ሐሳቦቻችን
981 subscribers
103 photos
4 videos
5 files
2 links
በዚ ቻናል ላይ የተለያዩ ሀሳቦቻችንን ፣ ምልከታዎቻችንን ፣ ትዝብታችንን ፣ ከተለያዩ መልኮች እያነሳን እንወያያለን!

ሀሳብና አስተያየት ካላቹ @haileabb
Download Telegram
ሐሳቦቻችን
‎Modern Education As a Pavlov Dog ‎ ዛሬ የመጣችልኝን ሀሳብ እዚህችው ጫር ጫር የተደረገች ናት ከተመቸን እንቀጥለዋለን ‎በ ስነ-ልቦናው (psychology) ዘርፍ እስከ ዛሬ ስምምነት ካልተደረሰባቸው ጉዳዮች መካከል ስለ ሰው ልጆች የስብዕና ፀባይዮች (Human behavior) ዋነኛው ነው። የሰው ልጅ የ ፀባዩ ወይም ስብዕናው (personality) ከየት ነው የሚመጣው? የሚለው ዛሬም…
Modern Education As a Pavlov Dog
Operant conditioning

‎ከዚህ በፊት ከላይ አንድ ሀሳብ ላይ ተጨዋውተን ነበር። Behavioral psychology በሚለው ፅንሰ ሐሳብ ላይ እንዴት የኛን ስነ ባህሪ በዚህ ቲዎሪ ታግዘው ተፅዕኖ እንዳሳደሩብንና ለራሳቸው በሚመቻቸው መንገድ ስነ ልቦናችንን እንደቀረፁህ  Pavlov theoryን አንስተን አይተናል። ዛሬ ደሞ ከዚህ የሳይኮሎጂ ጥናት ላይ B.F. Skinner ያደረገውን ምርምር ተመርኩዘን እንዴት የኛን ስነ ልቦና ለመቆጣጠር( shape) ለማድረግ እንደተጠቀሙበት እናያለን።

‎B.F Skinner እ.ኤ.አ 1904 -1990 የኖረ አሜሪካዊ ሳይኮሎጂስት ነው። ከ pavlov ቀጥሎ የሰው ልጅ ስነ ባህሪው የሚወሰነው ባከባቢው ዙሪያ ባለው መስተጋብር በሚታየው ነው እንጂ በሌሎች ነገሮች አይደለም ብሎ ያምናል። ሳይንስ ውስብስብ የሆነውን የሰውን አዕምሮ ማጥናት አይችልም ለምሳሌ ደብሮኛል ስንል ግለሰባዊ ነው(subjective) ይሄን ደሞ ሰውየው ከሚነግረን ውጪ ማረጋገጥ እንችልም ይልቅስ ባህሪውን(behavior) በማጥናት የሰውን አዕምሮ መመራመር ይቻላል ብሎ ያምናል።

‎እንደ B.F.Skinner ገለፃ ከሆነ ነፃ ፈቃድ ብሎ ነገር የለም። ሁሉም ነገር ካለፈው ድርጊታችን ጋር የተያያዘ ነው ብሎ ያምናል። አሁን የምታደርገው ነገር ወይ ማድረግ የሚከብድህ ነገር በሙሉ ከዚህ በፊት ለዛ ድርጊት ከ ቤተሰብህ ይሆናል ወይ ከ አከባቢህ የተሰጠህ ምላሽ ላይ የተመሰረተ ነው ብሎ ያብራራል። ለምሳሌ ልጅ ሆነህ ወይም አድገህ መሀል ጣትህን አውጥተህ ስትሳደብ የሆነ ሰው ቢቆነጥጥህ ይሄ ቅጣት  (negative punishment) ድርጊቱን ድጋሜ እንዳታደርገው (remove a pleasant behavior) በመሆኑ ጉዳዩን በድጋሜ እናዳታደርገው ያደርግሀል ይላል።

‎B.F.Skinner behavioral theory የሚከተል በመሆኑ ለዚህ ዘርፍ Reinforcement and Punishment የሚባሉ ለዘርፉ ትልቅ ነገርን ያበረከቱ ጥናቶችን አከናውኗል። ባጭር ባጭሩ ከታች ላስቀምጥላቹህ

‎Positive reinforcement የሚባለው ጥሩ ነገርን ስታደርጉ ያንን ጥሩ ነገር ደጋግማቹህ እንድታደርጉት የምትገፋፉበት ማበረታቻ ነው። ለምሳሌ እናታቹህ ከቤት አትውጡ ብላቹህ ገበያ ብትሄድ እና ከ ገበያ ስትመለስ እዛው ብታገኛቹህ የምቶዱትን ነገር በሽልማት መልክ ትሰጣቹሀለች ማለት ነው። Add a pleasant stimulus to increase behavior ይለዋል ቢ.ኤፍ

‎Negative reinforcement የሚባለው ደሞ እንዳታደርጉት የሚፈለገውን ነገር ማድረግ እንዳይኖርባቹህ እና ማድረግ ያለባቹሁን ጥሩ ነገር በደንብ እንድታደርጉ shape የምትደረጉበት መንገድ ነው። ምናልባት Negative reinforcement የሚለውን ስሙን ስታዩ ቅጣት ሊመስላቹህ ይችላል ግን ቅጣት ሳይሆን የምትጠሉትን ነገር እንዳታደርጉት በማድረግ ጥሩ ባህሪያቹሁን እንድትቀጥሉበት የሚያደርግ ነው። እሷም ገበያ ስትሄድ አንተን በዘዴ ለመያዝ ከቤት ካሎጣህ ማታ የምታጥበውን ዕቃ እኔ አጥብልሀለሁ ትልሀለች ማለት ነው። remove an unpleasant stimulus to increase behavior ማለት ነው።

‎Positive punishment ይሄኛው ደሞ ማድረግ የሌለባቹሁን መጥፎ ባህሪ እንዳታደርጉት የምትቀጡበት መንገድ ነው። ከላይ ባየነው መሰረት ቤቱን ባዶ ቤት ጥለህ ወተህ እየተጫወትክ እናትህ ከገበያ ስትመጣ ውጪ ብታገኝህ ማጠብ የማቶደውን እቃ ቃሳጥብሀለች ማለት ነው። add an unpleasant stimulus to decrease behavior ማለት ነው።

‎Negative punishment ማለት ደሞ አንተ ቤቱን ጥለህ ወተህ እናትህ ከገበያ ስትመጣ ስታገኝህ ማታ ማታ የምትወደውን የቲቪ ፕሮግራም እንዳታይ መከልከል ወይ ስልክህን ለ 1 ሳምንት መንጠቅ ማለት ነው። ይሄ የምትወደውን ነገር በመቀማት ይሄን ድርጊት ድጋሜ እንዳትደግመው ማድረግ ነው። remove a pleasant stimulus to decrease behavior ይለዋል ቢ.ኤፍ

‎ታዲያ እንዴት ነው ትምህርት ላይ ወይም ሌላ ቦታ የሚጠቀሙበት? ካልከኝ
‎ት/ት ቤት የሚሰጥህን የቤት ስራ ሳትሰራ ስትሄድ ያለውን negative punishment ድርጊትህን እንዳታደርገው አንተን ባህሪህን ማስተካከያ መንገድ ነው። ለጎበዙ ተማሪ positive reinforcement ይሰጠዋል ድርጊቱን እንዲቀጥል። ረባሹን ተማሪ ደሞ በተቃራኒው። ይህ በትምህርት ቤት በምታልፍበት እያንዳንዱ ክፍል ላይ ስነ ባህሪህን እያስተካከሉት ነው የሚሄዱት አይምሮም ያለፈውን ቅጣትና ሽልማት ኢ ንቁ የ አዕምሮ ክፍል እያስቀመጠ ጥሩ የተባለውን እየመዘገበ መጥፎ የተባለውን ይጥላል።

‎በ አንዳንድ እስር ቤቶች መፅሐፍ ማንበብ ከ ፍርድህ ቀን ላይ ያስቀንስልሀል ይሄ ደሞ positive reinforcement ነው። እንዲሁም ጥሩ ነገር በ ማረሚያ ቤት ከሰራህ ስልክ ይፈቀድልሀል ነፃ ጊዜ ይሰጥሀል ይሄ ከላይ ስታየው ቀላል ነው ውስጡ ግን ስነ ባህሪህን መልክ ማስያዣ ነው። በስራ ቦታ የሚሰጥህ ቦነስና የሚቀነስብህ የደሞዝ ቅጣት እያንዳንዱ ነገር ስነ ባህሪህ ላይ ተፅዕኖ አለው።

‎ለዛ ነው B.F.Skinner የሰው ልጅ ቅሉ አያስታውሰው እንጂ የትኛውም ድርጊቱ ምክንያት አለው። በልጅነቱ ወይም ካደገ በኋላ የሚያሳዩት የሰዎች reinforcement እና punishment ላይ የተመሰረተ እንጂ ሌላ ምክንያት አይደለም ይልሀል። ምናልባት ዛሬ ቆም ብለህ ለምንድነው ይሄን የማደርገው ብለህ እራስህን ብትጠይቅ የኋላ ታሪክህ ላይ ይሄን ድርጊት ስታደርገው ሰዎች የሰጡህ ቀና ምልከታ ላይ የተመሰረተ ነው ወይም ማድረግ የማትፈልገው ነገር ምናልባት ልጅ ሆነህ ቤተሰብህና አከባቢህ በዛ ጉዳይ ላይ ቁንጥጫ አሳርፈውብህ ይሆናል።

የቀሩትን ደሞ የሰው ልጅ ባህሪ ይወስናል የሚሉትን ሌሎቹን ዘርፎች እናያለን

@ourrthought
8👏3
People buy stories, not just a product

‎ ስለ advertisement ከዚህ በፊት ወደ ሦስት የሚጠጉ article አጋርቻቹሀለሁ። ስለ ማስታወቂያው (advertising) ደጋግሜ የማጋራቹህ ያለምክንያት አይደለም። የሰውን ልጅ አዕምሮ ለመበዝበዝ (manipulate) ለማድረግ አለማችን ላይ በ አሁን ወቅት ትልቁ መንገድ በመሆኑ ነው። ይሄ የማስታወቂያው አለም (advertisement world) የሚጠቀሙት የጭለማውን ስነ ልቦና (dark psychology) በመሆኑ ነው።

‎የማስታወቂያው አለም (advertisement) ከሚጠቀማቸው dark psychology  አንዱ ማህበራዊ ተቀባይነት (social affection) ነው። አንድ ትልቅ ተቋም ከምርቱ ይልቅ በጣም የሚጨነቀው ምርቱን ማስተዋወቁ ላይ ነው። ለዛም ነው people buy stories, not just a product የሚሉት። አንድ እቃ ስትገዛ አንተ ትልቅ ቦታ የምትሰጣቸው ሰዎች ወይ በዛ ያለ ሰው ያንን ምርት ከተጠቀሙት የነሱን ተመሳሳይ እቃ የምትገዛው። ሰዎች ተቀባይነትን ከሰዎች እንፈልጋለን ያንን ተቀባነት ከማህበረሰቡ ለማግኘት ማህበረሰቡ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን ነገር በማድረግ እዛ ቦታ ለመቀመጥ የምንፍጨረጨረው።

‎ የኛን አዕምሮ ከኛ በላይ በጥልቀት የሚያጠኑት እኚህ ትላልቅ ድርጅቶች ከምርት ጥራት በላይ ለምርቱ ትልቅ ታሪክ ለመገንባት የሚፍጨረጨሩት። በማስታወቂያ ላይ ሮናልዶ ሲጠጣ ያየኸውን ለስላሳ አድናቂው ብትሆንም ባትሆንም ያ ሮናልዶ የሚጠጣውን ስጠኝ ትላለህ የምትገዛው ለስላሳውን ሳይሆን ታሪኩን ነው የሚባለው ለዚህ ነው። የሆነ ጊዜ ቱዋላይት ላይ የሰራው አክተር አንድ የሽቶ ማስታወቂያ ይሰራል እና በዛን ሳምንት ያ ሽቶ በሚሊዮን ነው የተሸጠው ለምን? ካልከኝ ታሪክ ገንበተዋላ።
‎እስኪ ቆም ብለህ አስብ የምትገዛው ምርት የምር ጥራትና ጥንካሬውን አይተህ ነው የምትገዛው? ወይስ ምርቱ የሰራውን የማስታወቂያ ታሪክ ተመስርተህ? ለዛ ነው የሆነ ምርት ሲመጣ በብዙ ብር ከፍሎ ታላቅ አርቲስቶችን እየመረጡ ብራንድ አምባሳደር እየመረጡ ገጭ የሚያደርጉልህ እና አንተም ምርቱን ስትገዛ እንትና የሚያስተዋውቀው እንትና የያዘው እከሌ የሚጠቀመው የምትለው ለምን social affection ነው አዕምሮህ የሚያስበው። የጡት ማያዣ የሚሸጠው ሰውዬ ጡት መያዣውን ከልብሱ ላይ ደርቦ አድርጎ ሲሸጥ ብታየው ልትስቅ ትችላለህ ሴቷ ግን በተቃራኒው በፈገግታ ትቀርበዋለች።

‎ የሆነ ጊዜ ላይ ትዝ ካላቹህ የቲክቶኩ አንድ ብር የሚባለው ወጣት ልጅ ፊቱን ገለጠ በብዙ ብር ማስታወቂያ አሰርተው ፊቱን አሳየ የሚል ነገር በየቦታው ይታይ ነበር። እና የዛኔ አውቀኸውም ይሁን ሳታውቀው ለድርጅቱ ማስታወቂያውን ስታራግብ ነበር ድርጅቱም የምርቱን ታሪክ እየገነባ ነበር። አጀንዳ በሆንክ ቁጥር ወደ ፊት ትመጣለህ ሰው አፍ ላይ ትቀራለህ ለዛ ነው አንድ ብር ፊቱን ማሳየቱ እና ማስታወቂያ መስራቱ ለድርጅቱ ትልቅ ታሪክ የገነባላቸው። የምን ማስታወቂያ ሰራ? ስንት ከፈሉት? ድርጅቱ ምንድነው? እያልክ ሳታውቀው ስትሰራ የነበረው። ለዛ ነው ሉላ ገዙን ebs በቀላሉ ወደ ቦታው ያመጣት ከቂጧ በላይ የኮንዶም ማስታወቂያ መስራቷ ቲቪው ላይ ይበልጥ እንድትመሰጥ የሆነከው።

‎ ምን ልላቹህ ነው። የምትገዛው ከምርቱ በላይ ታሪኩን : ማስታወቂያውን : promotionኑን ነው የምትገዛው እናም ንቁ ሆነህ ጠብቅ የ አዕምሮህን ጓዳ ማን እንደሚበረብረው አይታወቅምና!

@ourrthought
🔥9👏1
ሐሳቦቻችን
Photo
ሰብአዊነት ምን ይሆን?

ምስል ከቃል በላይ ይናገራል እንዲባል አንዳንድ ምስሎች ከ ብዙህ ሺህ ገፆች በላይ ይናገራሉ። በአንድ ፎቶ እድሜ ልካችንን ብንፅፍ ልንገልፀው የማንችለውን ስሜቶች አምቆ የያዙ ናቸው። ከነዛ ውስጥ ይሄ ምስል አንዱ ነው ህፃኑና ጥንባሳው (child vulture) ፎቶ ነው። በሺህ ገፆች ስለ ርሀብ ብትፅፍ ከዚህ ምስል በላይ ልትገልፅ አትችልም።

‎በርግጥ ይህን ፎት ባየሁ ቁጥር ሰውነት ሰባዊነት የሚሉት ቃላቶች ያቃጭሉብኛል።

‎ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ march 1994 የ ፎቶግራፍ Pulitzer Prize አዋርድ ላይ አንድ የአለምን ቀልብ የሳበ አንድ ምስል አሸናፊ ሆነ። አሸናፊውም የ ደቡብ አፍሪካው ፎቶ ጋዜጠኛው (photojournalist)  Kevin Carter ህፃኑና ጥንባንሳው (child and vulture) የተሰኘው ፎቶግራፉ ነበር።

‎በ እ.ኤ.አ 1993 በ ሱዳን ውስጥ አለም ቦታ ያልሰጠው ታላቅ እርሀብ ተከሰተ። የርሀቡ ምንጭ ድርቅና የርስ በርስ ግጭት ነበር። ሱዳን ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ ታጣ አቅም ያለው ከ ሱዳን ሸሸ አቅም የሌለው በቤቱ ውስጥ በርሀብ አለቁ። ከነዛ ውስጥ በ kecin carter የ ፎቶግራፍ ውስጥ የሚታየው ህፃኑ Kong Nyong ነው። በርሀቡና በርስ በርስ ጦርነቱ ሱዳን ውስጥ ከመቶ ሺዎች በላይ ለሞት ተዳርገዋል።

‎የጊዜውን ሁኔታ ለመዘገብ kevin carter እና ጓደኞቹ ሁኔታውን ለመዘገብና የጦርነቱንና የርሀቡን ስር መስደድ ለመዘገብ በነፃ አገልጋይነት ወደ sudan ከተሙ። እሱና ጓደኞቹም እየተዟዟሩ ነገሩን መዘገበሰና መረጃ መሰብሰብ ጀመሩ። ያኔ ነው kevin Ayod ወደሚባለው የሱዳን መንደር የዘለቀው የዛኔ Kong Nyong በርዛት ዝሎ ብቻውን መሬት ላይ ተቀምጦ በመሞትና በመኖር መሀል እያለ ከጀርባው አንድ ጥንባንሳ እሱን ለመብላት አሰፍስፎ የደረሰ። ኬቭን ነገሩን እንደቀልድ አላየውም ከየትኛውም ፎቶዎቹ በላይ ይሄ ፎቶ ርሀቡን እንደሚያሳይለት በመተማመን ካሜራውን ደቅኖ ፎቶዎቹን ማንሳቱን ቀጠለ።

‎የተረጋገጠ መረጃ ባይኖርም kevin ወደ 20 ደቂቃ ገደማ ትክክለኛ የምትባለዋን ጊዜ ተጠባብቋል (the right time) የሚባለውን። ኬቨን ጥንባንሳው ክንፎቹን ዘርግቶ ህፃኑን እስኪቀርበው ጠበቀ ግን ጥንባንሳው ክንፎቹን ሳይዘረጋ እርሀቡን በ ህፃኑ ኒዮንግ ለማስታገስ አድፍጦ ቆየ። kevin ከ ሃያ ደቂቃዎች ቆይታ በኋላ ያሰበውን ፎቶ ባያነሳም ጥሩ እርሀቡን የሚገልፁለትን ፎቶ ካነሳ በኋላ ጥንባንሳውን ከህፃኑ አባሮለት ከአንድ ዛፍ ጥላ ስር በሁኔታው ተረብሾ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።

‎ እ.ኤ.አ 1994 ለ ፑልቲዘር አዋርድ እጩ ሆኖ በውድድሩ አሸናፊ ሆነበት። ይሄን ፎቶ ያዩ ብዙ እርዳታ ድርጅቶች ድጋፎቻቸውን ይዘው በሱዳን ከተሙ አለም በዚህች kevin ፎቶ ትኩረቱን ለ ሱዳን እርሀብ አደረገ። ግን አንድ ጥያቄ ተከትሎ መነሳት ጀመረ kevin ለዛ ምስኪን ህፃን ምን አደረክለት? መገብከው? ወደ እርዳታ ድርጅቶች አደረስከው? የሚሉ የህሊና ጥያቄዎችን ወረወሩበት ኬቨን ግን ምን አላደረገለትም ነበርና ጥያቄያቸውን በዝምታ አለፈ። ግን ለራሱ ይሄን ጥያቄ ሊያልፈው አልቻለም። አንዲት ጋዜጠኛ ሁለት ጥንባሳዎች ይታዩኛል አለችው። kevin አልተከራከራትም ከራሱ ህሊና ግን እርቅ መፍጠር አቃተው። በሱ ፎቶ ምክንያት ብዙ የሱዳን ህፃናት ከርሀብ ቢድኑም ብዙዎች ከሞት ቢተርፉም የ አንድ ህፃን ልጅ ነብስ ግን ፋታ ነሳችው። የሞቱም መንስኤው ሆነች ፀፀት ጥፋተኝነት ጭንቀት ለቀቀችበት። kevin እስከወዲያኛው ይሄን የህሊና ወቀሳ የሚያመልጥበት ነገር አሰበ እራሱንም በ ጆሀንስበርግ እ.ኤ.አ ደቡብ አፍሪካ  ላይ 1994 አጠፋ።

‎በርግጥም የሰው ልጅ ከህሊና ወቀሳ ሊያመልጥ ይችል ይሆን? የሚለውን የሚያሳይ ይመስለኛል። እንዲህ አይነቶቹን ነገር ሳጤን የሰው ልጅ የህግ ልቦናው በተፈጥሮ አብሮት የሚመጣና ለጥፋቶቹም የሚወቅሰው ብትር ነው ያስብለኛል። ምናልባል ከ ስራ ስነ ምግባር አንፃር ከታየ kevin ስራውን ከሚጠበቅበት በላይ ሰርቷል ሁኔታውን ዘግቦ ለ አለም አሳውቋል ዛሬም ድረስ የማይረሳ ምስል ከሳች እና የጦርነትና የርሀብን ክፋት የሚገልፅ ስራ ትቶልናል። ግን ደግሞ ከሰውነትና ከህሊና ወቀሳ አንፃር ካየነውስ የሚለውን ለናንተ ትቼዋለሁ።

‎መንገድ ላይ አልፈናቸው የምንሄደው አዛውንት የኔ ብጤዎች የሚፈጥሩብንን የህሊና ወቀሳ በምን ይሆን እያመለጥነው ያለነው? የህፃናቱን የዳቦ ግዛልኝ ጉትጎታ? ቀኑን ሙሉ አልበላሁም የሚለው ልጅ ያዘለ አባት? በርግን አልፈናቸው ወደ ቤታችን ገብተን ይሆናል ግን በሰላም እየተኛን መሆናችንን ከኛ በቀር ማን ያውቀዋል?

@ourrthought
👍10😢2💯1
ሲሆን የማትነግረኝ
ካለፈ በኋላ ለምን የምትለኝ
አንተን ብሎ ህሊና
እናትንና

ቸርነት ወ/ገብርኤል

@ourrthought
🔥10
ትንሽ የማውቃቸው መልካም ሰዎች አሉ። ያስተማሩትን የሚኖሩ : የሚኖሩትን የሰበኩ።

ሰውነት ይቀድማል!

‹‹ሰው ሁኑ! ቅድሚያ ሰውነት ይቀድማል!
ከሐይማኖት ሰውነት ይቀድማል! ከዘርም ሰውነት ይቅደም!
አላህ ሰውን ከሁሉ በላይ አልቆታል::

ሰው ሊገፋ፣ ሊሰደድ፣ ሊገደል፣ ሊናቅ፣ ሊወገዝ በፍፁም አይገባም:: ልዩ ፍጥረቴን ክብሩን ጠብቁ ይላል"

ያሚያምኑት አምላክ ነብሳቸውን ይቀበላቸው!

@ourrthought
16😢4
ላምጪው እንዲከፈል ሕግ ያስገድዳል (payable to the bearer on demand)

‎ ይህ ፅሑፍ ማንኛውም ብር ላይ ያለ ፅሑፍ ነው። ትርጉሙ በያዝከው የብር ኖት ገንዘቡን የሚመጥን አገልግሎት የማግኘት መብቱ አለህ ማለት ነው። ለምሳሌ የ 10 ብር ኖት ይዘህ የ 10 ብር አገልግሎት የማግኘት መፍቱ አለህ እንደማለት ነው። ላምጪው የሚለው ቃል የሚወክለው ገንዘቡን በ እጁ የያዘውን ግለሰብ ነው።

‎ ይሄ ሕግ አለም ላይ የትም ቦታና ሀይማኖት ላይ ታገኘዋለህ። ካርማ ማለት ያ ነው። የዘራኸውን ታጭዳለህ ለ አለም የሰጠኸውን መልሰኽ ታገኘዋለህ። በ ሀይማኖትም ቢሆን በክርስትናው "ሰው የዘራውን ያንኑ መልሶ ያጭዳል" ይላል። ጥላቻን ከዘራህ ጎተራህ በጥላቻ ይሞላል። የሰጠኸው ይመለስልሀል። ለአለም ምንድነው ይዘህ የምትሄደው? ገንዘብ ላይ ያለው ሕግ ለ አለምም ይሰራልና አለምም የተለየ ዘይቤ የላትም "payable to the bearer on demand" የሚለውን ትተገብረዋለችና።

@ourrthought
👍173
‎ ጊዜው አርአያ ያጣ የሚመስል ዘመን ነው። ምሳሌ የሚሆን ሰው መጠቆም እስኪቸግረን ድረስ አርዐያ ያጣ ዘመን ላይ ያለን ይመስላል። እንደ ሀገር ተስማምተን የምንጠቁማቸው ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው።


‎የፍቅር የጀግንነት ምሳሌ የምናደርጋቸው ሰዎች ራሱ ጥያቄ ውስጥ ይከታሉ። ባንድ ወቅት ጎፋ ጋር ለ ብዙ አመታት ፍቅረኛውን በመጠበቅ ላይ የሚቆመውን ሰውዬ እንደ አርዐያ አድርገው ሲያነሱት ይገርመኝ ነበር። ዘፈን እስኪሰራለት ድረስ እንደ ትልቅ ምሳሌነት በየሚዲያው ላይ ሲዘግቡት ማየቴ በጊዜው አስገርሞኝ ነበር። እሱ ሰውዬ ከፍቅር ምሳሌነት ከማቅረብ ይልቅ ወደ አዕምሮ ህሙማን አስገብተውት ሊታከም የሚገባው ሰው ነበር መሆን የነበረበት። ሰውዬው ከ እውነታው አለም የተለየና በቁም ቅዠት ውስጥ የገባ በድሮ ሁኔታ የቀረ ሰው ነው።    ፍቅረኛው በ አካል እንኳ መጥታ ሊለያት ያልቻለ ሰው ነው። እሱ ያለው አሁን ላይ አይደለም ድሮ ላይ እንደቆመ ነው። አዕምሮው በስርአቱ እያሰበለት ያልሆነን ከ እውነታው የተላቀቀን ሰውዬ ህክምና አግኝቶ እንዲድን ከማስቻል ይልቅ እኛ ግን ያደረግነው ለፍቅር የተከፈለ መስዋትነት ብለን አርዐያ ማድረጋችን ነው። ይሄ የሚያሳየው ምን ያክል ዘመኑ አርዐያ እንዳጣ ነው።

‎ አንድ ሰው የ አዕምሮ ታማሚ ነው ለማለት የሚያስችሉ ነገሮችን የሚያሟላ ሰው ነው። የ አዕምሮ ህመምተኞች ታማሚ የሚያስብላቸው አንዱ ነገር ይህን አለም እውነታውን መረዳት ባለመቻላቸው ነው። በከሚታየው ይልቅ የራሳቸውን ትንሽዬ አለም አዕምሮዋቸው ውስጥ ገንብተው ከ ሚታየው አለም ተነጥለው በራሳቸው አለም መኖራቸው ነው። መንገድ ላይ የምታዩዋቸው የ አዕምሮ ታማሚዎች መንገድ ላይ እያወሩ የሚሄዱት ለዛ ነው። ምንም ባሌለበት ነገሮችን የራሳቸው አዕምሮው ያሳያቸዋል የድሮድምፅ እንዲሰሙ ያደርጋቸዋል። ይሄ በ ሳይንሳዊ ስሙ ስኬዞፎርኒያ የሚባል ችግር ነው። ፍቅሩን በመጠባበቅ ላይ ያለ እውነታውን መቀበል ያቃተው በራሱ አለም (fantasy) ውስጥ የገባ ሰው ነው። ክህደት ውስጥ ያለ (denial) ምስኪን የ አዕምሮ ህመምተኛ ነው።

‎ጨለምተኛ አይነት እሳቤ ያለኝ ሰው አይደለሁም። ግን ደግሞ በየ ማህበራዊ ሚዲያ ለ አርዐያነት የሚቀርቡ ሰዎችን ስመለከት ትንሽ ግር ስለሚለኝ ነው። አሁን ላይ በ ፌስቡክ ፣ ቲክቶክ የሚወደዱ ሰዎች ተሳዳቢዎችና የሰውን ክብር የሚነኩ ሰዎችን መሆኑ የቱ ጋር ነው የቆምነው የሚለውን የሚያሳይ ነው። በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ብዙ መልካም ሰዎች ፣ ብዙ ባለ አዕምሮ ሰዎች ፣ ብዙ ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎች በየቦታው ድምፅ ሳያሰሙ አሉ። እነሱን ያብዛልን።

@ourrthought
👍101
ሐሳቦቻችን
Photo
ክፉ ሰዎች የሚሸወዱት ትልቁ ነገር ክፉ ለመሆን መልካምነት የተሻለ መንገድ መሆኑ አይገባቸውም። ግራ ያጋባል አይደል አባባሉ። አዎ ልክ ነው ስህተት የለውም አባባሉ። እናንተን ለመጉዳት የሚፈልግ ሰው ከክፋት ይልቅ የበዛ መልካምነት በጣም ቀላሉ ዘዴ ነው። ለምታደርጉት ነገር የበዛ ምስጋና ቢሰጧቹህና ትንሽ ትንሽ ነገር ቢቦጭቁላቹህ ምቾት እንዲሰማቹሁ ቢያደርጓቹህ አለቀላቹህ።

‎ከዛሬ 8 እና 9 አመት አከባቢ ርዕሱሡን የማላስታውሰው የ ኦሾ መፅሐፍ ላይ አንድ የሚገርመኝ አሀሳብ ነበር። በጊዜው ሳነበው ይሄማ የሌለ የማይመስል ነገር ነው ብዬ ነበር ያለፍኩት። ቃል በቃል ባላስታውሰውም ሀሳቡን ልንገራቹህ " ህይወትህ ላይ ክፉ ከሚሆኑብህ ሰዎች በላይ ሲበዛ መልካም የሚሆኑልህ ሰዎች ይጎዱሀል" አይነት ሀሳብ ነው።

‎ሀሳቡን ከላይ ስታየው ቀላል ቢመስልም ትልቅ እውነትነት ያለው ነው። ነፃነትህ ያለው ጥሩ የሚያደርግልህ ሰውዬ ጋር ነው ወይስ ክፉ የሚያደርግብህ ጋር ?  ብትባል የት ነው የምትለው? መልካም ከሚያደርግልህ ሰው በላይ በውለታው አስሮ ያስቀመጠህ ከወዴት ይገኛል?  ክፉ ናቸው የምትላቸው ሰዎች እንኳን እንዲህ በክፋታቸው ተብትበው አልያዙህም። ህይወታችን ላይ ይበልጥ አስረው የሚያስቀምጡን መጥፎ ከሚያደርጉብን በላይ አለቅጥ መልካም የሚሆኑልን ሰዎች ናቸው። በውለታቸው ተብትበው አስረውህ ሁል ጊዜ በነሱ ታስረህ እንደኖርክ ነው። ግንኙነቱን እንኳ ጥለህ እንዳትሄድ መልካምነታቸውን ያደረጉልህን ነገር እያሰብክ እየተጎዳህ መኖርን ትመርጣለህ። ክፉ አለቃ ካለህ ስራህን ለመልቀቅ እና አማራጭ ለመፈለግ አታመነታም። በጣም መልካምነቱ የበዛ አለቃ ቢኖርህ ግን ያደረገልህን ነገር እያሰብክ ውለታውን እየቆጠርክ እየተጎዳህ መስራትን ትሻለህ።

‎በረከት በላይነህ ጥሩ አከራይ ያለው ሰው መቼም ቢሆን ቤት አይሰራም ይላል። ምቾቱ ሌላ አማራጭ እንድትፈልግ አያደርግህም ሁሌም ተዘናንተህ እንደተቀመጥክ ነው። ጨቅጫቃ አከራይ ሲኖርህ ግን የራስህን ቤት እንዴት መስራት እንዳለብህ ያሳስብሀል። እስከ መቼ እንዲህ ኖራለሁ ትላለህ። አንስታይን ይመስለኛል "ህይወቴ ላይ እሺ ካሉኝ ሰዎች ይልቅ አይሆንም ያሉኝ ሰዎች ባለውለታዬ ናቸው። ነገሮችን በራሴ እንዳደርጋቸው አድርገውኛል" ይላል። የከፉብህን ሰዎች ብታስብ ህይወትህ ላይ ትልቁን ነገር ያደረጉልህ እነሱ መሆናቸውን ትረዳለህ። የኩረጃ ዘዴ እንደሌለ ያወክ ቀን ለማንበብ መነሳትህ አይቀርም።

‎ ቁራ ልጆቿ ከ እንቁላል ከተፈለፈሉላት በኋላ ከመኝታቸው ከላባ ጉዝጓዝ ስር እሾህ ታስቀምጣለች። ይሄን የምታደርገው ልጆቿ በላባው ሙቀትና ልስላሴ ተመስጠው መብረር እንዳይረሱ ነው። ምቾት ካለ ለምን ይበራሉ? ቀስ ቀስ እያለች ላባውን ታነሳባቸውና በመጨረሻ እሾሁን ታስቀርባቸዋለች የዛኔ እሾሁ ሲወጋቸው እሱን ሽሽት ይበራሉ። ህይወትህ ላይ የበዛ መልካምነት ያላቸው ሰዎች ከላባው ልስላሴ እና ሙቀት ነው የሚሰጡህ። እሾሁን የሚሰጡህ ሰዎች ክፉዎቹ ናቸው እነሱም እንድትበር ያደረጉህ ናቸው። ዙሪያህን ተመልከት ይበልጥ አሳስሮ ያስቀመጠህ ማን ነው?  ውለታቸው እንዳለብህ እያሰብክ የምትኖረው እነማንን ነው? ነገሮችን ያለህበትን ቦታ ትተህ እንዳትሄድ ያሰረህ ማን ነው? መልካም ሰዎቼ የምትላቸው አይደሉምን? አንዴ ሞክረህ ያቃተህን ነገር የሚሰሩልህ ሰዎች ጥሩ እንደሆኑልህ የምታስብ ከሆነ ይመችህ ይልቅስ በራስህ ሰርተህ እንዳትሞክረው ያደረጉህ ያለመቻልህ ተምሳሌት ሊሆኑም እንደሚችሉ ማሰብ ተገቢ ነው።

ዙሪያችን ላይ ለነበሩና ላሉ ክፉ ሰዎች ችርስ ምንም ነገር የማድረግ ነፃነታችን እና የ ችሎታዎቻችን ማሳያዎቻችን ናቹህና!

@ourrthought
9
Forwarded from ቀለም መጽሔት
ቀለም መፅሔት ቅፅ 1 ዕትም 4.pdf
6.1 MB
ቀለም መጽሔት🗞️

ቅፅ 1 እትም 4


እያነበባቹህ ለወዳጅዎ ያጋሩ
ለሀሳብ አስተያየት

@KelemMagazine

Telegram 👇❤️
@kelemofficial
5
ቀለም መጽሔት
ቀለም መፅሔት ቅፅ 1 ዕትም 4.pdf
እስኪ ደሞ የዚህ ወር ዕትሟን አጣጥሙ እና እንደተለመደው ልቦለድ ጥፈናል እና እያነበባቹህ ሀሳብ ካላቹህ በ ሀሳብ መስጫ ላይ አስቀምጡልኝ

@ourrthought
እምነ ርሀብ ይሔይስ ኩይናት

ከርሀብ ጦርነት ይሻላል

@ourrthought
😢6
ስለ አለቃ ገ/ሐና ትንሽ እንጨዋወት። መቼስ አለቃ በሚናገሩትና : በመልስ ምታቸው ይታወቃሉ። ስለሳቸውም እስከዛሬ ብዙ የተፃፉ መፅሐፍትን ማግኘት አልቻልኩም ከ ሊቁ አለቃ ገብረሐና እና ከ ጋብሮቮች ጋር አብሮ ከታተመላቸው ውጪ። ዛሬ ከ ሊቁ አለቃ ገብረሐና ከሚለው ሁለት እንቀንጭብ።


ባንድ ወቅት አለቃ ገ/ሐና ሚስታቸው ማዘንጊያሽ ወጥ እየሰራች በማማሰያ ጠለፍ እያደረገች በምላሷ አሁንም አሁንም ደጋግማ በመላስ እየቀመሰች አለቃ ደጋግመው ያስተውሏታል።

ይሄኔ አለቃ ተማረው " ማዘንጊያሽ እራታችን እሱ ከሆነ እኔም መቋሚያዬን ይዤ ልቅረብ" አሉ ይባላል።


ባንድ ወቅት አለቃ ለልጆቻቸው ልብስ ለመግዛት በጎቻቸውን ለመሸጥ ወደ ገበያ ይዘው ይሄዳሉ። ታዲያ አንድ ሰው መጥቶ ስንት ነው ቢላቸው። 8 ብር ይሉታል። ሰውየውም ቀበል አድርጎ "በዚህማ ወደል አህያ አልገዛበትም እንዴ" ቢላቸው። እኔ እንግዲህ ዋጋውን ነገርኩህ እንጂ የሚጥምህን አንተ ታውቃለህ" አሉት ይባላል።

ሰውን እንዳመጣጡ መሸኘትን ተክነውበታል መቼስ አለቃ ባሉበት ይመቻቸው!

@ourrthought
6😁5
ልመርቅላቹህ


እቴጌ ጣይቱና እህታቸው ወይዘሮ አሰለፈች የ እንጦጦ የራጉኤልን ቤተክርስቲያን ደረጃ አሻቅበው ሲወጡ አለቃ ከደረጃው ስር ነበሩና አንጋጠው ወደላይ ሲመለከቱ አዩና "አለቃ ምን አሻቅበህ ትመለከታለህ" ብለው ቢጠይቋቸው። አለቃም "መውጫዬን እየተመለከትኩኝ ነው" ብለው መለሱላቸው😎

@ourrthought
🤣111
ነፃነት ምን ይሆን?

ምናልባት አርዕስቱን ስታኑዩት ምንድነው ይሄን ጥያቄ የሚጠይቀው ትሉ ይሆናል። በርግጥም የ አማርኛ መዝገበ ቃላት ላይ ነፃነት የሚለውን ፍቺ ብትመለከቱ አርነት ፣ መብት የሚሉትን ፍቺዎች ይዘረዝርላቹሀል። ነፃነት ምንድነው የሚለውንም ብታዩ አንድ ሰው የራሱን ፍላጎትና ሀሳብ ያለማንም የውጭና የውስጥ ጣልቃ ገብነት የፈለገውን ነገር የማድረግና ስልጣን ነው።

በነፃነት ስም ብዙ ነገር ተፈፅሟል።
Edward Bernays በ 1929 እ.ኤ.አ በ አሜሪካ የነበረውን ሴት ልጅ በ አደባባይም ሆነ በጓዳ ሲጋራ አታጨስም የሚለውን ማህበረሰባዊ ክልከላ የሰበረበት ዘመቻ "Torches of Freedom" የሚል ነበር። የነፃነት ችቦ በነፃነት ስም ዴሞክራሲ የምትለዋን ሽፋን በማምጣት በ አሜሪካ የነበሩትን ከ 5 % በታች አጫሽ ልጃገረዶች ቁጥር ወደ 35 እንዳደረሰው ይገመታል። በዚህ አርዕስት ላይ YouTube ላይ አንድ ዶክመንተሪ አለ century of the self የሚል እዛ ላይ "Happiness machine part 1" ተመልከቱት።

ሌሎችንም ብንዘረዝር በነፃነት ስም ብዙ ነገሮች ተፈፅመዋል። ይሄ ልቅ ያጣ ነፃነት ተለጥጦ ተለጥጦ በ ዴሞክራሲ በ እኩልነት ስም በፆታ ግራ እስኪጋቡበት ድረስ ተለጥጧል። አሁን ላይ በ አውሮፓ ሀገሮች ላይ ግለሰብን ለ ራሱ ለግለሰቡ በመተው ከቤተሰብ ፣ ከ ሀይማኖት ፣ ከ ማህበረሰቡ የተነጠለ ግራ የገባው ሰው የተፈጠረለት ፆታ ሳይቀር ግራ ሲያጋባው ማየት መስተዋሉ የተለመደ ነው።

በርግጥ ሰው ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆን ይገባው ይሆን? Sigmund Freud የሰው ልጅ ደስታን የሚያሳድድና ስቃይን ከራሱ ላይ ለመቀነስ የራሱን ደስታ በማንኛውም መንገድ ማሳካት የሚፈልግ ባዮሎጂካዊ "Libido" የሚባል ነገር አለ ይለናል። ይሄ Libido ብዙ ጊዜ ከ ወሲባዊ ስሜት ጋር ብዙዎች የሚያይዙት ነው። ግን ደግሞ ይሄ ሊቢዶ በሰፊው የሚብራራ ነገር ነው። Libido የራሱን ደስታ የሚያሳድድ ኢ-ፍትሀዊ የሆነ ግፊት ነው። በሌላ መልኩ "Animal force" እንስሳዊ ደመነብስ የሚባለው ነው። በስሜት የሚነዳና የማያገናዝብ ስሜት እንደማለት ነው።

የሰው ልጅ ነፃ መሆንስ ይችል ይሆን? የሚለውን ብናይ ከሀይማኖት ፣ ከ ማህበረሰብ ፣ ከሲስተም እንኳ ነፃና ገለልተኛ ቢሆን ከራሱ ተራ ምኞት ግን ነፃ ሊወጣ አይችልም። የራሱን ባህሪ መግራት የማይችል ሰው እንዴት ነፃ ሊባል ይችላል? በራሱ ደመነብሳዊ ግፊት የሚመራ ሰው "libido" ያየለበት ሰው ነፃ ነው ማለት እንችል ይሆን? Hedonist የሚባሉ ሰዎች አሉ ግባቸው ደስታና ደስታ ነው ለነሱ እስከጠቀመ ድረስ ምንም ነገር ያደርጋሉ። እነዚህ ሰዎች የደስታቸው እስረኞች ናቸው። Sadistic የሚባሉም ሰዎች አሉ በሰው ሀዘንና ስቃይ የሚደሰቱ ናቸው። እነዚህም የራሳቸው እስረኞች ናቸው። ሁላችንም የራሳችን ከንቱ ምኞቶች ባርያ ነን።

የሀይማኖት ፣ የማህበረሰብ ክልከላዎች ነፃነታችንን ከመፈግ ይልቅ ከራሳችን ተራ ምኞቶች የሚታደጉን እንጂ እስር ቤት አይደሉም። ይሄን ስል ሁሉንም የሀይማኖትና የማህበረሰብ ክልከላዎች ማለቴ አይደለም። ሰው ነፃ መሆን ይችላል ብንል ዞሮ ዞሮ የሆነ የተተበተበበት ትብታብ አለ። አስተዳደጉ ፣ ቤተሰቡ ፣ ልማዱ ፣ ፖለቲካው ፣ ፍላጎቱ እነኚህ ነገር ይከተሉታል።

ሀሳቤን በ ሁለት ምሳሌ ላጠቃልል


በ Shawshank redemption ፊልም ላይ አንድ እረጅም ጊዜ የታሰረ ሰው አለ። ከ እስር ቤት መውጣት ይፈራል። ህይወቱን በ እስር ቤት አድርጓል የኔ የሚለው ነገሩን ሁላ ከዛ እስር ቤት ነው ያለው። ውጪ ላይ ጓደኞች የሉትም እስር ቤት ግን አሉት ታዲያ ይሄ ሰውዬ ነፃ መሆን ሲችል እሱ ግን እያሳበበ እስር ቤት መቆየቱን ይፈልግ ነበር። ይሄን ስናይ ሰው የለመደው ነገር ውስጥ ነው ነፃነቱ ያለው የሚለውን ያሳየናል። ምናልባት ከዚህ አለም ውጪ ያሉ ፍጡራን እኛን እንደ እስረኛ ይሆናል የሚቆጥሩን ሰማዩ የተደፋብን ከራሷ ባህር ወታ እንደማታውቅ እንቁራሪት አይነት ነገር እኛ ግን ምድር እስር መሆኗን አናውቀውም የለመድነው ነውና ከዛም ወተን አናውቅም።


በሀገራችን በድሮ ዘመን በባሪያ ንግድ ጊዜ ወዶ ገባ ባሮች ነበሩ። እኚህ ባሮች ነፃነት ሲሰጣቸው አንፈልግም ባርነት ይሻለናል ብለው በፈቃዳቸው ባርነትን የመረጡ ናቸው። ከተወሰኑ የባርነት ጊዜያት በኋላ ነፃነት ቢሰጣቸውም እነሱ ግን ባርነት ዘመዴ ያሉ ናቸው። የዛኔ አሳዳሪዎቻቸው በብረት አግለው ይጠብሷቸዋል ለዘላለም ባሪያቸው መሆኑን የሚገልፁበት መንገድ ነው። ባኖቹ ያን የሚያደርጉት ያማረ ምግብና መጠጥ በነፃ ስለሚያገኙ ነው። ከዛ ቢወጡ ሌላኛውን የነፃነቱን መንገድ አያውቁትምና ይፈሩታል በዛ ላይ ያማረና የላመ ይመገባሉ ያሳዳሪዎቻቸውን ያረጁ ልብሶች ይለብሳሉ። እንግዲያው በዚህ ዘዴ ሰው የሚያውቀው ነገር ውስጥ ነው ነፃነቱ ያለው እንድንል ያስችለናል።

ነፃነት ተለጥጦ ተለጥጦ ግለሰባዊ ነፃነት ላይ ደርሷል። ዘመነኛው ሰው ከሁሉ ንጡልና ጣዕም አልባ ሆኗል። ሰው ከነፃነት ይልቅ በነገሮች መታጠርና በሱ መኖሩ ከልቅ ነፃነት ይበልጥ ስሜት ይሰጠው ይሆን? ወይስ ሙሉ ለሙሉ ነፃ ሆኖ በራሱ መኖሩ ገደብ አልባ መሆኑ ይበልጥ ይጥመው ይሆን?

@ourrthought
👏92👍1
ሐሳቦቻችን
Photo
ህላዌነት!

‎ጠዋት ጠዋት ከህይወት ጋር የህላዌ ፍጥጫ ገጥማለሁ። መኖር በራሱ ምንድነው? የሚል መልስ የሌለው ጥያቄ አመነዥካለሁ። ይሄን ጥያቄ ላለፉት 5 አመታት ጀምሮ አጥብቄ ብጠይቅመ እስካሁን ረብ ያለው መልስ አግኝቼ አላውቅም። ሰው ምድር ላይ ምን ይሰራል? ለምን እንኖራለን? ከመፈጠራችን በፊት የት ነበርን? በርግጥስ ወዴት ነው ስንሞት የምንሄደው? የሚል ጥያቄ። በርግጥ ይሄን ጥያቄ ብጠይቅም የህይወትን ከንቱነት ከማባስ ይልቅ የጠቀመኝ ነገር የለም።

‎ ጎዳና ላይ ከአንድ ጎዳና ተዳዳሪ የተወለደ ልጅ ከጎዳና ውጪ ተስፋው ምንድነው? ከሚያውቀው አለም ውጪስ እንዴት ሊያስብ ይችላል? አሁን ከወለዱን ቤተሰቦቻችን ለመወለድ ምን ጥረናል? ሀብታም ቤት ውስጥ ለመወለድ ማን ጥረት አደረገ? ሰው ሲወለድ አካሉ እንዳይጎድል ምን ጥረት ያደረገው ነገር አለ?  ህይወት በዚህ ልክ ላንዱ መልካም ለሌላውስ ለምን የመረረስ ትሆናለች? መልስ ባላገኝም ሁሌ የማመነዥከው ጥያቄዬ ነው። እኔ ራሴ ምንድነው እዚህ እየሰራሁ ያለሁት (ምድር ላይ) የሚል የከንቱነት ጥያቄ እለት እለት እያላተመ ያላምጠኛል።

‎በርግጥ ሀይማኖቶች እንደነገሩን የሰው ልጅ ለምስጋና ብቻ ነው እዚህ ምድር ያለው? ፈጣሪ ባታመሰግነው የማይጎልበት ፣ ብታመሰግነውም የማይሞላለት ሆኖ ሳለ ስለምን የሰው ጫካ ምድር ላይ ይዘራል?ምን ሊበጀው?  ሌላ አላማ አለው እንዳልል ሰው እንደቀላል ነገር የከበረች እስትንፋሱ በመኪና ለሚቋጭባት አለም ፣ በተራ ፀብ ለሚሞትባት አለም ፣ አንዳንዱ ተሰቃይቶ ሳይኖር ለሚሞትባት አለም ፣ ተወለዱ ሞቱ ከሚል ውጪ ታሪክ ያልፃፈ ሰው ሳይ ደሞ በርግጥስ የተፈጠረበት አላማው ምንድነው? ያስብለኛል።

‎ ይህ ወለፈንዲነት እን ካሙ እንደሚሉት Nihilism አይነት እሳቤ ነው። የራስህን ምክንያት እስካልፈጠርክ ህይወት በራሷ ተራ ነገርና ምክንያት አልባ ናት ይላሉ። ይሄም ቢሆን አይዋጥልኝም። ሰውን ያህል የከበረ ፍጡር ያለምንም ምክንያት ይሄን ብሩህ አዕምሮ ይዞ እንዴት ይፈጠራል?  በዝግመተ ለውጡ ብቻ እዚህ ደረሰ?  እራሱን ለማኖር በሚያደርገው የኑሮ ትግል ብቻ የሰላ ሆነ? ይሄም አይዋጥልኝም። የራሴንም አለም ብገነባ ከከንቱነቱ ሊያስጥለኝ አልቻለም ፣ ሀይማኖቱም ምላሹ ሊያረካኝ አልቻለም።

ደስተኛ ሰዎች ያስቀኑኛል። የህላዌ ጥያቄ የሌለባቸው ሰዎች ዝም ብለው የሚኖሩቱ። ከንቱነት የለባቸው ፣ እርባናቢስነት የለባቸው። በገንዘባቸውም አለማቸውን የገነቡ ሰዎች ታድለዋል የህላዌ ጥያቄያቸውን በዛ ውስጥ መልሰውታል። በነዚህ ሰዎች እቀናለሁ በቁሳቁስ ህይወታቸውን በደስታ ለሚኖሩት ሰዎች ሳይ ድንቅ ይለኛል ሌላ ነገር የጎደለባቸው መኖሩን ዘንግተዋል ያላቸው በቅቷቸዋልና።

‎ምናልባት የሰው ስሪቱ ምድር ላይ መፈጠሩ ፣ ግቡ እራሱን ፈልጎ ማግኘቱ ብቻ ቢሆንስ? ማንነቱን የማወቅ ሂደት ብቻስ እራሱን የመፈለግ ቢሆንስ? መላዕክትን ፈጥሮ እንዳበቃ እንዲመራመሩ እንደተሰወረባቸው ሁሉ እኛም ያ ዕጣ ቢሆንስ የምድር ዕጣ ፈንታችን?


@ourrthought
6👍3
‎ሰው ሰውነትን ለመገንባት የሄደበት መንገድ የተሳሳተ እንደሆነ አስባለሁ። ምድር የእብዶች ጉባኤ ሆናለች። ዓለምን የ አመጻ ቤተሙከራ አድርገዋታል። ቀደም ባለው ጊዜ በቅዱሳቱና ተረታቱ መጻሐፍት እንደተነገረን በዚህ በ አመጻ ግብሩ አማልክት ሳይቀሩ ተሳታፊ ነበሩ። በጥንቱ ዘመን ሰዎች ጠንካራ ህብረትና መተባበር እንዲመሰርቱ ብሎም ትንንሽ ግዛቶችና ሀገራት እንዲፈጠሩ ጦርነቶች ሚና እንደነበራቸው ይነገራል። ምናልባት ዘመኑ < Age of formation> ስለነበር ይሄን ፈቅዶ ይሆናል። አሁን ግን ዘመኑ የመበስበስ ፣ የመፈራረስ < Age of decadence> በመሆኑ በጦርነት የምትፈራርስ እንጂ የምትገነባ ሀገር አትኖርም።


በፍም እሳት ማቃመስ
‎ ያዕቆብ ብርሀኑ


@ourrthought
👏7
ሚስት : ሴቶች ሁል ጊዜ ቤት ውስጥ ምግብ እየሰሩ ባላቸውን መመገብ ግዴታ ያለባቸው ይመስሀል እንዴ😡

ባል : አዎ ግዴታችሁ ነው!

ሚስት: እንዴት ሲባል😡

ባል: በህጉ መሠረት እስረኛ በቀን ሦስት ጊዜ መመገብ አለበት ይላል።🙄

ሚስት : እስረኛ ነኝ ብለህ ነው የምታስበው 🤬

ባል : ካልሆንኩኝ ሌላ ሴት ጋር እንድሄድ ፍቀጂልኛ☺️

ሚስት : ቁጭ በል : ንቅንቅ እንዳትል! ጥይቷን ደቅናበት

ከዛን በሰላም ተስማሙ! በንግግር የማይፈታ ነገር የለም።

@ourrthought
😁23🔥2