NNS (Nigus News Service) official Telegram channel
22 subscribers
21 photos
10 links
This is NNS's official Telegram channel.

For more updates please visit https://t.me/ngusnews
Download Telegram
ከህብረተሰቡ ባህልና ሞራል ያፈነገጡ ሕገወጥ ድርጊቶች ሲከናወኑባቸው የተገኙ ቤቶች ታሸጉ

🔒🔒🔒🔒🔒🔒🔒🔒🔒🔒🔒🔒🔒🔒

ትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ በተመራ የጋራ ግብረ ሃይል በተወሰደ እርምጃ በቦሌ ክ/ከተማ በቀነኒሳ ሆቴል 59 የሺሻ እቃ እንዲሁም ከህብረተሰቡ ባህልና ሞራል ያፈነገጡ ሕገወጥ ድርጊቶች ሲከናወኑ በመገኘቱ ሆቴሉ እንዲታሸግ መደረጉን ቢሮው ገልጿል።

በተመሳሳይ በማማስ ኪችን ህንፃ በሚገኘውና ዘኬጅ በተሰኘው የምሽት ክበብ ውስጥም 27 የሺሻ እቃ መያዙንና ክበቡም እንዲታሸግ መደረጉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Ⓝⓘⓖⓤⓢ Ⓝⓔⓦⓢ ⓢⓔⓡⓥⓘⓒⓔ

Source : EBC zena
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0i4rd7yCLAaSzP8zUydm32qy9eP5rAUXACWnozTY6bHhzodHWpA2ZKqBXMSgnEB9nl
👍1
በቻን ውድድር ለፍጻሜ የሚያልፉ አገራት ዛሬ ይለያሉ

⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️
19ኛ ቀኑን ያስቆጠረው የ7ኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና (ቻን) አስተናጋጇ አገር አልጄሪያ ከኒጀር፤ ማዳጋስካር ከሴኔጋል ዛሬ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ወደ ፍጻሜ የሚያልፉ አገራት የሚለዩበት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ።

ከምሽቱ 1 ሰዓት በሚሉድ ሀዴፊ ስታዲየም አስተናጋጇ አገር አልጄሪያ ከኒጀር ይጫወታሉ።

አልጄሪያ ኮትዲቭዋርን እንዲሁም ኒጀር ጋናን በሩብ ፍጻሜ በማሸነፍ ነው ለግማሽ ፍጻሜው ያለፉት።

በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በውድድሩ የመጀመሪያ ተሳትፎዋ ስኬታማ ጉዞ እያደረገች የምትገኘው ማዳጋስካር ከሴኔጋል ጋር ከምሽቱ 4 ሰአት በኔልሰን ማንዴላ ስታዲየም ጨዋታዋን ታደርጋለች።

ማዳጋስካር በሩብ ፍጻሜው ሞዛምቢክን እንዲሁም ሴኔጋል ሞሪታኒያን ማሸነፋቸው ይታወቃል።

የግማሽ ፍጻሜ አሸናፊ አገራት የፊታችን ቅዳሜ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በኔልሰን ማንዴላ ስታዲየም የፍጻሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ጥር 23/2015 (NNS)
Ⓝⓘⓖⓤⓢ Ⓝⓔⓦⓢ ⓢⓔⓡⓋⓛⓒⓔ
https://t.me/ngusnews
🔥1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አማካሪ ቡድናቸውን አነጋገሩ
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️

በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ቡድን በዛሬው ዕለት ሰብስበው ማነጋገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

የአማካሪ ቡድኑ አባላት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጠንከር ያሉ ግብአቶችን የማምጣት እና ለትግበራ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦችን የማመንጨት ሥራ እንዲሠሩ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት ፅሁፍ ገልፀዋል።

ጥር 23/2015 (NNS)
Ⓝⓘⓖⓤⓢ Ⓝⓔⓦⓢ ⓢⓔⓡⓥⓘⓒⓔ
https://t.me/ngusnews
👍1
በጥር የዝውውር መስኮት የመጨረሻ ቀን የተጠናቀቁ ተጠባቂ ዝውውሮች

⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️

👉ቼልሲ አርጀንቲናዊውን ኤንዞ
ፈርናንዴዝን ከቤኔፊካ በ 121 ሚሊዮን ዩሮ አስፈርሟል ተጫዋቹ በቼልሲ ቤት የ 8 ዓመት ኮንትራት ይፈርማል።

👉ማንችስተር ዩናይትድ ማርሴል ሳቢትዘር በውሰት ከባየር ሙኒክ አስፈርሟል ።

👉 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መሪው አርሰናል ጆርጂንሆን ከቼልሲ በ 12 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈርሟል ።

👉ሀኪም ዚዬች ወደ ፒኤስጂ አድርጎ የነበረው ዝውውር ሳይሳካ ቀርቷል። ሲልኩ በመዘግየታቸው ነው ተብሏል።

👉ኬይለር ናቫስ በውሰት ውል እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ድረስ ፒኤስጂን በመልቀቅ በኖቲንግሀም ፎረስት ይቆያል።

👉ሄክተር ቤለሪን የስፖርቲንግ ሊዝበን ተጫዋች ሆኗል።

👉ፉልሃም ሴድሪክ ሶሬስ በውሰት ከአርሰናል ማስፈረማቸውን ይፋ አድርጎዋል።

👉የማንችስተር ዩናይትዱ ተጫዋች አሌክስ ቱዋንዘቤ በውሰት ስቶክ ሲቲን ተቀላቅሏል።

👉ቶተንሃም ሆትስፐር ፔድሮ ፖሮ በ45 ሚሊየን ዩሮ  ከስፖርቲንግ ሊዝበን እስከ 2028 በሚያቆይ ውል ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

👉አልበርት ሳምቢ ላኮንጋ ከ አርሰናል በውሰት ፓላስን ተቀላቅሉዋል።

👉ባየርሙኒክ ጆኦ ካንሴሎን በውሰት ከማንቸስተር ሲቲ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል ።በስምምነቱ ላይ 70m ዩሮ በቋሚ ዝውውር የማስፈረም መብት አለው ።

ጥር 24/2015 (NNS)
Ⓝⓘⓖⓤⓢ Ⓝⓔⓦⓢ ⓢⓔⓡⓥⓘⓒⓔ
https://t.me/ngusnews
ከባሕላዊ ዕሴቶቻችን መላላት የሚመነጨው የፖለቲካ ስብራት ያለፉት 4 ዓመታት ውጤት አይደለም - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

አክራሪነት፣ ፅንፈኝነትና ከባሕላዊ ዕሴቶቻችን መላላት የሚመነጨው የፖለቲካ ስብራት ብዙዎች እንደሚያስቡት ያለፉት አራት ዓመታት ውጤት አለመሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በተሳሳተ ትርክት ላይ ተመስርቶ አክራሪነትና ፅንፈኝነት ባለፉት አሥርት ዓመታት በኢትዮጵያዊነት ማንነት እና ብሔርተኝነት ላይ መዘራቱን፤ እነሱን ለማስታገስ ሥራ ላይ የነበረው የአፈና ሥርዓት ያስከተለው ውጤት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዛሬ የሚስተዋሉ ጉዳዮች አዲሱ አካተች የዲሞክራሲ ሥርዓት ሁሉንም ነገር ግልጥልጥ በማድረጉ ነፃነትን በአግባቡ ማጣጣም ካለመቻል የመነጨ ነውም ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቱም የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ሂደትና በዚህ ረገድ የነበረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ውድቀት ውጤት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ባለፉት አሥርት ዓመታት ኢትዮጵያ በኮሜርሻል ሕግ የተበደረችው የገንዘብ መጠን የዛሬ አራት ዓመት የጠቅላላ ሀገር ውስጥ ምርት 60 በመቶ በላይ ደርሶ ነበር ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

የለውጥ አመራሩ መንግስቱን በተረከበ ማግስት አዳዲስ ብድሮች አግኝቶ ምርታማነትን በማሳደግ የሥራ አጥነት ችግር እንዳይቀረፍም ይህ ችግር እንቅፋት መሆኑን ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡

የዋጋ ግሽበቱ በኢኮኖሚ ዕድገቱ ተሸፍኖ ላለፉት 20 ዓመታት ሕዝቡን ምሬት ውስጥ እንደከተተው ቀጥሏልም ነው ያሉት፡፡

ከሰሞኑ በ2015 የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ያስተዋልነውም ይህንኑ ችግር ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ጥር 25/2015 (NNS)
Ⓝⓘⓖⓤⓢ Ⓝⓔⓦⓢ ⓢⓔⓡⓥⓘⓒⓔ
https://t.me/ngusnews
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ 212 ሚሊዮን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የ2023 የሁለትዮሽ ትብብር ስምምነት ተፈራረመዋል።

የትብብር ስምምነቱ ለግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች በተለይም በትግራይ፣ አማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ  እና ቤንሻንጉል-ጉሙዝ የሰብዓዊ ድጋፎችን በተደራጀ መንገድ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው።

በመሆኑም እ.ኤ.አ. በ2023 በጀት ዓመት 212 ሚሊዮን 493 ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም 44 ሚሊዮን ብር በዓይነት ለማህበሩ ድጋፍ ይደረግለታል፡፡

ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና ፀሃፊ አቶ ጌታቸው ታዓ እና የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የኢትዮጵያ ልዑክ ኃላፊ ኒኮላስ ቮን አርክስ ናቸው።

በስምምነቱ ወቅት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና ፀሃፊ ጌታቸው ታዓ እንደተናገሩት ትብብሩ የማህበሩን ሁለንተናዊ አቅምን ለመገንባት፣ የልማት ስራዎችን ለማገዝ እና በግጭት የተጎዱ ሰዎችን ለማቋቋም የተጀመረውን ስራ በሚፈለገው ደረጃ ማሳለጥ ያስችላል ብለዋል፡፡

ዋና ፀሃፊው  አያይዘውም ማህበሩ በመላ ሀገሪቱ በጦርነትና በተፈጥሮ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ እና ግጭቶችን ለመፍታት ለሚያደርገው ጥረት የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የኢትዮጵያ ልዑክ ኃላፊ ኒኮላስ ቮን አርክስ በበኩላቸው ስምምነቱ በአደጋ ጊዜ የሰብዓዊ ድጋፎችን ምላሽ ለመስጠት የማይተካ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።

ጥር 25/2015 (NNS)
Ⓝⓘⓖⓤⓢ Ⓝⓔⓦⓢ ⓢⓔⓡⓥⓘⓒⓔ
https://t.me/ngusnews
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አርብ ከቀኑ 11፡30 ላይ ያበቃል - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
**

የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት የሚያበቃ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።

ቀድመው ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የቅሬታቸውን መልስ www.neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

የቀረቡ ቅሬታዎች ተጣርተው ሲጠናቀቁ የቅሬታዎቹን ምላሽ በቀጣይ ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጾ፤ የቅሬታ ምላሽ ያልደረሳችሁ ተፈታኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ አሳስቧል።

በተመሳሳይ ያልተሟላ ወይም የተሳሳተ ወይም የሌላ ሰው መለያ ቁጥር በመጠቀም ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የስም ዝርዝራቸውን ዛሬ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገጽ ላይ በመመልከት ቅሬታቸውን በትክክለኛ መለያ ቁጥራቸው በድጋሚ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑንም አገልግሎቱ አስታውቋል።

ጥር 25/2015 (NNS)
Ⓝⓘⓖⓤⓢ Ⓝⓔⓦⓢ ⓢⓔⓡⓥⓘⓒⓔ
https://t.me/ngusnews
Channel name was changed to «NNS (Nigus News Service) official Telegram channel»
በወቅታዊ ጉዳይ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን የተሰጠ መግለጫ

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ በውስጣዊ አሠራር መፈታት እንዳለበት መንግሥት ያምናል።

ሀገራዊ ተቋማት አንድነታቸውንና ጥንካሬያቸውን ጠብቀው እንዲዘልቁ ከዚህ በፊትም ሆነ ችግሮች በተፈጠሩ ጊዜ ሁሉ መንግሥት የሚጠበቅበትን ሲወጣ ቆይቷል። ይሄንን ጥረቱን አሁንም አጠናክሮ ይቀጥላል።

የተቋማቱን አንድነት የሚፈታተኑ ችግሮች ከውስጥ ሲነሡ በውይይትና በውስጣዊ አሠራር እንዲፈቱ ድጋፍ ሲያደርግ ነበር። በተጨባጭም ውጤት አምጥቷል።

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በቤተ ክርስቲያኒቱ አሠራር መሠረት እንዲፈታ ሁሉም አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት ይኖርባቸዋል።

የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ሁለቱን ወገኖች በማቀራረብ ችግሩ በሰከነ መንገድ እንዲፈታ ማድረግ አለባቸው።

አማኞች ችግሩን ከማወሳሰብና ለሌሎች አካላት መጠቀሚያ ከመሆን በመታቀብ ገንቢ ሚና ሊጫወቱ ይገባል።

የጸጥታ አካላት የየአካባቢውን ሕዝብና የእምነት ተቋማት ሰላምና ጸጥታ ማስከበር ግዴታቸው ነው። ግጭት የሚያባብሱ አካላትንም ሥርዓት ማስያዝ አለባቸው።

የሚዲያ አካላት ችግሩን የሚያባብሱ ነገሮችን ከማቅረብ መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም መላው ሕዝብ ለችግሩ መፈታት የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ መንግሥት ያሳስባል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመሥራት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።

ስምምነቱን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው እና የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ገናነው ጐፌ ተፈራርመዋል።

የሥምምነት ሠነዱ በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ በየዘርፉ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት፣ ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን በማከናወን ወደ ተግባር ለመቀየር እና የማኅበረሰብ ሕይወትን ለመለወጥ በትብብር መሥራት ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በተጨማሪም ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ዕድገት በጋራ ይሠራሉ ፣ በዩኒቨርሲቲው የሚከናወኑ ማኅበረሰብ ተኮር ጉዳዮችንም በሚዲያ ተደራሽ ለማድረግ ይተባበራሉ ተብሏል፡፡https://www.fanabc.com/archives/181656
FBC (NIGUS NEWS SERVICE), [1/15/25, 12:15 PM]
የፋሲለደስ እድሳትና የጎንደር ኮሪደር ልማት ሥራ እድገት እጅግ አበረታች ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

ጎንደር፣ ጥር 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎንደር ከተማ እየተካሄዱ ያሉት የፋሲለደስ እድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች እድገት እጅግ አበረታች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጎንደር ከተማ እየተካሄዱ ያሉ የፋሲለደስ እድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷በጎንደር ከተማ እየተካሄዱ ያሉት የፋሲለደስ እድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች እድገት እጅግ አበረታች ናቸው ብለዋል፡፡

በሥራው ለተሳተፉ ሁሉ በተለይም በክብር ለተሞሉት እንግዳ ተቀባይ የጎንደር ነዋሪዎች በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል፡፡]
የፋሲለደስ እድሳትና የጎንደር ኮሪደር ልማት ሥራ እድገት እጅግ አበረታች ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎንደር ከተማ እየተካሄዱ ያሉት የፋሲለደስ እድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች እድገት እጅግ አበረታች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጎንደር ከተማ እየተካሄዱ ያሉ የፋሲለደስ እድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷በጎንደር ከተማ እየተካሄዱ ያሉት የፋሲለደስ እድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች እድገት እጅግ አበረታች ናቸው ብለዋል፡፡

በሥራው ለተሳተፉ ሁሉ በተለይም በክብር ለተሞሉት እንግዳ ተቀባይ የጎንደር ነዋሪዎች በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

NNS (Nigus News Service)