Nejashi Printing Press
4.71K subscribers
673 photos
10 videos
6 files
780 links
ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።
Download Telegram
አሥሩ የዚል-ሒጃ ቀናት፡፡
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ፡፡
*
* ዛሬ ዚል-ቂዕዳ 30ኛ ቀን ላይ ነው ያለነው፡፡

* በኢስላማዊው አቆጣጠር ነገ ሰኞ 1 ብሎ የሚገባው ወር የዚል-ሒጃ ወር ይባላል፡፡

* ዚል-ሒጃ እጅግ የተከበረ ወር ነው፡፡

* ጦርነት በውስጡ ከተከለከለባቸው ከአራቱ የተከበሩ ወራት ውስጥም አንዱ ናት፡፡

* ከወሩም የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት እጅግ የተከበሩ ናቸው፡፡

* ቀናቶቹ የዚል-ሒጃ ወር ሲጀምር ይጀምራሉ፡፡ የዒድ አል-አድሓ ቀን ያበቃሉ፡፡

*ፆም ምርጥ የአምልኮ ተግባር እንደመሆኑ በነኚህ የመጀመርያዎቹ ዘጠኝ ቀናት ውስጥ መፆም ይወደዳል ።

* ከነኚህ ቀናት ውስጥ ከ8ኛው ቀን ጀምሮ የሐጅ ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡

* እነኚህ ቀናት እጅግ ክቡር መሆናቸው የታወቀ ቢሆንም ብዙዎች በነኚህ ቀናት ዉስጥ ሲዘናጉ ይታያሉ፡፡

* በነኚህ ቀናት ዉስጥ የሚሠሩ መልካም ሥራዎች በየትኛዉም የዱንያ ቀናት ዉስጥ ከሚሠሩት በላይ አላህ ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፡፡

* የዐረፋ ቀን ፆም (ዘጠነኛው ቀን) የሁለት ዓመት ኃጢኣት ያስምራል፡፡ ያለፈን አንድ ዓመት እና የሚቀጥለዉን አንድ ዓመት፡፡

* የዐረፋ ቀን ፆም የሐጅ ሥራ ላይ ለሌለ ሰው ነው። ዐረፋ ላይ የሚቆም ሰው ይህን ቀን አይፆምም።

* ሐጅ አድራጊ በዚህ ቀን ውስጥ በዱዓና ኢስቲግፋር መበርታት ይኖርበታል ።

* አሥረኛው ቀን ዒድ ነው።

* የዒድ ቀን መፆም የተከለከለ ነው።

* ቀንም ሆነ ሌሊት በነኚህ ቀናት ዉስጥ በዒባዳ መበርታት ይገባል፡፡

* ለዒዱ ኡድሒያ ማረድ ሀሳቡ ያለው ሰው ቀነኚህ ቀናት ውስጥ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን መቆረጥ የለበትም።

* በነኚህ አሥር ሌሊቶች አላህ (ሱ.ወ.) ምሎባቸዋል፡፡ ይህም የቀናቱን ታላቅነት ያሳያል፡፡

* በነኚህ ቀናት ውስጥ የሚሠሩ መልካም ሥራዎች ተወዳጅ የመሆናቸውን ያህል በውስጣቸው የሚሠራ ኃጢኣትም ጥፋቱ ክቡድ ነው፡፡

* እነ ኢብኑ ዐመር እና አቢ ሁረይራ (ረ.ዐ.) በነኚህ ቀናት ዉስጥ ተክቢራ እያደረጉ ወደ ገበያ ይወጡ ነበር፡፡ ሰዎችም አብረዋቸው ተክቢራ (አሏሁ አክበር) ይላሉ፡፡

* በነኚህ ቀናት ዉስጥ ዚክር ማብዛት፣ አላህን ማላቅ ይወደዳል፡፡

* በነኚህ ቀናት ውስጥ ሱብሐነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ላ ኢላሀ ኢልለላሀ አላሁ አክበር ማለት ይወደዳል፡፡

* በዐረፋ ቀን ዱዓ መብዛት ይመረጣል፡፡ በተለይ ላ ኢላህ ኢልለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁልሙልኩ፣ ወለሁል ሐምዱ፣ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር … የሚለዉን፡፡

* በነኚህ ቀናት ዉስጥ የሚሠሩ የዒባዳ ዓይነቶች ቀናቶቹን ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ሶላት፣ ፆም፣ ሶደቃ፣ ሐጅ … ሁሉም የተሰባሰቡባቸው ናቸው፡፡

* ደጋጎች እነኚህን አሥርቶች ልዩ ትኩረት ይሠጧቸው ነበር፡፡
- የረመዷን ወር የመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት፣
- የዚል ሒጃ ወር የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት፣
- የሙሐረም ወር የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት፡፡

አሥርቱ ዚል ሒጃ ቀናት፤ ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ በመባል ይታወቃሉ፡፡

ያስታውሱ ቀናቱ ነገ ይጀምራሉ፡፡

መልካም የዒባዳ ጊዜ
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር

https://t.me/Nejashipp

https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/
ስምንተኛው ቀን አመሻሽ ላይ
የውም አት-ተርዊየህ
*****

የሐጅ ተግባራት ዛሬ ዚል-ሒጃ ስምንተኛው ቀን ላይ ጀምረዋል። በሐጅ ወቅት የኢሕራም ልብስ ከለበሱ በኋላ ሐጅ ይነየታል።
የኢሕራምን ሁለት ረከዓዎችን ከሰገዱ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ ሆይ! ሐጅ አስቤያለሁና አግራልኝ፤ ተቀበለኝ። አንተ ሰሚም፣ ዐዋቂም ነህና።”

ከዚያም “ተልቢያ” ለብበይከ-ልላሁምመ ለብበይክ… ይባላል።

በዚሁ ቀን ጸሐይ ከወጣች በኋላ ወደ ሚና ጉዞ ይጀመራል። ይህ ቀን የተርዊየህ (ውሃ የማጠጣት ቀን) ተብሎ ይታወቃል። በጥንት ጊዜ የሐጅ እንግዶችን የሚቀበሉ ሰዎች ለሐጃጆች ውሃ በማቀበል የሚያሳልፉት ቀን ነው።

በዚሁ ቀን ተልቢያን /ለብበይከ-ልላሁምመ ለብበይከ… ማለትን ማብዛት ይወደዳል። ዚክር ማድረግ፣ ለአላህ መተናነስና ለሱ ያለንን ፍራቻ መግለጽ አስፈላጊ ነው።

ወደ ሚና መሄድና እዚያው ማደር በነጋታው ለሚደረገው የዐረፋ ላይ የመቆም ሁኔታ ያዘጋጃል።
በአያመ ተሽሪቅ ውስጥ የሚፈፀሙ ሥርዓቶች
*
ከዒድ ቀን በኋላ ያሉ ሦስቱ የዚል-ሒጃ 11ኛ፣ 12ኛ እና 13ኛ ቀናት ቀናት “አያመ ተሸሪቅ” በመባል ይታወቃሉ፡፡ የዒድ ቀናቶች ናቸው፡፡ በነኚህ ቀናት ውስጥ ይበላል፣ ይጠጣል፣ የጠጠር ውርወራ ሥርዓት ይከናወናል፡፡


ውርወራው ሰባት ሰባት ጠጠሮች በሦስት ቦታዎች ላይ በመወርወር ይከናወናል።
ቦታዎቹና ቅደም ተከተላቸውም "ጀምረቱል-ኡላ" (የመጀመሪያው ጠጠር መወርወሪያ) "ጀምረቱል ውስጧ" (የመሃለኛው) ጠጠር መወርወሪያ እና "ጀምረቱል ዐቀበህ" የመጨረሻው የጠጠር መወርወሪያ ቦታዎች ናቸው።
የመወርወሪያ ጊዜም ፀሐይ ከእኩለ-ሰማይ ወደ ምእራብ ከወረደች በኋላ ጀምሮ እስከምትጠልቅ ድረስ ባለው ወቅት ነው።

በ "ጀምረቱል ኡላ እና በ ጀምረቱል ውስጧ የጠጠር መወርወሪያ ሥፍራ ላይ ጠጠሮችን ወርውሮረው እንደጨረሱ ወደ ቂባላ ዙሮ ዱዓእ ማድረግ ይመረጣል።
በ "ጀምረቱል_ዐቀበህ" (በመጨረሻው) የጠጠር መወርወሪያ ስፍራ ላይ ግን ጠጠሮችን ወርዉሮ መመለስ እንጂ ዱዓእ አይደረግም።

ትንሹን፣ መካከለኛውንና ትልቁን (የመጨረሻውን) የጠጠር ውርወራ ሥርዓት መፈፀም ተገቢ ነው፡፡ ለእያንዳንዳቸው ሰባት ሰባት ጠጠሮች ይወረወራል፡፡
እያንዳንዱን ጠጠር ሲወረወር ተክቢራ በማድረግ ይወደዳል፡፡ ሰባቱንም ጠጠሮች አከታትሎ መወርወር ሱንና ነው፡፡

የውርወራውን ሥርዓት በቅደም ተከተል መፈፀሙ መስፈርት ነው፡፡ በትንሹ ይጀምራል፡፡ መካከለኛውን ያስከትላል፡፡ በትልቁ ያጠናቅቃል፡፡

ጠጠሮች በሚወረውሩበት ገንዳ እና በሰውዬው መካከል ሦስት ክንድ እና ከዚያ በላይ ርቀት መኖሩ ሱንና ነው፡፡ ርቀቱ ከዚያ ያነሰ ከሆነ መጣል እንጅ መወርወር አይባልምና፡፡

የጠጠር ውርወራ ሥርዓት የሚጀመርበትን ወቅት በሚመለከት ታላቁ የውርወራ ሥርዓት ከዒድ ሌሊት አጋማሽ በኋላ የሚጀመር ሲሆን ሦስቱም ከዒድ ቀን አጋማሽ በኋላ ይጀመራሉ፡፡ በአያመ ተሸሪቅ የመጀመሪያው ቀን ተጀምረው በመጨረሻው (ዒድ በዋለ በአራተኛው ቀን) ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ይጠናቀቃሉ፡፡

ሐጅ አድራጊ ጠጠር መወርወር ሲጀምር ‹ለበይክ…› ማለቱን ማቆም ይኖርበታል፡

ከሐጅና ዑምራ መጽሐፍ

https://t.me/Nejashipp

https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/
ያ ጉድጓድ ውስጥ የተጣለው፣
በባልዲ ተንጠልጥሎ ከጉድጓዱ የወጣው እና
በርካሽ ዋጋ የተሸጠው፤

ኋላ ላይም ሚኒስቴር ሆኖ፣
ቀጥሎም የግብፅ ዋና ገዥ ሊሆን ጥቂት ቀርቶት የነበረው ነቢዩ ዩሱፍ (ዐ.ሰ.) ታሪኩ ምን ያስተምረናል መሰለህ…

በዘመንህ ውስጥ የሚያጋጥሙህ ከባባድ የሕይወት ገፆች ሁሉ፣
በሕይወት ውስጥ ወደፊት የሚመጣውን እጅግ ውቡን ሕይወትህን መንገድ ለመጥረግ የተላኩ መቅድሞች ሊሆኑ ይችላሉና ታገስ!
በአላህ ላይ መልካምን ብቻ ጠርጥር!፡፡
Forwarded from ABX (Muhammed Seid)
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ነጃሺ ማተሚያ ቤት ከዚህ በታች በተዘረዘረው ክፍት የስራ መደብ ዝርዝር መሰረት አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
*የስራ መደቡ መጠሪያ:- የማርኬቲንግ ባለሙያ
*ብዛት:-1
*የት/ት ደረጃ:- በማርኬቲንግ ወይንም ተዛማጅ የት/ት ዘርፍ የተመረቀች/ቀ
*የስራ ልምድ:-2 አመትና ከዚያ በላይ
*ፆታ:-ሴ/ወ
*ደሞዝ:-በስምምነት

አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁንና የስራ ልምዳችሁን 09_45_85_85_85 በቴሌግራም ወይንም
nejashipress@gmail.com ላይ መላክ ትችላላችሁ
ነጃሺ ማተሚያ ቤት

https://t.me/MuhammedSeidAbx
በዚያ ዕለትም ‘ሠንየተል ወዳዕ’ በተባለው ሥፍራ በርካታ የመዲና ሕዝብ ተሰብስቦ ምስጋናና ውዳሴ እያሰማ ተቀበላቸው፡፡ መዲና በታሪኳ እንደዚያ ቀን የደስታ እልልታ ገጥሟት አያውቅም፡፡
ዕለቱ በእርግጥም ኢስላም ጠባብ ከሆነው የመካ አስጨናቂ ሕይወት ወደ ሠፊውና አስደሳች ወደ ሆነው የመዲና ሕይወት ሽግግር ያደረገበት ታሪካዊ ቀን ነበር፡፡ የመዲና ሕዝቦች የአላህን ታላቅ በረከትና ጸጋ በደስታ ተቀብለው ምስጋናና ውዳሴ ያሰሙበት ድንቅ ዕለት፡፡ ለምን አመስጋኝ አይሆኑ!! ምድራቸው ታሪካዊውን የኢስላም ብርሃን ለዓለም እንድታደርስ ተመርጣለች፡፡ የመጨረሻውንና የነብያት ሁሉ መደምደሚያ የሆኑትን ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ተቀብላ ለማስተናገድ ከመታደል የበለጠ ምን ልቅና ትሻለች! ዕድለኛ ከተማ፡፡ በጊዜው ሁሉም “የአላህ መልዕክተኛ! የአላህ መልዕክተኛ! ሙሐመድ!” እያለ ደስታውን ሲገልጽ ይታይ ነበር።

ዝነኛው የጠለዐል በድሩ ዐለይና ነሺዳም በዚያ ቀን ተነሸደ።

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በታሪክ ገጾች የሚስተካከለው በሌለ የደመቀ አቀባበል መዲና ከገቡ በኋላ የሚያርፉበትን ሥፍራ ራሳቸው መወሰን አልፈለጉም ነበር፡፡ ከዚያ ይልቅ “ግመላቸው መለኮታዊ ምሪት” እንዳላትና እርሷ የምታርፍበትን ቦታ ትክክለኛው ማረፊያቸው እንደሆነ በማሳወቅ ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ በመጨረሻም የአቡ አዩብ አል-አንሷሪ (ረ.ዐ) ቤት ሲደርሱ አቡ አዩብ (ረ.ዐ) ተሸቀዳድመው ጓዛቸውን በመያዝ እቤታቸው አስገቡት፡፡

ከ" ለዓለማት እዝነት" መጽሐፍ
ትርጉም : አቡ ቢላል

https://t.me/Nejashipp

https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/
ምርጥ የሕፃናት እነፃ (ተርቢያ) መፃህፍት
ከኬጂ እስከ ስድስተኛ ክፍል