🗣 ዳግማዊ ልጥፍ ነው
አፍቅሮተ ሀዘን
@ourrthought
አፍቅሮተ ሀዘን
አለም አንተን በተጋጋሚ አልገፋችህም? የሰዎች ክህደት ልብህን በተደጋጋሚ አልሰቀሰቀህም? ህይወት ፊቷን አላዞረችብህም? ወይ የሆነ የያዘህ ህመም ከ አቅምህ በላይ አላሰቃየህም?
ሰዎች በባህሪያቸው ለራሳቸው በጣም የሚያዝኑ ፍጡሮች ናቸው። አብዛኛውን ጊዜ ስለ ራሱ እያሰበ የሚብሰለሰል እና እኔኮ በማለት ህመሙን በመተንተን የሚያዝን ብቸኛው ፍጡር ነው።
ሰዎች በጥሩ ነገር ብቻ እራሳቸውን የበላይ የሚያደርጉ ይመስልሀል? እንግዲያውስ ከመሠለህ ተሳስተሀል በችግርና በሀዘን እራሱን አንዱ ከ አንዱ የበላይ ለማድረግ የሚታትር አሳዛኝ ፍጡር ነው። የኔ በሽታኮ ከማንም በላይ ነው : አቤት የኔ ጨጓራ ከሰው ሁሉ ይለያል : የኔ ኩላሊት በስማብ ማንም አያክለው : አቤት ስንፍናዬ የኔ ከሰው ይብሳል : የኔን መሰልቸት ማን ይደርሰዋል... እያለ የራሱን ህመም በማጋነን በመልካም ነገር ያጣውን የበላይነት በዚህ ለመካስ የሚሞክር ፍጡር ነው።
ይንን ሀሳብ የሚያጠነክርልን ሀሳብ የታላቁ ፈላስፋ ኒቼን ሀሳብ እንዋስ ቃል በቃል ባይሆንም "ሰዎች ችግራቸውን : ቀሽምነታቸውን : ያለባቸውን ድክመት በኩራትና በልበ ሙሉነት የሚተነትኑ ፍጡሮች ናቸው" ይላል እሳቤው።
ግን ደግሞ ይሄን ድክመትና ችግር ለምን ያጎላሉ? ብዙ የሚጠቀሱ ነገሮች ቢኖሩም በዋናነት ግን የሚጠቀሰው ከልጅነት ጀምሮ ይሁን ካደጉ በኋላ ሰዎች ሲያማቸው ወይ ሲጎዱ ይበልጥ ትኩረትና እንክብካቤ ይሰጣቸዋል : ልጅ ሆነህ ሲያምህ የምትፈልገውን ነገር ቤተሰቦችህ ስለሚያደርጉልህ መዳንህ ሊያናድህ ይችላል : ይሄ ነገር ደግሞ በውስጣቸው አድጎ እንክብካቤንና ፍቅርን ለማግኘት የሚያደርጉት ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ ሊጠቀስ ይችላል።
ታዲያ በኒቼ ሀሳብ ሀሳቡን ስናጠናክር " ሰዎች ለመኖር ማበረታቻ የሚፈልጉ ብቸኛ ፍጡራን ናቸው" ይለናል። ከሰዎች ውጪ ያሉ ፍጡራን ማበረታቻ የሚፈልግ የለም። ሰዎች ግን ለመኖር ጉጉት : ተስፋ : ፍቅር : አይዞህ ባይነት : ሀዘኔታ የሚፈልግ በሰው የተደገፈ ፍጡር ነው። ታዲያ እንደዚህ ሆኖ ሳለ ህመሙን እያጎላ ፍቅር : እንክብካቤ : ድጋፍ ቢያገኝ ለመኖር ተስፋውን የሚቀጥልለት ከሆነ ዘንዳ ህመምን ሙጥኝ ማለቱ ያስጠይቀዋል ወይ? የሚለው አከራካሪ ይመስለኛል።
ለዚህም ይመስላል አንዳንድ ሰው የሚያዝንበትን ነገር ማጣት የማይፈልገው ብዙ ሰዎች ሀዘናቸውን መነጠቅ አይፈልጉም እሱ ነገር ከሌላቸው ለራሳቸው ምን እያሉ ያዝኑለታል? በዛ በሽታቸው ሰው የሚያዝንላቸው ከሆነ ያለዛ በሽታ የሰው ትኩረት ይነጠቀዋል : ለዛም ሀዘኑን በሽታውን እያስታመመ : እኔኮ እያለ በሽታውን ሀዘኑን እየደመረ : ሰዎችም ያዝኑለታል። ብዙ ሰዎች ሀዘንና ችግራቸውን ዛሬ ይወገድላቹ ቢባሉ አሻፈረኝ የሚሉ ይመስለኛል። ከዛ ህመም ውጪ እራሳቸውን ሲያስቡ አለም የሚጨክንባቸው ይመስላቸዋልና። አንዳንዴ ይህ እሳቤያቸው ወደ ናርሲስትነት ይወስዳቸዋል። ከራሳቸው/ህመማቸው/ ጋር በፍቅር ይወድቃሉ። አለምኮ ፊቱን አዙሮብኝ ብቻዬን ነው ያለፍኩት ምናም እያለ ይበልጥ ከራሱ ጋር ሙጥኝ ይላል።
ሌላው የክርስትና ሀይማኖትም ለድሀ ና ለ ህመምተኛ ይበልጥ የሚሰጠው ቦታ ሰዎች ችግራቸውን ለመውደድ እንደ ምክንያት ሊጠቀስ ይችላል።
አንተስ ከሁሉ የበለጠው ችግርህ : ህመምህ : መገፋትህ : መበደልህ : አካላዊ ቁስልህ የትኞቹ ናቸው? ትተክዝባቸዋለህ? በሰው ዘንድስ ሀዘኔታ እያሰገኘልህ ነው? @ourrthought
❤3🔥3😢2
እዚሁ የመጣልኝ ሐሳብ ላካፍላቹህ
ከ ስምንትና ከ ሰባት አመት በፊት የማውቃት አንድ ጥቅስ አለች "ደሀ ምኞቱን በመቀነስ ሀብታም ይሆናል" የምትል። የማን ጥቅስ እንደሆነ ባላውቅም ወደ ቡዲሂስት የሚጠጋጋ ሀሳብን ይዛለች። በጣም የምወዳት ጥቅስ ናት የምኞትን የመቀነስ ጥቅም የምታስረዳ አባባል ናት። አለማየሁ ገላጋይም አንዲት አባባል አለችው የድህነትና የሀብታም ልዩነት አንዲት መስመር ናት በቃኝ ማለትና አለማለት : በቃኝ ካልክ ሀብታም ነህ : በቃኝ ካላልክ ደሞ ደሀ ነህ የሚል።
የሰው ልጅ ግን በቃኝ ማለት ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ነው። በቁስ በሚመራ አለም ውስጥ እየኖርክ በቃኝስ ማለት ይቻላል ወይ? መልሱን ለናንተ ልተው። እንደኔ ሀሳብ በቁሳዊው አለም እየኖርክ : ነገራችን ሁሉ ቁሱ ላይ ተመስርቶ : የሰው ልጅ ፍላጎት ገደብ አልባ ሆኖ ሳለ በቃኝ የሚባልበት ሁለት መንገድ ያለ ይመስለኛል : አንደኛው እራስህን ከቁሱ አለም በማላቀቅ ወደ መንፈሳዊው አለም ፊትህን በማዞር : በሀይማኖት ውስጥ ሊሆን ይችላል ወይ ካዛ ውጪ መንፈሳዊው አለም ላይ በመጠንከር የቁስ አለም ጥማትህን በመንፈሳዊው መንገድ እያስታገስክ በመኖር። ወደ ገዳም መግባት አይነት ነገር። ሲቀጥል ደሞ ሚስቲካል (ተማህልሎ) ወይም አብርሆት(enlightened) ከሆን አልያ በ አብርሀም ማስሎ ስነ ተዋረድ ሀይራርኪይ አብርሆት (self actualization) ላይ መድረስ አለብህ።
@ourrthought
❤5🔥2
ዳርዊሽ እንዲ የምትል ጥቅስ አለችው
ዳዊት አለማየሁ ኢትዮጲያዬ በሚለው ዘፈኑ ላይ ደስ የምትለኝ ሀረግ አለች
"ጋራው የትም አለ ሸንተረር ወንዙ
እኔን የናፈቀኝ ሰው ከነ ወዙ"
የጥንት የነበረው ወዝ ያለው :
@ourrthought
"Yesterday, we were missing freedom. Today, we miss love. I'm afraid of tomorrow for we will miss humanity."
ትላንትና ነፃነትን ናፍቀናታል : ዛሬ ፍቅርን እንናፍቃለን : ነገ ላይ ሰብአዊነትን እንዳንናፍቀው እፈራለሁ!
በየጊዜው አካሄዳችን ሁሉ ወደ ጭካኔ የተገፋፋ ሆኗል። አንድ ቀን በጨመርን ቁጥር ከሰብአዊነት አንድ እርምጃ እያፈነገጥን ይመስለኛል።ሰዎች በባህሪያቸው መጥፎነትና እና ጭካኔ ውስጣችን አለ ብዬ አላምንም። ሰው ምንም ያክልንኳ በጊዜ ሂደት አሁን ያለበት የኒዎ ካፒታሊስት ዘመን ላይ ቢደርስም አሁንም ቢሆን ውስጡ ርዝራዥ መልካምነት ያጣል ብዬ አላምንም።
ቃየል አዳም ላይ ያነሳት ያቺ ድንጋይ መዘዟን አላሰበውም ነበር። አቤልን ወንድሙን ከገደለ በኋላ መከለያ ቤት ለማነፅ ነው የተነሳው። እራሱን ለመደበቅ ቅጥርን ሰርቶ ቁጭ ነው ያለው። ሰው ከመሰረቱ ጨካኝ ቢሆን ኖሮ አቤልን ከገደለ በኋላ በነፃነት የቀድሞ ኑሮውን ይኖር ነበር።
ጥንታዊው የሰው ልጅ ልበ ንፁህ ነበር። እንስሳትን እንኳ ለማደን ካልራበው በስተቀር እንደ ቀልድ አይገልም። ህይወቱን ለማስቀጠል ግድ ካልሆነበት በቀር እንስሳቱንና ተፈጥሮን ያፈቅራል። አሁን ግን ብዙ ሺህ ዶላሮች ከፍለን ለምግብነት ለማናውላቸው ያረጁ አጋዘኖችን ሚዳቆ : ዝሆን ለመግደል ቀስትና ጥይት አንግቦ በየ ፓርክ ይዞራል። ለድርጊቱም ሀሴትን ያገኛል።
ጥንት ጊዜ ነገስታት ጦርነትን ሲያደርጉ ብዙ ደም አንዳይፈስ ያሳስቡ ነበር። ጦርነት ያማራጭ ማጣት እንጂ ሰውን ለመማገድ የሚያደርጉት እንዳሁኑ ጊዜ የተራ ሽማግሌ የፖለቲካ ሹኩቻ አልነበረም። በሁለቱም ወገን ለሚሞቱት ያዝናሉ ክብር አላቸው። ከጦርነት በኋላ የማረኩትን እንደራሳቸው ወገን ተንከባክበው ወደ ሀገራቸው ይመልሷቸዋል።
በየ ፊልሞች : በየጌሞች በየ ዶክመንተሪው ውስጥ የሰውን አዕምሮ ብሬን ዋሽ አድርገውታል። ሞትን ጭካኔን እንደ ተራ የስክሪን ምስል አለማምደውናል። በየ ትምህርት ቤቱ ሀብት ጥቂት ነው (resource is scarce) እያሉ ስግብግብነትን (greedyness) በአዕምሮዋችን ይዘራሉ። እንዴት ተካፍለን መኖር እንዳለብን ሳይሆን እንዴት ተቀማምተን መኖር እንዳለብን በዘወርዋራው ይሰብኩናል። በፊት ማህበራዊ ሚዲያ (social media) እንዳሁኑ ሳይስፋፋ በፊት የሰው ልጅ ሞት ያስደነግጠን ነበር። አሁን ግን ጉዳዩ ሰው ሞተ ሳይሆን ምን ያክል ሰው ሞተ የሚለውን ለመስማት ጆሮዋችን ይቆማል።
ቢሆንም ግን ያቺ ትንሽ ብላቴና አና እንዳለችው የሰው ልጅ ከመሠረቱ ክፉ ነው ብዬ አላምን። ጥቂትም ቢሆን መልካምነት አያጣም።
ዳዊት አለማየሁ ኢትዮጲያዬ በሚለው ዘፈኑ ላይ ደስ የምትለኝ ሀረግ አለች
"ጋራው የትም አለ ሸንተረር ወንዙ
እኔን የናፈቀኝ ሰው ከነ ወዙ"
የጥንት የነበረው ወዝ ያለው :
የንፅህና ሰው ይናፍቀኛል። @ourrthought
❤8👍4
አንዳንድ ግለሰቦች ከስራ ድክም ብሎህ : ከ አለቃህ ጋር ተናቁረህ : ደሞዝህን ጨርሰህ : ባስ ተሰልፈህ በግድንግድ ሞንታርቦ ጆሮህ ስር ይጮሁብህና ስትበሳጭ ሴጣኑ ተበሳጨ ብለው ይደሰታሉ....ይልቅስ ብሮ ሴጣኑ እንኳ ሊበሳጭ በላይፍህ ሙድ እየያዘ ያለው አእምሮህ ውስጥ ያለው በሰው ብስጭት እየተደሰተ ያለው ነው። ስበሳጭ እርስ በርስ ስንናቆር ሴጣን ጮቤ ነው የሚረግጠው። እና የምናበሳጨውን እየለየን ሴጣንን ማበሳጨት ከሆነ አላማው በየ ቸርቹ እና ፀበል ቦታ በሽ ነው....
በዚህም post ብትበሳጩ የሚደሰት መንፈስ የለኝም
@ourrthought
በዚህም post ብትበሳጩ የሚደሰት መንፈስ የለኝም
@ourrthought
😁9👍2🔥2
አሁን ያለሁበት ሰፈር ውስጥ አንድ በ እድሜ ጠና ያሉ ሰውዬ አሉ ብዙ ጊዜ ማታ ማታ እንገናኛለን እና ሰላምታ ይሰጡኛል። መጀመሪያ ሰሞን ተመሳስዬባቸው ይመስለኝ ነበር ቀስ እያልኩኝ ስረዳቸው ግን ሁሉንም ሰው ነው ሰላም የሚሉት ባጠገባቸው የሚያልፈውን ሁሉ አወቁህ አላወቁህ ግድ የላቸውም።
እና አንዳንዴ ተክዤ ወይ ደብሮኝ እንዴት አመሸህ ብለውኝ ሲያልፉ ድብርቴ ሁሉ ነው የሚለቀኝ።
የሆነ ግዜ ላይ አንድ ሰውዬ ወደ ኤፍል ታዎር እራሱን ለማጥፋት ይሄዳል። ግን እራሱን ከማጥፋቱ በፊት አንድ ደብዳቤ ፅፎ በኪሱ ይዟል ደብዳቤዋም እንዲህ ትላለች :- አሁን ወደ ኤፍል ታዎር እራሴን ለማጥፋት እየሄድኩኝ ነው። ግን በመንገዴ ላይ አንድ ሰውንኳ አይቶኝ ፈገግ ካለ እራሴን ሳላጠፋ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ" ይላል። እረጅም መንገድ ተጉዞ ከቦታው ቢደርስም ግን ማንም ሰው አይቶት ፈገግ አላለም እናም እራሱን ከዛ ወርውሮ አጠፋ።
ምናለ የኔን ሰፈር ሰላምተኛ ሰውዬ አግኝተውት ቢሆን ኖሮ እላለሁ። አንዳንዴ ፈገግ የምትልለት ሰው የመኖሩ ምክንያት ልትሆን ትችላለህ። በቃ ምን ታወጣበታለህ ሰላም ብለህ ብታልፈው ፈገግታህን ብታሳየው ምናልባት የመኖር ምክንያት ትሆነው ይሆናል።

ፈግግታ አያስከፍልም ሰላምታ አያሰለችም!
@ourrthought
❤19❤🔥2👍2😢1
የነገን አሎልድም
ይሄ ፊልም ኳስ ቅሪላ ከማላፋት በዘለለ ብዙ ምስጢር እንዳለው የሚያሳይ ድንቅ ፊልም ነው። ዘዉጉን የደርግ ታሪክ ላይ ያደረገ ታሪካዊ ፊልም ነው።
ዋና ገፀ ባህሪው በደርግ ዘመነ መንግስት ላይ እራሱን ከ ጊዜው ፖለቲካ ምህዳር ለማውጣት የኳስ አሰልጣኝ መሆንን የመረጠ ገፀ ባህሪ ነው። ዋና ገፀ ባህሪው ከ ፓለቲካ ጋር ምንም ግንኙነትና ፍላጎት የሌለው ንፁህ ሰው ነው። ቢሆንም ግን እሱ የሚያሰለጥናቸው ወጣቶች አብዛኞቹ የ ኢህአፓ ምልምል ነብሰ ገዳይ ስኳድና አባል ናቸው። እሱ በማያውቀው መንገድ በኳስ እየተከለሉ ፖለቲካውን የሚያራምዱ ናቸው። የቀሩት ግን እንደ ዋናው ገፀ ባህሪ ፖለቲካ ሽሽት ኳሱ ውስጥ የተደበቁ ናቸው። ከማን ነው የሚደበቁት? ብትሉ ከጊዜው ፖለቲካ በተለይ ካረመኔው መላኩ ከሚባል የደርግ ልዩ ሰው ነው።
መላኩ ተፈራ( የአባቱን ስም እርግጠኛ አይደለሁም)
የእግዜር ታናሽ ወንድም
የዛሬን ማርልኝ የነገን አሎልድም " ተብሎ እስኪገጠምለት ባረመኔው የታወቀ ወንድ ሴት ሳይል እርጉዝ አዛውንት ሳይመርጥ በጭካኔ የሚደገል የሴጣን ታናሽ ወንድም ነው።
ታዲያ እኚ የ እግር ኳስ ተጫዋች በመምሰል በድብቅ የኢህአፓ አባል የሆኑት ወጣቶች ሲነቃባቸው ኳስ መጫወትም እያሰጋ ሲመጣ አሠልጣኙ ኳሱን ለማቆም ይገደዳል ታዲያ ያኔ ከሚስቱ ጋር ቁጭ ብሎ የሚያወራው ቃለ ምልልስ ዛሬም ድረስ ያቃጭልብኛል
"ይሄን ኳስ ይቅርብህ ብትባል እንቢ እያልክ ነበር ይሄው ጉድ መጣብህ"
"ምን ላርግ?
ምንም መሆን የማይቻልበት ጊዜ ሆነ። ኳሱን ባቆም ደርግ አብዮት ጠባቂ ያደርገኛል : ከነዛኞቹ ወገን ብሆን እነዚህኞቹ ይገሉኛል : ከነዚህኞቹ ወገን ብሆን እኚህኞቹ ይድሉኛል : ከሁለቱም ባልሆን መሀል ሰፋሪ በጥይት ይመታል እንዲሉ በጥይት እመታለሁ። ኳሱ መደበቂያዬም መሸሸጊያዬም ነበር : እሱም አሌሆነም ወሰዱብኝ።"
ሙሉ ፊልሙን የያዘ ዳይሎግ ነው። አሁንም ቢሆን ይህ ዘመን ኳስን መደበቂያው ያደረገ ይመስለኛል። ኳስ ወጣቱን ከድብርት : ከሀዘን : ከጦርነቱ ሀሳብ : ከወከባ : ሀዘኑን የሚያክምበት :ከብዙዎቹ ነገሩ የሚሸሸግበት : ህይወትን እያረፈ የሚጀምርበት : አለሙ ነው።
ኳስ ቅሪላ ብቻ ማልፋት አይደለም ክብ ኳስ ተከትሎ መሯሯጥ ብቻ አይደለም መደበቂያም ጭምር ነው ይሄን ደሞ አሁንም ቢሆን በዘመኔ የማየው ግልፅ ሀቅ ነው። ፊልሙን ብታዩት ብዙ ታተርፉበታላቹህ።

❤9🔥1
በድሮ ዘመን በንጉስ ጊዜ ነው አሉ
የዛኔ ውታፍ ነቃይ የሚባሉ አሉ ስራቸው ምን መሰላቹ ነገስታቱ እና ሹማምንቱ ከመቀመጫቸው ሲነሱ ቀሚሳቸው ወይ ልብሳቸው ቂጣቻው ላይ ሲወተፍ ከመቀመጫቸው ላይ በመሳብ የሚነቅሉ ናቸው።
እና አሁንም አሉ ይባላል አንዳንዶቹ ካድሬ የተቀሩት ፓርላማ ውስጥ ነው የሚሰሩት አሉ😂
ስራ አይናቅም ወገን እየበረታን@ourrthought
🤣20🔥2❤1
ሐሳቦቻችን
በድሮ ዘመን በንጉስ ጊዜ ነው አሉ የዛኔ ውታፍ ነቃይ የሚባሉ አሉ ስራቸው ምን መሰላቹ ነገስታቱ እና ሹማምንቱ ከመቀመጫቸው ሲነሱ ቀሚሳቸው ወይ ልብሳቸው ቂጣቻው ላይ ሲወተፍ ከመቀመጫቸው ላይ በመሳብ የሚነቅሉ ናቸው። እና አሁንም አሉ ይባላል አንዳንዶቹ ካድሬ የተቀሩት ፓርላማ ውስጥ ነው የሚሰሩት አሉ😂 ስራ አይናቅም ወገን እየበረታን @ourrthought
ውታፍ ነቃይ"የሚባል የስራ መደብ በዘመናዊው የስራ ገበታ ላይ ቢኖር የስራ ማስታወቂያው ምን ሊመስል እንደሚችል አስበው?
የስራ ማስታወቂያ
የስራ መደብ ከፍተኛ ውታፍ ነቃይ
የሚያስፈልገው የትምህርት ደረጃ በሰውነት ስነ-ጥበብ ወይም በጨርቃጨርቅ ኢንጂነሪንግ ሁለተኛ ዲግሪ ቢኖረው ይመረጣል።
ተፈላጊ ክህሎቶች
ፈጣንና ትክክለኛ የእጅ እንቅስቃሴ
ከፍተኛ የትኩረት አቅም
የሰውነት ቅርጾችን የመለየት ችሎታ በሹማምንቱ ፊት የመተናነስ ባህሪ
ተጨማሪ መረጃ ደሞዝ በየደረጃው በሚገኘው የውታፍ መጠንና አይነት ይወሰናል።የሚል ይሆን ነበር😂
ፂሆን

🤣7😁2
Obsessive Compulsive Disorder (OCD)
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የ ሳይኮሎጂ ተርሞችን መስማት የተለመደ ሆኗል አንዳንድ ሰውም የሆነ disorder ይመርጥና ትንሽ መመሳሰል ካየ አለብኝ ብሎ መጨነቅ እየተዘወተረ ነው ከነዛ ውስጥ አንዱ OCD አንዱ ነው።
OCD ማለት ምን ማለት ነው?
OCD ማለት አንድ ሰው አንድን ነገር ያለ በቂ ምክንያት ባላስፈላጊ ጉዳዮች ላይ አለ አግባብ ከሚጠበቀው በላይ የመጨነቅ : የመፍራት ችግር ሆኖ ለዛ ጭንቀታቸው : ፍርሀታቸው : አስተሳሰባቸው አላስፈላጊ የሆነ ምላሽ መስጠት እንደማለት ነው። በዚህ የ አዕምሮ ችግር የተጠቃ ሰው ከሌላው ሰው በቀላሉ የሚለዩበት ከምልክታቸው የሆነን ድርጊት ደግሞ ደጋግሞ ማድረግ ነው።
OCD ውስጥ የሚመደቡትን ዋና ዋናዎቹን እንመልከት
Contamination (መመረዝ)
ይሄኛው አይነት OCD ያለባቸው ሰዎች ከመጠን በላይ የጀርም ፣ የበሽታ እና የመመረዝ ፍራቻ አለባቸው። እዚህ ውስጥ የሚመደቡት ሰዎች በየደቂቃው እጃቸውን የመታጠብ : እጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር የመጠቀም : ገላቸውን ቶሎ ቶሎ መታጠብ : ቤታቸውን ማፅዳት የመሳሰሉት ችግሮች ይታይባቸዋል። ቆሻሻ እና ከጀርም ከመፍራታቸው የተነሳ ሰው ሰላም ለማት ይፈራሉ። መደበኛ ሰው ከሚያደርገው በላይ ጥንቃቄ ያደርጋሉ : ቤታቸው ውስጥ ቁጭ ብለው ከማንም ሳይገናኙ ራሱ በሰዐት ከ 20 እና 30 ጊዜ በላይ በሳሙና በሳኒታይዘር ሊታጠቡ ይችላሉ።
Ordering (የመሰደር ችግር)
ይሄ ችግር ያለባቸው ሰዎች ደግሞ ነገሮችን በቁጥር ወይ በቀለም ይየ በቁመት የመደርደር እና የማስተካከል ችግር ነው። እነዚህ ሰዎች የቆረጡትን የባስ ትኬት : ሻይ የጠጡበት ምንም ሊጠቅማቸው የማይችልን የቡዙ አመት ደረሰኝ ቤታቸው ሰብስበው በቀን ከፋፍለው በስርትተ ደርድረው ሊያስቀምጡ ይችላሉ። ሌሎቹ ደግሞ መፅሐፍ ድርድር አድርገው ትንሽ ከተዛነፈ ይረበሻሉ። ሁሉ ነገራቸው ድርድር ያለና የተስተካከለ ነው የሰው ቤት ሄደው ራሱ የተዛነፈ ነገር ሲያዩ ይጨናነቃሉ። ጫማ አውልቀው እኩል አድርገው ካላስቀመጡት ደስ አይላቸውም።
Harm or checkers (አደጋን መፍራት)
ይሄኛው የ OCD ውስጥ የሚካተቱት ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ሰውን የመጉዳትና እራሳቸውን የመጉዳት ፍራቻ አለባቸው። ለምሳሌ እነዚህ ሰዎች ከመተኛታቸው በፊት ክፍላቸው መቆለፉን ከ 5 ጊዜ በላይ ሊያዩ ይችላሉ። ከእንቅልፋቸው ተነስተው ሳይቀር በር መቆለፉን ቤታቸው ሰው አለመግባቱን ይፈትሻሉ እንደዛም እያደረጉ ሰላም አይሰማቸውም። አንዳንዶቹ ደግሞ አደጋን አብዝተው ይፈራሉ። ከዛ የተነሳ መኪና የማይነዱ አሉ ሰው ብገጭስ ብገድልስ በማለት።
Forbidden Thought (የተከለከሉ ሀሳቦችን ማሰብ)
እነኚህኞቹ ደግሞ ከ ባህል : ከሀይማኖት ከአስተዳደግ አንፃር የተከለከሉ ሀሳቦች ሲመጡብን የሚሰማን ፍርሀት ነው። ስለ ወሲብ ማሰብ ወይ ማውራት የተከለከለበት ያደገ ሰው ስለዛ ነገር በሀሳቡ ሲመጣበት የሚሰማው ፍርሀቻ : ወይ ሀይማኖቱን የሚፃረር ሀሳብ በ ሀሳቡ ከመጣበት ከመጠን በላይ ፍርሀቻ ውስጥ ይገባሉ ይሄንን ለማካካስ ከመጠን በላይ ያለፈ ፀሎተኛ ወይም ሀይማኖተኛ የመሆን ነገር ይመጣል አሁንም አሁንም መፀለይ ያበዛሉ።
ይሄ የ አዕምሮ ችግር ከየት ይመጣል?
ከ ቤተሰብ በ ጄኔቲክ : ከ አስተዳደግ ወይ ደግሞ በጦርነት ቦታዎች ላይ ማደግ ከመጠን ያለፈ ተጠራጣሪ (checker) ሊያደርገን ይችላል እና ደግሞ እራሳችንም አንድን ድርጊት ደጋግሞ ከማዘውተር የመላመድና በዚህ ችግር የመጋለጥ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።
ይሄን የ አዕምሮ ችግር ግን አለብኝ ለማለት ቢያንስ ይሄ ችግር ከናንተ ጋር ምን ያክል ዘልቋል (ከ 6 ወር በላይ) : በዚህ ችግር ምክንያት የለት ተለት ኑሮዋቹሁ ተበጥብጧል ወይ : ህይወታቹን መምራት እስኪያቅታቹህ ድረስ ሆኗል ወይ : በየቀኑ ሰላም ይነሳቹሀል ወይ የሚሉት ነገሮች ሊታሰቡ ይገባል። አንዶንዶቹ ነገሮች መጠናቸው አይብዛ እንጂ ብዙዎቹ ሰዎች ጋር ያሉ ነገሮች አሉ። ይሄ ችግር በ ካውንስሊንግ : በሳይካትሪስት የሚፈታ ችግር ስለሆነ የሚታከምና የሚድን ነው።@ourrthought
🔥4❤3👏1
Audio
ደሞ ውለታ ልዋልላቹህ
ርዕስ: በአሮጌ ጫንቃ የተጫነ አዲስነት
ጸሃፊ እና ተራኪ: ሀና ታዬ
🌼በቀለም መጽሔት የተዘጋጀ ልዩ የአዲስ አመት መዳረሻ ትረካ
ቀለም ሶስተኛ እትሟን ወደ እናንተ ለማድረስ ሽር ጉዷን እያጠናቀቀች ነው ፤ እስከዛው ገፃችንን ለወዳጅ ጓደኛዎ ያጋሩ፣ ቤተሰብ ይሁኑ።
ቀለም መጽሔት
@kelemofficial
ርዕስ: በአሮጌ ጫንቃ የተጫነ አዲስነት
ጸሃፊ እና ተራኪ: ሀና ታዬ
🌼በቀለም መጽሔት የተዘጋጀ ልዩ የአዲስ አመት መዳረሻ ትረካ
ቀለም ሶስተኛ እትሟን ወደ እናንተ ለማድረስ ሽር ጉዷን እያጠናቀቀች ነው ፤ እስከዛው ገፃችንን ለወዳጅ ጓደኛዎ ያጋሩ፣ ቤተሰብ ይሁኑ።
ቀለም መጽሔት
@kelemofficial
🔥8❤2
ገባ ገባ በሉና እየገዛቹህ አንብቡ ሁሌ እየተዋሳቹህ ማንበብም ነውር ነው።
like እየተጫናቹህ እለፉ ብዙ like ካለው መፅሐፍ ሽልማት አለው
ስልክ ቁጥር 0946523397
books Delivery inbox order 📚
Telegram @seblework
@ourrthought
like እየተጫናቹህ እለፉ ብዙ like ካለው መፅሐፍ ሽልማት አለው
ስልክ ቁጥር 0946523397
books Delivery inbox order 📚
Telegram @seblework
@ourrthought
👍5❤2
ዘመን አይፈረጥጥ፣ ጊዜም አይሸመጥጥ፣
ቀንም መሽቶ አይነጋ፤
ሰው ነው የሚጨልም፣ ሰው ነው የሚነጋ፡፡
ይላል ይስማዕከ
እናም ቺርስ በዚህ አመት አስበን ላላሳካናቸው እቅዳችን
ቺርስ ዘንድሮም ለምናቅደው
ቺርስ በየ አመቱ እራሳችንን እንለወጣለን ብለን ለምንዋሸው
ቺርስ ለ 2018 ዓ.ም ልዩነት ቢኖረውም ባይኖረውም እንኳን አደረሳቹህ🕊

❤14👍1😁1🤯1
ዘወትር ማለዳ ካንቀላፋሁበት እንቅልፌ የሚያነቃኝን ዶሮዬን አኩፋዳ ለማይሞላ ሆዴ ባረኩት! ከንግዲህ ለዘላለም መንቂያም የለኝ : ቀስቃሼ የለምና!
@ourrthought
❤10😢5🔥4
Forwarded from ው ል ብ ታ 🪔. . .
"ሰው ነው ብለሽ አስቢ "
"ማንን "
"እሱን"
"ማለት"
"በቃ ምንም ብታፈቅሪው ምንም ያክል ብታምኚው.... ሰው ነው ብለሽ አስቢ....... እንዳሰብሽው ባይሆን እና ስህተት ቢሰራ ህመምሽን ምትቋቋሚበት ትንሽ ጥንካሬ ለራስሽ አስቀምጪ ......ለሱ ካለሽ ፍቅር እና እምነት ትንሽ ለራስሽም አስቀሪ.... ሰው ነው ብለሽ አስቢ.... በፍቅርሽ እና በእምነትሽ ልክ ፍፁም አታድርጊው ጥንካሬ እንዲሆንሽ ለራስሽም የመፅናኛ ቃል አስቀምጪ ሰው ነው ብለሽ አስቢ .....
"ሰው ነው"

❤15
"አንቺ አለም አንቺ አለም የጀመረሽ እንጂ የጨረሰሽ የለም እንዲሉ"
አፀናፈ አለሙ ወሰን አልባ ነው። የኛም የህይወት ሩጫችን በዚህች አለም ውስጥ ለማይሞላ ኑሮ መንከላወስ ይመስል ከትርምሱ የሚያወጣን አጥተን ስንቃትት እንኖርና እንደዘበት እናልፋለን። ግን አለምን ደሞ የጨረሰ ሰው ባይኖርም በስነ-ጥበብ መነፅር ካለንበት አንዲት ክፍል ያላየነውን ያየነው እስኪመስለን ድረስ በምሳጤ ያስደቃኘናል። ከጫጫታው አለም መንጭቆ ገለል ያደርገናል ሠላም ይሰጠናል።
ሲሲፈስ የተባለ የግሪክ ንጉስ ባንድ ወቅት የሰውን ልጆች ሞት ሲፈጅ ፣ እንደው ያለምህረት በደስታ የሚኖሩትን ሰዎች እንዲያው እንደዘበት ሲቀጥፋቸው ፣ ያለርህራሄ የማሰቢያ ጊዜ ሳይሰጣቸው ያለ ቀጠሮ ሲያሰናብታቸው ፣ እቅዳቸውን የማጠናቀቂያ ማሰቢያ ጊዜ ሳይሰጥ ህይወታቸውን ሲነጥቅ ቢያይ ጊዜ ልቡ ትክዝ ብሎ እንደው ለነዚህ ምድራዊ የሰው ልጅ ፍጡራኖች ይሄን ሞት ባስርላቸው ደስታቸው ሙሉ ሆኖኮ ፍስሀ ይሆናሉ ብሎ አሰበ። እንደው ሲሲፈስ ልበ ሩሁሩህ ነውና : አማልክቱ ሳይሰሙ በድብቅ ያን አረመኔ ሞት ያዝ አድርጎ በሰንሰለት እስር ነዋ። ይሄኔ ሰዎች ፈነጩ ደስታቸው ማባሪያ አጣ። አማልክቱ ሲሲፈስ ሞትን በሰንሰለት ማሰሩንና ሰው ዘላለማዊ መሆኑን ቢያዩ ጊዜ ቁጣቸው ነደደ : ሞትን ከታሰረበት ሰንሰለት ፈተው ለቀቁ : ይሄን ጥፋት ያጠፋው ያ አረመኔ ሲስፈስን ምን እናድርገው ይሆን? ብለው አውጥተው አውርደው በመጨረሻ አንድ ሀሳብ አሰቡ ምን አትሉም? አንድ ግዙፍ ድንጋይ እያንከባለለ ለዘላለም ይኑር ብለው ወሰኑበት። ታዲያ ያ ግዙፉን ድንጋይ ወደ ተራራ አናት ይወስደዋል ድንጋዩ ልክ ተራራው ጫፍ ሲደርስ ወደ ታራራው ስር ይመለሳል ሲሲፈስም መልሶ ገፍቶ ጫፍ ያደርሰዋል መልሶ ይመለሳል ይሄ ታዲያ የዘላለም ቅጣቱ ነው።
ሲሲፈስ ይሄ ዘላለማዊ ቅጣቱ እንደሆነ ቢያውቅም ለሰው የከፈለው መስዋዕትነት ነውና ፈገግ ብሎ ለ አማልክቱ እያሳየ ያን ድንጋይ በደስታ ይገፋል። አማልክቱ በቅጣቱ እንደዛ መደሰቱን ሲያዩ ምን ብለው ይሆን? ፈገግታውንም እንንጠቀው? ብለውም አስበውም ይሆናል። መቼስ ቅጣታቸው ሲባክን ከማየት በላይ ምን ሊያስከፋቸው ይችላል ብላቹሁ። ታዲያ ሲሲፈስ አያስገርማቹሁም? እንዴት ብሎ ያን ዘላለማዊ ቅጣት በሳቅ ተቀበለው? የሚያልቅ ቅጣትስ ቢሆን ይሁን ግን ዘለአለም በሙሉ ያን ቅጣት እየሳቁ መቀበል አይደንቅም?
የኛስ ህይወት ከሲሲፈስ ህይወት በምን ይለያል? እንዲል አልበርት ካሙ ህይወት የማይሞላ ስልቻና የድግምግሞሽ አባዜ ነው። ዘፋኙም እንዳለው "አምላክ ስለሰራት ምድርን በክብነት : ዞሮ አይመጣ የለም ወደነበረበት" እንዲል : ህይትን ደጋግሞ መኖር ምስኪኑ የሰው ልጅ የማያመልጠው እጣው ነው። ግን ከዚህ አባዜ ወጥተን በምናብ አዲስ አለም የምንገባበት አንድ ነገር ያለ ይመስለኛል ምን ብትሉኝ ስነ-ጥበብ ነው። ልክ እንደሲሲፈስ በዚች አታካች አለም ላይ የህይወትን ድንጋይ በፈገግታ እንገፋ ዘንድ ብርታት የሚሆነን ማን እንደ ስነ-ጥበብ አለ። ኑሮ ድክም አድርጎን በቴያትር እርፍ ለማለት ፣ ደሞ ከሩጫው እርፍ ብለን መፅሐፋችንን ክፍት አድርገን የህይወትን ሌላ መልክ ለማየት መታደል ፣ በሙዚቃ ፋታ መውሰድ ፣ በግጥም መደመም ፣ በወግ ለመፈገግ ፣ በፊልም ለንመሰጥ የኑሮን ጣጣ ለትንሽም ጊዜ እናርፍ ዘንድ የህወትን ድንጋይ ሸክም ከጀርባችን አውርደን ህይወት ካዙሪቱ እንድንላቀቅ የምታደርገን ስነ-ጥበብ ናት።
ስንቶች በሙዚቃ እንደሚረጋጉ ፣ በግጥም እንደሚመሰጡ ፣ በቲያትር ሀሴት እንደሚያደርጉ ፣ በውዝዋዜ እንደሚፍታቱ የህይወትን ተለምዷዊ ስሪቱን እንዳመለጡ ድብርት ላይ ፈገግ እንዳሉበት ምስክር አያሻም። ቀለም መፅሔታችንም ከዚህ መታከት ታርፉ ዘንድ አለሁላቹህ ትላለች።
በታሪክ ወደኋላ ልንወስዳቹህ : ደሞም በዝክረ ጠቢባን አምዳችን ጠቢባንን ልናስታውስ : በግጥማችን አድማስን ልንዳስስ : በወጋችን እያስፈገግናቹህ ቁም ነገር እያስጨበጥን ሳቃቹሁን አብረን ልንስቅ : በፊል እንድንደመም : በአጫጭር ታሪኮች አሀ ልንል : ማን ይወደስልዎ ብለን አለም ያላወቃቸውን መልካም ሰዎች በብዕራችን ልናወድስ : ስነ ጥበባዊ ዜናዎችን እያነሳን ከህይወት እርፍ ትሉ ዘንድ ቀለም መፅሔታችን ዘመኑን ዋጅታ አለሁ ትላለች።
ቀለም መፅሔት የመጀመሪያ ዕትማችን ላይ አንባቢዎቻችን የሰጣቹሁን ሀሳብና አስተያየት ለኛ መሰላቸታችንን ፣ መታከታችንን ወዲያ ብለን በጉጉት ይህችን ሁለተኛ አምዳችንን ለማሰናዳት ትልቅ ብርታት ሆኖናል። ደሞም ለቀጣይ እንበረታ ዘንድ የናንተ በጎ አስተያየትና ሀሳብ ልክ እንደሲሲፈስ ጥንካሬ ይሆነናልና ሀሳባቹህ አይለየን እንላለን።
ቅፅ አንድ ቁጥር ሁለት ከመግቢያ ላይ የተወሰደ
@Kelemofficial

መቼስ ሰው ሲኖር የሚታወሰው በህይወት ሳለ ሰርቶ ባለፈው ነውና ነገ ላይ እነ እከሌ እኮ ኖረው ነበር ብቻ ከመባል ይሄን ሰርተው ነበር የምንባልባት አሻራችንን የምናሳርፍባት ናት። ታዲያ ነገ ላይ የህይወትን ታካችነት በምን አመለጣቹህ? ቢሉን በስነ-ጥበብ ለማለት : ለሌላውስ ምን አደረጋቹህ ቢሉን ቀለም መፅሔታችንን ልንተርክ : እንዴትስ ለሱ አልሰለቻቹሁ ቢሉን በአንባቢዎቻችን አበረታችን ለማለት ቀለምን እነሆ በረከት እንላለን።
ቅፅ አንድ ቁጥር ሁለት ከመግቢያ ላይ የተወሰደ
@Kelemofficial
👍5❤2