር

በውኑ ነብስ ነው የዘራኽባት ተባረክ አቦ

@ourrthought
🔥41
ነገረ ሀይማኖት ወ ጨዋታ

ዘነበ ወላ እንዳወጋት

ከለታት ባንዱ ቀን አንድ ሀበሻ በ ህንድ ሀገር ለጉብኝት ይከትማል። በጉብኝት ጊዜ ሲዘዋወር ታዲያ አንድ ህንዳዊ የ ቡዲሂዝም ተከታይ የ polytheism ተከታይ የሆነ የተለያዩ ምስል ያለባቸውን ምስሎችና ባል ስድስትም ባለ አራትም እግር እግር ጣዖቶችን ደርድሮ ሲፀልይ ይመለከታል።

ታዲያ ይሄ ሀበሻው ባየው ነገር ልቡ ይነካል። እንዴት ጣዖቶች ያመልካል? የ ጌታን ፍቅር ሰብኬው ከዚህ የጣዖት የዳቢሎስ ስራ ልታደገው ይገባል ብሎ እመር ብሎ ወደ ሰውየው ጠጋ ብሎ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትም መንገድም መሆን ስለሱ መሰቀሉን መፅሐፍ ቅዱስ እያጣቀሰ አይኑን ጨፍኖ (አልቅሶም ሊሆን ይችላል) ይሰብከዋል።

ህንዳዊውም ሰውዬ በጥሞና ከሰማው በኋላ "ይሄ ኢየሱስ ያልከው አምላክህ ክፉ ነው? ወይስ ደግ?" አለው ሽቅብ እያየው።

ሀበሻውም "የደጎች ደግ የመልካሞች መልካም ነው" አለ ስብከቱ ፍሬ እንዳገኘ ተሰምቶት እየፈነጠዘ።

ህንዱም " በጣም ጥሩ እንደነገርከኝ ከሆነ ድንቅ አምላክ ነው በውነቱ። እንደው የ አምላክህ ፎቶ ይኖርሀል" ሲል ይጠይቀዋል።

ሀበሻውም ፈጠን ብሎ" እንዴታ እንደውም የስቅለቱን ነው የምሰጥህ" ብሎ ትኩስ እንባውን እያዘራ ስቅለት ያለበትን ፎቶ ይሰጠዋል።

ህንዳዊው ባክብሮት ተቀብሎ በክብር ሳም ሳም ካደረገው በኋላ ከተደረደሩት ጣዖታት መካከል ፎቶውን እያስቀመጠው "በቃ ከዛሬ ጀምሮ 301 ኛው አምላኬ አድርጌ አመልከዋለሁ" ብሎ ወደ ፀሎቱ ተመለሰ።
***
moral of the story

ያመንከውንና የተቀበልከውን ነገር ሁሉ ሰዎች እንዲቀበሉት ማስገደድ ነውር ነው። አንተ የያዝከው እውነት በሌላ ጎን ላለ ሰው ከተረት ላይለይ ይችል ይሆናል።
በርግጥ ይሄ ሰውዬ ሲዖል ይገባል? ብባል በየት በኩል ልል እችላለሁ ቢያንስ ከ 301 አምላኮቹ አንዳቸው ያድኑታል።

@ourrthought
😁23👎1🤔1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሰብለ ወርቅ  መጽሐፍ የቆዩ መጸሐፍት

#ስልክ 0946523397 ይደውሉልን ፡


@sebleoldbook inbox 📑
1
ከራስ በላይ...

ዛሬ ከእንቅልፋችን በጊዜ ለምን ተነሳን? ካሉን ልብሶች ንፁህ የሆነውንና ያምርብናል ብለን ያሰብነውን ለምን መርጠን ለበስን? እግራችን እያጣየፈ ከቤት ይዞን ወጥቶ ወደ ትምህርት ቤት ወይንም መስሪያ ቤት ለምን ይወስደናል? እስከ አሁን አውቀን ተመራምረን የደረስንባቸው ነገሮች ለመኖራችን ዋስትናን ሰጥተውናል? ( ዓለም ላልተማረ ሰው ትልቅ ቦታ ብትሰጥ ግን ምን ያህላችን እንማር ነበር?)፤ ሰርተን ያካበትነው፣ ሰስተን የቆጠብነው ነገን ከስጋት ተላቀን መመልከት እንድንችል አድርጎናል?

ማህበረሰባዊነታችንስ? ምን ያህል የማይቀውን ብቸኝነት አስቀርቶልናል? የፈጠርናቸው ግንኙነቶች ራሳችንን ከመደበቂያነት ባለፈ እኛነታችንን ገልጦ በማሳየት ረገድ ምን ያህል ሚና አላቸው? በፍቅር ስም የመሰረትናቸው ግንኙነቶች ጥንካሬያቸው ምን ድረስ ነው? መፋታት ወይንም መለያየት አንዳችንን ለአንዳችን እንግዳ የሚያደርግን የሚደርገን ከሆነ ቀድሞውኑ የዝምድናው ህልውና ምን ያህል አስተማማኝ ነበረ?

አንዳችን ለአንዳችን መኖራችንን እየማልን ቃል እንገባለን። በህመም በጤናሽ፣ በሀዘን በሳቅህ፣ ላልከዳህ ላልከዳሽ እንላለን፤ ነገር ግን ጊዜው ደርሶ አብሮነት የሚፈተንበት ሰዓቱ ሲመጣ አብሮን የቆየውን " ከራስ በላይ ንፋስ " የሚለውን ብሂላችንን መዘን እንደ ጋሻ መዘዙን እንከልልበታለን።

በቁርጡ ቀን 'እኛነቱን' ያልጠበቀ አብሮነት እንዴት ያለ ይሁን???


#የዝናሽ-ልጅ

@ourrthought
18
ልፈወስ ተብሎ ከመም ከተሻረ
ይጠጣ የለም ወይ ኮሶ እየመረረ
አንዳንድ ጊዜ ዘራፍ ልበል እንጂ እንደወንድ
ወተት ብቻኮ ነው መገፋት የሚወድ

#ይሁኔ በላይ
#ምስጋናው_ደግ_ነው ከሚለው ሙዚቃ የተቀነጨበች

@ourrthought
👍9🔥2
Forwarded from ቀለም መጽሔት
ቀለም መጽሔት ቅጽ 1 እትም 6.pdf
5.7 MB
ቀለም መጽሔት🗞️

ቅፅ 1 እትም 6


እያነበባቹህ ለወዳጅዎ ያጋሩ
ለሀሳብ አስተያየት

@KelemMagazine

Telegram 👇❤️
@kelemofficial
👍41
ሳይታገሉ ያገኙት ነፃነት ከባርነት ይከፋል!

@ourrthought
👍95🔥3🤔2
ሰው አይመከርም!

ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለምዶም በሀዘኔታም ሰዎችን እንመክራለን። ግን ሰውን እንዲህ አድርግ እያሉ ሰዎችን መምከር በራሱ ሰዎቹ ላይ የሚያመጣው ጫና አለ። ማንኛውም ሰው ችግር ውስጥ ፈልጎ እንደማይገባው ሁሉ በሰው ምክርም ከዛ ችግር አይወጣም። ለጊዜው ሊወጣ ይችላል ግን ዘላቂ መፍትሄ የማግኘት እድሉ ጠባብ ነው። ባልተሰቀሉበት መስቀል መፍረድ ቀላል ነው እና ቀለል አድርገን ሰዎችን መምከር ለሰዎቹ ጫናውን ያብሰዋል።

ሁለት አይነት የ ምክክር ሂደት አለ Directive and Non directive ተብለው ይከፈላሉ።

Directive የሚባለው ሂደት ግለሰቡ ና አማካሪው ቁጭ ብለው ሰውየው እንዴት እዚህ ችግር ውስጥ እንደገባና እንዴት ከዚህ ውስጥ ሊወጣ እንደሚችል ከሰውየው ጋር የሚያቅዱበትና አማካሪው(counsellor) ግለሰቡ በቶሎ ችግሩን እንዲያገኘው የሚያግዝበት መንገድ ነው።

Non directive የሚባለው ደግሞ አማካሪው ምንም ጣልቃ ሳይገባበት ግለሰቡ እየመጣ ችግሩን ብቻ እያወራ የሚመለስበት ሲሆን ግለሰቡ ችግሩን በሚያወራበት ጊዜ እራሱ ለራሱ ንቁ እየሆነ የሚመጣበት ሂደት ነው።

ብዙ ሰዎች የስነ ልቦና የምክክር ሂደትን (counseling psychology) አንድ ችግር ያለበትን ሰው ቁጭ አድርጎ እየመከረ ማስተካከል ይመስላቸዋል። ግን የስነ-ልቦና አማካሪ (counselor) እንደዛ ያደርጋል? ወይ ካልን በፍፁም።

የ ምክክር ሂደት (counseling process) ችግር ያለበትን ሰው ቁጭ አድርጎ እየመከሩ የማስተካከል ሂደት ሳይሆን ግለሰቡ ያለበትን ችግር በራሱ እንዴት እንደሚያገኘውና እንደሚፈታው የሚያሳይ ሂደት ነው። እንጂ የመምከር አገልግሎት ሂደት አይደለም።

እና ምን ልላቹህ ነው ዝም ብሎ መስማት በራሱ ትልቅ እርዳታ ነው ግዴታ መምከር አይጠበቅባችሁም ለማለት ያክል ነው።

@ourrthought
👍125
ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት ወንድ አለ የሚያመነዝርና የማመንዘር እድሉን ያላገኘ!

በዕውቀቱ ስዩም


@ourrthought
🤣17🤔1