Natural and Social Science Department G-12ABC
373 subscribers
296 photos
7 videos
199 files
51 links
🎯AIM 🎯

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫

➥To create a modern and online study community
.
.
.

➥Description box
➽Home and Assignment Reminder
➽Motivational Speech's
➽Exam and Study Tips
➽YouTube video's
➽Announcement's
Download Telegram
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
Natural and Social Science Department G-12ABC
Video
To those Who want more information about this website you can go and check their telegram channel:
https://t.me/etemari_net
Forwarded from Addis Ababa Education Bureau (Abebe Chernet)
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ

(ቀን ሚያዚያ 21/ 2016 ዓ.ም) የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ወይም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (ኦን ላይን) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30 እና ሐምሌ 01/2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6 እና 7/2016 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ኤጀንሲ አሳውቋል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይን) ከሚሰጥባቸው ከተሞች አንዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስለመሆኑ ተሰምቷል።

ይህን ተከትሎ የፈተና ቅድመ ዝግጅት ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ሲካሄድ ውሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፤ " የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በከተማው በኦንላይን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው " ብለዋል።

ለፈተናው ኮምፒዩተሮች፣ ላፕቶፖችና ታብሌቶችን ጨምሮ ሌሎች ግብአቶችን የማሟላት ስራ ተጀምሯል ተብሏል።

የግል ትምህርት ቤቶች ለፈተናው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ከወዲሁ እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

ሙሉ በሙሉ ፈተናው በኦንላይን ባይሰጥም  በተመረጡ ከተሞች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቀሩት ተማሪዎች በተለመደው ሁኔታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በወረቀት ይፈተናሉ።

እስካሁን በየትኞቹ ከተሞች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን ይወስዳሉ የሚለው አይታወቅም። በምን አግባብ ተማሪዎቹ እንደሚመረጡም ለጊዜው በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
" የኦንላይን ፈተናው በተመረጡ 25 ከተሞች ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ 25 ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ገልጿል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በኦንላይን ለሚሰጠው ፈተና እንዲዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከሁሉም ክልሎች በተመረጡ 25 ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በወረቀት ከሚሰጠው ፈተና ጎን ለጎን የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው #ቤተሰቦቻቸው_ጋር_እያደሩ ፈተናውን ይወስዳሉ ሲሉ አሳውቀዋል።

ወ/ሮ አየለች ፤ ተማሪዎች ለፈተናው እንዲዘጋጁ፣ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ፣ ወላጆችንም ልጆቻቸውን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ፈተናው በኦንላይን የሚሰጥባቸውን 25 ከተሞች በዝርዝር ይፋ አላደረገም።

የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
Eng. Short Note
⭐️ለአዲስ አበባ (6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ) ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች አጭር መረጃ

የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 4-5/10/2016 ዓ.ም ይሰጣል(ፈተናው የ8ኛ ክፍልን ብቻ ይሸፍናል)

የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ  12-14/10/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል!!(ፈተናው የ6ኛ ክፍልን ብቻ ይሸፍናል)

⭐️ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በአዲስ አበባ   በበይነ መረብ (Online) ብቻ
በተመረጡ ት/ቤቶች ይሰጣል::

የ12ኛ ክፍል(Social )ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም በተመረጡ ት/ቤቶች  ይሰጣል::
(ፈተናው ከ9ኛ-11ኛ ክፍል  በነባሩ ስርዓተ ት/ት(ከኢኮኖሚክስ በስተቀር ) እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርዓተ ት/ት እንዲሁም ኢኮኖሚክስ በአዲሱ ስርዓተ ት/ት ይሸፍናል

የ12ኛ ክፍል(ተፈጥሮ ሳይንስl)ፈተና ከሐምሌ  9-11/2016 ዓ/ም
በተመረጡ ት/ቤቶች   የሚሰጥ   ይሆናል(ፈተናው ከ9ኛ-11ኛ በነባሩ ስርዓተ ት/ት እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርዓተ ት/ት ይሸፍናል

⭐️ተማሪዎች ይህንን መረጃ መሰረት በማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጉ::

ለሌሎች ሸር እናድርግ!!
👇👇👇👇👇👇👇👇

📌Join and share 👇👇👇
             ✳️  @Ethio600   🎯
             ✳️  @Ethio600   🎯
Please have hard copy of this short note.
Note update🚨

Englis
Exam Main Points
M.r Tesfay

@NSSD2024