ገብር ኄር
የዐብይ ጾም ስድስተኛ እሑድ(ሳምንት)
ይህን ሳምንት ቅድስት ቤተክርስቲያን ”ገብርኄር” የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች፡፡ ገብርኄር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ. 25:14-30 ነው፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ መስሎ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የዛሬው ወንጌል አስተማሪ የሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል፡፡ በተለይ ምንም እንኳን የቤተክርስቲያን ሓላፊነት የእገሌና የእገሊት ተበሎ ባይወሰንም ቤተ ክርስቲያን ባላት የአገልግሎት መዋቅር መሠረት የሓላፊነትን ቦታ ይዘው ለሚያገለግሉ ሰዎች አትኩሮት ሊሰጡባቸው የሚገባቸውን ነጥቦች ይጠቁማል፡፡ ይህን ለማየት ያመቸን ዘንድ ከታሪኩ የመጀመያ ክፍል በመነሣት ዋና ዋና የሆኑ ዐሳቦችን በአትኩሮት መመርመር ጠቃሚ ነው፡፡
በምሳሌያዊው ታሪክ መጀመሪያ ላይ የምናገኘው አንድ መንገድ ሊጀምር ያሰበ ሰው ከመሔዱ በፊት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት እንዲሁም ለሌላኛው አንድ መክሊት ነግደው ያተርፉበት ዘንድ እንደሰጣቸው ነው፡፡ ገና ከታሪኩ መጀመሪያ እንደምንረዳው የአገልጋዮቹ ጌታ ምንም እንኳን እርሱ ለመንገድ ቢዘጋጅም ሀብቱ ግን በተዘጋ ቤት ውስጥ ተቆልፎበት እንዲቀመጥ አልፈለገም፡፡ በዚህም አገልጋዮቹን ጠርቶ ገንዘቡን በአደራ ተቀብለው እንዲያተርፉበት ማዘዙን እንደማስረጃ ልናቀርብ እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ማትረፍ በመፈለጉ ብቻ ገንዘቡን ያለአግባብ አልበተነም፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ቀረቤታ የነበራቸውን አገልጋዮቹን ጠርቶ ያውም እንደየችሎታቸው መጠን ሓላፊነቱ ሳይከብዳቸው እንዲሠሩበት ገንዘቡን አከፋፈላቸው፡፡
ይህ ጌታ ቅንነትና ርኅራኄ የበዛለት እንደሆነ የሚያመላክተን ነገር አለ፡፡ ይኸውም ለአገልጋዮቹ ሓላፊነትን ቢሰጥም እንኳን ከእነርሱ ጋር በነበረው ቀረቤታ ማን ምን መሥራት ይችላል የሚለውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለእያንዳንዳቸው እንደ ሓላፊነት የመሸከም አቅማቸው አምስት ሁለት አንድ እያደረገ መስጠቱ ነው፡፡ ምናልባት ስስት ባልተላቀቀው ስሜት ለሚያስብ ሰው የዚህ ጌታ መክሊት አሰጣጥ አድልዎ ያለበት ሊመስለው ይችላል፡፡ ታሪኩን እስከ መጨረሻው ብንከታተለው ግን የሚያሳየን የባለ መክሊቱን ባለቤት ቅንነት ነው፡፡ ቀጥለን እንደምናነበው ይህ ጌታ ለአገልጋዮቹ አትርፉበት ብሎ መክሊቱን ሰጥቷቸው በሔደበት ሀገር አልቀረም፡፡ ይልቁንም እያንዳንዱ በተሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው እንደመጣ እናነባለን፡፡ ስለዚህ አገልጋዮቹ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩ እንደሚጠይቃቸው እያወቀ ከአቅማቸው በላይ የሆነ መክሊትን በመስጠት ምን ሠርተው የተሰጣቸውን መክሊት ያህል ማትረፍ እንደሚችሉ በማሰብ እንዲጨነቁ አልፈለገም፡፡ በተቃራኒው የምናየው ያለምንም ጭንቀት ከአእምሯቸው በላይ ሳይሆን ባላቸው ኀይል ተጠቅመው መሥራትና ማትረፍ የሚችሉትን ያህል መክሊት እንደሰጣቸው ነው፡፡
ከብዙ ጊዜም በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው ሲመጣ አምስት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ አምስት እንዲሁም ሁለት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ ሁለት መክሊት አትርፎ ጌታቸው ፊት እንደቆሙ ያ ጌታም በእነዚህ አገልጋዮቹ ታማኝነት ተደስቶ ወደ ደስታው እንዳስገባቸው እናያለን፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ያ አንድ መክሊት ተቀብሎ የነበረው ምድርን ቆፍሮ ያተርፍባት ዘንድ የተሰጠችውን መክሊት እንደቀበረ ከዚህም አልፎ ምን አደረክባት ተብሎ ሲጠየቅ የአመጽ ንግግር እንደተናገረ በዚህ ከፊቱ ያዘነው ጌታውም ያን ክፉ አገልጋይ እንዲቀጣ እንዳደረገው አናነባለን፡፡
በዚህኛው ክፍል ከተጠቀሰው ታሪክ ሦስቱን አካላት ማለት የመክሊቱን ሰጪ ጌታ፣ በጎ የተባሉ አገልጋዮችና ክፉ እና ሰነፍ የተባለውን አገልጋይ በተናጥል እንመልከታቸው፡፡
1. የአገልጋዮቹ ጌታ፡–
ይህ ሰው ለገንዘቡ ጠንቃቃ ከመሆኑ ባሻገር በአገልጋዮቹ ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለው እናያለን፡፡ በክፉው አገልጋይ ላይ ባለመታዘዙ ምክንያት የፈረደበትን ፍርድ /ልቅሶና ጥርስ ማፏጨት ወዳለበት በውጪ ወዳለ ጨለማ እንደአወጡት/ ስንመለከት የሚያሳየን የአገልጋዮቹን ጌታ ታላቅ ሥልጣን ነው፡፡ ምንም እንኳን ሥልጣኑ ጽኑ ቢሆንም ይህ ጌታ ፍርዱ ግን በእውነት ላይ የተመረኮዘ መሆኑን ደግሞ በድካማቸው ታግዘው በተሰጣቸው መክሊት ላተረፉት በጎ አገልጋዮች የሰጣቸውን ፍጹም ደስታ መጥቀስ ይቻላል፡፡
2. በጎ አገልጋዮች:-
በአገልጋዮቹ ጌታ በጎ አገልጋዮች የተባሉት አምስት መክሊት የተቀበለውና ሁለት መክሊት የተቀበለው ናቸው፡፡ እዚህ ጋር ማስተዋል የሚገባው እነዚህ ሁለቱ አገልጋዮች በጎ አገልጋዮች ለመባል ያበቃቸው አስቀድመው ብዙ ወይንም የተሻለ ቁጥር ያለው መክሊት ለመቀበል መብቃታቸው አይደለም፡፡ ጉዳዩ የመክሊቱ ቁጥር ሳይሆን በተሰጣቸው መክሊት መጠን የሚገባቸውን ያህል ደክመው ማትረፍ መቻላቸው ነው፡፡ ወይንም ያ ባለ አንድ መክሊት አገልጋይ ከሁለቱ ያሳነሰው ከአንድ በላይ መክሊት መቀበል የማይችል መሆኑ ሳይሆን በዚያችው በአንዷ መክሊት እንኳን መሥራት አለመቻሉ ነው፡፡
3. ክፉና ሰነፍ አገልጋይ:-
ይህ ሰው የተጠቀሱ ሦስት መሠረታዊ ችግሮች አሉበት፡፡
የአገልጋዮቹ ጌታ ወደ መንገድ ሊሔድ በተዘጋጀበት ወቅት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደችሎታቸው ገንዘቡን ሲሰጣቸው አትርፈው እንዲቆዩት ነው፡፡ ከላይ እንደተነገጋገርነው እንደ አቅማቸው መስጠቱም አቅማቸው በሚፈቅደው የሥራ ደረጃ እንዲሰማሩ በማሰብ ነበር፡፡ ይህ ሰነፍ አገልጋይ ግን ያደረገው ከታዘዘበት ዓላማ በተቃራኒው መልኩ ነው፡፡ ሊሠራበት የሚገባውን መክሊት ቀበረው፡፡ ይህም ለጌታው ትዕዛዝ ያለውን ቸልተኝነት ያሳያል፡፡
ጌታው በመጣ ጊዜ አመጽ የተመላበት የሐሰት ንግግር ተናግሯል፡- ከሔደበት ቦታ ተመልሶ ጌታው በተሰጠው መክሊት ምን እንዳደረገ ሲጠይቀው «አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበትም የምትሰበሰብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ ስለፈራሁም ሔድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፡፡» ሲል መለሰለት፡፡ ይህ ንግግር ከአመጽ ንግግርነቱ በተጨማሪ ውሸት አለበት፡፡ ምክንያቱም እርሱ እንዳለው ጌታው ካልዘራበት የሚያጭድ ካልበተነበት የሚሰበሰብ ጨካኝ ሰው ቢሆን ኖሮ ያደርግ የነበረው ምንም መክሊት ሳይሰጠው ከነትርፉ ሁለት መክሊቶችን ይጠይቀው ነበር፡፡ ነገር ግን ተጽፎ የምናነበው ትርፉን ከመጠየቅ በፊት አንድ መክሊት ሰጥቶት እንደበረ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አስቀድሞ ገንዘቡን ዘርቶ ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ጌታ ዘርቷልና ማጨድ ይገባዋል፤ በትኗልና መሰብሰብም መብቱ ነው፡፡
እርሱ መሥራት ሲሳነው እንኳን ዕድሉን ለሌሎች አልሰጠም፡- ይህ ሰው የተሰጠው መክሊት በትርፍ ሊመለስ እንደሚገባው ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ምክንያቱም ገና ሲቀበል ከጌታው የተቀበለው ትዕዛዝ ነውና፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን መውጣት መውረዱ ቢከብደውም ወጥተው ወርደው ማትረፍ ለሚችሉ ሰዎች አለመስጠቱ ተጨማሪ ጥፋቱ ነው፡፡ ይህን እንዳያደርግ ያሰረው ደግሞ ውስጡ የተቀረጸው የአመጽ መንፈስ ነው፡፡ ጌታው መጥቶ ስለ ትርፉ ሲጠይቀው የሚመልስለትን ረብ የለሽ ምክንያት እንደ መከላከያ አድርጎ ማሰቡ አእምሮው ሌላ አማራጭ እንዳያስብ የዘጋበት ይመስላል፡፡

❤2
የመጽሐፍ ቅዱስ መተርጉማን አባቶች የዚህን ምሳሌያዊ ታሪክ ምስጢር ሲያስተምሩ የአገልጋዮቹ ጌታ የፍጡራን ጌታ የሆነ የእግዚአብሔር ምሳሌ እንደሆነ እንዲሁም ሦስቱ አገልጋዮች በተለያየ ደረጃ ያሉ ምዕመናንን እንደሚወክሉ ያስተምራሉ፡፡
ከዚህ የወንጌል ክፍል ምን እንማራለን?
ከተጠቀሰው ታሪክ የምንማራቸው ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ዓበይት የሆኑትን ሁለቱን እንመልከታቸው፡፡
ለእያንዳንዳችን ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ እንዳለ እንረዳበታለን
እግዚአብሔር እያንዳንዳችን በሃይማኖት ሆነን የምናፈራውን ፍሬ ይፈልጋል፡፡ ምንም እንኳን ከእኛ ፍሬን ቢፈልግም ያን ፍሬ ማፍራት የምንችልበትን ኃይል ግን የእግዚአብሔርን ልጅነት ካገኘንበት ከዕለተ ጥምቀት ጀምሮ እንደሚያስፈልገን መጠን እየሰጠን ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበልናቸው ስጦታዎች በቁጥር እጅግ ብዙ ቢሆኑም በዓይነታቸው ግን ለሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው እያንዳንዱ ክርስቲያን ዳግመኛ በመወለድ ምስጢር ያገኘው የእግዚአብሔር ልጅነት ጸጋና ከልጅነት ጋር በተያያዘ የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው (ዮሐ.3፥3)። ሁለተኛው ዓይነት ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድና እንደ ሰውየው አቅም ለተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ማስፈፀሚያ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔር የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ትንቢት መናገር ፣ በተለያዩ ልሳናት መናገር ፣ አጋንንትን ማስወጣት … የመሳሰሉት ከዚህኛው ዓይነት ስጦታ የሚመደቡ ናቸው (1ኛ ቆሮ.12፥4)፡፡
በመጀመሪያውም ይሁን በሁለተኛው ዓይነት ስጦታ ተቀባዮች ዘንድ ግን ብዙ የሚያሳዝኑ ችግሮች አሉ፡፡ በዳግመኛ መወለድ ምሥጢር (በ40 ና 80 ቀን ጥምቀት) ስላገኘነው የልጅነት ጸጋ ጊዜ ሰጥቶ የሚያስብ ክርስቲያን ማግኘት በዚህ ዘመን በጣም አዳጋች ነው፡፡ በዓመት ውስጥ ክርስቲያንነቱ ለጥምቀት በዓልና ለመስቀል ደመራ ካልሆነ ትዝ የማይለው ቁጥሩ ቀላል አይደለም፡፡ ከዚህ የከፋው ደግሞ ከቤተ ዘመድ አንድ ሰው ምናልባትም ራሱም ሊሆን ይችላል ነፍሱ ከሥጋው ካልተለየች ወደ ቤተ ክርስቲያን ደጅ ብቅ አይልም፡፡
እግዚአብሔር ለእኛ የልጅነትን ጸጋ በመስጠቱ ለእኛ ያለውን ጥልቅ ፍቅሩን አሳይቶናል፡፡ ምክንያቱም ልጅነታችን ዋጋ ተከፍሎበታልና፡፡ እንዲሁ በቀላሉ አይደለም ልጆች የተባልነው፡፡ እኛ ልጅነትን እንድንቀበል አምላክ መከራን ተቀብሏል፡፡ የጥምቀታችን ውሃ የፈሰሰው በጦር ከተወጋው ከጌታ ጎን ነው (ዮሐ.19፥24)፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ይሄንን ሁሉ ሲያመለክት ”የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደሰጠን እዩ፡፡” (1ኛ ዮሐ.3-1) እኛ ልጆቹ እንሆን ዘንድ እግዚአብሔር ካሳየን የአባትነት ፍቅር በተጨማሪ ልጆቹ ስለመሆናችን የገባልንም ተስፋ ከአዕምሮ በላይ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ምዕመናን በላከው መልእክቱ ”እንኪያስ እናንተ ልጆች ናችሁ እንጂ ባሮች አይደላችሁም፡፡ ልጆች ከሆናችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ፡፡” (ገላ.4:7) በማለት ስለሚጠብቀን ተስፋ ነግሮናል፡፡
ስለዚህ በጣም ልንጠነቀቅበት የሚገባን የመጀመሪያው መክሊታችን ልጅነታችን መሆኑን መረዳት ያስፈልገናል፡፡ በዚህም መክሊት እንድንሰራ የታዘዝናቸውን ምግባራት እንድናፈራ የሚጠበቅብንን ፍሬዎች ማፍራት አለብን፡፡ ያለበለዚያ መክሊቱን እንደቀበረው ሰው መሆናችን ነው፡፡
እያንዳንዱ ስጦታ እንደሚያስጠይቅ እንረዳለን
እግዚአብሔር ያለ አንድ አላማ ለሰዎች ሓላፊነትን የሚያሰከትል ስጦታ አልሰጠም አይሰጥምም፡፡ ማንም ከእግዚአብሔር የተቀበለ ሰው የተሰጠው ስጦታ ለሆነ አላማ ነውና ጥያቄ አለበት፡፡ ጠያቂው ደግሞ የስጦታው ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ ማንም ይሁን ማን ግን ስለተሰጠው መክሊት ባለቤቱ ከፊቱ አቁሞ እንደሚጠይቀው መዘንጋት የለበትም፡፡እንግዲህ በአጠቃላይ መክሊት የተባለ ጸጋ ስጦታ ሲሆን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታ ሰጥቶናል፡፡ በተሰጠንም ስጦታ ልናገለግልበት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪ መክሊት ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ የሰማናትን ቃለ እግዚአብሔር ለሌላው ማሰማት ይገባናል ፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ማሰማቱ ብቻ ነው፡፡ በልቦናው አድሮ ሥራ የሚሠራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ በመሆኑም እርሱ በሰጠን የአገልግሎት በር ጸጋ በታማኝነት በማገልገል በሕይወት ዘመናችን ሁሉ መንፈሳዊውን ሀብት የምናተርፍ እንሆን ዘንድ የተላለፈልን አምላካዊ ምክር ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የተጠራነው ፍሬ ልናፈራና ሌላውንም ልናተርፍ መልካም ሥራን ልንሠራ እንጂ የሥጋችንን ፈቃድ በመከተል የኃጢአት ባሮች ልንሆን አይደለም፡፡ መጽሐፍ እንደሚነግረን ¨ሁሉ እንደተጠራ እንዲሁ ይኑር” (፩ኛ ቆሮ. ፯፥፳) ይላልና።
አሁን ባለንበት ወቅት በጎና ታማኝ አገልጋይ መሆን እንዳንችል ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ የችግሮቹም መሠረታዊ ምንጭ በተጠሩበት ጸንቶ መቆም ፈጽሞ አለመቻልና ለሥጋዊ ጥቅም ብቻ በማድላት ሓላፊነትን መዘንጋት ናቸው፡፡ በሥጋዊ አምሮት ፍላጎትና ምርጫ ውስጥ ደግሞ መንፈሳዊ ጸጋንና በረከትን ለማግኘት የሚያስችለንን የታማኝነት ሥራን መሥራት አይቻልምና በታማኝነት ከምናድነው ሰው ይልቅ መክሊታችንን በመቅበር ባለመታመን መሰናክል የምንሆንበት ሰው ሊበዛ እንደሚችል አያጠራጥርም፡፡ በመሆኑም ከእርሱ ዘንድ እንደ ዓቅማችን የተሰጠንን መንፈሳዊ ዕውቀት ሀብትና አገልግሎት ለሌላው በማድረስ መክሊታችንን ልናበዛ የምንችለውና አገልግሎታችን ወይም ክርስትናችን ውጤታማ የሚሆነው ምርጫችንን አውቀን እንደቃሉ ሆነንና ጸንተን ስንገኝ ብቻ ነው፡፡ ይህ ባለመሆኑ ነው ዛሬ ብዙዎቻችን በሕይወታችን ሌላውን ማትረፍ አቅቶን በእግዚአብሔርና በሰውም ዘንድ በሚያስወቅስ የስንፍና መንገድ ላይ ቆመን የምንገኘው፡፡ ስለዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው “ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ” (ማቴ. ፳፬፥፵፪) ብሎናል፡፡
ቃሉን የሰማንና የምናውቅ ሁላችን በሞቱ ላዳነን፣ በልጅነት ጸጋም ላከበረን፣ በትንሣኤውም ላረጋጋን፣ በመስቀሉ ጥልን ገድሎ ከራሱ ጋር ላስታረቀን፣ በውኂዘ ደሙም ሕይወትን፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ በረከትንና ዘለዓለማዊ ደስታን ለሰጠን አምላካችን በመታዘዝ አቅማችን በሚፈቅደው አገልግሎት ጸንቶ መገኘት ተገቢ ነው፡፡ በአገልግሎት የመጽናት ምልክቱ ደግሞ አትራፊነት ነው፡፡ ቅዱሳን ነቢያት፣ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ቅዱሳን ሊቃውንት በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ በአትራፊነት ይታወቃሉ፡፡ ለማትረፍ ግን ራሳቸውን ለእውነት ለአገልግሎት ለመከራ አሳልፈው በመስጠት ነው፤ በትንሹ መታመን ሲባል የእኛ አገልግሎት ከፈጣሪ ቸርነት ጋር ስለማይመጣጠን ነው፤ በብዙ እሾምሃለሁ ማለቱም በመንግሥተ ሰማያት ለዘለዓለም ከብሮ መኖርን ነው፡፡
ከቅዱሳን ነቢያትም ሐዋርያትም ሰብአ አርድእትም ሊቃውንትም የሰማነውና ያየነው እውነት ምንጊዜም ትጉህ ሠራተኛ የሚሠራው መልካም ሥራ ሁሉ ለቤተ ክርስቲያንም ለሀገርም የሚሰጠው ጥቅም እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ዘመን ልዑል እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን፤ ምእመናንን፤ ሀገርንና ሕዝብን ለመምራት የጠራንና የመረጠን፤ በአገልግሎት ዐደባባይ ያስቀመጠን ሰዎች እጅግ ዕድለኞች ነን፤ ምክንያቱም የሕዝብን ችግርና አቤቱታ ሰምቶ ተቀብሎ መፍትሔ መስጠት ትርፋማነት ነውና፤ ትርፋማነት ደግሞ ወደ ትልቁ የሹመት መሰላል መውጣት ነው፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ አገልግሎታችን ተደናቅፎ የሕዝባችን ችግር ሳይፈታ ቀርቶ የአገልግሎታችን ተቆጣጣሪ አምላካችን ቢጎበኘን “አንተ ሰነፍ አገልጋይ”

Telegram
ነአምን media
Buy adds:- https://telega.io/c/neamn_media
<< ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአበሔር!>>
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ
#ትምህርቶች
#ዝማሬዎችና
#ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስነ-ፅሁፎች
የሚለቀቁበት ቻናል ነው።
ለሁሉም መረጃና አስተያየትና በቻናሉ ላይ ለመፃፍና ለመሳተፍ @theofloss ያናግሩን መረጃውንም ያካፍሉን።

🥰1
ተብለን ወደ ውርደት አዘቅት እንዳንላክ መጠንቀቁ አይከፋም፡፡ የመሾም የመሻር የማሳደግና የማውረድ ሥልጣን የእግዚአብሔር ነውና፡፡ “ከእናንተ መካከል አንዱን እንኳ እንዳናስቸግር ቀንም ሌሊትም እንሠራ ነበር” (፩ኛ ተሰ. ፪፥፱) በጎና ታማኝ አገልጋዮች ሆነን እንድንገኝ ጠንክረን ልንሠራ ይገባናል፡፡
በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦
-፪ኛ ጢሞ ፪፥፩-፲፮
-፩ኛ ጴጥ ፭፥፩-፲፪
-የሐዋ ሥራ ፩፥፮-፱
ምስባኩም፦ መዝ ፴፱፥፰
"ከመ እግበር ፈቃድከ መከርኩ አምላኪየ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ"
"አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድኩ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው በታላቅ ጉባዔ ጽድቅህን አወራሁ"
ወንጌሉም፦ ማቴ ፳፭፥፲፬-፴፩
https://t.me/neamn_media
https://t.me/neamn_media
በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦
-፪ኛ ጢሞ ፪፥፩-፲፮
-፩ኛ ጴጥ ፭፥፩-፲፪
-የሐዋ ሥራ ፩፥፮-፱
ምስባኩም፦ መዝ ፴፱፥፰
"ከመ እግበር ፈቃድከ መከርኩ አምላኪየ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ"
"አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድኩ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው በታላቅ ጉባዔ ጽድቅህን አወራሁ"
ወንጌሉም፦ ማቴ ፳፭፥፲፬-፴፩
https://t.me/neamn_media
https://t.me/neamn_media
Telegram
ነአምን media
Buy adds:- https://telega.io/c/neamn_media
<< ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአበሔር!>>
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ
#ትምህርቶች
#ዝማሬዎችና
#ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስነ-ፅሁፎች
የሚለቀቁበት ቻናል ነው።
ለሁሉም መረጃና አስተያየትና በቻናሉ ላይ ለመፃፍና ለመሳተፍ @theofloss ያናግሩን መረጃውንም ያካፍሉን።
<< ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአበሔር!>>
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ
#ትምህርቶች
#ዝማሬዎችና
#ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስነ-ፅሁፎች
የሚለቀቁበት ቻናል ነው።
ለሁሉም መረጃና አስተያየትና በቻናሉ ላይ ለመፃፍና ለመሳተፍ @theofloss ያናግሩን መረጃውንም ያካፍሉን።
✟ገብር ኄር ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ ✟
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ'
✧ገብር ኄር ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ የዓቢይ ፆም ስድስተኛ ሳምንት ቸር አገልጋይ ትምህርታዊ ዝማሬ||
✞ቸር አገልጋይ ማነው✞
ቸር አገልጋይ ማነው ለንጉስ የታመነ
መክሊቱን ያልቀበረ አትርፎ የከበረ
። አዝ-----
ባለ አምስቱ መክሊት መልካም ያደረገው
በመውጣት በመውረድ አትርፎ መጥቶ ነው
በጥቂቱ ታምኖ በብዙ የተሾመው
ባለ አምስቱ መክሊት ሊቀ ጳጳሱ ነው
። አዝ-----
ሣይሠለች የተጋ ባለሁለት መክሊት
የታመነ እረኛ በፍቅር እና በእምነት
ግባ የተባለው ወደ ጌታው ደስታ
አጥምቆ ያቆርባል ካህኑ የጌታ
። አዝ-----
ለሚበልጠው ፀጋ ተጠርቶ የነበረ
መክሊቱን ደብቆ ቆፍሮ የቀበረ
ሰነፍ ባሪያ ተብሎ ወደ ፍርድ ተጣለ
ማኔ ቴቄል ፋሬስ በአምላክ ፊት ቀለለ
። አዝ-----
ፈቃድህን ማድረግ ነፍሱ ለምትወደው
ወንጌልህን መግለፅ የየዕለት ግብሩ ነው
ህግህ ለዘለዓለም ተፅፎ ይኖራል
በታላቅ ጉባኤ ፅድቅህ ይነገራል
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
@neamn_media
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞ቸር አገልጋይ ማነው✞
ቸር አገልጋይ ማነው ለንጉስ የታመነ
መክሊቱን ያልቀበረ አትርፎ የከበረ
። አዝ-----
ባለ አምስቱ መክሊት መልካም ያደረገው
በመውጣት በመውረድ አትርፎ መጥቶ ነው
በጥቂቱ ታምኖ በብዙ የተሾመው
ባለ አምስቱ መክሊት ሊቀ ጳጳሱ ነው
። አዝ-----
ሣይሠለች የተጋ ባለሁለት መክሊት
የታመነ እረኛ በፍቅር እና በእምነት
ግባ የተባለው ወደ ጌታው ደስታ
አጥምቆ ያቆርባል ካህኑ የጌታ
። አዝ-----
ለሚበልጠው ፀጋ ተጠርቶ የነበረ
መክሊቱን ደብቆ ቆፍሮ የቀበረ
ሰነፍ ባሪያ ተብሎ ወደ ፍርድ ተጣለ
ማኔ ቴቄል ፋሬስ በአምላክ ፊት ቀለለ
። አዝ-----
ፈቃድህን ማድረግ ነፍሱ ለምትወደው
ወንጌልህን መግለፅ የየዕለት ግብሩ ነው
ህግህ ለዘለዓለም ተፅፎ ይኖራል
በታላቅ ጉባኤ ፅድቅህ ይነገራል
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
@neamn_media
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
በእነዚህ ነገሮች ሀገር ትፈርሳለች ።
፩ . የኃጢአት ባርያ የሆነ ሰው፦ በነገሠ ፣በተሾመ፣አለቃ በሆነ ጊዜ ነው ።
፪ . ሊሠራ የማይወድ ሰነፍ እህልን በጠገበ ጊዜ ነው ።
፫ . በሥራዋ የተናቀች፣የተጠላች ሴት ቸር ባል ባገኘች ጊዜ ነው ።
፬ . ሴት ባርያ እመቤቷን በወረሰች ጊዜ ነው ።
ምሳ ፳፬ ፥
https://t.me/neamn_media
፩ . የኃጢአት ባርያ የሆነ ሰው፦ በነገሠ ፣በተሾመ፣አለቃ በሆነ ጊዜ ነው ።
፪ . ሊሠራ የማይወድ ሰነፍ እህልን በጠገበ ጊዜ ነው ።
፫ . በሥራዋ የተናቀች፣የተጠላች ሴት ቸር ባል ባገኘች ጊዜ ነው ።
፬ . ሴት ባርያ እመቤቷን በወረሰች ጊዜ ነው ።
ምሳ ፳፬ ፥
https://t.me/neamn_media
❤5
ውሻ ነኝ
ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ ባለ ብዙ ታሪክ ሊቀ ጳጳስ ነበር፡፡ በእርሱ ዘመን ታዲያ ብዙ ሰዎች ወደ ክርስትና እየተመለሱ ይጠመቁ ነበር፡፡ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ታዲያ አንዳንዶች የማትደገመዋን አንዲት ጥምቀት እንደ ጠበል ደጋግመው መጠመቅ ጀመሩ፡፡
ቅዱስ ያዕቆብ ለዚህ መላ አበጀ። አንድ ሰው ከተጠመቀ በኋላ በአንገቱ ላይ የማይወልቅ ክር እንዲያስር አደረገ፡፡
በሒደትም ይህን ክር ያሰረ ሰው የተጠመቀ ክርስቲያን መሆኑ ምልክት ሆነ የኋላ ሊቃውንትም ይህንን የማዕተብ ሥርዓት ከኦሪት እስከ ሐዲስ አጣቅሰው አስፋፍተው አስተማሩበት፡፡
ቅዱስ ያዕቆብ በክርስቲያኖች ላይ ይህንን ክር በማሰሩ ታዲያ የክርስትና ተቃራኒዎች ዘበቱበት ‘ብለህ ብለህ ደግሞ እንደ ውሻ በየሰዉ አንገት ላይ ክር ማሰር ጀመርህ?’ ብለው ተሳለቁበት
ቅዱስ ያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ ፦
‘ውሻ ለጌታው ታማኝ ነው ፤
እኔ ለክርስቶስ ታማኝ ውሻው ነኝ’
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
https://t.me/neamn_media
ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ ባለ ብዙ ታሪክ ሊቀ ጳጳስ ነበር፡፡ በእርሱ ዘመን ታዲያ ብዙ ሰዎች ወደ ክርስትና እየተመለሱ ይጠመቁ ነበር፡፡ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ታዲያ አንዳንዶች የማትደገመዋን አንዲት ጥምቀት እንደ ጠበል ደጋግመው መጠመቅ ጀመሩ፡፡
ቅዱስ ያዕቆብ ለዚህ መላ አበጀ። አንድ ሰው ከተጠመቀ በኋላ በአንገቱ ላይ የማይወልቅ ክር እንዲያስር አደረገ፡፡
በሒደትም ይህን ክር ያሰረ ሰው የተጠመቀ ክርስቲያን መሆኑ ምልክት ሆነ የኋላ ሊቃውንትም ይህንን የማዕተብ ሥርዓት ከኦሪት እስከ ሐዲስ አጣቅሰው አስፋፍተው አስተማሩበት፡፡
ቅዱስ ያዕቆብ በክርስቲያኖች ላይ ይህንን ክር በማሰሩ ታዲያ የክርስትና ተቃራኒዎች ዘበቱበት ‘ብለህ ብለህ ደግሞ እንደ ውሻ በየሰዉ አንገት ላይ ክር ማሰር ጀመርህ?’ ብለው ተሳለቁበት
ቅዱስ ያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ ፦
‘ውሻ ለጌታው ታማኝ ነው ፤
እኔ ለክርስቶስ ታማኝ ውሻው ነኝ’
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
https://t.me/neamn_media
Telegram
ነአምን media
Buy adds:- https://telega.io/c/neamn_media
<< ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአበሔር!>>
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ
#ትምህርቶች
#ዝማሬዎችና
#ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስነ-ፅሁፎች
የሚለቀቁበት ቻናል ነው።
ለሁሉም መረጃና አስተያየትና በቻናሉ ላይ ለመፃፍና ለመሳተፍ @theofloss ያናግሩን መረጃውንም ያካፍሉን።
<< ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአበሔር!>>
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ
#ትምህርቶች
#ዝማሬዎችና
#ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስነ-ፅሁፎች
የሚለቀቁበት ቻናል ነው።
ለሁሉም መረጃና አስተያየትና በቻናሉ ላይ ለመፃፍና ለመሳተፍ @theofloss ያናግሩን መረጃውንም ያካፍሉን።
❤1
የቆሸሸው ቅርጫት
በአንድ ገጠራማ አካባቢ ከከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ እርሻ ውስጥ አንድ አረጋዊ አባት ከልጅ ልጃቸው ጋር ይኖሩ ነበር። አረጋዊው በየማለዳው እየተነሱ በኩራዝ መብራት መጽሐፍ ቅዱስን እና ዳዊትን ያነቡ ነበር። የልጅ ልጃቸውም አያቱን እንደ አርአያ በመውሰድ እሳቸውን ለመምሰል ይጥራል።
አንድ ቀን ልጁ አያቱን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- "አባባ! እኔም እንደ እርስዎ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እሞክራለሁ። ነገር ግን የማነበው ነገር እምብዛም አይገባኝም፤ የሚገባኝንም ቢሆን መጽሐፉን ስዘጋው ወዲያውኑ እረሳዋለሁ። ታዲያ የማነበው ነገር ወዲያው ከጠፋብኝ ማንበቤ ምን ጥቅም አለው?"
አረጋዊው አባት በምድጃው ላይ የነበረውን የከሰል ማራገፊያ አሮጌ ቅርጫት ወደ ልጁ ገፋ አደረጉና እንዲህ አሉት፡- "ልጄ፣ እስቲ ይህንን የከሰል ቅርጫት ይዘህ ወደ ወንዙ ሂድና ውሃ ቀድተህ አምጣልኝ።"
ልጁም የታዘዘውን ለማድረግ ቅርጫቱን ይዞ ወደ ወንዝ ወረደ። ቅርጫቱን ውሃ ውስጥ ነክሮ በፍጥነት ወደ ቤት ለመድረስ ቢሮጥም፣ ልክ ቤት ሲደርስ ውሃው በቅርጫቱ ቀዳዳዎች ፈስሶ ያልቃል። አያቱ ሳቁና "በሚቀጥለው ጊዜ ፈጠን ማለት አለብህ" ብለው እንደገና ላኩት።
ልጁ በድጋሚ ሞከረ፣ ጠንክሮ ሮጠ፣ ነገር ግን ቅርጫቱ ውሃ ሊይዝለት አልቻለም። አያቱ ለሶስተኛ ጊዜ ላኩት። ልጁ እያለከለከ፣ "አባባ፣ ይህ እኮ የማይቻል ነገር ነው! ቅርጫት ውሃ አይይዝም!" አለ። አያቱ ግን "እኔ የጠየቅሁህ ውሃ እንድታመጣ ነው፤ እስቲ በድጋሚ ሞክር" አሉት።
ልጁ የማይቻል መሆኑን ለአያቱ ለማሳየት፣ ውሃውን ቀድቶ በፍጥነት ሮጠ፤ ነገር ግን አሁንም ባዶውን ደረሰ። በንዴት ቅርጫቱን ወርውሮ፣ "አየህ አባባ! ምንም ጥቅም የለውም!" አለ።
አረጋዊው አባት ፈገግ አሉና፣ "ምንም ጥቅም የለውም ብለህ ታስባለህ? እስቲ ቅርጫቱን ተመልከተው" አሉት።
ልጁ ቅርጫቱን በትኩረት ተመለከተ። ቅድም ከሰል ተሸክሞ ያጠቁረው፣ የቆሸሸውና ያረጀው ቅርጫት፣ አሁን ግን በውሃው ተለቅልቆ ከውስጥም ከውጭም ነፅቷል። አዲስ እስከሚመስል ድረስ ጽድት ብሏል።
አያቱ ቀጠሉና እንዲህ አሉ፡- "ልጄ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስታነብ የሚሆነውም ይኸው ነው። ምን እንዳነበብክ ሊጠፋህ ይችላል፣ ወይንም ላይገባህ ይችላል። ነገር ግን ቃሉን ባነበብክ ቁጥር ልክ እንደዚህ ቅርጫት፤ ከውስጥህ ያለውን ቆሻሻ፣ ክፋትና ኃጢአት እያጠበ ያነጻሃል። ውሃው ባይቀመጥም ቅርጫቱን እንዳፀዳው ሁሉ፣ ቃሉም በልብህ ባይቀመጥ እንኳ ሕይወትህን ይቀድሰዋል።"
የእግዚአብሔር ቃል ለማወቅ ብቻ ሳይሆን ለቅድስና እንደሆነ ያስተምራል። ብንረሳው እንኳን በምናነብበት ቅጽበት ነፍሳችንን የማንጻት ኃይል አለው።
ተስፋ አለመቁረጥ፡ ለውጥ ወዲያውኑ ባይታየንም፣ በመንፈሳዊ ልምምድ (ጸሎት፣ ንባብ) ውስጥ መመላለስ በራሱ ሳናውቀው ማንነታችንን እየቀረጸውና እያጠራው እንደሚሄድ ያስገነዝባል።
ሼር ✞ https://t.me/neamn_media ✞

❤3
የሥርዓተ ምሕላ ታሪክ
እንኳን ለሆሳዕና ምህላ አደረሳችሁ ምሕላ ማለት ተማሕለለ ማለደ ተማለለ ለመነ አቤት አቤት አለ ምሕላ ያዘ፤ ተማፀነ ካለው ግሥ የተገኘ ነው።
ምሕላ ማለት ልመና ምልጃ፣ የማኅበር የሕዝብ ጸሎት ማለት ነው ምሕላ ከጥንት ከአበው የተመሠረተና ተያይዞ የመጣ በየባህሉ እየተዜመ በየዘመኑ ሲደረስ የቆየ ነው።
ምህላ ማለት እግዚአብሔር በነቢዩ አድሮ
ኑ እንዋቀስ እንዳለው ምህላ ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መዋቀስ ወደ እግዚአብሔር ማልቀስ ማለት ነው።
ምሕላ በሁለት ይክፈላል የመጀመሪያው ቋሚ ምህላ ይባላል ከዓመት ዓመት የሚቀርብ ወይም በየወሩ በየዓመቱ ጊዜውንና ወቅቱን ጠብቆ የሚደረስ ምሕላ ሲሆን ይህም የራሱ ኣፈጻጸም ሥርአት አለው።
ሁለተኛው ወቅታዊ ጊዜያዊ ምሕላ ነው ይህ አባር ቸነፈር ሲነሣ ዝናብ ሲጠፋ አየር ንብረት ሲዛባ በሔራዊ አደጋ ሲመጣ የሚቀርብ ምህላ ነው። በብሉይ ኪዳንም በሐዲስ ኪዳንም ያሉ አበው ሲፈጽሙት የኖረና የሚኖር ስርአት ነው።
በዚህ መሠረት ቅዱስ ያሬድ እነዚህንና ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሰ በዜማው ቃኝቶ መዝሙረ ዳዊትን ለክቶ ቀምሮ ዐረፍተ ክፍል እያወጣ በሚያሳዝንና ልብን በሚነካ ዓለመ ሥጋን እያናናቀ ዓለመ ነፍስን እያጸደቀ ምግባረ ሥጋን እየወቀሰ ምግባረ ነፍስን እያወደሰ በሰማያዊ ዜማ አደራጅቶ ከጥንቱ አብልጦ አጣጥሞ ሥርዓቱን አሲይዞ ለአሥር አዝማን ከፍሎ በየዘመኑና በየሰዓቱ እንዲጸለይ አድርጎታል።
እነዚህ አሥሩ ምህላዎች የሚባሉት ፦
ምሕላ ክረምት፣
ምሕላ ዘዮሐንስ፣
ምሕላ ዘመስቀል፣
ምሕላ ጽጌ፣
ምሕላ ዘስብከት፣
ምሕላ ዘመርዓዊ፣
ምሕላ ዘምኩራብ፣
ምሕላ ዘገብር ኄር፣
ምሕላ ዘሆሣዕና፣
ምሕላ ዘጰራቅሊጦስ ናቸው።
ከእነዚህም ሰባቱ ንቱጋን ሲሆኑ ሦስቱ ምሉዓን ናቸው ።
ምሉዓን የተባሉት ሦስቱ ምህላዎች፡-
ምሕላ ዮሐንስ፣
ምሕላ ስብከት
ምሕላ ሆሣዕና ናቸው።
በእነዚህ ምሕላዎች ‹‹ብፁዕ ብእሲ ዘኢሆረ በምክረ ረሲዓን›› ብሎ መቶ ሃምሳውን መዝሙረ ዳዊት አሥራ አምስቱም መኃልየ ነቢያትን በዜማ ስለሚደረሱ ምሉዓን ተብለዋል።
በሰባቱ ምሕላዎች ግን መዝሙረ ዳዊቱ ሙሉዉን ሳይሆን አርእስቱ ብቻ ስለሚደረስ ንቱጋን ተብለዋል፤ ምሉዕ ማለት በቁሙ የሞላ የበዛ ማለት ነው።
ንቱግ ማለት ደግሞ በተቃራኒው ጎደሎ ያልሞላ ማለት ነው። አንድም ዐቢይ ምህላ ንዑስ ምህላ ይባላሉ። እነዚህም ምህላዎች የሚውሉበት ቀን
፩ኛ. ምህላ ዘክረምት በዓርብ፣
፪ኛ. ምህላ ዘዮሐንስ በረቡዕ፣
፫ኛ. ምህላ ዘመስቀል በዐርብ፣
፬ኛ. ምህላ ዘጽጌ በረቡዕ፣
፭ኛ. ምህላ ዘስብከት በዐርብ፣
፮ኛ. ምህላ ዘመርዓዊ በረቡዕ፣
፯ኛ. ምህላ ዘምኩራብ በዐርብ፣
፰ኛ. ምህላ ዘገብር ኄር በረቡዕ፣
፱ኛ. ምሕላ ዘሆሣዕና በዐርብ፣
፲ኛ. ምህላ ዘጰራቅሊጦስ በረቡዕ ይውላሉ።
ከእነዚህ ምህላዎች አንዱ የዛሬው ተጽኢኖ ተብሎ የሚጠራው የሆሳዕና ምህላ ነው። 150 መዝሙረ ዳዊት በዜማና በንባብ እየተቀናጀ የሚቀርብበት የምህላዎች ሁሉ አውራ ነው።
መ/ር ነቢዩ ኤልያስ

ኢሳ ፩ ፥ ፲፭፣

ኢዩ ፩ ፥ ፲፬፣ ማቴ ፲፯ ፥ ፲፬ ዘፀአት ፴ ፥ ፲ ኢዩ ፲ ፥ ፲፬ ኢዩኤል ፪፥ ፲፭
በዚህ መሠረት ቅዱስ ያሬድ እነዚህንና ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሰ በዜማው ቃኝቶ መዝሙረ ዳዊትን ለክቶ ቀምሮ ዐረፍተ ክፍል እያወጣ በሚያሳዝንና ልብን በሚነካ ዓለመ ሥጋን እያናናቀ ዓለመ ነፍስን እያጸደቀ ምግባረ ሥጋን እየወቀሰ ምግባረ ነፍስን እያወደሰ በሰማያዊ ዜማ አደራጅቶ ከጥንቱ አብልጦ አጣጥሞ ሥርዓቱን አሲይዞ ለአሥር አዝማን ከፍሎ በየዘመኑና በየሰዓቱ እንዲጸለይ አድርጎታል።
እነዚህ አሥሩ ምህላዎች የሚባሉት ፦
ምሕላ ክረምት፣
ምሕላ ዘዮሐንስ፣
ምሕላ ዘመስቀል፣
ምሕላ ጽጌ፣
ምሕላ ዘስብከት፣
ምሕላ ዘመርዓዊ፣
ምሕላ ዘምኩራብ፣
ምሕላ ዘገብር ኄር፣
ምሕላ ዘሆሣዕና፣
ምሕላ ዘጰራቅሊጦስ ናቸው።
ከእነዚህም ሰባቱ ንቱጋን ሲሆኑ ሦስቱ ምሉዓን ናቸው ።
ምሉዓን የተባሉት ሦስቱ ምህላዎች፡-
ምሕላ ዮሐንስ፣
ምሕላ ስብከት
ምሕላ ሆሣዕና ናቸው።
በእነዚህ ምሕላዎች ‹‹ብፁዕ ብእሲ ዘኢሆረ በምክረ ረሲዓን›› ብሎ መቶ ሃምሳውን መዝሙረ ዳዊት አሥራ አምስቱም መኃልየ ነቢያትን በዜማ ስለሚደረሱ ምሉዓን ተብለዋል።
በሰባቱ ምሕላዎች ግን መዝሙረ ዳዊቱ ሙሉዉን ሳይሆን አርእስቱ ብቻ ስለሚደረስ ንቱጋን ተብለዋል፤ ምሉዕ ማለት በቁሙ የሞላ የበዛ ማለት ነው።
ንቱግ ማለት ደግሞ በተቃራኒው ጎደሎ ያልሞላ ማለት ነው። አንድም ዐቢይ ምህላ ንዑስ ምህላ ይባላሉ። እነዚህም ምህላዎች የሚውሉበት ቀን
፩ኛ. ምህላ ዘክረምት በዓርብ፣
፪ኛ. ምህላ ዘዮሐንስ በረቡዕ፣
፫ኛ. ምህላ ዘመስቀል በዐርብ፣
፬ኛ. ምህላ ዘጽጌ በረቡዕ፣
፭ኛ. ምህላ ዘስብከት በዐርብ፣
፮ኛ. ምህላ ዘመርዓዊ በረቡዕ፣
፯ኛ. ምህላ ዘምኩራብ በዐርብ፣
፰ኛ. ምህላ ዘገብር ኄር በረቡዕ፣
፱ኛ. ምሕላ ዘሆሣዕና በዐርብ፣
፲ኛ. ምህላ ዘጰራቅሊጦስ በረቡዕ ይውላሉ።
ከእነዚህ ምህላዎች አንዱ የዛሬው ተጽኢኖ ተብሎ የሚጠራው የሆሳዕና ምህላ ነው። 150 መዝሙረ ዳዊት በዜማና በንባብ እየተቀናጀ የሚቀርብበት የምህላዎች ሁሉ አውራ ነው።
መ/ር ነቢዩ ኤልያስ
https://t.me/neamn_media
Telegram
ነአምን media
Buy adds:- https://telega.io/c/neamn_media
<< ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአበሔር!>>
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ
#ትምህርቶች
#ዝማሬዎችና
#ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስነ-ፅሁፎች
የሚለቀቁበት ቻናል ነው።
ለሁሉም መረጃና አስተያየትና በቻናሉ ላይ ለመፃፍና ለመሳተፍ @theofloss ያናግሩን መረጃውንም ያካፍሉን።
<< ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአበሔር!>>
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ
#ትምህርቶች
#ዝማሬዎችና
#ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስነ-ፅሁፎች
የሚለቀቁበት ቻናል ነው።
ለሁሉም መረጃና አስተያየትና በቻናሉ ላይ ለመፃፍና ለመሳተፍ @theofloss ያናግሩን መረጃውንም ያካፍሉን።
❤1
Forwarded from Orthodox Tewahdo
⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ
📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖
✝ ይቀላቀሉን ✝

☦ለእኔ የሞተው ፍቅር‼️
"እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቷል..."
የዓለም ጌታ ስለ እኛ የተቀበለውን መራራ መከራና የፈሰሰውን ደሙን የምናስብበት የሕማማት ሳምንት።

✞ በሰሙነ ሕማማት ይህንን አድርጉ ✞
( በሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ )
-------------------------
ለኹሉም እንዲዳረስ ሼር ይደረግ !
ሰሙነ ሕማማት አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ቤዛ ሆኖ ተላልፎ መሰጠቱን የምናስታውስበት ሳምንት ነው።
ይህንን ምክንያት በማድረግ የሥርዓት ለውጥ ሲደረግ ሲመለከቱ ግራ የሚጋቡና ሥርዓተ አምልኮውን በሚገባ ከመከታተል ይልቅ ሥርዓት የጣሱ እየመሰላቸው የሚጨነቁ ስላሉ ልናደርገው የሚገባንን እጽፍላችኋለሁ።
1️⃣. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ ፊትንና መላ ሰውነትን በትዕምርተ መስቀል {በመስቀል ምልክት} ማማተብ አይከለከልም። ከካህን እጅ ቡራኬ አንቀበልም በካህኑ እጅ ያለውን መስቀል አንሳለምምና ማማተብም የለብንም በሚል ፍልስፍና ካልሆነ ማማተብ ክልክል ነው ተብሎ የተጻፈበት ቦታ የለምና።
2️⃣. የሚከለከል ጸሎት የሌለ መሆኑን አውቃችሁ ያስለመዳችሁትን ጸሎት በትጋት ጸልዩ። መሥዋዕት ካለመሠዋታችን ቅዳሴ ካለመቀደሳችን በቀር በዚህ ሳምንት ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጀምሮ እስከ ሊቃውንት ድርሳናት ድረስ በቤተ ክርስቲያን የማይጸለይ ጸሎት የለምና።
3️⃣. ሰላምታ መስጠት ከጸሎተ ሐሙስ ዕለት በቀር አልተከለከለም፤ እሱም ቢሆን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በይሁዳ ሰላምታ ተላልፎ መሰጠቱን ለማስተዎስ እንጅ ሌላ የተለየ ምክንያት ስለሌለው በመርሳት ወይም በሌላ ከድፍረት በተለየ ምክንያት ሰላምታ ያቀረበላችሁን ሰው ልታስደነግጡና ትልቅ ኃጢአት እንደሠራ አድርጋችሁ ልታስጨንቁት አይገባም።
4️⃣. “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ” ብሎ መጻሕፍትን ማንበብ ወይም ሌላ ሥራን መጀመር ይቻላል። ስመ እግዚአብሔር መጥራት የምንከለከልበት ጊዜ መቸም የለምና።
5️⃣. የጌታችንን ሕማሙንና ሞቱን የሚያስታውሱ መጻሕፍትን በማንበብና በመስማት ጊዜአችንን መወሰን ይገባናል።
6️⃣. በዚህ ሳምንት ተድላ ደስታን ሲያደርጉ መገኘት ከአይሁድ ጋር እንደ መተባበር የሚያስቆጥር ስለሆነ አብዝቶ በመብላትና በመጠጣት፣ ያማረውንና ጌጠኛውን ልብስ በመልበስ፣ ባልና ሚስት በምንጣፍ በመገናኘት እንዲሁም በልዩ ልዩ ምክንያት ከምናደርጋቸው ተድላ ደስታዎች መራቅ ይገባናል። ቅዱሳን በዘመናቸው ሁሉ ባሰቡት ጊዜ የሚያስጨንቃቸውን የክርስቶስን መከራ እያሰብን ለጥቂት ጊዜም እንኳን ቢሆን የክርስቶስን መከራ በሰውነታችን ማሰብ ይገባናል።
የተቻለው እንደ ጴጥሮስ የራሱን ኃጢአት እያሰበ እንደ ማርያም መግደላዊት የክርስቶስን ሞት እያዘከረ ሊያለቅስ ይገባዋል።
በወዲያኛው ዓለም ከማልቀስ የሚያድነን ዛሬ የራሳችንን ኃጢአት አስበን የክርስቶስን ሞት አዘክረን የምናለቅሰው ለቅሶ ነው እንጅ ዛሬ ከተደሰትን ደስታችንን በዚህ ዓለም ማድረጋችን አይደለምን?
7️⃣. በተቻለን መጠን በቤተ ክርስቲያን መዋል ይገባናል፤ ሕማማተ መስቀልን የሚያስታውሱ መጻሕፍት የሚነበቡበት ሳምንት ስለሆነ ነው። ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያት በቤተ ክርስቲያን መዋል እንኳን ባይቻላችሁ ባላችሁበት ቦታ ሁናችሁ እየዋሻችሁ በሐሰት የከሰሱትን፣ እየቀማችሁ ልብሱን የገፈፉትን፣ ሰው እየደበደባችሁ በጅራፍ የገረፉትን፣ በወንድሞቻችሁና በእኅቶቻችሁ ላይ እየፈረዳችሁ በክርስቶስ ላይ የፈረዱበትን፣ በሰዎች ላይ እየተዘባበታችሁ የተዘባበቱበትን፣ በሳቅና በሽንገላ ሰውን እየሸነገላችሁ ሽንገላ በተሞላበት ሰላምታ ጌታውንና መምህሩን አሳልፎ የሰጠ ይሁዳን ልትመስሉ አይገባም።
ይልቁንም በአይሁድ እጅ ተላልፎ ቢሰጥም ንጹሓ ባሕርይ መሆኑን በማመን እስከ ቀራንዮ የተከተሉትን ደቀመዛሙርት ልትመስሉ ይገባል። እግራችሁ በመቅደሱ ውስጥ ባይቆምም ልባችሁን ከመቅደስ ልታወጡት አይገባም። እያዘናችሁ ባላችሁበት ቦታ ዋሉ።
8️⃣. በቤታችሁም ሆነ በቤተ ክርስቲያን አብዝታችሁ ስገዱ። ስለሁላችንም ቤዛ የሚሆን ክርስቶስ በፊታችን መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ እያያችሁት ትቆማላችሁን? አይሁድ ገፍተውት አንድ ጊዜ ወደ ምድር በወደቀ ጊዜ ለወደቀው መውደቅ ዘመናችንን ሙሉ ብንወድቅ ብንነሣ ውለታ መክፈል እንችል ይመስላችኋል?
ቅዱሳን ሳያቋርጡ ሲሰግዱ የሚኖሩት ክርስቶስ በፊታቸው በአይሁድ እጅ እየተገፋ መስቀሉን እንደተሸከመ ሲወድቅ በዓይነ ሕሊናቸው ስለሚያዩት ነው።
በስንክሳር ተጽፎ የምናገኘው ዜና ሞታቸው እየሰገዱ ሳሉ ሞት ነፍሳቸውን ከሥጋቸው ለይቶ እንደሚወስዳትና ለስገደት ታጥቀው እንደተንበረከኩ እንደሚገኙ ይነግረናል። የተሰቀለውን ክርስቶስን የሚያስብ ሰው ለሰውነቱ ዕረፍትን አይሻም።
9️⃣. ከሁሉም ሰው ጋር ፍቅርን አድርጉ። ሰውን ለመውደድ ምክንያት አታብጁ። ክርስቶስ አሳልፎ የሰጠውን ይሁዳን “ወዳጄ” ብሎ ሲጠራው አትሰሙትም?
እግዚአብሔርን አንተን ያለ ምክንያት እንደ ወደደህ አንተም ያለ ምክንያት ሰውን መውደድ ልመድ። ክርስቶስ አንተን ጠላቱ ሆነህ ሳለ ፍቅርን ካላጎደለብህ ለጠላትህ ፍቅርን አታጉድልበት።
ክርስቶስ ይሁዳን ‘’ወዳጀ’’ ብሎ ከጠራው አንተም ይሁዳዎችህን ወዳጀ ብለህ ጥራቸው። አውቃለሁ ጠላትን መውደድ መራራ ሐሞትን ከመጠጣት በላይ መራራ ነው። ነገር ግን እኔም ለይሁዳዎቻችን ፍቅርን እንስጥ ማለቴ መራራ ሐሞት የጠጣ ክርስቶስን እንድንመስለው ነው።
1️⃣0️⃣. ለሁሉም መስጠት በምትችሉት መጠን ስጡ እንጅ አትቀበሉ። ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነውና በመስጠታችሁ ብፁዓን ተብለው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገቡት ትቆጠራላችሁ።
ምናልባትም የምትሰጡት ገንዘብ ባይኖራችሁ ዕዳ ይሆንባችሁም ቢሆንም ገንዘብ ለሰጧችሁ ባለጠጎች የምትሰጡት ጸሎት ሊኖራችሁ ይገባል። ከምንጊዜውም የበለጠውን ስጦታ የተቀበልንበት ሳምንት መሆኑን እያሰባችሁ አንዳች የምጸጡት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ስጦታ የሌላችሁ ባዶዎች እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ።
ከሁሉ በላይ የሆነውን ስጦታ የጌታን ሥጋና ደም እነሆ ተቀብለናል።
ክርስቶስ መድኃኒነ
መጽአ ወሐመ በእንቲአነ
ወበሕማማቲሁ ቤዘወነ‼
( ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ )

❤4
የሰሙነ ሕማማት ሰኞ
መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡
በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡
በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡
አንጽሆተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦
ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡
በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡

🥰2
፩
ድርሳን በእንተ ሕማማቲሁ ለክርስቶስ
የተወደዳችሁ የክርስቶስ ወዳጆች ሆይ ስለገነት የተባለው ነገር ሐሰት አይደለም፡፡ ልቡናችንን የሚያበራ የጽድቅ ፍሬ እግዚአብሔርን በማወቅ አግኝተናልና፡፡ የማይጠወልግ አበባ የማይረግፍም ቅጠል ወጣልን፡፡ እነሆ ዛሬ የማይጠፋና የማያልቅ ፍሬን አገኘን፡፡ ወንድሞች ሆይገነት (ዕፀ በለስ) ከዕፀ ሕይወት በስተምሥራቅ እንደ ተተከለች በተረዳ ነገር እነግራችኋለሁ፡፡
ስለዚህ ስለ ዕፀ በለስ እግዚአብሔር ከእርሱ በበላችሁ ቀን የሞት ሞት ትሞታላችሁ አለ፡፡ ስለዚህ ዕፀ ሕይወት ግን መንፈስ ቅዱስ በዳዊት ላይ አድሮ እግዚአብሔርቸር እንደሆነ ቀምሳችሁ ዕወቁት አለ፡፡ መልኩ ያማረ ሲበሉትም የሚጣፍጥ ሰፊም እንደ ሆነ፡፡ እርሱም እንደ ወይራ ፍሬ ቅባቱ ብዙ ነው፡፡ እንደ ዘንባባ ዝንጣፊም ቁመቱ ረጅም ነው፡፡ እንደ ወይንም ፍሬው የበዛና የጣፈጠ ነው፡፡
ከእርሱም ከትንሣኤ በኋላ በሉ፡፡ እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቀምሳችሁ ዕወቁት፡፡ ወንድሞች ሆይ በዚቺ ዕለት በዚህ ዕፅ ምክንያት አይሁድ እንደ አፈሩ ምእመናን ደግሞ እግዚአብሔርን እንዳመሰገኑት አስተውሉ። በመንፈስ ቅዱስ ሀብት የተነገረውን የነቢዩ የዳዊትን ትንቢት ስሙ፡፡ በፈሳሽ አጠገብ እንደተተከለች ዕንጨት ፍሬዋን በየጊዜው እንደምትሰጥ ቅጠሎቿም እንደማይረግፉ ነው አለ፡፡ ከውኃ ዳር የተተከለች ይህቺ ዕፅ የሰጠችው ፍሬ ምንድን ነው? ፍሬ የተባሉትስ እነዚህ በከበረች ጥምቀት የተጠመቁት ናቸው፡፡
በየጊዜው ያለውም ከክርስቶስ ጋር በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ የተገለጸው የፈያታዊ ዘየማን ሃይማኖት ነው፡፡ ጌታም እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ አለው፡፡ ቅጠሎቿ አይረግፉም ያለውም በጸናች ሃይማኖት የበቀሉ ሕዝበ ክርስቲያን ናቸው፡፡
ወንድሞች ሆይ እናንተ ሁላችሁ በሰማይ እንዳሉ ወፎች ከዚች ዕፅ በታች እንደ ሆናችሁ አስቡ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ በፈቃዱ ታሟልና፡፡ በንጉሥ ራስ እንዳለ የመመኪያ ዘውድ እና የጦር ዕቃ ችንካሮችን ታገሠ፡፡ ጌታ ሞትን ወደ እርሱ ይመጣ ዘንድ በፈቃዱ ባዘዘው ጊዜ ደቀመዛሙርቱን እውነት እውነት እላችኋለሁ በዚች ሌሊት ሁላችሁ ትክዱኛላችሁ:: እረኛውን እመታለሁ፤ መንጎችም ይበተናሉ፤ ተብሎ በነቢይ ተነግሯልና አላቸው፡፡.....
ይቀጥላል...
(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 153-179)

፪
ድርሳን በእንተ ሕማማቲሁ ለክርስቶስ
...ደቀመዛሙርቱ ይህን በሰሙ ጊዜ ፈጽመው አዘኑ፡፡ እነርሱ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ሞቱን አላመኑም ነበርና ይህን አደነቁ፡፡ በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ በሐሳቡ በመንፈሳዊ ቅናት ተናደደ፡፡ ጌታ ሆይ ሁሉም ደቀመዛሙርት ቢክዱህ እኔ ግን አልክድህም፡፡ እንደ እነርሱ አድርገህ አትቁጠረኝ፡፡ እኔንስ ከደቀመዛሙርት ሁሉ አብልጨ እንደምወድህ አንተ ታውቅ የለምን? በመርከብ ላይ በአንድነት ተቀምጠን ሳለ በውኃው ላይ ስትሂድ እኔ ብቻዬን ደፍሬ ወደ ባሕሩ ገባሁ ወደ አንተም መጣሁ፡፡ ያንጊዜ እንደወደድኩህ አሁንም እንደ ባዕድ አልክድሕም፡፡ ከአንተ ጋር እሞታለሁ በእኔ ላይም ምንም ምን አመፃም አልተገኘብኝም፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ እንዲህ አለው:: ጴጥሮስ ሆይ በራስህ አትመካ፡፡ ወደ ባሕር በገባህ ጊዜም አላመንከኝም፡፡ በዚህም ምክንያት ወደ ባሕርልትሰጥም ወደደህ፡፡ እኔ ግን ይቅር አልሁህ፡፡ እጄን ዘርግቼም አነሣሁህ፡፡
ጴጥሮስ ሆይ አንተ አብሬህ እሞታለሁ ትላለህ፡፡ ነገርግን አብረኸኝ አትሞትም፡፡ ይልቁንም ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፡፡ ከደቀመዛሙርቶቼ ያንተን ያክል የሚክደኝ የለም:: አሁንም የምነግርህን ምልክት አስተውል፡፡ ሁሉንም ከመሆኑ በፊት ማወቅ የሚችል ሥልጣንም እንዳለኝ ዕወቅ፡፡ እውነት እውነት እልሃለሁ በዚች ሌሊት ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፡፡
ጌታችን ይህን ሲለው የአራት ቤት ጭፍሮች ሾተልና ጎመድ ይዘው ሊይዙት መጡ፡፡ ወደ ሊቀ ካህናቱ ግቢም ወሰዱት፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸው ቃል ይፈጸም ዘንድም በዚህ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ በየራሳቸው ተበተኑ፡፡ ጴጥሮስ ግን ብቻውን ጌታ ኢየሱስን ይከተለው ነበር፡፡ ከጭፍሮች ጋራም ተቀመጠ፡፡ ወቅቱ ብርድ ነበርና እሳት አንድደው ይሞቁ ነበር፡፡
ጴጥሮስም ከእነርሱ ጋር አብሮ ይሞቅ ነበር። በዚያም ጊዜ አንዲት ሴት አገልጋይ ወደ እርሱ መጣች:: ወደ ጴጥሮስም ቀርባ ለተያዘው ለኢየሱስ ተማሪውና ወዳጁ ነህ አለችው፡፡ ጴጥሮስም ያቺን ሴት ይህንን ሰው አላውቀውም ከእኔ ራቂ፡፡ እኔስ ከደቀመዛሙርቱ ወገንም አይደለሁም ብሎ መለሰላት፡፡
ሴትዮዋም ጴጥሮስን ሐሰትን ተናገርህ በእውነት አንተ ከእርሱ ወገን ነህ፡፡ አነጋገርህም ያሳውቅብሃል፡፡ በፍቅርም ወደ እርሱ ትመለከታለህ በማለት መለሰችለት፡፡ ጴጥሮስ ግን ይህንን ሰው እንደማያውቀው ይክድና ይምል ጀመር፡፡ ጴጥሮስም አንቺ ሴት ስለምን ታስጨንቂኛለሽ? ሌላ ሰው መስዬሽ ይሆናል፡፡ ከደቀመዛሙርቱ ወገን ብሆን ኑሮስ ነፍሴን አድናት ዘንድ ከዚህ በሸሸሁ ነበር፡፡ እዚህም ባልቆምሁ ነበር፡፡ ይህ ቢሆንስ ከእርሱ ጋር በያዙኝ ነበር አላት፡፡
ያች ሴትም መልሳ ጴጥሮስን ልትሸነግለኝ አትችልም፡፡ በእውነት አንተ ከእርሱ ወገን ነህ አለችው፡፡ ያን ጊዜም ጴጥሮስ ብዙ ሕዝብ ከዚያች ሴት ጋር የሚነጋገረውን ቃሉን ይሰሙት ዘንድ ወደ እርሱ ሲመጡ ዐየ፡፡ እርሱም ራሱን እየወቀሰ ያንንም ሰው እንደማያወቀው እየማለ አንቺ ሴት ያለ በደሌ ስለምን ወደ መከራ ትስቢኛለሽ አላት፡፡......

፫
ድርሳን በእንተ ሕማማቲሁ ለክርስቶስ
....ጴጥሮስ ከዚች ሴት ጋር በሕዝብ ሁሉ ፊት እንደዚህ እያለ በተነጋገረ ጊዜ ጌታ ኢየሱስ አሩቅ ሆኖ ዐየው። በፍጥነትም ጴጥሮስ ሆይ ከጥቂጥ ጊዜ በፊት ከአንተ ጋር እሞታለሁ አልክድህም ስትል የነበርህ አንተ ራስ አልነበርክምን? በማለት ተናገረው፡፡
ጴጥሮስ ሆይ ድፍረትህ፤ የቃልህ ጽናትና የበዛው ፍቅርህ ወዴት አለ? የዚች የተናቀች አገልጋይ ነገሯ ከተሳለ ሰይፍ ይልቅ አስፈራህ፤ ሥጋህም ሳይቈስል ካድኸኝ፡፡ ጴጥሮስ ሆይ በሰው ፊት የሚያምነኝን እኔ በአባቴ ፊት አምነዋለሁ ያልሁትን ቃል አልሰማህምን? ጴጥሮስ ሆይ እኔ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንሁ የተናገርህ አንተ አልነበርህምን? ጴጥሮስ ሆይ ፍጹም ደስታ በነበረ ጊዜ ታፈቅረኛለህ፡፡ ኀዘንና መከራን ባየህ ጊዜ ደግሞ ትጠላኛለህ፡፡
ጌታችን ጴጥሮስን እንዲህ እያለ ሲገሥጸው ያን ጊዜ ዶሮ ጮኸ፡፡ ጴጥሮስም በእርሱ ላይ የሆነውን ባሰበ ጊዜ ወደ ውጭ ወጥቶ መራራ ልቅሶን አለቀሰ፡፡ የክሕደቱን እድፍም በዕንባው አጠበ፡፡ የጴጥሮስ ዕንባው ወደ መጀመሪያ አነዋወሩ መለሰችው፡፡ ያን ጊዜም አይሁድ ጌታ ኢየሱስን ወስደው ሰቀሉት፡፡ ልብሱንም ተካፈሉት፡፡ ዕጣም ተጣጣሉበት፡፡ ይህም ልብሴን ለራሳቸው ተካፈሉት፤ ዕጣም ተጣጣሉበት፤ ያለው የነቢዩ የዳዊት ቃል ይደርስ ይፈጸም ዘንድ ሆነ፡፡
አይሁድም ጌታችንን ኢየሱስን ክርስቶስን በመስቀል ላይበሰቀሉት ጊዜ ስለ ሰቀሉት ሰዎች አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይህን ኃጢአት ይቅር በላቸው:: አባት ሆይ በፈቃዳቸው እጃቸውን በእኔ ላይ አልዘረጉምና ይህንን ኃጢአት ይቅር በላቸው፡፡ አባት ሆይ ይህንን በደል ተውላቸው፡፡ እነርሱ በቅናት ሰክረዋልና፡፡ አባት ሆይ ይህን ሁሉ እቀበል ዘንድ እኔ በፈቃዴ መጥቻለሁና ይህን ኃጢአት አጥፋላቸው እያለ ጸለየ፡፡
ይህ ሽፍታም በመስቀል ተሰቅሎ በነበረ ጊዜ አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው፡፡ ደቀመዛሙርት ከብዙ ፍርሀት የተነሣ ከግርፋት ራሳቸውን ሠወሩ፤ በየራሳቸው ተበታተኑ። ይህ ሽፍታ ግን በመስቀል ተቸንክሮ ሳለ ወደ ቃለ የሕይወት ቃልን የሚሰብክ ሐዋርያ ሆነ፡፡.....

የሰሙነ ሕማማት ረቡዕ
ምክረ አይሁድ ይባላል፦
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ. 26÷1-14፣ ማር. 14÷1-2፣ ሉቃ. 22÷1-6) የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡
የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፦
ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቱዋ ማርያም) "ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ" ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ይባላል፡፡
የእንባ ቀንም ይባላል፦
ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና። (ማቴ. 26÷6-13፣ ማር. 14÷9፣ ዮሐ. 12÷8) ኃጢአትን በማሰብ ማልቀስና ራስን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ከምታስተምረን ማርያም እንተ እፍረት እንባን ለንስሐ ሕይወት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

👏1
፬
ድርሳን በእንተ ሕማማቲሁ ለክርስቶስ
.....በግራ የተሰቀለውን ሽፍታም አንተ እግዚአብሔርን አትፈራውምን ለእኛስ ይህ በእኛ ላይ የመጣው ፍርድ ይገባናል፡፡ ይህ ጻድቅ ግን ምንም ምን የሠራው ክፉ ነገር የለም አለው፡፡ ይህ ድንቅ ታላቅ ነው:: ወንበዴው እጅግ ጥበበኛን ሆኗልና፡፡ ነፍሰ ገዳዩም ከፍጹም ኃጢአቱ ድኖ በአንዲት ቃል ባለ ሃይማኖት ሆኗልና፡፡
በግራ የተሰቀለውን ወንበዴ ባለንጀራውን እንዲህ ብሎ አሳፈረው፡፡ አንተ ሰነፍ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ ባይሆን ኑሮስ ፀሐይ ባልጨለመ ነበር፡፡ ከኃጢአት ሁሉ ንጹሕ ባይሆን ኑሮስ የቤተ ምኵራቡ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ክፍል ባልተቀደደም ነበር፡፡ የሰማይና የምድር ጌታ ባይሆን ኑሮስ መቃብራት ባልተከፈቱም ነበር፡፡
አንተ ወንበዴ ሆይ አሁን እንኳ እስኪ ከስሕተትህ ተመለስ፡፡ ለመሞት ተቃርበሃል ጊዜህም ደርሷልና፡፡ ነፋሳት በታላቅ ኃይል እንዴት እንደሚነፍሱ አታይምን? የሰማያትና የምድር ኃይላት እንዴት እንደሚርዱ አትመለከትምን? የፀሐይስ ብርሃኑ እንዴት እንደ ጠፋ አታይምን? ከዋክብትስ እንዴት እንደ ወደቁ አትመለከትምን? ባሕርንስ እንዴት እንደታወከች አትመለከታትምን?
አንተ ወንበዴ ሆይ ጌታ አባት ሆይ ይህንን ኃጢአት ይቅር በላቸው ብሎ በታላቅ ቃል ባይናገር ኑሮስ ከዐይን ጥቅሻ ፈጥነው በጠፉ ነበር። ወንበዴው ሆይ ዝም በል። ይህ ጻድቅ ምንም ምን ክፉ ሥራ አልሠራምና። ነገርግን አይሁድ በቅናት ሰቀሉት እንጂ፡፡ የቀኙ ሽፍታ በግራ ለተሰቀለው ሽፍታ እንደዚህ በማለ ተናገረ፡፡
ከዚህም በኋላ የቀኙ ሽፍታ ወደ ጌታ ኢየሱስ ተመልሶ አቤቱ ጌታዬ እና አምላኪየ ነፍሴን ከዚህ ከሓዲ ጋር አታጥፋት፡፡ ነገር ግን በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ እንጂ አለ፡፡ እነሆ አሁን በጌትነትህ ክብር የግርማህን ታላቅነት ዐይቻለሁ፡፡ አቤቱ አንተ ያልካደኝ ብፁዕ ነው ብለሃልና፡፡ እኔ ከጌትነትህ ኃይል የተነሣ ከተቀደደው ከቤተ ምኵራቡ መጋረጃ በዕውቀት የተሻልሁ አይደለሁም፡፡....