STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#MekdelaAmbaUniversity

መቅደላ አንባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ ነው!

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
#MekdelaAmbaUniversity

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት እና የነባር መደበኛ ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው የካቲት 02 እና 03/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MekdelaAmbaUniversity

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ዓመት #የኤክስቴንሽን ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 07 እና 08/2013 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የምዝገባ ጥሪው በሁለቱም ካምፓሶች (ቱሉ አውሊያ እና መካነሰላም) ትምህርታቸውን ይከታተሉ ለነበሩ #የኤክስቴንሽን ተማሪዎች መሆኑ ተገልጿል።

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ1ኛ ዓመትና ነባር መደበኛ ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም ምዝገባ የካቲት 02 እና 03/2014 ዓ.ም ይከናወናል ማለቱ አይዘነጋም።
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MekdelaAmbaUniversity

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዙር ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

"ዩኒቨርሲቲው ከደረሰበት ውድመትና ዘረፋ ራሱን ዳግም በማደራጀትና ቅደመ ዝግጅቶችን በማድረግ" ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን የተቋሙ ፕሬዝዳንት ታምሬ ዘውዴ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ዳግም የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስቀጠል ከትናንት ጀምሮ ተማሪዎችን እየተቀበለ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ለተማሪዎች አገልግሎት የሚያስፈልጉ ማደሪያና መማሪያ ክፍሎች፣ መመገቢያ አዳራሽ፣ ውሃ፣ መብራትና ሌሎችም መሟላታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር የ1ኛ፣ የ3ኛ እና የ4ኛ ዓመት ተማሪዎችን መቀበል የተጀመረ ሲሆን በቀጣይ የቀሪ ተማሪዎች ቅበላ ይደረጋል ብለዋል። #ENA

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MekdelaAmbaUniversity

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ሥራውን በድጋሜ ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ላለፉት 5 ወራት ከመደበኛ ሥራው ውጭ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን የካቲት 02 እና 03/2014 ዓ.ም ተቀብሏል፡፡

ተቋሙ የስነ-ልቦና ስልጠና ለመምህራን፣ ለአስተዳደር ሰራተኞች እና ለተማሪዎች በዋናው ግቢ (ቱሉ አውሊያ ካምፓስ) የካቲት 04 እና 05/2014 ዓ.ም እየሰጠ ሲሆን በሁለተኛ ካምፓሱ (መካነ ሰላም ግቢ) ደግሞ
የካቲት 07 እና 08/2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MekdelaAmbaUniversity

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም #የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የሞጁል ቲቶሪያል የሚሰጠው ከሐምሌ 21 እስከ 24/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ምዝገባ ሐምሌ 29 እና 30/2014 ዓ.ም ተከናውኖ፤ ትምህርት ነሐሴ 02/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

( ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል። )


ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MekdelaAmbaUniversity

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ እና ነባር እና አዲስ ገቢ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥር 16 እስከ 18/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በዚህም፦
- የሁለተኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ነባር መደበኛ ተማሪዎች፣
- በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪ የነበራችሁና የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ፣
- በ2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦ በዋናው ግቢ (ቱሉ አውሊያ) ብቻ

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሔዱ ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ እንዲሁም ስምንት 3x4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ መያዝ ይኖርባችኋል።

Note:
በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመማር መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት እንደሚያሳውቅ ኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡ የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot