❖ቅዱሱን ቁርባን ከተቀበሉ በኋላ በአፍ ውስጥ እያለ በሕሊና የሚጸልዩት ጸሎት የሚመሰክሩት ምስክርነት፣ የሚያመሰግኑት ምስጋና የሚከተለው ነው።
❖“ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ሥሉስ ዘኢይትነገር፤ ሀበኒ ከመ እንሣዕ ለሕይወት ዘንተ ሥጋ ወደመ ዘእንበለ ኩነኔ። ሀበኒ እግበር ፍሬ ዘያሠምረከ፤ ከመ አስተርኢ በስብሐቲከ፤ ወእሕየው ለከ እንዘ እገብር ዘዚአከ ፈቃደ። በተአምኖ እጼውአከ አብ ወእጼውዕ መንግሥተከ። ይትቀደስ እግዚኦ ስምከ በላዕሌነ። እስመ ኃያል አንተ እኩት ወስቡሕ፤ ወለከ ስብሐት ለዓለመ ዓለም፡፡” የሚለውን ጸልየው ይላኩት (ይዋጡት)። ትርጉሙም፦
❖“የማይመረመር ልዩ ሦስት ሳይፈረድብኝ ይህን ሥጋውን ደሙን ሕይወተ ሥጋ ሕይወተ ነፍስ ሊሆነኝ እቀበል ዘንድ መቀበሉን ፍቀድልኝ፤ ስጠኝ (አዋሕድልኝ)፤ ደስ የሚያሰኝህ ፍሬ ሃይማኖት አፈራ ዘንድ፤ ምግባረ ነፍስ እሠራ ዘንድ መሥራቱን ስጠኝ (ፍቀድልኝ)። በጎ ሥራ ሠርቼ በክብርህ ከብሬ እታይ ዘንድ (አመሠግንህ ዘንድ)፤ ሕያው ሆኜ ላንተ ምግባረ ነፍስ እየሠራሁ ምስጋና ሳቀርብ እኖር ዘንድ (አመስግኜህ እኖር ዘንድ)። አምኜ አቡነ ዘበሰማያት ብዬ እለምናለሁ (እጠራሃለሁ)። ጌትነትህንም እለምናለሁ፤ መንፈስ ቅዱስ ይምጣልኝ ብዬ (ትምጸአ መንግሥተከ ብዬ) እለምንሃለሁ። አቤቱ ስመ አምላክነትህን ግለጽልን፤ (ስመ ወላዲነትህን፥ ተወላዲነትህን፥ሠራፂነትህን ግለጽልን)። ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተህ የፈጠርክ፤ ከመኖርም ወደ አለመኖር የምታሳልፍ ኃያል ከሃሊ አንተ ነህና እኩት ስቡሕ ተብለህ ትመሰገናለህ። ላንተ ክብር ምስጋና ይገባሃል።” የሚል ነው።
❖ ቆራቢያን ቅዱሱን ቁርባን በተቀበሉ ጊዜ እጃቸውን ካፋቸው ላይ ማኖር ይኖርባቸዋል። ይህም ለጥንቃቄ፣ እንዳይነጥብ ነው። ከአፍ ያለውን ተልኮ (ቀስ በቀስ ውጦ) እስኪያበቃ ድረስ ነው። ከጥርስ፥ ከትናጋ፥ ከምላስ ተጣብቆ (ተላኮ) እንዳይቀርና እንዳይነጥብ ነው። ሥጋ ወደሙ በጥርስ አይላመጥም።
❖ቆራቢያን ሥጋውን ተቀብለው ወደ ደሙ ሲሔዱ በሕሊናቸው “ፈጽሞ ደስ ብሎኝ በነፍስ በሥጋ እንዳመሰግንህ አድርገኝ፤ መለኮት የተዋሐደውን ሥጋውን ደሙን ከመቀበሌ የተነሣ፤” ይላሉ። ደሙን ሲቀበሉ ደግሞ “እውነት ነው! ከሰማይ የወረደ የክርስቶስ ደሙ ነው፤ ይላሉ። ደሙን ከተቀበሉ በኋላ ደግሞ በሕሊናቸው የሚጸልዩት ይህ ነው “አቤቱ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በነፍስ በሥጋ ለሠራሁት ኃጢአት ማስተሠሪያ ይሆነኝ ዘንድ ንጹሕ ክቡር የሚሆን ሥጋህን ደምህን እነሆ ተቀበልሁ”። ተቀዳሚ ተከታይ የሌለህ ሰው ወዳጅ የምትሆን ወልድ ምስጋናህን እናገር ዘንድ እንዳመሰግንህ አድርገኝ። አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ሰው የሆንህ አንተ ነህና በሥጋ የተመሰገንህ (የተገለጽህ)። እስከ ዘለዓለሙ ታድነኝ ዘንድ ክቡር ጽኑ በሚሆን ስምህ ስላመንሁ (ስለተጠራሁ) አቤቱ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ላንተ ክብር ምስጋና ይገባሃል። ባገልጋይህ (በስመ ክርስትናው የገባሬ ሠራዩን ቄስ ስሙን ጠርቶ) እጅ ሥጋህን ከደምህ፤ ደምህን ከሥጋህ አንድ አድርገህ የሰጠኸኝ ከምእመናን ጋራ አንድ ታደርገኝ ዘንድ ፈጽሜ እለምንሃለሁ። በረድኤት ተቀበለኝ። የቀደመውን ኃጢአቴን አትዘከርብኝ (አታስብብኝ)፤ ይቅር በለኝ፤ የሰጠኸኝ ጸጋህን በእኔ አድራ ያለች ረድኤትህንም አመሰግናለሁ።” ይላሉ።
❖ከዚህ በኋላ ካህኑም፣ ዲያቆኑም፣ ሕዝቡም በቅብበሎሽ የሚያቀርቡት ምስጋናና ጸሎት አለ። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሚያቀርቡት ቅኔ (ክብር ይእቲ፤ እጣነ ሞገር) የሚዘምሩት ዝማሬ አለ። ሁሉም ግን ስለ ሥጋውና ደሙ ክብር በተመለከተ የሚቀርብ በመሆኑ ምሥጢሩ ምሥጢረ ሥጋዌን በተለይም ምሥጢረ ቁርባንን የሚያዘክር ነው የሚሆነው።
🌾✞ #ሠርሆተ_ሕዝብ
በሥርዓተ ቅዳሴው መጨረሻ ላይ ራሱን የቻለ የመሰናበቻ ሥርዓትና ጸሎት አለ። ቀደም ብሎም ሐዳፌ ነፍስና አንብሮተ እድ የሚባሉ ስለ ሁሉም የሚቀርቡ ጸሎታትና ምስጋናዎች ይቀርባሉ። ካህኑ የማሰናበቻውን ጸሎትና ቡራኬ ከፈጸመ በኋላ ዲያቆኑ እትዉ በሰላም ብሎ ሕዝቡን ያሰናብታል፡፡ ዲያቆኑ ከማሰናበቱ በፊት ንፍቁ ቄስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ፣ሊቃነ መላእክትን ፣ዐርባዕቱ እንስሳን ፣አርእስተ አበውን፣ መጥምቀ መለኮትን፣ ዐርባዕቱ ወንጌላዊያንን፣ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን፣ እያማፀነ በነሱ ጸሎት፣ በነሱ ምልጃ ጠብቃቸው እያለ ይለምናል፡፡ በመቀጠልም “አድንኑ አርእስቲክሙ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ፤ በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ፤” በማለት ዲያቆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑን ለቡራኬ ያዘጋጃቸዋል። ከቡራኬ በኋላም “እትዉ በሰላም፤ በሰላም ግቡ፤” ብሎ ያሰናብታቸዋል። “በሕይወት በጤንነት እሾህ ሳይወጋችሁ፥ እንቅፋት ሳይመታችሁ፤ወደ ቤታችሁ ግቡ፤” ይላል። ምሥጢሩ ግን ሥጋውን ደሙን በመቀበላችሁ ኃጢአታችሁ ተሠረየላችሁ፤ ባንድነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ግቡ፤” ማለቱ ነው። “ዕትዉ” የ “ንዑ ኃቤየ” ምሳሌ ነውና።