Art and motivational speechs
7 subscribers
11 photos
1 link
Find ur talent
Download Telegram
Forwarded from DID U KNOW️⁉️
The world's first meme was created in 1921

From our @Historychannal
ትናንትን መድገም

እውነት ነው ያለፉት ጊዜያት ዛሬ የደረስክበትን ወስነዋል፤ አሁን ወሳኙ ግን ትናንትን የምታይበት መነፅር ሳይሆን ነገን አሻግረህ የምታይበት ነው። ስለ ነገ ምን እያሰብክ ነው?

ትላንት አልፏል፤ ዛሬ እጅህ ላይ ነው፤ ይሄን ካላስተዋልክ ግን ትናንትን መድገም እጣ ፈንታህ ይሆናል!
Channel name was changed to «Art and motivational speechs»
Channel photo updated
በህይወታችን ውስጥ ጨካኝ ቀናት እና ፈታኝ ጊዜያት ይኖራሉ ። እኛን የሚሰሩንም እነሱ ናቸው ። በየትኛውም ከባድ የህይወት አጋጣሚ ውስጥ ስናልፍ ትልቅ ትምህርት እንማራለን ።ትምህርቱ ደግሞ እኛን ይቀይረናል ።ቢያንስ ቢያንስ '' ሁሉም ነገር ያልፋል '' የሚል የህይወት እውነትን እንረዳለን ።


ሰናይ ቅዳሜ
ውሃ በተፈጥሮው ቀለም የለውም፤ ጣዕም የለውም፤ እንዲሁም ጠረን(ሽታ) የለውም፡፡

ነገር ግን ውሃ በአንድ ቦታ ለረጅም ጊዜ ከተቋተ እና ቆሻሻ ወደ ውስጡ መግባት ከጀመረ ቀለሙን መለወጥ፣ መጥፎ ሽታ ማምጣት እንዲሁም አለፍ ሲል በውስጡ አልጌ መብቀል ይጀምራል፡፡

በአንፃሩ ውሃ በውስጡ ማጣፈጫዎች (ጆሊ ጁስ፣ ማር) ከተጨመረበት ከተፈጥሮው በተለየ ጣፋጭና ተወዳጅ ይሆናል፡፡

የሰው ልጅም ልን እንደ ውሃ ነው፡፡ ሰው በተፈጥሮው እንደውሃ የፀዳ ነው፡፡ ሲወለድ እየደለም ክፋትና ተንኮልን ይቅርና መልካምንም አያውቅም። በቃ Neutral ሆኖ ነው የሚወለደው፡፡

ነገር ግን ከውልደት በኀላ በመልካም ሰዎችና በመልካም ተግባሮች ተከበው በመልካም ስፍራ የሚያድጉ ልክ በማር እንደተበጠበጠው ውሃ እድሜ ልክ ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች ጣፋጭ ሁነው ይኖራሉ፡፡

በአንፃሩ በመጥፎ ምግባር፣ በመጥፎ ሰዎችና በመጥፎ ስፍራ ሁነው የሚያድጉት ለእይታ እስኪጠሉ ድረስ እንደ ቆሸሸው ውሃ ይጠላሉ፡፡

ስለዚህ በእየቀኑ ወደ ልባችን መልካሙን በማስገባት፤ በምካም ሰዎች ተከበን በመልካም ስፍራ በመገኘት ለእራሳችንም ሆነ ለሌሎች ጣፋጭ እንሁን፡፡

🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን🙌

🔊Share and join @success1515
Ezi group lay add yaderekuachihu lijoch inbox me @Elfaz1 for additional information

ለበለጠ መረጃ የካምፓኒያችን Official

website⭕️🔰👇

www.alphagenuine.com

Telegram⭕️🔰👇

@Breakthroughsc

YouTube⭕️🔰👇

https://www.youtube.com/channel/UC-QcViiKMPZU6fUKqKfviVA
Forwarded from ኩልሲማ (Am Reading...)
እውነታው ሲመዘን!

• የትምህርት ደረጃህ በያዝከው ወረቀት ቢታይም፣ የአዋቂነትህ ጥልቀት ግን በባህሪህ ይታያል!
• የስልጣንህ ከፍታ በሹመትህ ቢታይም፣ የተጽእኖህ ስፋት ግን በአገልጋይ መሪነትህ ይታያል!
• የሃሳብህ ብዛት በንግግር ቢታይም፣ የስኬታማነትህ ጥራት ግን በተግባራዊነትህ ይታያል!
• ደጋፊነትህ በመፈክርህ ቢታይም፣ የአብሮነትህ እውነተኛነት በአጋርነትህ ይታያል!
• ቢዚነትህ ብዙ በመስራትህ ቢታይም፣ የስኬታማነትህ ቀጣይነት ግን ከዓላማህ አንጻር በምታከናውናቸው ነገሮች ይታያል!
• ሃብትህ ባለህ ገንዘብና ቁሳቁስ ቢታይም፣ የብልጽግናህ ዓላማ-መርነት ገንዘብህን በምታውልበት ሁኔታ ይታያል!


🙏የተዋበ ቀን🙏


👇👇👇ሼር👇👇👇
@kulsima
👇👇ለአስተያየቶ👇👇
@Nejent
Forwarded from ኩልሲማ (Am Reading...)
ኑሮ ድክም ሲላችሁ!

አንዳንድ ጊዜ ኑሮ ራሱ ድክም ይላል! ኑሮ ድክም ሲላችሁ . . . . ቀድሞ ያጓጓቹሁ የነበሩ ነገሮች አሁን ግድም አይሰጧችሁም . . . የፈጠራ ብቃታችሁ ይጠፋባችኋል . . . ከሰዎች ጋር የመገናኘት ፍላጎታችሁን ታጣላችሁ . . . ሕይወት ትርጉም የሌለው ይመስላችኋል . . . የበፊቱ “ጤናማ” ሕይወታችሁ እንደገና የሚመለስ አይመስላችሁም . . .

አስታውሱ . . .
• ሁሉም ሰው አንዳንድ ጊዜ ይህ ስሜት እንደሚያጠቃው አስታውሱ
• ስሜቱ ጊዜያዊ እንደሆነና ተመልሶ እንደሚሄድ አስታውሱ
• ቀድሞ ከለመዳችኋቸው የየእለት የሕይወት ኡደቶች ለጊዜው አረፍ ማለታችሁን አስታውሱ
• ከስሜቱ እስከምትወጡ ድረስ ይህንን ስሜታችሁን በመገንዘብ አብሮነቱን በሚሰጣችሁ ሰው ላይ ብቻ ማተኮራችሁ ችግር እንደሌለበት አስታውሱ
• ከዚህ ስሜት ለመውጣት ከሚያግዟችሁ ማሕበራዊ መድረኮች በስተቀር ለተወሰነ ጊዜ እረፍት መውሰዳችሁን አስታውሱ

አይዟችሁ! ነገ ጠዋት “ስፖስት” በተሻለ ስሜት ውስጥ ሆናችሁ እንገናኛለን!

🙏የተዋበ ቀን🙏

Dr eyob

👇👇👇ሼር👇👇👇
@kulsima
👇👇ለአስተያየቶ👇👇
@Nejent
Forwarded from ኩልሲማ (Am Reading...)
የአጋጣሚውን ተጠቀም

የአጋጣሚ ትንሽ የለውም፤
ህይወት በክስተቶች የተሞላች ነች። የክስተቱ ባለቤት ማንም ይሁን ማንም፣ የክስተቱ ተቀባይ ግን አንተ ልትሆን ትችላለህ። አንድ ነገር ሲመጣብህና ሲመጣልህ አንድ አይነት ምላሽ አትሰጥም። የመጣብህን እንዳመጣጡ ትመልሳለህ፣ የመጣለህን ግን በአግባቡ ትቀበለዋለህ፣ ትጠቀመዋለህ። ለዚህም የዘወትር ዝግጁነትህ ወሳኝ ነው። በህይወትህ የሚመጡልህ መልካም አጋጣሚዎች ህይወትህን እስከ ወዲያኛው የመቀየር ሃይል አላቸው። መቼም እስከ ዛሬ ስንት አጋጣሚዎችን እንዳሳለፍክ፣ እንዳባከንክ አንተ ታውቃለህ፤ ለሚቀጥሉት ድንቅ አጋጣሚዎች ግን በፍፁም ሳይጠቅሙህ እንዲያልፋ መፍቀድ የለብህም። አዎ! እራስህን በብዙ ማዘጋጀት ይኖርብሃል።
ጊዜና አጋጣሚ አንድ ናቸው አብረው ይመጣሉ፤ አብረውም ላይመለሱ ይሔዳሉ።
አዎ! አንዳች ነገር እንዳታመልጥህ ዘወትር ተዘጋጅተህ ጠብቅ። ከተጠቀምክበት ዓለም መጥፎና ከባድ ገፅ ብቻ ሳይሆን ቀላል ብልሃትህንና ዝግጁነትህን ብቻ የሚሹ ብዙ የህይወት በረከቶችምና ብዙ አጋጣሚዎችም አሏት፤
ዋናው ያንተ በተገቢው ሰዓት፣
በትክክለኛው ቦታ፣
በተገቢው አኳሃን የተገኘውን አድል፣ አጋጣሚ ሳያመነቱ ተጠቅሞ መገኘት ነው።

🙏የተዋበ ቀን🙏

👇👇👇ሼር👇👇👇
@kulsima
👇👇ለአስተያየቶ👇👇
@Nejent
Forwarded from zelalem fissha
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ የታይኩንስ ቡድን አባላት።
የፊታችን እሁድ በጉጉት የምንጠብቀው ትልቅ የቡድን ቤተሰብ ጊዜ እናካሂዳለን !!!

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
You all are invited
Forwarded from ኩልሲማ (Am Reading...)
👉የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግክ ክፍሉን የደገመን ተማሪ ጠይቀዉ !

👉የአንድን ወር ዋጋ ለማወቅ ከፈለግክ ካለወሩ የተወለደ ህፃን የወለደችን ሴት ጠይቃት !

👉የአንድን ሳምንት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ በየሳምንቱ የሚወጣን ጋዜጣ አሳታሚ ጠይቀዉ !

👉የአንድን ቀን ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ የወሳኝ ፈተናን ዉጤት ነገ ለመስማት የሚጠብቅን ተማሪ ጠይቀዉ !

👉የአንድን ሰአት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ አዲስ ፍቅረኞችን ጠይቃቸዉ !

👉የአንድን ደቂቃ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ አዉቶቢስ ለትንሽ ያመለጠዉን ሰዉ ጠይቀዉ !

👉የአንድን ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ከአደጋ ለጥቂት ያመለጠን ሰዉ ጠይቀዉ !

👉የአንድን ሚሊ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ በኦሎምፒክ ሩጫ ለጥቂት የተቀደመን ሯጭ ጠይቀዉ!

ጊዜ=ህይወት! ስለዚህ ጊዜህን ስታባክን ህይወትህን ታባክናለህ! ጊዜህን በትክክል ስትመራ ደግሞ ሕይወትህን በትክክል ትመራለህ!!

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ


🙏 የተዋበ ቀን🙏


👇👇👇ሼር👇👇👇
@kulsima
👇👇ለአስተያየቶ👇👇
@Nejent
Forwarded from ኩልሲማ (Am Reading...)
ጠንክረህ ስራ

ትልቁ የስኬት ሚስጥር የማይቆም ጥረት ነው
በዚህ አለም ላይ የምትፈልገው ነገር ካለ ጠንክረህ መስራት አለብህ ዋጋ መክፈል አለብህ ጠንክሮ ያልሰራ ሰው ከፍታው ላይ አይወጣም። ጠንካራ ጎንህ ላይ ጠንክረህ ስራ ወደራስህ አተኩር ረጅም ስአት ቁጭ ብለህ አስብ በሙሉ አቅምህ ስራ በሙሉ አቅምህ ተማር
አሁን ከጠነከርክ ከበረታህ ከባድ ጊዜያት ባንተ ላይ አቅም አይኖራቸውም ምርጥ ጊዜያት ደሞ ወደ ከፍታህ ይወስዱሀል። ጠንክረህ የምትሰራ ከሆነ የትም ብትሄድ ይሳካልሀል አንተ የምታውቃቸው ስኬታማ ሰወች እድለኞች አይደሉም ። የአለማችን ቁጥር አንዱ ተከፋይ
The Rock (Dwayn.Johnson) እንዲህ ይላል ላቤ ከአቧራው ጋር ተጣብቆ ገላየ እስኪጠቁር ድረስ ያለ እረፍት እሰራ ነበር ጅም ከሆንኩ ብረት እያነሳሁ ነው ቤት ከሆንኩ መሬት ላይ ፑሽ አፕ እየሰራሁ ነው በህንወቴ የሚመክረኝ ሰው አልነበረም። ግን አንድ ነገር አውቃሉ ከምታውቃቸው ስዎች ጠንክረህ የምትሰራው አንተ መሆን አለብህ።
ሌሊት ስምንት ስአት ከቤቴ ወደ ዋሽንግተን ዮኒቨርሲቲ በእግሬ እሄዳለሁ እስከ ጥዋት ድረስ ፕሮግራሚንግ እለማመድ ነበር ይህን ለረጅም አመትደጋግሜ አድርጌዋለሁ ለዛ ነው ማይክሮ ሶፍትን የፈጠርኩት።
Bill Gates
ህይወትህን የሚቀይረው በየቀኑ የምታደርገው ልማድህ ነው።


🙏የተዋበ ቀን🙏


👇👇👇ሼር👇👇👇
@kulsima
👇👇ለአስተያየቶ👇👇
@Nejent
Forwarded from ኩልሲማ (Am Reading...)
ከመቶ አመት በፊት አንድ ሰውዪ የጠዋቱን ጋዚጣ ሲመለከት የሙታን ስም ዝርዝር የሚወጣበት አምድ ላይ የገዛ ስሙን ተጽፎ በማንበቡ ከመገረሙም በላይ እጅግ ደነገጠ፡፡ ጋዜጣው ላይ በስህተት የእሱን መሞት የተመለከተ ዘገባ ወጥቷል፡፡ በመጀመሪያ ላይ በጣም ተሽበረ፡፡ “አለሁ ወይስ ሞቻለሁ?” ሲልም አሰበ፡፡ ቀልቡን ከሰበሰበ በኋላ ደግሞ ስለ እሱ ሰዎች ምን እንዳሉ ለማወቅ ጉጉት አደረበት፡፡ በአምዱ ላይ የተጻፈው ጽሁፍ “የድማሚቱ ንጉስ ሞተ” ይልና በማስከተልም “ሟቹ በህይወት ዘመኑ የሞት ነጋዲ ነበር” ይላል፡፡ ይህ ሰው ድማሚትን በመፈልሰፉ የተነሳ ‘የሞት ነጋዲ’ መባሉን ሲያነብ “ሰዎች የምሚያስታውሱኝ በዚህ መልኩ ነውን?” በማለት ራሱን ጠየቀ፡፡ በዚህ መልኩ መታወስ እንደማይኖርበትም ውሳኔ ላይ ደረሰ፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ ስለሠላም ለመስራት ተነሳ፡፡ይህ የድማሚት ንጉስ የተባለው ሰው አልፍሬድ ኖቤል ሲሆን ባለንበት ዘመን በታላቁ ኖቤል ሽልማት ይታወሳል፡፡ በምን እንድትታወስ ትፈልጋለህ


🙏የተዋበ ቀን🙏

👇👇👇ሼር👇👇👇
@kulsima
👇👇ለአስተያየቶ👇👇
@Nejent
Forwarded from ኩልሲማ (Am Reading...)
ትኩረታችንን ወደምንፈልገው ህይወት እናድርግ
አብዛኛውን ጊዜ እኛን በማይመለከቱን ሌሎች አጀንዳዎች ታጥረን ዋናውን የህይወታችንን ግብ እንደረሳን እንስተዋለን። ውዱን ጊዜያችንንም በማይሆን ተራ ነገር እናጠፋለን፡፡
ጊዜያችንን ሁሉም ነገር ውስጥ ጥልቅ በማለት የምናጠፋ ስንቶች ነን።
ራሳችንን ከዚህ በማሻሻል ዋናው የህይወት ግባችን ላይ ማተኮር የግድ ነው አቅማችንን ለማሳደግ ፡-
📌የህይወታችን ዋናው ግባችን ( Main Goal) ላይ ትኩረት ማድረግ
📌 በቀጣይ ለስብዕናችን እድገት ( Personal Development ) ትኩረት መስጠት
📌ያለፈውን ስህተት መርሳት
📌ወደፊት ስለሚሆነው ነገር ብቻ (Focus on Future ) ትኩረት በማድረግ ህይወታችንን መቀዬር እንችላለን፡፡


🙏የተዋበ ቀን🙏

👇👇👇ሼር👇👇👇
@kulsima
👇👇ለአስተያየቶ👇👇
@Nejent
ኩልሲማ:
ትላንት ከተጠየኩት አስደንጋጭ ጥያቄ ላካፍላቹ

አሰልጣኙ ከፊትለፊቴ ቆሞ ድንገተኛ ጥያቄ ጠየቀኝ።" ዛሬ አሁን በዚ ሰዐት የሙት መንፈስ መጥቶ ነፍስሽን ሊያወጣት ነው እንበልና ምን ይሰማሻል? ምን ትያለሽ? "እጅግ በጣም ደነገጥኩ" ። "አልፈልግም" አልኩት። "ለምን?" ሲለኝ "አልተዘጋጀሁም፤ማድረግ ያለብኝን አላደረኩም፤የተፈጠርኩበትን የምኖርለትን ነገር ሙሉ ለሙሉ አላጠናከኩም አላሳካሁም " አልኩት። "አሪፍ እንበልና ከ 6 ወር በኃላ ተመልሶ እንደሚመጣ ነግሮሽ ቢሄድ አንቺ በ 6 ወር ውስጥ ምን ምን ታደርጊያለሽ አለኝ"። መስራት ማድረግ መሆን ማሳካት የምፈልጋቸውን ነገራቶች እንድፅፋቸው አዘዘኝ። ፅፌ አነበብኩለት።ቀጣዩ ጥያቄ ይበልጥ ያስደነግጥ ነበር። "ታድያ እነዚን የዘረዘርሻቸውን ነገራቶች እንዳትኖሪ እንዳትሆኚ እንዳታሳኪ ምን ከለከለሽ?። ምን ይሆን?………

እርግጠኛ ባልሆንበት ነገ ላይ የምንፈልገውን እንዳንኖር ምን ይሆን ያገደን?

📌ስንፍና?
📌ቸልተኝነት?
📌ጊዜ አለን ብለን ማሰባችን?
📌 ወይስ ስለራሳችን ግድ ስለማይሰጠን?





👇👇ሼር👇👇

👇👇ለአስተያየቶ👇👇
@Golden1521
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

"ሳይፀልዩ ማደር"

የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ፣
ሚዳቋ ፀለየች...
አውጣኝ አውጣኝ አለች ለፈጠራት ጌታ።

ነብሩም ተርቦ፣
ወደ አምላኩ ቀርቦ።
ሚዳቆዋን አይቶ-አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ፣
ፈቅዶ እንዲሰጠው አምላኩን ጠየቀ።

የሁለቱም አምላክ የሁላችን ሰሪ፣
ጸሎታቸውን ሰማቸው ፈጣሪ።

አምላክም በድምፁ ሚዳቆዋን አላት፣
እሩጠሽ አምልጪ ከበረታ ጠላት።
ነብሩንም አለው እሩጥ ተከተላት፤ ምግብ አርገ ብላት።

ሚዳቆዋም ስትሮጥ ከነብሩ ለማምለጥ፣
ነብሩም ሲከተላት ሆዱን ሊሞላባት።
ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ፣
ሆዱን ብትረግጠው የተኛ ከርከሮ።
ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር፣
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነበር።

አውጣኝ ያለው ወቶ አብላኝ ያለው በላ፣
ሳይፀልይ የተኛው ከርከሮ ተበላ።

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌
....going to success ☀️:
"ወጣት ስትሆን ገንዘብ ላይኖርህ ይችላል፤ ግን ቢያንስ በእርጅና ጊዜህ ደሀ መሆን የለብህም" የሚል ፅሁፍ አንብቤ ነበር፤ እውነት ነው አሁን ብትቸገር ከሰው ብታንስ ምንም አይደል፤ ችግሩ ታሪክህን ለመቀየር ምንም ካለደረክ ነው።

ወዳጄ ነገ በጤናውም፣ በደስታውም፣ በገንዘቡም፣ በመንፈሳዊ ህይወቱም፣ በቤተሰብ ግንኙነቱም ሀብታም መሆን አለብህ! መሆን ከፈለክ ደግሞ ካሁኑ ማሰብ ጀምር!


🙏የተዋበ ቀን🙏
አመስጋኝ_እንሁን!
ከዕለታት አንድ ቀን ሙላ ናስሩዲን በአንድ ተራራ አጠገብ ሲያልፍ ተንሸራትቶ ወንዝ ይገባል:: ከውሃው ጋር ሲታገል ቆይቶ ሞት አፋፍ ላይ ሲቃረብ፣ ሃይማኖት ባለፈበት ያላለፈው ሰው ወደ ፈጣሪው ጮኸ፡፡

“አምላኬ ሆይ! .… እባክህን ከሞት አድነኝ ካዳንከኝ ከዛሬ ጀምሮ እፀልያለሁ! … ትዕዛዛትህንም እፈፅማለሁ! …” እያለ ጮኸ፡፡ በዚህ ጊዜ ከወንዙ ዳርቻ ያለ አንድ የዛፍ ስር አጋጠመውና ለቀም አድርጎ፣

“አምላክ ሆይ ግዴለም አትቸገር” አለ፡፡

ገና ይህን ተናግሮ ሳይጨርስ ግን የጨበጠው ግንድ ተሰብሮ ተመልሶ ወንዙ ውስጥ ገባ፡፡ ተደናግጦም፣ “ምነው አምላክ ሆይ ቀልድ አታውቅም እንዴ?” አለ ይባላል።

ይቺ ትንሽ ቀልድ የአእምሮአችንን አሰራር ቁልጭ አድርጋ ታሳየናለች፡፡ ሁላችንም ፈጣሪያችንን የምናስታውሰው በመከራችን እንጂ በደስታችን ቀን አይደለም::

ወደ ቤተ-ክርስቲያን ወይም መስጊድ የምንሄደው መቼ ነው? ጤነኞችና ደስተኞች በሆንበት ሰዓት? አይደለም ችግር ወይም መከራ(በሽታ) ሲደርስብን ብቻ ነው።

በህይወታችን ውስጥ ሃብት ኖሮንም ብዙም ደስተኞች አይደለንም ፡፡ ድሆች ስንሆን ደግሞ ችግራችንና ስቃያችን የበረታ ይሆናል፡፡ ጤነኞች ስንሆን ጤነኞች በመሆናችን አምላክን አናመሰግንም:: ስንታመም ግን፣ ህይወታችንንና በአጠቃላይ መኖራችንን እንረግማለን፡፡ አንዳንዶቻችን እንዲያውም ያሉንን መልካም ነገሮች ሁሉ ለመራገም ትንሽ የራስ ምታት ትበቃናለች። ስለዚህ ሁሌም አመስጋኝ እንሁን።