✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
29.7K subscribers
90 photos
7 videos
49 links
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
➜ መዝሙር ➜የቅዱሳን ታሪኮች
➜ስብከት
✞ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ
https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen
Https://YouTube.com/tomi_8019
Https://www.tiktok.com/@tomi8019
Https://www.Instagram.com/@tomi801977
Download Telegram
ጥር 21/2016 #አስተርእዮ_ማርያም (እረፍታ ለሶልያና)

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለእናታችን #ሶልያና_ለአስተርእዮ_ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን

ሞት ለሚሞት ሰዉ ይገባዋል #የማርያም ሞት ግን
እጅግ ያስገርማል

👉 #አስተርእዮ ማለት መታየት #መገለጥ ማለት ነው ቃሉ አስተርአየ ታየ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው

👉ከጌታችን የልደት በዓል ጀምሮ እስከ ጥር መጨረሻ ያለው ጊዜ ዘመነ #አስተርእዮ በመባል ይታወቃል

👉የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር #አስተርእዮ_ማርያም ተብሏል

👉እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ /21/ በእሑድ ቀን ነብሷ ከስጋዋ ተለየች

👉ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች #ወላዲተ_አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ” "የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ" ብሏታል መኃ. ፪፥፲ /2፥10/

"ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዴት ያስገርማል
የማርያም ነገር"

👉እመቤታችን ሆይ #ሐዋርያት በሱባዔ ትንሣዔሽን ለማየት በቅተዋልና እኛም በዓለ ዕረፍትሽን አክብረን ልጅሽ በሰጠሽ ቃል ኪዳን በቀኙ እንቆም ዘንድ ለምኝልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️