ኢትዮጵያዊነት
64 subscribers
282 photos
1 video
2 files
32 links
ኢትዮጰያን ምን ያህል ያውቋታል?
ኑ ስለ ኢትዮጲያዊነት እንወያይ

አርጀንቲና! ኢትዮጵያን በስም ብቻ ነው የማውቃት ነው ያልከው?እውነት ብለሃል ኢትዮጵያን በስም ብቻ ማወቅህ አይገርምም፡፡እንኳን አንተ ዜጎቿ ራሳቸው በስም ብቻ ነው የሚያውቋት፡፡........የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ!!
Download Telegram
<<ምንድን ነው የምትፈልጊው አለኝ?>>
<< ከምትወጂው ጋር መኖር ወይንስ ከሚወድሽ ጋር መኖር? >>
ጭል ጭል የምትል ለራስ የማትበቃ ፍቅር ይዞ፤ ፍቅርን መስጠት እንደሚችል ሆኖ ሲጠይቅ ...
ጥርሴን ሳልገልጥ የምፀት ፈገግ ብዬ..

<<መኖር ፤መኖር ነው የምፈልገው>>... አልኩት።
እሱ የሌለበት ደስ ሲል.. በህይወት ውስጥ ወይ መውደድ ወይ መወደድ ብቻ እንደሌለ፣ ሳልመርጥ እየወደድኩ እየተወደድኩ እኖራለሁ።


t.me/yelbenlenante
"የማያነብ ሰው ማንበብ ከማይችል ሰው ተለይቶ ሊታይ አይገባውም።" ማርክ ቱዋይን
ማንበብ ምግባርን ከመግራት አንፃር ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል ብዬ አምናለሁ።
ንባብን እንደልጓም እቆጥረዋለሁ ከስነ-ምግባር አንፃር።ባነበብከዉ ልክ ወደ ውስጥህ ትመለከታለህ።አካሄድህን ትመዝነዋለህ።ቆም ብለህ ትመለከተዋለህ።በአንፃራዊነት ምንም እንኳ በጥናት ባይደገፍም የሚያነብ ሰዉ ከማያነብ ሰዉ የተሻለ ስነምግባር እንደሚኖረው አስባለሁ።
መልካም ቀን!🙏

t.me/yelbenlenante
Good morning💖
“የሰዉ ልጅ በጣም የሚገርም ፍጡር ነዉ፡፡ ገንዘብ ለማግኘት ሲል ጤናዉን መስዋእት ያደርጋል፡፡ ከዛ መልሶ ጤናዉን ለማግኘት ያለዉን ገንዘብ በሙሉ ያፈሳል፡፡

ስለነገ በጣም ይጨነቅና ዛሬን መኖር ይረሳል ፣ ዉጤቱ ደግሞ ዛሬንም ነገንም እንዳይኖር ያደርገዋል፡፡ ሰዉ አንድም ቀን እንደማይሞት አድርጎ ይመላለሳል ነገር ግን አንድም ቀን ሳይኖር ይሞታል”

""" ዳላይ ላማ""

ስለነገ የሚያውቅ የለምና ዛሬን እራሳችንንም ሌሎችንም ደስተኛ በማድረግ እንኑራት፡፡
ውብ ቀን

t.me/yelbenlenante
#3D_ፍቅር !!

"...የግራ እጄን በቀኝ እጇ ይዛ በግራ እጇ አቅፋኛለች።
ስንራመድ ሁለት ሳይሆን አንድ እንመስላለን እቅፍቅፍ ብለን ።
ቀና ብላ ስታየኝ ጥቁር ቸኮላት የመሰለው ውብ ፊቷ ፣ በረዶ የመሰሉት ነጫጭ ጥርሶቿ ፣ ጥቁር ዞማ ፀጉሯ ፣ ሰርጎድ ብላ የምትታየው ዲምፕሏ ፣ ትላልቅና የሚያማምሩ ዐይኖቿ ... አፍንጫዋ ላይ ያለችው ጌጥ ቀጥ ሊያደርጉኝ ሲሞክሩ እየሳቀች ጉንጬን ሳም ስታደርገኝ በቁሜ እፈዛለሁ፣ እደነዝዛለሁ!!
በዛፎች የተከበበችውንና ቀዝቃዛውን ከዚራን ለፍቅራችን ማድመቂያ አደረግናት።

አብዛኛው ሰው እዚያ ስፍራ የማዘውተሩን ሚስጥር የደረስኩበት ዘግይቼ ነው።
ማታ ማታ ጥንድ ጥንድ ሆነው በሚጓዙ ፍቅረኛሞች ትደምቃለች።
ትኩስ የፍቅር መናኸሪያ ትሆናለች። ከከንፈር ላይ የማር ጠብታን የሚልሱና የሚቀምሱ የሚመስሉ ተሳሳሚዎች፣ ድምፃቸውን ገደብ አልባ በሆነ ሳቅ የሞሉባት ሳቂታዎች በርክተው የሚታዩት ማታ ነው።

በዚህ መንገድ ነበር ብዙውን ጊዜያችንን ጥብቅ'ብቅ ብለን ብዙ ሳቅና ጨዋታ የሞላውን ወሬ እያወራን የምናዘግመው!

ከሩትዬ ጋር ድሬዳዋን ደመቅንባት ... ከግንፍሌ እስከ ቅዳሜ ገበያ ...ከኮንጎ ሜዳ እስከ ደቻቱ ሳባ ዳቦ ....ከሳሬምመጋላ ....ከፍል ውሃቀፊራ ያልተጓዝንበት የለም ።

አንድ ቀን ነምበር ዋን አከባቢ የሚገኘው ፋሲካ ሆቴል ቁጭ ብለን እያወራን ተቅበጠበጠች።
የጠጠጣችው ዋይን መሆኑ አልጠፋኝም።
ሞቅ ብሏታል በዚያ ላይ የለበሰችው ወይን መሳይ ቀለም ያለው ቀሚስ ጭኗን ገለጥ አድርጎ ያሳያል።
የልብሱ አሰራር ከወገቧ ቀጠን ብሎ ሽንጧን ይዞ ዳሌዋ አከባቢ የተወጠረ የልብስ መስቀያ ይመስል ሞላ ብሏል።
ጠይም ከንፈሯን በስሱ ጥቁር የከንፈር ቀለም ተቀብታዋለች።

ምሽቷ በዚያን ሳምንት ካሳለፍናቸው የፍቅርና የፍንደቃ ጊዜያት ምርጧ ምሽት ነበረች።

"....ሙቀቱ ከላይ የለበስኩትን የመኝታ ልብስ እንዳወልቅ አስገድዶኛል።
እንግዳ መሆኔ እንደፈለኩ እንድሆንና እንዳደርግ አልተመቸኝም።

በደብዛዛው የበራችው ዜሮ አምፖል ቤቱን ጭላንጭል ብርሃን እንዲበራ አድርጋዋለች።
ቤቱ ውስጥ የተኙት አብዛኞቹ እራቁታቸውን ናቸው።

ራቁቴን እገላበጣለሁ የበላሁት ለውዝ ከሙቀቱ ጋር ተደምሮ የሆነ ቀስቃሽ ሆነውብኝ ተወጥሬያለሁ።

ውሃ ሰማያዊ የተቀባው የግድግዳ ቀለም ላይ የተሰቀሉት የተለያዩ የቤት ውስጥ ጌጣጌጦች እይታን ይማርካሉ!!

ድሬዳዋ ከቀን ይልቅ ማታ ሞቃት ናት።
ሞቃት ብቻ ናት ከምል ትግላለች ብል ሳይቀል አይቀርም።
ቀን ላይ ጭር ትላለች በተለይ ከ8:00- 10:00 ሁሉም እረፍት ያደርጋል። መቃም የፈለገ በዛፎች ወደ ተከበበችው ከዚራ ጎራ ይልና ከዛፎቹ ስር ጎዝጉዞ ይቅማል፣ ይጫወታል።

ማታ እንደ ዲምላይት ከጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ በብርሃን ትጥበረበራለች።

ሩትዬ ሁልጊዜ እጆቿን ትከሻዬ ላይ ጣል ሳታደርግ አትንቀሳቀስም።
አንድ ቀን ቁርስ ልንበላ ከመንገድ ዳር ቁጭ ብለን
ፉል በሳልሳ አዘን እስኪወጣልን ዐይኔን በስስት እየተመለከተች ጉንጬን ሳም እያደረገች እኔ እየተሽኮረመምኩ እያለ አንዱ " ዋው ስታስቀኑ! " አለ

ፊቷ እንደ ሌሊት ጨረቃ ጥርት እንደ ፀሐይ ሙቀት ሲረጭ ተሰማኝ ።
እጆቻችንን አቆላልፈን ምግቡ ሲመጣ አንዳችን ሌላውን እየተጎራረስን መንገድ ዳር የተቀመጡት ሰዎች ሁሉ ይስመርላችሁ እያሉ ይመርቁናል።
ድሬዳዋ የመንገድ ላይ ምግብ መመገድ እንደ አንድ ባህል ተደርጎ የተወሰደ ይመስላል።
ጥዋት ቀለል ያሉ ቁርሶች ...ፉል በድንች ... ፉል በእንቁላል፣ ፉል በሳልሳ ( የአከባቢው መጠሪያ ነው እኛ ጋር ስልስ በመባል ይታወቃል ቲማቲም ተቀምሞ ማለት ነው።) መሰል ምግቦች ተመራጭ ናቸው።

እራት ላይ እንዲሁ የተለያዩ ነገር ግን ድንች የሌለው ምግብ በጭራሽ አይኖርም።
ድንችን ጠዋትም ቀንም ማታም በሚመገቧቸው ምግቦች ስለማትጠፋ 3D ተብላ ትጠራለች።

ከሩትዬ ጋር ድሬዳዋን ክንፍ አውጥተን ቦረቅንባት አንድ ቀን የሆነ ቦታ ልውሰድህ አለችኝ።
እንግዳ መሆኔ ብዙ ቦታዎችን ለማየት ጉጉት አድሮብኝ እሺ ብዬ አብሬያት ሄድኩ!
ድሬደዋ ከተማን ለሁለት ሰንጥቆ የሚያልፈውን የጎርፍ መንገድ ወይም አሸዋ ሜዳ አቀናን ! ደስ ይላል በዚያው ስፍራ ያሉ ቤቶች ዙሪያቸውን በረጃጅም የኮንክሪት አጥር ታጥረዋል ለምን እንደሆነ አልጠፋኝም።

ከዚያ መልስ በድሬዳዋና ሐረር አከባቢ ከሚታወቁት ምግቦች ጣፋጮቹን እየዞርን ፈጀናቸው።

መላዋ ( በስንዴ ዱቂት አልያም በፉርኖ የሚሰራ ጣፋጭ ምግብ !
ሙሸበቅ፣ በቅላባ፣ ሀላዋ( ውስጡ ለውዝ ያለው ጣፋጭ ምግብ)
ፈጢራ (በማር የሚሰራ )
ባጊያ ይሄም በስኳርና በፉርኖ ዱቄት የሚዘጋጅ ...
ሚጣጢስ ብቻ ሁሏንሜ ጣፋጭ ምግብ የተባለ ሁሉ አልቀረንም ....እሱን ጨርሰን በኢትዮጵያ ብቸኛው የተማሪዎች ባንድ የተዘጋጀውን ሙዚቃ ታድመን ፣ ጨፍረን ... ጨረኔ ከጠረኗ ተደባልቆ ..ድክም ብለን መንገድ ላይ ስንሄድ መንገድ ላይ ሶስት ውሃ ሰማያዊ ቀለም ተቀብተው የተቀመጡ እንስራዎች አገኘን አስታውሳው እየሳቀች ይህ በእኛ አጠራር ጃህላ ይባላል እነዚህ የምታያቸው ደግሞ የተፈጥሮ ፍሪጆች ቀመባል ይታወቃሉ አለችኝ።

ከእንስራዎቹ አጠገብ ዕድሜ ጠገብ የዘንባባ ዛፎች አሉ ከውሃው ጎንጨት ስል ቅዝቃዜው ቶንሲሌን ሊቀሰቅሰው ትንሽ ቀረው።

በጉብኝታችን ወቅት ከዚራ አከባቢ የሚገኘውን ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን .... የጃንሆይን ቤተ መንግሥት!!

ልዑል ራስ መኮንን በ 1885 ዓ.ም ቆርቁረው በ 1887 ዓ.ም ቤተመንግሥቱን ሠሩ። ሁለተኛም የኢትዮጵያ መንግስት አልጋወራሽና ባለ ሙሉ ሥልጣን እንደራሴ በነበረበት ጊዜ 1914 ዓ.ም ልዑል ራስ መኮንን የሠሩትን አሻሽለው እና አስፋፍተው ተሰራ።

በሶስተኛውም ጊዜ በ 1947 ዓ.ም ልዑል ራስ መኮንን ከመሠረቱበት ቦታ ላይ የመሠረት መልኩን ሳይለወጥ ልዑል መኮንን ኃይለሥላሴ መስፍነ ሐረር ፕላኑን አሻሽሎ ባቀረበው አይነት ሁለተኛውን ፎቅ ተጨምሮበት እንዲሰራ ፈቅደው ይኸውም ሥራ 1947 ዓ.ም ተጀምሮ በ 1955 ዓ.ም ተጠናቀቀ።

ባሳለፍኳቸው ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በጣም ብዙ የተላመድኳቸው ቤተሰቦቿና አንዳንድ ጓደኞቿን መለየት እንደ ሞት ያህል ይሰማኝ ደመር።

ያንን አጉራሽ ፣ አልባሽ ፣ ሰው የሚጠግብ የማይመስለው ቤተሰቧን ጥሎ መሄድ አልቻልኩም ነገ ዛሬ እየተባልኩኝ ሁለት ቀናትን አሳልፌ በስተመጨረሻ እስከ ናዝሬት ድረስ የባቡር ቲኬት ቆረጥኩ !

እኔና ሩትዬ የምንገናኝ ቢሆንም ቤተሰቦቿንና አንዳንድ ሰዎችን ድጋሚ የማገኛቸው በፈጣሪ ፈቃድ ሴለሆነ ተላቀስን ስመው መርቀው ሸኙኝ።

ገና ባቡር ውስጥ ገብቼ እንደተቀመጥኩ ነበር እያንዳንዱ ሁነት እንደመስታወት ጥርት ብሎ መታየት የጀመረው !

ጉዞውን አብዛኞቹ በእንቅልፍ ቢገፉትም እኔ ግን የሃይማኖት ግርማን " ከዚራ ነው ቤቴ እያልኩ በትኋንና በቁንጫ እንደ ተሰቃየሁ መዳረሻ ላይ ደረስኩ !

እግሬ መሬት ቢረግጥም መንፈሴ ግን እዛው ድሬ ሩትዬ ጋር ነው።

ትዝታዎቹ ክልልል ብለው ይመጡብኛል።

ጠዋት ማታና ቀን ላይ ልክ እንደ ድንቹ 3D ፍቅሯን የምትለግሰኝ!!

ምንም እንኳን እኔ ስፅፈው ባንዛዛውም ትክክለኛውን ስለድሬ መረጃ ስለሰጠኸኝ ደጀኔ ማሙዬ አመሰግናለሁ!!!

አብርሃም ኑናቶ
💖ነግቷል ተነሱ
😏" ኤጭ_ደሞ_ነጋ!" የሚል አለ

🙏" እሰይ_ነጋ!" የሚል አለ::

ህይውት ውብ ብትሆንም ለአማራሪ ግን ፉንጋ ናት::በውስጡ የተሸከመው ጨለማ አስተሳሰብ የህይወትን የውበት ብርሃን ይጋርድበታል::
ህይወትም አትወደውም::ስለሚጠላት ትጠላዋለች::ዳሩ ግን ጠልታው ሳይሆን የሰጣትን መልሳ ስለምትሰጥ ነው::

ከህይወት በላይ ህይወትን የምትመለከቱበት መንገድ ዋና ነው::ምልከታችሁ የህይወት መነፅራችሁ ስለሆነ ተጠንቀቁ::አንድ ጊዜ ህይወትን የምትመለከቱበት መነፅር ከተበላሸ የምትመለከቱት ነገር ሁሉ ይበላሻል::
ምልከታችሁ ምን ይመስላል ? ውብ ነው ፉንጋ ? አመስጋኝ ነው ? አማራሪ ? ተስፈኛ ነው? ወይስ ጨለምተኛ?

በጣም እጅግ በጣም ተጠንቀቁ::

🌕የህይውትን በጎ ነገር የሚያጎላ የአመለካከት መነፅር ያዙ አመስግኑ ይቅርበሉ አፍቅሩ ተስፋአድርጉ ስጡ አሁን ውስጥ በደስታኑሩ ከህይወት ወንዝ ጋር ፍሰሱ::

መልካም የስራ የስኬት የደስታ ጊዜ!
t.me/yelbenlenante

💖ከሆነ ቦታ የተነበበች📚
#ዘቅጠናል በቃ እንመን !!

እኔ አንተ ሁላችን እውነትነቱ ባልተረጋገጠ ነገር ሀገር እናጫርሳለን። ለፖለቲካ ጥቅም ያውም ልንበላው ወይም ላንበላው ለምንችለው ነገር ንፁሃን ዜጎችን ደም እናፋስሳለን።

እኮ እንመን ዘቅጠናል!

ቅዱስ ቁርዓንም ሆነ መፅሐፍ ቅዱስ እንዲሁም የሌሎች ኃይማኖታዊ ማስተማሪያ መጽሐፍት (ሰይጣናዊ ካልሆኑ በቀር) የትኛውንም ኃይማኖት በማጥፋት ያንተን አስፋፋ ፣ ኃይማኖትህን አስተምር ፣ ግደል ጨፍጭፍ አይልም። እኛ ግን እያደረግነው ነው ።

እኮ ዘቅጠናል እንመን።


እኛ በፖለቲካ ፣ በኃይማኖት ፣ በብሔር ፣ በጎሳ እንናከሳለን ምስኪናን ወገኖቻችን የሚያርሱበት በሬ አጥተው ትከሻቸው እስኪላጥ ፣ መዳፋቸው እስኪገሸለጥ እየጎተቱ ሲያርሱ እኛ በለው፣ ፍለጠው ፣ አቃጥለው ወዘተ እንላለን።
ነገ የኑሮ ውድነት ተፈጠረ እያልን እናማርራለን ዛሬ ግን ጎራ ለይተን እንናከሳለን።

እኮ ዘቅጠናል እንመን ።


ነገ ከእነዚህ ሰዎች ጥቂቶቹ አሁን እያከናወኑት ባለው ነገር ( በእጃቸው ሲያርሱ ቢሞቱ ) ከእኛ በላይ አልቃሽ፣ ከእኛ በላይ ነጠላ ዘቅዛቂ የለም። ነገር ግን ዛሬ እኛ አናውቃቸውም ።

እኮ ዘቅጠናል እንመን በቃ እንመን !


አንተ የኃይማኖት ሰባኪ ነህ ...አንቺ የትልቅ ተቋም መሪ ነሽ ፣ እናንተ ባለስልጣናት ናችሁ ዛሬ ስሩ ነገ እዬዬ አትበሉ።

ይገርማል!!🤔🤔🤔🤔



እኔ አባቴን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ ቤተሰቦቼ የእሴልምና እምነት ተከታዮች ናቸው። ታድያ ማን ማንን ይግደል?

አባትህ /ሽ ባይሆን እንኳን የሆነ ዘመድሽ የሌላ ኃይማኖት ተከታይ ነው እና ልትገዳደሉ ነው?

እኮ እመነዋ ዘቅጠናል።

ለኃይማኖትህ ስትል ሌላ እየገደልክ እኔ መንግሥቱን እወርሳለሁ ፣ ስሙን አወድሳለሁ ፣ በቤቱ እሰግዳለሁ ... ሶላት አወርዳለሁ እያልክ ታስባለህ ...? ታዲያ አልዘቀጥክም ዘቅጠሃል እመን ...... !!


የሆነች ነገር ስታገኝ ኢትዮጵያዬ እያልክ ታላዝናለህ ግን በቅፅበት ረስተህ ልትንዳት/ ልታፈርሳት ዜጋዋን ታፈናቅላለህ ፤ ታቃጥላለህ ፤ ታርዳለህ እኮ ዘቅጠሃል እመን ...!!

ስማኝ ሀገርህን በደስታህ ጊዜ ብቻ አትውደዳት ፣
ችግሯንም ችግሬህ አድርገህ ተቀበል።
ኃይማኖትህም ፣ አንተም ቤተሰብህም የምትኖሩት ሀገርህ ስትኖር ነው።


ወገኔ ሌሎች ሀገራት ላይ የደረሰው የግድ እኛ ላይ መድረስ እኮ የለበትም።

ከአፍጋኒስታ ፣ ከየመን ፣ ከኢራቅ ... ከሶርያ ልንማር ይገባል።

አምላካችን ሆይ የሰይጣንን ክንፉን ሰብረህ ሀገራችንና ዜጎቿን ጠብቅልን !!


t.me/yelbenlenante
አያችሁ.... በእኔ ትውልድ ውሸት በዝቷል። የውሸት የሚመስል ፍቅር አድጎ፣ጎልምሶ፣ነጭ ጸጉር አውጥቶ አርጅቷል። ውሸቱ እውነት መስሏል። እውነተኛ ፍቅር ደግሞ እልም ብሎ እየጠፋ ነው። ግን ውሸት የፈለገውን ያህል ቢለመድ እውነትን አይሆንም። ውሸት አድጎ፣ ጎልምሶና አርጅቶ ሸበት ቢያወጣም ሽማግሌ ውሸት ይሆናል እንጂ እውነትን መሆን አይችልም።

ብዙዎች እውነት የሚመስላቸው የፍቅር ታሪክ ጠቅለል ተደርጎ ሲገለጥ እንዲህ ነው። ልጁና ልጅቷ ተገናኙ። ስልክ ተቀያየሩ። ቴከስት አደረገላት። መለሰችለት። ተገናኙ። አንድ ሁለት ቀናት ሻይ አብረው ጠጡ። ከዛም መሳሳም ጀመሩ። በሳምንቱ መጨረሻ አንሶላ ሲጋፈፉ አደሩ። ደስ ይላል አይደል? በዓለም ላይ የሚታየውን ነገር ያሳያልም አይደል? …ይሄ ነው የተለመደው አይደል?... በብዙ ትህትናና ፍቅር እላለሁ.... እኔ ግን እኔ ይህንን መጻፍ አልችልም። አይመጣልኝም። ጣቶቼ ይተሳሰራሉ። እኔ ሳዬ… ትንሽ ለየት ያለ ነገር መርጫለሁ። በእኔ ትውልድ ውስጥ እየጠፋ ያለንና የማይታይን ፍቅር አይነት ፈልጌ እያገኘሁ መተረክን ይሻለኛል ብያለሁ። የሚያምን፣ ለእኔ የማይል፣ ምክንያት የለሽ፣ ከስጋዊ ስሜት ይልቅ የነፍስ ትስስር ላይ መሰረት ያደረገ፣ አብሮ በመሆን ብቻ የሚደሰት፣ ምህረታዊ፣ ዋጋ የሚከፍል …. እውነተኛ ፍቅርን አሁንም እንዳለ ለትውልዴ ማስታወስ እፈልጋለሁ።
.
.
.

ይሄ እውነተኛ ፍቅር የት ነው ያለው?... ይሄ ፍቅር በቀደም ዜና ላይ የሰማሁት... ከ63 አመታት ጋብቻ ቡኃላ አጠገብ ለአጠገብ ተኝተው...እጅ ለእጅ ተያይዘው በደቂቃዎች ልዩነት ያሸለቡት ጥንዶች ጋር አለ። ይሄ ፍቅር እዚህ መድረክ ላይ ይታየኛል….አሁን እዚህ መድረክ ላይ የማየው ይህን ፍቅር ነው።ሌሎች ደግሞ ሳዬ ይሄ የምትጽፊው በደራሲዎች ምናብ ውስጥ እንጂ በተግባር የለም ይሉኛል። የት ነው እስኪ የሚገኘው?... ሲሉም ይጠይቁኛል…እኔም ፈገግ እላለሁ። በመጀመሪያ እኔ ደራሲ እኮ አይደለሁም። እኔ ያየሁትንና የሰማሁትን ብቻ ነው የምጽፈው። …. የት ነው የሚገኘው? ለሚለው ጥያቄ ደግሞ ቀላሉ መልስ ልባችን ውስጥ ነው። እያንዳንዳችን ጋር አለ።በልባችን ውስጥ ብንፈልገው አናጣውም። ተሸፍኖ ሊሆን ይችላል? አዎ!!! ተረስቶ ሊሆን ይችላል? በሚገባ!!!! ግን ይህ ፍቅር ከልባችን ፈጽሞ አይጠፋም። አለ። በተጨማሪም አንድ የማምነው ነገር አለ። ሁላችንም ለእውነተኛ ፍቅር ቢያንስ አንድ ጊዜ እድል ይሰጠናል። እንዴት እንደምናስተናግደው ግን የምንወስነው እኛው ነን። ምናልባት አንቺ ‘…ሰገጤ!..’ ነው የምትይው እሱ ግን ወደድኩሽ እያለ ብዙ የሚጽፍልሽ ልጅ፣… ወይንም መናገር አቅቷት ዝም ብላ አይን አይንህን የምታይህ ልጅ፣… ዛሬ ታክሲ ላይ የተዋወቀሽ ወጣት፣… ችግረኛ መስላህ ሳታያት የቀረኸው አፍቃሪህ…. እኔ እንጃ እኔ አላውቅም … ነገር ግን እውነተኛ ፍቅር በሆነ ሰው ከሆነ ስፍራ ላይ በሩን ያንኳኳል። የፍቅርን ድምጽ አድምጦ በሩን መክፈት የኛ ስራ ነው። እኛ ልባችንን ከከፈትንና በስፍራችን ላይ ከተገኘን እውነተኛ ፍቅር ትላንትም ነበረ። ዛሬም አለ። ወደፊትም ይኖራል። በቦታችን ላይ ያልተገኘነው እኛ ነን … ውዶች ።
.
.
.❤️❤️❤️❤️❤️❤️

ጠብቅሻለሁ

t.me/yelbenlenante
አሜሪካዊው ቢሊዬነር ስቲቭ ጆብስ በህይወቱ መጨረሻ ሰዓት ላይ ያስተላለፈው
አስደናቂ መልዕክት፦ ስቲቭ ጆብስ በ56 አመቱ ያረፈ አሜሪካዊ ቢሊዬነር ሲሆን
ህይወቱ ያለፈው በካንሰር በሽታ ነው፡ በንግዱ አለም ውስጥ የመጨረሻ ከፍታ
ጫፍ የሚባለው ቦታ ደርሻለሁ፣ ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ ሀብት ደስታን ማግኘት
አልቻልኩም። በልፋቴ ካከማቸሁት ሃብት ያገኘሁት ደስታ እዚህ ግባ የማይባል
ነው። አሁን በህይወቴ የመጨረሻው ሰዓት አካባቢ አልጋ ላይ ሆኜ ያሳለፍኩትን
ነገር ሁሉ ወደሗላ ሳስበው፤ እኮራበት የነበረው ሀብቴና ዝናዬ ከንቱ እና ትርጉም
አልባ እንደሆነ ተረድቻለሁ።
~አንድን ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባልህ
ልትቀጥረው ትችላለህ፤ እየተሰቃየህበት ያለውን ህመም እንዲሸከምልህ ግን
ልትቀጥረው አትችልም፡፡ -ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ፣ ዳግም
ሊገኙም ይችላሉ፤ አንድ ጊዜ ካመለጠ ደግመህ ልታገኘው የማትችለው አንድ
ነገር ግን አለ. እርሱም # ህይወትህ ነው!! ~አንድ ሰው የቀዶ ጥገና
ወደሚደረግለት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው አንድ መጽሃፍ ትዝ ቢለው
የመጽሐፉ ርዕስ "ጤናማ ህይወት የመኖር ሚስጥር" የሚል ሊሆን እንደሚችል
ጥርጥር የለውም። -በየትኛውም የህይወት ከፍታ ላይ ብንሆን የህይወታችን
መጋረጃ የሚዘጋበትን ቅጽበት ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት አንድ ቀን መምጣቱ
አይቀርም። -ለቤተሰብህ፣ ለትዳር አጋርህ እና ለጏደኞችህ የፍቅርን ውርስ
አስቀምጥላቸው። -ራስህን ተንከባከብ ፣ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት
ይኑርህ።
-እያደግን ስንሄድና የህይወት ትርጉሙ ሲገባን ውድ ሰዓትም አሰርን ርካሽ ሰዓት
፣ ሁለቱም የሚነግሩን ጊዜ እኩል መሆኑ ይገባናል፡ -በኪሳችን ውድ ቦርሳም
ያዝን ርካሽ ቦርሳ፣ በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም። -
የአንድ ሚሊዮን ብር መኪናም ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና ፣የመንገዱ
ርዝመት አይቀየርም፤ አቅጣጫውም ያው አንድ ነው፥ የምንደርሰውም ያው
እዚያው ቦታ ነው። -ውድ መጠጥም ጠጣን ርካሽ መጠጥ፣ ስካሩና አድሮ
የሚያመጣው ራስ ምታት ለውጥ የለውም። -ሰፊ ግቢ ውስጥ ኖርንም ጠባብ
ቤት፣ ብቸኝነቱ ያው እኩል ነው፡፡ የውስጥ ደስታ በቁሳቁስ እንደማይገኝ ያን ጊዜ
ይገባሃል። ~አውሮፕላን ላይ የክብር ቦታም ተቀመጥክ ወይም ተራ ቦታ
አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ እኩል ቁልቁል ትወርዳለህ። | እውነተኛው ደስታ
የሚገኘው ከቤተሰብህ፣ ከጓደኞችህ፣ ከዘመዶችህ ጋር በሚኖርህ ውብ ጊዜኣት
ብቻ ነው፡፡ ከእነርሱ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ፣ በምትጫወተው ጨዋታ፣
በምትዘምረው መዝሙር፣ በምትስቀው ሳቅ እውነተኛ ደስታን ታገኛለህ።
5 ሊካዱ የማይችሉ የህይወት እውነታዎች አሉ ~ልጆችህ ሀብታም እንዲሆኑ
አታስተምራቸው፥ ይልቅ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ አስተምራቸው።
ሲያድጉ የነገሮች ዋጋ ሳይሆን ጥቅማቸው ይገባቸዋል። ~ምግብህን እንደ
መድሃኒት ውሰድ ካልሆነ መድሃኒት እንደምግብ ትወስዳልህ፡፡ -የሚወድህ ሰው
በቀላሉ አይለይህም፣ ከኣንተ ለመለየት 99 ምክንያት ቢኖረው እንኳ መለየት
በማይችልባት አንዲት ነገር ላይ ፀንቶ ይቆማል። - ሰው ሆኖ በመፈጠርና "ሰው
በመሆን" መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፥ ይህ የሚገባቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው። -
ስትወለድ ውድ ነበርክ፣ ስትሞትም ውድ ትሆናለህ፣ በመካከል ያለውን
ማስተካከል ያንተ ፋንታ ነው። -በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ ሩቅ
ለመድረስ ከፈለግህ ግን ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ

ምንጭ ፦ ከመፅሐፍ ገፆች

t.me/yelbenlenante
http://m.dewstalk.top/ccd9QUhhc2BGWFNWAwsCVFcpDnIwfmcOZFpyTCMzJDZSDCEyUT0aIg4aMiEzDRtbFwEPPA9HYw08QU0HFQo9D0MORRkAVBdfWSws&p=eqpstg&_mi1675396607853




ወገን ይሄ ነገር እውነት ነው እንዴ እውነት ከሆነ ለምን እናንተስ ይቅርባችሁ ወዳጆቼ ብዬ ይዤላችሁ መጣሁ! እውነት ከሆነ ይቅናችሁ!!
#ፈጣን_ገዢ_ይፈለጋል !!

አያት ሁለት አከባቢ ያለ ኮንዶሚኒየም
ዋጋው 6.8 ሚሊዮን ብር ... የተወሰነ መደራደሪያ
72 ካሬ ባለ 2 መኝታ
5ኛ ፎቅ
ውሃና መብራት ...ኪችን ካቢኔት የለውም።
ሊፍት አለው !!

ብሩ ለአስቸኳይ ነገር ተፈልጎ ነው።

+251972557950
+251 95 478 7835 ይደውሉ !!
#ራስን_የማዳን_ልምምድ !!

ራስን ​ማዳን አስተሳሰብ አይደለም። ልምምድ እንጂ!
​የመጀመሪያው ውሸት "አንድ ሰው መጥቶ ያድነኛል።" ሲሆን ሁለተኛው ውሸት ግን የተለየ ነው "ነገሮች ሲረጋጉ ራሴን ማዳን እጀምራለሁ።"
​ይህ ሁለተኛው ውሸት ብልህ ሰዎችን እንኳን ለዓመታት ባለበት እንዲረግጡ ያደርጋቸዋል። ምክንያቱም ህይወት አትረጋጋም። አለባበሷን ትቀይራለች እንጂ። "መረጋጋትን" ጠብቀህ ኃላፊነት ለመውሰድ የምትሞክር ከሆነ ዓለም ለማይሰጥህ ፈቃድ እየተጠባበቅህ ነው።
​ እውነታው ይህ ነው። ራስን ማዳን አስተሳሰብ አይደለም። ተግባራዊ ልምምድ ነው።

በሱስ ​አብዛኛው ሰው ጥገኛ መሆን ፈልጎ አይደለም። ነገር ግን "እፎይታ" ለማግኘት ሱስ ውስጥ ይዘፈቃሉ። እፎይታ ሽልማታቸው ይሆናል።
​ዕዳ ሲከፈልላቸው እፎይ ይላሉ።
​ችግሩ ሲወገድላቸው እፎይ ይላሉ።
ሰው ነገሮችን ሲያቀላጥፍላቸው እፎይ ይላሉ።
​ከዚያም አእምሮህ እንዲህ ብሎ ይለምዳል፦ "ባጋጠመኝ ቁጥር ለሌላ ሰው አሳልፌ እሰጣለሁ።" ይህ ደግሞ የህይወትህ መመርያ ይሆናል። ደካማ ስለሆንክ ሳይሆን ራስህን ስላሰለጠንከው ነው። የሰለጠንክበትን ደግሞ ትደጋግመዋለህ።
​"በሌላ ሰው መታገዝ" የሚያስከፍለው እውነተኛ ዋጋ
​ማንም ሰው ጮክ ብሎ የማይናገረው እውነት እዚህ አለ። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች አንተን "የሚያድኑህ" አንተን ትንሽ አድርገው ለማስቀረት ነው። ይህን የሚያደርጉት ሁልጊዜ በክፋት ሳይሆን ባለማወቅ ሊሆን ይችላል። አንተ ሁልጊዜ እርዳታ የምትፈልግ ሰው ሆነህ ከቀጠልክ ለእነሱ የሚከተሉትን ሚናዎች ይሰጣቸዋል።
​ጀግናው!
​ችግር ፈቺው!
​አቅራቢው!
​ተቆጣጣሪው!
​ስለዚህ ማዳኑ ለጋስነት ቢመስልም የማይታዩ ሰንሰለቶች አሉት።
​ለእነሱ ስሜታዊ ታዛዥነት ይኖርብሃል።
​እንዳታሳዝናቸው በመስጋት ውስጥ ትኖራለህ።
​ይህን ዝግጅት ሊያፈርሱ የሚችሉ እርምጃዎችን ከመውሰድ ትቆጠባለህ።
​ነፃነትህን በምቾት ትለውጣለህ። ​ምቾት ግን ውድ ነው። የህይወትን ሰላላ ያሳጣሃል።
​ራስን ማዳን ማለት "ብቻን መሆን" ማለት አይደለም።
​አንድ ነገር ግልጽ ይሁን ራስን ማዳን ማለት መገለል ማለት አይደለም። ባለቤትነት ማለት ነው።
​በእነዚህ ሁለት ነገሮች መካከል ልዩነት አለ።
​ድጋፍ እንድታድግ ይረዳሃል። "ስርዓቱን እንድትገነባ እረዳሃለሁ" ይላል።
​ማዳን ባለህበት እንድትቀጥል ያደርግሃል። "እንዳትቀየር እኔ እጨርሰዋለሁ" ይላል።
​አንዱ አቅምን ይፈጥራል። ሌላኛው ግን ጥገኝነትን። እርዳታ መቀበል ትችላለህ። ነገር ግን ያ እርዳታ ሲወገድ የበለጠ ጠንካራ የሚያደርግህ ከሆነ ብቻ ነው።
​የ72 ሰዓት ራስን የማዳን ዝግጅት
​ይህ ነገር እንዲሳካ ከፈለግህ የሚከተሉትን አድርግ።
​ደረጃ 1  ማዕበሉን ስም ስጠው። (የሚያስቸግርህን ነገር ማለት ነው።)
ያለ ድራማ በአንድ አረፍተ ነገር ብቻ ጻፈው።
​"የቤት ኪራይ ከፍዬ አላውቅም። ችግሩን ግን እየሸሸሁት ነው።"
​"ስራዬን እጠላዋለሁ። ማታ ማታ ግን በሌላ ነገር ራሴን እያደነዘዝኩ ነው።"
​"ጤናዬ እየተጓደለ ነው። እኔ ግን ደህና እንደሆንኩ እያስመስልኩ ነው።"
​ደረጃ 2  የመቆጣጠሪያ ነጥብህን ምረጥ።
ጠይቅ "ከዚህ ውስጥ የትኛው ክፍል ነው በእርግጥ የእኔ የሆነው? ፍትሃዊ ነው አይደለም የሚለውን ተወው። እኔ ምን መቆጣጠር እችላለሁ?"
​ደረጃ 3  ትንሿን ሊቀለበስ የማይችል እርምጃ ውሰድ።
እቅድ አይደለም። ጥናት አይደለም። ስልክህ ላይ የሚጻፍ ማስታወሻም አይደለም። እውነታን የሚፈጥር ተግባር እንጂ።
​ከፊል ክፍያ መክፈል።
​ያንን ምቾት የማይሰጥ ኢሜይል መላክ።
​ቀጠሮ ማስያዝ።
​ያማረረህን ነገር መሰረዝ።
​ደረጃ 4 ገደብ ፍጠር።
ገደብ ማለት የፍላጎት ኃይልን የሚተካ ነገር ነው።
​በየቀኑ የተወሰነ ገንዘብ ወደ ቁጠባ አካውንት በራሱ ጊዜ እንዲዘዋወር ማድረግ።
​ያንን የሚያዘናጋ መተግበሪያ መቆለፍ።
​ቀጣዩን እርምጃ በጊዜ ሰሌዳህ ላይ ማስፈር።
​ደረጃ 5 ማስረጃ አምጣ።
ማስረጃ ማለት አሮጌውን ማንነት የሚገድል ነው። "እየሞከርኩ ነው" ማለት አይሰራም። ማስረጃ ብቻ!
ትንሽም ቢሆን...!
​አንድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት።
​አንድ የሽያጭ ጥሪ ማድረግ።
​አንድ ጽሑፍ ማውጣት።
​አንድ ጤናማ ምግብ መመገብ።
​በ72 ሰዓታት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መለወጥ አይጠበቅብህም። መሪው በእጅህ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ብቻ ነው የሚያስፈልግህ።
          ​ራስን የማዳን ውል!
​ይህንን በዝግታ አንብብና ዝግጁ መሆንህን ወስን።
​ለመዘጋጀት ስሜት አልጠብቅም።
​መረባበሽን ከማይቻል ነገር ጋር አላደባልቅም።
​ድጋፍን እቀበላለሁ። ግን ኃላፊነትን ለሌላ አሳልፌ አልሰጥም።
​ከኋላ ጸጸት ይልቅ አሁን ያለውን ምቾት ማጣት እመርጣለሁ።
​ጡንቻዬን እገነባለሁ እንጂ ጊዜያዊ እፎይታን አላሳድድም።
​ሁሉንም ነገር የሚያጋልጡ ጥያቄዎች
​የት ጋር ነው ኃላፊነት ለመውሰድ "ተቃርቤ" የምተወው?
​መፍትሄው ማንነቴን ስለሚቀይረው ደጋግሜ የምዞረው ችግር የትኛው ነው?
​ባለሁበት ብቀጥል ማን ይጠቀማል?
​አሁን በምስጢር ምን አይነት "መዳን" ነው እየተመኘሁ ያለሁት?
​ማንም እንደማይመጣ ባውቅ ኖሮ ዛሬ ምን አደርግ ነበር?
​ታማኝ ሁን። ከዚያም አንዲት ሊቀለበስ የማይችል እርምጃ ውሰድ። ምክንያቱም መጠበቅን ስታቆም ህይወትህ አንተን መስማት ትጀምራለች። አንዴ ራስህን ማዳን ከለመድክ... ገመድ መፈለግህን ታቆማለህ። ጀልባ መገንባት ትጀምራለህ።


ቀጥታ ትርጉም :- አብርሃም ኑናቶ

t.me/yelbenlenante