ሐሳቦቻችን
981 subscribers
103 photos
4 videos
5 files
2 links
በዚ ቻናል ላይ የተለያዩ ሀሳቦቻችንን ፣ ምልከታዎቻችንን ፣ ትዝብታችንን ፣ ከተለያዩ መልኮች እያነሳን እንወያያለን!

ሀሳብና አስተያየት ካላቹ @haileabb
Download Telegram
"ሰው ነው ብለሽ አስቢ "

"ማንን "

"እሱን"

"ማለት"

"በቃ ምንም ብታፈቅሪው ምንም ያክል ብታምኚው.... ሰው ነው ብለሽ አስቢ....... እንዳሰብሽው ባይሆን እና ስህተት ቢሰራ ህመምሽን ምትቋቋሚበት ትንሽ ጥንካሬ ለራስሽ አስቀምጪ ......ለሱ ካለሽ ፍቅር እና እምነት ትንሽ ለራስሽም አስቀሪ.... ሰው ነው ብለሽ አስቢ.... በፍቅርሽ እና በእምነትሽ ልክ ፍፁም አታድርጊው ጥንካሬ እንዲሆንሽ ለራስሽም የመፅናኛ ቃል አስቀምጪ ሰው ነው ብለሽ አስቢ .....

"ሰው ነው"
15
"አንቺ አለም አንቺ አለም የጀመረሽ እንጂ የጨረሰሽ የለም እንዲሉ"

አፀናፈ አለሙ ወሰን አልባ ነው። የኛም የህይወት ሩጫችን በዚህች አለም ውስጥ ለማይሞላ ኑሮ መንከላወስ ይመስል ከትርምሱ የሚያወጣን አጥተን ስንቃትት እንኖርና እንደዘበት እናልፋለን። ግን አለምን ደሞ የጨረሰ ሰው ባይኖርም በስነ-ጥበብ መነፅር ካለንበት አንዲት ክፍል ያላየነውን ያየነው እስኪመስለን ድረስ በምሳጤ ያስደቃኘናል። ከጫጫታው አለም መንጭቆ ገለል ያደርገናል ሠላም ይሰጠናል።

ሲሲፈስ የተባለ የግሪክ ንጉስ ባንድ ወቅት የሰውን ልጆች ሞት ሲፈጅ ፣ እንደው ያለምህረት በደስታ የሚኖሩትን ሰዎች እንዲያው እንደዘበት ሲቀጥፋቸው ፣ ያለርህራሄ የማሰቢያ ጊዜ ሳይሰጣቸው ያለ ቀጠሮ ሲያሰናብታቸው ፣ እቅዳቸውን የማጠናቀቂያ ማሰቢያ ጊዜ ሳይሰጥ ህይወታቸውን ሲነጥቅ ቢያይ ጊዜ ልቡ ትክዝ ብሎ እንደው ለነዚህ ምድራዊ የሰው ልጅ ፍጡራኖች ይሄን ሞት ባስርላቸው ደስታቸው ሙሉ ሆኖኮ ፍስሀ ይሆናሉ ብሎ አሰበ። እንደው ሲሲፈስ ልበ ሩሁሩህ ነውና : አማልክቱ ሳይሰሙ በድብቅ ያን አረመኔ ሞት ያዝ አድርጎ በሰንሰለት እስር ነዋ። ይሄኔ ሰዎች ፈነጩ ደስታቸው ማባሪያ አጣ። አማልክቱ ሲሲፈስ ሞትን በሰንሰለት ማሰሩንና ሰው ዘላለማዊ መሆኑን ቢያዩ ጊዜ ቁጣቸው ነደደ : ሞትን ከታሰረበት ሰንሰለት ፈተው ለቀቁ : ይሄን ጥፋት ያጠፋው ያ አረመኔ ሲስፈስን ምን እናድርገው ይሆን? ብለው አውጥተው አውርደው በመጨረሻ አንድ ሀሳብ አሰቡ ምን አትሉም? አንድ ግዙፍ ድንጋይ እያንከባለለ ለዘላለም ይኑር ብለው ወሰኑበት። ታዲያ ያ ግዙፉን ድንጋይ ወደ ተራራ አናት ይወስደዋል ድንጋዩ ልክ ተራራው ጫፍ ሲደርስ ወደ ታራራው ስር ይመለሳል ሲሲፈስም መልሶ ገፍቶ ጫፍ ያደርሰዋል መልሶ ይመለሳል ይሄ ታዲያ የዘላለም ቅጣቱ ነው።

ሲሲፈስ ይሄ ዘላለማዊ ቅጣቱ እንደሆነ ቢያውቅም ለሰው የከፈለው መስዋዕትነት ነውና ፈገግ ብሎ ለ አማልክቱ እያሳየ ያን ድንጋይ በደስታ ይገፋል። አማልክቱ በቅጣቱ እንደዛ መደሰቱን ሲያዩ ምን ብለው ይሆን? ፈገግታውንም እንንጠቀው? ብለውም አስበውም ይሆናል። መቼስ ቅጣታቸው ሲባክን ከማየት በላይ ምን ሊያስከፋቸው ይችላል ብላቹሁ። ታዲያ ሲሲፈስ አያስገርማቹሁም? እንዴት ብሎ ያን ዘላለማዊ ቅጣት በሳቅ ተቀበለው? የሚያልቅ ቅጣትስ ቢሆን ይሁን ግን ዘለአለም በሙሉ ያን ቅጣት እየሳቁ መቀበል አይደንቅም?

የኛስ ህይወት ከሲሲፈስ ህይወት በምን ይለያል? እንዲል አልበርት ካሙ ህይወት የማይሞላ ስልቻና የድግምግሞሽ አባዜ ነው። ዘፋኙም እንዳለው "አምላክ ስለሰራት ምድርን በክብነት : ዞሮ አይመጣ የለም ወደነበረበት" እንዲል : ህይትን ደጋግሞ መኖር ምስኪኑ የሰው ልጅ የማያመልጠው እጣው ነው። ግን ከዚህ አባዜ ወጥተን በምናብ አዲስ አለም የምንገባበት አንድ ነገር ያለ ይመስለኛል ምን ብትሉኝ ስነ-ጥበብ ነው። ልክ እንደሲሲፈስ በዚች አታካች አለም ላይ የህይወትን ድንጋይ በፈገግታ እንገፋ ዘንድ ብርታት የሚሆነን ማን እንደ ስነ-ጥበብ አለ። ኑሮ ድክም አድርጎን በቴያትር እርፍ ለማለት ፣ ደሞ ከሩጫው እርፍ ብለን መፅሐፋችንን ክፍት አድርገን የህይወትን ሌላ መልክ ለማየት መታደል ፣ በሙዚቃ ፋታ መውሰድ ፣ በግጥም መደመም ፣ በወግ ለመፈገግ ፣ በፊልም ለንመሰጥ የኑሮን ጣጣ ለትንሽም ጊዜ እናርፍ ዘንድ የህወትን ድንጋይ ሸክም ከጀርባችን አውርደን ህይወት ካዙሪቱ እንድንላቀቅ የምታደርገን ስነ-ጥበብ ናት።

ስንቶች በሙዚቃ እንደሚረጋጉ ፣ በግጥም እንደሚመሰጡ ፣ በቲያትር ሀሴት እንደሚያደርጉ ፣ በውዝዋዜ እንደሚፍታቱ የህይወትን ተለምዷዊ ስሪቱን እንዳመለጡ ድብርት ላይ ፈገግ እንዳሉበት ምስክር አያሻም። ቀለም መፅሔታችንም ከዚህ መታከት ታርፉ ዘንድ አለሁላቹህ ትላለች።

በታሪክ ወደኋላ ልንወስዳቹህ : ደሞም በዝክረ ጠቢባን አምዳችን ጠቢባንን ልናስታውስ : በግጥማችን አድማስን ልንዳስስ : በወጋችን እያስፈገግናቹህ ቁም ነገር እያስጨበጥን ሳቃቹሁን አብረን ልንስቅ : በፊል እንድንደመም : በአጫጭር ታሪኮች አሀ ልንል : ማን ይወደስልዎ ብለን አለም ያላወቃቸውን መልካም ሰዎች በብዕራችን ልናወድስ : ስነ ጥበባዊ ዜናዎችን እያነሳን ከህይወት እርፍ ትሉ ዘንድ ቀለም መፅሔታችን ዘመኑን ዋጅታ አለሁ ትላለች።

ቀለም መፅሔት የመጀመሪያ ዕትማችን ላይ አንባቢዎቻችን የሰጣቹሁን ሀሳብና አስተያየት ለኛ መሰላቸታችንን ፣ መታከታችንን ወዲያ ብለን በጉጉት ይህችን ሁለተኛ አምዳችንን ለማሰናዳት ትልቅ ብርታት ሆኖናል። ደሞም ለቀጣይ እንበረታ ዘንድ የናንተ በጎ አስተያየትና ሀሳብ ልክ እንደሲሲፈስ ጥንካሬ ይሆነናልና ሀሳባቹህ አይለየን እንላለን።

መቼስ ሰው ሲኖር የሚታወሰው በህይወት ሳለ ሰርቶ ባለፈው ነውና ነገ ላይ እነ እከሌ እኮ ኖረው ነበር ብቻ ከመባል ይሄን ሰርተው ነበር የምንባልባት አሻራችንን የምናሳርፍባት ናት። ታዲያ ነገ ላይ የህይወትን ታካችነት በምን አመለጣቹህ? ቢሉን በስነ-ጥበብ ለማለት : ለሌላውስ ምን አደረጋቹህ ቢሉን ቀለም መፅሔታችንን ልንተርክ : እንዴትስ ለሱ አልሰለቻቹሁ ቢሉን በአንባቢዎቻችን አበረታችን ለማለት ቀለምን እነሆ በረከት እንላለን።


ቅፅ አንድ ቁጥር ሁለት ከመግቢያ ላይ የተወሰደ


@Kelemofficial
👍52
AI the new form of western colonial exploitation

ሰሞኑን የዮናስ ጎርፌን podcast ስመለከት አንድ በጣም ድንቅ ትንተና በ AI ዙሪያ ተመለከትኩኝ

ምዕራባውያኑ ከጥንት ጀምሮ የ አፍሪካን ሀብት ለመቀራመት ሲያቅዱ እንዲው በዘፈቀደ አይደለም በደንብ አጥንተውን ነው። እኛ የባሪያ ንግድ ላይ እንዳለን እነሱ በ ሀይማኖቱ በኩል ሊበዘብዙን ከች ብለው ነበር። ሀይማኖቱ ላይ ልንባንን አከባቢ ደሞ ዘዴ ቀይረው በድህረ ዘመናዊ በኩል ብቅ አሉ። አሁን ደሞ እኛ በ ዲፕሎማሲ በኩል ወዳጅ ሀገር መስለው እየበዘበዙን : በፖሊሲያችን ውስጥ ገብተው በ እርዳታ መልክ መበዝበዝ ላይ መሆናቸውን ነቃ እንዳልን እነሱ ሌላ መላ ዘይደው በ AI ከች ብለዋል እኛ ግን ገና ነገሩ የተገለጠልን አይመስልም እንዳንቀላፋን አለን።

Digital Colonialism አዲሱ አፍሪካን በባርነት የሚደፍቁበት መሳሪያቸውን ይዘው ደጃፋችን ላይ አሸሼ ገዳሜ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። እንዴት ካልከኝ ወንድም አለም ከ ከላይ ከነገርኳቹህ podcast ላይ እየቀነጨብን እንመልከት።

Biometric voting system የሚባለው በ AI የታገዘው የምርጫ ሂደት በ ጎረቤታችን ኬንያ እና ጋና አካሂደዋል። ይሄ የምርጫ ዘዴ የመራጩን ፊት ወይም የጣት አሻራ ወይም ድምፅ በመጠቀም የሚካሄድ አንድ ሰው ከአንድ ጊዜ በላይ እንዳይመርጥ የሚቆጣጠር ማን ምን እንደመረጠ መቼ እንደመረጠ ምርጫ ጣቢያውን ሁሉንም መረጃ ይሰበስባል። እንዲሁም ስንት የምርጫ ኮረጆ እንዳለ የትኛው ውስጥ ስንት የካርድ ብዛት እንደተጣለ የወንድ የሴት ብዛት ምን ይሄ ብቻ የሞተ ሰው መታወቂያ ወስደህ ወይም እዛ አከባቢ የማይኖር ሰው ቢመርጥ በቀላሉ ይነግርሀል። ይሄ ታዲያ ችግሩ ምንድነው? ብትሉ ይሄን ሰርቨር የሚቆጣጠሩት ምዕራባውያኑ እና እነ ቻይና ናቸው። ሁሉ በጄ በደጄ በሆነላቸው መረጃ መሰረት የሚፈልጉትን የ አሻንጉሊት መሪ የማስቀመጥ እድላቸው ሰፊና አስጊ ነው። ከዛ በላይ ከምርጫ በኋላ እኚ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች ያልመረጣቸውን ሰው በቀላሉ ለይተው ለማጥቃት ይረዳቸዋል።

ዮናስ ሲተነትንም አፍሪካ በቅርቡ የህዝብ ብዛቷን : የፆታውን ልዩነት : የየ ሀይማኖቱን ብዛትና ተከታይ ቁጥር : ውልደትና ሞት : ስራ አጥ : ሽማግሌ ህፃን ወጣት : እንዲሁም የምንጋደልበት የመሳሪያ ብዛት ከነ ቀልሀው ጭምር በዚህ AI በመታገዝ መረጃ ለመሸመት ጫፍ ላይ ናት። ችግሩ የሚመጣው እዚህ ጋር ነው ይሄን መረጃ ከምዕራባውያኑ እጅ ስንሸምት የምናወጣውን የገንዘብ ብዛት አስቡት። መረጃው በእጃቸው ያለ በመሆኑ ዳግም የነሱን ደጅ ማንኳኳት የማይቀርልን መራር እውነት ነው። ያ ደሞ እጅ አዙር የከፋው ባርነት ነው።

AI በ ጤና : በሳይንስበ : በ አርት : በ ግብርና : ፖለቲካ : በሚሊትሪ : በት/ት ምኑ ቅጡ የማይገባበት ቀዳዳ የለም። አለም የነበራትን አዝጋሚ ለውጥና የመረጃ ስርጭት መጠን የሚቀይር ነው። አፍሪካ በ 2025 ከዚህ ከቴክኖሎጂው ዘርፍ ከ 185 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ እንደሚኖራት ይገመታል። በዚህ የመረጃ ፍጥነት ውስጥ አብሮ አብሮ ያልተጓዘ መጨረሻው ወደ ኋላ መቅረት ነው።

አሁን ላይ AI ቴክኖሎጂው የደረሰበት የስልጣኔ ደረጃ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ መሻሻል ነው። ለምሳሌ በጤናው ዘርፍ አንድ እናት ልጇ ሳይወለድ ማህፀን ውስጥ እያለ ያለበትን የ ህመም አይነት እንዲሁም ምን ቢደረግ እንደሚድን ይነግራታል። አንድ የ ኦቲዝም ተጠቂ ልጅ ፀንሳ ቢሆን ከመወለዱ በፊት ልጁ የሚያስፈልጉትን የህክምና አይነት በመዘርዘር ሲወለድ ጤነኛ ልጅ ይወለዳል ይሄ ደሞ ታላቅ ፍስሀ ነው። አንተ ራሱ የታመምከውን እና እንዴት እንደምትድን በቀላሉ ይነግርሀል ግን ደግሞ በያ ዳላር ግድ ነው።

በግብርናውም ዘርፍ ካየነው ሰብሉ መቼ ቢታጨድ መቼ ቢሰበሰብ ምን በሽታ እንዳጠቃው ወደፊት ሊያጠቁት የሚችሉትን የበሽታ አይነት እንዲሁም የገበያውን ሁኔታ ሳይቀር በቀላሉ በስማርት ስልኩ በ ሰከንድ ውስጥ ይነግረዋል። ከዛም በተጨማሪ እዛ ቦታ ላይ ምን ቢተክልና እንደሚያዋጣው እና ቢዘራ እንደሚያተርፍ ከነ ኪሳራው በቀላሉ ያብራራለታል። ወዳጄ በ እያንዳንዱ ጉዳይ የሚሰጥህን ማብራሪያ እና ዳታ አንተ ዘመንህን ሙሉ ብትለፋ የማታውቀውን መረጃ ነው። ግን ለዚህ መረጃ ደሞ ቀርሺ ግድ ነው። ጨላ ካለ ከ AI መረጃ አለ ነው ጉዳዩ ባባዬ። ዳታንም በ እርዳታ መጠበቅ ሼም ነው አፍንጫህን ላስ ይሉሀል።

ሌላው ትልቁ ፈተና የሚገጥማት ከ ሀይማኖት መሪዎቿ ነው። ይሄን የ AI ዘመን ሰራሽ ቴክኖሎጂ የሚሰራውን ስራ ሲመለከቱ ከመጨረሻው ዘመን ጋር ጥቅስ እያጣቀሱ ከጉዳዩ መሸሽ እኛ አፍሪካውያን ስራችን አድርገነዋል።

የዲጅታል ፖስፖርት ግብይት : ያለ ገንዘብ ግብይት ሲፈፀም እንዲሁም የተለያዩ የ AI ቴክኖሎጂ የ አፍሪካ ህዝቦች ሲመለከቱ የ 666 ስራ የዘመን መጨረሻ በማለት ከጉዳዩ ገሸሽ እንዲሉ በየ ቤተ እምነቱ ሲሰበክ እየዋለ ይገኛል። እኛ ሀገር ሲኒማ ሲመጣ የሴጣን ቤት : እህል ወፍጮ ሲፈጭ ሰላቢ በላው: ውሀ በቧንቧ ሲመጣ ሴጣን ሽቅብ ሳበው: መኪና ሲመጣ የሴጣን ኩርኩር: ፎቶ ካሜራ ሲመጣ አጋንንት ስራ ማለት የጥንት ልምዳችን ነው። በ 1970ዎቹ እና 80 ዎቹ ኮምፒዩተር ወደ ሀገራችን ሲገባ አብዛኛው የፕሮቴስታንት መድረክ ይሄን የ አጋንንት ስራ ሲቃወሙ እና ሲፀልዩ እንደነበር በዚህ podcast ላይ ይዳስስልናል። እንደውም የሆነ የሀዋሳ ቸርች ውስጥ ኮንፈረንስ ተዘጋጅቶ ይሄን የሴጣን ስራና ሀሰተኛው መሲህ ተንኮል ቀኑን ሙሉ ሲቃወሙ ውለዋል። ይሄ ታዲያ ሀገራችን ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ የሚቃወሙት ድርጊት ነው።

ሀገራችን የ ዲጅታል መታወቂያ አሁን መጠቀሟን እንኳ በየ ሀይማኖት ተቋሙ የ 666 ስራ መሆኑን የሚተነትኑ ነበሩ። ይልቅ አፍሪካ የሚያዋጣት ልክ እንደ አንድ የቴክኖሎጂ በረከት ጉዳዩን ቆጥራው ከሀይማኖት አላቃው ጉዳዩ ላይ ካልተሳተፈች ነገ ላይ ስትባንን ጉዳዩ ውስጥ ለመግባት ግመል በመርፌ ቀዳዳ አይነት ዘይቤ ነው። ዘመኑን ዋጂ የሚለውን ቃልም አብሮ ማስታወሱ ጠቃሚ ይመስለኛል።

ታዲያ መፍትሄው ምንድነው? ብትሉ ይሄን የ AI Digital world control system ውስጥ አፍሪካ በራሷ ልጆችና ከራሷ እሴት ጋር የሚቀራረብ system ውስጥ መግባትና መሳተፍ አለባት። ካልሆነ ግን የ AI ቴክኖሎጂ የገንዘብ ማስፋፊያ የሚገኘው ከ ቻይና እና አውሮፓ ቅኝ ገዥዎቻችን ነው። የራስህን መረጃ ሰብስበው ይሸጡልሀል በዛ ላይ ከፈለጉ አዛብተው ይሰጡህና ድጋሜ እናግዝህ ብለው ክቻሳ ይሉልሀል አንተ ኢሉሚናቲ እያልክ 24 ፀልይ። አፍሪካ በራሷ መንገድ የምትቆጣጠረው የ ዲጅታል ዳታ ቋት ያሻታል። የማትቆጣጠርና የዳታው ባለቤት ካልሆነች ግን ከፊታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ትልቁን Digital colonization ባርነት እንቀምሰዋለን። መውጫውም እንደሌሎቹ ቀላል አይሆንም።

link ከታች ኮመት ላይ አስቀምጥላቹሀለሁ ገብታቹህ ሙሉውን ማብራሪያ ስሙት።


@ourrthought
👍73
👏1
የመፅሐፍ ዳሰሳ
ርዕስ : አባቴ ያቺን ሰዐት
የገፅ ብዛት: 415
የህትመት ጊዜ: 2002 ዓ.ም
ይዘት : ደርግ ላይ በ ግምቦት 8 መፈንቅለ መንግስት ታሪክ ላይ የሚያተኩር

‎ ይሄ መፅሐፍ በ ግንቦት 8, 1981 የከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ዙሪያ የሚያጠነጥን ድንቅ መፅሐፍ ሲሆን መፅሐፉን የፃፈው የጀነራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ ደረጄ ደምሴ ከ ልጅነቱ ጀምሮ ከ አባቱ ጋር የተለያዩ ቦታዎችን አብሮ በመዞሩ እንዲሁም በወጣትነት ጊዜው አንዳንድ ከሻቢያ ጋር የተደረጉ ውጊያዎችን በአካል ቦታው ላይ ሆኖ በመታዘቡ መፅሐፉ በቂ መረጃ እንዲኖረው አስችሎታል። የ ግንቦት 8,1981 መፈንቅለ መንግስት እንዴት ሊከሽፍ ቻለ?  ያቀደውስ ማነው?  ምን ያክል ዋጋ ያስከፍላል የሚሉትን የሚዳስስ እንዲሁም ይሄን መፈንቅለ መንግስት በዋናነት ያቀነባበሩት የ ሜ/ጀነራል ደምሴ ቡልቶን የ ምፅዋ ጦርነቶች በመጠኑ የሚያስቃኝ ነው።

‎በመፅሐፉ ውስጥ ጀነራል ደምሴ ቡልቶ ምን ያክል ለሙያቸው ክብር እንዳላቸው ያካበቱትን ብቃት የጦር ሜዳ ጀግንነት እንዲሁም የ አመራር ብልሀት ያትታል። የተወለዱት 1926 ዓ.ም ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት 1981 ድረስ 38 አመታትን በውትድርና አሳልፈዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ የ ኢትዮጵያን አየር ሀይል የደብረዘይትን ያቋቋሙት አብረዋቸው ከተማሩት ጋር በሆመን እሳቸው ናቸው። ኮሪያ ከዘመቱት ውስጥም አንዱ ናቸው። ከ 1950ዎቹ ጀምሮ እስከ 1981 ዓ.ም ያልተዋጉት ጦርነት የለም ማለት ይቻላል። ዘምተውም የተሸነፉበት ቦታ የለም። በርግጥ ጀነራል ደምሴ ቡልቶን የማያደንቅ ማን አለ? መንግስቱ ሀ/ማርያም እንኳ ብቃታቸውን የመሰከሩላቸው ናቸው። በሐረር ጦር የወታደር መምሪያ መምህር በነበሩበት ጊዜ መንግስቱ ሀ/ማርያምንም አስተምረውታል።

‎ደርግ በስልጣን በቆየባቸው የ 17 አመታት የጊዜያዊ ወታደራዊ ዘመነ መንግስት ቆይታ ውስጥ 47 ጀነራሎችን ገድሏል። ይሄ ቁጥር በ 81 መፈንቅለ መንግስት ጊዜ እራሳቸውን ያጠፉትን ጀነራሎች ሳያካትት ነው። ምናልባት ይሄ ቁጥር በሰው ብዛት ካሰላኸው ቀላል ሊመስል ይችላል። ግን ደግሞ በ ሙያዊ ትንተና ካየነው አንድ ሰው ከተራ ወታደርነት እስከ ጀነራልነት እስኪደርስ ድረስ በትንሹ ከ 24-30 አታት ይፈጁበታል። አንዳንዴ 30 አመትም አገልግለው ብቃቱ ከሌላቸው እዛም ላይደርሱ ይችላሉ። እንግዲህ በ ወታደራዊ ሙያቸው 30 አመት ያሳለፉ ጀነራሎችን አጥተናል እንደማለት ነው።

‎ከመፅሐፉ በጣም የገረመኝና ለማመን የከበደኝ አንድ ጉዳይ ነበር። በ ከረን ከ ሻቢያ ጋር በሚዋጉበት ወቅት ትዕዛዝ ለማስተላለፍ በሚሞክሩበት ጊዜ በሞገድ ግጭት ምክንያት የሻቢያና የኢትዮጲያ ሞገድ አንዱ ወደ አንዱ መስመር ይገባል። ይሄ ማለት ለምሳሌ በሬድዮ ግንኙነት ወቅት የኢትዮጲያ መስመር ላይ የሻቢያው መስመር ይገባል እንደማለት ነው። ታዲያ በዚህ ጊዜ የኢትዮጲያ የሬድዮ ሞገድ ሻቢያ ከያዘው በ ሻቢያ የስልክ መስመር በኩል የኢትዮጲያ ወታደሮች እርስ በርስ እንዲገናኙ ይፈቀድላቸዋል ማለት ነው። ሻቢያም መልክት ለማስተላለፍ የሱ መስመር ሞገዱ ቢጋጭበት በ ኢትዮጵያ የስልክ መስመር በኩል ጓዶቹን በመስመር ፈልገው እንዲያገናኙት ይጠይቃል። ታዲያ ይሄ የሚካሄደው እልም ባለ ጦርነት ቀጠና ውስጥ ነው። በጦርነት ውስጥ ቢሆኑም እንኳ አሻፈረኝ በኛ መስመር ያንተን ጓድ አናገናኝም አይሉም ይከባበራሉ በትህትና መስመሩን ፈልገው ያገናኙታል ግሩም ነው በውነቱ።

‎መፈንቅለ መንግስቱ መንግስቱ ሀ/ማርያም ለስብሰባ ወደ ጀርመን ሀገር ለመሄድ ባሰቡበት ወቅት ለማድረግ የታቀደ ነበር። የሚሄዱበት ሄሊኮፍተር ከ ኢትዮጵያ ራዳር ክልል ሳይወጣ በፊት ኤርትራ ላይ ወይ ተመቶ እንዲወድቅ አልያ ተገዶ እንዲያርፍ እና በእስር እንዲቆዩ የታቀደ ነበር። አየር ሀይል ግን መቶ መጣሉን አላመነበትም ነበር። አዲስ አበባ የነበረው የ ግንቦት 8ቱ እቅድ ቢከሽፍም ግንቦት 9 እና 10 ኤርትራ ያለውን 1/2 ጦር ጀነራል ደምሴና ጀነራል ወርቁ እንዲሁም ሌሎችን ጀነራሎች በማሰባሰብ መፈንቅለ መንግስቱን ለመቀጠል ያቀዱ ቢሆንም የ አየር ሀይል ወታደሮች ግን ውስጥ ውስጡን ተነጋግረው የኤርትራውም ሊከሽፍ ችሏል።

‎ መፅሐፉ እንዳተተው ከሆነ በመፈንቅለ መንግስቱ ሌላው ለዚህ መፈንቅለ መንግስት መክሸፍ መፅሐፉ በዋናነት ተጠያቂ ያደረገው አካል በመፈንቅለ መንግስቱ መደረግ ተስማምቶ በመጨረሻ የከዳቸውን ኮ/ ተስፋዬ ወ/ሥላሴንና ጀነራል አበበ አበራ አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው መፈንቅለ መንግስት ጦላይ የነበረውን ሀይል እንዲቀላቀላቸው ትዕዛዝ ሳይሰጥ ጀ/ ሀ/ጊዮርጊስን ገድሎ መጥፋቱን በዋናነት ተጠያቂ ያደርጋል።

‎መፈንቅለ መንግስቱን አብዛኞቹ ከፍተኛ ጀነራሎች ያመኑበት ጉዳይ ቢሆንም እቅዱ በመክሸፉ ግን የ 29 ጀነራሎች ህይወት ለማለፍ ምክንያት ሆኗል ከዛ ውስጥ 21ዱ ከተያዙበት ቦታ በመንግስቱ ትዕዛዝ እንዲገደሉ ሆኗል። በ 15 አመት የሱማሌ የሻቢያ የህወሀት ውጉያ የሞቱ ጀነራሎች ግን ከ 5 አይበልጡም ነበር።

‎ ያ መፈንቅለ መንግስት ባይከሽፍ ኖሮ የሀገራችን አሁናዊ ሁኔታ ምን ይመስል ነበር? የሚለውን ከመፅሐፉ ተነስተን እንመልከት። መፈንቅለ መንግስት በሚካሄድበት ወቅት ጀነራል ደምሴ ቡልቶ ለ ሻቢያ ለ ኢሳያስ አፎርቂ ደውለው የ 15 ቀን የተኩስ አቁም ጠይቀው ሀገሪቷ ላይ ያለውን የመፈንቅለ መንግስት አስረድተው ከመገንጠል ውጪ ሌሎች ጥያቄዎቻቸውን እንደሚመልሱላቸው ተነጋግረው ተማምነው ነበር። ሻቢያም የኢትዮጵያን ጦር እንደማያሸንፍ ያውቀው ነበር የጉሬላ ጦርነት ብቅ ጥልቅ እያሉ ለመዋጋት እንጂ እዚ ደረጃ እንደርሳለን ብለው አያስቡም ነበር። ታዲያ ስልጣን አግኝተው ኤርትራ ላይ የአስተዳደር ቦታ ከተቀመጡ ሰላም እንደሚፈጥሩ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም እና ህዝቡ በዲሞክራሱ የራሱን መሪ ከመረጠ ችግር እንደማይፈጥሩ ተማምነው ነበር።

‎ከዚህ መፈንቅለ መንግስት በኋላ ሀገሪቷ በጊዜው አሏት ከሚባሉ ጉምቱ እና ትላልቅ ልምድ የነበራቸውን ጀነራሎችን በማጣታችን ከ 81 በኋላ በነበሩት ውጊያዎች ላይ ልምድ የሌላቸው የጦር አዛዦች ባለመኖራቸው ምክንያት ያለምንም በቂ ልምድ በ 30 አመታት ሊደረስበት የሚገባ የጀነራልነት ማዕረግ ላይ በ 15 አመት ልምድ ብቻ ቦታውን በመያዝ እንዲሁም ለ መንግስቱ ሀ/ማርያም ባላቸው ታማኝነት ብቻ የጀነራልነት ማዕረግ ላይ ደርሰዋል። ከዛን በኋላም ሻቢያ በቀላሉ ኤርትራ ላይ የበላይ ሊሆን ችሏል እንዲሁም ህወሀት ሀይሉን አደራጅቶ ስልጣን ለመያዝ በሩ ወለል ብሎላቸዋል። ደርግም ውድቀቱን አፍጥኖታል።

ኤርትራ ውስጥ የነበሩት ጀነራሎች በ ሄሊኮፕተር ወደ ጎረቤት ሀገር በቀላሉ የመሄድ እድል ቢኖራቸውም ጥለው መፈርጠጥን ግን አልመረጡም ነበር እስከ መጨረሻው ቆይተው እምነታቸውን ጠብቀው ተሰውተዋል። ከዚህ መፈንቅለ መንግስት ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ ሚስጥር በሆነ መንገድ ጀ/ ቁምላቸው ወደ ውጪ ሀገር ሊሰደድ ችሏል።

‎ ባጠቃላይ መፅሐፉ ብዙ እውነቶችንና መረጃዎችን የያዘ ቢሆንም ፀሐፊው የጀ/ደምሴ ልጅ የሆነው ደረጀ ለ ደርግ ሊቀመንበሮች ገለልተኛ ያልሆነባቸው ቦታዎች መኖሩን ያመላክታል። ቢሆንም ግን ለንባብ የማይሰለችና ጥንቅቅ ያለ መፅሐፍ መሆኑ ጥርጥር የለውም እንድታነቡት ጋብዛለሁ።

ኃይለአብ

@kelemofficial
2👍1🔥1
ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
²⁷ ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?


ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።


ማቴዎስ ወንጌል

አሜን🙏

@ourrthought
🙏83
ወደ ኋላ መመለስ ይኖርብን ይሆን?

ጥንታዊውን ሰው በዛሬ ቅኝት ለመቃኘት ካሻህ ቡሽሜንን (Bushmen tribes) መጎብኘት በቂህ ነው። እኚህ ጎሳዎች ለ አለም ወደኋላ ቀርተዋል ልብስ የላቸውም ፣ ጫማ አይጫሙም፣ ቤት የላቸውም ፣ ዛሬም አድነው ይመገባሉ ፣ ተፈጥሮን በራሳቸው መረዳት ይረዷታል ከልባቸው ደስተኛ ናቸው በቃ ዛሬ አድነው ከበሉ ዛፋቸው ስር ጥላቸው ላይ አረፍ ብለው ሀሴት ያደርጋሉ ከህይወት የሚጠብቁት ሌላ ታምር የለም። አለም ላይ ሀያሏ ሀገር ማን ናት ፣ ቢሊየነሩ ሰው ማነው? ፣ ዝነኛዋ እከሌ ማን ናት ጉዳያቸው አይደለም።

‎ ታዲያ ባንድ ወቅት አንድ የ አውሮጳ  ጋዜጠኛ እነሱን ለመጎብኘት ሄደ ያሰበውና ያገኘው ግራ አጋባው እነሱ ሚዳቆ አድነው የሚያገኙትን ደስታ የዘመንን ነን ብለን የምናስበው ሰዎች ፎቅ ደርድረን አናገኘውም። ከዛም ጥያቄውን ማስከተል ጀመረ። ህይወት ከንቱ አይሆንባችሁም? አላቸው ምንድነው ይሄ ሰውዬ የሚያወራው አይነት አዩት ሚዳቆ ካደኑ የምን ከንቱነት ነው ደሞ ሆ። ከዛም ቀጠለ እራሱን የሚያጠፋ ሰው ጎሳችሁ ውስጥ አለ? አላቸው ግራ ገባቸው እንዴት ነው ሰው ራሱን የሚያጠፋው? ጋዜጠኛውም ያው ህይወት ከንቱ ሆናበት ተስፋ ቆርጦ አብራራ : ሰው ጭራሽ ተስፋ ይቆርጣል : ደሞም እራሱን ያጠፋል ደነገጡ። አድኖ ከበላ እሳቱን ከሞቀ ተፈጥሮን እየኮመኮመ ከኖረ ጭራሽ ምን ልሁን ብሎ ነው የሚያጠፋው? በሰሙት ነገር ተገርመው ሊሞቱ ምን ቀራቸው። በርግጥ ሰው እራሱን ማጥፋት መቻሉንም ያመኑትም አይመስሉም።

‎ዘመነኛዎቹ እኛ ግን በብዙ ርቀት ጥለናቸው ብንሄድ ደስታ ደሞ ከኛ ዘንድ ጓዙን ይዞ ከሸሸን ሰነባብቷል። ምንም ቢኖረን ለመደሰት አቅቶናል ያለን ነገር ደስታ ሳይሆን ስቃ የጨመረብን ይመስላል። ግን የሰው ልጅ መመራመሩ ፣ ጨረቃን መርገጡ ፣ ጠፈርን ማሰሱ ፣ ቴክኖሎጂን ነጋ ጠባ ማዘመኑ ፣ መኪና ፣ ስልክ ፣ ቤት ፣ ልብስ የመሳሰሉት ለኛ ለዘመነኛዎቹ ሰዎች ምን አተረፈልን? የሚለው ጥያቄ ሁሌም ቢሆን ያሳስበኛል። ዘመናዊው ሰው ደስታውን በማሰስ ፍለጋ ውስጥ እያንዳንዱ የሚከፍታቸው በሮች ሀዘንን ከመሰብሰብ ውጪ ምን አተረፈለት?  እያንዳንዱ ግኝት ውስጥ ሌላ ከመጨመር እና አልረካም ባይ ስብዕና ካማግበስበስ በቀር።

‎እኛ ዘመነኛ ነን የምንል ስልጡኖቹ ሰዎች አንድን ማቴሪያል ከመገልገያነት ባለፈ ለሀዘናችን ምንጭ አልሆነምን?  ማነው ስልኩን ለስልክነት ብቻ የሚልገው? የያዘውን የድሮ ሞዴል ስልክ አሽቀንጥሮ አዲስ ምርት ለመያዝ ያለው ጭንቀት አይበዛምን? የሚኖርበትን ቤት ቁርና ወበቅ ከተቀላከለ በቂዬ ነው ብሎ የሚያስብ ማነው? የሚኖርበትን ተልካሻ ቤት ለመቀየር እና በሰዎች ዘመናዊ ቤት የሚቀናው አይበዛምን? መኪና ከሌለው ሰው በላይ መኪና ያለው ሰውዬ ጭንቀቱ ይበዛል ምክንያቱም የያዛትን መኪና ቶሎ ወዲያ አሽቀንጥሮ አዲስ ሞዴል ስለመንዳት እንጂ መንገዱን ስለማሳጠሩ አይደለም ጭንቀቱ። ዘመነኛዎቹ ሰዎች ውድድር ውስጥ እንጂ ኑሮውን ለራሱ መኖር ያቆመ ይመስላል። dopamine የምናመነጨው ስልክ ስንገዛ ሳይሆን ከሰዎች የበለጠ ስልክ እንደያዝን ስናስብ ነው ለዛ ነው በየጊዜዎ iPhone በወጣ ቁጥር እሱን ለመግዛት ሌሎቹን ለመብለጥ ጫማ የምንለካካው።

‎ ዛሬም ድረስ ወሬህ ኤለን መስክ በሀብት ሰንጠረዡ ላይ ሁለተኛ ስለመሆኑ እንጂ በገንዘቡ ምን ተጠቀመ? የሚለውን አናስበውም በ ሀብት አንደኛ ደረጃ ላይ ያለው ሰውዬና 100 ደረጃ ላይ ያለው ሰውዬ የኑሮ ልዩነታቸው ምንድነው? ሁለቱም ጭንቀታቸው አንደኛ የሀብት ደረጃ ላይ ለመቀመጥ እንጂ ስለተቀመጠው ገንዘባቸው አይደለም። ቁሳዊው አለም የሚለካው በቁጥር ነው ቁጥር ደሞ ማለቂያ የለውም።

‎በዘመንን ቁጥር ስቃያችን መቅለሉ ሳይሆን መብዛቱስ ቢሆን የሚጨምረው?  እውነትስ በነዛ በ ማሳይ ጎሳዎች ላይ ጣትህን ቀስረህ ለመሳለቅ ምን አቅም አለህ? የሰው ልጅ እነሱ ከሚኖሩት ኑሮ ለህይወቱ ባያስፈልጉትስ? አሁን ያለን ነገር የሰበሰብነው ያካበትነው ምን ያክሉ ለመኖራችን የግዴታ አስፈላጊ ነው? ሰው ከበላ ከጠጣ ተኝቶ ከተነሳ ከዚህ ሌላ አሁን ያለንበት የህይወት አዙሪት ትርኪ ምርኪ ቢሆንስ?  ምናልባት እነዚህን የቡሽሜን ጎሳዎች በብዙ ዘመን ጥለናቸው እንደሄድን እና እነሱ ኋላ ቀር እንደሆኑ ብናስብም እነሱ የሚኖሩበትን የደስተኛ ህይወት ግን በዚህ ሁሉ መዘመን ውስጥ ጥቂቷን እያገኘነው አይመስለኝም።

‎ እንደ ቡሽሜን ጎሳዎች እያደኑ መብላት ከዛም የሳር ጎጆህ ካልደረስክ በመሸብህ ቦታ እሳትህን አንድደህ ለጥ ማለት ጉብልህን እቅፍ አድርገህ ከልብህ መኖር የህይወት ከንቱነት የለ ኮተት የለ በቃ እስክትሞት መኖር ቀንህ ሲመጣ ከወዲያኛው አለም መሻገር አበቃ። ታዲያ እኛ ነን ወደነሱ መመለስ ያለብን ወይስ እነሱንም የኛን ህይወት አቅምሰን ንፅህናቸውን እንንጠቃቸው? የሚለውን ለዘመነኛው ሰው መጠየቅ እሻለሁ

@ourrthought
❤‍🔥10👍3👌1
እስቲ የታዘብኩትን ጀባ ልበላችሁ። ከሀገረ ዝዋይ ወደ ሀገረ ሀረር ጉዞዬን ለመጀመር የሰዓታት ልዩነት ነበር የቀረኝ። አንበሳው ተብሎ ከሚጠራው ሆቴል አጠገብ ቡናዬን እየጠጣሁ ነበር። ከዚህ ሆቴል ፊት ለፊት አደባባይ መሳይ ሰፊ ስፍራ አለ።

በዚህ ስፍራ ላይ በቀኝ በኩል የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ትልቅ ሞንታርቦ ከበው "እየሱስ ጌታ ነው" እያሉ እየተቀባበሉ በስሜታዊነት ይጮሀሉ። ከእነሱ በስተ ግራ በኩል ደግሞ የቀን ሰራተኞች መጥቶ የሚወስዳቸውን መኪና ጥበቃ ሰብሰብ ብለው ቆመዋል። አከባቢው በቆንጆ ህብር የተዋቀረ በመሰለበት በዚህ ቅፅበት ታዲያ የቀን ሰራተኞቹ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው " አላህ ወክበር" ብለው መጮህ ጀመሩ። አከባቢው በድንገት የሆነ ሰላምን በሚነሳ ጭንቅንቅ ውስጥ ገባ።

የገረመኝ ይሄ አልነበረም። የቀን ሰራተኞቹ የእስልምና እምነት ተከታይ ቢሆኑ ነገሩን ዝም ብሎ ማለፍ በተቻለ ነበር፤ ነገር ግን በውስጡ ብዙ አይነት እምነት ተከታዮች ነበሩ። ጉዳዩ የራስን ሀይማኖት ህልውና ማስጠበቅ አልነበረም፤ በቃ በውስጣችን ተዘርቶ ያለው 'የቲፎዞ' ስሜት ነበር ነገሩን የደበላለቀው።

በነገሩ ግራ የተጋቡት ሞንታርቦ ከባቢዎች ለጥቂት ቅፅበታት በዝምታ ተዋጡ፤ የነሱ ዝምታም ለእንጀራ ጉዳይ መቆፈሪያ የያዙትን ዝም አሰኛቸው። ከዚያም በነገሩ የተግባቡ ይመስል ሁለቱም አካላት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው መፈክራቸውን ማሰማት ቀጠሉ።

በዚህ መሀል የተመቻቸ ቦታ ላይ ሆኜ የሀገሬን ህዝቦች እርስ በእርስ እየተከፋፈሉ በየምክንያቱ ለመናቆር ያላቸውን ዝንባሌ ስመለከት ከውስጤ አንዳች የሚረብሽ ነገር ተሰማኝ። አሁን ባለው ዝንባሌ የሚቀር የማይመስለው የሀይማኖት ግጭት በሀገሬ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ውድመት ሳስበው ቀፈፈኝ።

ለማንኛውም፤ ከእርስ በእርስ ጦርነት አርፋ ለማታውቀው ሀገሬና የሀገሬ ልጆች "ቺርስ" እላለሁ፤ ቡና እየጠጣችሁ።

ዜድ

@ourrthought
👍91
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለዚህ ነው ህይወትን የማላምናት 😂 እንዲህ ያለ ፈተና ነው የገጠመን ጃል

@ourrthought
😁15🥰2
Forwarded from ቀለም መጽሔት
ቀለም ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 እትም 3.pdf
6.8 MB
ቀለም መጽሔት🗞️

ቅፅ 1 / እትም 3


ለሀሳብ አስተያየት
@KelemMagazine

Telegram 👇
@kelemofficial
3
ቀለም መጽሔት
ቀለም ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 እትም 3.pdf
እቺን መፅሔት እያነበባችኋት ያው እንደተለመደው አንድ ወግ ፈላስፋው ጋንኤል የምትለው የኔ ናት ነበብ ነበብ አድርጉ በዛውም telegram channel ላይ ተቀላቀሉ።

መቼስ ጊዜው ብዙ ሀሳብ የሚሰርቅበት ጥድፊያ የበዛበት ነው። ከጥድፊያው አረፍ ስትሉ እንዲህ አይነት ፅሑፎችን እያነበባቹህ ዘና በሉ

@ourrthought
7
አልፎ አልፎ ድረሰት ልልቀቅባቹህ ጃል

ድንገት በጨዋታችን መሀል ኮስተር አለና ወደ ሰማይ አንጋጦ በለሆሳስ ማውራት ጀመረ

"ምናልባት.... ከልባችን የምኖዳቸው ሰዎች ቢጠሉንስ?
ምናልባት እንዲኖረን የምንፈልገው ነገር የሚያጠፋን ቢሆንስ?
ምናልባት.... ህይወት ላይ ስኬት ማግኘት ሳይሆን መታገሉ ቢሆንስ?
ምናልባት.... የህይወታችን ትልቁ ስኬት ብለን የምናስበው ነገር ስንደርስበት ተራ ቢሆንብንስ?
ምናልባት.... የምንጠላው ነገር ውስጥ ቢሆንስ ደስታች ያለው?" ብሎ መልስ ፍለጋ አይነት ዘንበል ብሎ አይን አይኔን አተኩሮ ያየኝ ጀመር።

እንጃ......ብቻ ስለነገሮች ከማሰብ ይልቅ እየኖርኩኝ የሚሆነውን ማየት ነው የምመርጠው.....ነገር ሁሉ በጊዜው ውብ ነው ይባል የለ.....የነገውን ነገ ስደርስበት ነው ማወቅን የምሻው.....ብዬው አይኔን አሸሸሁበት

ነገውን እያሰበ ዛሬን ከሚኖር ሰው በላይ ከደስታ የራቀና በጥንቃቄ የተሞላ ስሜት አልባ የለም....ህይወቱ የስሌት ነው....ህይወት ላይ ደግሞ ከስሌት በላይ በስሜት ሲሆን ደስታ ይሰጣል....ከራሴ ጋር ወደ ውስጤ ጠፋሁ.....

@ourrthought
11👍1
የሰው ልጅ ለ አዕምሮው ማስተዋል ከሌለው
‎ለልቡ ርህራሄ ከሌለው ሀይማኖት የለውም
‎ሰው ሲተርፈው ነው ፎቅ የሚሰራው ፈጣሪም ከላይ ይታዘባቹሀል


መንገድ ላይ አንድ የኔ ብጤ ሲናገር ከሰማሁት!

ደራሲዎችሽ ባከኑብሽ ሐገሬ


@ourrthought
🔥92👍1
ሐሳቦቻችን
‎Modern Education As a Pavlov Dog ‎ ዛሬ የመጣችልኝን ሀሳብ እዚህችው ጫር ጫር የተደረገች ናት ከተመቸን እንቀጥለዋለን ‎በ ስነ-ልቦናው (psychology) ዘርፍ እስከ ዛሬ ስምምነት ካልተደረሰባቸው ጉዳዮች መካከል ስለ ሰው ልጆች የስብዕና ፀባይዮች (Human behavior) ዋነኛው ነው። የሰው ልጅ የ ፀባዩ ወይም ስብዕናው (personality) ከየት ነው የሚመጣው? የሚለው ዛሬም…
Modern Education As a Pavlov Dog
Operant conditioning

‎ከዚህ በፊት ከላይ አንድ ሀሳብ ላይ ተጨዋውተን ነበር። Behavioral psychology በሚለው ፅንሰ ሐሳብ ላይ እንዴት የኛን ስነ ባህሪ በዚህ ቲዎሪ ታግዘው ተፅዕኖ እንዳሳደሩብንና ለራሳቸው በሚመቻቸው መንገድ ስነ ልቦናችንን እንደቀረፁህ  Pavlov theoryን አንስተን አይተናል። ዛሬ ደሞ ከዚህ የሳይኮሎጂ ጥናት ላይ B.F. Skinner ያደረገውን ምርምር ተመርኩዘን እንዴት የኛን ስነ ልቦና ለመቆጣጠር( shape) ለማድረግ እንደተጠቀሙበት እናያለን።

‎B.F Skinner እ.ኤ.አ 1904 -1990 የኖረ አሜሪካዊ ሳይኮሎጂስት ነው። ከ pavlov ቀጥሎ የሰው ልጅ ስነ ባህሪው የሚወሰነው ባከባቢው ዙሪያ ባለው መስተጋብር በሚታየው ነው እንጂ በሌሎች ነገሮች አይደለም ብሎ ያምናል። ሳይንስ ውስብስብ የሆነውን የሰውን አዕምሮ ማጥናት አይችልም ለምሳሌ ደብሮኛል ስንል ግለሰባዊ ነው(subjective) ይሄን ደሞ ሰውየው ከሚነግረን ውጪ ማረጋገጥ እንችልም ይልቅስ ባህሪውን(behavior) በማጥናት የሰውን አዕምሮ መመራመር ይቻላል ብሎ ያምናል።

‎እንደ B.F.Skinner ገለፃ ከሆነ ነፃ ፈቃድ ብሎ ነገር የለም። ሁሉም ነገር ካለፈው ድርጊታችን ጋር የተያያዘ ነው ብሎ ያምናል። አሁን የምታደርገው ነገር ወይ ማድረግ የሚከብድህ ነገር በሙሉ ከዚህ በፊት ለዛ ድርጊት ከ ቤተሰብህ ይሆናል ወይ ከ አከባቢህ የተሰጠህ ምላሽ ላይ የተመሰረተ ነው ብሎ ያብራራል። ለምሳሌ ልጅ ሆነህ ወይም አድገህ መሀል ጣትህን አውጥተህ ስትሳደብ የሆነ ሰው ቢቆነጥጥህ ይሄ ቅጣት  (negative punishment) ድርጊቱን ድጋሜ እንዳታደርገው (remove a pleasant behavior) በመሆኑ ጉዳዩን በድጋሜ እናዳታደርገው ያደርግሀል ይላል።

‎B.F.Skinner behavioral theory የሚከተል በመሆኑ ለዚህ ዘርፍ Reinforcement and Punishment የሚባሉ ለዘርፉ ትልቅ ነገርን ያበረከቱ ጥናቶችን አከናውኗል። ባጭር ባጭሩ ከታች ላስቀምጥላቹህ

‎Positive reinforcement የሚባለው ጥሩ ነገርን ስታደርጉ ያንን ጥሩ ነገር ደጋግማቹህ እንድታደርጉት የምትገፋፉበት ማበረታቻ ነው። ለምሳሌ እናታቹህ ከቤት አትውጡ ብላቹህ ገበያ ብትሄድ እና ከ ገበያ ስትመለስ እዛው ብታገኛቹህ የምቶዱትን ነገር በሽልማት መልክ ትሰጣቹሀለች ማለት ነው። Add a pleasant stimulus to increase behavior ይለዋል ቢ.ኤፍ

‎Negative reinforcement የሚባለው ደሞ እንዳታደርጉት የሚፈለገውን ነገር ማድረግ እንዳይኖርባቹህ እና ማድረግ ያለባቹሁን ጥሩ ነገር በደንብ እንድታደርጉ shape የምትደረጉበት መንገድ ነው። ምናልባት Negative reinforcement የሚለውን ስሙን ስታዩ ቅጣት ሊመስላቹህ ይችላል ግን ቅጣት ሳይሆን የምትጠሉትን ነገር እንዳታደርጉት በማድረግ ጥሩ ባህሪያቹሁን እንድትቀጥሉበት የሚያደርግ ነው። እሷም ገበያ ስትሄድ አንተን በዘዴ ለመያዝ ከቤት ካሎጣህ ማታ የምታጥበውን ዕቃ እኔ አጥብልሀለሁ ትልሀለች ማለት ነው። remove an unpleasant stimulus to increase behavior ማለት ነው።

‎Positive punishment ይሄኛው ደሞ ማድረግ የሌለባቹሁን መጥፎ ባህሪ እንዳታደርጉት የምትቀጡበት መንገድ ነው። ከላይ ባየነው መሰረት ቤቱን ባዶ ቤት ጥለህ ወተህ እየተጫወትክ እናትህ ከገበያ ስትመጣ ውጪ ብታገኝህ ማጠብ የማቶደውን እቃ ቃሳጥብሀለች ማለት ነው። add an unpleasant stimulus to decrease behavior ማለት ነው።

‎Negative punishment ማለት ደሞ አንተ ቤቱን ጥለህ ወተህ እናትህ ከገበያ ስትመጣ ስታገኝህ ማታ ማታ የምትወደውን የቲቪ ፕሮግራም እንዳታይ መከልከል ወይ ስልክህን ለ 1 ሳምንት መንጠቅ ማለት ነው። ይሄ የምትወደውን ነገር በመቀማት ይሄን ድርጊት ድጋሜ እንዳትደግመው ማድረግ ነው። remove a pleasant stimulus to decrease behavior ይለዋል ቢ.ኤፍ

‎ታዲያ እንዴት ነው ትምህርት ላይ ወይም ሌላ ቦታ የሚጠቀሙበት? ካልከኝ
‎ት/ት ቤት የሚሰጥህን የቤት ስራ ሳትሰራ ስትሄድ ያለውን negative punishment ድርጊትህን እንዳታደርገው አንተን ባህሪህን ማስተካከያ መንገድ ነው። ለጎበዙ ተማሪ positive reinforcement ይሰጠዋል ድርጊቱን እንዲቀጥል። ረባሹን ተማሪ ደሞ በተቃራኒው። ይህ በትምህርት ቤት በምታልፍበት እያንዳንዱ ክፍል ላይ ስነ ባህሪህን እያስተካከሉት ነው የሚሄዱት አይምሮም ያለፈውን ቅጣትና ሽልማት ኢ ንቁ የ አዕምሮ ክፍል እያስቀመጠ ጥሩ የተባለውን እየመዘገበ መጥፎ የተባለውን ይጥላል።

‎በ አንዳንድ እስር ቤቶች መፅሐፍ ማንበብ ከ ፍርድህ ቀን ላይ ያስቀንስልሀል ይሄ ደሞ positive reinforcement ነው። እንዲሁም ጥሩ ነገር በ ማረሚያ ቤት ከሰራህ ስልክ ይፈቀድልሀል ነፃ ጊዜ ይሰጥሀል ይሄ ከላይ ስታየው ቀላል ነው ውስጡ ግን ስነ ባህሪህን መልክ ማስያዣ ነው። በስራ ቦታ የሚሰጥህ ቦነስና የሚቀነስብህ የደሞዝ ቅጣት እያንዳንዱ ነገር ስነ ባህሪህ ላይ ተፅዕኖ አለው።

‎ለዛ ነው B.F.Skinner የሰው ልጅ ቅሉ አያስታውሰው እንጂ የትኛውም ድርጊቱ ምክንያት አለው። በልጅነቱ ወይም ካደገ በኋላ የሚያሳዩት የሰዎች reinforcement እና punishment ላይ የተመሰረተ እንጂ ሌላ ምክንያት አይደለም ይልሀል። ምናልባት ዛሬ ቆም ብለህ ለምንድነው ይሄን የማደርገው ብለህ እራስህን ብትጠይቅ የኋላ ታሪክህ ላይ ይሄን ድርጊት ስታደርገው ሰዎች የሰጡህ ቀና ምልከታ ላይ የተመሰረተ ነው ወይም ማድረግ የማትፈልገው ነገር ምናልባት ልጅ ሆነህ ቤተሰብህና አከባቢህ በዛ ጉዳይ ላይ ቁንጥጫ አሳርፈውብህ ይሆናል።

የቀሩትን ደሞ የሰው ልጅ ባህሪ ይወስናል የሚሉትን ሌሎቹን ዘርፎች እናያለን

@ourrthought
8👏3
People buy stories, not just a product

‎ ስለ advertisement ከዚህ በፊት ወደ ሦስት የሚጠጉ article አጋርቻቹሀለሁ። ስለ ማስታወቂያው (advertising) ደጋግሜ የማጋራቹህ ያለምክንያት አይደለም። የሰውን ልጅ አዕምሮ ለመበዝበዝ (manipulate) ለማድረግ አለማችን ላይ በ አሁን ወቅት ትልቁ መንገድ በመሆኑ ነው። ይሄ የማስታወቂያው አለም (advertisement world) የሚጠቀሙት የጭለማውን ስነ ልቦና (dark psychology) በመሆኑ ነው።

‎የማስታወቂያው አለም (advertisement) ከሚጠቀማቸው dark psychology  አንዱ ማህበራዊ ተቀባይነት (social affection) ነው። አንድ ትልቅ ተቋም ከምርቱ ይልቅ በጣም የሚጨነቀው ምርቱን ማስተዋወቁ ላይ ነው። ለዛም ነው people buy stories, not just a product የሚሉት። አንድ እቃ ስትገዛ አንተ ትልቅ ቦታ የምትሰጣቸው ሰዎች ወይ በዛ ያለ ሰው ያንን ምርት ከተጠቀሙት የነሱን ተመሳሳይ እቃ የምትገዛው። ሰዎች ተቀባይነትን ከሰዎች እንፈልጋለን ያንን ተቀባነት ከማህበረሰቡ ለማግኘት ማህበረሰቡ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን ነገር በማድረግ እዛ ቦታ ለመቀመጥ የምንፍጨረጨረው።

‎ የኛን አዕምሮ ከኛ በላይ በጥልቀት የሚያጠኑት እኚህ ትላልቅ ድርጅቶች ከምርት ጥራት በላይ ለምርቱ ትልቅ ታሪክ ለመገንባት የሚፍጨረጨሩት። በማስታወቂያ ላይ ሮናልዶ ሲጠጣ ያየኸውን ለስላሳ አድናቂው ብትሆንም ባትሆንም ያ ሮናልዶ የሚጠጣውን ስጠኝ ትላለህ የምትገዛው ለስላሳውን ሳይሆን ታሪኩን ነው የሚባለው ለዚህ ነው። የሆነ ጊዜ ቱዋላይት ላይ የሰራው አክተር አንድ የሽቶ ማስታወቂያ ይሰራል እና በዛን ሳምንት ያ ሽቶ በሚሊዮን ነው የተሸጠው ለምን? ካልከኝ ታሪክ ገንበተዋላ።
‎እስኪ ቆም ብለህ አስብ የምትገዛው ምርት የምር ጥራትና ጥንካሬውን አይተህ ነው የምትገዛው? ወይስ ምርቱ የሰራውን የማስታወቂያ ታሪክ ተመስርተህ? ለዛ ነው የሆነ ምርት ሲመጣ በብዙ ብር ከፍሎ ታላቅ አርቲስቶችን እየመረጡ ብራንድ አምባሳደር እየመረጡ ገጭ የሚያደርጉልህ እና አንተም ምርቱን ስትገዛ እንትና የሚያስተዋውቀው እንትና የያዘው እከሌ የሚጠቀመው የምትለው ለምን social affection ነው አዕምሮህ የሚያስበው። የጡት ማያዣ የሚሸጠው ሰውዬ ጡት መያዣውን ከልብሱ ላይ ደርቦ አድርጎ ሲሸጥ ብታየው ልትስቅ ትችላለህ ሴቷ ግን በተቃራኒው በፈገግታ ትቀርበዋለች።

‎ የሆነ ጊዜ ላይ ትዝ ካላቹህ የቲክቶኩ አንድ ብር የሚባለው ወጣት ልጅ ፊቱን ገለጠ በብዙ ብር ማስታወቂያ አሰርተው ፊቱን አሳየ የሚል ነገር በየቦታው ይታይ ነበር። እና የዛኔ አውቀኸውም ይሁን ሳታውቀው ለድርጅቱ ማስታወቂያውን ስታራግብ ነበር ድርጅቱም የምርቱን ታሪክ እየገነባ ነበር። አጀንዳ በሆንክ ቁጥር ወደ ፊት ትመጣለህ ሰው አፍ ላይ ትቀራለህ ለዛ ነው አንድ ብር ፊቱን ማሳየቱ እና ማስታወቂያ መስራቱ ለድርጅቱ ትልቅ ታሪክ የገነባላቸው። የምን ማስታወቂያ ሰራ? ስንት ከፈሉት? ድርጅቱ ምንድነው? እያልክ ሳታውቀው ስትሰራ የነበረው። ለዛ ነው ሉላ ገዙን ebs በቀላሉ ወደ ቦታው ያመጣት ከቂጧ በላይ የኮንዶም ማስታወቂያ መስራቷ ቲቪው ላይ ይበልጥ እንድትመሰጥ የሆነከው።

‎ ምን ልላቹህ ነው። የምትገዛው ከምርቱ በላይ ታሪኩን : ማስታወቂያውን : promotionኑን ነው የምትገዛው እናም ንቁ ሆነህ ጠብቅ የ አዕምሮህን ጓዳ ማን እንደሚበረብረው አይታወቅምና!

@ourrthought
🔥9👏1