ነአምን media
43.5K subscribers
1.79K photos
139 videos
9 files
952 links
Buy adds:- https://telega.io/c/neamn_media

<< ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአበሔር!>>
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ
#ትምህርቶች
#ዝማሬዎችና
#ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስነ-ፅሁፎች
የሚለቀቁበት ቻናል ነው።

ለሁሉም መረጃና አስተያየትና በቻናሉ ላይ ለመፃፍና ለመሳተፍ @theofloss ያናግሩን መረጃውንም ያካፍሉን።
Download Telegram
የሰሙነ ህማማት ሐሙስ

ጸሎተ ሐሙስ

በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡  የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ (ማቴ. 26፥36-46 ዮሐ.17)

ሕፅበተ ሐሙስ ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡

የምስጢር ቀን ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡

የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-
ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል (ሉቃ. 22፥20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳስ ሐሙስ ተባለ፡፡

የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት (ዮሐ. 15፥15)፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡
1
Forwarded from Quality button
ትስቡጣ ማለት ገዢ ማለት ነው።
"ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።"

ኢሳይያስ 53፥7
1
የክርስቶስ 13ቱ ሕማማት👇
ነአምን media
የክርስቶስ 13ቱ ሕማማት👇
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል በዕለተ ዓርብ ተቀብሏል እነዚህም👇

1) ተአስሮተ ድኅር ( የኋሊት መታሰር )
👉 የዮሐንስ ወንጌል ( ም 18 ÷ 12 )
👉 ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ( ም  1 ÷ 46 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ብንያሚ ( ም 89 ÷ 15 )


2) ተጸፍዖ መልታሕት ( ፊትን በጥፊ መመታት )
👉 የማቴዎስ ወንጌል ( ም 26 ÷ 67 )
👉 የማርቆስ ወንጌል ( ም 14 ÷ 65 )
👉 የሉቃስ ወንጌል ( ም 22 ÷ 64 )
👉 የዮሐንስ ወንጌል ( ም 18 ÷ 22 )

👉 ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ( ም 1 ÷ 49 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዮሐንስ ( ም 103 ÷ 14 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዘዮሐንስ ( ም  113 ÷ 9 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዘዮሐንስ ( ም 114 ÷ 25 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤጲፋንዮስ ( ም 55 ÷ 35 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አትናቴዎስ ( ም 30 ÷ 37 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቴዎዶስዮስ ( ም 82 ÷ 21-23 )

3) ወሪቀ ምራቅ (ምራቅ መተፋት)
👉 ትንቢተ ኢሳይያስ ( ም 50 ÷ 6 )
👉 የማቴዎስ ወንጌል ( ም 26 ÷ 67 )
👉 የማቴዎስ ወንጌል ( ም 27 ÷ 30 )
👉 የማርቆስ ወንጌል ( ም 10 ÷ 34 )
👉 የማርቆስ ወንጌል ( ም 14 ÷ 65 )
👉 የማርቆስ ወንጌል ( ም 15 ÷ 19 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ሄሬኔዎስ ( ም 7 ÷ 25 )

👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዮሐንስ ( ም 103 ÷ 14 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤጲፋንዮስ ( ም 55 ÷ 35 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አትናቴዎስ ( ም 30 ÷ 37 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቴዎዶስዮስ ( ም 82 ÷ 21-23 )

4) ተኰርዖተ ርዕስ (ራስ በዘንግ መመታት)
👉 ትንቢተ ኢሳይያስ ( ም 1 ÷ 5 )
👉 የማቴዎስ ወንጌል ( ም 27 ÷ 30 )
👉 የማርቆስ ወንጌል ( ም 15 ÷ 19 )


5) ተቀሥፎ ዘባን (ጀርባን መገረፍ)
👉 ትንቢተ ኢሳይያስ ( ም 50 ÷ 6 )
👉 የማቴዎስ ወንጌል ( ም 20 ÷ 19 )
👉 የማቴዎስ ወንጌል ( ም 27 ÷ 26 )
👉 የሉቃስ ወንጌል ( ም 23 ÷ 16 )
👉 የዮሐንስ ወንጌል ( ም 19 ÷ 1 )
👉 1ኛ የጴጥሮስ መልዕክት ( ም 2 ÷ 24 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤጲፋንዮስ ( ም 55 ÷ 35 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አትናቴዎስ ( ም 30 ÷ 37 )


6) አክሊለ ሦክ ( የእሾህ አክሊል መድፋት )
👉 የማቴዎስ ወንጌል ( ም 27 ÷ 29 )
👉 የዮሐንስ ወንጌል ( ም 19 ÷ 2 - 5 )
👉 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቴዎዶስዮስ ( ም 82 ÷ 21 )


7) ጸዊረ መስቀል ( መስቀል መሸከም )
👉 የሉቃስ ወንጌል ( ም 23 ÷ 26 )
👉 የዮሐንስ ወንጌል ( ም 19 ÷ 17 )
👉 መጽሐፈ ምስጢር ( ም 14 ÷ 27 )


8) ሰትየ ሐሞት (አሞት / ሆምጣጤ መጠጣት )
👉 መዝሙረ ዳዊት ( ም 68 ÷ 21 )
👉 የማቴዎስ ወንጌል ( ም 27 ÷ 34 - 48 )
👉 የማርቆስ ወንጌል ( ም 15 ÷ 36 )
👉 የሉቃስ ወንጌል ( ም 23 ÷ 36 )
👉 የዮሐንስ ወንጌል ( ም 19 ÷ 28 - 30 )


የተቀሩት አምስቱ ቅንዋተ መስቀል ናቸው። ስማቸውም የዕብራይስጥ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አራቱ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈ ምስጢር በተሰኘው መጽሐፋቸው ጠቅሰዋቸዋል ( መጽሐፈ ምስጢር 14 ÷ 27 ) እነርሱም 👇

👉 ሳዶር | የመጀመሪያ :- ሁለቱን መስቀል በማያያዝ የተቸነከረ ነው።

👉 አላዶር | ሁለተኛ :- ቀኝ እጁን የተቸነከረበት ችንካር ነው።

👉 ዳናት | ሦስተኛ :- ግራ እጁን የተቸነከረበት ችንካር ነው።

👉 አዴራ | አራተኛ :- እግሮቹን አጣምረው የቸነከሩበት ችንካር ነው።

👉 ሮዳስ | አምስተኛ :- ኢናንአ (ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ) የሚለውን ጲላጦስ በዕብራይስጥ ፣ በሮማይስጥ ፣ በግሪክ ተፅፎ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራስ በላይ የተሰቀለበት ችንካር ነው።
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ግራ ጎኑን የወጋው ወታደር ማን ነው ⁉️
የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡

ወየው ወየው ወየው አማኑኤል አምላካችን፡፡

ወየው ወየው ወየው መድኃኒታችን ኢየሱስ፡፡

ወየው ወየው ወየው መድኃኒታችን ኢየሱስ፡፡

ወየው ወየው ወየው ንጉሣችን ክርስቶስ፡፡

ወየው ወየው ወየው ጻድቁን ከዕንጨት አወረዱት፡፡

ሥጋውንም ለመገነዝ ከርቤ የሚባል የጣፈጠ ሽቱንና ንጹሕ በፍታን አመጡ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ፡፡

ከድንግል ማርያም የተወለደ አቤቱ ይቅር በለን፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ የማይሞት የማይለወጥ በዮርዳኖስ የተጠመቀ በመስቀልም የተሰቀለ አቤቱ ይቅር በለን፡፡"

#ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
1
ቄጠማ በግንባራችን ለምን እናስራለን ?

ቄጠማ የምሥራች ምልክት ነው ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ የተወሰደው በኖኅ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ ጋር በማቆራኘት ነው ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ኾነው እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውኃ ተጥለቅልቀዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ ይዞአቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ ትመልሳለች፡፡ ኖኅም በዚህ ቄጠማ የውኃውን መድረቅ ተረድቶ ተደስቷል
(ዘፍ. ፱፥፩-፳፱)

ቄጠማ ለጥፋት ውኃ መድረቅ የምሥራች መንገሪያ እንደ ኾነ ዅሉ

አሁንም ‹‹በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ፤›› ስትል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡

ምእመናንም የምሥራች ተምሳሌት የኾነውን ቄጠማ በግንባራቸው ያስሩታል፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ዅሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን፤ ከዋዕየ ሲኦል (የሲኦል ቃጠሎ) ወደ ጥንተ ማኅደራቸው ገነት መመለሳቸውን በዚህ አኳኋን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከብራሉ፡፡

                           መ/ር ነቢዩ ኤልያስ

https://t.me/neamn_media
"ዓለም እንደ አጠቃላይ በጨለማ ተውጦ ሲተረማመስ የሚታየው ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ምርጫው ስላደረገ ነው።"  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወስምንቱ ዓመተ ምሕረት!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን-

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ከሀገር ዉጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፣

በቤዛዊ መሥዋዕትነቱ ከሞተ ኃጢአት ታድጎ የትንሣኤ ሙታንን በር የከፈተልን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
"ወአነ እሜው ነፍስየ ቤዛ አባግዕየ ከመ ካዕበ አንሥእ፤አንሥእ፤
ዳግመኛ አነሣት ዘንድ ነፍሴን የበገቼ ቤዛ አድርጌ እሰጣለሁ ዮሐ 10፥17

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰብአዊ ክዋኔው ሰው ቢሆንም በመለኮታዊ ክዋኔው የአብና የመንፈስ ቅዱስ ቃል ወይም ወልደ እግዚአብሔር ነው፣
በመሆኑም በሰብአዊ ክዋኔው መዋች ሲሆን በመለኮታዊ ክዋኔው ተነሽና አንሺ ነው፤ ከዚህ አንጻር ሥግው ቃል ሁለቱንም ተግባራት በአንድ አካልና ክዋኔ የመፈጸም ሥልጣን አለው፣ ይህም በመሆኑ ራሴን የማኖርና የማንሣት ሥልጣን አለኝ በማለት እውነታውንና ምንነቱን አሳየ፤

ጌታችን ይህንን አስመልክቶ ከመሞቱና ከመነሣቱ በፊት ለቅዱሳን ሐዋርያት በተደጋጋሚ አስረድቶአል፣ ስለሆነም የጌታችን ሞትና ትንሣኤ ድንገተኛና የግድ ሳይሆን ታውቆ ያደረና የውድ እንደሆነ ከዚህ እውነታ እንረዳለን፤

ጌታችን ይህንን ተግባር በውድ ፈቃዱ የፈጸመው በእግዚአብሔር አሰራር ከዚህ ውጭ የዓለም ድኅነት የሚከናወንበት ዕድል ስለሌለ ነው፤ በእግዚአብሔር አሰራር ኃጢአትና በደል የሚሰረዘው በቤዛዊ መሥዋዕት ብቻ እንደሆነ ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ በነበረው የቤዛዊ መሥዋዕት አቀራረብ የታወቀ ነው፤

በመሆኑም የሰውን ምልአት ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ሰርዞ ሰውን ከሞት ቅጣት ነጻ ለማውጣት ብቃት ያለው ቤዛዊ መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነበረበት፤ ይሁን እንጂ ለዚህ ዓይነቱ ቤዛዊ መሥዋዕት ብቁ የሆነ ከፍጡራን ወገን ስላልተገኘ "ለሊሁ መሥዋዕት፣ ወለሊሁ ሠዋዒ፣ ወለሊሁ ተወካፌ መሥዋዕት ማለትም" ራሱ መሥዋዕት፣ ራሱ መሥዋዕት አቅራቢ ሊቀ ካህናት፣ ራሱ ተወካፌ መሥዋዕት አምላክ ሆኖ የቤዛነታችንን መሥዋዕት ራሱ በራሱ ለራሱ አቀረበ"፤

በዚህ ቤዛዊ መሥዋዕትም እኛን ከሞት ቅጣት ነጻ አደረገን፤ትንሣኤያችንንም በትንሣኤው አበሰረ፣ በክርስትና ሃይማኖት የሚገኝ ፍጹም ድኅነትና ነጻነት በዚህ ቤዛዊ መሥዋዕት ላይ የተመሠረተ ነው፤

የተወዳደችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን በትንሣኤው ትንሣኤያችንን ሲያበስረን የትንሣኤ ሰዎች ሆነን በመንፈስና በሞራል በማደግ ብርሃናተ ዓለም ልንሆን እንጂ እንደገና የጨለማው ኃይል መሳሪያዎች ልንሆን አይደለም፤ የሞቱና የትንሣኤው ምስጢር በንጹሁ ኅሊናችን ካስተዋልነው ውስጣችን እሱን ለመቀበል የሚያዳግተው አይደለም፤

ከዚህ አንጻር በትንሣኤው አምነን ትንሣኤያችንን እየተጠባበቅን የምንገኝ ሕዝበ ክርስቲያን በቅን አስተሳሰብ፣በርቱዕ አእምሮና በኃይለ ሃይማኖት እየታገዝን ጨለማውን ዓለም ወደ ብርሃን ለመለወጥ መጣርና መትጋት ይጠበቅብናል፤

የጨለማው ዓለም መንፈስ ሊያጠፋን ካልሆነ በቀር እንደማይጠቅመን በተጨባጭ የምናውቀው ነው፤ ወደድንም ጠላንም ያለን ብቸኛ አማራጭ ብርሃንን መከተል ነው፤ እሱም እግዚአብሔር ነው በብርሃን የሚመላለስ እንደማይጐዳ በእግዚአብሔር የሚኖርም ተጐድቶ አያውቅምና ነው፤

ዓለም እንደ አጠቃላይ በጨለማ ተውጦ ሲተረማመስ የሚታየው ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ምርጫው ስላደረገ ነው፤ ስለሆነም የኛ ምርጫ ብርሃን የሆነውን እግዚአብሔር እንዲሆን የቤተ ክርስቲያን የዘወትር ጥሪ ነው ፤

በመጨረሻም፡-

የትንሣኤ በዓላችንን ስናከብር ዓለም በክፋቱ ያጨለመባቸውን ወገኖች ጦማችው እንዳይውሉ ካለን ከፍለን የተራቡትን በማብላት፤ የተጠሙትን በማጠጣት፣ የታረዙትን በማልበስና የዕለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ በማድረግ ቀኑ ለሁላችንም ፍጹም ብርሃን ሆኖ ይውል ዘንድ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪያችንን በእግዚአብሑር ስም እናስተላልፋለን፤

መልካም የትንሣኤ በዓል ያድርግልን!!

“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ"

“ወስብሐት ለእግዚአብሔር

                   አባ ማትያስ
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤

          ሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
             አዲስ አበባ' ኢትዮጵያ
1👍1
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

ሰኞ
ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

ማክሰኞ
ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

ረቡዕ
አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

ሐሙስ
አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

አርብ
ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

ቅዳሜ
ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

እሁድ
ዳግም ትንሳኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡


https://t.me/neamn_media
1
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
የ125 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀራው።  ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ JOIN REQUEST ላኩ 🏃‍♀️🏃‍♂️
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
🙏የሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙሮችን ለማግኘት ይቀላቀሉን 👇👇👇