Nigat Media
132 subscribers
520 photos
22 videos
277 links
Nigat Media ያልተዛባ መረጃን በተለየ አቀራረብ!
👉 https://www.nigatmedia.com
👉 https://www.am.nigatmedia.com
👉 https://www.facebook.com/nigatmedia1
👉 https://www.youtube.com/nigatmedia
Download Telegram
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት #ከግብጽ እና #ከኳታር መሪዎች ጋር በስልክ ያወሩ ሲሆን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ከሩቶ ጋር በናይሮቢ መክረዋል‼️

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ ማህሙድ ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ እና ከኳታሩ ኢሚር ታሚም አል ታኒ ጋር በስልክ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው እና በቀጠናዉ ጉዳይ ዙሪያ ማውራታቸው ተገለጸ።

ሶማሊያ ደህንነቷን እና መረጋጋቷን ለማስጠበቅ በምታደርገው ጥረት ግብጽ ከጎኗ እንደምትቆም አጽንኦት ሰጥተው አልሲሲ በስልክ ውይይታቸው ወቅት መግለጻቸውን ጽ/ቤታቸው ጠቁሟል።

#የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ሞሃመድ ኦመርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን የኬንያ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። ሁለቱም ባለስልጣናት በመከሩበት ወቅት በኬንያ የደቡብ #ሱዳን ልዩ ልዑክ አኮል ኩር ኩክ መታደማቸውንም ዘገባዎቹ አመላክተዋል። 

የውይይታቸው ዋነኛ አጀንዳ የቀጠናውን ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ መፍታት በሚቻልበት መንገድ እና አልሸባብን መዋጋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ እንደነበር ተጠቁሟል።