ረመዳን Ramadan vibe official
141 subscribers
137 photos
7 videos
1 file
14 links
forgiveness.” “Make this Ramadan the turning point in your life. break free from the deceptions of this world and indulge into the sweetness of EEMAN.” “Don't be a servant of Ramadan be a servant of ALLAH be consistent.”

Islamic News
Daily Hadith
Download Telegram
#ይህን_ሼር_ካላረጋቹ_ምን_ልታረጉ_ነው?!
ነብዩ ሙሐመድ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ከ3000 በላይ የተዓምር (ሞዕጂዛ)ባለቤት የሆኑ ነብይ፡-
----------------------------------
☞ ሙሀመድ ጨረቃ ለሁለት የተከፈለለት ነብይ
☞ ሙሀመድ ከጣቶቹ መሃል ውሃ የፈለቀለት ነብይ
☞ ሙሀመድ የታላቁ ሙዕጂዛ የቁርአን ባለቤት የሆነ ነብይ
☞ ሙሀመድ ወደሱ ግመል እያለቀሰ በመምጣት የበደል ስሞታ
ያቀረበለት ነብይ
☞ ሙሀመድ ደረቅ እንጨት በሱ ናፍቆት ያለቀሰለት ነብይ
☞ሙሀመድ ተኩላ የአላህ መልዕክተኛ መሆኑን የመሰከረለት
ነብይ
☞ሙሀመድ ዛፍ መሬት እየቀደደች ወደሱ በመምጣት
መልዕክተኝነቱን የመሰከረችለት ነበይ
☞ ሙሀመድ በጦርነት ምክንያት የወጣችን የቀታዳን አይን
ወደቦታው የመለሰለት ነበይ
☞ ሙሀመድ የታላቁ ምልጃ ባለቤት የሆነ ነብይ
☞ ሙሀመድ የቀብር ሰዎች ዋይታ ይሰማው የነበረ ነበይ
☞ ሙሀመድ የኢስራእና የሚዕራጅ ባለቤት የሆነ ነብይ
☞ ሙሀመድ ሁሉንም አንቢያዎች በበይተል መቅዲስ ኢማም
ሆኖ ያሰገደ ነብይ
☞ ሙሀመድ ጀነትና ጀሃነምን በአይኑ ያየ ነብይ
☞ ሙሀመድ የኡሁድ ተራራ የተንቀጠቀጠለት በኋላም "ተረጋጋ"
ብለው እግሩን ሲያሳርፍበት የተረጋጋለት ነብይ
☞ ሙሀመድ ምግብ በእጃቸው ላይ ሆኖ ተስቢህ
የሚያደርግለት ነብይ
☞ ሙሀመድ ድንጋዩም ዛፉም ሰላምታ የሚያቀርብለት ነበይ
☞ ሙሀመድ እሳቸውን በመግደል ሴራ የተመረዘው ስጋ
እንዳይበሉት የተመረዘ መሆኑን በመናገር ራሱን ያጋለጠለት
ነበይ
☞ ሙሀመድ ለእርድ የቀረቡ ስድስት ግመሎች ቅድሚያ በሱ
እጅ ለመታረድ የተሽቀዳደሙለት ነብይ
☞ ሙሀመድ አይነስውር ሰውየ በነገሩት የተወሱል ዱዓ አይኑን
ያበራለት ነብይ
☞ ሙሀመድ በበድር ዘመቻ ጊዜ ከውጊያ በፊት የእያንዳንዱን
ሙሽሪክ መውደቂያ(መገደያ) ቦታ " እገሌ እዚህ ቦታ ይወድቃል
እገሌ እዚህ ቦታ ይገደላል" በማለት ቀድሞ የተናገረ በኋላም
ሳይዛነፍ እንዳለው የሆነለት ነብይ
☞ ሙሀመድ ከፊቱ እንደሚያየው ከኋላውም የሚያይ ነብይ
☞ ሙሀመድ ላቡ ከሚስክ የበለጠ መአዛ የነበረው ነብይ
☞ ሙሀመድ ለዛቱ ጥላ የሌለው ነብይ
☞ ሙሀመድ ትንሽ መጠጥና ምግብ በሱ በረካ እጅግ በርካታ
ሰውና ሰራዊት ያጠግብለት የነበረ ነብይ
☞ ሙሀመድ ድምፁ ማንም ሊያደርስበት በማይችልበት ቦታ
ላይ የሚደርስለት ነብይ
☞ ሙሀመድ በዘመቻ ላይ የመላኢካ ወታደሮች ኑስራ(እርዳታ)
የሚያደርግለት ነብይ
☞ ሙሀመድ የሱ ዳበሳ በረከት የሆነለት ነብይ (ለምሳሌ
በሀንዞላ እንደታየው)
☞ ሙሀመድ ምራቁ በረካ የሆነለት ነብይ
☞ ሙሀመድ መላ ሰውነቱ በረካ የሆነለት ነብይ አሏሁ
አክበር !!!!
እንዴት የላቀ ሙዕጂዛ ነው? ኢማሙ ሻፊዒይ እንዳሉት
« ﻣﺎ ﺃﻋﻄﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻧﺒﻴﺎ ﻣﻌﺠﺰﺓ ﺇﻻ ﻭﺃﻋﻄﻰ ﻣﺤﻤﺪﺍ ﻣﺜﻠﻬﺎ ﺃﻭ
ﺃﻛﺒﺮ ﻣﻨﻬﺎ »
«አሏህ ለማንም ነብይ ሙዕጂዛን አልሰጠም ለሙሐመድ የሱን
መሳይ ወይም ከዛ በላይ ከሰጠ በስተቀር»። ሷለሏሁ ዐለይሂ
ወሰለም
Join https://t.me/Officalramadan
Forwarded from Sawsan
አንዲት እህታችን የጡት ካንሠር በሽተኝ ናት።እኛን እስከ የውመልቂያማ ድረስ አማና ጥላብናለች፣ይሄውም ይሄንን መሴጅ ከፍቶ ያነበበ መሴጁ የደረሰው በሙሉ በአሏህ ስም ዱዓ እንድናደርግላት ጠይቃናለች።የጡት ካንሠሩ (ደረጃ4) ላይ ደርሷል፣ወደ መላው አካሏና ወደ አጥንቷ ከመሰራጨቱና ከመዳረሱ በፊት ዱዓ እንድናደርግላት ጠይቃናለች።መልእክቱን እንብባችሁ ከመዝጋታችሁ በፊት ለምታውቋቸው ሰዎች በሙሉ አስተላልፉልኝ " ብላለች።
"አማና ከባድ ነው አማና ተራራን እንኳ ያንቀጠቅጣል"።
@tewbaa
@tewbaa
@tewbas
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ አላህን ፍሩ ሙሉውን ካላነበቡ አይጀምሩት❗️❗️

አንድ ቀን ጂብሪል(ዐ.ሰ) ያለወትሮው ረሱል ሰዐወ ዘንድ ፊቱ ጠቁሮ መጣ።
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በዚህ ሁኔታ ሲያዩት ግዜ፦"አንት ጅብሪል ምነው ፊትህ እኮ ተቀየሯል?" አሉት። ጅብሪልም፦"አንተ ሙሀመድ አሁን የመጣሁበት ሰዐት አላህ(ሱ.ወ) የጀሀነም አቀጣጣዮችን እንዲያቀጣጥሏት ባዘዛቸው ሰዐት
ነው። ጀሀነም እውነት መሆኗን ላወቀ፣እሳትም እውነት መሆኗን ላወቀ፣የቀብር ቅጣት እውነት መሆኑን ላወቀ፣የአላህ ቅጣት ትልቅ መሆኑን ላመነ ሰው ከሷ መትረፉን ሳያረጋግጥ መረጋጋት የለባትም" ብሎ መለሰላቸው።
ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)፦"አንተ ጅብሪል እስቲ ስለጀሀነም ንገረኝ" አሉት።
ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦"አዎ አላህ ጀሀነምን 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ቀይ እስክትሆን ድረስ ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ነጭ እስክትሆን ድረስ ከዚያም 1ሺህ
አመታት አቀጣጠላት ጥቁር እስክትሆን ድረስ.....አሁን /ጀሀነም ጥቁር ጨለማማ ናት።ነበልባሏ እና ፍሟ አይጠፋም።
ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ.... የመርፌ ቀዳዳ ያህል ጀሀነም ብትከፈት ዱንያ ላይ ያለ ነገር ሁሉ ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር።
ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ....ከጀሀነም ሰዎች ልብስ አንዷ በሰማይና በምድር መሀከል ብትንጠለጠል ከግማቱ የተነሳ ምድር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ ይሞት ነበር።
ያ በዕውነት ነቢይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ....አላህ ቁርአን ላይ የጠቀሰው የጀሀነም ሰንሰለት አንዷ እንኳን በተራራ ላይ ብትቀመጥ ተራራው እስከ ሰባተኛው መሬት ድረስ ይቀልጣል።
ያ በዕውነት በላከህ አላህ እምላለሁ....በምዕራብ አንድ ሰውዬ በጀሀነም ቢቀጣ ኖሮ በምስራቅ ያለው ሰው ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር። ሙቀቷ ጠንካራ ነው፣ጥልቀቷ እሩቅ/ስምጥ ነው፣ጌጧ ብረት ነው፣መጠጧም የፈላ ውሀ እና ምግል ሲሆን፣ልብሷም ከእሳት የተለካ ነው። 7 በሮች አሏት።ለያንዳንዱ በር የተለያዩ በሮችም አሏቸው ለሴቶችም ለወንዶችም" ብሎ መለሰላቸው።
ረሱልም(ሰ.ዐ.ወ)፦"እኛ እንደምንጠቀመው አይነት በር ነው?"
ብለው ...ሲጠይቁት
ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦" አይ አይደለም ከላይ ወደ ታች የተደረደረ በር
ነው።ከአንደኛው በር ወደ ሌላኛው በር ያለው ርቀት 70 አመት ያስኬዳል። እያንዳንዱ በር ከሌላኛው በር ግለቱ በ70 እጥፍ ይበልጣል።የአላህ ጠላቶች ወደጀሀነም ይነዳሉ። ልክ በሯ ላይ እንደደረሱ ዘባኒያ የተባሉ የጀሀነም ወታደሮች በሰንሰለት ይቀበሏቸዋል። ሰንሰለቱን በአፋቸው አስገብተው በመቀመጫዎቻቸው ያስወጡታል። ግራ እጁ ከአንገቱ ጋር ይጠፈራል ቀኝ እጁም ከልቡ ጋር ተጠፍሮ ይታሰራል። እያንዳንዱ ሰው ከሸይጧን ቁራኛው ጋር በሰንሰለት ይጠፈራል።ከዚያምሕ
በፊቶቻቸው እየተጎተቱ መላዕክት ደግሞ ከብረት በሆነ መዶሻ ይመቷቸዋል።ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት ሲሞክሩ ወደዛው ይመልሷቸዋል"ብሎ መለሰላቸው።
ነቢያችንም(ሰ.ዐ.ወ)፦"በነዚህ በሮች የሚገቡት እነማን ናቸው?"ብለው ጠየቁት።
ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦ "በታችኛው በር የሚገቡት
1፦ሙናፊቆች
2፦በዒሳ ዐሰ ማዕድ የካዱት
3፦"የፊርዐውን ቤተሰቦች...ሲሆኑ
የ አንደኛው በሩ ስም ሀዊያ ይባለል።
ሁለተኛው በር ስሙ ጀሂም ሲሆን በሱ የሚገቡት ሙሽሪኮች ናቸው።
ሶስተኛው በር ሳብያኖች ነው የሚገቡበት ስሙም ሰቀር ይባላል።
በአራተኛው በር ኢብሊስ እና ተከታዮቹ መጁሶችም ይገቡበታል ስሙም ለዟ ይባላል።
አምስተኛው በር የሁዶች የሚገቡበት ሲሆን ስሙም ሁጠማ ይባላል።
ስድስተኛው በር ስሙ ዐዚዝ ሲሆን የሚገቡበት ክርስቲያኖች ናቸው።"ብሎ ከዘረዘረላቸው በኋላ ሰባተኛውን ለመጥቀስ ፍርሀት ያዘው።
ነቢያችንም(ሰ.ዐ.ወ)፦"ሰባተኛውን በር ለምን አትነግረኝም?" ብለው ሲጠይቁት ጂብሪልም(ዐ.ሰ)፦"በሱ በር የሚገቡት ካንተ ዑመት የሆኑ ትላልቅ ወንጀሎችን ሰርተው ሳይቶብቱ/ሳይፀፀቱ የሞቱ ናቸው" ብሎ ሲመልስላቸው ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እራሳቸውን ስተው ወደቁ። ከዚያም ጅብሪልም የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ)ጭንቅላት ታፋው ላይ አሳረፈ።ልክ ሲነቁ ቀና አሉና፦"አንተ ጅብሪል ችግሬ በዛ ሀዘኔም በረታብኝ ከኔ ኡመት ጀሀነም ሚገባ አለ እንዴ?" ብለው ሲጠይቁት ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦" አዎን ካንተ ኡመት የትላልቅ ወንጀል ባለቤቶች ይገባሉ"ብሎ መለሰላቸው፣ የዐይናችን ማረፊያ ከእናት ከአባት በላይ ለኛ አዛኝ የሆኑትም ነቢይ ይሄን ሲሰሙ ተንሰቅስቀው ማልቀስ ጀመሩ።ጅብሪልም አብሯቸው አለቀሰ።
😭😭😭😭/ፊዳከ አቢ ውኡሚ ያ ረሱለላህ/😭😭😭😭
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ይህኔ፦"ያጅብሪል አንተም ታለቅሳለክ?" አሉት ።
ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦"እንዴት አላለቅስ የኔንስ መጨረሻ በምን አውቃለሁ?
እብሊስ እኮ ከመላእክት በላይ አላህን ይገዛ ነበር አላቸው 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

ያ አሏህ ያ ረህማን ሙስሊሞች አድርገህ እንደፈጠርከን ሙስሊሞች አድርገህ ውሰደን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ይህን ሀዲስ አንተ ጋር ወይም አንቺ ጋር እንዲቀር አታድርጉ
ቢያንስ ለ 10 ሰው እንላከው

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
https://t.me/Officalramadan
#አንተ #የጥቁር #ሴት #ልጅ!“ ተብለህ ብትሰደብ፣ምላሽህ ምን ይሆናል?

🌿ቢላል(ረዐ) እንዲህ ነው የመለሰው....
በአንድ ወቅት፣ የረሱል (ሰዐወ) ባልደረቦች (ረዐ) ሰብሰብ ብለው
ረሱልን (ሰዐወ) እየጠበቁ ነበር። በወቅቱ ከነበሩት ውስጥ፣ ኻሊድ ኢብን
ወሊድ፣
አብዱራህማን ኢብን አውፍ፣ ቢላል ኢብን ረባህና አቡዘር (ረዐ)
ይገኙበታል።
ከነዚህ ውስጥ ደግሞ ቆዳው ጥቁር የሆነ ሰው #ቢላል አል ሀበሽ (ረዐ)
ብቻ ነበር። አቡዘር (በዘገባው ውስጥ ስለምን እንደሆነ በግልጽ
ስላልተቀመጠ
ጉዳይ) መናገር ይጀምርና ቢላል ደግሞ ያርመዋል። አቡዘር(ረዐ) በዚህ
ክስተት በጣም ይበሳጭና😡 “ አንተ የጥቁር ሴት ልጅ! ልታርመኝ
ትሞክራለህ?”
ሲል ያንባርቅበታል። ቢላል(ረዐ)፣ አቡዘር (ረዐ) በተናገረው ነገር
እንደተከፋ በሚያስታውቅ ሁኔታ ከተቀመጠበት ተነሳና “በአላህ
ይሁንብኝ፣ ለረሱል
(ሰዐወ) እከስሀለሁ!” ብሎ ሄደ። ሄዶም ለረሱል (ሰዐወ) ስለሆነው
ነገር ነገራቸው።

💐💐ረሱልም (ሰዐወ) በሰሙት ነበር በጣም ተበሳጩ። አቡዘር (ረዐ)
እየተቻኮለ መጥቶ ረሱልን (ሰዐወ) አገኛቸውና “አሰላሙ አለይከ ያ
ረሱሉላህ”
ይላቸዋል። (በዛ ወቅት የነበረውን ነገር አቡዘር ራሱ ሲናገር እንዲህ
ይላል)
”እጅግ በጣም ከመናደዳቸው የተነሳ፣ ለሰላምታዬ እንኳ መልስ
የሰጡኝም አይመስለኝም” ከዛም እንዲህ አሉ “አንተ አቡዘር! በእናቱ
ምክንያት (ቢላልን) አዋረድከው? #በእርግጥ አንተ የጃሂሊያ ባህሪይ
ከውስጥህ ያለ ሰው ነህ!” (ይህን ሲሉ በመስማቱ) አቡዘር (በፀፀት)
አለቀሰ!😭😭
“የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አላህ እንዲምረኝ ይለምኑልኝ!” ሲልም
ተማፀናቸው። ይህን ብሏቸው እያለቀሰ ከመስጂድ ሲወጣ፣ ቢላልን
(ረዐ)
አገኘው! (ከቢላል ፊት ለፊት) መሬት ላይ ፊቱን ደፍቶ “ቢላል ሆይ!
እግርህን አንስተህ ጭንቅላቴ ላይ እስካለደረግክ(እስካልረገጥከኝ) ድረስ ከዚህ
ቦታ አልነሳም። አንተ ክቡር ነህ፤ እኔ ደግሞ የተዋረድኩ (ትንሽ) ነኝ”
ይለዋል።
ቢላል (ረዐ) በክስተቱ በጣም በማዘኑ ማልቀስ 😥😥ይጀምራል። አጎንብሶም
የአቡዘርን ጉንጭ እየሳመ “ለአላህ (ሱወ) ሱጁድ ያደረገ ፊት ፈጽሞ
አይረገጥም፤ ይሳማል እንጂ!” ብሎታል። (ቡኻሪ ዘግበውታል)
አንድ ጊዜ ረሱል (ﷺ) አለቀሱ❗️

ሶሀቦችም፦ ያረሱል አላህ ለምን #ተገዙ (ያለቅሳሉ )የአሏህ መልክተኛ ሆይ!? በማለት ጠየቋቸዉ

ረሱል'ም (ﷺ)፦ ወንድሞቼ ናፈቁኝ አሉ

ሶሃቦችም፦ እኛ ወንድሞችህ አይደለንም እንዴ፤ ሲሉ ጠየቁ?

ረሱል'ም (ﷺ)፦ እናንተ ባልደርቦቼ ናችሁ፤ ወንድሞቼ ከኔ በኋላ የሚመጡት እኔን ሳያዩ በኔ የሚያምኑት ናቸዉ። አሉ!!!

♡ ፊዲከ ኡሚ ወሩሂ ያረሱለሏህ
ያ! ማለት ደግሞ እኔን ፣ አንተን ፣ አንቺን...
በአጠቃላይ እኛን በመናፈቅ ነው ያለቀሱት።

▪️ሳያዩን ለናፈቁን ነብይ እስቲ ሰለዋት አዉርዱ!!
▪️ያጀመዓ ሰሉ አለ ነቢ! (ﷺ)
__\\___________
ለማስታወስ ያክል
=============
ረመዳን 1 ወር ከ 20 ቀን ገደማ ነው የቀረው!
በተለያዬ ምክንያት የባለፈ አመት # ቀዷ ያለባችሁ ካላችሁ ከወዲሁ አሟሉ !!

ሌሎችንም አስታውሱ !
አላህ በሰላም ያድርሰን
https://t.me/Officalramadan
Abu Hurairah (May Allah be pleased with him) reported: The Messenger of Allah (SAW) said, "He who does not acquire knowledge with the sole intention of seeking the Pleasure of Allah but for worldly gain, will not smell the fragrance of Jannah on the Day of Resurrection."

[Abu Dawud]. (Riyad as-Salihin 1391, Book 12, Hadith 16)

Knowledge can benefit you in this world alone or in this world and the Hereafter. Make your choice and let your intention reflect that.
👉 አደራ አደራ 👈

*ይህ አብዛኞቻችን የምንፈፅመው ስህተት ነው*
አብዛኞቻችን አዛን እያለ ወሬ እናወራለን። የተከበሩት የአለማት ነብይ ሙሀመድ (ሱለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ) እንዲህ ይሉናል “አዛን ሲል ምንም ነገር መስራት አቁሙ። ቁርዐን መቅራት እንኳ ቢሆን። አዛን እያለ የሚያወራ ሰው ሲሞት የሸሀዳ ቃል አይገጥመውም
*መልዕክቱን ለወንድም እህቶቻችን ባገኘነው መንገድ እናስተላልፍ።

ለአላህ ስትሉ ቢያንስ ለ 10 ሰው ሸር አድርጉ
ከሻዕባን ወር 15'ኛው ሌሊት
(ليلة النصف من شعبان)
===================

የሚያዝን፣ የሚራራ፣ የሚምር ...." ጌታ " ባርያ መሆን ምነኛ መታደል ነው::የበዛ ዕድል፤ የማያልቅ ገፀ- በረከት ፤ሁሌ አዲስ ፤አንዱ ሲያልቅ ሌላ ኽይር ስራ.... ...!እነሆ የዛሬዋ ፀሀይ ስትጠልቅ የተከበረችው 15ኛዋ የሸዕባን ሌሊት ትጀምራለች፤ይህች ሌሊት ልዩና የተከበረች ናት::
ይህች ሌሊት ብዙ በረከትንና መልካም ስጦታን የያዘች ሌሊት ነች፣ከታቢዒዮች መሀከል ሌሊቷን በተለያዩ ዒባዳዎች ህያው አድርገው የሚያሳልፏት ነበሩ፣በዚህች ሌሊት ልዩ ደረጃ ዙሪያ የተለያዩ ነቢያዊ ሀዲሶች ተዘግበዋል፣ከነዛም መሀከል:–
①አቡ ሙሳ አል አሽዐሪይ(ረ.ዐ)እንዳስተላለፉት፤
የአላህ መልእክተኛﷺእንዲህ ብለዋል
*«إِنَّ اللَّهَ لَيَطَّلِعُ فِي لَيْلَةِ النِّصْفِ مِنْ شَعْبَانَ،*فَيَغْفِرُ لِجَمِيعِ خَلْقِهِ،*إِلَّا لِمُشْرِكٍ أَوْ مُشَاحِنٍ» *.

*رواه ابن ماجه وابن حبان وغيرهما.
قال الإمام الهيثمي في مجمع الزوائد:
"رَوَاهُ الطَّبَرَانِيُّ فِي الْكَبِيرِ وَالْأَوْسَطِ،
"በሸዕባን አጋማሽ ሌሊት ላይ በእርግጥም አሏህ በእዝነቱ (ብቅ ይልና) በሱ ላጋራና ለተጣሉ ሰዎች ሲቀር ለሁሉም ፍጡራኖቹ ማሀርታውን ይለግሳል"
ኢብኑ ማጀህ ኢብኑ ሂባንና ሌሎችም ዘግበውታል።

ኢማም ሀይሰሚይ መጅመዑ ዘዋኢድ በሚለው መፅሀፋቸው ላይ"ይህን ሀዲስ ጦበራኒይ በ"ከቢር"እን በ"አውሰጥ"የሀዲስ ጥራዛቸው ላይ ዘግበውታል፣እናም ሁሉም የሀዲሱ አቀባዮች ታማኝ ናቸውም"ብለዋል

②ሰዪደህ ዓኢሸህ(ረ.ዐ)እንዲህ ትላለች
: فقدت النبي صلى الله عليه وسلم ذات ليلة، فخرجت أطلبه، فإذا هو بالبقيع، رافعاً رأسه إلى السماء. فقال : (أكنت تخافين أن يحيف الله عليك ورسوله؟) فقلت : يا رسول الله ظننت أنك أتيت بعض نسائك.
فقال : (إن الله تبارك وتعالى ينزل ليلة النصف من شعبان إلى السماء الدنيا، فيغفر لأكثر من عدد شعر غنم بني كلب)
خرّجه الإمام أحمد والترمذي وابن ماجه .
የዛች ሌሊት የአላህ መልእክተኛንﷺ አጣዃቸውና፥ ለመፈለግ ወጣሁ፤እሳቸውም "በቂዕ" ውስጥ ራሳቸውን ወደ ሰማይ ቀና አርገው ነበር፤እንዲህም አሉኝ "አላህና መልእክተኛው ባንቺ ላይ በዳይ እንዳይሆኑ ትፈሪያለሽን?አሉኝ::እኔም" አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንዷ ባልተቤቶ ዘንድ ሄደው ይሆናል ብዬ ጠርጥሬ
ነበር"አልኳቸው::ከዛ እሳቸው እንዲህ አሉኝ "በእርግጥም በረከቱ የበዛና የላቀው አላህ በሸዕባን አጋማሽ
ሌሊት ወደ ቅርቢቷ ሰማይ–እዝነቱ–ይወርድና፣ከ"በኒ ከልብ"ጎሳ በግና ፍየሎች ቁጥር በላይ ለሆኑ ባሮቹ ይምራል)

ኢማም አህመድ፣ቱርሙዚይ፣ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል
ዐብደሏህ ቢን

③ዐምር(ረ.ዐ)እንዳስተላለፉት፣የአላህ መልእክተኛﷺእንዲህ ብለዋል፣
(إن الله ليطلع إلى خلقه ليلة النصف من شعبان، فيغفر لعباده، إلا اثنين : مشاحن، أو قاتل نفس).
وخرّجه إمام أحمد
وابن حبان في "صحيحه" من حديث معاذ، مرفوعاً.
"በሸዕባን አጋማሽ ሌሊት ላይ በእርግጥም አሏህ በእዝነቱ (ብቅ ይልና) ከተጣላና ነፍስን ከገደለ ሰው ውጪ፥ ለሁሉም ባሮቹ ማሀርታውን ይለግሳል"
ኢማም አህመድ እንዲሁም ኢብኑ ሂባን በ"ሶሂሃቸው"ከሙዐዝ ሀዲስ ወደ ሰዪዳችን ከፍ አድርገው ዘግበውታል

ስለ ሌሊቷ - ከዑለማኦች አንደበት
=======================
①ኢማሙ ሻፊዒይ(ረህመቱሏሂ ዐለይህ)
وَبَلَغَنَا أَنَّهُ كَانَ يُقَالُ : إنَّ الدُّعَاءَ يُسْتَجَابُ فِي خَمْسِ لَيَالٍ فِي لَيْلَةِ الْجُمُعَةِ, وَلَيْلَةِ الْأَضْحَى, وَلَيْلَةِ الْفِطْرِ, وَأَوَّلِ لَيْلَةٍ مِنْ رَجَبٍ, وَلَيْلَةِ النِّصْفِ مِنْ شَعْبَانَ.
በአምስት ሌሊቶች ዱዐእ ተቀባይነቱ የጎላ ነው ይባል እንደነበረ ደርሶናል::እነርሱም:–
1:የጁሙዐ ሌሊት
2:የዒደል አድሀ ሌሊት
3:የዒደል ፊጥር ሌሊት
4:የረጀብ ወር የመጀመሪያው ሌሊት
5:የሸዕባን 15 ሌሊት ናቸው
አል ኡም 1/265
🔹🔹🔹
②ኢብኑ ረጀብ አል ሀንበሊይ(ረህመቱሏሂ ዐለይህ)"ለጧኢፉል መዓሪፍ"በተባለው መፅሀፋቸው ውስጥ

(አንድ ሙዕሚን በዚህች ሌሊት ዒባዳዎች ላይ ሊጠነክር፣እንዲሁም ወንጀሉ እንዲማርና እንዲሸፈን፣ችግሮችም እንዲወገዱ ዱዐ በማድረግ ሊያሳልፈው ይገባል::ከዛ በፊት ግን በዛች ሌሊት አሏህ ወደሱ ለተመለሰ ይመለሳልና ተውበት(ወደ አሏህ መመለስን)ያስቀድም!ብለዋል::
🔹🔹🔹
③ዐጧእ ቢን የሳር(ረህመቱሏሂ ዐለይህ) በ"ለጧኢፉል መዓሪፍ" ኪታብ ላይ እንደተጠቀሰው"ከለይለተል ቀድር ቀጥሎ ከሸዕባን 15ኛው ሌሊት የምትበልጥ አንድም ሌሊት የለችም!

በዚህች ሌሊህ አሏህ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ "እዝነቱን" ያወርድና በሱ ካጋራ፣ከተጣሉና፣ዝምድና ቆራጭ ከሆኑ ሰዎች ውጪ ለሁሉም ባሮቹ ይምራል)ብለዋል።
🔹🔹🔹
④ኢማም አል ከርማኒ(ረ.ዐ)
"ኻሊድ ቢን መዕዳን፣ሉቅማን ቢን ዓሚር፣እና ሌሎችም በዚህች ሌሊት ከልብሶቻቸው ውስጥ ምርጡን ይለብሳሉ፣ሽቶን ይቀባሉ፣ኩል ይኳላሉ፣በዛች ሌሊት በመስጂድ ውስጥ እየሰገዱ ያሳልፋሉ,ኢስሃቅ ቢን ራሀወይሂም በዚህ ተግባር ላይ ገጥመዋቸዋል" መሳኢል 🔹🔹🔹
⑤ኢማም አል ቁስጠላኒ(ረ.ዐ)እንዲህ ብለዋል
"ኻሊድ ቢን መዕዳንን እና መክሁልን የመሳሰሉ፣ከሻም ሀገር የሆኑ ታቢዒዮች በሻዕባን ወር አጋማሽ ሌሊት ላይ በአምልኮ ላይ ይለፉ ነበር፣ሰዎችም ሌሊቷን ማላቅ ከነሱ ነው የያዙት"
አል መዋሂብ 2/259
🔹🔹🔹
⑥ኢብኑ ሀጀር አል ሀይሠሚይ(ረ.ዐ)እንዲህ ብለዋል:-
"ጭማቂው ይህች ሌሊት ደረጃ ያላት፣ልዩ የሆነ መሀርታና፣የዱዓእ ተቀባይነት የሚከሰትባት ሌሊት ነች"
አል ፈታወል ፊቅሂየቱል ኩብራ 3/377
🔹🔹🔹
⑦ከሀንበሊይ መዝሀብ ሊቃውንቶች ውስጥ አንዱ የሆኑት ኢማም አል በሀውቲይ(ረ.ዐ)እንዲህ ይላሉ:-
"የሸዕባን ወር አጋማሿ ሌሊትማ በውስጧ ትሩፋት አለ፣ከሰለፎች መሀከል በሌሊቷ ውስጥ የሚሰግዱ ነበሩ"
ሸርሁ ሙንተሀል ኢራዳት 2/80
🔹🔹🔹
⑧ኢብኑ ኑጀይም(ረ.ዐ)እንዲህ ይላሉ,
"ከሚወደዱ ተግባራት መሀከል የረመዷንን አስርት ሌሊቶች፤የሁለቱን ዒድ ሌሊቶች፤የዙል ሂጃ አስሩን ሌሊቶች፤የሸዕባን አጋማሽ ሌሊትን ሀዲሶች ላይ እንደተገኘው ህያው ማድረግ ነው
አል በህሩ ራኢቅ 2/56
__\\\____
እናም ይህ የተከበረ ለይል እንዳያመልጠን በዱዓ በዚክር በሶላት በቁርኣንና በተለያዩ በጎ ተግባራት እናሳልፈው::
___
በአኢማ ሚድያ እና ኮምኒኬሽን ዲፓርትመንት የተሰናዳ
3ጊዜ ፋቲሃና ያሲንን እንቅራ የመጀመሪያው እድሜያችን እንዲያረዘመዉ ሁለተኛዉ አላህ በላን እንዲመልስልን ሶስተኛዉ ከሰዉ የተብቃቃን ሊያደርገን ከዛ ዱዐ እናድርግ