Natural and Social Science Department G-12ABC
373 subscribers
296 photos
7 videos
199 files
51 links
🎯AIM 🎯

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫

➥To create a modern and online study community
.
.
.

➥Description box
➽Home and Assignment Reminder
➽Motivational Speech's
➽Exam and Study Tips
➽YouTube video's
➽Announcement's
Download Telegram
ጥቂት ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች
~
ትምህርት እየተጀመረ ነው። ፈተና ሲደርስ መደናበር ወይም የአመቱ መጨረሻ ላይ ውጤትን ጭንቅ ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ምንም ፋይዳ የለውም። ይልቁንም በየትኛውም ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎች ከቀን አንድ ጀምረው በቁም ነገር መዘጋጀት ነው የሚያዋጣው። ከልቡ የተዘጋጀ ሰው በአላህ ፈቃድ የልፋቱን አያጣም። ጥሮ ግሮ ውጤት ባይመጣ እንኳ ሰበብ ያደረሰ ሰው የሚጠበቅበትን ተወጥቷል።
ይህን እንደ መግቢያ ካልኩኝ ለተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የተሻለ ስብእና እንዲኖራቸው ያግዛሉ ያልኳቸውን የተወሰኑ ነጥቦት እንደሚከተለው አስፍሬያለሁና በማሰራጨት ብታግዙኝ ደስ ይለኛል።

① መምህርህን አክብር። አስተማሪህ ለደሞዝ ቢሰራም ላንተ ውለታ እየዋለ ነው። ኋላ ከሚፀፅትህ ዛሬ ለአስተማሪህ ትሁት ሁን። እድሜውንም አክብር። የሚያስተምርህን መናቅ የሚያጎርስህን መንከስ ነው። እንዲያዝንብህ፣ "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" እንዲል አታድርገው። ውለታ ይግባህ። የወጣትነት ስሜት ድፍን ቅል አያድርግህ።
"አስተማሪን መናቅ እውቀትን መናቅ ነው።"
"ለእውቀት ያለህ ክብር መጠኑ ለአስተማሪህ ባለህ ክብር ልክ ነው።"

② ተባባሪ ሁን። እንዳቅምህ የምታግዛቸው በርካታ ደካማ ተማሪዎች በዙሪያህ አሉ። የእለት ጉርስ የሚጎድላቸው፤ የደንብ ልብስ አቀበት የሆነባቸው፤ የሳሙና፣ የኮፒ፣ የታክሲ፣ የቤት ኪራይ፣ የህክምና፣ የደብተር፣ … የሚቸግራቸው፤ ብዙ ናቸው። ቢቻል አስተባብራችሁ የተቀናጀ ስራ ስሩ። ካልሆነ የራስህን ሐላፊነት ተወጣ። ደካማ ተማሪዎችን አስጠና፣ አግዝ። በዱንያ እርካታን ታገኝበታለህ። ልምድን ትቀስምበታለህ። ህይወትን ትማርበታለህ። በኣኺራ እጥፍ ድርብ ትሸለምበታለህ።

③ ከመንደሬነት ራቅ። የሰፈር፣ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የአካባቢ ብሽሽቅ ውስጥ አትግባ። ዘረኝነትን በየትኛውም መልኩ ተፀየፍ። ዘረኞችንም ከቻልክ ምከር። ካልሆነ አፍንጫህን ይዘህ ሽሻቸው። በዘርህ ከማንም በላይም፣ ከማንም በታችም አይደለህም። ለዘር ተኮር ቀልዶች ጥርስህን አታሳይ። ሌሎችን በዘር አትውጋ። በዘር ለሚተነኩስህም ንቀህ እለፍ እንጂ እሳት ጎርሰህ አትነሳ። የማንም ሙገሳ ከፍ እንደማያደርግህ ሁሉ የማንም ትችትም ዝቅ አያደግህም። ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ለራስህ ሹክ በለው።
"ዘረኝነት ጥንብ ሲሆን ዘረኛ ደግሞ ጥንብ አንሳ ነው።"

④ ለዲንህ ጊዜ ስጥ። አንተ ያለ ዲንህ ባዶ ነህ። ያለ ዲን ስኬትም ስኬት፣ ህይወትም ህይወት አይደለም። ስለ ዲንህ ስትማር ክፍል ውስጥ ዲንህን አታስነካም። የተሳሳተ ቲዎሪ አያነቃንቅህም። ውሎህ በፕሮግራም ይሆናል። ሕይወትህ ጣእም ይኖረዋል። ስለዚህ ቁርኣን ቅራ። አስቀራ። ኪታብ ተማር። አስተምር። ደዕዋ ሞክር። ሶላት ስገድ። ስታልፍ ስታገድም ዚክርህን አድርግ። ዲንህን በራስህ ላይ አንፀባርቅ። ዲንህ የሚወራ ሳይሆን የሚንኖር ነው።
"ዲንህ ህይወትህ ነው። ዲንህ ከሌለ አንተ እራስህ የለህም።"

⑤ በትምህርትህ ላይ ሃላፊነት ይሰማህ። ቤተሰብ የላከህ ለዋዛ አይደለም። ገንዘቡም፣ ጊዜውም፣ ድካሙም ዋጋ አይጣ። ስለዚህ በወጉ ተማር። ክፍል ውስጥ በሚገባ ተከታተል። ንቁ ተሳትፎ ይኑርህ። በሚገባ አጥና ። ስንፍናን አትቀበል። "አልችልምን" አርቅ ። ኩረጃን፣ ጥገኝነትን ተፀየፍ። በጥረትህ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ወኔ ይኑርህ። አትጠራጠር! ስትጥር ዛሬ ካለህበት የተሻለ ትሆናለህ። ባለ መጣሩ እንደ ሰነፍ የሚታይ፣ ራሱን የማያውቅ ስንት ባለ ብሩህ አእምሮ አለ?! መማርህ ካንተ አልፎ ለወገን የሚተርፍ ዋጋ ሊኖረው እንደሚችል ተረዳ።
"Education is a better safeguard of liberty than a standing army."

⑥ ራስህን ሁን። የመጣውን ፋሺን ሁሉ ካልሞከርኩ አትበል። ለራስህ ክብር ስጥ። አንተ የማስታወቂያ አሻንጉሊት አይደለህም። አርአያህን ለይ። መልካም ስብእና ያላቸውን እንጂ፣ ያለ ቁም ነገር ስማቸው የገነነ ሰዎችን ለመምሰል አትፍሰስ። አንተ ህሊና የተሰጠህ ክቡር ፍጡር እንጂ በቀደዱለት የሚፈስ የቦይ ውሃ አይደለህም።
"ራሱን ያላገኘ ሌሎችን ሲከተል ይኖራል።"

⑦ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም። አንተ ዘንድ አላህ ከሰጠህ ሃብት ሁሉ ርካሹ ጊዜህ የሆነ'ለት ያለ ጥርጥር ከስረሀል። ወደ ጨለማ ጥግ ከሚያደርስ የድንግዝግዝ ባቡር ላይ ተሳፍረሀል።
እባክህን ሕይወትህ ላይ አንዳች እሴት በማይጨምሩ ነገሮች ዳግም የማታገኘው ውድ ጊዜህን አታባክን። የምልህ እየገባህ ከሆነ በሙዚቃ ከመመሰጥ፣ ፊልም ጋር ከመርመጥመጥ፣ የፈረንጅ እርግጫ ከማሳደድና መሰል አልባሌ ነገሮችን ራቅ እያልኩህ ነው። እነዚህ ነገሮች ከእለት መዝናኛነት ባለፈ ተሻጋሪ ሱስ የሚሆኑ ወጥመዶች ናቸው።
"ጊዜ ሰይፍ ነው። ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል።"
"አንተ የጊዜያት ድምር እንጂ ሌላ አይደለህም። እያንዳንዷ የጊዜ ክፍልፋይ ስታልፍ አንተ ራስህ እያለፍክ ነው።"

⑧ ጓደኞችህን ለይ። ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም። እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀል። አልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ ራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ። ጓደኝነታችሁ የምትጠቀሙበት እንጂ የምትጎዱበት እንዳይሆን በስርኣት ተመካከሩ።
"ሰው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከት።"

⑨ መልካም ስነ ምግባርን ተላበስ። አትሸማቀቅ፤ ግን አትኮፈስ። ትሁት ሁን፤ ግን አትልፈስፈስ። ሰከን በል፤ ግን አትፍዘዝ። ረጋ በል፤ አትንጣጣ። ከአንደበትህ ክፉ አይውጣ።
ፊትህ ሁሌ በፈገግታ ይታጀብ። ተግባቢና ለሰዎች ቀላል ሁን። የደረስክበትን ሁሉ በሰላምታ አውደው። በትህትና አጊጥ። በቅንነት አሸብርቅ። "መጣብን" ሳይሆን "መጣልን" የምትባል ሁን። አታጣላ። አታባላ። ሃሜትና ውሸትን ክላ።
"ህዝብ ማለት ስነ ምግባር ነው። ስነ ምግባር የሌለው ህዝብ ካለ አይቆጠርም።"

(10) በትምህርት ሕይወትህ ላይ ሳለህ መዝናኛህን ቁም ነገር መጨበጫ አድርገው። ቁም ነገር አዘል መፃህፍትን አንብብ። ከቻልክ እንደ የመጀመሪያ እርዳታ /first aid/ አሰጣጥ፣ ቴኳንዶ፣ የእጅ ሙያዎች፣ የችግኝ ወይም የጓሮ አትክልት አተካከል፣ እና መሰል ጠቃሚ ስልጠናዎችን ሰልጥን፣ አሰልጥን። አካባቢህን አስተባብረህ አፅዳ።
"ራስን ብቁ ዜጋ ማድረግ ለሀገርም ለወገንም እሴት መጨመር ነው።"

(11) ከህገ ወጥ ፆታዊ ግንኙነት አጥብቀህ ራቅ። ህጋዊ በሆነ መልኩ ተረጋግተህ ለምትደርስበት ነገር በህገ ወጥ መልኩ ለማግኘት እየቸኮልክ ስብእናህን አታቆሽሽ። የሌላን ህይወትም አታበላሽ። ከአላማህም አትሰናከል። ክፉ ምሳሌም አትሁን።
"ስድ ግንኙነት ለህሊና ጠባሳ፣ ለቤተሰብ ጦስ፣ ለህዝብ መቅሰፍት ያስከትላል።"
"ከጓደኞቿ የወጣች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ትሆናለች።"
(12) ከደባል ሱሶች ራቅ። አላማ ያለው ሰው ከሱስ ጋር አይነካካም። ለነፃነቱ ዋጋ የሚሰጥ ሰው በተልካሻ ነገሮች አይታሰርም። ደግሞም ውለታ ቢስ አትሁን። አንተ አክብረህ ያማረ ቪላ፣ ወይም ቆንጆ መኪና፣ ወይም ሚሊየን ገንዘብ ቆጥረህ የሰጠኸው ሰው አይንህ እያየ ከፊትህ በእሳት ቢያጋየው ምን ይሰማሀል? ሰውስ ምን ይላል? አላህ በክብር የሰጠህን ህይወት በጫትና በሲጋራ መግደል ማለት ከዚህ የከፋ ውለታቢስነት ነው። ራስህን በሱስ የምትገድለው ከቤተሰብ በተቆነጠረ ሳንቲም ከሆነ ግን አንተ ዘመን ተሻጋሪ ገልቱ ነህ። እንስሳ ነህ ብየ የእንስሳን ክብር ዝቅ ማድረግ አልፈልግም።
"ራስን በሱስ በመጉዳትና ራስን በማጥፋት መካከል ያለው ልዩነት የጊዜ ርዝማኔ ነው።"

(13) ለወላጆችህ በጎ ሁን። አቅምህ የሚችለውን ሁሉ ሁንላቸው። የሚረኩብህ እንጂ የሚሸማቀቁብህ፤ የሚዘኑብህ እንጂ የሚሳቀቁብህ፤ የምታሳርፋቸው እንጂ የምታሳፍራቸው አትሁን። ቤተሰብህ ላይ ጥገኛ ሆነህ ሳለ አልፈህ የምትፏልልባቸው ከሆነ ግን በርግጠኝነት መጥፊያህን ይዘሀል። "የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል" ይባላል።
"የቤት ቀጋ፣ የውጭ አልጋ አትሁን።"

(14) አላማ ይኑርህ። ለአላማህ ትጋ። ወደ አላማህ ተጓዝ። ወዴት ነው የምትሄደው? ታውቀዋለህ? ምንድነው የምትፈልገው? ይገባሃል? ምን ሰበብ እያደረስክ ነው? መቼስ ሰሜን ለመድረስ ወደ ደቡብ አይኬድም። ጤፍ ዘርቶ ባቄላ አይጠበቅም። ባጭሩ አላማህንም፣ አቅጣጫህንም፣ ሚናህንም እወቅ።
"የሚሄድበትን የማያውቅ የትኛውም መንገድ ይወስደዋል።"
(15) የኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ቁርጠኛ ሁን። የሶላትና የጥናት ጊዜህን የሚበላ፣ አሰተሳሰብህን የሚበክል፣ መጥፎ ምስሎችን ከመመልከት ሱስ የሚያጣብቅ እንዳይሆን ደጋግሞ ማሰብ ይገባል። ማህበራዊ መገናኛዎችም ሱስ እንዳይሆኑብህ ተጠንቀቅ። ብትችል ቲክቶክ ከሚሉት ጥሩ ያልሆነ ሰፈር ከነጭራሹ ብትርቅ መልካም ነው። አጠቃላይ ከኢንተርኔት ጋር ያለህ ትስስር የሚያንፅህ እንጂ የሚያጠፋህ እንዳይሆን ደጋግመህ አስብበት።
ሰላም!
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 21/2011)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
📢 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ዌብሳይት

🤗 እየገባችሁ የተለያዩ መረጃዎችን ማግኘት ትችላላችሁ።

1 AA SCI. & TECH UNIVERSITY
http://www.aastu.edu.et/
2 Adama science & technology University
http://www.astu.edu.et/
3 Addis Ababa University
http://www.aau.edu.et/
4 Adigrat University
http://www.adu.edu.et/
5 Ambo University
http://www.ambou.academia.edu/
6 Arba Minch University
http://www.amu.edu.et/
7Arsi University
https://www.arsiun.edu.et/
8 ASOSSA UNIVERSITY
http://www.asu.edu.et/
9 Axum University
http://www.aku.edu.et/
10 Bahir Dar University
http://www.bdu.edu.et/
11 BONGA UNIVERSITY
http://www.bongau.edu.et/
12 BULE HORRA UNIVERSITY
http://www.bhu.edu.et/
13 DEBARK UNIVERSITY
http://www.dku.edu.et
14 Debrebirhan University
http://www.dbu.edu.et/
15 Debremarkos University
http://www.dmu.edu.et/
16 DEBRETABOR UNIVERSITY
http://www.dtu.edu.et/
17 DEMBI DOLO UNIVERSITY
http://www.dedu.edu.et
18 Dilla University
http://www.du.edu.et/
19 Dire Dawa University
http://www.ddu.edu.et/
20 Gambella University
http://www.gmu.edu.et
21 Gondar University
http://www.uog.edu.et/en/
22 Haramaya University
http://www.haramaya.edu.et/
23 Hawassa University
http://www.hu.edu.et/hu/
24 INJIBARA UNIVERSITY
http://www.inu.edu.et/
25 Jigjiga University
https://www.jju.edu.et/
26 Jimma University
https://www.ju.edu.et/
27 JINKA UNIVERSITY
http://www.jnu.et/
28 KEBRI DEHAR UNIVERSITY
http://www.kdu.edu.et/
29 Kotebe Metropolitan University
http://www.kmu.edu.et/
30 Meda Welabu University
http://www.mwu.edu.et/
31 Mekelle University
http://www.mu.edu.et/
32 MEKIDELA AMBA UNIVERSITY
http://www.mau.education/
33 METU UNIVERSITY
http://www.meu.edu.et/
34 Mizan-Tepi University
http://www.mtu.edu.et/
35 Oda Bultum
http://www.odabultum.edu.et
36 RAYA UNIVERSITY
http://www.rayu.org/
37 Selale University
http://www.seu.edu.et
38 Semera University
https://www.su.edu.et/
39 WACHAMO UNIVERSITY
http://www.wachemouniversity.academia.edu/
40 Welketie UNIVERSITY
http://www.wku.edu.et
41 WERABE UNIVERSITY
http://www.edu.et/
42 Wolayita Sodo University
http://www.wsu.edu.et/
43 Woldiya University
http://www.fh2web.academia.edu/
44 Wollega University
http://www.wuni.academia.edu/
45 Wollo University
http://www.wollo.academia.edu/
#AASTU

በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት 3 እና 4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

► የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
► ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
► የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
► አራት 3X4 ፎቶግራፍ።

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://t.me/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
የንዝረቱ ደረጃ 4.9 ሲሆን የተከሰተው መተሃራ አካባቢ መሆኑን የጀርመን የጂኦሳይንስ ማዕከል ዘግቧል።

«ለትንሽዬዋ መንቀጥቀጥ እንደዚ የተረበሽን ትልቁ ቂያማ ቢመጣብን እንዴት ልንሆን ነው? ዋ ነፍሴ! የአሏህ አቻቻል ነው እንጂ እንደወንጀላችን ብዛትማ መሬት እንድትውጠን ባደረገ ነበር! ተውበት እናድርግ!» አሕመድ የሕያ
"በሀገራችን አነስተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።መሬት መንቀጥቀጥ አላህ ባሮቹን ከሚያስፈራራበት እና ከሚያስጠነቅቅበት ክስተቶች መካከል አንዱ ነው::"

-ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

በእኛ እግር ዘወትር የምትረገጠው መሬት በጌታዋ ትዕዛዝ ትንቀጠቀጣለች:: ህዝቦች በወንጀል ሲዘፈቁ፣ ሽርክ እና ጥፋት ሲንሰራፋ፣ በምድራችን ብክለት ሲስፋፋ ጌታችን አላህ ሰዎች ከጥፋታቸው ታርመው ወደሱ ይመለሱ ዘንድ ማስጠንቀቂያዎችን ይልካል:: ከነዚህ ማስጠንቀቂያዎች አንዱ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው::

ይህ ማስጠንቀቂያ ካለንበት የወንጀል አረንቋ በመውጣት ወደ አላህ እንድንመለስ የማንቂያ ደውል ነው::

በሀገራችን የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ በትንሹ ተከስቶ ያለፈ ቢሆንም ከበድ ያለ ሆኖ ቢከሰት ባለንበት የወንጀል አረንቋ እንደተዘፈቅን ወደ ጌታችን ፊት የምንቀርብበት ሁኔታ ይፈጠር ነበር::

ይህ ከመሆኑ በፊት አሁን ላይ እድል አግኝተናል:: ወደ አላህ እንመለስ:: ጌታችንን አብዝተን ምህረትን እንለምን:: አላህ እንዲታረቀን ፣በእዝነቱ እንዲያየን በዱኣ ልንበረታ ይገባል ሲሉ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

©ሀሩን ሚድያ
Aselamualeykum all!
Tomorrow you will fill the university placement form, so you all should come to school at 4:00 o'clock local time in the morning.
NB.
Think on which university you choose first, second, etc...to minimize confusion during filling it
📢 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ዌብሳይት

🤗 እየገባችሁ የተለያዩ መረጃዎችን ማግኘት ትችላላችሁ።

1 AA SCI. & TECH UNIVERSITY
http://www.aastu.edu.et/
2 Adama science & technology University
http://www.astu.edu.et/
3 Addis Ababa University
http://www.aau.edu.et/
4 Adigrat University
http://www.adu.edu.et/
5 Ambo University
http://www.ambou.academia.edu/
6 Arba Minch University
http://www.amu.edu.et/
7Arsi University
https://www.arsiun.edu.et/
8 ASOSSA UNIVERSITY
http://www.asu.edu.et/
9 Axum University
http://www.aku.edu.et/
10 Bahir Dar University
http://www.bdu.edu.et/
11 BONGA UNIVERSITY
http://www.bongau.edu.et/
12 BULE HORRA UNIVERSITY
http://www.bhu.edu.et/
13 DEBARK UNIVERSITY
http://www.dku.edu.et
14 Debrebirhan University
http://www.dbu.edu.et/
15 Debremarkos University
http://www.dmu.edu.et/
16 DEBRETABOR UNIVERSITY
http://www.dtu.edu.et/
17 DEMBI DOLO UNIVERSITY
http://www.dedu.edu.et
18 Dilla University
http://www.du.edu.et/
19 Dire Dawa University
http://www.ddu.edu.et/
20 Gambella University
http://www.gmu.edu.et
21 Gondar University
http://www.uog.edu.et/en/
22 Haramaya University
http://www.haramaya.edu.et/
23 Hawassa University
http://www.hu.edu.et/hu/
24 INJIBARA UNIVERSITY
http://www.inu.edu.et/
25 Jigjiga University
https://www.jju.edu.et/
26 Jimma University
https://www.ju.edu.et/
27 JINKA UNIVERSITY
http://www.jnu.et/
28 KEBRI DEHAR UNIVERSITY
http://www.kdu.edu.et/
29 Kotebe Metropolitan University
http://www.kmu.edu.et/
30 Meda Welabu University
http://www.mwu.edu.et/
31 Mekelle University
http://www.mu.edu.et/
32 MEKIDELA AMBA UNIVERSITY
http://www.mau.education/
33 METU UNIVERSITY
http://www.meu.edu.et/
34 Mizan-Tepi University
http://www.mtu.edu.et/
35 Oda Bultum
http://www.odabultum.edu.et
36 RAYA UNIVERSITY
http://www.rayu.org/
37 Selale University
http://www.seu.edu.et
38 Semera University
https://www.su.edu.et/
39 WACHAMO UNIVERSITY
http://www.wachemouniversity.academia.edu/
40 Welketie UNIVERSITY
http://www.wku.edu.et
41 WERABE UNIVERSITY
http://www.edu.et/
42 Wolayita Sodo University
http://www.wsu.edu.et/
43 Woldiya University
http://www.fh2web.academia.edu/
44 Wollega University
http://www.wuni.academia.edu/
45 Wollo University
http://www.wollo.academia.edu/
Natural and Social Science Department G-12ABC pinned ÂŤAselamualeykum all! Tomorrow you will fill the university placement form, so you all should come to school at 4:00 o'clock local time in the morning. NB. Think on which university you choose first, second, etc...to minimize confusion during filling itÂť
#AAU

ለ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ያገኛችሁ የአንደኛ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

ከአዲስ አበባ ውጪ የምትመጡ ተማሪዎች ጥቅምት 5 እና 6/2017 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ካምፓስ በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የማደሪያ አገልግሎት ለተሰጣችሁ ብርድ ልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ አለባችሁ፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትኖሩ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል https://portal.aau.edu.et/NewStudent/DormitoryPlacement በመግባት ማየት ትችላላችሁ።

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በመርካቶ፣ በላምበረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን ገልጿል።

ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ ሆኖ ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች እና ዶክመንቶች ይዛችሁ ሪፖርት የምታደርጉት ሰኞ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ለሁሉም ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ (Orientation) ቅዳሜ ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የትምህርት ኮርሶች ምዝገባ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን፤ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት ማክሰኞ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

@tikvahuniversity
Forwarded from New Vision College Furi Campus 2022 Kolleejjii Niwuu Viyzinii Kampaasii Furii 2015
Forwarded from New Vision College Furi Campus 2022 Kolleejjii Niwuu Viyzinii Kampaasii Furii 2015
Forwarded from New Vision College Furi Campus 2022 Kolleejjii Niwuu Viyzinii Kampaasii Furii 2015
📘ሀረማያ ዩንቨርሲቲ

መገኛ፡ ሀረማያ :ከሀረር 17ኪ/ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ወይም ሀረር ከመግባታችን በፊት የ10ብር መንገድ ሲቀረን ያለች ከተማ ናት ሃረማያ
🚍 ድሬም ቅርብ ናት የ50ብር  መንገድ ብቻ

የአየር ሁኔታ፡ ብርዳማ ነው በተለይ ምሽት ላይ በጣም ይበርዳል
ሀረማያ ሀሩር ነው ምናምን የሚባለውን አትስሙ በርግጥ አንዳንድ የሙቀት ወራት አሉ ግን ብዙውን ጊዜ ቅዝቃዜው ያመዝናል ፤ ስለዚህ ወፍራም ልብስ መያዝ ይኖርባቹሃል ።
ብርድ ልብስ ምናምን መሸከም ካልፈለጋቹህ ሀረማያ ልብስ እና አንዳንድ ሸቀጦች ርካሽ በመሆናቸው ግቢ ከገባቹህ በኋላ መሸመት ትችላላችሁ
ይህን መረጃ በመስጠት ለተባበራችሁኝ ለEthio university news አባላት ላቅ ያለ ምስጋና ይድረስልኝ።


በውስጡ ያሉ ግቢዎች ፡ አንድ ትልቅ ግቢ ሆኖ በውስጡ ግን ሶስት የተያያዙ subግብዎች አሉት በተጨማሪም ሀረር ከተማ ላይም ሌላ ግቢ አለው

Subግቢዎች

1 Main campus
👉All social departments
👉Computer science
👉Business
👉Economics
👉Natural computational science
👉Law
👉Teaching and
👉Agriculture....

2 Gandajay.........(Techno campus )
👉Engineering above second year
👉Food science

3 Station
👉Fresh Engineering students and
👉Veterinary

4 Hareri
👉Medicine
👉Health
👉Pharmacy

📶ግቢው ውስጥ አሪፍ የሚባሉት agri,law and computer science ናቸው ።


🍞🍚🍣ምግብ ቤቶች🍝🍔🍣
ምግብ ኢትዮ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ቀዳሚው ነው ማለት ይቻላል።

(-_-)[ ምሳ ](-_-)

5️⃣በሳምንት አምስት ቀን Therefore አለ

1️⃣ ቀን ፓስታ

1️⃣ ቀን ደግሞ መኮረኒ


     🔰ቁርስ

🍔ሳንድዊች
🍝አንድ ቀን ማርማራታ
🍣ሁለት ቀን ዳቦ በስጋ ፍርፍር
🍚አንድ ቀን በሩዝ
🍞አንድ ቀን አንድ 🍞 ዳቦ

የጫት ነገር የማይሆንላቹህ አልያም ጫትን እንደ ምግብ የምትጠቀሙ ተማሪዎች ስለምትኖሩ ሌላ ግቢ ሄዳቹህ እሰጥ አገባ ውስጥ ከመግባትና ብሎም የዲሲፕሊን ኮሚቴ ጋር ከመጨቃጨቅ ሀረማያ ዩንቨርሲቲ ጎራ ብትሉ pis አለው። ( ጫት መቃም አይካበድም እንደ ህግ ግን ክልክል ነው )
አደራችሁን ከጫት ለመራቅ ሞክሩ ፤ በተለይ ለጫት አዲስ የሆንችሁና ምናልባትም ከነ ጭራሹ የማታውቁት ፍሬሽ ተማሪዎች ከተማው ላይ ባለው የጎላ የጫት ተጠቃሚነት እንዳትረበሹ ብሎም እንዳትሞክሩት ለማሳሰብ እወዳልሁ።

♻️[ Water ]

🚰የውሃ ችግር የለብንም ቢጠፋ ቢጠፋ እንኳ ካፌ አይጠፋም ስለዚህ ከካፌ መጠቀም ይቻላል ግን አይጠፋም
🚺ለሴቶች በየ ብሎካችው ውሃ አለላቸው


ሀረማያ ዩንቨርሲቲ የሚመደብ  ሰው የብሄር ቀልድ ምናምን እንዳይቀልድ በጣም Serious ጉዳይ ነው ፤ ባሁኑ ሰዓት የትኛውም ግቢ የሚገባ ተማሪ ከዘረኝነት የፀዳ ካልሆነ  አዛ ነው። እኛ ጋር ግን ባስ ይላል   ብሄርተኝነት ምናምን ....F ነው ግሬዱ

በተረፈ  ዝርፊያና ሌላ አስጊ ሁኔታ የለም፤ለፍሬሽ ተማሪዎች ደግሞ ሰርቪስ ተዘጋጅቶ ይጠብቃቸዋል


እንግሊዘኛን በአማርኛ ለመማር፤ስለ ፍሬሽማን እና ስለ ኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ሙሉ መረጃ ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/Remedial00
https://t.me/Remedial00
https://t.me/Remedial00
WELKITIE  UNIVERSITY

መገኛ፡ ደቡብ ክልል/ጉራጌ

የአየር ሁኔታ፡አየሩ አሪፍ የሚባል ነው ግን መጀመርያ አከባቢ ይሞቃል ፤ ለሴቶች ጥላ ነገር መያዝ ይኖርባቹሃል ትንሽ ፀሃዩ....☂️🌂☔️

በውስጡ ያሉ ግቢዎች፡ ሁለት ናቸው

textile and main ይባላሉ

♨️ textile ግቢ ከተማ ዉስጥ  ያለ ሲሆን በውስጡም
🌻Textile
🌻Garment and
🌻 designing( exam አለው )


MAIN ግቢ ደግሞ ከከተማዋ የ10 ብር ትራንስፖርት ሲሆን ጉብሬ የሚባል SUB CITYቦታ ላይ ይገኛል

በ ዉስጡ ያሉት dep. ደሞ
👉Engineering and Technology
             ✍️civil
          ✍️chemical
         ✍️ Electrical
        ✍️food process
      ✍️HWRE(water)
     ✍️mechanical
    ✍️ cotm
  ✍️architecture (ፈተና አለው)
Note▶️ምህንድስና ክፍል ላይ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በጣም አሪፍ ነው

👉computer science
✍️Software
✍️ CS (computer science)
✍️IS( Information system)
✍️IT( Information technology)
👉 social science
✍️midwifery
✍️ nursing
✍️FB
✍️Law
✍️Psychology ...
👉social/natural comptitional
✍️ Mathematics
✍️Sport
✍️ Physics
Health
HO ..
🏩Medicine --> እስካሁን ግን በህክምና አላስመረቀም


🍔🍔🍔🍔🍔🍔🍔🍔🍔🍔
የምግብ ቤቶች ዋጋ

         ካፌ
๖ۣۜም๖ۣۜሳ
🍱በሳምንት ሶስት ቀን ዜrፎr
🍴 አትክልት አለ ግን ብዙም አይነፋም
🍛ምስር ፣
🍳 ክክ እና
🍲ሽሮ love

๖ۣۜቁ๖ۣۜር๖ۣۜስ

➡️ፍርፍር
➡️🍚 ሩዝ እና
➡️ቅንጬ

ˡᵃᵘⁿᶜʰ
ግቢ ውስጥ  3 ላዉንቾች አሉ ዋጋቸዉም
🍥በያይነት 13-15
🍥ፓስታ በሱጎ 13
🍥ፓስታበአትክልት 13-15

ለነን ካፌ ተማሪዎች ኩፖን ከገዛቹህ 12.5-13.5 ነው
ት
☕️ቡና 2.5
☕️ሻይ 1.5
☕️ቀሽር 3
☕️ስፕሪስ 3

Note ▶️ ካፌ ላይ ጨጓራ ምናምን ላለባቹህ ልጆች special ቡፌ አለ ከክሊኒክ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ከሆነ

🏪ክሊኒክ በመሻሻል ላይ ቢሆንም እንደማንኛውም ግቢ ደስ የማይል ነገር አለው

❌ውሃ በፈረቃ ይለቀቃል ካልተለቀቀ ላውንች አካባቢ እንደልብ ስለሚገኝ no ጣጣ

❌Toilets ደስ አይሉም ትንሽ ይደብራል

⭕️ዶርምም ብዙም አያስደስትም ግን የብዙዎቹ ግቢዎች ችግር ስለሆነ ...



ግቢ ዉስጥ እና በዙሪያው  አስፈሪ ነገር   የለም

እንደሌሎች ግቢዎች  ሃይማኖታዊ ተቋማት በቅርቡ ስለሚገኙ ምንም ዓይነት ጭንቅ እንዳይሰማቹህ

ℹ️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️ℹ️
በነገራችን ላይ ግቢው ዲሲፕሊን ላይ በጣም ሃርድ ነው medicine በተቀበል በ መጀመርያው አመት 16 medicine ተማሪዎችን አባሯል በ ዲሲፕሊን ምክንያት ማለት ነው እንዲሁም ሊመረቅ ሳምንት የቀረዉም ልጅ አባሯል እና ተማሪዎች ግድ ጸባያቸዉን ማስተካከል አለባቸዉ በተልይ ድብድብ፡ጫት፡ሲጋራ ምናምን ከባድ penalty አላቸው

ሌላ ደሞ አንዳንድ ፍሬሽ ተማሪዎች ሊጠነቀቁ የሚገባቸዉ ነገር ጫት በብዛት  ስላለ እንዳይሸወዱ ፤ በተለይ ጉብሬ ግቢ የሚደርሳቹህ ተማሪዎች በርጫ በበርጫ ስለሆነ ሀገሩ ....
https://t.me/freshmantricks00
https://t.me/freshmantricks00
https://t.me/freshmantricks00
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ

መገኛ ፡ ሃዋሳ ፥ ከአዲስ አበባ ቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ ውብ ከተማ
#Location Southern nation nationalities and peoples representative in sidama zone hawassa city

የአየር ሁኔታ፡ ሞstly በቀኑ ክፍለ ጊዜ ሞቃታማ ሁና አመሻሽ ላይ ደስ የሚል አየር አላት ፤ ከተማዋ በራሱ የሆነ ደስ የሚል ነገር አላት 💐
#weather condition hot
Rainy almost the entire year the weather is more of similar to addis ababa
ይህን መረጃ በመስጠት ለተባበራችሁኝ ለ@amharictutorialclass
ቤተሰቦች ላቅ ይህ ምስጋና ይድረስልኝ።


በውስጡ ያሉ ግቢዎች ፡ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በውስጡ ብዙ ግቢዎች ያሉ ሲሆን ከነሱም ውስጥ

👉 1 Main campus
📍Location: Hawassa town (found on the enterance of the city)
Depts
- governance
- engineering
- social others
- art
- architect
- tourism
- hotel management
- Sport
- law
- Computational science ..

👉 2 Techno campus
📍Location: beside the main campus connected with the main campus though bridge
Depts
--> Engineering
--> information system
--> programming
--> Enla,discrit,

--> for engineering and computer science students until 3rd year after that the student will be transfered to main campus..


👉 3 Agri campus

📍Location: located on the middle o fthe city around piyasa

Depts
--> animal

👉 4 Yirgalem campus

📍Location: Yirgalem town (near hawassa city..)

Depts
-->FB faculty of business
- marketing management
- logistic
-Accounting
-Cooperative
- management
-economics

👉 5 Referral campus

📍Location:
located around the lake hawassa amazing view from the dorm nice sunset ...

Departments
--> Medicine
--> HO
--> nursing
--> environmental health
--> radiology
--> ophtometry
--> psychiatry

👉6 wendo genet agriculture
📍 Location:wendo genet
Dep' --> plant...

መብራት አይጠፋም for the white house ኤንድ for african dorms አንዳንዴ yitefal


ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሀገራችን ላይ አሉ ከሚባሉ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ጥራቱም ሆነ በግቢ ውበቱ አንደኛ ደረጃ ከሚባሉት ተርታ የሚመደብ ግቢ ነው።
ትምሮ በተወሰነ መልኩ ሊያጨናንቅ ይችላል ግን በግቢው ውበትና በከተማው ማብለጭለጭ ካልተሸነፋቹህ የትምህርቱ ነገር ሙድ አለው።
ጨብሲ ዘጭ ነው ሶ እንዳትበላሹ።
ከጨበሱ አይቸክሉ ፣🍺🚫
ከቸከሉ አይጨብሱ 🍻🚫
👆👆👆 እንዳትሰሙ 🙈🙉🙊

የምግብ ቤቶች ዋጋ
የምግብ ዋጋ በaverage ከ15-40 ብር ይደርሳል፥ የሁሉም ግቢዎች ዋጋ ይለያያል ።
ቡና ምናምን 5 ብር
ነን ካፌ ለሚፈልጉ ተማሪዎች ደግሞ fair በሆነ ዋጋ ....

🗣SHARE PLEASE🙏🙏

https://t.me/Freshman_tricks
https://t.me/Freshman_tricks
ምን ፊልዶችን እናጥና⁉️
================
✍ ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዋና አላማዬ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቢሆንም እየተማራችሁ ላላችሁና ለተመረቃችሁ ጭምርም ሊጠቅም ስለሚችል አንብቡት፤ ለሌሎችም አሰራጩት። የረጅም ጽሑፍ phobia ስላለባችሁ ቀጥታ ወደ ነጥቡ እገባለሁ።

*
①) ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፦
ከአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስና ከርሱ ጋር ተያያዥ ወደሆኑ መስኮች የሚያስኬዷችሁን ፊልዶች ደጥኑ።
የዘንድሮውን የ2024 የፊዚክስ የኖቬል ሽልማት ትናንትና የወሰዱት ሳይንቲስቶች ለሽልማት ያበቃቸው ቀጥታ ንጹህ የሆነ የፊዚክስ ሥራ እንዳይመስላችሁ። ማሽን ለርኒንግን ተጠቅመው በANN የሠሩት የፊዚክስ ሃሳብ ነው። ሳይንቲስቶቹ Geoffrey E. Hinton ከUniversity of Toronto, Canada እና John J. Hopfield
ከPrinceton University, NJ, USA ናቸው። ለሽልማት የበቁት “for foundational discoveries and inventions that enable machine learning with artificial neural networks” በሚል ምክንያት ነው።

ስለዚህ በቀጣይ ኤአይ የማይነካው መስክ አለ ማለት ከባድ እየሆነ ነው። በግብርና፣ በጤና፣ በደህንነት፣ … ያልገባበት የለም ማለት ይቻላል።

ስለሆነም የሚጠቆሙ መስኮች፦

1. Artificial Intelligence (AI) and Machine Learning (ML)
2. Biotechnology and Genetics
3. Climate Science and Environmental Studies
4. Quantum Computing and Physics
5. Neuroscience and Cognitive Science
6. Materials Science and Nanotechnology
7. Data Science and Bioinformatics

♠
②) ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች፦
ቴክኖሎጂው በናንተም ፊልድ መጥቷል። ስለዚህ ቴክኖሎጂውን ከፊልዳችሁ ጋር ለማዛመድ የሚያስችሉ መስኮች ላይ አተኩሩ። እኛ ሃገር ላይ ቶሎ ላይተኩ ቢችሉም ወደፊት በቴክኖሎጂው ሊተኩና ሊፈናቀሉ ከሚችሉና ስጋት ካለባቸው መስኮች ራቁ።

ስለሆነም በናንተ ዘርፍ የሚጠቆሙ መስኮች፦

1. Digital Sociology and Internet Studies
2. Public Policy and Global Governance
3. Behavioral Economics and Decision Sciences
4. Psychology and Mental Health Studies
5. Sustainability and Development Studies
6. Criminology and Cybersecurity
7. Cultural Anthropology and Diversity Studies


እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት በቀጥታ እንድትመርጡ ከሚቀርቡላችሁ አማራጮች ጋር በስም ላይገናኙ ይችላሉ። ምረጡ የተባላችሁት ዝርዝሩ ቢኖረኝ በራንክ ለማስቀመጥ ይመቸኝ ነበር። ግን ስለሌለኝ እነዚህን ዝርዝሮች ከያዛችሁ በኋላ እንድትመርጡ ከቀረቡላችሁ ጋር አዛምዱ።


♠
③) ውጤት ላልመጣላችሁ፦
ናቹራልና ሶሻል የሚለው ስለማይገድባችሁ መክሊታችሁንና የውስጥ ፍላጎታችሁን አዳምጡና ከላይ ከተዘረዘሩት መስኮች በአንዱ በግላችሁ ራሳችሁን አስተምሩ። በቂ ማቴሪያል ኢንተርኔት ላይ አለ። ጉዟችሁን ማፋጠን ከፈለጋችሁ ለዓይን መክፈቻ ያክል አጫጭር ስልጠናዎችን በብቃትና ተግባር ተኮር በሆነ መልኩ የሚሰጡ የቴክኒክና የግል ተቋማትን አፈላልጋችሁ እነርሱ ጋር ተማሩ። አንደዜ በመስመሩ ከገባችሁ ቀሪውን ትቆሰቁሱታላችሁ።


ለሃሳቤ ማጠናከሪያ ኔክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ከሁለት ቀን በፊት ኦክቶበር 7 "The Future of Jobs Report 2024" በሚል ያወጣውን ጽሑፍና WEF (World Economic Forum) ባለፈ አመት ያወጣውን
The Future of Jobs Report 2023 ተጠቅሚያለሁ።

አላህ ያግዛችሁ። ሳትጨናነቁ ሰበቡን አድርሱ። በአላህ ተመኩ። ቁም ነገሩ ማለፍ ብቻ ሳይሆን ሥራው ዓለም የሚፈለግ ተግባር ተኮር ዕውቀት መጨበጡም ላይ ነውና ሳትዘናጉ ሥሩ። ያላለፋችሁ የህይዎታችሁ ፍፃሜ ነው ማለት አይደለምና ከበረታችሁና በቁጭት የአላማ ሰው ከሆናችሁ ካለፉት በላይ ሁላ የምትሆኑበት አጋጣሚ ይኖራልና ተስፋ ሳትቆርጡ በርቱ።

ከወደዳችሁትና ይጠቅማል ካላችሁ ለሌሎችም አጋሯቸው።

♠
ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
=========
ኦክቶበር 09, 2024

||
ተጨማሪ ጠቃሚ ጽሑፎችን ስትፈልጉ በነዚህ የሶሻል ሚዲያ ገፆቼ ልታገኙኝ ትችላላችሁ።

t.me/MuradTadesse
t.me/STEMwithMurad
x.com/MuradTadesse
https://www.linkedin.com/in/murad-tadesse-a0a919160