ላምጪው እንዲከፈል ሕግ ያስገድዳል (payable to the bearer on demand)
@ourrthought
ይህ ፅሑፍ ማንኛውም ብር ላይ ያለ ፅሑፍ ነው። ትርጉሙ በያዝከው የብር ኖት ገንዘቡን የሚመጥን አገልግሎት የማግኘት መብቱ አለህ ማለት ነው። ለምሳሌ የ 10 ብር ኖት ይዘህ የ 10 ብር አገልግሎት የማግኘት መፍቱ አለህ እንደማለት ነው። ላምጪው የሚለው ቃል የሚወክለው ገንዘቡን በ እጁ የያዘውን ግለሰብ ነው።
ይሄ ሕግ አለም ላይ የትም ቦታና ሀይማኖት ላይ ታገኘዋለህ። ካርማ ማለት ያ ነው። የዘራኸውን ታጭዳለህ ለ አለም የሰጠኸውን መልሰኽ ታገኘዋለህ። በ ሀይማኖትም ቢሆን በክርስትናው "ሰው የዘራውን ያንኑ መልሶ ያጭዳል" ይላል። ጥላቻን ከዘራህ ጎተራህ በጥላቻ ይሞላል። የሰጠኸው ይመለስልሀል። ለአለም ምንድነው ይዘህ የምትሄደው? ገንዘብ ላይ ያለው ሕግ ለ አለምም ይሰራልና አለምም የተለየ ዘይቤ የላትም "payable to the bearer on demand" የሚለውን ትተገብረዋለችና።
@ourrthought
👍17❤3
ጊዜው አርአያ ያጣ የሚመስል ዘመን ነው። ምሳሌ የሚሆን ሰው መጠቆም እስኪቸግረን ድረስ አርዐያ ያጣ ዘመን ላይ ያለን ይመስላል። እንደ ሀገር ተስማምተን የምንጠቁማቸው ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው።
የፍቅር የጀግንነት ምሳሌ የምናደርጋቸው ሰዎች ራሱ ጥያቄ ውስጥ ይከታሉ። ባንድ ወቅት ጎፋ ጋር ለ ብዙ አመታት ፍቅረኛውን በመጠበቅ ላይ የሚቆመውን ሰውዬ እንደ አርዐያ አድርገው ሲያነሱት ይገርመኝ ነበር። ዘፈን እስኪሰራለት ድረስ እንደ ትልቅ ምሳሌነት በየሚዲያው ላይ ሲዘግቡት ማየቴ በጊዜው አስገርሞኝ ነበር። እሱ ሰውዬ ከፍቅር ምሳሌነት ከማቅረብ ይልቅ ወደ አዕምሮ ህሙማን አስገብተውት ሊታከም የሚገባው ሰው ነበር መሆን የነበረበት። ሰውዬው ከ እውነታው አለም የተለየና በቁም ቅዠት ውስጥ የገባ በድሮ ሁኔታ የቀረ ሰው ነው። ፍቅረኛው በ አካል እንኳ መጥታ ሊለያት ያልቻለ ሰው ነው። እሱ ያለው አሁን ላይ አይደለም ድሮ ላይ እንደቆመ ነው። አዕምሮው በስርአቱ እያሰበለት ያልሆነን ከ እውነታው የተላቀቀን ሰውዬ ህክምና አግኝቶ እንዲድን ከማስቻል ይልቅ እኛ ግን ያደረግነው ለፍቅር የተከፈለ መስዋትነት ብለን አርዐያ ማድረጋችን ነው። ይሄ የሚያሳየው ምን ያክል ዘመኑ አርዐያ እንዳጣ ነው።
አንድ ሰው የ አዕምሮ ታማሚ ነው ለማለት የሚያስችሉ ነገሮችን የሚያሟላ ሰው ነው። የ አዕምሮ ህመምተኞች ታማሚ የሚያስብላቸው አንዱ ነገር ይህን አለም እውነታውን መረዳት ባለመቻላቸው ነው። በከሚታየው ይልቅ የራሳቸውን ትንሽዬ አለም አዕምሮዋቸው ውስጥ ገንብተው ከ ሚታየው አለም ተነጥለው በራሳቸው አለም መኖራቸው ነው። መንገድ ላይ የምታዩዋቸው የ አዕምሮ ታማሚዎች መንገድ ላይ እያወሩ የሚሄዱት ለዛ ነው። ምንም ባሌለበት ነገሮችን የራሳቸው አዕምሮው ያሳያቸዋል የድሮድምፅ እንዲሰሙ ያደርጋቸዋል። ይሄ በ ሳይንሳዊ ስሙ ስኬዞፎርኒያ የሚባል ችግር ነው። ፍቅሩን በመጠባበቅ ላይ ያለ እውነታውን መቀበል ያቃተው በራሱ አለም (fantasy) ውስጥ የገባ ሰው ነው። ክህደት ውስጥ ያለ (denial) ምስኪን የ አዕምሮ ህመምተኛ ነው።
ጨለምተኛ አይነት እሳቤ ያለኝ ሰው አይደለሁም። ግን ደግሞ በየ ማህበራዊ ሚዲያ ለ አርዐያነት የሚቀርቡ ሰዎችን ስመለከት ትንሽ ግር ስለሚለኝ ነው። አሁን ላይ በ ፌስቡክ ፣ ቲክቶክ የሚወደዱ ሰዎች ተሳዳቢዎችና የሰውን ክብር የሚነኩ ሰዎችን መሆኑ የቱ ጋር ነው የቆምነው የሚለውን የሚያሳይ ነው። በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ብዙ መልካም ሰዎች ፣ ብዙ ባለ አዕምሮ ሰዎች ፣ ብዙ ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎች በየቦታው ድምፅ ሳያሰሙ አሉ። እነሱን ያብዛልን።
@ourrthought
👍10❤1
ሐሳቦቻችን
Photo
ክፉ ሰዎች የሚሸወዱት ትልቁ ነገር ክፉ ለመሆን መልካምነት የተሻለ መንገድ መሆኑ አይገባቸውም። ግራ ያጋባል አይደል አባባሉ። አዎ ልክ ነው ስህተት የለውም አባባሉ። እናንተን ለመጉዳት የሚፈልግ ሰው ከክፋት ይልቅ የበዛ መልካምነት በጣም ቀላሉ ዘዴ ነው። ለምታደርጉት ነገር የበዛ ምስጋና ቢሰጧቹህና ትንሽ ትንሽ ነገር ቢቦጭቁላቹህ ምቾት እንዲሰማቹሁ ቢያደርጓቹህ አለቀላቹህ።
ከዛሬ 8 እና 9 አመት አከባቢ ርዕሱሡን የማላስታውሰው የ ኦሾ መፅሐፍ ላይ አንድ የሚገርመኝ አሀሳብ ነበር። በጊዜው ሳነበው ይሄማ የሌለ የማይመስል ነገር ነው ብዬ ነበር ያለፍኩት። ቃል በቃል ባላስታውሰውም ሀሳቡን ልንገራቹህ " ህይወትህ ላይ ክፉ ከሚሆኑብህ ሰዎች በላይ ሲበዛ መልካም የሚሆኑልህ ሰዎች ይጎዱሀል" አይነት ሀሳብ ነው።
ሀሳቡን ከላይ ስታየው ቀላል ቢመስልም ትልቅ እውነትነት ያለው ነው። ነፃነትህ ያለው ጥሩ የሚያደርግልህ ሰውዬ ጋር ነው ወይስ ክፉ የሚያደርግብህ ጋር ? ብትባል የት ነው የምትለው? መልካም ከሚያደርግልህ ሰው በላይ በውለታው አስሮ ያስቀመጠህ ከወዴት ይገኛል? ክፉ ናቸው የምትላቸው ሰዎች እንኳን እንዲህ በክፋታቸው ተብትበው አልያዙህም። ህይወታችን ላይ ይበልጥ አስረው የሚያስቀምጡን መጥፎ ከሚያደርጉብን በላይ አለቅጥ መልካም የሚሆኑልን ሰዎች ናቸው። በውለታቸው ተብትበው አስረውህ ሁል ጊዜ በነሱ ታስረህ እንደኖርክ ነው። ግንኙነቱን እንኳ ጥለህ እንዳትሄድ መልካምነታቸውን ያደረጉልህን ነገር እያሰብክ እየተጎዳህ መኖርን ትመርጣለህ። ክፉ አለቃ ካለህ ስራህን ለመልቀቅ እና አማራጭ ለመፈለግ አታመነታም። በጣም መልካምነቱ የበዛ አለቃ ቢኖርህ ግን ያደረገልህን ነገር እያሰብክ ውለታውን እየቆጠርክ እየተጎዳህ መስራትን ትሻለህ።
በረከት በላይነህ ጥሩ አከራይ ያለው ሰው መቼም ቢሆን ቤት አይሰራም ይላል። ምቾቱ ሌላ አማራጭ እንድትፈልግ አያደርግህም ሁሌም ተዘናንተህ እንደተቀመጥክ ነው። ጨቅጫቃ አከራይ ሲኖርህ ግን የራስህን ቤት እንዴት መስራት እንዳለብህ ያሳስብሀል። እስከ መቼ እንዲህ ኖራለሁ ትላለህ። አንስታይን ይመስለኛል "ህይወቴ ላይ እሺ ካሉኝ ሰዎች ይልቅ አይሆንም ያሉኝ ሰዎች ባለውለታዬ ናቸው። ነገሮችን በራሴ እንዳደርጋቸው አድርገውኛል" ይላል። የከፉብህን ሰዎች ብታስብ ህይወትህ ላይ ትልቁን ነገር ያደረጉልህ እነሱ መሆናቸውን ትረዳለህ። የኩረጃ ዘዴ እንደሌለ ያወክ ቀን ለማንበብ መነሳትህ አይቀርም።
ቁራ ልጆቿ ከ እንቁላል ከተፈለፈሉላት በኋላ ከመኝታቸው ከላባ ጉዝጓዝ ስር እሾህ ታስቀምጣለች። ይሄን የምታደርገው ልጆቿ በላባው ሙቀትና ልስላሴ ተመስጠው መብረር እንዳይረሱ ነው። ምቾት ካለ ለምን ይበራሉ? ቀስ ቀስ እያለች ላባውን ታነሳባቸውና በመጨረሻ እሾሁን ታስቀርባቸዋለች የዛኔ እሾሁ ሲወጋቸው እሱን ሽሽት ይበራሉ። ህይወትህ ላይ የበዛ መልካምነት ያላቸው ሰዎች ከላባው ልስላሴ እና ሙቀት ነው የሚሰጡህ። እሾሁን የሚሰጡህ ሰዎች ክፉዎቹ ናቸው እነሱም እንድትበር ያደረጉህ ናቸው። ዙሪያህን ተመልከት ይበልጥ አሳስሮ ያስቀመጠህ ማን ነው? ውለታቸው እንዳለብህ እያሰብክ የምትኖረው እነማንን ነው? ነገሮችን ያለህበትን ቦታ ትተህ እንዳትሄድ ያሰረህ ማን ነው? መልካም ሰዎቼ የምትላቸው አይደሉምን? አንዴ ሞክረህ ያቃተህን ነገር የሚሰሩልህ ሰዎች ጥሩ እንደሆኑልህ የምታስብ ከሆነ ይመችህ ይልቅስ በራስህ ሰርተህ እንዳትሞክረው ያደረጉህ ያለመቻልህ ተምሳሌት ሊሆኑም እንደሚችሉ ማሰብ ተገቢ ነው።
ዙሪያችን ላይ ለነበሩና ላሉ ክፉ ሰዎች ችርስ ምንም ነገር የማድረግ ነፃነታችን እና የ ችሎታዎቻችን ማሳያዎቻችን ናቹህና!

❤9
ሐሳቦቻችን
AI the new form of western colonial exploitation ሰሞኑን የዮናስ ጎርፌን podcast ስመለከት አንድ በጣም ድንቅ ትንተና በ AI ዙሪያ ተመለከትኩኝ ምዕራባውያኑ ከጥንት ጀምሮ የ አፍሪካን ሀብት ለመቀራመት ሲያቅዱ እንዲው በዘፈቀደ አይደለም በደንብ አጥንተውን ነው። እኛ የባሪያ ንግድ ላይ እንዳለን እነሱ በ ሀይማኖቱ በኩል ሊበዘብዙን ከች ብለው ነበር። ሀይማኖቱ ላይ ልንባንን…
በቀደም በዚህ ዙሪያ ከላይ ሀሳብ አጋርቻቹህ ነበር።
በሩዋንዳ በአፍሪካ የመጀመሪያው የኤአይ
ማበልፀጊያ ማዕከል ሊቋቋም ነው
17.5 ሚሊዮን ዶላር ባጀት ተመድቦለታ
ጥሩ ጅማሮ ነው የሚበረታታ
@ourrthought
በሩዋንዳ በአፍሪካ የመጀመሪያው የኤአይ
ማበልፀጊያ ማዕከል ሊቋቋም ነው
17.5 ሚሊዮን ዶላር ባጀት ተመድቦለታ
ጥሩ ጅማሮ ነው የሚበረታታ
@ourrthought
👍6
ስለ አለቃ ገ/ሐና ትንሽ እንጨዋወት። መቼስ አለቃ በሚናገሩትና : በመልስ ምታቸው ይታወቃሉ። ስለሳቸውም እስከዛሬ ብዙ የተፃፉ መፅሐፍትን ማግኘት አልቻልኩም ከ ሊቁ አለቃ ገብረሐና እና ከ ጋብሮቮች ጋር አብሮ ከታተመላቸው ውጪ። ዛሬ ከ ሊቁ አለቃ ገብረሐና ከሚለው ሁለት እንቀንጭብ።
፩
ባንድ ወቅት አለቃ ገ/ሐና ሚስታቸው ማዘንጊያሽ ወጥ እየሰራች በማማሰያ ጠለፍ እያደረገች በምላሷ አሁንም አሁንም ደጋግማ በመላስ እየቀመሰች አለቃ ደጋግመው ያስተውሏታል።
ይሄኔ አለቃ ተማረው " ማዘንጊያሽ እራታችን እሱ ከሆነ እኔም መቋሚያዬን ይዤ ልቅረብ" አሉ ይባላል።
፪
ባንድ ወቅት አለቃ ለልጆቻቸው ልብስ ለመግዛት በጎቻቸውን ለመሸጥ ወደ ገበያ ይዘው ይሄዳሉ። ታዲያ አንድ ሰው መጥቶ ስንት ነው ቢላቸው። 8 ብር ይሉታል። ሰውየውም ቀበል አድርጎ "በዚህማ ወደል አህያ አልገዛበትም እንዴ" ቢላቸው። እኔ እንግዲህ ዋጋውን ነገርኩህ እንጂ የሚጥምህን አንተ ታውቃለህ" አሉት ይባላል።
ሰውን እንዳመጣጡ መሸኘትን ተክነውበታል መቼስ አለቃ ባሉበት ይመቻቸው!

❤6😁5
ልመርቅላቹህ
፫
እቴጌ ጣይቱና እህታቸው ወይዘሮ አሰለፈች የ እንጦጦ የራጉኤልን ቤተክርስቲያን ደረጃ አሻቅበው ሲወጡ አለቃ ከደረጃው ስር ነበሩና አንጋጠው ወደላይ ሲመለከቱ አዩና "አለቃ ምን አሻቅበህ ትመለከታለህ" ብለው ቢጠይቋቸው። አለቃም "መውጫዬን እየተመለከትኩኝ ነው" ብለው መለሱላቸው😎
@ourrthought
፫
እቴጌ ጣይቱና እህታቸው ወይዘሮ አሰለፈች የ እንጦጦ የራጉኤልን ቤተክርስቲያን ደረጃ አሻቅበው ሲወጡ አለቃ ከደረጃው ስር ነበሩና አንጋጠው ወደላይ ሲመለከቱ አዩና "አለቃ ምን አሻቅበህ ትመለከታለህ" ብለው ቢጠይቋቸው። አለቃም "መውጫዬን እየተመለከትኩኝ ነው" ብለው መለሱላቸው😎
@ourrthought
🤣11❤1
ነፃነት ምን ይሆን?
ምናልባት አርዕስቱን ስታኑዩት ምንድነው ይሄን ጥያቄ የሚጠይቀው ትሉ ይሆናል። በርግጥም የ አማርኛ መዝገበ ቃላት ላይ ነፃነት የሚለውን ፍቺ ብትመለከቱ አርነት ፣ መብት የሚሉትን ፍቺዎች ይዘረዝርላቹሀል። ነፃነት ምንድነው የሚለውንም ብታዩ አንድ ሰው የራሱን ፍላጎትና ሀሳብ ያለማንም የውጭና የውስጥ ጣልቃ ገብነት የፈለገውን ነገር የማድረግና ስልጣን ነው።
በነፃነት ስም ብዙ ነገር ተፈፅሟል። Edward Bernays በ 1929 እ.ኤ.አ በ አሜሪካ የነበረውን ሴት ልጅ በ አደባባይም ሆነ በጓዳ ሲጋራ አታጨስም የሚለውን ማህበረሰባዊ ክልከላ የሰበረበት ዘመቻ "Torches of Freedom" የሚል ነበር። የነፃነት ችቦ በነፃነት ስም ዴሞክራሲ የምትለዋን ሽፋን በማምጣት በ አሜሪካ የነበሩትን ከ 5 % በታች አጫሽ ልጃገረዶች ቁጥር ወደ 35 እንዳደረሰው ይገመታል። በዚህ አርዕስት ላይ YouTube ላይ አንድ ዶክመንተሪ አለ century of the self የሚል እዛ ላይ "Happiness machine part 1" ተመልከቱት።
ሌሎችንም ብንዘረዝር በነፃነት ስም ብዙ ነገሮች ተፈፅመዋል። ይሄ ልቅ ያጣ ነፃነት ተለጥጦ ተለጥጦ በ ዴሞክራሲ በ እኩልነት ስም በፆታ ግራ እስኪጋቡበት ድረስ ተለጥጧል። አሁን ላይ በ አውሮፓ ሀገሮች ላይ ግለሰብን ለ ራሱ ለግለሰቡ በመተው ከቤተሰብ ፣ ከ ሀይማኖት ፣ ከ ማህበረሰቡ የተነጠለ ግራ የገባው ሰው የተፈጠረለት ፆታ ሳይቀር ግራ ሲያጋባው ማየት መስተዋሉ የተለመደ ነው።
በርግጥ ሰው ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆን ይገባው ይሆን? Sigmund Freud የሰው ልጅ ደስታን የሚያሳድድና ስቃይን ከራሱ ላይ ለመቀነስ የራሱን ደስታ በማንኛውም መንገድ ማሳካት የሚፈልግ ባዮሎጂካዊ "Libido" የሚባል ነገር አለ ይለናል። ይሄ Libido ብዙ ጊዜ ከ ወሲባዊ ስሜት ጋር ብዙዎች የሚያይዙት ነው። ግን ደግሞ ይሄ ሊቢዶ በሰፊው የሚብራራ ነገር ነው። Libido የራሱን ደስታ የሚያሳድድ ኢ-ፍትሀዊ የሆነ ግፊት ነው። በሌላ መልኩ "Animal force" እንስሳዊ ደመነብስ የሚባለው ነው። በስሜት የሚነዳና የማያገናዝብ ስሜት እንደማለት ነው።
የሰው ልጅ ነፃ መሆንስ ይችል ይሆን? የሚለውን ብናይ ከሀይማኖት ፣ ከ ማህበረሰብ ፣ ከሲስተም እንኳ ነፃና ገለልተኛ ቢሆን ከራሱ ተራ ምኞት ግን ነፃ ሊወጣ አይችልም። የራሱን ባህሪ መግራት የማይችል ሰው እንዴት ነፃ ሊባል ይችላል? በራሱ ደመነብሳዊ ግፊት የሚመራ ሰው "libido" ያየለበት ሰው ነፃ ነው ማለት እንችል ይሆን? Hedonist የሚባሉ ሰዎች አሉ ግባቸው ደስታና ደስታ ነው ለነሱ እስከጠቀመ ድረስ ምንም ነገር ያደርጋሉ። እነዚህ ሰዎች የደስታቸው እስረኞች ናቸው። Sadistic የሚባሉም ሰዎች አሉ በሰው ሀዘንና ስቃይ የሚደሰቱ ናቸው። እነዚህም የራሳቸው እስረኞች ናቸው። ሁላችንም የራሳችን ከንቱ ምኞቶች ባርያ ነን።
የሀይማኖት ፣ የማህበረሰብ ክልከላዎች ነፃነታችንን ከመፈግ ይልቅ ከራሳችን ተራ ምኞቶች የሚታደጉን እንጂ እስር ቤት አይደሉም። ይሄን ስል ሁሉንም የሀይማኖትና የማህበረሰብ ክልከላዎች ማለቴ አይደለም። ሰው ነፃ መሆን ይችላል ብንል ዞሮ ዞሮ የሆነ የተተበተበበት ትብታብ አለ። አስተዳደጉ ፣ ቤተሰቡ ፣ ልማዱ ፣ ፖለቲካው ፣ ፍላጎቱ እነኚህ ነገር ይከተሉታል።
ሀሳቤን በ ሁለት ምሳሌ ላጠቃልል
፩
በ Shawshank redemption ፊልም ላይ አንድ እረጅም ጊዜ የታሰረ ሰው አለ። ከ እስር ቤት መውጣት ይፈራል። ህይወቱን በ እስር ቤት አድርጓል የኔ የሚለው ነገሩን ሁላ ከዛ እስር ቤት ነው ያለው። ውጪ ላይ ጓደኞች የሉትም እስር ቤት ግን አሉት ታዲያ ይሄ ሰውዬ ነፃ መሆን ሲችል እሱ ግን እያሳበበ እስር ቤት መቆየቱን ይፈልግ ነበር። ይሄን ስናይ ሰው የለመደው ነገር ውስጥ ነው ነፃነቱ ያለው የሚለውን ያሳየናል። ምናልባት ከዚህ አለም ውጪ ያሉ ፍጡራን እኛን እንደ እስረኛ ይሆናል የሚቆጥሩን ሰማዩ የተደፋብን ከራሷ ባህር ወታ እንደማታውቅ እንቁራሪት አይነት ነገር እኛ ግን ምድር እስር መሆኗን አናውቀውም የለመድነው ነውና ከዛም ወተን አናውቅም።
፪
በሀገራችን በድሮ ዘመን በባሪያ ንግድ ጊዜ ወዶ ገባ ባሮች ነበሩ። እኚህ ባሮች ነፃነት ሲሰጣቸው አንፈልግም ባርነት ይሻለናል ብለው በፈቃዳቸው ባርነትን የመረጡ ናቸው። ከተወሰኑ የባርነት ጊዜያት በኋላ ነፃነት ቢሰጣቸውም እነሱ ግን ባርነት ዘመዴ ያሉ ናቸው። የዛኔ አሳዳሪዎቻቸው በብረት አግለው ይጠብሷቸዋል ለዘላለም ባሪያቸው መሆኑን የሚገልፁበት መንገድ ነው። ባኖቹ ያን የሚያደርጉት ያማረ ምግብና መጠጥ በነፃ ስለሚያገኙ ነው። ከዛ ቢወጡ ሌላኛውን የነፃነቱን መንገድ አያውቁትምና ይፈሩታል በዛ ላይ ያማረና የላመ ይመገባሉ ያሳዳሪዎቻቸውን ያረጁ ልብሶች ይለብሳሉ። እንግዲያው በዚህ ዘዴ ሰው የሚያውቀው ነገር ውስጥ ነው ነፃነቱ ያለው እንድንል ያስችለናል።
ነፃነት ተለጥጦ ተለጥጦ ግለሰባዊ ነፃነት ላይ ደርሷል። ዘመነኛው ሰው ከሁሉ ንጡልና ጣዕም አልባ ሆኗል። ሰው ከነፃነት ይልቅ በነገሮች መታጠርና በሱ መኖሩ ከልቅ ነፃነት ይበልጥ ስሜት ይሰጠው ይሆን? ወይስ ሙሉ ለሙሉ ነፃ ሆኖ በራሱ መኖሩ ገደብ አልባ መሆኑ ይበልጥ ይጥመው ይሆን?
@ourrthought👏9❤2👍1
ሐሳቦቻችን
Photo
ህላዌነት!
@ourrthought
ጠዋት ጠዋት ከህይወት ጋር የህላዌ ፍጥጫ ገጥማለሁ። መኖር በራሱ ምንድነው? የሚል መልስ የሌለው ጥያቄ አመነዥካለሁ። ይሄን ጥያቄ ላለፉት 5 አመታት ጀምሮ አጥብቄ ብጠይቅመ እስካሁን ረብ ያለው መልስ አግኝቼ አላውቅም። ሰው ምድር ላይ ምን ይሰራል? ለምን እንኖራለን? ከመፈጠራችን በፊት የት ነበርን? በርግጥስ ወዴት ነው ስንሞት የምንሄደው? የሚል ጥያቄ። በርግጥ ይሄን ጥያቄ ብጠይቅም የህይወትን ከንቱነት ከማባስ ይልቅ የጠቀመኝ ነገር የለም።
ጎዳና ላይ ከአንድ ጎዳና ተዳዳሪ የተወለደ ልጅ ከጎዳና ውጪ ተስፋው ምንድነው? ከሚያውቀው አለም ውጪስ እንዴት ሊያስብ ይችላል? አሁን ከወለዱን ቤተሰቦቻችን ለመወለድ ምን ጥረናል? ሀብታም ቤት ውስጥ ለመወለድ ማን ጥረት አደረገ? ሰው ሲወለድ አካሉ እንዳይጎድል ምን ጥረት ያደረገው ነገር አለ? ህይወት በዚህ ልክ ላንዱ መልካም ለሌላውስ ለምን የመረረስ ትሆናለች? መልስ ባላገኝም ሁሌ የማመነዥከው ጥያቄዬ ነው። እኔ ራሴ ምንድነው እዚህ እየሰራሁ ያለሁት (ምድር ላይ) የሚል የከንቱነት ጥያቄ እለት እለት እያላተመ ያላምጠኛል።
በርግጥ ሀይማኖቶች እንደነገሩን የሰው ልጅ ለምስጋና ብቻ ነው እዚህ ምድር ያለው? ፈጣሪ ባታመሰግነው የማይጎልበት ፣ ብታመሰግነውም የማይሞላለት ሆኖ ሳለ ስለምን የሰው ጫካ ምድር ላይ ይዘራል?ምን ሊበጀው? ሌላ አላማ አለው እንዳልል ሰው እንደቀላል ነገር የከበረች እስትንፋሱ በመኪና ለሚቋጭባት አለም ፣ በተራ ፀብ ለሚሞትባት አለም ፣ አንዳንዱ ተሰቃይቶ ሳይኖር ለሚሞትባት አለም ፣ ተወለዱ ሞቱ ከሚል ውጪ ታሪክ ያልፃፈ ሰው ሳይ ደሞ በርግጥስ የተፈጠረበት አላማው ምንድነው? ያስብለኛል።
ይህ ወለፈንዲነት እን ካሙ እንደሚሉት Nihilism አይነት እሳቤ ነው። የራስህን ምክንያት እስካልፈጠርክ ህይወት በራሷ ተራ ነገርና ምክንያት አልባ ናት ይላሉ። ይሄም ቢሆን አይዋጥልኝም። ሰውን ያህል የከበረ ፍጡር ያለምንም ምክንያት ይሄን ብሩህ አዕምሮ ይዞ እንዴት ይፈጠራል? በዝግመተ ለውጡ ብቻ እዚህ ደረሰ? እራሱን ለማኖር በሚያደርገው የኑሮ ትግል ብቻ የሰላ ሆነ? ይሄም አይዋጥልኝም። የራሴንም አለም ብገነባ ከከንቱነቱ ሊያስጥለኝ አልቻለም ፣ ሀይማኖቱም ምላሹ ሊያረካኝ አልቻለም።
ደስተኛ ሰዎች ያስቀኑኛል። የህላዌ ጥያቄ የሌለባቸው ሰዎች ዝም ብለው የሚኖሩቱ። ከንቱነት የለባቸው ፣ እርባናቢስነት የለባቸው። በገንዘባቸውም አለማቸውን የገነቡ ሰዎች ታድለዋል የህላዌ ጥያቄያቸውን በዛ ውስጥ መልሰውታል። በነዚህ ሰዎች እቀናለሁ በቁሳቁስ ህይወታቸውን በደስታ ለሚኖሩት ሰዎች ሳይ ድንቅ ይለኛል ሌላ ነገር የጎደለባቸው መኖሩን ዘንግተዋል ያላቸው በቅቷቸዋልና።
ምናልባት የሰው ስሪቱ ምድር ላይ መፈጠሩ ፣ ግቡ እራሱን ፈልጎ ማግኘቱ ብቻ ቢሆንስ? ማንነቱን የማወቅ ሂደት ብቻስ እራሱን የመፈለግ ቢሆንስ? መላዕክትን ፈጥሮ እንዳበቃ እንዲመራመሩ እንደተሰወረባቸው ሁሉ እኛም ያ ዕጣ ቢሆንስ የምድር ዕጣ ፈንታችን?@ourrthought
❤6👍3
ሰው ሰውነትን ለመገንባት የሄደበት መንገድ የተሳሳተ እንደሆነ አስባለሁ። ምድር የእብዶች ጉባኤ ሆናለች። ዓለምን የ አመጻ ቤተሙከራ አድርገዋታል። ቀደም ባለው ጊዜ በቅዱሳቱና ተረታቱ መጻሐፍት እንደተነገረን በዚህ በ አመጻ ግብሩ አማልክት ሳይቀሩ ተሳታፊ ነበሩ። በጥንቱ ዘመን ሰዎች ጠንካራ ህብረትና መተባበር እንዲመሰርቱ ብሎም ትንንሽ ግዛቶችና ሀገራት እንዲፈጠሩ ጦርነቶች ሚና እንደነበራቸው ይነገራል። ምናልባት ዘመኑ < Age of formation> ስለነበር ይሄን ፈቅዶ ይሆናል። አሁን ግን ዘመኑ የመበስበስ ፣ የመፈራረስ < Age of decadence> በመሆኑ በጦርነት የምትፈራርስ እንጂ የምትገነባ ሀገር አትኖርም።
በፍም እሳት ማቃመስ
ያዕቆብ ብርሀኑ
@ourrthought
👏7
ሚስት : ሴቶች ሁል ጊዜ ቤት ውስጥ ምግብ እየሰሩ ባላቸውን መመገብ ግዴታ ያለባቸው ይመስሀል እንዴ😡
ባል : አዎ ግዴታችሁ ነው!
ሚስት: እንዴት ሲባል😡
ባል: በህጉ መሠረት እስረኛ በቀን ሦስት ጊዜ መመገብ አለበት ይላል።🙄
ሚስት : እስረኛ ነኝ ብለህ ነው የምታስበው 🤬
ባል : ካልሆንኩኝ ሌላ ሴት ጋር እንድሄድ ፍቀጂልኛ☺️
ሚስት : ቁጭ በል : ንቅንቅ እንዳትል! ጥይቷን ደቅናበት
ከዛን በሰላም ተስማሙ! በንግግር የማይፈታ ነገር የለም።

😁23🔥2
ሀበሻ ልቦና ውስጥ እግዜር አፈግፍጓል
ዓለማየሁ ገላጋይ የተጠላው እንዳልተጠላው በሚለው መፅሐፉ መግቢያ ላይ "ሰዎች ሲበረቱ እግዚአብሔር ያፈገፍጋል።
ከህሊናቸው ፣ ከመንፈሳቸው ፣ ከነብሳቸው ይወጣል።" ብሎ ይጀምርና በዚሁ ምዕራፉ ዝቅ ብሎ ደሞ " ኢትዮጵያውያን መች ይበረታሉ?
እግዚአብሔራቸው የሚያፈገፍግበት ቀኑ መቼ ነው?
ከህሊናቸው ፣ ከመንፈሳቸው ፣ ከነብሳቸው የሚወጣው?
ፍዳቸውን ስራቸውን ፤ ሀብታቸውን እንደምን ይተውላቸዋል?" ይላል። እኔም እላለሁ የ እግዚአብሔር መልኩ በኢትዮጵያውያን ላይ የት አለና? በመንፈሳችን ፣ በህሊናችን ፣ በነብሳችን እግዚአብሔርን ካሸሸን አያሌ ብዙ ጊዜያት ተቆጠሩ።
በቅርቡ የአለም መንግስታት በአለም ላይ ያለውን የ ሀይማኖት ስብጥር ባስቀመጠበት ቻርተሩ ላይ ሀገራችን በ አማኞች ብዛት ከ አለም በቁጥር 1 የ አማኝ ብዛት ያለባት ሀገር እንደሆነች ይገልፃል። አስቡት ሀገራችን በቁጥሩ ብትመራም የሀይማኖቶቹን ስነ ምግባር በመጣስ ሰብዐዊነትን በመደፍጠጥ የሚደርሰን የለም። ሀይማኖተኛ ነን በምንልበት ሀገር ላይ በ ሀይማኖት የምንገዳደል ፣ ሰው ዘቅዝቀን የምንገድል ፣ በ ቪዲዮ እየቀረፅን የምናርድ ፣ ህፃናትን የምንጨፈጭፍ ከኛስ ውጪ በጭካኔው የሚበልጠን ይኖር ይሆን?
እግዚአብሔር ሲባል ውጪ ያለ አካል የምናስስ ከሆነ ያስቀኛል። እግዚአብሔር የልባችን ቅንነትና መልካምነት አይደለምን? እኛ ግን ከልባችን ይልቅ ግዙፍ ቤተመቅደሶችን በብዙ ብር እንገነባለን። "ሰማይም ለዙፋኔ : ምድርም ለመረገጫዬ አትበቃኝም" ላለው ፈጣሪ በቤተመቅደሶቻችን ልናጥረው ቤተ እምነቶች ይታነፃሉ። ልባችን ግን ከዛ ርቋል : በምንለው ልክ ቅንነትና አምልኮ ውስጣችን የለም : ለይምሰል ልምድ ሆኖብን በየ ቤተክርስቲያኑና መስጂዱ እንመላለሳለን እንጂ።
ለ አውሮፓውያን የ እግዜርን መሞት ኒቼ በ Thus spake Zarathustra መፅሐፉ እንዳረዳቸው። ለእኛም የሚያረዳንን በመጠባበቅ አመታት አልፎናል። ዛሬም ድረስ ስለሌለን መልካምነትና ቅንነት ከበሮ እንደልቃለን። እኛኮ ዘመንን የቀደምን ህዝቦች ነን እያልን ስናወራ እንኳ እፍረቱ የለንም። ዛሬም ድረስ ላሊበላ ስለሰራው ቤተመቅደስ እኛኮ ብለን እንታበያለን ግን እንዴት እንኳ እንደተሰራ ማብራራቱ ከብዶናል። የ ሐረር መስጂዶችን ዛሬ የሚያንፃቸው ቀርቶ የሚያብራራቸውም የለም ግን ዘወትር ባለፈው ተተብትበን ማንትቤዎቻችን ስለሰሩት ነገር እኛ እንደሰራን ይወራል። ኢትዮጵያውያን ፈርሀ እግዚያር ናቸው ይባላል። እኛ ግን ፈጣሪን በልባችን ከቀበርነው አመታት አልፈዋል። በስሙ ዛሬም ድረስ ይነገድበት ይሆናል እንጂ የፈጣሪን መልክ በህዝባችን ላይ ካጣነው የትየለሌ ዘመን ሆኗል። ፈጣሪ ከሀበሻ ልብ ውስጥ አፈግፍጓል።
Sigmund Freud "Identification" ego defense mechanism የሚባል እሳቤ አለው። እራሱን ከፀፀትና ከተጠያቂነት እራሱን ego ውን የሚሸፍንበት ከዛ ዘዴዎች ውስጥ እኛ እንደ ሀገር collective conscious የምንጠቀመው Identification የሚባል ዘዴ ነው። ይሄ ego defense mechanism እኛ ያላሳካነውን ግን ሌሎች ሰዎች ያሳኩትን ነገር እራሳችንን አካተን ማሰብና መፅናናት ነው። አሁን ኢትዮጵያ ምን አይነት ሀገር ናት ብትሉ አንድ ሰው አቁማቹሁ ጥንት ስልጣኔ ያነፅን ላሊበላን የገነባን ጣሊያንን ያባረርን ብሎ ነው የሚያብራራው እራሱን ያልነበረበት ቦታ ከቶ ነው ሚያብራራው። ይሄ ዘዴ ደሞ Identification ego defense ይባላል። በሀይማኖቱም ተመሳሳይ ነው። የድሮውን ፅድቃችንን እንጂ አሁን ላይ የምናወራው ፅድቅ የለንም።
ሀበሻ የፈጣሪን ስም የሚጠራው ለስንፍናው እና ለንዋይ ከሆነ ሰነባበተ። ቅዱስ መፅሐፉም የሚለውም "ኢትዮጵያዊ ቀለሙን ነብር ዥንጉርጉርነቱን አይተውም" የሚለው። ይሄ ይሄ ስንፍናችንን ይሆን?
@ourrthought
🙏6💔4❤3👏2
የ/አ/ጨ/ላ/ማ
የተባበሩት የአለም ጨጓራ ላጭ እና አቃጣይ ማህበር ድርጅት ሀገራችን ነው ለካ ያለው። ከላይ እስከ ታች ያለክፍያ በትጋት የምንሰራው ብቸኛው ስራ ነው።
ከመ አርዮስ ውጉዝ
@ourrthought
የተባበሩት የአለም ጨጓራ ላጭ እና አቃጣይ ማህበር ድርጅት ሀገራችን ነው ለካ ያለው። ከላይ እስከ ታች ያለክፍያ በትጋት የምንሰራው ብቸኛው ስራ ነው።
ከመ አርዮስ ውጉዝ
@ourrthought
😢4🤣1
ፈረንጅ ትራንስፖርት ለትንሽ ሲያመልጠው : አርፍጃለሁ ማለት ነው ለሌላ ጊዜ በጊዜ ነው የምነሳው ቀደም ብዬ። ላሁን ቀጣይዋን ልያዝና ልድረስ።
ሀበሻ ትራንስፖርት ሲያመልጠው : ፈጣሪዬ ከ አደጋ ሊያተርፈኝ ነው ያስመለጠኝ። ቆይ እንደውም የ አደጋ ዜና ልከታተል ብሎ ያመለጠውን መኪና ተገለበጠ የሚል ዜና ይጠባበቃል።
ዘይገርም ነው ጃል😤
@ourrthought
ሀበሻ ትራንስፖርት ሲያመልጠው : ፈጣሪዬ ከ አደጋ ሊያተርፈኝ ነው ያስመለጠኝ። ቆይ እንደውም የ አደጋ ዜና ልከታተል ብሎ ያመለጠውን መኪና ተገለበጠ የሚል ዜና ይጠባበቃል።
ዘይገርም ነው ጃል😤
@ourrthought
😁26❤1
ቴ/ተክለ አረጋይ ፍልስምና በሚለው መፅሐፉ ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝን ቃለመጠይቅ ባደረገበት ላይ ስለ ህይወት የተናገረው ነገር ይገዛኛል። ሐሳቧ እንዲህ ናት " ህይወት ማለት ወይ ማዘን ወይ መደሰት በሚሉት የመንቶ እሳቤ የሚመራ አይደለም። ብዙ ሰው ደስተኛ ካልሆነ ያዘነ ይመስለዋል ፣ ካዘነ ደሞ ደስተኛ ያልሆነ ይመስለዋል። እና ህይወቱ በነዚህ ሁለት ፅንፎች የሚመራ ይመስለዋል። ግን ህይወት ላይ ስንኖር መደበኛ ኑሮ ነው የምንኖረው። ደስታም ሆነ መከራ በየፈረቃ እየተቀያየረ የሚመጣ ነገር እንጂ አብዛኛው ኑሮዋችን ዝም ብለን ነው የምንኖረው። ደስታም የሆነ ጊዜ ላይ ይመጣል : ሀዘንም እንደዛው። ሁለቱም በሆነ ወቅት እየሄዱ የሚመጡ ጉዳዮች ናቸው።" የምትል ሀሳብ ናት።
እና አስተውለን ካየነው ሀሳቡ ገዢ ሀሳብ ነው። አብዛኛው ኑሮዋችን ሀዘንም ደስታም ውጡ የለሌለበት ዝም ያለ ነው። ለሁሉም ነገር ቢሆን መደበኛ ስሜት ነው የሚኖረን መከፋትም መደሰትም የሌለበት ህይወት ነው። ይሄን ካለማስተዋል አንዳንዴ ህይወታችን ሙሉ በስቃይ ያለፍን ይመስለናል። ወይ ደሞ በደስታ ብቻ የተሞላ። ይሄን ዝም ያለውን ኑሮ ልብ ብለነው አናውቅም። ህይወታችን ላይ መቼ ነው የምንደሰተው? ብለን ወደ ኋላ ስንመለከት የሚታወሰን የተሰቃየንባቸው የመከራ ጊዜያቶቻችን ናቸው።
ግን ይሄን ዝም ያለውን መከፋትም መደሰትም የሌለበትን ህይወት ማስታወስ የቻለ ህይወት ደስታ ወይ ደሞ መከራ ብቻ እንዳልሆነ ይረዳል። ይልቅስ ደስታም ሆነ መከራ እየተፈራረቁ የሚመጡ የህይወት ዑደቶች እንደሆኑ ልብ ይሏል።

👍6❤4
ሐሳቦቻችን
Photo
Existential crisis + Nihilistic = suicide
በየ ዘመናቱ ብንመለከት ዘመኑን የሚመራ መንፈስ (sprit of the time) አለው። ይህ ጊዜውን የሚመራ መንፈስ ማለት ጊዜው ላይ ያለው የህዝቡ ስነ ልቦና ባብዛኛው የሚያጋድልበት ጉዳይ ማለት ነው። ከጥንት ጀምሮ ብንመለከት በየ ዘመናቱ የሰውን ልጅ በጋራ የሚመሩት የጋራ ደመነብሱን (collective unconscious) የሚዘውሩት እንደነበሩ ታስተውላላቹህ። የ ኢንዱስትሪ አብዮት ፣ የ ሶሻሊስም ፣ ካፒታሊዝም ፣ የጥቁሮች ነፃነት ንቅናቄ ፣ የሴት ልጅ ነፃነት ንቅናቄ..... አሁን ላይ የጊዜው መንፈስ ያለው የሰው የጋራ ደመነብስ የሚዘወርለት የጊዜውን መንፈስ ብትመለከቱ ባብዛኛው የህይወት ትርጉም ማጣት ላይ ያተኩራል።
ዘመኑ በዚህ ደረጃ የህይወት ትርጉም ማጣት ጋር ተፋጠጠ? የሚለውን ጥያቄ እንዴት ከሌላው ዘመን በተለየ መልኩ በዚህ ድህረ ካፒታሊስት አለም ላይ በረታ? የሚለውን በትንሹ ተንትነን እንመልከተው።
ወደ ጥንት የሰው ልጅ ዘር መለስ ብለን የተመለከትን እንደሆነ ሰዎች በጋራ ህይወታቸውን እያቆዩ ለመኖር ከተፈጥሮና ከ አራዊቱ ጋር ሲታገሉ የሚኖሩበትን መንገድ እናስተውላለን። ይህ ትግላቸው እንግዲህ የማያቋርጥ በመሆኑ ህይወታቸው በሙሉ በውጥረት የተሞላና ለምንድነው የተፈጠርኩት ከሚለው ጥያቄ በላይ እንዴት ነው ነብሴን የማቆየው ብለው የሚታገሉበት ዘመን ነበር።
ከጥንቱ የሰው ልጅ መለስ ብለን ቀረብ ለሚሉት ዘመን ላይ ስንመለከት አሁንም ቢሆን ሰዎች ትልቁ የህይወታቸው ትግል ህይወታቸውን የማሰቀጠል (survival mode) ላይ ሆነው በዚህ ሁኔታ ውስጥ ግን የህይወትን ምንነት በሀይማኖቶች ውስጥ ትርጉም እየሰጡ በዛም ጥያቄ እረክተው እናገኛቸዋለን።
ከላይ ባየናቸው ሁለቱ ምሳሌዎች ሰዎች ከህይወት ትርጉም በላይ ህይወታቸውን የሚያቆዩበት ነገር ይበልጥ እንደሚያስጨንቃቸው እናያለን። ታዲያ የዛኔ እምብዛም የሌለው የህይወት ትርጉም ማጣት አሁን ለምን ትልቁ ፈተና ሆነ? ብለን እንተንትነው። የሰው ልጅ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በማህበረሰብ እሴትና ደንብ ፣ በሀይማኖት ፣ በስነ ምግባር ፣ በህግጋቶች በመሳሰሉት ነገሮች ታጥሮ የህይወቱን ትርጉም በነዚህ ውስጥ እየመለሰ የሚኖር ሆኖ የቆየ ነበር። አሁን ላይ ግን በነፃነት ስም እንዲሁም የግለሰባዊነት መስፋፋት የሰው ልጅ ከ ሀይማኖት ፣ ከቤተሰብ ፣ ከማህበረሰቡ ፣ ከ ሞራል ፣ ከህግጋት ገደቦች ተነጥሎ ተነጥሎ ብቻውን በመቅረቱ የህይወት ትርጉምን ምላሽ የሚሰጥበት መንገድን አጥቷል። በራሱ መንገድም የሚሰጠው ትርጉም የሚያረካው አልሆነም። መነሻው እራሱ ነውና ከባዶ ነገር ላይ ተነስቶ የሚሰጠው ትርጉም በየጊዜው እየተቀያየረ በነገሮች ግራ የተጋባ ሆኗል።
ይህ ጥያቄ (የህይወት ትርጉም) ከ አፍሪካ ይልቅ በምዕራቡ አለም ላይ ይበልጥ የሚሰተዋል ጉዳይ ነው። የምዕራቡ አለም ያለበት የጊዜ መንፈስ (sprite of the time) ግለሰባዊ ነፃነት (individual liberty) ሰዎች ለጥያቄው መልስ ለመስጠት የሚነሱበት መነሻ ቦታን አሳጥቷቸዋል። ሌላው የሚታገሉለት ነገር በመቀነሱ ለዚህ ቀውስ ዳርጓቸዋል። ወደ አፍሪካ ስንመጣ አፍሪካ ላይ ዛሬም ድረስ የ ሀይማኖቶች ፣ ማህበራዊ መስተጋብሩ ፣ ባህል ፣ እሴት አለመፈረሳቸው ይሄን ጥያቄ ለመመለስ ሲረዳቸው ማስተዋል ይቻላል። አፍሪካ ውስጥ አሁንም ድረስ ለኑሮ የመታገሉ (survival mode) ላይ መሆናችን የህይወታችንን ትርጉም ለምንድነው የምኖረው? ከሚለው ጥያቄ በላይ እንዴት ነው የምኖረው? የሚለውን ለመመለስ በሚደረገው ትግል ውስጥ የህይወት ጥያቄያቸውን የሚኖሩበትን ምክንያት በ ህይወት መቆየት ጋር በማያያዛችን እራስን ከማጥፋት ከ አውሮፓውያን ይልቅ በኛ የማይስተዋለው ለዛ ነው።
እንደ መጠቅለያ አንድ ማህበረሰብ ለህይወት ለመቆየት በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ ለህይወቱ የሚታገለው ነገሮች እየተቀነሱና አልጋ ባልጋ እየሆኑ በመጡ ቀጥር ይህ ጥያቄ በ እጅጉ ይበረታል። ሁሉን በማግኘት ውስጥ ሁሉን እንደማጣት ያለ የተራነት ስሜት ማለት ነው።
ከ አንድ ወዳጄ ጋር በሀሳብ ዙሪያ ስንጨዋወት የ አፍሪካን ኑሮ እንዲህ መሆኑን እያማረረና የ አውሮፓ ኑሮ አልጋ ባልጋ መሆኑን እያወደሰ አብራራልኝ። በርግጥ ሀሳቡ ልክ ቢሆንም የኔ ምላሽ የነበረው ቢያንስ እኛ ይሄን ኑሮ ለማሸነፍ በምናደርገው ትግል ውስጥ የህይወት ትርጉማችንን መስራት ችለናል። ለብዙ ሰው ይሄን ህይወት ማሸነፍ የህይወት ዘመን ግቡ ነው። ይሄ ደሞ መልካም ጎን አለው ህይወቱን ከከንቱነት ታድጎለታልና። አፍሪካ ውስጥ ያለ ህይወት በራሱ የህይወት ግብ መሆን ይችላል። ህይወትን ማቆየት (survival mode) ከህይወት ከንቱነት(Nihilistic thought) የተሻለ ነው።
ይህ ዘመን ከመሞት በላይ ለመኖር ከባድ ፈተና ያለበት ጊዜ ነው። ህይወትን ማቆየት በራሱ የህይወት ትርጉም ነው።
@ourrthought#ሐሳቦቻችን
#ourrthought
❤9👏4🔥1