ክፍል 3
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ዜማ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘወትር
ፈጣሪዋን የምታመሰግንበት ልዩ ዜማ /መዝሙር/ ከመላእክት
የተገኘ ነው፡፡ ስለዚህ መዝሙራችን እስከ አሁን በዓለም ተወዳዳሪ
አልተገኘለትም የተገኘውም በኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ
አማካኝነት ነው፡፡
እኛም አሁን የምንዘምረው መዝሙር በቅዱስ ያሬድ
ዜማ ነው፡፡ የቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያው ዜማም አርያም
ይባላል፡፡ አርያም ማለትም ልዑል ከፍተኛ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ
ያሬድ የመጀመሪያውን ዜማ አርያም ብሎ የሰየመው ከሰማይ ካሉ
መላእክት ሰምቶ መዘመር ስለጀመረ ነው፡፡ ይህም ሲታወቅ
‹‹ቀዳሚ ዜማ ተሰምአ እም ሰማይ›› እያለ ይሄድ እንደነበር
ሊቃውንት ይተርካሉ፡፡ ይህ ታላቅ ሊቅ በመንፈሳዊ ተመስጦ ሰማየ
ሰማያት ተነጥቆ ከመላእክት ያገኘው ዜማ ዓይነቱ ሦስት ነው፡፡
እነዚህም፡- 1ኛ. ግእዝ
2ኛ. ዕዝል
3ኛ. አራራይ ይባላሉ፡፡
እስከ አሁን በዓለም የማናቸውም ፍጥረት ዜማ ጣዕሙ ይለያይ
እንጂ በእነዚህ የዜማ ዓይነቶች ብቻ የተጠቃለለ ነው፡፡ እነዚህ
ሦስቱ የዜማ ስልቶችም ምሳሌና ትርጉም አላቸው ይኸውም፡-
ግእዝ፡- ርቱዕ ማለት ነው፡፡ አብን ርቱዕ ሎቱ ነአኰቶ ክብር ምስጋና ለእርሱ
ይሁን ማለት ነው፡፡
ዕዝል፡- ጽኑዕ ማለት ነው፡፡ ወልድ ጽኑዕ መከራ ተቀብሎ አዳምን እንዳዳነው
ለማጠየቅ ነው፡፡
አራራይ ፡- ጥዑም ማለት ነው፡፡ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን እንደተጎናጸፍን
ለማስረዳት ነው፡፡
ይህም ቢሆን ታዲያ ተነጣጥለው አይቀሩም ግእዝ ከተሰኘው
ዜማ ዕዝልና አራራይ ይወጣሉ፡፡ ይህም በአሐዱ አብ ዜማ
ይታወቃል፡፡ ምሥጢረ ሥላሴም ከአብ እምቅድመ ዓለም ወልድ
ለመወለዱ፣ መንፈስ ቅዱስ ለመስረጹ ምሳሌ ነው፡፡ ከዚህም ጋር
የንባቡና የድምፁ ቃና አንድ መሆን የሥላሴን አንድነት ሲያስረዳ
የዜማው ሦስት ዓይነት መሆን ደግሞ የሦስትነታቸው ምሳሌ
ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የያሬድ ዜማ በቂና ጥሩ ጥሩ ምሳሌ ያላቸው
8 ዐበይት ምልክቶች አሉት፡፡ እነዚህም ዜማውን ለሚማር
ደቀመዝሙርና ለሚዘምረው ሁሉ ፈረንጆች ኖታ እንደሚሉት
በምልክትነት ሲያገለግል ምሳሌያቸውና ምሥጢራቸው ግን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ስለእኛ የተቀበለውን
መከራ የሚያስታውሱን ናቸው፡፡
እነዚህም ኋላ ሊቃውንት ከጨመሯቸው ከድርስና ከአንብር
በስተቀር ዋናዎቹ የቅዱስ ያሬድ ብቻ ሲዘረዘሩ፡-
1. ይዘት ( . ) ፡- በአይሁድ ጭፍሮች ለመያዙ
2. ሂደት ( — )፡- ታስሮ ለመጎተቱ
3. ጭረት ( ﺮ )፡- ለግርፋቱ ሰንበር
4. ድፋት ( ┌┐ )፡- አክሊል ሾኽ ለመድፋቱ
5. ደረት ( └┘ )፡- ሲሰቅሉት በመስቀሉ ላይ አንጋለው ከደረቱ ላይ
ቆመው እየረገጡት ለመቸንከሩ
6. ርክርክ ( ፡ )፡- ለደሙ ነጠብጣብ አወራረድና ለችንካሮች
ምልክት
7. ቁርጥ ( ├ )፡- በጦር ተወግቶ ፈጽሞ መሞቱ ለመታወቁ
8. ቅንአት ( ﺭ )፡- በቅንአት አይሁድ ለመግደላቸው
ከላይ የተጠቀሱት ምልክትና መስታወሻዎች ሲሆኑ 8 መሆናቸው
8ቱ ማኅበረ አይሁድ ተባብረውና ተማክረው በብዙ መከራ
ለመግደላቸው ምሳሌ ነው፡፡
እነርሱም ፡- 1. ጸሐፍት ፈሪሳውያን
2. ሰዱቃውያን
3. ረበናት /አይሁድ መምህራን/
4. መገብተ ምኵራብ /የምኵራብ ሹማምንቶች/
5. ሊቀ ካህናት
6. መላሕቅተ ሕዝብ /የሕዝብ ሽማግላች/
7. ኃጥአን
8. መጸብኃን ቀራጮች ናቸው፡፡
በሊቃውንት የተጨመሩ ምልክቶች፡-
9. አንብር ( ⊏ )
10. ድርስ ( ስ )
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን የማኅበር
ጸሎት ሲደርስ በጣዕመ ዜማ ወይም መዝሙር ማመስገንና
መጸለይ የተለመደና የተወደደ ሥርዓት ነው፡፡
ይህ ሁሉ ሲከናወን ለምስጋናውና ለጸሎቱ ማጎልመሻ ሆነው
የሚቀርቡት ንዋይተ ቅድሳትና የጸሎት ቅደም ተከተል ሁሉ በቂ
ምክንያትና ምሳሌ ያለው ሆኖ መገኘቱ እኛን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ልጆች ሁሉ በጣም ያኮራናል፡፡
ይህንንም ለመረዳት በጸሎተ ቅዳሴና በማኅሌት ምስጋና መዝሙር
በሚቆምበት ጊዜ የሚፈጸመውን ከልብ መመልከትና ማገናዘብ
ይገባል፡፡
ይቀጥላል.......
ዲ/ን ማቴዎስ ተሾመ
👇👇👇👇👇
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️

ስላሴን አመስግኑ
ስላሴን አመስግኑ(2)
የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት
ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ
ምስጋና ይገባል ከጧት አስከማታ
ኩሩቤል ሱራፌል የሚያመሰገኑ
መላአክት በሰማይ የሚዘመሩልህ
እኛም የ አዳም ልጆች እንዘምራለን
በሰማይ በምድር እንጠራሃለን
ብራብ በስላሴ እጠግባለሁኝ
ብጠማም በ አምላኬ እረካለሁኝ
ስላሴ አምባዬ ክብሬም ናቸውና
ሁሌም የመሩኛል በህይወት ጎዳና
ዲ/ን ማቴዎስ ተሾመ
👇👇👇👇👇
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ስላሴን አመስግኑ(2)
የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት
ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ
ምስጋና ይገባል ከጧት አስከማታ
ኩሩቤል ሱራፌል የሚያመሰገኑ
መላአክት በሰማይ የሚዘመሩልህ
እኛም የ አዳም ልጆች እንዘምራለን
በሰማይ በምድር እንጠራሃለን
ብራብ በስላሴ እጠግባለሁኝ
ብጠማም በ አምላኬ እረካለሁኝ
ስላሴ አምባዬ ክብሬም ናቸውና
ሁሌም የመሩኛል በህይወት ጎዳና
ዲ/ን ማቴዎስ ተሾመ
👇👇👇👇👇
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከ ዛሬ
ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከ ዛሬ
ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ (2)
መክሊቴን ቀብሬ ባሳዝንህ
መብራቴንም ይዤ ባልጠብቅህ
በታላቅ ይቅርታ እንዳትረሳኝ
በፍቅር ጎብኝተህ ከሞት አውጣኝ
ከቤትህ እርቄ መች ጠገብኩኝ
በረሀብ በእርዛት ተቸገርኩኝ
አምናለሁ አምላኬ እንድትምረኝ
ለይቅርታ መጣሁ ተቀበለኝ
አንዳች እንደሌለኝ አውቀዋለሁ
በአንተ ቸርነት ግን እመካለሁ
የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል
ይቅርታህ ለባሪያህ ይደርሰኛል
በመቅደስህ ቆሜ ለመዘመር
ሥራህን ለትውልድ ለመመስከር
እኔ ማነኝ ብዬ አስባለሁ
አምላክ ቸርነትህን አደንቃለሁ
በሰው እጅ መመካት አቁሜያለሁ
ረዳቴ አንተ ነህ አውቄያለሁ
አንተ ከጠበቅከኝ በህይወቴ
ቅጥርህ አይደፈርም መድሀኒቴ
የኔን ሥራ ተወው ተግባሬን
የመስቀሉን ነገር መርሳቴን
አዚሜን አንስተህ አንተን ልይህ
እየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ
ዲ/ን ማቴዎስ ተሾመ
👇👇👇👇👇
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከ ዛሬ
ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ (2)
መክሊቴን ቀብሬ ባሳዝንህ
መብራቴንም ይዤ ባልጠብቅህ
በታላቅ ይቅርታ እንዳትረሳኝ
በፍቅር ጎብኝተህ ከሞት አውጣኝ
ከቤትህ እርቄ መች ጠገብኩኝ
በረሀብ በእርዛት ተቸገርኩኝ
አምናለሁ አምላኬ እንድትምረኝ
ለይቅርታ መጣሁ ተቀበለኝ
አንዳች እንደሌለኝ አውቀዋለሁ
በአንተ ቸርነት ግን እመካለሁ
የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል
ይቅርታህ ለባሪያህ ይደርሰኛል
በመቅደስህ ቆሜ ለመዘመር
ሥራህን ለትውልድ ለመመስከር
እኔ ማነኝ ብዬ አስባለሁ
አምላክ ቸርነትህን አደንቃለሁ
በሰው እጅ መመካት አቁሜያለሁ
ረዳቴ አንተ ነህ አውቄያለሁ
አንተ ከጠበቅከኝ በህይወቴ
ቅጥርህ አይደፈርም መድሀኒቴ
የኔን ሥራ ተወው ተግባሬን
የመስቀሉን ነገር መርሳቴን
አዚሜን አንስተህ አንተን ልይህ
እየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ
ዲ/ን ማቴዎስ ተሾመ
👇👇👇👇👇
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ክፍል አራት
ማኅሌት
ማኅሌት ማለት ኃለየ፣ ዘፈነ፣ ዘመረ፣ አመሰገነ ካለው
የግእዝ ቃል የወጣ ሆኖ የምስጋና መዝሙር ለእግዚአብሔር
ማቅረብ ማለት ነው፡፡
የዚህም ይዘትና አፈፃፀም በአጠቃላይ አቋቋም ይባላል፡፡ አቋቋም
ማለት የመቆም ሥርዓት ማለት ሲሆን የበለጠ ሲብራራ ማኅሌቱ
ተቁሞ ካህናቱ የሚያገለግሉበት ጊዜ የአገልግሎት ሥርዓት
የዜማውን ስልት የሚገልፅ ነው፡፡ በዚህም ውስጥ በበዓላት ቀን
ማኅሌቱ የሚገለጥባቸው መንገዶች አሉ እነዚህም፡-
1. መቃኘት
2. መቀበል
3. መምራት
4. መመራት
5. ዝማሜ
6. ቁም /ንዑስ መርግድ/
7. ዐቢይ መርግድ
8. ጽፋት /ከአመላለስ መልስ ወረብ ጋር/
9. ድርብ ጽፋት
10. የጭብጨባ ጽፋት ናቸው፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትም ለምን ዐሥር ሆኑ ቢባልም
ዳዊት‹‹ወበመዝሙር ዘዐሠርቱ አውታሪሁ እዜምር ለከ›› ማለት
‹‹ዐሥር አውታር ባለው በገናም እዘምርልሃለሁ›› ያለውን
መሠረት በማድረግ አይሁድ ጌታን ለመያዝ ይሁዳን አመልካች
አድርገው ለመፈለጋቸው ምሳሌ ነው፡፡ መዝ. 143፥9
እነዚህም ግሩም የሆነ ምሳሌና ታሪካዊ ትርጉም አሏቸው፡፡
ይቀጥላል..............
ዲ/ን ማቴዎስ ተሾመ
👇👇👇👇👇
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ማኅሌት
ማኅሌት ማለት ኃለየ፣ ዘፈነ፣ ዘመረ፣ አመሰገነ ካለው
የግእዝ ቃል የወጣ ሆኖ የምስጋና መዝሙር ለእግዚአብሔር
ማቅረብ ማለት ነው፡፡
የዚህም ይዘትና አፈፃፀም በአጠቃላይ አቋቋም ይባላል፡፡ አቋቋም
ማለት የመቆም ሥርዓት ማለት ሲሆን የበለጠ ሲብራራ ማኅሌቱ
ተቁሞ ካህናቱ የሚያገለግሉበት ጊዜ የአገልግሎት ሥርዓት
የዜማውን ስልት የሚገልፅ ነው፡፡ በዚህም ውስጥ በበዓላት ቀን
ማኅሌቱ የሚገለጥባቸው መንገዶች አሉ እነዚህም፡-
1. መቃኘት
2. መቀበል
3. መምራት
4. መመራት
5. ዝማሜ
6. ቁም /ንዑስ መርግድ/
7. ዐቢይ መርግድ
8. ጽፋት /ከአመላለስ መልስ ወረብ ጋር/
9. ድርብ ጽፋት
10. የጭብጨባ ጽፋት ናቸው፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትም ለምን ዐሥር ሆኑ ቢባልም
ዳዊት‹‹ወበመዝሙር ዘዐሠርቱ አውታሪሁ እዜምር ለከ›› ማለት
‹‹ዐሥር አውታር ባለው በገናም እዘምርልሃለሁ›› ያለውን
መሠረት በማድረግ አይሁድ ጌታን ለመያዝ ይሁዳን አመልካች
አድርገው ለመፈለጋቸው ምሳሌ ነው፡፡ መዝ. 143፥9
እነዚህም ግሩም የሆነ ምሳሌና ታሪካዊ ትርጉም አሏቸው፡፡
ይቀጥላል..............
ዲ/ን ማቴዎስ ተሾመ
👇👇👇👇👇
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ወደማደሪያው ገብቼ
ወደማደሪያው ገብቸ ልስገድ
ለእግዚአብሔር(2)
ምስጋናንም ላቅርብ ስለስሙ ክብር(2)
አድርጎልኛልና አመሰግነዋለሁ
በአጸደ መቅደሱ እሰግድለታለሁ
ስለስሙ ክብር ውድቄ እነሳለሁ(2)
በመከራየ ቀን ሁኖኛል መከታ
ቤቱ ተገኝቼ በፍጹም ደስታ
የከንፈሬን ፍሬ ልሰዋ በዕልልታ(2)
አስር አውታር ባለው በበገና
በመላዕክቱ ፊት ለማቅረብ ምስጋና
የአፌንም ነገር ሰምቶልኛልና(2)
ለስሙ ልንበርከክ ለዕርሱ እንደሚገባ
ስለቴን ልፈጽም ላቅርብለት መባ
ወዳደባባዩ በዕልልታ ልግባ(2)
አሸበሽባለሁ ድምጼን አሰምቼ
በቤተ መቅደሱ ለሊት ተገኝቸ
እንደካህናቱ እጆቸን ዘርግቼ(2)
ዲ/ን ማቴዎስ ተሾመ
👇👇👇👇👇
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ወደማደሪያው ገብቸ ልስገድ
ለእግዚአብሔር(2)
ምስጋናንም ላቅርብ ስለስሙ ክብር(2)
አድርጎልኛልና አመሰግነዋለሁ
በአጸደ መቅደሱ እሰግድለታለሁ
ስለስሙ ክብር ውድቄ እነሳለሁ(2)
በመከራየ ቀን ሁኖኛል መከታ
ቤቱ ተገኝቼ በፍጹም ደስታ
የከንፈሬን ፍሬ ልሰዋ በዕልልታ(2)
አስር አውታር ባለው በበገና
በመላዕክቱ ፊት ለማቅረብ ምስጋና
የአፌንም ነገር ሰምቶልኛልና(2)
ለስሙ ልንበርከክ ለዕርሱ እንደሚገባ
ስለቴን ልፈጽም ላቅርብለት መባ
ወዳደባባዩ በዕልልታ ልግባ(2)
አሸበሽባለሁ ድምጼን አሰምቼ
በቤተ መቅደሱ ለሊት ተገኝቸ
እንደካህናቱ እጆቸን ዘርግቼ(2)
ዲ/ን ማቴዎስ ተሾመ
👇👇👇👇👇
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
👍1
ድል አለ በስምህ
ድል አለ በሰምህ
ድል አለ በቃልህ (2)
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ሰልህ
ባህር ይከፈላል መድሀኒአለም ሰልህ
ቃዴስን ታላቁን በርሀ
አለፍነው ሳንጠማ ውኃ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የፀና ሰምህ ነው
አምላኬ የፀና ሰምህ ነው
በእልልታ ቢፈርሰ እያረኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ባንተ ነው(2)
ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማረ ውኃ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ሰለ ሆንክ ነው አ ዶናይ
ሰለ ሆንክ ነው ሁሉን ቻይ
የቆምነው ዛሬ በህይወት
ሰምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግሰ
ሆነኸን ነው ክብርና ሞገስ
ዲ/ን ማቴዎስ ተሾመ
👇👇👇👇👇
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ድል አለ በሰምህ
ድል አለ በቃልህ (2)
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ሰልህ
ባህር ይከፈላል መድሀኒአለም ሰልህ
ቃዴስን ታላቁን በርሀ
አለፍነው ሳንጠማ ውኃ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የፀና ሰምህ ነው
አምላኬ የፀና ሰምህ ነው
በእልልታ ቢፈርሰ እያረኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ባንተ ነው(2)
ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማረ ውኃ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ሰለ ሆንክ ነው አ ዶናይ
ሰለ ሆንክ ነው ሁሉን ቻይ
የቆምነው ዛሬ በህይወት
ሰምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግሰ
ሆነኸን ነው ክብርና ሞገስ
ዲ/ን ማቴዎስ ተሾመ
👇👇👇👇👇
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
👉@mezmura👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
#ቡሄ፣ #ጅራፍ_ማስጮህ፣
#ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው?
ደብረ ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ አንዱ ነው። ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡
በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ (#ቡሄ፣ #ጅራፍ ማስጮህ፣ #ችቦ ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡
#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
#ሙልሙል_ዳቦ
ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን
አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡
ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡
#ችቦ_ማብራት
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡
#የጅራፍ_ምሳሌነት
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡
የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣ ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው።
ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን
🥔🥔🥔
📚ኰኲሐ ሃይማኖት📚
ለወዳጅዎ ሼር ያርጉላቸው
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•═╮
💚 @Kukuha_haymanot 💚
💛 @Kukuha_haymanot 💛
❤️ @Kukuha_haymanot ❤️
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•═╯

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለግዜር የተፃፈ ደብዳቤ
እንደምነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው?
እኛማ.....
ለእልፍ አእላፍ አለቃ… ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ …መድረክ ላይ ለፍፈን
ፆለት ቤታችንን ….እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ …..ህግጋቱን አልፈን
ደብዳቤ ላክንልህ፤
አይንህን ካየነው ሁለት ሽ ዘመን እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ
እንደውም እንደውም...
‹‹በመጣለሁ ተስፋ ሁለት ሽ ዘመን ቀጥሮን ከጠፋ
በቀጠሮው ሰአት መምጣት ከተሳነው
‹‹እግዜር አበሻ ነው›› እያሉ ያሙሃል!!
እኔ ምን አውቃለሁ...
አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሲሉኝ ...ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ
እግዚኦ በሉ ሲባል ...እንባየን የማፈስ
ሃሌ ሉያ ሲሉኝ ...በሳቅ ልቤ እሚፈርስ
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
እኔ ምን አውቃለሁ...
ግን አንተ ደህና ነህ?
ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ ?
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አትከፋም አንዳንዴ!
ከሆነስ ሆነና ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
አብረሃም ሰላም ነው...
እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው ?
እኛማ ይሄውልህ...
በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን
‹‹ኤሎሄ›› እንላለን ጎጆ እንድጥልልን....
ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን እ ን ደ ጉ ድ ተገፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን !!
አባታችን ሙሴ እነዴት ነው ለክብሩ
ውቂያኖስ መክፈያው ደህናናት ብትሩ?
እኛማ ይሄውልህ....
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን
ን ገ ር ል ን ና ብትሩን ያውሰን ?!
እናልህ እግዜር ሆይ....
ከተስፋዋ ምድር ወደሌላ ተስፋ አለን እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን መመለሻ መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን...!
ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን...
‹‹የመሄድ ዘመን ነው ባህር የመሻገር
‹‹ዱላህን ላክልን›› ብሎሃል በልልኝ!!
ሰማይ ቤት እንዴት ነው? ....ዳዊትስ ደህና ነው?
ዛሬም ይዘምራል ...ዛሬም ይፎክራል ?
ሰላም ነው ጠጠሩ .... ሰላም ናት ወንጭፉ?
እዛስ አቅል ገዛ ጎሊያድ ተራራው ጎሊያድ ግዙፉ?
እልፍ አላፍ ጎሊያድ ከቦን ሲደነፋ
ወንጭፉን ጠቅልሎ ምነው ዳዊት ጠፋ ?
ብሎሃል በልልኝ!!
ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ
‹‹ወንጭፍህን ስጠው ለዚህ ታሪክ አውሪ››
ብለህ እዘዝልን!!
እንዴት ነህ ጌታ ሆይ... ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
የሙሴ አልጋ ወራሽ እያሱ ሰላም ነው....?
ያቆማትን ፀሃይ ግቢ ቢላት ምነው?!
ያው እንደምታውቀው
አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሃይ የምንሞቀው...
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
የመጣው ወር ሀሉ ፀሃይ እያዘለ
የተሸመው ሁሉ ‹ፀሃይ ነኝ› እያለ
ያስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ
ያስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር
ባቃጠላት ምድጃ አገር
ምን ታምር ሊኖር ይችላል ፀሃይ ሁኖ እንደመፈጠር!!
ኧረ እግዜር በናትህ....
ኧረ እግዜር በናትህ...በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና!!
እናልህ እግዜር ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል
ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል...
ጳውሎስ ሲሉን ...አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን ...ወይየ
ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን
ስማችንን ሸጠን ...ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን!
ስንቱ ባለካባ ክብርህ የተሰጠው
ለሰላሳ ፍራንክ ለተራ ጭብጨባ አደራህን ሸጠው !
ተወው የኛን ነገር ...ሰማይ ቤት እንዴት ነው ....
ሂዋንስ ደህና ናት?
ያው የልጅ ልጆቿ በግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርምህ ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም ባይኑ ያገምጡታል
ሰይጣንም ደህና ነውኑሮ ተስማምቶታል....
ሰውን ለማሳሳት ላይ ታች ማለት ትቷል
ሳይጠራው የሚጎርፍ ህዝብ በዝቶለታል...!
ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና!!
©አሌክስ አብረሃም
@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
እንደምነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው?
እኛማ.....
ለእልፍ አእላፍ አለቃ… ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ …መድረክ ላይ ለፍፈን
ፆለት ቤታችንን ….እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ …..ህግጋቱን አልፈን
ደብዳቤ ላክንልህ፤
አይንህን ካየነው ሁለት ሽ ዘመን እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ
እንደውም እንደውም...
‹‹በመጣለሁ ተስፋ ሁለት ሽ ዘመን ቀጥሮን ከጠፋ
በቀጠሮው ሰአት መምጣት ከተሳነው
‹‹እግዜር አበሻ ነው›› እያሉ ያሙሃል!!
እኔ ምን አውቃለሁ...
አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሲሉኝ ...ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ
እግዚኦ በሉ ሲባል ...እንባየን የማፈስ
ሃሌ ሉያ ሲሉኝ ...በሳቅ ልቤ እሚፈርስ
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
እኔ ምን አውቃለሁ...
ግን አንተ ደህና ነህ?
ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ ?
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አትከፋም አንዳንዴ!
ከሆነስ ሆነና ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
አብረሃም ሰላም ነው...
እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው ?
እኛማ ይሄውልህ...
በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን
‹‹ኤሎሄ›› እንላለን ጎጆ እንድጥልልን....
ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን እ ን ደ ጉ ድ ተገፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን !!
አባታችን ሙሴ እነዴት ነው ለክብሩ
ውቂያኖስ መክፈያው ደህናናት ብትሩ?
እኛማ ይሄውልህ....
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን
ን ገ ር ል ን ና ብትሩን ያውሰን ?!
እናልህ እግዜር ሆይ....
ከተስፋዋ ምድር ወደሌላ ተስፋ አለን እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን መመለሻ መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን...!
ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን...
‹‹የመሄድ ዘመን ነው ባህር የመሻገር
‹‹ዱላህን ላክልን›› ብሎሃል በልልኝ!!
ሰማይ ቤት እንዴት ነው? ....ዳዊትስ ደህና ነው?
ዛሬም ይዘምራል ...ዛሬም ይፎክራል ?
ሰላም ነው ጠጠሩ .... ሰላም ናት ወንጭፉ?
እዛስ አቅል ገዛ ጎሊያድ ተራራው ጎሊያድ ግዙፉ?
እልፍ አላፍ ጎሊያድ ከቦን ሲደነፋ
ወንጭፉን ጠቅልሎ ምነው ዳዊት ጠፋ ?
ብሎሃል በልልኝ!!
ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ
‹‹ወንጭፍህን ስጠው ለዚህ ታሪክ አውሪ››
ብለህ እዘዝልን!!
እንዴት ነህ ጌታ ሆይ... ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
የሙሴ አልጋ ወራሽ እያሱ ሰላም ነው....?
ያቆማትን ፀሃይ ግቢ ቢላት ምነው?!
ያው እንደምታውቀው
አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሃይ የምንሞቀው...
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
የመጣው ወር ሀሉ ፀሃይ እያዘለ
የተሸመው ሁሉ ‹ፀሃይ ነኝ› እያለ
ያስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ
ያስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር
ባቃጠላት ምድጃ አገር
ምን ታምር ሊኖር ይችላል ፀሃይ ሁኖ እንደመፈጠር!!
ኧረ እግዜር በናትህ....
ኧረ እግዜር በናትህ...በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና!!
እናልህ እግዜር ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል
ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል...
ጳውሎስ ሲሉን ...አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን ...ወይየ
ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን
ስማችንን ሸጠን ...ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን!
ስንቱ ባለካባ ክብርህ የተሰጠው
ለሰላሳ ፍራንክ ለተራ ጭብጨባ አደራህን ሸጠው !
ተወው የኛን ነገር ...ሰማይ ቤት እንዴት ነው ....
ሂዋንስ ደህና ናት?
ያው የልጅ ልጆቿ በግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርምህ ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም ባይኑ ያገምጡታል
ሰይጣንም ደህና ነውኑሮ ተስማምቶታል....
ሰውን ለማሳሳት ላይ ታች ማለት ትቷል
ሳይጠራው የሚጎርፍ ህዝብ በዝቶለታል...!
ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና!!
©አሌክስ አብረሃም
@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
#ገድሉታምራቱ
ገድሉ ታምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣዖትን አዋርዶ የተሸለመው
የተዋህዶ ኮከብ ተክለ ሐዋርያ
አባ ተክለሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
--አዝ
ዳግማዊ ዩሐንስ ጠፍር የታጠቀ
ፍፁም ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ
የፀጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ
በደብረሊባኖስ መናኝ አስከተለ
--አዝ
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት
ባለ ስድስት ክንፉ ተክልዬ የእኔ አባት
እርሱስ አንበሳ ነው ይናገር ደብረ አስቦ
ሌጊዮን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
--አዝ
ከካህናት መካከል ህሩይ ነው ተክልዬ
መጣሁ ከገዳምህ ልሳለምህ ብዬ
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ወልድ ዋህድ ብለህ ምድሪቷን ቀደስካት
--አዝ
የባረከው ውሃ የረገጥከው መሬት
ጥላህ ያረፈበት ሆኗል ፀበል እምነት
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክልዬ ዛሬም እንደ ጥንቱ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
@orthodoxonly
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ገድሉ ታምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣዖትን አዋርዶ የተሸለመው
የተዋህዶ ኮከብ ተክለ ሐዋርያ
አባ ተክለሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
--አዝ
ዳግማዊ ዩሐንስ ጠፍር የታጠቀ
ፍፁም ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ
የፀጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ
በደብረሊባኖስ መናኝ አስከተለ
--አዝ
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት
ባለ ስድስት ክንፉ ተክልዬ የእኔ አባት
እርሱስ አንበሳ ነው ይናገር ደብረ አስቦ
ሌጊዮን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
--አዝ
ከካህናት መካከል ህሩይ ነው ተክልዬ
መጣሁ ከገዳምህ ልሳለምህ ብዬ
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ወልድ ዋህድ ብለህ ምድሪቷን ቀደስካት
--አዝ
የባረከው ውሃ የረገጥከው መሬት
ጥላህ ያረፈበት ሆኗል ፀበል እምነት
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክልዬ ዛሬም እንደ ጥንቱ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
@orthodoxonly
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✥በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✥
✥ጳጉሜ 3 ለሚከበረ ቅዱስ ሩፋኤል ለአመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን✥
አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)
✥ በየዓመቱ ጳጉሜ 3 የቅዱስ ሩፋኤል መልአክ ነው ፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል የጦቢትን ዓይን ያበራና ወለተ ራጉኤልን ተቆራኝቷት ከነበረው ጋኔን ያላቀቃት መሆኑ በመጽሐፈ ጦቢት በስፋት ተገልጿል፡፡ ጦቢት በፋርስ ንጉሥ በስልምናሶር ዘመን የተማረከ ከነገደ ንፍታሌም የተወለደ ጽኑዕ እሥራኤላዊ ነው፡፡ እግዚአብሔር በስልምናሶር ፊት የመወደድን ግርማና ባለሟልነትን ስለ ሰጠው አለቃ አድርጎ ሾሞት ነበር፡፡ ለወገኖቹ ምጽዋት በመስጠት ሕገ ርትዕን በመሥራት የተጋ ሰው ነበር፡፡ ሐና የምትባል ሚስት አግብቶ አንድ ልጅ ወልዷል፡፡
✥ስልምናሶር ሞቶ ሰናክሬም በነገሠ ጊዜ ከሹመቱ ስለሻረው ደግሞ ወደ ምድያም መሔድ አልቻለም፡፡ ሣራ ወለተ ራጉኤል ከፍተኛ ችግር ደርሶባት ነበር፡፡ ችግሯም ሕፃናት ወልጄ ቤት ንብረት ይዤ እኖራለሁ በማለት ባል አገባች ነገር ግን በዚች ሴት አስማንድዮስ የሚባል ጋኔን አድሮ ያገባችውን ሰው ገደለባት ሌላም ባል ብታገባ ሞተባት እንደዚህ እየሆነ በጠቅላላ ሰባት ድረስ ያሉትን ባሎችን ገደለባት፡፡ የራጉኤል ልጅ ሣራ በዚህ ሁኔታ በኀዘን ተውጣ ስትኖር በነበረበት ጊዜ ጦቢት ሸምግሎ ስለ ነበር ልጁ ጦብያን ጠርቶ በዚህ ዓለም እስካለ ድረስ ሊሠራው የሚገባውን መንፈሳዊ ሥራ እንዲሠራ በጥብቅ ከመከረው በኋላ በመጨረሻ ልጄ እኔ ሳልሞት የኑሮ ጓደኛህን ፈልግ፣ ስትፈልግም ዕወቅበት፣ እኛ የአብርሃም የይስሐቅና የያዕቆብ ዘሮች ነን ስለዚህ ከእነርሱ ወገን የሆነችውን እንድታገባ ከዚህም ሌላ ከገባኤል ዘንድ በአደራ ያስቀመጥኩት ገንዘብ አለና እኔ በሕይወት እያለሁ ብታመጣው የተሻለ ነው አለው፡፡
✥ጦብያም ያባቱን ምክር ሁሉ በጽሞና ካዳመጠ በኋላ ‹አባባ የነገርከኝን ነገር ሁሉ በተቻለኝ መጠን እፈጽማለሁ ግን ከገባኤል ጋር ስላለው ገንዘብ እንዴት ለማምጣት እችላለሁ? ሀገሩን አላውቀውም› አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ነገሩ አሳሳቢ ሆኖ ስላገኘው ጦቢት ልጁ ጦብያን ‹አብሮህ የሚሄድ ሰው እስቲ ፈልግ ምናልባት አብሮ የሚሄድ ጓደኛ ታገኝ ይሆናል ደመወዝም ሰጥተን ቢሆን ካንተ ጋር የሚሄድ አንድ ሰው ግድ ያስፈልግሃልና ሂድ ሰው ፈልግ› አለው፡፡ አብሮት የሚሄደው ሰው ለመፈለግም ቢሄድ አንድ መልካም ጐበዝ አገኘ ይኸውም መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ጦብያ ግን መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መሆኑን ፈጽሞ አላወቀም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ጦብያ መልአኩን ሰው መስሎ እንዳገኘው ‹የሜዶን ክፍል ወደ ምትሆነውና ራጌስ ወደ ምትባለው ሀገር ከእኔ ጋር ለመሄድ ትችላለህን የድካምህን ዋጋ የጠየቅኸውን ያህል እሰጥሃለሁ› ሲል ጠየቀው ቅዱስ ሩፋኤልም ‹እሺ ካንተ ጋር ለመሄድ ፈቃኛ ነኝ መንገዱንም ሆነ ሀገሩን በሚገባ አውቀዋለሁ ከገባኤል ቤት ብዙ ጊዜ ኑሬአለሁና› አለው፡፡
✥ ከዚህ በኋላ ጦብያ በል ከአባቴ ጋር ላስተዋውቅህ ብሎ ወደ አባቱ ወስዶ አስተዋወቀው ከእኔ ጋር የሚሄደው ሰው ይህ ነው በማለት ካስተዋወቀው በኋላ ጦቢትም ከወዴት እንደ መጣ ማን ተብሎ እንደሚጠራ ጠየቀው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልም የታላቅ ወንድምህ ወገን ከመሆንም ሌላ ስሜም አዛርያስ ይባላል አለው፡፡ ጦቢ. 5.12 ፡፡ ጦቢትም የወንድሙ ዘመድ መሆኑን ከሰማ በኋላ ‹አንተስ ወንድሜ ነህ በል የልጄ የጦብያን ነገር አደራ ከሀገር ወጥቶ አያውቅምና እንዳይደነግጥ ደኅና አድርገህ እንድትይዝልኝ› ብሎ ስንቃቸውን አስይዞ ሸኛቸው፡፡ አዛርያስ /ቅዱስ ሩፋኤል/ በመንገድ ይመራው ነበር፡፡
✥በዚህም ቅዱስ ሩፋኤል ‹መራኄ ፍኖት› /መንገድ መሪ/ ይባላል፡፡ እነርሱ ሲሄዱ ውለው ማታ ጤግሮስ ከተባለው ታላቅ ወንዝ ደረሱና ከዚያም ለማደር ወሰኑ፡፡ በዚህ ጊዜ ከድካሙ ጽናት የተነሣ ጦብያ ሊታጠብ ወደ ወንዙ ወረደና ልብሱን አውልቆ መታጠብ ሲጀምር አንድ ዓሣ ሊውጠው ከባሕር ወጣ፡፡ ወዲያውም መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ጦብያን ያዘው ፤ ዓሣውን እንዳትለቀው አለው ፤ ጦቢያም ከዓሳው ጋር ግብ ግብ ገጥሞ እየጐተተ ወደ የብስ አወጣው ፡፡ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሩፋኤል ጦብያን እንዲህ ሲል አዘዘው፡፡ ዓሣውን እረደው ጉበቱንና ሐሞቱን ተጠንቅቀህ ያዘው ሌላውን ግን ጠብሰን እንበላዋለን አለው፡፡ ጦብያም መልአኩ እንዳዘዘው ዓሣውን አርዶ ሐሞቱንና ጉበቱን ያዘ፣ ሌላውን ሥጋውን ግን ጠብሰው ራታቸው አደረጉት፡፡
✥ጦብያም ያንን የዓሣውን ጉበትና ሐሞት ለምን እንደሚያገለግል ለመረዳት ‹ይህን ያዘው ያልከኝ ለምንድን ነው?› ሲል ጠየቀው ቅዱስ ሩፋኤልም ጋኔን ያደረበት ሰው ሲገኝ ይህንን ከዕጣን ጋር ቢያጤሱበት ጋኔኑ ይለቃል ሲል መለሰለት፣፡ በዚህ ሁኔታ አንድ ባንድ ሲነጋገሩ ከቆዩ በኋላ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ጦብያን ‹ዛሬ ከራጉኤል ቤት እናድራለን፡፡ እርሱ ዘመድህ ነው፡፡ የእርሱም ልጅ ሣራ የምትባል ቆንጆ ልጅ አለችው፡፡ እሷን ለሚስትነት ይሰጥህ ዘንድ ለራጉኤል እነግርልሃለሁ› አለው፡፡ ጦብያም ‹ያች ልጅ ከዚህ በፊት ሰባት ሰዎች እንዳገቧትና ሰባቱም ባገቧት ሌሊት ደርቀው /ሞተው/ እንደሚያድሩ ሰምቻለሁ፡፡

✥ስለዚህ እኔ ላባቴና ለእናቴ አንድ ልጅ ነኝ እርስዋን አግብቼ ከዚህ በፊት እንዳገቧት ሰዎች እኔም የሞትኩ እንደሆነ አባቴንና እናቴን የሚረዳቸው የለም ቢሞቱም የሚቀብራቸው አያገኙምና እፈራለሁ› አለው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ግን ‹አባትህ ከዘመዶችህ ወገን ካልሆኑ በስተቀር ሌላ ሴት እንዳታገባ ሲል የነገረህን ረሳኸውን? በል ሰባት ባሎቿ ሙተውባታል ስለምትለው እኔ መድኃኒቱን አሳይሃለሁ ፤ አይዞህ አትፍራ አትሞትም የዓሣውን ሐሞትና ጉበቱን ለምን መሰለህ ያዘው ያልኩህ ? እንግዲህ ሐሞቱንና ጉበቱን ከዕጣን ጋር ጨምረህ ስታጤስበት በሣራ አድሮ የነበረው አስማንድዮስ የተባለው ጋኔን ወጥቶ ይሄዳል ፈጽሞም ወደ እርሷ በገባህም ጊዜ ሁለታችሁ ይቅር ባይ ወደ ሆነው እግዚአብሔር ጸልዩ እርሷም የተዘጋጀች ናት፡፡ ከእኛ ጋርም ወደ ሀገርህ ይዘናት እንሄዳለን› አለው፡፡ ጦብያም ይህንን ቃል በሰማ ጊዜ ደስ አለውና ከእርሷ በስተቀር ሌላ እንዳያገባ በሙሉ አሳቡ ወሰነ፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ ራጉኤል ቤት እንደ ደረሱ ሣራ በደስታ ተቀበለቻቸው የሣራ አባትም ጦብያን ገና እንዳለው ሚስቱ አድናን ‹ይህ ልጅ የእኔ ዘመድ ጦቢትን ይመስላል› አላት ከዚያም ጋር አያይዞ ‹ልጆች ከየት ሀገር መጣችሁ?› አላቸው፡፡ እነሱም ‹ከነነዌ ሀገር ነው የመጣን› አሉት፡፡ ‹ከዚያም ሀገር ጦቢት የሚባል ወንድም ነበረኝ ታውቁት ይሆን?› ሲል ጠየቃቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ጦቢያ አባቱን ሲጠራለት ‹እናውቀዋለን፡፡
✥ እኔም ራሴ የጦቢት ልጅ ነኝ› አለው፡፡ ከዚያ በኋላ ራጉኤል ‹የወንድሜ ልጅ ነህን?› ብለ እቅፍ አድርጐ ሳመው፡፡ አድናም ሳመችውና ሁሉም ተያይዘው የናፍቆት ልቅሶ ተላቀሱ፡፡ ከወንድሙ እንደ መጡም ሲገነዘብ በግ አርዶ በጥሩ ሁኔታ ጋበዛቸው፡፡ ትም ከበሉ በኋላ ጦብያ ቅዱስ ሩፋኤል በመንገድ የነገረውን በልቡ ሲያወጣ ሲያወርድ ስለ ዋለ ቅዱስ ሩፋኤልን ያንን በመንገድ የነገርከኝን አሁን ፈጽምልኝ ሲለው ሰምቶ ስለ ልጅቷ መሆኑን ስለ ገባው ራጉኤል ጦብያን ‹ልጄ ይህች ልጅ ላንተ የምትገባ ናት ሰጥቸሃለሁ አይዞህ አትጠራጠር አሁንም ብላ ጠጣ ለዛሬም ደስ ይበልህ አለውና ሣራ ካለችበት የጫጉላ ቤት አግብተው ዘጉት፡፡ ጦብያም ሣራን በይ እኅቴ ኑሮዋችን እንዲቃናልንና ጋብቻችን እንዲባረክልን አስቀድመን ወደ ፈጣሪያችን ጸሎት እናድርግ› አላትና አብረው ጸሎት ካደረጉ በኋላ ያንንየያዘውንና የዓሣ ጉበትና ሐሞት ከዕጣን ውስጥ ከተተው ፡፡
✥ በመጨረሻም ከጦብያ ጋር ሄዶ የነበረው መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልን የድካሙን ዋጋ ገንዘብ ለመስጠት ጠሩት እርሱ ግን ጦቢትንና ጦብያን ‹ፈጣሪያችሁን አመስግኑ እናንተ እስከ ዛሬ ድረስ ከየት እንደመጣሁ ማን እንደ ሆንኩ አላወቃችሁኝም፡፡ የእግዚአብሔር ምሥጢር ግን በክብር ሊገለጥ ይገባል እንጂ ሊሰውሩት ስለማይገባ የእኔን ተፈጥሮና ስም ልነግራችሁ እፈልጋለሁ ተፈጥሮዬ መልአክ ነኝ፣ ሥራዬም የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ› ሲል ገለጠላቸው፡፡
✥ እነርሱም ወድቀው የአክብሮት ስግደት ሰገዱለት፡፡ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት፡፡ /መጽ. ጦቢት/፡፡ ስለዚህ እንግዶችን መቀበል አንርሳ፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንዶች ሳያውቁ የመላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና፡፡ ዕብ. 13.1-2 ፡፡ ጦቢት ከእህሉ ከፍሎ ለተራበ የሚያበላ ከልብሱ ለተራቆተ ሰው የሚያለብስ እግዚአብሔርን ዘወትር የሚያመሰግን ለወገኖቹ የሚራራ አሥራት በኩራት የሚያወጣ ሰው ነበር፡፡ በመሆኑም በሥራው ሁሉ እንዲረዳው በችግሩ ጊዜ እንዲያጸናው ቅዱስ ሩፋኤል ተልኮለታል፡፡
✥ እኛም በሕይወታችን የጐደለብንን ነገር እንዲሞላልን ጐዳናችንን እንዲያስተካክልልን ከክፉ ጋኔን እንዲጠብቀን አምላክ ቅዱስ ሩፋኤል ተለመነን ቅዱስ ሩፋኤልንም አማልደን ማለትን ገንዘብ እናድርግ፡፡ ጳጉሜ የዘመን መሸጋገሪያ እንደ ሆነች ዕለተ ምጽአትም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የምንሸጋገርባት ስለሆነች ከወዲሁ የቅዱስ ሩፋኤልን የመታሰቢያ በዓሉን ስናከብር በአማላጅነቱ ከቅዱሳን ኅብረት እንዲደምረን በንስሐ ታጥበን ደጅ ልንጠና ይገባል፡፡
✥ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን የኢትዮጰያ መመኪያ ሊቅ፤ጻድቅ፤ሐዋርያና ጀግና ንጉስ፤እመቤታችን የምትወደው ዘወትር የምታነጋግረው አባት አጼ ዘርአ ያዕቆብ የዕረፍት ቀኑ ነው ።ይህ አባት ከሁሉም በላይ የምንመካባት ትውልድ የሚድንባት የዳነባት የጻድቃኔ ማርያምን ታቦት ከግብጽ ደብረ ምጥማቅ ይዞልን የመጣ አባት ነው።በዘመኑ የተነሱትን የተለያዩ መናፍቃንንም ድል ነስቶ አሳፍሯል፤ በተለይም ለእመቤታችንና ለመስቀል ስግደት አይገባም ብለው የተነሱትን ደቂቀ እስጢፋኖስ ከሊቃ...ውንት ጋር አከራክሮ ከረታቸው በኃላ በዚያ ቦታ ላይ ታላቅ የብርሃን አምድ ቆሞ ታይቷል፤ ይህንንም ብርሃን ከሩቅ አገር ድረስ እየመጡ ይመለከቱት ነበር በዚህም ቦታው ደብረ ብርሃን ተብሎ ተጠርቷል፤ ሰሜን ሸዋ ውስጥ የሚገኝ ነው።አጼ ዘርአ ያዕቆብ ትውልድ የሚማርባቸው መጽሀፈ ምእላድ ፤ መጽሀፈ ብርሃን የመሳሰሉ ጣፋጭ መጽሐፍትን የጻፈ ሲሆን ከአባታች ሆይ ቀጥሎ ያለውን የእመቤታችንን ምስጋና ''በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ'' የሚለውን ጸሎት የደረሰ አባት ነው፤የጻፋቸው መጽሐፍት ዛሬም ድረስ ቤተክህነት በሚገኘው ላይብራሪ ይገኛሉ። ከቅዱስ ሩፋኤልና ከአባታችን ዘርአ ያዕቆብ በረከት ያደለን።
🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼
╔✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_ዓመት❀
╚✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╝
የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏
በቴሌ ግራም
👉t.me/orthodoxonly
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

#የራማው_ልዑል
ራማው ልዑል ገብርኤል /2/
ተመላለስ መሀላችን
ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ/2/
ብርሃን ለባሽ እሳታዊው መልአክ
አንተ አማልደን ከመሐሪው አምላክ /2/
የምሥራች ነጋሪ ድንቅን ልደት አብሣሪ
የጽድቅ ፋና የድህነት ጎዳና /2/
ላመኑብህ ለተማጸኑብህ
ተጥኖ ደራሽ አለኝታቸው ነህ/2/
የአናንያ የአዛርያ የሚሳኤል ከለላቸው
ከእሳት ነበልባል ያዳንካቸው/2/
ምሰሶ ዐምዳችን መጠጊያችን
ቅዱስ ገብርኤል ከለላችን/2/
ዕለት ዕለት የምንማልድህ
ልጆችህን ይምራን መንፈስህ /2/
ራማው ልዑል ገብርኤል /2/
ተመላለስ መሀላችን
ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ/2/
ብርሃን ለባሽ እሳታዊው መልአክ
አንተ አማልደን ከመሐሪው አምላክ /2/
የምሥራች ነጋሪ ድንቅን ልደት አብሣሪ
የጽድቅ ፋና የድህነት ጎዳና /2/
ላመኑብህ ለተማጸኑብህ
ተጥኖ ደራሽ አለኝታቸው ነህ/2/
የአናንያ የአዛርያ የሚሳኤል ከለላቸው
ከእሳት ነበልባል ያዳንካቸው/2/
ምሰሶ ዐምዳችን መጠጊያችን
ቅዱስ ገብርኤል ከለላችን/2/
ዕለት ዕለት የምንማልድህ
ልጆችህን ይምራን መንፈስህ /2/
👍1
መቶ_ሃያው_የክርስቶስ_ቤተሰቦች።
ሐዋርያት (፲፪/12 ናቸው)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
*ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ (ስምዖን)
*ቅዱስ እንድርያስ (የጴጥሮስ ወንድም)
*ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
*ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ
*ቅዱስ ፊሊጶስ
*ቅዱስ በርተሎሜዎስ
*ቅዱስ ቶማስ ዘህንደኬ (ዲዲሞስ)
*ቅዱስ ማቴዎስ (ቀራጭ)
*ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እማትያስ
*ቅዱስ ታዴዎስ (ልብድዮስ)
*ቅዱስ ናትናኤል (ስምዖን ቀነናዊ)
*ቅዱስ ማትያስ
ቅዱሳን አርድእት (፸፪/72 ናቸው)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
+ወንጌላዊው ማርቆስ
+ሊቀ ዲያቆናት እስጢፋኖስ
+ሐዋርያው ጳውሎስ
+ቅዱስ ጢሞቴዎስ (የጳውሎስ የመንፈስ ልጅ)
+ቅዱስ ሲላስ
+ቅዱስ በርናባስ
+ቅዱስ ቲቶ (የጳውሎስ የመንፈስ ልጅ)
+ቅዱስ ፊሊሞና (የጳውሎስ የመንፈስ ልጅ)
+ቅዱስ ቀሌምንጦስ
+ቅዱስ ዘኬዎስ
+ቅዱስ ቆርኔሌዎስ
+ቅዱስ ቴዎፍሎስ
+ቅዱስ ኤውዴዎስ
+ቅዱስ አግናቴዎስ
+ቅዱስ አናንያኖስ (ይሁዳ)
+ቅዱስ ማልኮስ (አድሊጦስ)
+ቅዱስ ኤሌናስ (ኢተኮስ)
+ቅዱስ አርሳጢስ (አርጣቦሉ)
+ቅዱስ አስተራቲዮስ (ሐናንያ)
+ቅዱስ አርስጦበሌስ
+ቅዱስ ጋይዮስ
+ቅዱስ አድማጥስ
+ቅዱስ ሉኪዮስ
+ቅዱስ ድዮናስዮስ
+ቅዱስ መርአንዮስ
+ቅዱስ አርክቦንዮስ
+ቅዱስ አናሲሞስ
+ቅዱስ ከርላዲስ
+ቅዱስ አኪላስ
+ቅዱስ ንኪትስ (ኢያሶን)
+ቅዱስ ቀርጶስ (ጢባርዮስ)
+ቅዱስ ክርስቶፎሮስ
+ቅዱስ ፊሊጶስ ካልዕ
+ቅዱስ ጰርኮሮስ
+ቅዱስ ኒቃሮና
+ቅዱስ ጢሞና
+ቅዱስ ጰርሚና
+ቅዱስ ኒቆላዎስ
+ወንጌላዊው ሉቃስ
+ቅዱስ ዮሴፍ
+ቅዱስ ኒቆዲሞስ
+ቅዱስ ያዕቆብ እሁሁ ለእግዚእነ
+ቅዱስ አብሮኮሮስ
+ቅዱስ ሮፎስ
+ቅዱስ እስክንድሮስ
+ቅዱስ ስልዋኖስ
+ቅዱስ ሳንቲኖስ
+ቅዱስ ኢዮስጦስ
+ቅዱስ አክዩቁ (አጋቦስ)
+ቅዱስ አፍሮዲጡ
+ቅዱስ አንሞስ
+ቅዱስ ገማልኤል
+ቅዱስ አንዲራኒቆስ
+ቅዱስ አናንያ
+ቅዱስ ድርሶቅላ
+ቅዱስ አቄላ
+ቅዱስ አጴንጤስ
+ቅዱስ አንደራኒቆስ
+ቅዱስ ዮልያል
+ቅዱስ ጰልያጦስ
+ቅዱስ መርማርያን
+ቅዱስ ኬፋ
+ቅዱስ ኡርባኖስ
+ቅዱስ ስጠክን
+ቅዱስ አጤሌን
+ቅዱስ አክሌምንጦስ
+ቅዱስ ሄሮድያኖስ
+ቅዱስ ጥርፌናስ
+ቅዱስ ጠርፌስ
+ቅዱስ አስከሪጦስ
+ቅዱስ ሉቅዮስ
+ቅዱስ ሱሲ
ቅዱሳት አንስት (፴፮/36 ናቸው)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
*ቅድስት ኤልሳቤጥ
*ቅድስት ሐና
*ቅድስት ቤርዜዳን (ቤርስት)
*ቅድስት ማርና (መልቲዳን)
*ቅድስት ሰሎሜ
*ቅድስት ማርያም መግደላዊት
*ቅድስት ማርያም እንተ እፍረት (እህተ አልዓዛር)
*ቅድስት ሐና ነቢይት
*ቅድስት ማርያም እሞሙ ለደቂቀ ዘብዴዎስ
*ቅድስት ሲፍያ (በርበራ)
*ቅድስት ዮልያና (ዮና)
*ቅድስት ሶፍያ (መርኬዛ)
*ቅድስት አውጋንያ
*ቅድስት አርሴማ
*ቅድስት ዮስቲና
*ቅድስት ጤግላ
*ቅድስት አርኒ
*ቅድስት እሌኒ
*ቅድስት ኢዮጰራቅሊያ
*ቅድስት ቴዎክላ (አሞና)
*ቅድስት ቅድስት ጲስ
*ቅድስት አላጲስ
*ቅድስት አጋጲስ
*ቅድስት እርሶንያ
*ቅድስት ጲላግያ
*ቅድስት አንጦልያ
*ቅድስት አሞን (ማርያም
*ቅድስት ኢየሉጣ
*ቅድስት መሪና
*ማርታ እህተ አልዓዛር
*የማርቆስ እናት ማርያም
*ቅድስት ሣራ (ሶፍያ)
*ቅድስት ዮሐና (ዮላና)
*ቅድስት ሶስና ናቸው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
════◉❖◉════
ሐዋርያት (፲፪/12 ናቸው)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
*ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ (ስምዖን)
*ቅዱስ እንድርያስ (የጴጥሮስ ወንድም)
*ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
*ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ
*ቅዱስ ፊሊጶስ
*ቅዱስ በርተሎሜዎስ
*ቅዱስ ቶማስ ዘህንደኬ (ዲዲሞስ)
*ቅዱስ ማቴዎስ (ቀራጭ)
*ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እማትያስ
*ቅዱስ ታዴዎስ (ልብድዮስ)
*ቅዱስ ናትናኤል (ስምዖን ቀነናዊ)
*ቅዱስ ማትያስ
ቅዱሳን አርድእት (፸፪/72 ናቸው)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
+ወንጌላዊው ማርቆስ
+ሊቀ ዲያቆናት እስጢፋኖስ
+ሐዋርያው ጳውሎስ
+ቅዱስ ጢሞቴዎስ (የጳውሎስ የመንፈስ ልጅ)
+ቅዱስ ሲላስ
+ቅዱስ በርናባስ
+ቅዱስ ቲቶ (የጳውሎስ የመንፈስ ልጅ)
+ቅዱስ ፊሊሞና (የጳውሎስ የመንፈስ ልጅ)
+ቅዱስ ቀሌምንጦስ
+ቅዱስ ዘኬዎስ
+ቅዱስ ቆርኔሌዎስ
+ቅዱስ ቴዎፍሎስ
+ቅዱስ ኤውዴዎስ
+ቅዱስ አግናቴዎስ
+ቅዱስ አናንያኖስ (ይሁዳ)
+ቅዱስ ማልኮስ (አድሊጦስ)
+ቅዱስ ኤሌናስ (ኢተኮስ)
+ቅዱስ አርሳጢስ (አርጣቦሉ)
+ቅዱስ አስተራቲዮስ (ሐናንያ)
+ቅዱስ አርስጦበሌስ
+ቅዱስ ጋይዮስ
+ቅዱስ አድማጥስ
+ቅዱስ ሉኪዮስ
+ቅዱስ ድዮናስዮስ
+ቅዱስ መርአንዮስ
+ቅዱስ አርክቦንዮስ
+ቅዱስ አናሲሞስ
+ቅዱስ ከርላዲስ
+ቅዱስ አኪላስ
+ቅዱስ ንኪትስ (ኢያሶን)
+ቅዱስ ቀርጶስ (ጢባርዮስ)
+ቅዱስ ክርስቶፎሮስ
+ቅዱስ ፊሊጶስ ካልዕ
+ቅዱስ ጰርኮሮስ
+ቅዱስ ኒቃሮና
+ቅዱስ ጢሞና
+ቅዱስ ጰርሚና
+ቅዱስ ኒቆላዎስ
+ወንጌላዊው ሉቃስ
+ቅዱስ ዮሴፍ
+ቅዱስ ኒቆዲሞስ
+ቅዱስ ያዕቆብ እሁሁ ለእግዚእነ
+ቅዱስ አብሮኮሮስ
+ቅዱስ ሮፎስ
+ቅዱስ እስክንድሮስ
+ቅዱስ ስልዋኖስ
+ቅዱስ ሳንቲኖስ
+ቅዱስ ኢዮስጦስ
+ቅዱስ አክዩቁ (አጋቦስ)
+ቅዱስ አፍሮዲጡ
+ቅዱስ አንሞስ
+ቅዱስ ገማልኤል
+ቅዱስ አንዲራኒቆስ
+ቅዱስ አናንያ
+ቅዱስ ድርሶቅላ
+ቅዱስ አቄላ
+ቅዱስ አጴንጤስ
+ቅዱስ አንደራኒቆስ
+ቅዱስ ዮልያል
+ቅዱስ ጰልያጦስ
+ቅዱስ መርማርያን
+ቅዱስ ኬፋ
+ቅዱስ ኡርባኖስ
+ቅዱስ ስጠክን
+ቅዱስ አጤሌን
+ቅዱስ አክሌምንጦስ
+ቅዱስ ሄሮድያኖስ
+ቅዱስ ጥርፌናስ
+ቅዱስ ጠርፌስ
+ቅዱስ አስከሪጦስ
+ቅዱስ ሉቅዮስ
+ቅዱስ ሱሲ
ቅዱሳት አንስት (፴፮/36 ናቸው)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
*ቅድስት ኤልሳቤጥ
*ቅድስት ሐና
*ቅድስት ቤርዜዳን (ቤርስት)
*ቅድስት ማርና (መልቲዳን)
*ቅድስት ሰሎሜ
*ቅድስት ማርያም መግደላዊት
*ቅድስት ማርያም እንተ እፍረት (እህተ አልዓዛር)
*ቅድስት ሐና ነቢይት
*ቅድስት ማርያም እሞሙ ለደቂቀ ዘብዴዎስ
*ቅድስት ሲፍያ (በርበራ)
*ቅድስት ዮልያና (ዮና)
*ቅድስት ሶፍያ (መርኬዛ)
*ቅድስት አውጋንያ
*ቅድስት አርሴማ
*ቅድስት ዮስቲና
*ቅድስት ጤግላ
*ቅድስት አርኒ
*ቅድስት እሌኒ
*ቅድስት ኢዮጰራቅሊያ
*ቅድስት ቴዎክላ (አሞና)
*ቅድስት ቅድስት ጲስ
*ቅድስት አላጲስ
*ቅድስት አጋጲስ
*ቅድስት እርሶንያ
*ቅድስት ጲላግያ
*ቅድስት አንጦልያ
*ቅድስት አሞን (ማርያም
*ቅድስት ኢየሉጣ
*ቅድስት መሪና
*ማርታ እህተ አልዓዛር
*የማርቆስ እናት ማርያም
*ቅድስት ሣራ (ሶፍያ)
*ቅድስት ዮሐና (ዮላና)
*ቅድስት ሶስና ናቸው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
════◉❖◉════
👍1
✝መልካም የ ልደት ባአል✝
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች እንኩዋን ለጌታችችን ለመዳኒታችችን ለኢየሱስ ኽርስቶስ የልደት በኣል በሰላም አደረሰን አደረሳቹ በአሉ የሰላም የፍቅር የጤና የመተሳሰብ ይሁንላቹ !!!
🌹 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
መልካም የገና በዓል ውዱ/ዷ ጓደኛዬ።
✞ እንሆ፥ለሕዝቡ፡ዅሉ፡የሚኾን፡ታላቅ፡ደስታ፡የምሥራች፡እነግራችዃለኹና፡አትፍሩ፤ዛሬ፡በዳዊት፡ከተማ፡መድኀኒት፡ርሱም፡ክርስቶስ፡ጌታ፡የኾነ፡ተወልዶላችዃልና።✝
✞ሉቃ2:14 ✞
✞ሕፃን ተወልዶልናል ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ሀያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል ✞
✞ት.ኢሳ 9.6✞
መልካም በዓል።

ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትር
ያርክየኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች በሙሉ ይህንን ፕሮፋይል በማድረግ ከቅዱስ አባታችን ጎን መሆናችንን እናሳይ ጥላቶቻቸውን እናሳፍር።
ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ሼር
ያርክየኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች በሙሉ ይህንን ፕሮፋይል በማድረግ ከቅዱስ አባታችን ጎን መሆናችንን እናሳይ ጥላቶቻቸውን እናሳፍር።
ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ሼር