ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
²⁷ ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?
ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።
ማቴዎስ ወንጌል
አሜን🙏
@ourrthought
🙏8❤3
ወደ ኋላ መመለስ ይኖርብን ይሆን?
ጥንታዊውን ሰው በዛሬ ቅኝት ለመቃኘት ካሻህ ቡሽሜንን (Bushmen tribes) መጎብኘት በቂህ ነው። እኚህ ጎሳዎች ለ አለም ወደኋላ ቀርተዋል ልብስ የላቸውም ፣ ጫማ አይጫሙም፣ ቤት የላቸውም ፣ ዛሬም አድነው ይመገባሉ ፣ ተፈጥሮን በራሳቸው መረዳት ይረዷታል ከልባቸው ደስተኛ ናቸው በቃ ዛሬ አድነው ከበሉ ዛፋቸው ስር ጥላቸው ላይ አረፍ ብለው ሀሴት ያደርጋሉ ከህይወት የሚጠብቁት ሌላ ታምር የለም። አለም ላይ ሀያሏ ሀገር ማን ናት ፣ ቢሊየነሩ ሰው ማነው? ፣ ዝነኛዋ እከሌ ማን ናት ጉዳያቸው አይደለም።
ታዲያ ባንድ ወቅት አንድ የ አውሮጳ ጋዜጠኛ እነሱን ለመጎብኘት ሄደ ያሰበውና ያገኘው ግራ አጋባው እነሱ ሚዳቆ አድነው የሚያገኙትን ደስታ የዘመንን ነን ብለን የምናስበው ሰዎች ፎቅ ደርድረን አናገኘውም። ከዛም ጥያቄውን ማስከተል ጀመረ። ህይወት ከንቱ አይሆንባችሁም? አላቸው ምንድነው ይሄ ሰውዬ የሚያወራው አይነት አዩት ሚዳቆ ካደኑ የምን ከንቱነት ነው ደሞ ሆ። ከዛም ቀጠለ እራሱን የሚያጠፋ ሰው ጎሳችሁ ውስጥ አለ? አላቸው ግራ ገባቸው እንዴት ነው ሰው ራሱን የሚያጠፋው? ጋዜጠኛውም ያው ህይወት ከንቱ ሆናበት ተስፋ ቆርጦ አብራራ : ሰው ጭራሽ ተስፋ ይቆርጣል : ደሞም እራሱን ያጠፋል ደነገጡ። አድኖ ከበላ እሳቱን ከሞቀ ተፈጥሮን እየኮመኮመ ከኖረ ጭራሽ ምን ልሁን ብሎ ነው የሚያጠፋው? በሰሙት ነገር ተገርመው ሊሞቱ ምን ቀራቸው። በርግጥ ሰው እራሱን ማጥፋት መቻሉንም ያመኑትም አይመስሉም።
ዘመነኛዎቹ እኛ ግን በብዙ ርቀት ጥለናቸው ብንሄድ ደስታ ደሞ ከኛ ዘንድ ጓዙን ይዞ ከሸሸን ሰነባብቷል። ምንም ቢኖረን ለመደሰት አቅቶናል ያለን ነገር ደስታ ሳይሆን ስቃ የጨመረብን ይመስላል። ግን የሰው ልጅ መመራመሩ ፣ ጨረቃን መርገጡ ፣ ጠፈርን ማሰሱ ፣ ቴክኖሎጂን ነጋ ጠባ ማዘመኑ ፣ መኪና ፣ ስልክ ፣ ቤት ፣ ልብስ የመሳሰሉት ለኛ ለዘመነኛዎቹ ሰዎች ምን አተረፈልን? የሚለው ጥያቄ ሁሌም ቢሆን ያሳስበኛል። ዘመናዊው ሰው ደስታውን በማሰስ ፍለጋ ውስጥ እያንዳንዱ የሚከፍታቸው በሮች ሀዘንን ከመሰብሰብ ውጪ ምን አተረፈለት? እያንዳንዱ ግኝት ውስጥ ሌላ ከመጨመር እና አልረካም ባይ ስብዕና ካማግበስበስ በቀር።
እኛ ዘመነኛ ነን የምንል ስልጡኖቹ ሰዎች አንድን ማቴሪያል ከመገልገያነት ባለፈ ለሀዘናችን ምንጭ አልሆነምን? ማነው ስልኩን ለስልክነት ብቻ የሚልገው? የያዘውን የድሮ ሞዴል ስልክ አሽቀንጥሮ አዲስ ምርት ለመያዝ ያለው ጭንቀት አይበዛምን? የሚኖርበትን ቤት ቁርና ወበቅ ከተቀላከለ በቂዬ ነው ብሎ የሚያስብ ማነው? የሚኖርበትን ተልካሻ ቤት ለመቀየር እና በሰዎች ዘመናዊ ቤት የሚቀናው አይበዛምን? መኪና ከሌለው ሰው በላይ መኪና ያለው ሰውዬ ጭንቀቱ ይበዛል ምክንያቱም የያዛትን መኪና ቶሎ ወዲያ አሽቀንጥሮ አዲስ ሞዴል ስለመንዳት እንጂ መንገዱን ስለማሳጠሩ አይደለም ጭንቀቱ። ዘመነኛዎቹ ሰዎች ውድድር ውስጥ እንጂ ኑሮውን ለራሱ መኖር ያቆመ ይመስላል። dopamine የምናመነጨው ስልክ ስንገዛ ሳይሆን ከሰዎች የበለጠ ስልክ እንደያዝን ስናስብ ነው ለዛ ነው በየጊዜዎ iPhone በወጣ ቁጥር እሱን ለመግዛት ሌሎቹን ለመብለጥ ጫማ የምንለካካው።
ዛሬም ድረስ ወሬህ ኤለን መስክ በሀብት ሰንጠረዡ ላይ ሁለተኛ ስለመሆኑ እንጂ በገንዘቡ ምን ተጠቀመ? የሚለውን አናስበውም በ ሀብት አንደኛ ደረጃ ላይ ያለው ሰውዬና 100 ደረጃ ላይ ያለው ሰውዬ የኑሮ ልዩነታቸው ምንድነው? ሁለቱም ጭንቀታቸው አንደኛ የሀብት ደረጃ ላይ ለመቀመጥ እንጂ ስለተቀመጠው ገንዘባቸው አይደለም። ቁሳዊው አለም የሚለካው በቁጥር ነው ቁጥር ደሞ ማለቂያ የለውም።
በዘመንን ቁጥር ስቃያችን መቅለሉ ሳይሆን መብዛቱስ ቢሆን የሚጨምረው? እውነትስ በነዛ በ ማሳይ ጎሳዎች ላይ ጣትህን ቀስረህ ለመሳለቅ ምን አቅም አለህ? የሰው ልጅ እነሱ ከሚኖሩት ኑሮ ለህይወቱ ባያስፈልጉትስ? አሁን ያለን ነገር የሰበሰብነው ያካበትነው ምን ያክሉ ለመኖራችን የግዴታ አስፈላጊ ነው? ሰው ከበላ ከጠጣ ተኝቶ ከተነሳ ከዚህ ሌላ አሁን ያለንበት የህይወት አዙሪት ትርኪ ምርኪ ቢሆንስ? ምናልባት እነዚህን የቡሽሜን ጎሳዎች በብዙ ዘመን ጥለናቸው እንደሄድን እና እነሱ ኋላ ቀር እንደሆኑ ብናስብም እነሱ የሚኖሩበትን የደስተኛ ህይወት ግን በዚህ ሁሉ መዘመን ውስጥ ጥቂቷን እያገኘነው አይመስለኝም።
እንደ ቡሽሜን ጎሳዎች እያደኑ መብላት ከዛም የሳር ጎጆህ ካልደረስክ በመሸብህ ቦታ እሳትህን አንድደህ ለጥ ማለት ጉብልህን እቅፍ አድርገህ ከልብህ መኖር የህይወት ከንቱነት የለ ኮተት የለ በቃ እስክትሞት መኖር ቀንህ ሲመጣ ከወዲያኛው አለም መሻገር አበቃ። ታዲያ እኛ ነን ወደነሱ መመለስ ያለብን ወይስ እነሱንም የኛን ህይወት አቅምሰን ንፅህናቸውን እንንጠቃቸው? የሚለውን ለዘመነኛው ሰው መጠየቅ እሻለሁ

❤🔥10👍3👌1
እስቲ የታዘብኩትን ጀባ ልበላችሁ። ከሀገረ ዝዋይ ወደ ሀገረ ሀረር ጉዞዬን ለመጀመር የሰዓታት ልዩነት ነበር የቀረኝ። አንበሳው ተብሎ ከሚጠራው ሆቴል አጠገብ ቡናዬን እየጠጣሁ ነበር። ከዚህ ሆቴል ፊት ለፊት አደባባይ መሳይ ሰፊ ስፍራ አለ።
በዚህ ስፍራ ላይ በቀኝ በኩል የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ትልቅ ሞንታርቦ ከበው "እየሱስ ጌታ ነው" እያሉ እየተቀባበሉ በስሜታዊነት ይጮሀሉ። ከእነሱ በስተ ግራ በኩል ደግሞ የቀን ሰራተኞች መጥቶ የሚወስዳቸውን መኪና ጥበቃ ሰብሰብ ብለው ቆመዋል። አከባቢው በቆንጆ ህብር የተዋቀረ በመሰለበት በዚህ ቅፅበት ታዲያ የቀን ሰራተኞቹ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው " አላህ ወክበር" ብለው መጮህ ጀመሩ። አከባቢው በድንገት የሆነ ሰላምን በሚነሳ ጭንቅንቅ ውስጥ ገባ።
የገረመኝ ይሄ አልነበረም። የቀን ሰራተኞቹ የእስልምና እምነት ተከታይ ቢሆኑ ነገሩን ዝም ብሎ ማለፍ በተቻለ ነበር፤ ነገር ግን በውስጡ ብዙ አይነት እምነት ተከታዮች ነበሩ። ጉዳዩ የራስን ሀይማኖት ህልውና ማስጠበቅ አልነበረም፤ በቃ በውስጣችን ተዘርቶ ያለው 'የቲፎዞ' ስሜት ነበር ነገሩን የደበላለቀው።
በነገሩ ግራ የተጋቡት ሞንታርቦ ከባቢዎች ለጥቂት ቅፅበታት በዝምታ ተዋጡ፤ የነሱ ዝምታም ለእንጀራ ጉዳይ መቆፈሪያ የያዙትን ዝም አሰኛቸው። ከዚያም በነገሩ የተግባቡ ይመስል ሁለቱም አካላት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው መፈክራቸውን ማሰማት ቀጠሉ።
በዚህ መሀል የተመቻቸ ቦታ ላይ ሆኜ የሀገሬን ህዝቦች እርስ በእርስ እየተከፋፈሉ በየምክንያቱ ለመናቆር ያላቸውን ዝንባሌ ስመለከት ከውስጤ አንዳች የሚረብሽ ነገር ተሰማኝ። አሁን ባለው ዝንባሌ የሚቀር የማይመስለው የሀይማኖት ግጭት በሀገሬ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ውድመት ሳስበው ቀፈፈኝ።
ለማንኛውም፤ ከእርስ በእርስ ጦርነት አርፋ ለማታውቀው ሀገሬና የሀገሬ ልጆች "ቺርስ" እላለሁ፤ ቡና እየጠጣችሁ።
ዜድ

👍9❤1
ቀለም መጽሔት
ቀለም ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 እትም 3.pdf
እቺን መፅሔት እያነበባችኋት ያው እንደተለመደው አንድ ወግ ፈላስፋው ጋንኤል የምትለው የኔ ናት ነበብ ነበብ አድርጉ በዛውም telegram channel ላይ ተቀላቀሉ።
መቼስ ጊዜው ብዙ ሀሳብ የሚሰርቅበት ጥድፊያ የበዛበት ነው። ከጥድፊያው አረፍ ስትሉ እንዲህ አይነት ፅሑፎችን እያነበባቹህ ዘና በሉ
@ourrthought
መቼስ ጊዜው ብዙ ሀሳብ የሚሰርቅበት ጥድፊያ የበዛበት ነው። ከጥድፊያው አረፍ ስትሉ እንዲህ አይነት ፅሑፎችን እያነበባቹህ ዘና በሉ
@ourrthought
❤7
አልፎ አልፎ ድረሰት ልልቀቅባቹህ ጃል
ድንገት በጨዋታችን መሀል ኮስተር አለና ወደ ሰማይ አንጋጦ በለሆሳስ ማውራት ጀመረ
"ምናልባት.... ከልባችን የምኖዳቸው ሰዎች ቢጠሉንስ?
ምናልባት እንዲኖረን የምንፈልገው ነገር የሚያጠፋን ቢሆንስ?
ምናልባት.... ህይወት ላይ ስኬት ማግኘት ሳይሆን መታገሉ ቢሆንስ?
ምናልባት.... የህይወታችን ትልቁ ስኬት ብለን የምናስበው ነገር ስንደርስበት ተራ ቢሆንብንስ?
ምናልባት.... የምንጠላው ነገር ውስጥ ቢሆንስ ደስታች ያለው?" ብሎ መልስ ፍለጋ አይነት ዘንበል ብሎ አይን አይኔን አተኩሮ ያየኝ ጀመር።
እንጃ......ብቻ ስለነገሮች ከማሰብ ይልቅ እየኖርኩኝ የሚሆነውን ማየት ነው የምመርጠው.....ነገር ሁሉ በጊዜው ውብ ነው ይባል የለ.....የነገውን ነገ ስደርስበት ነው ማወቅን የምሻው.....ብዬው አይኔን አሸሸሁበት
ነገውን እያሰበ ዛሬን ከሚኖር ሰው በላይ ከደስታ የራቀና በጥንቃቄ የተሞላ ስሜት አልባ የለም....ህይወቱ የስሌት ነው....ህይወት ላይ ደግሞ ከስሌት በላይ በስሜት ሲሆን ደስታ ይሰጣል....ከራሴ ጋር ወደ ውስጤ ጠፋሁ.....

❤11👍1
የሰው ልጅ ለ አዕምሮው ማስተዋል ከሌለው
ለልቡ ርህራሄ ከሌለው ሀይማኖት የለውም
ሰው ሲተርፈው ነው ፎቅ የሚሰራው ፈጣሪም ከላይ ይታዘባቹሀል
መንገድ ላይ አንድ የኔ ብጤ ሲናገር ከሰማሁት!
ደራሲዎችሽ ባከኑብሽ ሐገሬ
@ourrthought
ለልቡ ርህራሄ ከሌለው ሀይማኖት የለውም
ሰው ሲተርፈው ነው ፎቅ የሚሰራው ፈጣሪም ከላይ ይታዘባቹሀል
መንገድ ላይ አንድ የኔ ብጤ ሲናገር ከሰማሁት!
ደራሲዎችሽ ባከኑብሽ ሐገሬ
@ourrthought
🔥9❤2👍1
ሐሳቦቻችን
Modern Education As a Pavlov Dog ዛሬ የመጣችልኝን ሀሳብ እዚህችው ጫር ጫር የተደረገች ናት ከተመቸን እንቀጥለዋለን በ ስነ-ልቦናው (psychology) ዘርፍ እስከ ዛሬ ስምምነት ካልተደረሰባቸው ጉዳዮች መካከል ስለ ሰው ልጆች የስብዕና ፀባይዮች (Human behavior) ዋነኛው ነው። የሰው ልጅ የ ፀባዩ ወይም ስብዕናው (personality) ከየት ነው የሚመጣው? የሚለው ዛሬም…
Modern Education As a Pavlov Dog
Operant conditioning
ከዚህ በፊት ከላይ አንድ ሀሳብ ላይ ተጨዋውተን ነበር። Behavioral psychology በሚለው ፅንሰ ሐሳብ ላይ እንዴት የኛን ስነ ባህሪ በዚህ ቲዎሪ ታግዘው ተፅዕኖ እንዳሳደሩብንና ለራሳቸው በሚመቻቸው መንገድ ስነ ልቦናችንን እንደቀረፁህ Pavlov theoryን አንስተን አይተናል። ዛሬ ደሞ ከዚህ የሳይኮሎጂ ጥናት ላይ B.F. Skinner ያደረገውን ምርምር ተመርኩዘን እንዴት የኛን ስነ ልቦና ለመቆጣጠር( shape) ለማድረግ እንደተጠቀሙበት እናያለን።
B.F Skinner እ.ኤ.አ 1904 -1990 የኖረ አሜሪካዊ ሳይኮሎጂስት ነው። ከ pavlov ቀጥሎ የሰው ልጅ ስነ ባህሪው የሚወሰነው ባከባቢው ዙሪያ ባለው መስተጋብር በሚታየው ነው እንጂ በሌሎች ነገሮች አይደለም ብሎ ያምናል። ሳይንስ ውስብስብ የሆነውን የሰውን አዕምሮ ማጥናት አይችልም ለምሳሌ ደብሮኛል ስንል ግለሰባዊ ነው(subjective) ይሄን ደሞ ሰውየው ከሚነግረን ውጪ ማረጋገጥ እንችልም ይልቅስ ባህሪውን(behavior) በማጥናት የሰውን አዕምሮ መመራመር ይቻላል ብሎ ያምናል።
እንደ B.F.Skinner ገለፃ ከሆነ ነፃ ፈቃድ ብሎ ነገር የለም። ሁሉም ነገር ካለፈው ድርጊታችን ጋር የተያያዘ ነው ብሎ ያምናል። አሁን የምታደርገው ነገር ወይ ማድረግ የሚከብድህ ነገር በሙሉ ከዚህ በፊት ለዛ ድርጊት ከ ቤተሰብህ ይሆናል ወይ ከ አከባቢህ የተሰጠህ ምላሽ ላይ የተመሰረተ ነው ብሎ ያብራራል። ለምሳሌ ልጅ ሆነህ ወይም አድገህ መሀል ጣትህን አውጥተህ ስትሳደብ የሆነ ሰው ቢቆነጥጥህ ይሄ ቅጣት (negative punishment) ድርጊቱን ድጋሜ እንዳታደርገው (remove a pleasant behavior) በመሆኑ ጉዳዩን በድጋሜ እናዳታደርገው ያደርግሀል ይላል።
B.F.Skinner behavioral theory የሚከተል በመሆኑ ለዚህ ዘርፍ Reinforcement and Punishment የሚባሉ ለዘርፉ ትልቅ ነገርን ያበረከቱ ጥናቶችን አከናውኗል። ባጭር ባጭሩ ከታች ላስቀምጥላቹህ
Positive reinforcement የሚባለው ጥሩ ነገርን ስታደርጉ ያንን ጥሩ ነገር ደጋግማቹህ እንድታደርጉት የምትገፋፉበት ማበረታቻ ነው። ለምሳሌ እናታቹህ ከቤት አትውጡ ብላቹህ ገበያ ብትሄድ እና ከ ገበያ ስትመለስ እዛው ብታገኛቹህ የምቶዱትን ነገር በሽልማት መልክ ትሰጣቹሀለች ማለት ነው። Add a pleasant stimulus to increase behavior ይለዋል ቢ.ኤፍ
Negative reinforcement የሚባለው ደሞ እንዳታደርጉት የሚፈለገውን ነገር ማድረግ እንዳይኖርባቹህ እና ማድረግ ያለባቹሁን ጥሩ ነገር በደንብ እንድታደርጉ shape የምትደረጉበት መንገድ ነው። ምናልባት Negative reinforcement የሚለውን ስሙን ስታዩ ቅጣት ሊመስላቹህ ይችላል ግን ቅጣት ሳይሆን የምትጠሉትን ነገር እንዳታደርጉት በማድረግ ጥሩ ባህሪያቹሁን እንድትቀጥሉበት የሚያደርግ ነው። እሷም ገበያ ስትሄድ አንተን በዘዴ ለመያዝ ከቤት ካሎጣህ ማታ የምታጥበውን ዕቃ እኔ አጥብልሀለሁ ትልሀለች ማለት ነው። remove an unpleasant stimulus to increase behavior ማለት ነው።
Positive punishment ይሄኛው ደሞ ማድረግ የሌለባቹሁን መጥፎ ባህሪ እንዳታደርጉት የምትቀጡበት መንገድ ነው። ከላይ ባየነው መሰረት ቤቱን ባዶ ቤት ጥለህ ወተህ እየተጫወትክ እናትህ ከገበያ ስትመጣ ውጪ ብታገኝህ ማጠብ የማቶደውን እቃ ቃሳጥብሀለች ማለት ነው። add an unpleasant stimulus to decrease behavior ማለት ነው።
Negative punishment ማለት ደሞ አንተ ቤቱን ጥለህ ወተህ እናትህ ከገበያ ስትመጣ ስታገኝህ ማታ ማታ የምትወደውን የቲቪ ፕሮግራም እንዳታይ መከልከል ወይ ስልክህን ለ 1 ሳምንት መንጠቅ ማለት ነው። ይሄ የምትወደውን ነገር በመቀማት ይሄን ድርጊት ድጋሜ እንዳትደግመው ማድረግ ነው። remove a pleasant stimulus to decrease behavior ይለዋል ቢ.ኤፍ
ታዲያ እንዴት ነው ትምህርት ላይ ወይም ሌላ ቦታ የሚጠቀሙበት? ካልከኝ
ት/ት ቤት የሚሰጥህን የቤት ስራ ሳትሰራ ስትሄድ ያለውን negative punishment ድርጊትህን እንዳታደርገው አንተን ባህሪህን ማስተካከያ መንገድ ነው። ለጎበዙ ተማሪ positive reinforcement ይሰጠዋል ድርጊቱን እንዲቀጥል። ረባሹን ተማሪ ደሞ በተቃራኒው። ይህ በትምህርት ቤት በምታልፍበት እያንዳንዱ ክፍል ላይ ስነ ባህሪህን እያስተካከሉት ነው የሚሄዱት አይምሮም ያለፈውን ቅጣትና ሽልማት ኢ ንቁ የ አዕምሮ ክፍል እያስቀመጠ ጥሩ የተባለውን እየመዘገበ መጥፎ የተባለውን ይጥላል።
በ አንዳንድ እስር ቤቶች መፅሐፍ ማንበብ ከ ፍርድህ ቀን ላይ ያስቀንስልሀል ይሄ ደሞ positive reinforcement ነው። እንዲሁም ጥሩ ነገር በ ማረሚያ ቤት ከሰራህ ስልክ ይፈቀድልሀል ነፃ ጊዜ ይሰጥሀል ይሄ ከላይ ስታየው ቀላል ነው ውስጡ ግን ስነ ባህሪህን መልክ ማስያዣ ነው። በስራ ቦታ የሚሰጥህ ቦነስና የሚቀነስብህ የደሞዝ ቅጣት እያንዳንዱ ነገር ስነ ባህሪህ ላይ ተፅዕኖ አለው።
ለዛ ነው B.F.Skinner የሰው ልጅ ቅሉ አያስታውሰው እንጂ የትኛውም ድርጊቱ ምክንያት አለው። በልጅነቱ ወይም ካደገ በኋላ የሚያሳዩት የሰዎች reinforcement እና punishment ላይ የተመሰረተ እንጂ ሌላ ምክንያት አይደለም ይልሀል። ምናልባት ዛሬ ቆም ብለህ ለምንድነው ይሄን የማደርገው ብለህ እራስህን ብትጠይቅ የኋላ ታሪክህ ላይ ይሄን ድርጊት ስታደርገው ሰዎች የሰጡህ ቀና ምልከታ ላይ የተመሰረተ ነው ወይም ማድረግ የማትፈልገው ነገር ምናልባት ልጅ ሆነህ ቤተሰብህና አከባቢህ በዛ ጉዳይ ላይ ቁንጥጫ አሳርፈውብህ ይሆናል።
የቀሩትን ደሞ የሰው ልጅ ባህሪ ይወስናል የሚሉትን ሌሎቹን ዘርፎች እናያለን

❤8👏3
People buy stories, not just a product
ስለ advertisement ከዚህ በፊት ወደ ሦስት የሚጠጉ article አጋርቻቹሀለሁ። ስለ ማስታወቂያው (advertising) ደጋግሜ የማጋራቹህ ያለምክንያት አይደለም። የሰውን ልጅ አዕምሮ ለመበዝበዝ (manipulate) ለማድረግ አለማችን ላይ በ አሁን ወቅት ትልቁ መንገድ በመሆኑ ነው። ይሄ የማስታወቂያው አለም (advertisement world) የሚጠቀሙት የጭለማውን ስነ ልቦና (dark psychology) በመሆኑ ነው።
የማስታወቂያው አለም (advertisement) ከሚጠቀማቸው dark psychology አንዱ ማህበራዊ ተቀባይነት (social affection) ነው። አንድ ትልቅ ተቋም ከምርቱ ይልቅ በጣም የሚጨነቀው ምርቱን ማስተዋወቁ ላይ ነው። ለዛም ነው people buy stories, not just a product የሚሉት። አንድ እቃ ስትገዛ አንተ ትልቅ ቦታ የምትሰጣቸው ሰዎች ወይ በዛ ያለ ሰው ያንን ምርት ከተጠቀሙት የነሱን ተመሳሳይ እቃ የምትገዛው። ሰዎች ተቀባይነትን ከሰዎች እንፈልጋለን ያንን ተቀባነት ከማህበረሰቡ ለማግኘት ማህበረሰቡ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን ነገር በማድረግ እዛ ቦታ ለመቀመጥ የምንፍጨረጨረው።
የኛን አዕምሮ ከኛ በላይ በጥልቀት የሚያጠኑት እኚህ ትላልቅ ድርጅቶች ከምርት ጥራት በላይ ለምርቱ ትልቅ ታሪክ ለመገንባት የሚፍጨረጨሩት። በማስታወቂያ ላይ ሮናልዶ ሲጠጣ ያየኸውን ለስላሳ አድናቂው ብትሆንም ባትሆንም ያ ሮናልዶ የሚጠጣውን ስጠኝ ትላለህ የምትገዛው ለስላሳውን ሳይሆን ታሪኩን ነው የሚባለው ለዚህ ነው። የሆነ ጊዜ ቱዋላይት ላይ የሰራው አክተር አንድ የሽቶ ማስታወቂያ ይሰራል እና በዛን ሳምንት ያ ሽቶ በሚሊዮን ነው የተሸጠው ለምን? ካልከኝ ታሪክ ገንበተዋላ።
እስኪ ቆም ብለህ አስብ የምትገዛው ምርት የምር ጥራትና ጥንካሬውን አይተህ ነው የምትገዛው? ወይስ ምርቱ የሰራውን የማስታወቂያ ታሪክ ተመስርተህ? ለዛ ነው የሆነ ምርት ሲመጣ በብዙ ብር ከፍሎ ታላቅ አርቲስቶችን እየመረጡ ብራንድ አምባሳደር እየመረጡ ገጭ የሚያደርጉልህ እና አንተም ምርቱን ስትገዛ እንትና የሚያስተዋውቀው እንትና የያዘው እከሌ የሚጠቀመው የምትለው ለምን social affection ነው አዕምሮህ የሚያስበው። የጡት ማያዣ የሚሸጠው ሰውዬ ጡት መያዣውን ከልብሱ ላይ ደርቦ አድርጎ ሲሸጥ ብታየው ልትስቅ ትችላለህ ሴቷ ግን በተቃራኒው በፈገግታ ትቀርበዋለች።
የሆነ ጊዜ ላይ ትዝ ካላቹህ የቲክቶኩ አንድ ብር የሚባለው ወጣት ልጅ ፊቱን ገለጠ በብዙ ብር ማስታወቂያ አሰርተው ፊቱን አሳየ የሚል ነገር በየቦታው ይታይ ነበር። እና የዛኔ አውቀኸውም ይሁን ሳታውቀው ለድርጅቱ ማስታወቂያውን ስታራግብ ነበር ድርጅቱም የምርቱን ታሪክ እየገነባ ነበር። አጀንዳ በሆንክ ቁጥር ወደ ፊት ትመጣለህ ሰው አፍ ላይ ትቀራለህ ለዛ ነው አንድ ብር ፊቱን ማሳየቱ እና ማስታወቂያ መስራቱ ለድርጅቱ ትልቅ ታሪክ የገነባላቸው። የምን ማስታወቂያ ሰራ? ስንት ከፈሉት? ድርጅቱ ምንድነው? እያልክ ሳታውቀው ስትሰራ የነበረው። ለዛ ነው ሉላ ገዙን ebs በቀላሉ ወደ ቦታው ያመጣት ከቂጧ በላይ የኮንዶም ማስታወቂያ መስራቷ ቲቪው ላይ ይበልጥ እንድትመሰጥ የሆነከው።
ምን ልላቹህ ነው። የምትገዛው ከምርቱ በላይ ታሪኩን : ማስታወቂያውን : promotionኑን ነው የምትገዛው እናም ንቁ ሆነህ ጠብቅ የ አዕምሮህን ጓዳ ማን እንደሚበረብረው አይታወቅምና!
@ourrthought
🔥9👏1
ሐሳቦቻችን
Photo
ሰብአዊነት ምን ይሆን?
ምስል ከቃል በላይ ይናገራል እንዲባል አንዳንድ ምስሎች ከ ብዙህ ሺህ ገፆች በላይ ይናገራሉ። በአንድ ፎቶ እድሜ ልካችንን ብንፅፍ ልንገልፀው የማንችለውን ስሜቶች አምቆ የያዙ ናቸው። ከነዛ ውስጥ ይሄ ምስል አንዱ ነው ህፃኑና ጥንባሳው (child vulture) ፎቶ ነው። በሺህ ገፆች ስለ ርሀብ ብትፅፍ ከዚህ ምስል በላይ ልትገልፅ አትችልም።
በርግጥ ይህን ፎት ባየሁ ቁጥር ሰውነት ሰባዊነት የሚሉት ቃላቶች ያቃጭሉብኛል።
እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ march 1994 የ ፎቶግራፍ Pulitzer Prize አዋርድ ላይ አንድ የአለምን ቀልብ የሳበ አንድ ምስል አሸናፊ ሆነ። አሸናፊውም የ ደቡብ አፍሪካው ፎቶ ጋዜጠኛው (photojournalist) Kevin Carter ህፃኑና ጥንባንሳው (child and vulture) የተሰኘው ፎቶግራፉ ነበር።
በ እ.ኤ.አ 1993 በ ሱዳን ውስጥ አለም ቦታ ያልሰጠው ታላቅ እርሀብ ተከሰተ። የርሀቡ ምንጭ ድርቅና የርስ በርስ ግጭት ነበር። ሱዳን ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ ታጣ አቅም ያለው ከ ሱዳን ሸሸ አቅም የሌለው በቤቱ ውስጥ በርሀብ አለቁ። ከነዛ ውስጥ በ kecin carter የ ፎቶግራፍ ውስጥ የሚታየው ህፃኑ Kong Nyong ነው። በርሀቡና በርስ በርስ ጦርነቱ ሱዳን ውስጥ ከመቶ ሺዎች በላይ ለሞት ተዳርገዋል።
የጊዜውን ሁኔታ ለመዘገብ kevin carter እና ጓደኞቹ ሁኔታውን ለመዘገብና የጦርነቱንና የርሀቡን ስር መስደድ ለመዘገብ በነፃ አገልጋይነት ወደ sudan ከተሙ። እሱና ጓደኞቹም እየተዟዟሩ ነገሩን መዘገበሰና መረጃ መሰብሰብ ጀመሩ። ያኔ ነው kevin Ayod ወደሚባለው የሱዳን መንደር የዘለቀው የዛኔ Kong Nyong በርዛት ዝሎ ብቻውን መሬት ላይ ተቀምጦ በመሞትና በመኖር መሀል እያለ ከጀርባው አንድ ጥንባንሳ እሱን ለመብላት አሰፍስፎ የደረሰ። ኬቭን ነገሩን እንደቀልድ አላየውም ከየትኛውም ፎቶዎቹ በላይ ይሄ ፎቶ ርሀቡን እንደሚያሳይለት በመተማመን ካሜራውን ደቅኖ ፎቶዎቹን ማንሳቱን ቀጠለ።
የተረጋገጠ መረጃ ባይኖርም kevin ወደ 20 ደቂቃ ገደማ ትክክለኛ የምትባለዋን ጊዜ ተጠባብቋል (the right time) የሚባለውን። ኬቨን ጥንባንሳው ክንፎቹን ዘርግቶ ህፃኑን እስኪቀርበው ጠበቀ ግን ጥንባንሳው ክንፎቹን ሳይዘረጋ እርሀቡን በ ህፃኑ ኒዮንግ ለማስታገስ አድፍጦ ቆየ። kevin ከ ሃያ ደቂቃዎች ቆይታ በኋላ ያሰበውን ፎቶ ባያነሳም ጥሩ እርሀቡን የሚገልፁለትን ፎቶ ካነሳ በኋላ ጥንባንሳውን ከህፃኑ አባሮለት ከአንድ ዛፍ ጥላ ስር በሁኔታው ተረብሾ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።
እ.ኤ.አ 1994 ለ ፑልቲዘር አዋርድ እጩ ሆኖ በውድድሩ አሸናፊ ሆነበት። ይሄን ፎቶ ያዩ ብዙ እርዳታ ድርጅቶች ድጋፎቻቸውን ይዘው በሱዳን ከተሙ አለም በዚህች kevin ፎቶ ትኩረቱን ለ ሱዳን እርሀብ አደረገ። ግን አንድ ጥያቄ ተከትሎ መነሳት ጀመረ kevin ለዛ ምስኪን ህፃን ምን አደረክለት? መገብከው? ወደ እርዳታ ድርጅቶች አደረስከው? የሚሉ የህሊና ጥያቄዎችን ወረወሩበት ኬቨን ግን ምን አላደረገለትም ነበርና ጥያቄያቸውን በዝምታ አለፈ። ግን ለራሱ ይሄን ጥያቄ ሊያልፈው አልቻለም። አንዲት ጋዜጠኛ ሁለት ጥንባሳዎች ይታዩኛል አለችው። kevin አልተከራከራትም ከራሱ ህሊና ግን እርቅ መፍጠር አቃተው። በሱ ፎቶ ምክንያት ብዙ የሱዳን ህፃናት ከርሀብ ቢድኑም ብዙዎች ከሞት ቢተርፉም የ አንድ ህፃን ልጅ ነብስ ግን ፋታ ነሳችው። የሞቱም መንስኤው ሆነች ፀፀት ጥፋተኝነት ጭንቀት ለቀቀችበት። kevin እስከወዲያኛው ይሄን የህሊና ወቀሳ የሚያመልጥበት ነገር አሰበ እራሱንም በ ጆሀንስበርግ እ.ኤ.አ ደቡብ አፍሪካ ላይ 1994 አጠፋ።
በርግጥም የሰው ልጅ ከህሊና ወቀሳ ሊያመልጥ ይችል ይሆን? የሚለውን የሚያሳይ ይመስለኛል። እንዲህ አይነቶቹን ነገር ሳጤን የሰው ልጅ የህግ ልቦናው በተፈጥሮ አብሮት የሚመጣና ለጥፋቶቹም የሚወቅሰው ብትር ነው ያስብለኛል። ምናልባል ከ ስራ ስነ ምግባር አንፃር ከታየ kevin ስራውን ከሚጠበቅበት በላይ ሰርቷል ሁኔታውን ዘግቦ ለ አለም አሳውቋል ዛሬም ድረስ የማይረሳ ምስል ከሳች እና የጦርነትና የርሀብን ክፋት የሚገልፅ ስራ ትቶልናል። ግን ደግሞ ከሰውነትና ከህሊና ወቀሳ አንፃር ካየነውስ የሚለውን ለናንተ ትቼዋለሁ።
መንገድ ላይ አልፈናቸው የምንሄደው አዛውንት የኔ ብጤዎች የሚፈጥሩብንን የህሊና ወቀሳ በምን ይሆን እያመለጥነው ያለነው? የህፃናቱን የዳቦ ግዛልኝ ጉትጎታ? ቀኑን ሙሉ አልበላሁም የሚለው ልጅ ያዘለ አባት? በርግን አልፈናቸው ወደ ቤታችን ገብተን ይሆናል ግን በሰላም እየተኛን መሆናችንን ከኛ በቀር ማን ያውቀዋል?
@ourrthought
👍10😢2💯1
ትንሽ የማውቃቸው መልካም ሰዎች አሉ። ያስተማሩትን የሚኖሩ : የሚኖሩትን የሰበኩ።
ሰውነት ይቀድማል!
‹‹ሰው ሁኑ! ቅድሚያ ሰውነት ይቀድማል!
ከሐይማኖት ሰውነት ይቀድማል! ከዘርም ሰውነት ይቅደም!
አላህ ሰውን ከሁሉ በላይ አልቆታል::
ሰው ሊገፋ፣ ሊሰደድ፣ ሊገደል፣ ሊናቅ፣ ሊወገዝ በፍፁም አይገባም:: ልዩ ፍጥረቴን ክብሩን ጠብቁ ይላል"
ያሚያምኑት አምላክ ነብሳቸውን ይቀበላቸው!
@ourrthought
❤16😢4
ላምጪው እንዲከፈል ሕግ ያስገድዳል (payable to the bearer on demand)
@ourrthought
ይህ ፅሑፍ ማንኛውም ብር ላይ ያለ ፅሑፍ ነው። ትርጉሙ በያዝከው የብር ኖት ገንዘቡን የሚመጥን አገልግሎት የማግኘት መብቱ አለህ ማለት ነው። ለምሳሌ የ 10 ብር ኖት ይዘህ የ 10 ብር አገልግሎት የማግኘት መፍቱ አለህ እንደማለት ነው። ላምጪው የሚለው ቃል የሚወክለው ገንዘቡን በ እጁ የያዘውን ግለሰብ ነው።
ይሄ ሕግ አለም ላይ የትም ቦታና ሀይማኖት ላይ ታገኘዋለህ። ካርማ ማለት ያ ነው። የዘራኸውን ታጭዳለህ ለ አለም የሰጠኸውን መልሰኽ ታገኘዋለህ። በ ሀይማኖትም ቢሆን በክርስትናው "ሰው የዘራውን ያንኑ መልሶ ያጭዳል" ይላል። ጥላቻን ከዘራህ ጎተራህ በጥላቻ ይሞላል። የሰጠኸው ይመለስልሀል። ለአለም ምንድነው ይዘህ የምትሄደው? ገንዘብ ላይ ያለው ሕግ ለ አለምም ይሰራልና አለምም የተለየ ዘይቤ የላትም "payable to the bearer on demand" የሚለውን ትተገብረዋለችና።
@ourrthought
👍17❤3
ጊዜው አርአያ ያጣ የሚመስል ዘመን ነው። ምሳሌ የሚሆን ሰው መጠቆም እስኪቸግረን ድረስ አርዐያ ያጣ ዘመን ላይ ያለን ይመስላል። እንደ ሀገር ተስማምተን የምንጠቁማቸው ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው።
የፍቅር የጀግንነት ምሳሌ የምናደርጋቸው ሰዎች ራሱ ጥያቄ ውስጥ ይከታሉ። ባንድ ወቅት ጎፋ ጋር ለ ብዙ አመታት ፍቅረኛውን በመጠበቅ ላይ የሚቆመውን ሰውዬ እንደ አርዐያ አድርገው ሲያነሱት ይገርመኝ ነበር። ዘፈን እስኪሰራለት ድረስ እንደ ትልቅ ምሳሌነት በየሚዲያው ላይ ሲዘግቡት ማየቴ በጊዜው አስገርሞኝ ነበር። እሱ ሰውዬ ከፍቅር ምሳሌነት ከማቅረብ ይልቅ ወደ አዕምሮ ህሙማን አስገብተውት ሊታከም የሚገባው ሰው ነበር መሆን የነበረበት። ሰውዬው ከ እውነታው አለም የተለየና በቁም ቅዠት ውስጥ የገባ በድሮ ሁኔታ የቀረ ሰው ነው። ፍቅረኛው በ አካል እንኳ መጥታ ሊለያት ያልቻለ ሰው ነው። እሱ ያለው አሁን ላይ አይደለም ድሮ ላይ እንደቆመ ነው። አዕምሮው በስርአቱ እያሰበለት ያልሆነን ከ እውነታው የተላቀቀን ሰውዬ ህክምና አግኝቶ እንዲድን ከማስቻል ይልቅ እኛ ግን ያደረግነው ለፍቅር የተከፈለ መስዋትነት ብለን አርዐያ ማድረጋችን ነው። ይሄ የሚያሳየው ምን ያክል ዘመኑ አርዐያ እንዳጣ ነው።
አንድ ሰው የ አዕምሮ ታማሚ ነው ለማለት የሚያስችሉ ነገሮችን የሚያሟላ ሰው ነው። የ አዕምሮ ህመምተኞች ታማሚ የሚያስብላቸው አንዱ ነገር ይህን አለም እውነታውን መረዳት ባለመቻላቸው ነው። በከሚታየው ይልቅ የራሳቸውን ትንሽዬ አለም አዕምሮዋቸው ውስጥ ገንብተው ከ ሚታየው አለም ተነጥለው በራሳቸው አለም መኖራቸው ነው። መንገድ ላይ የምታዩዋቸው የ አዕምሮ ታማሚዎች መንገድ ላይ እያወሩ የሚሄዱት ለዛ ነው። ምንም ባሌለበት ነገሮችን የራሳቸው አዕምሮው ያሳያቸዋል የድሮድምፅ እንዲሰሙ ያደርጋቸዋል። ይሄ በ ሳይንሳዊ ስሙ ስኬዞፎርኒያ የሚባል ችግር ነው። ፍቅሩን በመጠባበቅ ላይ ያለ እውነታውን መቀበል ያቃተው በራሱ አለም (fantasy) ውስጥ የገባ ሰው ነው። ክህደት ውስጥ ያለ (denial) ምስኪን የ አዕምሮ ህመምተኛ ነው።
ጨለምተኛ አይነት እሳቤ ያለኝ ሰው አይደለሁም። ግን ደግሞ በየ ማህበራዊ ሚዲያ ለ አርዐያነት የሚቀርቡ ሰዎችን ስመለከት ትንሽ ግር ስለሚለኝ ነው። አሁን ላይ በ ፌስቡክ ፣ ቲክቶክ የሚወደዱ ሰዎች ተሳዳቢዎችና የሰውን ክብር የሚነኩ ሰዎችን መሆኑ የቱ ጋር ነው የቆምነው የሚለውን የሚያሳይ ነው። በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ብዙ መልካም ሰዎች ፣ ብዙ ባለ አዕምሮ ሰዎች ፣ ብዙ ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎች በየቦታው ድምፅ ሳያሰሙ አሉ። እነሱን ያብዛልን።
@ourrthought
👍10❤1
ሐሳቦቻችን
Photo
ክፉ ሰዎች የሚሸወዱት ትልቁ ነገር ክፉ ለመሆን መልካምነት የተሻለ መንገድ መሆኑ አይገባቸውም። ግራ ያጋባል አይደል አባባሉ። አዎ ልክ ነው ስህተት የለውም አባባሉ። እናንተን ለመጉዳት የሚፈልግ ሰው ከክፋት ይልቅ የበዛ መልካምነት በጣም ቀላሉ ዘዴ ነው። ለምታደርጉት ነገር የበዛ ምስጋና ቢሰጧቹህና ትንሽ ትንሽ ነገር ቢቦጭቁላቹህ ምቾት እንዲሰማቹሁ ቢያደርጓቹህ አለቀላቹህ።
ከዛሬ 8 እና 9 አመት አከባቢ ርዕሱሡን የማላስታውሰው የ ኦሾ መፅሐፍ ላይ አንድ የሚገርመኝ አሀሳብ ነበር። በጊዜው ሳነበው ይሄማ የሌለ የማይመስል ነገር ነው ብዬ ነበር ያለፍኩት። ቃል በቃል ባላስታውሰውም ሀሳቡን ልንገራቹህ " ህይወትህ ላይ ክፉ ከሚሆኑብህ ሰዎች በላይ ሲበዛ መልካም የሚሆኑልህ ሰዎች ይጎዱሀል" አይነት ሀሳብ ነው።
ሀሳቡን ከላይ ስታየው ቀላል ቢመስልም ትልቅ እውነትነት ያለው ነው። ነፃነትህ ያለው ጥሩ የሚያደርግልህ ሰውዬ ጋር ነው ወይስ ክፉ የሚያደርግብህ ጋር ? ብትባል የት ነው የምትለው? መልካም ከሚያደርግልህ ሰው በላይ በውለታው አስሮ ያስቀመጠህ ከወዴት ይገኛል? ክፉ ናቸው የምትላቸው ሰዎች እንኳን እንዲህ በክፋታቸው ተብትበው አልያዙህም። ህይወታችን ላይ ይበልጥ አስረው የሚያስቀምጡን መጥፎ ከሚያደርጉብን በላይ አለቅጥ መልካም የሚሆኑልን ሰዎች ናቸው። በውለታቸው ተብትበው አስረውህ ሁል ጊዜ በነሱ ታስረህ እንደኖርክ ነው። ግንኙነቱን እንኳ ጥለህ እንዳትሄድ መልካምነታቸውን ያደረጉልህን ነገር እያሰብክ እየተጎዳህ መኖርን ትመርጣለህ። ክፉ አለቃ ካለህ ስራህን ለመልቀቅ እና አማራጭ ለመፈለግ አታመነታም። በጣም መልካምነቱ የበዛ አለቃ ቢኖርህ ግን ያደረገልህን ነገር እያሰብክ ውለታውን እየቆጠርክ እየተጎዳህ መስራትን ትሻለህ።
በረከት በላይነህ ጥሩ አከራይ ያለው ሰው መቼም ቢሆን ቤት አይሰራም ይላል። ምቾቱ ሌላ አማራጭ እንድትፈልግ አያደርግህም ሁሌም ተዘናንተህ እንደተቀመጥክ ነው። ጨቅጫቃ አከራይ ሲኖርህ ግን የራስህን ቤት እንዴት መስራት እንዳለብህ ያሳስብሀል። እስከ መቼ እንዲህ ኖራለሁ ትላለህ። አንስታይን ይመስለኛል "ህይወቴ ላይ እሺ ካሉኝ ሰዎች ይልቅ አይሆንም ያሉኝ ሰዎች ባለውለታዬ ናቸው። ነገሮችን በራሴ እንዳደርጋቸው አድርገውኛል" ይላል። የከፉብህን ሰዎች ብታስብ ህይወትህ ላይ ትልቁን ነገር ያደረጉልህ እነሱ መሆናቸውን ትረዳለህ። የኩረጃ ዘዴ እንደሌለ ያወክ ቀን ለማንበብ መነሳትህ አይቀርም።
ቁራ ልጆቿ ከ እንቁላል ከተፈለፈሉላት በኋላ ከመኝታቸው ከላባ ጉዝጓዝ ስር እሾህ ታስቀምጣለች። ይሄን የምታደርገው ልጆቿ በላባው ሙቀትና ልስላሴ ተመስጠው መብረር እንዳይረሱ ነው። ምቾት ካለ ለምን ይበራሉ? ቀስ ቀስ እያለች ላባውን ታነሳባቸውና በመጨረሻ እሾሁን ታስቀርባቸዋለች የዛኔ እሾሁ ሲወጋቸው እሱን ሽሽት ይበራሉ። ህይወትህ ላይ የበዛ መልካምነት ያላቸው ሰዎች ከላባው ልስላሴ እና ሙቀት ነው የሚሰጡህ። እሾሁን የሚሰጡህ ሰዎች ክፉዎቹ ናቸው እነሱም እንድትበር ያደረጉህ ናቸው። ዙሪያህን ተመልከት ይበልጥ አሳስሮ ያስቀመጠህ ማን ነው? ውለታቸው እንዳለብህ እያሰብክ የምትኖረው እነማንን ነው? ነገሮችን ያለህበትን ቦታ ትተህ እንዳትሄድ ያሰረህ ማን ነው? መልካም ሰዎቼ የምትላቸው አይደሉምን? አንዴ ሞክረህ ያቃተህን ነገር የሚሰሩልህ ሰዎች ጥሩ እንደሆኑልህ የምታስብ ከሆነ ይመችህ ይልቅስ በራስህ ሰርተህ እንዳትሞክረው ያደረጉህ ያለመቻልህ ተምሳሌት ሊሆኑም እንደሚችሉ ማሰብ ተገቢ ነው።
ዙሪያችን ላይ ለነበሩና ላሉ ክፉ ሰዎች ችርስ ምንም ነገር የማድረግ ነፃነታችን እና የ ችሎታዎቻችን ማሳያዎቻችን ናቹህና!

❤9