STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.8K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በዘንዘልማ ካምፓስ ሰሞኑን ማታ ማታ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ተኩስ ከፍተው እንደነበር የግቢው ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ የዘንዘልማ ካምፓስ ተማሪ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ በግቢያቸው ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ገልጿል። በአካባቢው የቦንብ ፍዳታም እንደነበር ጠቁሟል።

ይኸው ተማሪ " በዘንዘልማ ካምፓስ ተኩስ አዲሳችን አልነበረም " ሲል ገልጾ ከትላንት በስቲያ በአጥር ዘለው የገቡ አካላት ጥይት እየተኮሱ እስከ ዋና መግቢያ በር መሄዳቸውን ጠቁሟል።

" የገባነው ‘ግቡ’ ተብሎ ነው፤ ብዙ ተማሪ የለም። ወደ 100 ብንሆን ነው " ሲልም አክሏል። ተኩስን ኖርማል ሲቪል ልብስ የለበሱ ሰዎች መክፈታቸውን ነው የተናገረው።

ጥር 16 ቀን 2016 ዓ/ም በተጨማሪ ማብራሪያ የሰጠ አንድ የግቢው ተማሪ ፤ በዘንዘልማ ያለው ሁኔታው ስለሚያሰጋ ወደ ዋናው ካምፓስ መሄዱንና የቀሩት ጓደኞቹ በሁኔታው መጨነቃቸውን እንደገለፁለት ተናግሯል።

" እስከ 18 ድረስ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ " የሚል ወረቀቶችም መበተኑን ከጓደኞቹ ዘንድ እንደሰማ በመግለፅ ያለንበትን ሁኔታ የሚመለከተው አካል ይወቅልን ብሏል።

የዩኒቨርሲቲው ሁነኛ አካል ጉዳዩን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ጉዳዩን #እንዳልሰሙና አጣርተው ምላሽ እንደሚሰጡ ቢገልጹም፣ በድጋሚ ሲደወልና የፅሑፍ መልዕክት ቢላክላቸውም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

፨ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችን የመግቢያ ቀን የመግቢያ ቀኑ ሊደርስ 3 ቀን ሲቀረው ዛሬ ላልተወሰነ ጊዜ ያራዘመ መሆኑን ማሳወቁ ይታወቃል።

[ዘገባው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ነው]

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT