STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማትና_እውቅና_ፈቃድ_የተሰጣቸው_የትምህርት_መስኮች.pdf
6 MB
#Repost

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም ድረስ ያጠናቀራቸውን አጠቃላይ የ350 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት መስኮቻቸውን የእውቅና ፈቃድ የሚገልጽ የተሟላ መረጃ ከላይ ተያይዟል።

ከ350ው 330ዎቹ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ 20 ተቋማት በርቀት ትምህርት እውቅና የተሰጣቸው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በክልል መንግስታት የሚተዳደሩ ተቋማት ይገኙበታል።

የእውቅና ፈቃድ ባልታደሰባቸው የትምህርት መስኮች #አዲስ_ተማሪ_መቀበል_እንዳይችሉ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

ይህ መረጃ እስከ የካቲት ወር ድረስ ያለውን የእውቅና ፈቃድ ነው።

በሂደት ላይ ያሉ የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄዎች ውሳኔ ሲያገኙ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የእውቅና ፈቃድ ሲሰረዝና በሌሎች ምክንያቶች የውሳኔ ለውጦች በሚኖሩበት ወቅት የመረጃ ለውጥ ሊኖር ይችላል።

በመሆኑም ፦
- ተማሪዎች፣
- ወላጆች፣
- ቀጣሪና የሙያ ፈቃድ የሚሰጡ ድርጅቶች ፣
- የሚዲያና ማስታወቂያ ተቋማት ፣ እንዲሁም መላው ህብረተሰብ የተቋማቱን ወቅታዊ መረጃ በመከታተል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ተቋማት ይፋ ከተደረገው የእውቅና ፈቃድ መረጃ ውጪ ተማሪ ተቀብለው ቢያስተምሩ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

[ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና እውቅና ፈቃድ የተሰጣቸው የትምህርት መስኮች ከላይ በ #PDF ተያይዟል ]

#ሼር #Share

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Repost #AAU

ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም. ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር እንደሚቀጥል ተገለፀ


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ የአስራር ለውጦች እያደረገ ቢሆንም በተያዘው ዓመት የተማሪዎች ቅበላ በምደባ እንደሚሆን አስታወቀ።

የዩኒቨርስቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ የተቋሙን ሽግግር በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሲሰጡ፤ በ2016 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መሰረት እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው እስከ አንድ ዓመት ተኩል ይፈጃል ተብሎ በሚጠበቅ የሽግግር ሂደት ላይ እንዳለ የተናገሩት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ ሳሙኤል ሙሉ በሙሉ ራስ ገዝ መሆን ሲችል አዳዲስ ተማሪዎችን በዩኒቨርስቲው መስፈርት መሰረት አወዳድሮ እንደሚቀበልም ጠቁመዋል።

የተቋሙ ራስ ገዝ መሆን ከፍለው መማር የማይችሉ ተማሪዎችን አይቀበልም ማለት አይደለም ያሉት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ፤ የዩኒቨርስቲውን መግቢያ የሚያሟሉ ብቁ ተማሪዎች በመንግስት ድጋፍ ዩኒቨርስቲውን መቀላቀል እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወደራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር ለማገዝ ቻንስለር ጨምሮ የቦርድ አመራሮችና ፕሬዝዳንቶች መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ ሂደቱ ሲጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በዓለም አቀፍ መስፈርቶች ተወዳድረው እንደሚቀጠሩ ተጠቁሟል።

ተቋሙ ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ተማሪዎችን በምደባ እንደማይቀበል አስታውቆ ነበር።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Repost #AAU

ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም. ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር እንደሚቀጥል ተገለፀ


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ የአስራር ለውጦች እያደረገ ቢሆንም በተያዘው ዓመት የተማሪዎች ቅበላ በምደባ እንደሚሆን አስታወቀ።

የዩኒቨርስቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ የተቋሙን ሽግግር በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሲሰጡ፤ በ2016 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መሰረት እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው እስከ አንድ ዓመት ተኩል ይፈጃል ተብሎ በሚጠበቅ የሽግግር ሂደት ላይ እንዳለ የተናገሩት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ ሳሙኤል ሙሉ በሙሉ ራስ ገዝ መሆን ሲችል አዳዲስ ተማሪዎችን በዩኒቨርስቲው መስፈርት መሰረት አወዳድሮ እንደሚቀበልም ጠቁመዋል።

የተቋሙ ራስ ገዝ መሆን ከፍለው መማር የማይችሉ ተማሪዎችን አይቀበልም ማለት አይደለም ያሉት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ፤ የዩኒቨርስቲውን መግቢያ የሚያሟሉ ብቁ ተማሪዎች በመንግስት ድጋፍ ዩኒቨርስቲውን መቀላቀል እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወደራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር ለማገዝ ቻንስለር ጨምሮ የቦርድ አመራሮችና ፕሬዝዳንቶች መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ ሂደቱ ሲጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በዓለም አቀፍ መስፈርቶች ተወዳድረው እንደሚቀጠሩ ተጠቁሟል።

ተቋሙ ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ተማሪዎችን በምደባ እንደማይቀበል አስታውቆ ነበር።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Repost
#ለጥንቃቄ

ቴሌግራም ላይ ከተለያዩ ሰዎች አጭር ጹሑፍና ሊንክ እየተላከሎት ነው ?

ቴሌግራም ላይ ከተለያዩ ሰዎች ጹሑፍና ሊንክ ያለው መልዕክቶች እየተላኩ ነው። ብዙዎች ይህ ጉዳይ በተደጋጋሚ እየደረሳቸው እንደሆነና የጥንቃቄ መልዕክቱን እንድናስተላልፍ ጠይቀውናል።

በመልዕክት የሚላከው ሊንክ ምንድን ነው?

በመልዕክቱ አብሮ የሚደርሶት ሊንክ የቴሌግራም አካውንቶን ለመጥለፍ የተዘጋጀ ቴሌግራምን የሚመስል ድረ-ገጽ ነው። ሊንኩን ሲከፍቱት ስልክ ቁጥር አስገብተው ወደ ቴሌግራም እንዲገቡ ይጠይቆቃል።

ቁጥሮን አስገብተው የሚመጣው ሌላኛው ገጽ በቴሌግራሞት የተላከሎትን አጭር የማረጋገጫ ቁጥር እንዲያስገቡ የሚጠይቅ ነው።

የተላከሎትን የማረጋገጫ ቁጥር ካስገቡ የእርሶን ቴሌግራም በቀጥታ ይህን ወጥመድ ያዘጋጁ ሰዎችም መጠቀም ይጀምራሉ። በዚህም መልዕክቶችን ለሌሎች መላክና እርሶ እንደላኩት አድርገው ማቅረብ ይችላሉ።
ይህ ገጽ ልክ ቴሌግራምን እንዲመስል ተደርጎ የተሰራ ሲሆን የሚያስገቡት መረጃ ግን ወደ ቴሌግራም ሳይሆን ይህንን ወደ ሚቆጣጠሩት ሰዎች የሚላክ ነው። ይህ አይነቱ ማጭበርበር ማጥመድ (Phishing) በመባል ይታወቃል።

ምን ማድረግ እችላለሁ ?
ይህ ችግር ካጋጠሞት ቀጥታ ቴሌግራሞት ላይ Setting ላይ በመግባት #Device የሚለውን በመጫን የእርሶ አካውንት በምን በምን ስልኮች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ማየት ይችላሉ። በዚህም ከእርሶ ቁጥጥር ውጪ ያሉ ስልኮችን በሙሉ ማስወጣትና እርሶ የሚጠቀሙበትን ብቻ ማስቀረት ይችላሉ።
ሁለተኛው መንገድ ይህ ችግር ከተመፈጠሩ በፊት የሚያገለግል ሲሆን ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) መጠቀም ድንገት ለእንደዚህ አይነት ችግሮች ብንጋለጥ ተጨማሪ የደኅንነት ማረጋገጫ ይሆነናል።
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
#repost

የመውጫ ፈተና ከረቡዕ ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

በዚህ ፈተና ወቅት ከተማሪዎች እና ከፈታኞች ምን እጠበቃል ?

[ ከተፈታኞች የሚጠበቅ ]

- ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍላቸው ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

- ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው።

- ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

- ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

- ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

- ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

- በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገርም ሆነ ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

- ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

- ተፈታኞች በምንም አይነት ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

- ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው ፈታኝ መምህራን እና ለአስተባባሪዎች መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

NB. ሁሉም ተፈታኞች ወደ ፈተና መፈተኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

[ ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ ]

- የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

- ፈታኝ መምራህን የተፈታኝ ተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

- በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

- የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

- በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከመተኛ ክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

- ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

- ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

- ሲኮርጅ ወይም ሲያስኮርጅ የተገኘ ማንኛውም ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ፈተናው ከጀመረ ከ15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

- የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ ይጠብቅባቸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነው የሰበሰበው።

ለመላው ተፈታኞች መልካም ፈተና ይሆን ዘንድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይመኛል !

(መልዕክቱ በባለፈው ዓመት የፈተና ወቅት የተዘጋጀ እና በቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ላይ የተለጠፈ ነው)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot