STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.9K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ #ፈተና እና #ምዝገባ በኦንላይን እንደሚሰጥ ተገለፀ!

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲሰጥ በቅድሚያ ትምህርት ቤቶች ኮቪድ-19 መከላከልን መርህ ባደረገ መልኩ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።ከፈተናው አስቀድሞም የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት የማረጋገጥ ስራ በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰራም ተገልጿል።

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እና ምዝገባ በኦንላይን እንደሚካሄድ እና ተማሪዎች የ45 ቀን የማካካሻ እና የቴክኖሎጂ መለማመጃ ጊዜም እንደሚሰጣቸው ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት እና ፈተናዎችም የሚሰጡት ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማሟላት ሲችሉ ብቻ መሆኑም ተገልጿል።ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ያቅስመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ:- MoE

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ExitExam

የትምህርት ጥራት #ፈተና_በመስጠት ብቻ ይረጋገጣል ?

ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀመር ይታወቃል።

ለመሆኑ ፈተና በመፈተን ብቻ የትምህርት ጥራት ማምጣት ይቻላል ? ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ምላሽ አለው።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) የተናገሩት ፦

" የትምህርት ጥራት ፈተና ብቻ በመስጠት የሚሳካ ፤ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም።

በአጠቃላይ ግን በትምህርት እና ስልጠና ዘርፉ በተለይም በትምህርቱ ዋና ችግር አለ ተብሎ የተለየው ዋና የትምህርት ሴክተሩ ስብራት ነው ተብሎ የተለየው ትምህርታችን ጥራትም ተገቢነትም ጎሎታል።

ስለዚህ አስመርቀን የምናስወጣው በሙሉ ባይባልም የጥራት ፣ የብቃት ችግር አለበት ይሄንን መፍታት ያስፈልጋል።

ለዚህ የሚሆን በሁሉም ደረጃ ከግብዓትም ጋር ከሂደቱም ጋር የሚያያዝ እንደዚሁም ውጤቱን ከማረጋገጥ ጋር የሚያያዝ ስራዎች መሰራት አለባቸው ተብሎ በመንግስት ቁልፍ የሪፎርሞች ተጀምረዋል አንደኛው ከመውጫ ፈተና ጋር የሚያያዝ ነው።

ይሄ የመውጫ ፈተና በዋናነት የሚመለከተው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃንን ነው ሁለተኛ ዲግሪ እና ሌሎችን አይመለከትም የሚጀምረው በ2015 ሰፋ ብሎ ነው እንጂ ከዚህ በፊትም የተጀማመሩ ስራዎች አሉ የተጀመሩ ፕሮግራሞች አሉ።

ዋናው ቁም ነገሩ በግብአት ደረጃ ጥራቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል የምሩቁን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን የመማር ማስተማር ሂደቱ ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ መምራት እና መስጠት ያስፈልጋል።

በጥሩ ግብዓት ከተደገፈ እና ጥሩ ሂደት ካለው በውጤቱ ማረጋገጥ ይገባል ከሚል መነሻ የተጀመረ የሪፎርም ስራ ነው "

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#የሥነ_ዜጋ እና #ሥነ_ምግባር ትምህርት ከ12ተኛ ክፍል #ፈተና እንዲወጣ ተደረገ‼️


ትምህርት ሚኒስቴር የ12ተኛ ክፍል ፈተና ላይ ከሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ውስጥ የሥነ ዜጋ እና ሥነ ምግባር ትምህርትን ሲያስወጣ፣ በአንጻሩ የኢኮኖሚክስ ትምህርት በማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ውስጥ ተካተተ።

በዚህ ዓመት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት መተግበር የጀመረው ትምህርት ሚኒስቴር፤ የ12ተኛ ክፍል የፈተና ዝርዝር ላይ ለውጥ ማድረጉን ያሳወቀው ሐሙስ ጥር 9/2016 በጻፈው ደብዳቤ ነው። በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት ዓይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

#የተፈጥሮ_ሣይንስ፦ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

#የማኅበራዊ_ሣይንስ፦ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።


የ12ተኛ ክፍል ፈተና ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ የሚሰጠውን ትምህርት የሚያካትት ሲሆን፣ ዘንድሮ ግን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ፈተና የሚወጣው ከ12ተኛ ክፍል ብቻ እንደሆነ ትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ላይ ጠቅሷል።

ኩረጃን እና የፈተና ስርቆትን ለመከላከል በጥብቅ ቁጥጥር ውስጥ ከ2014 ዓ.ል. ጀምሮ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ መሰጠት የተጀመረው የ12ተኛ ክፍል ፈተና፤ ባለፉት ዓመታት እጅጉን ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች የሚያልፉበት ሆኗል።

የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ፈተና መቼ ሊሰጥ እንደታሰበ ጥያቄ የቀረበላቸው የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ፤ “አሁን ከክልሎች ጋር ምክክር እያደረግን ነው። በቅርቡ እናሳውቃለን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot