NBC ETHIOPIA TV
Photo
"አንድ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ሌሎች መልካም ነገሮችን ይስባል" ርዕሰ መተዳድር አረጋ ከበደ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት የሥራ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርዕሰ መተዳድር አረጋ ከበደ የመቻቻል፣ የፍቅር እና የሥራ ወዳድ ተምሳሌት በኾነው በወሎ ምድር እንዲህ አይነት ፕሮጀክት በመሠራቱ ደስተኛ ነኝ ብለው እስካሁን ያላየናቸው ሃብቶች እየተለዩ ወደ ተጨባጭ አቅም እየተቀየሩ ናቸው ነው ያሉት።
የልማት ጸጋዎችን እንድናይ ላደረጉን እና ሠርተው ላሳዩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
ባለሀብቱ በላይነህ ክንዴ እንዲህ አይነት ሥራ በመሥራታቸው ምስጋና ይገባቸዋል ነው ያሉት። ለሕዝብ እና ለሀገር የሚቆረቆሩ ባለሀብት መኾናቸውንም ገልጸዋል። ሀገር ችግር በገጠማት ጊዜም ኾነ በልማት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ መኾናቸውን ነው ያነሱት።
ዛሬ ያዘጋጁት መርሐ ግብር ለወሎ ሕዝብ ምስጋና ለማቅረብ መኾኑን ነው የተናገሩት። የአካባቢው ሕዝብ አንድም ቀን ፕሮጄክቱ ሳይስተጓጎል እንዲጠናቀቅ ስላደረገ ምስጋና ይገባዋል ነው ያሉት።
ፕሮጄክቱ ፋይዳው ብዙ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ "አንድ ፕሮጄክት ሲጠናቀቅ ሌሎች መልካም ነገሮችን እንደሚሰብም" ተናግረዋል።
ወሎ በታሪክ፣ በሃይማኖት እና በተፈጥሮ የታደለ መኾኑን ነው የተናገሩት። ሐይቅ አካባቢ ደግሞ የብዙ ጸጋዎች ባለቤት መኾኑን አንስተዋል።
ሐይቅ እስጢፋኖስ የመጀመሪያው ዩኒቨርሲቲ እና የታሪክ ሃብታም መኾኑንም ጠቅሰው የሐይቅ እስጢፋኖስ አባቶች መገለጫቸው ሥራ እና ጸሎት መኾኑንም አንስተዋል።
ፕሮጄክቱ ለአካባቢው የቱሪዝም መዳረሻነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ነው የተናገሩት። እንዲህ አይነት ጸጋዎችን እያወጡ መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
፡፡ ፡፡ ፡፡
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት
#Ethiopia

❤2👍1😁1
የሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም የኤንቢሲ ኢትዮጵያ የምሽት ዜናዎች
NBC Ethiopia
:: :: :: :: :: :: ::
✔️ የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ለአፍታም የሚቆም አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
✔️ የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ጸጋን የመለየት፣ የማልማትና ወደ ሀብት የመቀየር ትልቅ ማሳያ ነው -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡
✔️ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር መክረዋል
✔️ የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሃግሰት የሆርሙዝ ሰርጥ እገዳ ይቀጥላል
፡፡ ፡፡ ፡፡
እነዚህ ጨምሮ በርካታ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መረጃዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን፤ አብሮነታችሁ አይለየን፡፡
ወቅታዊና ፈጣን መረጃዎች ለማግኘት የNBC ኢትዮጵያን ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ይወዳጁ፤ ይከታተሉ 👇👇👇
📌 ዩቱዩብ፦ https://youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 ዩቱዩብ 2 :- https://youtube.com/@nbceth_ent
📌 ፌስቡክ፦ https://facebook.com/ethiopiannbc
📌 ቲክቶክ፦ https://tiktok.com/@nbcethiopia
📌 ቴሌግራም፦ https://t.me/nbcethiopiatv
📌ኢንስታግራም:- https://instagram.com/nbcethiopia
📌 X (ቲዊተር) :- https://x.com/nbc_ethiopia
📌 ሊንክድኢን ፡- https://lnkd.in/edjAWMWi
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት
#Ethiopia
#usa
#Trump
#Israel

❤1
"የወደፊቷን ኢትዮጵያ በፅኑ ፌደራላዊ መሰረት ላይ ለመገንባት መሻሻል የሚገባቸው ነገሮች ብዙ ናቸው"
@NBCETHIOPIA ጋራ ሀገር
👉 https://youtu.be/SVDtFdD5QlM
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት
#Ethiopia
@NBCETHIOPIA ጋራ ሀገር
👉 https://youtu.be/SVDtFdD5QlM
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት
#Ethiopia
YouTube
"የወደፊቷን ኢትዮጵያ በፅኑ ፌደራላዊ መሰረት ላይ ለመገንባት መሻሻል የሚገባቸው ነገሮች ብዙ ናቸው" _ጋራ ሀገር @NBCETHIOPIA
National Media SC is here to support, the success of our country's transformational journey; to develop a civic-democratic political culture; which will be free from extremism and racism; for peace to prevail; for building a market-led economy; it is a corporation…
📌 "ልማት የሚያደናቅፍ ጉቶ ካለ ነቅለን እንጥላለን" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
NBCETHIOPIA NBC ማታ
👉 https://youtu.be/RK2qGqRGN4Q
። ። ።
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት
#Ethiopia
NBCETHIOPIA NBC ማታ
👉 https://youtu.be/RK2qGqRGN4Q
። ። ።
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት
#Ethiopia
YouTube
"ልማት የሚያደናቅፍ ጉቶ ካለ ነቅለን እንጥላለን" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) | NBC ማታ @NBCETHIOPIA
National Media SC is here to support, the success of our country's transformational journey; to develop a civic-democratic political culture; which will be free from extremism and racism; for peace to prevail; for building a market-led economy; it is a corporation…
" ዘጠኝ ጦርነት አስቁሜያለሁ" ትራምፕ
አሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል እና ሊባኖስ መካከል ለ10 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረሱን አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ይፋ ያደረጉት ከሁለቱ ሀገራት መሪዎች ጋር በጣም ጥሩ ያሉትን ውይይት ካደረጉ በኋላ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ ከሊባኖሱ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን እና ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር መነጋገራቸውን አረጋግጠዋል።
የተኩስ አቁሙ ለ10 ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ ይህም ለዘላቂ ሰላም እንደ መጀመሪያ እርምጃ ተወስዷል።
ባለፈው ማክሰኞ በዋሽንግተን ዲ.ሲ. በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረገው ውይይት፣ ካለፉት 34 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተብሏል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄ.ዲ ቫንስን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮን እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጄኔራል ዳን ኬይንን ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ከሁለቱ ሀገራት ጋር እንዲሰሩ መመሪያ ሰጥተዋቸዋል ።
ትራምፕ በዓለም ዙሪያ 9 ጦርነቶችን መፍታት ችያለሁ፣ ይህ ደግሞ 10ኛው ይሆናል በማለት በልበ ሙሉነት ተናግረዋል።
የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት በበኩሉ፣ ፕሬዝዳንት አውን ለአሜሪካው አቻቸው ትራምፕ ለሰላም ጥረታቸው ምስጋና ማቅረባቸውን ገልጿል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የ10 ቀኑን ድርድር በበጎ እንደተቀበሉት ዘ ጋርዲያን እና ፍራንስ 24 አስነብበዋል፡፡
በ_ቶማይ መኮንን

❤2👎1
ሊዮኔል ሜሲ የክለብ ባለቤት ሆነ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አርጀንቲናዊው ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ በስፔን እግርኳስ 5ተኛው እርከን ላይ የሚወዳደረውን ኮርኔላ በባለቤትነት መያዙ ይፋ ሆነ።
መቀመጫውን በካታላን ያደረገው ኮርኔላ የ 8 ጊዜ የባለንዶር አሸናፊው ሊዮ ሜሲ ክለቡን የግሉ ለማድረግ ማጠናቀቅ ያለበት ሂደት ሁሉ መፈፀሙን ይፋ አድርጓል።
ክለቡ አክሎም እርምጃው ሜሲ ከባርሴሎና ጋር ያለውን የጠበቀ ቁርኝት እንደሚያጠናክርለት ገልፆ በካታሎኒያ ያሉ ባለተሰጥኦ ታዳጊዎችን እድገት ለማስቀጠል ያለውን ፍላጎት ያሳያል ብሏል።
1500 ተመልካች የሚይዝ ስታዲየም ባለቤት በሆነው ኮርኔላ ከዚህ ቀደም የአሁኑ የአርሰናል ግብ ጠባቂ ዳቪድ ራያ እና የቀድሞ የሜሲ የቡድን አጋር ጆርዲ አልባ ተጫውተው ማለፍ ችለዋል።
የሊዮኔል ሜሲ የምንግዜም ተቀናቃኝ ፖርቹጋላዊው ክርስትያኖ ሮናልድ በቅርቡ በስፔን ሴጉንዳ ዲቪዢን እየተጫወተ የሚገኘውን አልሜሪያ 25% የሚሆን የባለቤትነት ድርሻ መያዙ የሚዘነጋ አይደለም።
በ-ዳንኤል መምሩ
፡፡ ፡፡ ፡፡
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት
#Ethiopia
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አርጀንቲናዊው ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ በስፔን እግርኳስ 5ተኛው እርከን ላይ የሚወዳደረውን ኮርኔላ በባለቤትነት መያዙ ይፋ ሆነ።
መቀመጫውን በካታላን ያደረገው ኮርኔላ የ 8 ጊዜ የባለንዶር አሸናፊው ሊዮ ሜሲ ክለቡን የግሉ ለማድረግ ማጠናቀቅ ያለበት ሂደት ሁሉ መፈፀሙን ይፋ አድርጓል።
ክለቡ አክሎም እርምጃው ሜሲ ከባርሴሎና ጋር ያለውን የጠበቀ ቁርኝት እንደሚያጠናክርለት ገልፆ በካታሎኒያ ያሉ ባለተሰጥኦ ታዳጊዎችን እድገት ለማስቀጠል ያለውን ፍላጎት ያሳያል ብሏል።
1500 ተመልካች የሚይዝ ስታዲየም ባለቤት በሆነው ኮርኔላ ከዚህ ቀደም የአሁኑ የአርሰናል ግብ ጠባቂ ዳቪድ ራያ እና የቀድሞ የሜሲ የቡድን አጋር ጆርዲ አልባ ተጫውተው ማለፍ ችለዋል።
የሊዮኔል ሜሲ የምንግዜም ተቀናቃኝ ፖርቹጋላዊው ክርስትያኖ ሮናልድ በቅርቡ በስፔን ሴጉንዳ ዲቪዢን እየተጫወተ የሚገኘውን አልሜሪያ 25% የሚሆን የባለቤትነት ድርሻ መያዙ የሚዘነጋ አይደለም።
በ-ዳንኤል መምሩ
፡፡ ፡፡ ፡፡
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት
#Ethiopia
የፒዬሬ ኮምፓኒ ድርጊት በቤልጂየም ፓርላማ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የባየርን ሚውኒኩ አሠልጣኝ ቪንሶ ኮምፓኒ አባት የሆኑት ፒዬሬ ኮምፓኒ ትናንት ወደ ፓርላማው ሲያመሩ የባቫሪያኑን ስካርፍ አድርገው ነበር።
በ 1975 በሀገራቸው ኮንጎ የነበረውን አምባገነን ስርዓት በመሸሽ ወደ ቤልጂየም የተሰደዱት ፒዬሮ በሀገሪቱ የመጀመሪያ ስራቸው የታክሲ ሹፌርነት ነበር።
ከታክሲ ሹፌርነታቸው ጎን ለጎን የትምህርት ደረጃቸውን በማሳደግ የመካኒካል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ የሆኑት የ 78 አመቱ አዛውንት በቤልጂየም ሃንስሆረን በምትባል ከተማ ከንቲባ ሆነው በመሾም የመጀመሪያው ጥቁር ግለሰብም መሆን ችለዋል።
በቤልጂየም የፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነው ሌስ ኡንጋሼ ፓርቲ አባል የሆኑት ፒዬሬ በ 2024 በተካሄደው ምርጫ የሀገሪቱን ፓርላማ በመቀላቀል በታሪክ የመጀመሪያው ጥቁር በሚል ሌላ አዲስ ታሪክም ማፃፍ ችለዋል።
ልጃቸው ቪንሶ ኮምፓኒ ከሰሞኑ ባየርን ሚውኒክን እየመራ ሪያል ማድሪድን ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውጪ ማድረግ ችሏል።
ይሄንን ሲመለከቱ ያደሩት አባትም ትናንት በቤልጂየም ፓርላማ የባየርን ሚውኒክን ስካርፍ አንገታቸው ላይ ጣል አድርገው በመገኘት የማህበራዊ ትስስር ገፆችን ማድመቅ ችለዋል።
ቪንሶ ኮምፓኒ ከዚህ ቀደም "አባቴ ጀግናዬ ነው። ዛሬ ያለኝ ሁሉ እሱ በከፈለው ዋጋ የመጣ ነው። ጽናትን አስተምሮኛል። ነገሮች ሲከብዱ እሱ ስላሳለፈው ነገር አስባለሁ” በማለት ተናግሮ ነበር።